You are on page 1of 2

ቀን 12/10/2013 ዓ/ም

የንብረት ክፍፍል ስምምነት ውል

ተስማሚዎች ---------------- 1 ኛ አቶ ሚሊዬን አደፍርስ ሞልቶታል

አድራሻ አ/አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቤ/ቁጥር አዲስ

2 ኛ/ ወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ እሸቴ

አድራሻ አ/አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቤ/ቁጥር አዲስ

እኛ የንብረት ክፍፍል ውል ስምምነት አድራጊዎች በፌደራል የመጀመሪ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ 1 ኛ ቤተሰብ
ችሎት በነበረን የፍቺ ክርክር ጉዳይ ፍ/ቤቱ በመ/ቁ 117139 በቀን 23/4/2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት ጋብቻችን የፈረሰ
ሲሆን የጋራ ንብረታችንን በተመለከተ ተስማሚዎች በጋራ ያፈራነውን ንብረት በስምምነት እንድንካፈል በተሰጠው
ትእዛዝ መሰረት ጋብቻችን ጸንቶ በቆየበት ጊዜ ያፈራነውን ንብረት እንደሚከተለው ለመካፈል ተስማምተናል፡፡

የጋራ ንብረትን በተመለከተ

1 ኛ/ በወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ ስም የሚገኘዉ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቤት ቁጥር አዲስ የካርታ ቁጥር
ቦሌ 8/14/8/12/29787/00 ብሎክ ቁጥር CS-31 የፓርሴል ቁጥር B6 የሆነ G+3 መኖሪያ ቤት አሁን ባለዉ የወቅቱ የገበያ
ዋጋ ከዛሬ ጀምሮ ለመሸጥና እኩል ለመካፈል ተስማምተናል፡፡ አሁን ያለዉ የገበያ ዋጋም በ 14,000,000 ብር ( አስራ
አራት ሚሊዬን ብር) በመሆኑ 2 ኛ ተስማሚ ወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ ለማስቀረት የፈለገች በመሆኑ የ 1 ኛ ተስማሚ ድርሻን
ግማሹን 7,000,000 ብር (ሰባት ሚሊዬን ብር) ከዛሬ ጀምሮ በሁለት ወር ጊዜ ዉስጥ ልትሰጠዉ ተስማምተናል፡፡ ነገር
ግን 2 ኛ ተስማሚ ወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ የ 1 ኛ ተስማሚ ድርሻን በተባለዉ ጊዜ ሀሉንም ገንዘብ አጠቃላ መክፈል
ካልቻለት ቤቱን ለሌላ ሰዉ በወቅቱ በሚኖረዉ የገበያ ዋጋ ሸጥን እኩል ለመካፈል ተስማምተናል፡፡

2 ኛ/ በወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ ስም የሚገኘዉ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ክልል የካ 2 ሳይት ህንፃ ቁጥር B30 የወለል ቁጥር B-
30/06 የካርታ ቁጥር 012/11623/00/11639 የሆነዉ ኮንዶሚኒየም ቤት ባለዉ የወቅቱ የገበያ ዋጋ ከዛሬ ጀምሮ
ለመሸጥና እኩል ለመካፈል ተስማምተናል፡፡ አሁን ያለዉ የገበያም ዋጋ 2,500,000 ብር (ሁለት ሚሊዬን አምስት መቶ
ሺህ ብር) በመሆኑ 2 ኛ ተስማሚ ወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ ለማስቀረት የፈለገች በመሆኑ የ 1 ኛ ተስማሚ ድርሻን ግማሹን
1,250,000 ብር (አንደ ሚሊዬን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ከዛሬ ጀምሮ በ 15 ቀን ጊዜ ዉስጥ ልትሰጠዉ እንዲሁም
ቤቱ ከታህሳስ ወር 2013 ዓ.ም ድረስ በወር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ወ/ሮ ሰናይነት ክፍሌ ያከራየችዉንና ወደፊትም ቤቱ
እስከሚሸጥ የምታከራየዉን ግማሹን ለ 1 ኛ ተስማሚ ሚሊዬን አደፍርስ ልትሰጥ ተስማምተናል፡፡ ነገር ግን 2 ኛ
ተስማሚ ወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ የ 1 ኛ ተስማሚ ድርሻን በተባለዉ ጊዜ ሀሉንም ገንዘብ አጠቃላ መክፈል ካልቻለት ቤቱን
ለሌላ ሰዉ በወቅቱ በሚኖረዉ የገበያ ዋጋ ሸጥን እኩል ለመካፈል ተስማምተናል፡፡

3 ኛ/ በአቶ ሚሊዬን አደፍርስ ስም የሚገኘዉ በቦሌ ክፍለ ከተማ ሀያት ሳይት ብሎክ 08 የቤት ቁጥር 1002 የካርታ ቁጥር
ቦሌ 10/175/2/25/57773100 የሆነዉ ኮንዶሚኒየም ቤት የአቶ ሚሊዬን አደፍርስ የግሉ ሆኖ እንዲቀጥል
ተስማምተናል፡፡

4 ኛ/ በወ/ሮ ሰናይት ስም የሚገኘዉ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሾላ ገበያ በቀድሞ የንግድ ቤት ቁጥር 2-258 በአሁኑ
ደግሞ የንግድ ሱቅ ቁጥር 743 የሚገኘዉ የንግድ ሱቅ እና የሾላ ገበያ አክሲዬን ማህበር ወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ
እንድትወስድና የግሏ እንዲሆን ተስማምተናል፡፡

5 ኛ) በወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ ስም የሚገኘዉ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ክልል የሚገኘዉ አዲና የገበያ ማዕከል አክሲዬን
ማህበር በሁለታችን ስም እንዲመዘገብና ባለዉ የገበያ ዋጋ ሸጠን ለመካፈል ተስማምተናል፡፡
6 ኛ/ የቤት እቃን በተመለከተ 1 ኛ ተስማሚ ከሚጠቀምበት አንድ ቴሌቪዠን እና አንድ አልጋ በስተቀር ሙሉ በሙሉ
ሁለተኛ ተስማሚ እንድትወስድ ተስማምተናል፡፡

እኛ ተስማመሚዎች በዚህ ላይ ከሰፈሩት ዉጪ ባሉትም የንብረት ጉዳዬች ተነጋግረን ተቻችለን ተስማምተን የጨረስን
ስለሆነ ከዚህ በላይ ከተስማማነው ውጭ አንዳችን ከሌላችን የምንጠይቀው ገንዘብም ሆነ ንብረት የሌለ መሆነን
እያረጋገጥን የንብረት ክፍፍል ውል የተስማማን መሆኑን በተለመደው ፊርማችን እናረጋግጣለን፡፡

የውል አድራጊዎች ስምና ፊርማ

1 ኛ/ አቶ ሚሊዬን አደፍርስ ሞልቶታል 2 ኛ/ ወ/ሮ ሰናይት ክፍሌ እሸቴ

…………………………………… ………………………………

You might also like