You are on page 1of 3

ህዳር 6 ቀን 2010 ዓ.

የቤት ኪራይ ውል ስምምነት

አከራይ፡…………………. ወ/ሮ አለሜ ግርማ /ዜግነት አሜሪካዊ በትውልድ ኢትዮጵያዊት/

ህጋዊ ወኪል ……………… ወ/ሪት መሠረት ግፋወሰን ይልማ

የውክልና ስልጣን ቁጥር ቅ/1160/1/2010 በ 20/22209 ዓ.ም በተሰጠኝ ስልጣን መሠረት

አድራሻ፡ ………………… አ.አ ክ/ከተማ የካ ወረዳ 11 የቤት ቁ. 838

ተከራይ፡ ………………… ወ/ሮ አልሰሙ አሸናፊ /ዜግነት ኢትዮጵያዊት/

የፓስፖርት ቁጥር፡ EQ 0045843

እኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የካርታ ቁጥር የካ/218801/11 የተሰጠበትን ቀን

20/06/2011 ዓ.ም የቦታው ስፋት 500 ካሬ ሜትር ሙሉ ግቢ የሆነውን ለተከራይ ለመኖርያ ቤትነት ሊገለገሉበት በወር

ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ እየከፈሉ ከህዳር 06 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 05 ቀን 2015 ዓ.ም
ድረስ ማለትም በሁለት ዓመት ውል አከራይቻቸዋለሁ፡፡ የገንዘቡን አከፋፈል በተመለከተ የሶስት ወር ቅድሚያ ክፍያ ብር

66,000.00 ብር /ስልሳ ሺህ ብር/ ተቀብያለሁ፡፡

እኔም ተከራይ ከላይ አድራሻው እና የካርታ ቁጥሩ የተገለፀውን ሙሉ ግቢ የሆነውን ለመኖሪያነት ልገለገልበት

በወር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ሂሳብ ከፍዬ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30, 2015 ዓ.ም
ተከራይቼ ተስማምተን ተዋውለናል፡፡

ተከራይ ቤቱን ሲያስረክቡ ቤቱን በአያያዝ ወይም በአጠቃላይ ጉድለት የተነሳ ለሚደርሰው ማንኛውም ብልሽት

ተከራይ በግል ወጪያቸው አድሰው እና አስተካክለው የተሰበረ እና የተበላሸ ቢኖር ጉድለቱን በነበረበት አሟልተው

ሊያስረክቡን ተስማምተን መከራየቴን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡

የተከራይ ግዴታ፡-
1. ተከራይ ቤቱን እና በቤቱ ውስጥ የተረከቡትን እንዲሁም የግቢን አትክልት የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው፡፡

2. ተከራ ቤቱን በሙሉም ሆነ በከፊል ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍም ሆነ ማከራየት እንዲሁም ከተከራዩበት

ዓላማ ውጭ መጠቀም አይችሉም፡፡

3. ተከራይ ቤቱን ከተከራዩበት ቀን ጀምሮ እንደ አጠቃቀማቸው ወርሃዊ የመብራት እና የውሃ ቢል እና የጥበቃ

መክፈል አለባቸው፡፡ ሳይከፍሉ ጊዜ አሳልፈው አገልግሎቱ ቢቋረጥ የአገልግሎቱን ማስቀጠያ ከግል ወጭያቸው

ሸፍነው ያስቀጥላሉ፡፡

4. ተከራይ ቤቱን ለመልቀቅ ሲፈልጉ ለአከራይ የአንድ ወር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡

5. አከራይ ስምምነቱን ለማቋረጥ ከፈለጉ የአንድ ወር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ለተከራይ ሲሰጡ ተከራይ ይህ

የአንድ ወር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መቀበል አለባቸው፡፡

6. አከራይ ቤቱን በከፊልም ሆነ በሙሉ የአከራይን ስምምነት ሳያገኙ በምንም አይነት መቀየር የለባቸውም፡፡

የአከራይ ግዴታ፡-

1. አከራይ ቤቱን ካከራዩ በኋላ የተከራዮች ሰላም እንዳይበላሽ በማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
2. አከራዮች በቤቱ ውስጥ የሚገኙትን አገልግሎት የሲስተም ችግር ካጋጠመው አፋጣኝ የጥገና ሥራ የማድረግ
ግዴታ አለባቸው፡፡
3. አከራይ ቤቱን ለማስለቀቅ ሲፈልጉ ለተከራይ የአንድ ወር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዴታ
አለባቸው፡፡

የዚህ ውል ጊዜ ገደብ ካለቀ እና ሁለቱም ወገኖች ከተስማሙ ውሉን ለማደስ ካልተስማሙ ግን የአንድ ወር ቅድሚያ

ማስጠንቀቂያ አንዱ ወገን ለሌላው ወገን በመስጠት ይህንን ውል በተፈፀመው መሰረት ለማፍረስ የውል ግዴታ

ገብተናል፡፡

ይህንን ውል ስንዋዋል የነበሩ ምስክሮች፡-

1. ወ/ሮ ዮዲት አያሌው/ዜግነት ኢትዮጵያዊት/

አድራሻ፡- የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር ………………

2. አቶ ስለሽ አሰፋ /ዜግነት ኢትዮጵያዊ/

አድራሻ፡- አ.አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር 496


እኛም ምስክሮችከላይ አከራዮች እና ተከራይ የተጠቀሱት የኪራይ ውል ስምምነት ሲፈፅሙ አይተን እና

ሰምተን በውሉ ሰነድ ላይ በእማኝነት ፈርመናል፡፡

የአከራይ ስም እና ፊርማ የተከራይ ስም እና ፊርማ

የምስክሮች ስም እና ፊርማ

You might also like