You are on page 1of 1

ቀን፡01/07/2015 ዓ.

የቤት ኪራይ ውል ስምምነት

አከራይ፡ እስራኤል ዮሀንስ ፓናዮቲ ዜግነት ኢትዮጵያዊ ህጋዊ ወኪል

የወ/ሮ አንማው ታጠቀው ተመስገን /ዜግነት ኢትዮጵየዊ/

አድራሻ፡- አአ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር አዲስ

ተከራይ ፡ ወ/ሮ ሰዓዳ ሐዊ ኸይሩ

አድራሻ፡- አአ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር አዲስ

1. እኔ አከራይ በወኪል አድራጊዬ ጋር ባልና ሚስት ስንሆን የጋራ ንብረታችን የሆነውን እና በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘውን በአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር አዲስ የሆነው የንግድ ቤት ለምግብ ቤት አገልግሎት እንዲጠቀሙበት ከሚያዚያ 1 ቀን
2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 1 ቀን 2018 ለሶስት አመት ድረስ የሚቆይ የኪራይ ውል አከራይቻቸዋለሁ፡፡ የስድስት ወር ክፍያ ሲያበቃ
በቅድሚያ በየ 2 ወሩ ሊከፍሉኝ ተስማምቼ ተዋውያለሁ፡፡

2. እኔም ተከራይ ከላይ አድራሻው ከተጠቀሰው ቤት ላይ በወር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ሂሳብ የተከራየሁ ሲሆን በዛሬው ቀን በዚህ ውል
ደረሰኝነት የስድስት ወር ክፍያ ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ ሲሆን እሁን የ 3 ወሩን ብር 15,000 አስራ አምስት ሽህ ብር/ ከፍዬ ቀሪውን የ 3
ወሩን ብር 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር/ ተከራይቼ ቤቱን በራሴ ወጪ አድሼ ስጨርስ ልከፍል ተስማምቻለሁ፡፡

3. ተከራይ የተከራዩት ቤት ሲያስረክቡ ቤቱን በአያያዝ ወይም በአጠቃቀም ጉድለት የተነሳ የተበላሸ ካለ በነበረበት አሟልተው ሊያስረክቡኝ
ተስማምተናል። ተከራይ የተከራዩትን ቤት ለሌላ ሶስተኛ ወገን በከፊልም ሆነ በሙሉ ቤቱን ማከራየትም ሆነ ማስተላለፍ እንደማይችሉ
ተስማምተው ውሉን ፈርመዋል።

4. የውሃ የመብራት ክፍያ በተመለከተ ተከራይ ከተከራዩበት ቀን አንስቶ ወቅቱን ጠብቀው በተጠቀሙበት መጠን ይከፍላሉ። ቤቱንም
በሚለቀበት ጊዜ ቀሪ ሂሳብ ካለ አጠናቀው ከፍለው በተጠቀሙበት መጠን ይከፍላሉ። ቤቱን በሚለቁበት ጊዜ ቀሪ ሂሳብ ካለ አጠናቀው
ከፍለው በስማቸው በዚህ ቤት ቁጥር ያወጡትን ንግድ ፈቃድ ተመላሽ አድርገው ለአከራይ የኪሊራንስ ኮፒ ይሰጣሉ ቴኦቲ 10 ፐርሰንት
በተመለከተ በአከራይ በኩል ከተከራይ ተቀብለው ለመንግስት ሊከፍሉ ተስማምተዋል፡፡

5. ይህ ውል ከሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ለሶስት አመት ድረስ ውሉ የፀና ሲሆን በውሉ ዘመን
ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ከውል ሰጪም ሆነ ከውል ተቀባይ በኩል ይህንን ቤት ለመልቀቅ ሆነ ለማስለቀቅ በሚፈልግብት ግዜ ሁለቱም
ተዋዋይ ወገኖች የአንድ ወር ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በቃልም ሆነ በፅሁፍም መስጠት አለባቸው፡፡

6. ይህ የኪራይ ውል በ 5000 ብር የሚቆየው ለሁለት ዓመት ሲሆን የሶስተኛው አመት ክፍያ መጠን በሠዓቱ ማለትም በ 3 ኛው አመት
በጊዜው በድርድር ይወሰናል፡፡

7. ተከራይ ቤቱን ከተከራዩበት አገልግሎት ውጪ ለሌላ አላማ ማዋል አይችሉም፡፡

 ይህንን ውል ለማፍረስ የሚሞክር ወገን ቢኖር ውሉን ላከበረ ወገን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1889/18890 ገደብና ኪሳራ ብር 200/ሁለት መቶ
ብር/ ከፍሎ ውሉና ገደቡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1675/1731/2005 መሰረት ውሉ በህግ ፊት የፀና ነው፡፡

የአከራይ ስምና ፊርማ የተከራይ ስምና ፊርማ

……….………………….. …………………………….

You might also like