You are on page 1of 3

ሶል የባህል አልባሳት መሸጫ ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

SOL TRADITIONAL COLTHS SALES PLC

የስራ ቅጥር ውል ፎርም


የሰራው ሁኔታ ቋሚ ጊዜያዊ
ይህ ውል ሶል የባህል አልባሳት መሸጫ ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በኋላ ድርጅት ተብሎ በሚጠቀሰው
እና በአቶ/ወ/ ______________________ከዚህ በኋላ ሠራተኛ ተብለው በሚጠቀሱት መካከል በሚከተለው
ሁኔታ ተፈፅሟል፡፡

አንቀጽ አንድ

ሶል የባህል አልባሳት መሸጫ ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ
20 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በማሰራት አስፈላጊ የመንግስት ግብር የሚከፈልበት በወር
ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) ይከፍላቸዋል፡፡

አንቀጽ ሁለት

1. ሠራተኛው በድርጅቱ የተዘጋጀውን የሥራ መመሪያ እና ደንብ ማክበር አለበት፡፡

አንቀጽ ሦስት

ይህ ውል ከተፈረመበት ዕለት ጀምሮ ለአንድ ዓመት የፀና ሆኖ እንደ ሥራው አስፈላጊነት እየታየ በአዲስ ውል
ካልተተካ ውሉ የተቋረጠ መሆኑን በሁለቱም ወገኖች ግንዛቤ ይደረጋል፡፡

2. የሥራ ውል መቋረጥ

ስልክ ቁጥር 09-13-59-30-03 ፖስታ ሣ.ቁ 90246 አዲስ አበባ


ሶል የባህል አልባሳት መሸጫ ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
SOL TRADITIONAL COLTHS SALES PLC

2.1 መሠረተ ሃሳብ

ማንኛውም የድርጅቱ ሠራተኛ ሥራውን በልዩ ልዩ ምክንያቶች መቀጠል ስይችል ሲቀር ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ከድርጅቱ ጋር ያለው የሥራ ውል ሊቋረጥ ይችላል፡፡

የሥራ ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች

1. ሁለቱ ወገኖች ውሉን ለማቋረጥ ሲስማሙ


2. ሠራተኛው በገዛ ፈቃዱ ሥራውን ሲለቅ
3. በሠራተኛው ችሎታ ማነስ ምክንያት ከሥራ ሲሰናበት
4. በድርጅቱ ደንብና በህጉ መሠረት ከሥራ የሚያስወጣ ጥፋት ሠራተኛው ሲፈፅም
5. ድርጅቱ የጀመረውን ስራ ሲያጠናቅቅ
6. በተጨማሪም ተመሳሳይነት ባላቸው ሌሎች ምክንያቶች

የሥራ ውል ሲቋረጥ መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች

ስራውን ለመልቀቅ የሚፈልግ ሠራተኛ የ 30 ቀን ማስጠንቀቂያ ለድርጅቱ በቅድሚያ በፅሁፍ መስጠት አለበት

1. የተረከበውን የድርጅቱን ንብረት ማስረከብ አለበት


2. የድርጅቱን መታወቂያ መመለስ አለበት

አንቀጽ አራት
የሰራተኞው ተያዥ

እኔ ወ/ሪት ውብአለም ሐይሉ ገ/ፃዲቅ የጉዳይ አስፈፃሚ የስራ መደብ ተቀጥሬ በወር ብር 1200.00 (አንድ
ሺ ሁለት መቶ ብር) እየተከፈለኝ የድርጅቱን ህግና ደንብ በማክበር ለመስራት ተስማምቸሃለሁ፡፡

ስልክ ቁጥር 09-13-59-30-03 ፖስታ ሣ.ቁ 90246 አዲስ አበባ


ሶል የባህል አልባሳት መሸጫ ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
SOL TRADITIONAL COLTHS SALES PLC

እኔም }Á» ለወ/ሪት ውብአለም ሐይሉ በተመደቡበት ስራ ላይ ማንኛውንም አይነት የንብረትም ሆነ የገንዘብ
ጉድለት ወይም የድርጅቱን ህግና ደንብ የሚፃረር ተግባር ከፈፀሙ ለሚደርሰው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂ
እንደምሆን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡

አንቀጽ አምስት
የዚህ ውል ተዋዋዮች ከ 30 ቀን በፊት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላሉ፡፡
ይህ ውል ከዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

የድርጅቱ ተወካይ ውል ተቀባይ

ስም_____________________ ስም________________________

ፊርማ ________________ ፊርማ____________________

ቀን__________________ ቀን__________________

ምስክሮች ፊርማ

1.

2.

ስልክ ቁጥር 09-13-59-30-03 ፖስታ ሣ.ቁ 90246 አዲስ አበባ

You might also like