You are on page 1of 5

Amharic Form- Rental 

Agreement
ቀን ——————–

የቤት ኪራይ ውል
አከራይ፡ አቶ/ወ/ሮ/የድርጅቱ ስም———————————–

          አድራሻ፡ —–(ከተማ)፣———-(ክፍለ ከተማ)

          ቀበሌ —— ፣የቤት ቁጥር ——–

ስልክ ቁጥር፡ ———————–

ተከራይ፡ አቶ/ወ/ሮ/የድርጅቱ ስም———————————–

አድራሻ፡ —–(ከተማ)፣———-(ክፍለ ከተማ)

ቀበሌ —— ፣የቤት ቁጥር ——–

ስልክ ቁጥር፡ ———————–

አንቀጽ አንድ
የውሉ አላማ
 
1. አከራይ የግላቸው የሆነውንና በስማቸው ተመዝግቦ በ——– ከተማ ——- ክፍለ ከተማ ቀበሌ ——-
የሚገኘውን የቤት ቁጥር —— የሆነውን መኖሪያ ቤታቸውን በዚህ ውል መሰረት ተከራይ ለሆነው ለ
———– አዲስ አበባ ላለው ለ————አገልግሎት ብቻ እንዲጠቀምበት በዚህ ውል መሰረት
አከራይተውታል፡፡
አንቀጽ ሁለት
የውሉ ዘመን
 
1. ይህ ውል ከ———–ቀን ——- ዓ.ም ጀምሮ ለ——- አመት የፀና ነው፡፡
2. ውሉን ለማደስ ሁለቱ ወገኖች ሲስማሙና አዲስ ውል በጽሁፍ ሲዋዋሉ ይህ ውል ቀሪ ይሆናል፡፡
3. ውሉን ለማደስ የፈለገ ወገን ፍላጎቱን የውሉ ጊዜ ከማለቁ በፊት ባሉት ——– ቀናት ውስጥ በጽሁፍ
መግለጽ አለበት፡፡
አንቀጽ ሶስት
የኪራይ መጠን
 
1. ተከራይ ከላይ በአንቀፅ 1 ላይ የተገለፀውን ቤት በወር — ብር ለአከራይ በጥሬ ገንዘብ ወይም በህጋዊ ቼክ
ለመክፈል ተስማምቷል፡፡
2. አከራይ ከ—-ኛው የውል ጊዜ በኋላ አስፈላጊ ሲሆን የአካባቢን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት
ምክንያታዊ የሆነ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ሊያደርግ ይችላል፡፡
 
አንቀጽ አራት
የኪራይ አከፋፈል
 
1. ተከራይ ይህ ውል በሁለቱ ወገኖች መካከል ሲፈረም ለአከራይ የ—- ጊዜን የቤት ኪራይ ማለትም ከቀን
———— እስከ ———– ዓ.ም ———) ለአከራይ ይህ ውል ሲፈረም ከፍሏል፡፡
2. ተከራይ ቀሪውን የ—— የቤት ኪራይ ማለትም ከ ———እስከ —— ዓ.ም ድረስ ያለውን (የተጨማሪ
እሴት ታክስን ጨምሮ) ———) በቀን ——— ዓ.ም ለአከራይ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ አምስት
የአከራይ መብትና ግዴታ
 
1. አከራይ በዚህ ውል ላይ የተገለጸውን ቤት ይህ ውል በተፈረመ በ ——– ቀናት ውስጥ የጥገናና የእድሳት
ስራዎች በማጠናቀቅ ለተከራይ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
2. አከራይ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የሚፈጠሩ ብልሽቶችን እና ጉዳቶችን የማስተካከል ግዴታ አለባቸው፡፡
3. አከራይ አስፈላጊ ሲሆን ተከራይ ቤቱን በአግባቡ እየተጠቀመበት መሆኑን ለማረጋገጥ ወይም በተፈጥሮ
አደጋ ምክንያት የሚፈጠሩ ብልሽቶችን እና ጉዳቶችን ለማስተካከል ወይም ለህንጻው ደህንነት አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝ ለተከራይ የ — ቀናት ማስታወቂያ ሰጥተው ቤቱ ውስጥ የመግባት፣ቤቱን የመጎብኘትና
አስፈላጊ ጥገናዎችን የማድረግ መብት አላቸው፡፡
4. አከራይ ከቤቱ ጋር በተገናኘ የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ ለመንግስት የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡
5. አከራይ ከሶስተኛ ወገን በማንኛውም ጊዜ ለሚነሳ የቤት ባለቤትነት ጥያቄም ሆነ የአፈጻጸም ክስ
በቀደምትነት የተከራይን መብት ያስከብራል፡፡
አንቀጽ ስድስት
የተከራይ መብትና ግዴታዎች
 
1. ተከራይ በዚህ ውል ላይ የተገለጸውን ቤት በውሉ ጊዜ ውስጥ ለ—— አገልግሎት የመጠቀም መብት
አለው፡፡
2. ተከራይ ቤቱን በአግባቡና በጥንቃቄ የመጠበቅና የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡
3. ተከራይ በራሱ ጥፋት በቤቱ ላይም ሆነ በግቢው ውስጥ የሚያደርሰውን ጉዳት በራሱ ወጪ ወዲያውኑ
የማስተካከል ግዴታ አለበት፡፡
4. ተከራይ የቤት ኪራዩን ከላይ በአንቀጽ ሶስትና አራት መሰረት የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
5. ተከራይ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ለተከራየው ቤት የተጠቀመበትን የመብራት፣የውሃና የስልክ አገልግሎት
ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
6. ተከራይ ያለ አከራይ የጽሁፍ ፈቃድ የተከራየውን ቤት ጣሪያና ግድግዳ መብሳት እና ማፍረስም ወይም
በቤቱ ላይ የማሻሻያ ለውጥ ማድረግ ወይም ቀለም መለወጥ አይችልም፡፡
7. ተከራይ ከቤቱ ጋር በተያያዘ በራሱ ጥፋት የተነሳ በሌላ ወገን ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ጥያቄ ሀላፊነት
አለበት፡፡
አንቀጽ ሰባት
በቤቱ ላይ ያለን ጥቅም አሳልፎ መስጠት
 
1. ተከራይ በውሉ ላይ የተገለጸውን ቤት ለመጠቀም ያለውን ህጋዊ መብቱን የአከራይን በጽሁፍ የተገለጸ
ፍቃደኝነት ካላገኘ በስተቀር ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይችልም፡፡
አንቀጽ ስምንት
ሕግን ማክበር
1. ተከራይ በውሉ ጊዜ ውስጥ ከቤቱ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ የሆኑትን ህጎችና ደንቦች የማክበር ግዴታ
አለበት፡፡
አንቀጽ ዘጠኝ
ቤቱን ባለበት ሁኔታ ማስረከብ
 
1. ተከራይ የቤት ኪራዩ የውል ዘመን ሲያበቃ ቤቱን በ —-ቀን—— ዓ.ም በተረከበበትና በጥሩ ሁኔታ
ለአከራይ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
2. ተከራይ በቤቱ ላይ የይዘት፣የቅርጽ፣የአቋም ወይም የውበት ለውጥ ሳያስከትል ሊንቀሳቀስ ወይም ሊነሳ
የሚችል ንብረት ካለው የውሉ ጊዜ ሲያበቃ አንስቶ የመውሰድ መብት አለው፡፡
አንቀጽ አስር
ማስጠንቀቂያ
 
1. አከራይ ቤቱን በአንቀጽ —- መሰረት ለተከራይ ካላስረከብ ተከራይ የ—- ቀን የማስረከቢያ ጊዜ በጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል፡፡
2. ተከራይ በአንቀጽ —- እና በአንቀጽ —- መሰረት የቤት ኪራዩን ካልከፈለ አከራይ የ —- ቀን የመክፈያ ጊዜ
በጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጡታል፡፡
3. ተከራይ በአንቀጽ ስምንት መሰረት ቤቱን ማስረከብ ካልቻለ አከራይ የ—- ቀን የማስረከቢያ ጊዜ በጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ይሰጡታል፡፡
4. ሌሎች በዚህ ውል ውስጥ የተገለጹት ግዴታዎች በአግባቡ ካልተፈጸሙ ውሉን ላላከበረው ወገን የ —- ቀን
የጽሁፍ ማስጠንቀቂ ይሰጠዋል፡፡
አንቀጽ አስራ አንድ
ቅጣት
 
1. አከራይ ከላይ በአንቀጽ ዘጠኝ(1) በተገለጸው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰረት ቤቱን ካላስረከበ ለተከራይ
—— ብር ቅጣት ከፍሎ ውሉ ቀሪ ይሆናል፡፡
2. ተከራይ ከላይ በአንቀጽ ዘጠኝ(2) መሰረት በተገለጸው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰረት የቤት ኪራዩን
ካልከፈል ላልከፈለበት ለእያንዳንዱ ቀን ብር —– ቅጣት ከቤት ኪራዩ በተጨማሪ የመክፈል ግዴታ
አለበት፡፡
3. ተከራይ በአንቀጽ 6(6) በተገለጸው መሰረት በቤቱ ላይ ለውጥ ካደረገ ብር —— ቅጣት ለተከራይ ከፍሎ
ውሉ ቀሪ ይሆናል፡፡
4. ተከራይ ከላይ በአንቀጽ ዘጠኝ(3) መሰረት በተገለጸው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰረት ቤቱን ማስረከብ
ካልቻለ ላላስረከበበት ለእያንዳንዱ ቀን —– ብር ቅጣት የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
5. ተከራይ ወይም አከራይ ከላይ በአንቀጽ ዘጠኝ(4) መሰረት በተገለጸው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰረት
በውሉ ላይ የተገለጹትን ግዴታዎች መወጣት ካልቻለ ውሉን ያላከበረው ወገን ውሉን ላከበረው ወገን —–
ብር ከፍሎ ውሉ ቀሪ ይሆናል፡፡
አንቀጽ አስራ ሁለት
ውልን ማሻሻል
1. አከራይና ተከራይ ይህንን ውል ሊያሻሽሉ፣ሊለውጡ ወይም ሊቀይሩ የሚችሉት በጽሁፍ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
አንቀጽ አስራ ሶስት
ውሉ ቀሪ የሚሆንባቸው ምክንያቶች
 
1. ተከራይና አከራይ በጽሁፍ ሲስማሙ ውሉ ቀሪ ይሆናል፡፡
2. በአንቀጽ አስራ አንድ(1)፣(3)፣(5) በተገለጹት ምክንያቶች መሰረት ውሉ ቀሪ ሊሆን ይችላል፡፡
3. የውሉ ዘመን በአከራይና በተከራይ የጽሁፍ ስምምነት ካልተራዘመ በስተቀር የውሉ ዘመን ሲያበቃ ውሉ
ቀሪ ይሆናል፡፡
አንቀጽ አስራ አራት
ግጭት መፍቻ
1. በአከራይና ተከራይ መካከል ከዚህ ውል አፈጻጸም ጋር በተያያዘ አለመግባባት፣ግጭት ወይም ቅራኔ ቢፈጠር
ሁለቱም ወገኞች በመመካከር ለመፍታት ተስማምተዋል፡፡ነገር ግን አለመግባባታቸውን በመመካከር
ለመፍታት ካልቻሉ ጉዳዩን ወደ——————(ፍ/ቤት)(አርቢትሬሽን) ይወስዳሉ፡፡
 
ይህ ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1731፣2005፣1889 እና 1890 መሰረት በህግ ፊት የጸና ነው፡፡

ይህ ውል ዛሬ —– ቀን —- ዓ.ም በ——— ከተማ ተፈጸመ፡፡

  አከራይ                           ተከራይ
———————                               ———————

   ስም                                            ስም

——————–                               ———————-

  ፊርማ                                           ፊርማ

———————–                             ———————–

   ቀን                                             ቀን

ምስክሮች
ስም                           አድራሻ                           ፊርማ

You might also like