You are on page 1of 63

ምዕራፍ አንድ - ጠቅላላ ድንጋጌዎች

አንቀፅ - አንድ
ትርጓሜ
1. ባንክ፡- ማለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማለት ነው፡፡
2. ማህበር፡- ማለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር ማለት ነው፡፡
3. አሰሪ፡- ማለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማለት ነዉ፡፡
4. የስራ መሪ፡- ማለት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 2 (10) ስር የተጠቀሱትን የሚያጠቃልል ሆኖ ከዚህ
በታች የተዘረዘሩትን ይጨምራል፡-
4.1. ፕሬዝዳንት
4.2. ኤክስኪውቲቭ ም/ፕሬዝዳንት
4.3. ቺፍ ኦፍ እሰታፍ
4.4. ም/ፕሬዝዳንቶች
4.5. ዳይሬክተሮች
4.6. ሥራ አስኪያጆች
4.7. በሥራቸው ሠራተኞችን የሚያስተዳድሩ ቡድን መሪዎች
4.8. ለቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ተጠሪ የሆኑ ሥራ አስኪያጆች
4.9. የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጆች

5. ሠራተኛ፡- ማለት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት ከአሰሪው ጋር
በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት ያለው ግለሰብ ማለት ሲሆን የማህበሩ አባል የሆነ ሠራተኛን ይመለከታል፡፡

6. “ደመወዝ” ማለት አንድ ሠራተኛ በሥራ ውሉ መሠረት ለሚያከናውነው ሥራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ነው፡፡
ሆኖም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 53/2 የተጠቀሱት ክፍያዎች እንደ ደመወዝ
አይቆጠሩም፡፡
አንቀፅ - ሁለት
የስምምነቱ አላማ
1. ሠራተኛው የማናቸውም የሥራ ውጤት ምንጭ እና መሠረት በመሆኑ ለጉልበቱ ተመጣጣኝ ክፍያ አግኝቶ የሥራ
መብቱ ተከብሮ የኑሮው ደረጃ እንዲሻሻል አስፈላጊ መሆኑን በማመን የገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ እና በመንግስት የልማት
ዕቅዶች መሠረት ባንኩ የውድድር አቅሙን በማጠናከር ትርፋማ ሆኖ ለመቆየት፥ ሠራተኛው የመስራት ፍላጎቱንና
ችሎታውን አዳብሮ ሙሉ ጉልበቱን እና ዕውቀቱን በመጠቀም የተሠጠውን የሥራ ኃላፊነት በቅን ልቦና እና
በቅልጥፍና እንዲያከናውን ማድረግ፤
2. የባንኩ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማዎች በተገቢዉ ሁኔታ እንዲሳኩ ለማድረግ የባንኩ የደንበኞች አገልግሎት
እንዲሳለጥ፣ ትርፋማነቱ እና ዕድገቱ እንዲረጋገጥ፣ እንዲሁም የገበያ ድርሻዉ እንዲሻሻል በማድረግ የባንኩ ህልውና
ተጠብቆ የሠራተኛው የሥራ ዋስትና እንዲረጋገጥ ማድረግ፤
1
3. በባንኩ ሠራተኞች፤በባንኩ እና በማህበሩ መካከል ያለውን ግንኙነት በመርህ ላይ የተመሠረተ እና ጤናማ በማድረግ፡
በጋራ በመሥራት፣ የባንኩን ራዕይ፡ ተልዕኮ እና ዓላማ በማሳካት እና ህልውናውን እንዲሁም የሠራተኛውን የሥራ
ዋስትና በማረጋገጥ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን የሚያስችል ለተደራዳሪ ወገኖች መብት እና ግዴታ ዕውቅና ሰጥቶ
አብሮ ለመስራት እንዲያስችል፤
4. በአጠቃላይ በሠራተኞች፣ በባንኩ እና በማኅበሩ መካከል ያለውን ግንኙነት ጤናማ እና ገንቢ ብሎም ሠላማዊ
የኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲኖር፤ የባንኩን የአመራር ወይም የአሰሪነት ነፃነት የማይገታ፣ የሠራተኛውን ደኀንነትና
ጤንነት ሊንከባከብ፣ ሰብአዊ ክብሩን ሊጠብቅ፣እንዲሁም ምቹ እና ተስማሚ የሥራ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ለማድረግ
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረታዊ ፅንሰ ሐሳብ እና ሌሎች ሕጎች ፣ ደንቦች እና ድንጋጌዎች
መርህን በመከተል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማኅበር መካከል የጋራ መተዳደሪያ
ደንብ በማስፈለጉ ይህ የህብረት ስምምነት ተፈርሟል፡፡

አንቀጽ - ሶስት

የስምምነቱ ወሰን
በሕግ ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በስተቀር ይህ ስምምነት በባንኩ፣ በማህበሩ እና በማህበሩ አባል ሠራተኞች
መካከል ተፈፃሚ የሚደረግ ሆኖ ፤ ከሌሎች ስምምነቱን ከማይፃረሩ የባንኩ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በማጣመር
እንደቅጥር ውል አካል ሆኖ ይቆጠራል፡፡

ምዕራፍ ሁለት

የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዴታ

አንቀጽ አራት

ማህበሩን ስለማወቅ
በዚህ የህብረት ስምምነት ውስጥ ስለ ተጠቀሱት ጉዳዮችና ሌሎች አባል ሠራተኛውን በሚመለከቱ የሥራ
ሁኔታዎች ሠራተኞችን የመወከል ፣ ከባንኩ ጋር የህብረት ስምምነት የመደራደር ፣ የመፈራረምና የማሻሻል ፣
የሠራተኛውን ቅሬታ በቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት ደንቦች ለባንኩ አቅርቦ መፍትሔ የማስገኘት መብት
ማህበሩ ያለው መሆኑን ባንኩ አውቆ ተቀብሎታል፡፡

አንቀጽ - አምስት

2
የባንኩ መብት
በዚህ የህብረት ስምምነት ዉስጥ የተጠቀሱት የማህበሩ እና የሰራተኛዉ መብቶች እንደተጠበቁ ሆነው ባንኩ በአዋጅ ቁጥር
1156/2011 እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 202/1987 እና ማሻሻሻያ ደንብ ቁጥር 134/1999
መሰረት፦
1. ባንኩ ሥራውን የመምራት፣ የባንኩን ፖሊሲና ስትራቴጂ የማውጣት፣ የሥራ ዕቅድ፣ ደንብና መመሪያ የማውጣት
እና በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችሉ ተገቢ እርምጃዎች የመውሰድ መብት አለዉ፡፡
2. ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማስተዳደር፣ የደረጃና የደመወዝ እድገት የመስጠት፣ የመቆጣጠር፣ የማዛወር፣ የመቅጣት፣
የመሾም፣ የመሻር፣ የማገድ ወይም የማሠናበት መብት አለዉ፡፡
3. በዚህ ሕብረት ስምምነት አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 7 ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ከሠራተኛው ጋር በሚደረግ
ውይይት የሥራ ግብ (goals) ለሠራተኛው አዘጋጅቶ ይሰጣል፡፡ በተሰጠው ግብ (goals) እና (Targets) መሰረትም
የሰራተኛውን የሥራ አፈፃፀም ይመዝናል፡፡

አንቀጽ - ስድስት

የባንኩ ግዴታ
1. ባንኩ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ የሰፈሩትን ድንጋጌዎች በሙሉ ሥራ ላይ
የማዋል ግዴታ አለበት፤ ሠራተኛው በሕግ፣ በአሰራር ወይም በዚህ ህብረት ስምምነት ያገኘውን መብትና ጥቅም
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሊቀንስበት አይችልም፡ ሆኖም በህግ ወይም በመመሪያ ከተደነገጉት መብቶች
ይልቅ የህብረት ስምምነቱ ለሰራተኛው የተሻለ ጥቅም ወይም መብት የሚያስገኝ ከሆነ የህብረት ስምምነቱ ተፈጻሚ
ይሆናል፤ ስለሆነም በአንድ ጉዳይ ላይ ተደራራቢ የሆነ የመብትና የጥቅም ጥያቄ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
2. ባንኩ በዚህ ህብረት ስምምነት ላይ በሰፈረው መሠረት የባንኩ ሠራተኞች ማግኘት የሚገባቸውን ደመወዝና ጥቅማ
ጥቅሞች በወቅቱ ይሰጣል ፤ ይከፍላል፡፡
3. ባንኩ የሥራ ቦታዎች እና የሥራ መሣሪያዎች በተቀመጠው ደረጃ (standard) መሰረት መሟላቱን ያረጋግጣል ፤
እንደአግባብነቱ ለሰራተኛው አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጤና አመቺ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ
መሳርያዎችና ቁሳቁሶች በሙሉ ደረጃቸውን ጠብቀዉ በወቅቱ የማቅረብ እና ይህም በሁሉም የስራ ክፍሎች
በተቀመጠው ደረጃ (standard) መሰረት መሟላቱን ያረጋግጣል፡፡
4. ባንኩ በማንኛውም ሁኔታ በማህበሩ ሥራ ውስጥ ጣልቃ አይገባም፤ በሠራተኞች ወይም በማህበሩና በአባሎቹ
መካከል አለመግባባትን የሚፈጥር እና ሊፈጥር የሚችል ድርጊት ወይም ማንኛውም ቅራኔ እንዲፈጠር
አይገፋፋም፡፡
5. ባንኩ ማህበሩ አንዲጠናከር ይረዳል፤ በማህበሩ በኩል በሚቀርቡለት ጥያቄዎች መሠረት በውይይትና በምክክር ላይ
ተመስርቶ አስፈሊጊውን ትብብር ሁሉ ያደርጋል፤ አግባብነት ያለው እገዛና ድጋፍም ይሰጣል፡፡

3
6. ባንኩ የሠራተኛዉን የሥራ ሰዓት በአግባቡ ያከብራል፡፡
7. ባንኩ ለእያንዳንዱ የሥራ መደብ የተዘጋጀውን የሥራ መዘርዝር (Job Description) ለሠራተኛ አዘጋጅቶ በሲስተም
(በኦራክል) ወይም በጽሁፍ እንዲያገኙት ያደርጋል፡፡ እንዲሁም ይህን ህብረት ስምምነት ጨምሮ ለሰራተኛው
አግባብነት ያላቸውን የባንኩ ደንብ እና መመሪያዎች በሁሉም ሠራተኞች ዘንድ እንዲታወቁ አስፈላጊውን ሁሉ
ማድረግ አለበት።
8. በባንኩ ዋናው መ/ቤት ዉስጥ ለማህበሩ ዋና መ/ቤት ቢሮ ይሰጣል፤ ይህ ከአቅም በላይ ከሆነ ግን የባንኩ ዋና መስሪያ
ቤት ከሚገኝበት አቅራቢያ አመቺ በሆነ ቦታ ቢሮ ይሰጣል፡፡ ለዲስትሪክት ተጠሪ ጽ/ቤቶች ከማህበሩ ጋር
በመወያያት እንደ አመቺነቱ ቢሮ ይሰጣል፡፡

9. የባንኩ ቅርንጫፎች፣ የዲስትሪክት ጽ/ቤቶች፣ የዋናዉ መ/ቤት ክፍሎች እና ሌሎች የባንኩ የሥራ ክፍሎች
በሚገኙበት ቦታዎች ሁሉ ባንኩ በሚጠቀምበት የማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ላይ የማህበሩ ህጋዊ ማህተም
ያረፈባቸው ሠራተኛውንና ማህበሩን የሚመለከቱ ልዩ ልዩ የውስጥ ማስታወቂያዎች እንዲለጠፉ ባንኩ ይፈቅዳል፡፡
ሆኖም ባንኩን እና ሠራተኛውን በሚመለከቱ የጋራ ጉዳዮች ላይ የሚወጡ ማስታወቂያዎች ማኅበሩ ከባንኩ ጋር
በመነጋገር ያወጣል፡፡

10. ማህበሩ በባንኩ የውስጥ መገናኛ መረብ (Portal) ላይ የሚጠቀምበት አንድ ገፅ (Menu) ባንኩ ይሰጣል፡፡
11. ሠራተኞች ተቀጥረው የሙከራ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ፣ ሲዘዋወሩ፣ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ሲወሰድባቸው፣ ጡረታ
ሲወጡ ፣ አደጋ ሲደርስባቸው ፣ ወደ ሥራ መሪ ሲያድጉ እና ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ባንኩ ለማህበሩ ዋና ጽ/ቤት
በግልባጭ ያሳውቃል፡፡
12. ሠራተኞች አቤቱታ ወይም ቅሬታ በሚያቀርቡበት ጊዜ የባንኩ አመራሮች በየደረጃዉ ከሚገኙ የማህበሩ ተወካዮች
ጋር በመሆን እንደ ጉዳዩ አሳሳቢነት በሥራ ሰዓትም ሆነ ከሥራ ሰዓት ውጪ በስምምነት በሚወስኑት ጊዜና ቦታ
በመገኘት ቅሬታዉን ይመረምራል መፍትሄም ይሰጣል፡፡

13. የባንኩ ሠራተኞች የባንኩን ሥራ በሚያከናውኑበት ጊዜ ድንገተኛ ህመም ወይም አደጋ ቢደርስባቸው በየደረጃው
የሚገኙ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ወይም ወኪሎች በአካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል ወይም የጤና ተቋምም ሆነ
እርዳታ ወደሚገኝበት ቦታ የባንኩ መኪና እንዲያደርስ ያደርጋሉ፡፡ በቅርብ የሚገኝ የባንኩ መኪና ከሌለም
በአካባቢው የትራንስፖርት አገልግሎት በማመቻቸት እርዳታ ወደሚገኝበት ቦታ ያደርሳል፡፡

14. ‘ከላይ በአንቀጽ 5(1) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የማህበር አባል የሆነን ማንኛውም ሠራተኛ በማህበር አባልነቱ
ወይም በማህበሩ የሥራ እንቅስቃሴ ተካፋይ በመሆኑ ምክንያት ባንኩ አይጎዳውም ወይም አድልዎ
አያደርግበትም፡፡

4
15. በየደረጃው የሚገኙ የማህበር መሪዎች በመሪነታቸውና በተወካይነታቸው ምንም ዓይነት አድሎና አስተዳደራዊ
በደል አይፈጸምባቸውም፧።

16. የባንኩን ንብረት እና ገንዘብ ከሙሰኞች ወይም ከአባካኞች ለሚከላከል ሠራተኛ በዚህ ምክንያት ከሚደርስበት እና
ሊደርስበት ከሚችል ጥቃት ባንኩ ይጠብቃል፡፡

17. ባንኩ ሰራተኛውን በሚመለከቱ ኮሚቴዎች ውስጥ ማለትም፡ በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፣ በሲስተም በተደገፈ የደረጃ
ዕድገት ኮሚቴ፣ በዝውውር ኮሚቴ፣ የአስተዳደር (የሥነ-ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ) ኮሚቴ እና በሌሎች አስፈላጊ
በሆኑ ኮሚቴዎች ውስጥ ማህበሩን ያሳትፋል፡፡

18. ባንኩ በየሦስት ወሩ፣ በየግማሽ ዓመቱ እና በየዓመቱ የባንኩን የሥራ አፈፃፀም ለመገምገም በሚያደርጋቸዉ የሥራ
መሪዎች ስብሰባ ላይ የማህበሩን አመራሮች ያሳትፋል፤ ያላቸዉን አጠቃላይ አስተያየት እንዲገልፁም ዕድል
ይሰጣል፡፡

19. የህብረት ስምምነት ተጠናቅቆ ከተፈረመ በኋላ ባንኩ የስምምነቱን በቂ ኮፒ እንደ አስፈላጊነቱ በራሱ ወጪ አሳትሞ
ለማህበሩና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው መ/ቤቶች ይሰጣል፤ ለእያንዳንዱ የባንኩ ሠራተኛም በሲስተም ተደራሽ
ያደርጋል፡፡

አንቀጽ - ሰባት
የማህበሩ መብት
1. የማህበሩ መሪዎችና በየደረጃው ያሉ ተወካዮች እንዲሁም የጽ/ቤት ሠራተኞች በሥራ ሰዓትም ሆነ ከሥራ ሰዓት
ውጪ በማህበሩ ጽ/ቤቶች ገብተው የመሥራት መብት አላቸው ፤ ሆኖም የማህበሩ ጽ/ቤት ባንኩ በሚገለገልበት ህንጻ
ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ከሥራ ሰዓት ውጪ ገብተው ለመሥራት የባንኩ የመግቢያ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል፡፡

2. በባንኩ በሚቋቋሙ የተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ ሠራተኛውን የሚወክሉ አባላት ተጠሪነታቸው ለማህበሩ በመሆኑ
ማህበሩ አባላቱን የመሰየም፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የመቀየር፣ ውክልናቸውንም የመሰረዝና በሌሎች አባላት
የመተካት መብት አለው፡፡

3. ከማህበሩ የሚወከሉ ተወካዮችም ሆኑ የባንኩ ሠራተኞች በሙሉ ወይም በከፊል በሚሳተፉባቸው ሠራተኛውን
በሚመለከቱ ስብሰባዎች ላይ የተያዙትንና የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ የስብሰባ ቃለ ጉባዔዎች ቅጅ ማህበሩ የማግኘት
መብት አለዉ፡፡

4. ባንኩ ሠራተኛውንና ባንኩን አስመልክቶ በየወቅቱ የሚያወጣቸውን የሥራ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የሥራ
ሁኔታዎች እና የባንኩ የበላይ አመራሮች የሚያስተላልፏቸውን ዘዋሪ ደብዳቤዎች ቅጅ ማህበሩ የማግኘት መብት
አለው፡፡
5
5. ማህበሩ ባንኩን በቅድሚያ በማሳወቅ በባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ አባላቱን የመሰብሰብ መብት አለው፡፡

6. ማህበሩ ሠራተኛውን የሚመለከት መረጃ እንዲሰጠው በጠየቀ ጊዜ መረጃውን የማግኘት መብት አለው፡፡ ሆኖም
ማህበሩ ከባንኩ በወሰደው መረጃ በባንኩም ሆነ በሰራተኛው ላይ የሚደርስ ጉዳት ካለ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡

አንቀጽ ስምንት

የማህበሩ ግዴታ

1. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅና በዚህ ህብረት ስምምነት ውስጥ የሰፈሩትን በሙሉ ሥራ ላይ ያውላል፤ ባንኩም
በህግም ሆነ በዚህ ኀብረት ስምምነት ያገኘውን መብትና ጥቅም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ አይፃረርም፡፡

2. ሠራተኛው ይህን ህብረት ስምምነት እና ባንኩ የሚያወጣቸውን ሕጎች፣ደንቦች እና መመሪያዎች በሚገባ በመረዳት
እና በማክበር ጠንካራ ዲሲፕሊን እንዲኖረው ማህበሩ ጥረት ያደርጋል፡፡

3. መንግሥት የሚያወጣቸው ፖሊሲዎች፡ሕጐችና ደንቦችን መሠረት በማድረግ ባንኩ የሚያወጣቸውን የባንኩን የሥራ
ደንብ፣ መመሪያዎችንና እቅዶችን ለማስፈጸም ማህበሩ ይተባበራል፡፡

4. ባንኩ ሠራተኛውን ለማሠልጠንና ለማስተማር በሚዘረጋው ፕሮግራም ውስጥ ሠራተኛውን በማስተባበርና


በማሰልጠን ረገድ ማህበሩ ሙሉ ተሳትፎና ትብብር ያደርጋል፡፡

5. የማህበሩ አመራሮች ከባንኩ የተረከቧቸውን ማናቸውንም ንብረቶች ለማህበሩ አገልግሎት ያዉላሉ፤ በጥንቃቄም
ይጠብቃሉ፡፡

6. ማህበሩ ህጋዊ መሪዎቹን ስም ዝርዝር ከነሥራ ኃላፊነታቸው በወቅቱ ለባንኩ ያሳውቃል፡፡ እንዲሁም ማህበሩ
የአባል ሰራተኞቹን ስም ዝርዝር መዝገብ ይይዛል ፤ ለአባላቶቹም የአባልነት መታወቂያ ይሰጣል፡፡

7. ባንኩ ራዕይዉን ለማሳካት እና ዕድገቱን ለማረጋገጥ በሚያካሄደው እንቅስቃሴ ውስጥ ማህበሩ ይሳተፋል
አስፈላጊውንም ድጋፍ ያደርጋል፡፡

አንቀጽ - ዘጠኝ

የሠራተኛው መብት

1. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ፣ በሌሎች ህጐች ፣ በፍ/ቤት ትዕዛዞችና በዚህ የህብረት ስምምነት የዲሲፕሊን
ድንጋጌዎች መሠረት የሚከለከልበት ምክንያት እስከሌለ ድረስ ማንኛውም የማህበሩ አባል ሰራተኛ በዚህ ህብረት
ስምምነት ውሰጥ የተጠቀሱትን መብቶችና ጥቅሞች በሙሉ ያገኛል፡፡

6
2. ሠራተኛዉ በግሉም ሆነ በማህበሩ አማካይነት ቅሬታ የማቅረብ እና መልስ የማግኘት መብት አለዉ፡፡

3. ሠራተኛዉ በራሱ ወይም በተወካዮቹ አማካኝነት የሠራተኛውን ተሳትፎ በሚጠይቁ የባንኩ የሥራ እቅድ አወጣጥ፤
የሥራ አፈጻጸም ግምገማና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ የማድረግና አስተያየቱን በጽሑፍም ሆነ በቃል
የመግለጽ መብት አለው፡፡

4. ሠራተኛው በሥራ ላይ እያለ በየጊዜው ያገኛቸውን የሥራ አፈፃፀም ውጤቶች ቅጂ የማግኘት መብት አለዉ፡፡

5. ሠራተኛው አስቀድሞ ሳያውቀው በኦራክል ሲስተም ላይ የሚገባም ሆነ በግል ማኅደሩ የተቀመጠ ማንኛውንም ጎጂ
የፅሑፍ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

አንቀጽ - አስር

የሠራተኛው ግዴታ

በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 የተገለጹት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሠራተኛው የሚከተሉት
ግዴታዎች ይኖሩታል፡፡

1. ሠራተኛዉ የዚህን የህብረት ስምምነት ድንጋጌዎችን ፣ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ድንጋጌዎችን ፣ ሌሎች የመንግሥት
ህጎችን ፣ ደንቦችን፣ፖሊሲዎችን እና ባንኩ እነዚህን ተንተርሶ የሚያወጣቸውን መመሪያዎች ያከብራል፡፡

2. ሠራተኛው በተመደበበት የሥራ መስክ ከቅርብ ሀላፊው ጋር በመሆን በተሠጠው ጎል እና ታርጌት (Goal and
Target) መሠረት ሥራውን ያከናውናል፡፡

3. ሠራተኛው የሚሰጠው የሥራ መዘርዝር በሲስተም ወይም በፅሑፍ ይደርሰዋል ፤ በዚሁ መሠረትም ሥራውን በአግባቡ
ያከናውናል፤ ሆኖም ከሥራ መዘርዝሩ የተለየ ሥራ እንዲያከናውን በፅሑፍ ሲጠየቅ ሥራውን ያከናዉናል፡፡

4. ሠራተኛው ሙሉ ችሎታውን ፣ ያለውን ሀይል ሳይቆጥብ እና ሳይለግም የተሰጠውን የሥራ ድርሻ በትክክልና
በቅልጥፍና ወይም በብቃት ያከናውናል፡፡

5. በማንኛውም ጊዜ የክፍል ኃላፊውም ሆነ የበላይ ኃላፊ ሥራውን በሚመለከት የሚያደርገውን ተገቢ ቁጥጥር
ይቀበላል፤በባንኩ ደንብና መመሪያ መሠረት የሚሰጠውን ትዕዛዝም ያከብራል፡፡

6. ማንኛውንም በኃላፊነት የተረከባቸውን የባንኩንና የደንበኞችን ንብረትና ገንዘብ እንዱሁም ዕቃዎች በጥንቃቄ
ይጠብቃል ፤ መመለስ የሚገባቸውንም በወቅቱ ያስረክባል፡፡

7
7. ሠራተኛዉ ማንኛውንም የባንኩንም ሆነ የደንበኞችን ምስጢር ወይም መረጃ ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል በስተቀር
ለሌላ ወገን አይገለጽም፤ ለግሉም ሆነ ለ 3 ኛ ወገን መገልገያ ወይም ጥቅም ማግኛ አያደርግም፡፡

8. በሥራ ጓደኞቹ ሕይወትና የአእምሮ ደህንነት ላይ እንደዚሁም በደንበኞች እና በባንኩ ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ
ድርጊቶችን አይፈጽምም፡፡

9. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና ሲጠየቅ የትርፍ ሰዓት ሥራ ከክፍያ ጋር ይሰራል፡፡

10. በመጠጥ ወይም አእምሮን በሚያደነዝዙ ዕጾች ተመርዞ በሥራ ገበታ ላይ መገኘት የለበትም፡፡

11. ስለ ጤና አጠባበቅ ባንኩ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት በየጊዜው የሚሰጠውን ክትባትና ሌላም ሕክምና ይፈፅማል፡፡

12. በሠራተኞች እንዲሁም በሠራተኞችና በባንኩ መካከል አለመግባባት የሚፈጥር ህገ-ወጥ ድርጊት ወይም ማንኛውንም
ጠብ አያነሳም፡፡

13. ሠራተኛዉ የባንኩን የሥራ ሰዓት በሚገባ ያከብራል፤ በሥራ ሰዓት ከሥራ አካባቢ ላይ ተነስቶ ከመሄዱ በፊት ከቅርብ
ኃላፊው ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

14. በሥራ ገበታው ላይ ያልተገኘን ሠራተኛ ሥራ ለማሟላት ከክፍል ሀላፊው ወይም ከበላይ ሀላፊው የሚሰጠውን
ተገቢውን ትዕዛዝ በሲስተም ወይም በፅሁፍ ተቀብሎ ይፈጽማል፡፡

15. ደንበኛ የህልውናችን መሠረት መሆኑን በመገንዘብ የባንኩን ደንበኞች በክብር፣ በቅልጥፍና እና በጥራት
ያስተናግዳል፤ የአገልግሎት ጥራትን በመጠበቅ ትርፋማነትን ያሳድጋል፡፡

16. ሠራተኛዉ የባንኩን ኮምፒዩተሮች እና የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች ሳይፈቀድለት አይገባም ፤ ሲፈቀድለት በአግባቡ
ይይዛል፣ ለባንኩ አገልግሎት ብቻ ይጠቀማል፤ የሚስጢር ቁልፉን ለሌላ ሦስተኛ ወገን አሳልፎ አይሰጥም፡፡

17. በሥራ ባልደረባው ወይም በባለጉዳይ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ማድረግ የተከለከለ ነዉ፡፡

18. ከሙስና፣ ከማጭበርበር፣ ከማስገደድ፣ ከማታለል ድርጊትና ከአድልዎ ነፃ ይሆናል፡፡ እነዚህም በሌሎች ቢፈጸሙ
ለቅርብ ሃላፊው ፣ ለባንኩ የሥነ ምግባር መኮንን፣ ለባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና/ ወይም ለባንኩ የሥራ አመራር
ቦርድ በሚስጥር ያሳውቃል፡፡

19. የግል ወይም የሌሎች ቡድኖች ጥቅምን ከባንኩ እና ከባንኩ ተገልጋይ ጥቅም አያስበልጥም፡፡ ይህም እንዲሆን ምክር
አይሰጥም፡፡

8
20. የባንኩን ደንበኞች ተገቢ በሆነ ሁኔታ የማስተናገድ፣ የአገልግሎት ጥራቱን ጠብቆ ደንበኞችን ሳያጉላሉ በወቅቱ
ተገቢውን ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

21. ሠራተኛው በስራ ሰአት የባንኩን የአለባበስ ሥርአት መመሪያ ተከትሎ ሁሌም ስራውን ያከናውናል፤ባንኩም ወጥ የሆነ
የአለባበስ ፕሮቶኮል እንዲኖር ተገቢውን ጥረት ያደርጋል፡፡

22. ለሠራተኛው የጋራ ደህንነት ሲባል የጦር መሣሪያ ወይም ሌሎች ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ መሳርያዎችን ይዞ መግባት
የለበትም፡፡

23. በባንኩ የስራ ሰአትና የሥራ ቦታ እንዲሁም ባንኩ ለስራ መገልገያ በሰጠው መሳርያ ተጠቅሞ የግል ስራ መስራት፣
ሌሎች ሀይማኖታዊም ሆነ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ፅሁፎችን፣ አርማዎችን፣ የቪዲዮና የድምፅ ምስሎችን መጠቀም
አይችልም፡፡

24. ሠራተኛዉ በሕግ ከተፈቀደለት አሰራር ውጪ የባንኩን ክብር እና ገፅታ በሚጎዳ መልኩ ማንኛዉንም እንቅስቃሴ
አያደርግም፡፡

አንቀጽ - አሥራ አንድ

የማህበር አባልነት

1. በዚህ ኅብረት ሥምምነት በአንቀፅ አንድ ንዑስ አንቀፅ አራት ስር ከተጠቀሱት በስተቀር በባንኩ የቅጥር ደንብ
መሠረት በደመወዝ የተቀጠረ ሠራተኛ የማኅበሩ አባል መሆን ይችላል፡፡

2. በዚህ ኅብረት ሥምምነት በአንቀፅ አንድ ንዑስ አንቀፅ አራት ስር በተጠቀሱት የሥራ መሪ መደቦች ላይ ሲሠራ
የቆየ ሠራተኛ ወደ ሠራተኛ የሥራ መደብ ከተዛወረ የሠራተኛ ማኅበሩ አባል መሆን ይችላል፡፡

3. ከዚህ በላይ ከተዘረዘረው ሌላ አዲስ የሥራ መደብ ባንኩ ሲከፍት በሥራ መደቡ የሚመደበው ሠራተኛ
የማኔጅመንት ወይም የሠራተኛ መደብ ውስጥ የሚካተት ስለመሆኑ አጠራጣሪ በሆነ ጊዜ የማኀበሩ አባል ሊሆን
ስለመቻል አለመቻሉ በባንኩና በማህበሩ መካከል በሚደረገው ውይይት ወይም ድርድር ይወስናል፡፡

አንቀጽ - አሥራ ሁለት

የአባልነት መዋጮ
1. ባንኩ ከአባል ሰራተኛዉ የወር ደመወዝ 1% የማህበር አባልነት መዋጮ ቆርጦ በየወሩ በማሕበሩ ሂሳብ ላይ ገቢ
ያደርጋል፡፡

9
2. ባንኩ ከማሕበሩ አባላት ደመወዝ ተቀንሶ ወደ ማሕበሩ ሂሳብ ገቢ የተደረገውን ገንዘብ የሚያመለክት የደመወዝ
መክፈያ ሰነድ ቅጂ በየወሩ ለማህበሩ ይሰጣል፡፡

3. ከማህበሩ አባላት ላይ የሚቆረጠው የመዋጮ ሂሣብ በጊዜው እንዲጣራ ባንኩ ከማኅበሩ ጋር ትብብር ያደርጋል፡፡
የሂሳብ ልዩነትም ሲፈጠር ባንኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጣርቶ እንዲያልቅ ያደርጋል፡፡ ባንኩ ከማኅበሩ አባላት
በየወሩ ከደመወዛቸው ላይ የተቀነሰውንና ወደ ማኅበሩ ሂሳብ ውስጥ ገቢ የተደረገውን ገንዘብ የሚያመለክት
የደመወዝ መክፈያ ሰነድ ቅጂ ለማህበሩ ይሰጣል፡፡(ሰብ አርቲክል ላይ አንድ አይነት ነዉ)

4. ይህንኑ የአባልነት መዋጮ ከወር ደመወዝ ላይ እንዳይቆረጥ ሠራተኛው ለማህበሩ ሠጥቶት የነበረውን ሥልጣን
መሻሩን የሚገልጽ የአባልነት መዋጮ መሠረዣ ፎርም ሞልቶ ለማኅበሩ እንዲሁም በግልባጭ ለባንኩ በፅሁፍ
ካሳወቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ወር ድረስ ማህበሩ የሠራተኛውን ሀሳብ ያስቀየረ መሆኑን ለባንኩ በደብዳቤ
ካልገለፀ በቀር ባንኩ ከሠራተኛው ደመወዝ የሚቆርጠውን የአባልነት መዋጮ ያቋርጣል፡፡

አንቀጽ - አሥራ ሦስት

የጋራ ውይይትና ግንኙነት


1. በዚህ ሕብረት ስምምነት ውስጥ ስለተዘረዘሩትም ሆነ በዚህ ሕብረት ስምምነት ውስጥ ስላልተገለጹ ጠቅላላ የስራ
ሁኔታዎች ላይ ለመወያየት ባንኩ እና ማህበሩ በየሶስት ወሩ አንዱ ወገን ለሌላው ወገን በሚያቀርበው የስብሰባ
አጀንዳ መሰረት ቋሚ የውይይት መድረክ ይኖራቸዋል፡፡

2. ከላይ በዚህ አንቀፅ ንዑሰ አንቀፅ (1) ላይ የተጠቀሰዉ እንደተጠበቀ ሆኖ አስቸኳይ ጉዳዮች በሚከሰቱበት ጊዜ
አንዱ ወገን ጥያቄ ካቀረበ በማንኛውም ጊዜ ውይይት ይደረጋል፡፡

3. በቋሚ የውይይት መድረክ ወቅት ሁለቱም ወገኖች ከስብሰባዉ ቀን አንድ ሳምንት አስቀድሞ አጀንዳ
ይለዋወጣሉ፡፡

4. በአስቸኳይ ስብሰባ ወቅት ውይይቱን የጠየቀዉ ወገን ከሦስት ቀን አስቀድሞ አጀንዳዎቹን ለሌላኛዉ ወገን
ይሰጣል፡፡

5. የቋሚ የውይይት መድረኩንም ሆነ የአስቸኳይ ስብሰባውን ሰዓት እና ቦታ ባንኩ ያመቻቻል፡፡

6. ሁለቱ ወገኖች ፈቅደው ካልተስማሙ በስተቀር በአጀንዳ ባልተያዙ ጉዳዬች ላይ ውይይት አይደረግም፡፡

7. በውይይት ወቅት ከእያንዳንዱ ወገን ከሁለት ያላነሱ ወኪሎች የሚገኙ ሆኖ ሁለቱ ወገኖች ተስማምተው
የተሳታፊዎችን ቁጥር ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

10
8. በእያንዳንዱ ስብሰባ የሚቀርቡ ሃሳቦች በሁለቱም ወገኖች በተመረጠ የቃለ-ጉባኤ ጸሃፊ አማካኝነት ተመዝግበው
ይያዛሉ፡፡ ስብሰባው በተካሄደ ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ቃለ-ጉባኤ ፀሐፊው ሁለቱንም ወገኖች ካስፈረመ በኋላ
ቅጂው ለሁለቱም ወገኖች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

9. ከዚህ በላይ በውይይቱ ላይ የተወሰነው ውሳኔ በሁለቱም ወገኖች ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ሆኖም ውሳኔው የህብረት
ስምምነቱን የሚያሻሽል ሆኖ ሲገኝ በሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳዩ ሚኒስቴር መመዝገብ ይኖርበታል፡፡

10. ባንኩን፣ ሰራተኛውንና ማህበሩን የሚመለከቱ አስፈላጊ መረጃዎችን የሰራተኛ ማህበሩ በባንኩ የሰው ሃይል
አስተዳደር በኩል የማግኘት መብት አለው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ባንኩ ከማህበሩ የሚፈልጋቸዉ መረጃዎች ካሉ
ከማህበሩ ፕሬዝዳንት ወይም የማህበሩ ፕሬዝዳንት በወከለው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በኩል የማግኘት
መብት አለዉ፡፡

ምዕራፍ ሦስት
የሰው ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች

አንቀፅ - አስራ አራት


ስለሠራተኛ ቅጥር እና የሙከራ ጊዜ
1. አዲስ ሠራተኞችን ለመቅጠር የቃልና የፅሁፍ ፈተና ወይም መመዘኛ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፈተናውን
የማዘጋጀት፣ የመፈተን፣ የማረም ተግባር የባንኩ ይሆናል፡፡
2. አዲስ ሠራተኛ የሚቀጠረው በዝውውር ወይም በደረጃ ዕድገት ቦታውን የሚሸፍንና ለቦታው የተቀመጠውን
ተፈላጊ መመዘኛ የሚያሟላ ነባር የባንኩ ሠራተኛ ሲታጣ ሆኖ የስራ ባህሪያቸው የተለየ ክህሎት የሚጠይቅ
ሲሆን፤ እንዲሁም ጀማሪ የባንክና የማኔጅመነት ሰልጣኞችን እንደ ቢዝነሱ ፍላጎት ለውስጥ ሠራተኞች ቅድምያ
በመስጠት ከውጭ ሊቀጥር ይችላል፡፡
3. ባንኩ አዲስ ሠራተኞችን ሲቀጥር በአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና በባንኩ የቅጥር ሥነ-
ሥርዓት መመሪያ መሠረት ሆኖ አዲስ ሠራተኞችን የቅጥር ፎርም ሲያስሞላ የማህበሩ ተወካይ በተገኘበት
የአባልነት መጠየቂያ ፎርም አብሮ አያይዞ ያቀርባል፡፡
4. የባንኩን የቅጥር መሥፈርቶች አሟልቶ የሚቀጠር ማንኛውም ሠራተኛ ከመቀጠሩ በፊት ተያዥ እንዲያቀርብ
ይደረጋል፡፡
5. ሠራተኛ በሚቀጠርበት ጊዜ ለጤንነት ምርመራ የሚከፈለውን ወይም የተከፈለውን ወጪ ባንኩ ይሸፍናል፡፡
6. በሙከራ ላይ ያለ ሠራተኛ ለሠራተኛ ከሚሰጥ ብድር በስተቀር ማንኛውም የባንኩ ቋሚ ሠራተኛ የሚያገኛቸውን
መብቶችና ጥቅሞች ሁሉ ያገኛል፡፡
7. የአዲስ ቅጥር ሠራተኛ የሙከራ ጊዜ ስልሣ (60) ተከታታይ ቀናት ሲሆን ስልሣ (60) ቀናትን የጨረሰ ሰራተኛ
ላልተወሰነ ጊዜ መቀጠሩን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ይሰጠዋል፡፡

11
8. የሙከራ ጊዜ ካለቀ በኋላ ሠራተኛው ሥራውን ከቀጠለ ለሙከራ ከተቀጠረበት ጊዜ ጀምሮ በውሉ ለታቀደው ጊዜ
ወይም ሥራ እንደተቀጠረ ይቆጠራል፡፡
9. ሠራተኛው በሙከራ ጊዜ ለተቀጠረበት ሥራ ብቁ ካልሆነ ወይም ሠራተኛው በባንኩ መሥራት ካልፈለገ
በተባለው የሙከራ ጊዜ ውስጥ ባንኩ ወይም ሠራተኛው በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 11(5) እና 11(6)
ድንጋጌዎች መሠረት የሥራውን ውል መሠረዝ ይችላል፡፡ በዚሁ ሁኔታ ከባንኩ የሚሰናበት ሠራተኛም የስንብት
ወቅት ክፍያዎች እና ጥቅሞች አያገኝም፡፡
10. ሠራተኛው የሙከራ ጊዜውን እንደጨረሰ የተመደበበትን የሥራ ክፍልና የሚያከናውናቸውን ተግባራት
የሚያስረዳ የሥራ መዘርዝር (Job Description) ይሰጠዋል፤ እንዲሁም ከባንኩ ጋር ያዘጋጁትን የመመዘኛ
መስፈርት ወይንም የሥራ ግብ (Target) ተቀብሎ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
11. አዲስ ሠራተኛ በሚቀጠርበት ጊዜ ባንኩ የማስተዋወቂያ (Orientation) ፕሮግራም ይሰጣል፡፡ ማህበሩንም
በፕሮግራሙ ላይ በመጋበዝ ስለዓላማው ለሠራተኞች ማብራሪያ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
12. ባንኩ የስራ ልምድ በሚጠይቅ የስራ መደብ ላይ ሰራተኛን ከቀጠረ ሰራተኛው ከዉጪ ይዞት የመጣዉ አግባብነት
ያለው የሥራ ልምድ ይያዝለታል፡፡

አንቀፅ - አስራ አምስት

ሠራተኛውን ስለማሰልጠንና ስለማስተማር


1. ጠቅላላ

1.1. ባንኩ የሠራተኛዉን ዕዉቀትና ክህሎት ለማዳበር፣ የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ፤ ሙያቸውን እንዲያሻሽሉ፣
ለቀጣይ የኃላፊነት ቦታ ለማብቃት እና የወደፊት የዕድገት መሰላላቸዉን ለማሳለጥ የተለያዩ ኮርሶችን፣
ሴሚናሮችን እና ስልጠናዎችን አቅዶ ይሰጣል፤ ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
1.2. ባንኩ የተለያዩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ወይም እንዲዘጋጅ በማድረግ ሠራተኞች ያላቸውን
እውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ እና የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም ሠራተኞች
ሙያቸውን እንዲያሻሽሉ እና ሁለገብ የባንክ ዕውቀት እና ክህሎት እንዲያዳብሩ በማድረግ ለቀጣይ
የሀላፊነት ቦታ ለማብቃት እና የወደፊት የዕድገት መሰላላቸውን ለማሳለጥ ይሰራል፡፡
1.3. የሠራተኛውን የሥራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት መሰረት በማድረግ አነስተኛ ውጤት ያመጣ ሠራተኛን ቢያንስ
የተቀመጠለትን ዝቅተኛ መለኪያ (Meets expectation) እንዲያመጣ እንዲሁም የተሻለ ውጤት ያመጣን
ሠራተኛ የበለጠ ለማነሳሳት ባንኩ እንደአስፈላጊነቱ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡
2. ትምህርት እና ስልጠና፡-

12
2.1. ባንኩ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ሠራተኛው በሙያና በችሎታው ተሻሽሎ ለተመደበበት ሥራ ብቁ
እንዲሆን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ለሠራተኛው ያመቻቻል፡፡
2.2. ባንኩ የሚያመቻቸዉ የትምህርት ዕድል እንደተጠበቀ ሆኖ ሠራተኛዉ በራሱ ጥረት ወይም በግሉ በፈጠረዉ
ዕድል መማር ይችላል፡፡
2.3. ከማንኛዉም የባንኩ ሥራ እና ፍላጎት ጋር ግንኙነት ያለው የትምህርት ዕድል (Scholarship) ሀገር ውስጥም
ሆነ ከሀገር ውጪ ሲገኝ ሁሉም እንዲያዉቁት እና እንዲወዳደሩ ይደረጋል፡፡
2.4. በውጭ ሀገርም ሆነ በአገር ውስጥ በግል በተገኘም ሆነ በባንኩ በተመቻቸ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል አግኝቶ
በባንኩ ወጪ የሚሳተፍ ሠራተኛ ትምህርቱን(ስልጠናውን) ተከታትሎ ካጠናቀቀ በኋላ
በትምህርቱ(በስልጠናው) ላይ የቆየበትን ጊዜ ያህል በባንኩ ውስጥ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ ያለበት
መሆኑን አውቆ በፅሑፍ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም በተለያዩ የቴክኒካል ስልጠናዎች ከአንድ ዓመት
ላልበለጠ ጊዜ የሚሳተፉ ሠራተኞች የአገልግሎት ቆይታ በባንኩ የሚወሰን ይሆናል፡፡
2.5. ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀፅ 4 የተገለፀው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ መደበኛ ሥራውን እያከናወነ በርቀት
ወይም በማታ የትምህርት ፕሮግራም በባንኩ ወጪ እንዲማር የተፈቀደለት ሠራተኛ ትምህርቱን ካጠናቀቀ
በኋላ በትምህርቱ ላይ የቆየበትን ጊዜ ግማሽ (1/2) ያህል በባንኩ ውስጥ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ
አለበት፡፡
2.6. በውጭ ሀገር በባንኩ ወጪ የከፍተኛ ትምህርት እንዲያጠና /የስልጠና ፕሮግራም እንዲከታተል/ የተደረገ
ሠራተኛ በታቀደለት ጊዜ ውስጥ ጨርሶ እስኪመለስ ድረስ ለተፈቀደለት የሥልጠና ጊዜ ባንኩ ደመወዙን
እና የቤት ኪራይ አበሉን ለቤተሰቡ ወይም ለህጋዊ ተወካዩ ይከፍላል፡፡ የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት
ወጪንም ይሸፍናል፡፡ ሆኖም የትምህርት ቆይታ ጊዜውን የሚያራዝም አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጠር በባንኩ
ይወሰናል፡፡
2.7. በሀገር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት (ሥልጠና) እንዲያጠናና ሴሚናር ወይም ኮርስ እንዲከታተል በባንኩ
የተፈቀደለት ሠራተኛ በታቀደለት ጊዜ ውስጥ ጨርሶ እስኪመለስ ድረስ ባንኩ ሙሉ ደመወዙን እና የቤት
ኪራይ አበሉን ለሠራተኛው ይከፍላል፡፡ሆኖም የትምህርት ቆይታ ጊዜውን የሚያራዝም አስገዳጅ ሁኔታ
ሲፈጠር በባንኩ ይወሰናል፡፡
2.8. ከፍ ሲል በንዑስ አንቀጽ 4 የተጠቀሰውን ባንኩን የማገልገል ግዴታ ሠራተኛው ሳይፈጽም ቢቀር ለትምህርት
ወይም ለሥልጠና የተከፈለለትን ወጪና በትምህርት ወይም በሥልጠና ጊዜ የተከፈለውን ደመወዝና
የትራንስፖርት ወጪ ለባንኩ ተመላሽ ያደርጋል፡፡ አፈፃፀሙ በባንኩ ይወሰናል፡፡
2.9. ከፍ ሲል በንዑስ አንቀጽ 2.5 የተጠቀሰውን ባንኩን የማገልገል ግዴታ ሠራተኛው ሳይፈጽም ቢቀር
ለትምህርት ወይም ለሥልጠና የተከፈለለትን ወጪ ለባንኩ ተመላሽ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙ በባንኩ
ይወሰናል፡፡

13
2.10. በትርፍ ጊዜያቸው እስከ ሁለተኛ ደረጃ ለሚማሩ ሠራተኞች ባንኩ ለመማሪያ (Tuition fee) እና
ለመመዝገቢያ (Registration fee) 100% ይከፍላል፡፡
2.11. በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ባገኙ የግል እና የመንግስት ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም በሌሎች
ተመሳሳይ ተቋማት በማታው የትምህርት ፕሮግራም ለሚማሩ ሠራተኞች ከትምህርቱ የሚያገኙት እውቀት
ከባንክ ሙያ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው እና ለባንኩ ስራ ጠቀሜታ ያለው ሆኖ ሲገኝ ማለትም
በማኔጅመንት፤ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን፤ በአካውንቲንግ፤ በኢኮኖሚክስ፣ በባንኪንግና ፋይናንስ፣
በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT)፤ በህግ እና ኢንጅነሪንግ ላይ ትኩረት በመስጠት ለሁለተኛ ዲግሪ
ለመጀመሪያ ዲግሪ እና ዲፕሎማ መማሪያ (Tuition fee) እና ለመመዝገቢያ (Registration fee) ወጪ
ከተፈቀደላቸው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ባንኩ 100% ይከፍላል።
2.12. ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀፅ 2.10 መሠረት ባንኩ በየዓመቱ ያለፉትን ዓመታት ሠልጣኞች ቁጥር መሠረት
በማድረግ ሠራተኞች የሁለተኛ ዲግሪ ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ እና የዲፕሎማ አመልካቾችን በማወዳደር
የትምህርት ዕድል ይሰጣል፡፡ የመወዳደሪያ መሥፈርቱንም ባንኩ እና ማኅበሩ በጋራ ያወጣሉ።
2.13. ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ለሚማሩ ሠራተኞች በመጀመሪያ ሲቀጠሩ ከደረሱበት ክፍል ጀምሮ
የሚማሩትን ትምህርት ባንኩ እየከፈለ ያስተምራቸዋል፡፡ ሆኖም ፈተናውን ወድቀው እንደገና ቢማሩ ባንኩ
ለደገመበት ክፍል አይከፈለውም።
2.14. ባንኩን በማስፈቀድ የውጭ አገር ቋንቋዎችን ለሚማሩ ሠራተኞች ባንኩ ወጪአቸውን 100% ይከፍላል፡፡
2.15. በግል ጥረታቸው የውጭ የትምህርት ዕድል ያገኙ ሠራተኞች ባንኩ ስፖንሰር የማያደርግ ከሆነ እና
የትምህርት አይነቱ ባንኩን የሚጠቅም ሲሆን በዓመት ውስጥ ቁጥራቸው ሳይበዛ ትምህርታቸውን ጨርሰው
እስከሚመጡ ድረስ ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
2.16. አስፈላጊነታቸው በታመነባቸው ከባንኩ የሥራ መስኮች ጋር በተገናኙ የትምህርት ዘርፎች ላይ ሠራተኞችን
በማወዳደር ለሦስተኛ ዲግሪ (PhD) የትምህርት ዕድል ሊሰጥ ይችላል፡፡ የትምህርቱ ቆይታ ጊዜውም
ትምህርቱ የሚፈቅድለት ጊዜ ያህል ሆኖ ሠራተኛውም ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ባንኩን አምስት (5)
ዓመት ለማገልገል አስቀድሞ ውል መግባት አለበት፡፡

3. ማስረጃ ስለማቅረብ

3.1. ባንኩ ስፖንሰር ያደረገዉ ሠራተኛ ትምህርቱን በሚገባ መከታተሉን የሚገልጽ ማስረጃ ከሚማርበት
ትምህርት ቤት በየሴሚስተሩ መጨረሻ ማቅረብ አለበት፡፡
3.2. ሠራተኛው ለእያንዳንዱ ትምህርት ገንዘብ የከፈለበትን ደረሰኝና የወሰዳቸውን እና የሚወስዳቸውን ኮርሶች
/የትምህርት አይነቶች/ ዝርዝር ያቀርባል፡፡ በወሰዳቸው የትምህርት አይነቶችም ማለፉ ወይም ሲ(C) እና
ከዚህ በላይ ወጤት ማግኘቱ ሲረጋገጥ ወጪው ከነመመዝገቢያው ወዲያውኑ ይተካለታል፡፡ ሆኖም

14
ለተከፈለለት የትምህርት ዓይነት የፈተና ውጤቱን እንዲያስመዘግብ ሲጠየቅ ካልቀረበ ባንኩ በቅድሚያ
የከፈለለትን ወጪ እንዲመልስ ያደርጋል፡፡
3.3. በሚከተሉት ምክንያቶች ብቻ ካልሆነ በስተቀር ሠራተኛው ድጋሚ ለሚወስዳቸው ኮርሶች (ትምህርት) ወጪ
ባንኩ አይከፍልም፡፡

3.3.1. በባንኩ አነሳሽነት ወይም ትዕዛዝ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ በመዛወሩ ምክንያት በተከታታይ ከሶስት
ሳምንት በላይ ትምህርቱን ባለመከታተል፤
3.3.2. በሐኪም በተረጋገጠ የጤንነት ችግር ምክንያት በተከታታይ ከሶስት ሳምንታት በላይ ትምህርቱን
ባለመከታተል፤
3.3.3. ከባንኩ ሥራ ጋር በተያያዘም ሆነ ሌሎች ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች ሠራተኛው በሕግ ወይም በፍርድ
ቤት ትዕዛዝ ከሶስት ሳምንታት በላይ ትምህርቱን ሳይከታተል ቢቀርና ጥፋተኛ አለመሆኑ ሲረጋገጥ፤
3.3.4. ሴት ሠራተኞች በወሊድ ምክንያት ትምህርታቸውን ለመከታተል ሳይችሉ ቀርተው ሲያቋርጡ፤
3.3.5. ሠራተኛው ቀድሞ የዲፕሎማ ተማሪ የነበረ ሆኖ የዲፕሎማ ትምህርቱን ባጠናቀቀበት ጊዜ ባገኘው ከፍተኛ
ውጤት ሳቢያ ወደ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲዞር የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ፈቅዶለት የአድቫንስ ስታንዲንግ
ትምህርት በሚከታተልበት ጊዜ ቀድሞ ማለትም በዲፕሎማ ፕሮግራም ወቅት “ሲ” (c) ያገኘባቸውን
የትምህርት ዓይነቶች ለዲግሪ ፕሮግራሙ የማያበቃው በመሆኑ እንደገና እንዲወስደው ሲደረግ፤
3.3.6. በአካዳሚክ ዲስሚሳል ከዩኒቨርሲቲ የተባረረ ሠራተኛ እንደገና ትምህርቱን ለመቀጠል (Readmission)
አመልክቶ በዩኒቨርሲቲው ሲፈቀድለት ባንኩም ሲያምንበት ቀደም ሲል የጀመረውን የትምህርት ዘርፍ
አንዲያጠናቅቅ ለቀሪው ትምህርት ወጪውን ይከፍልለታል፡፡

3.4. የርቀት (Distance) ትምህርት የሚከታተል ሠራተኛ ከሆነ በራሱ ጥፋት ትምህርቱን በማቆም ወይም
የሚፈለጉ ሰነዶችን በወቅቱ ባለመላክ ትምህርት ቤቱ ቢሰርዘው ወይንም ራሱ ትምህርቱን ቢያቋርጥና ሌላ
ትምህርት ለመቀጠል ቢፈልግ ወጪውን አይከፍልለትም፡፡ ባንኩ ለትምህርቱ ያወጣውንም የመማሪያ ወጪ
እንዲመለስ ያደርጋል፡፡
3.5. በትርፍ ጊዜ በሀገር ውስጥ በሚገኙ የትምህርት ተቋማትም ሆነ በውጭ ሀገር ባለ የትምህርት ተቋማት በባንኩ
ወጪ በርቀት ትምህርት ለመማር የሚቻለው በአንድ ጊዜ አንድ የትምህርት ዘርፍ ብቻ ነው፡፡

4. የትምህርት ማስረጃዎችን ስለሚያቀርቡ ሠራተኞች

4.1. በዚህ የህብረት ስምምነት ውስጥ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሠራተኛው ትምህርቱን
ተከታትሎ መጨረሱን የሚያረጋግጥ ዲግሪ ሲያቀርብና ለተማረውም ትምህርት ክፍት የሥራ መደብ ሲኖር
በውድድር ሥርዓት መሠረት ይመደባል።
4.2. በዩኒቨርሲቲ የማታ ትምህርታቸውን በመቀጠል ለዲግሪ ፕሮግራም የመጨረሻ ዓመት የደረሱ ሠራተኞች
በማታው ክፍለ ጊዜ የማይሰጡትን የትምህርት ዓይነቶች ለመማር ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ
15
ይሰጣቸዋል፡፡ ሆኖም የዚህ አይነት ፈቃድ የተሰጠው ሠራተኛ መደበኛ ሥራውን ያለተጨማሪ ክፍያ
በትርፍ ጊዜው ማጠናቀቅ አለበት፡፡
4.3. ከላይ በቁጥር 3.3.5 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ቀደም ዲግሪ የነበረው ሠራተኛ በሌላ የትምህርት
ዓይነት ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ ለመማር፣ ከዚህ ቀደም ዲፕሎማ የነበረው ሠራተኛ ደግሞ በተመሳሳይ
ትምህርት ዲግሪ ወይም በሌላ ትምህርት ዓይነት ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ ለመማር ሲፈልግ ከከፍተኛ
ተቋሙና ከባንኩ በኩል እስከተፈቀደ ድረስ ባንኩ ወጪውን ይከፍላል፡፡
4.4. ሠራተኛው በራሱ ለሚያገኘው የትምህርት ዕድል ባንኩ የመልቀቂያና ተገቢውን የድጋፍ ደብዳቤ በመስጠት
ይተባበራል፡፡

አንቀፅ - አስራ ስድስት

የሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም አስተዳደር (EmployeePerformanceManagement)


1. ትርጓሜ፡-

የሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም አስተዳደር ማለት ከባንኩ ዓላማዎች የመነጩ እና የሠራተኞች የሥራ መዘርዝርን መሠረት
ያደረጉ ግቦችን እና ዓላማዎችን ለሠራተኞች በመስጠት አፈፃፀማቸውን በመከታተል ውጤት መስጠት እና በውጤቱም
መሰረት የማሻሻያ ዕርምጃዎችን መውሰድ እንዲሁም ዕውቅናዎችን ወይም ሽልማቶችን መስጠት ማለት ነው፡፡

2. ዓላማ እና አስፈላጊነት፡-

2.1. የሠራተኞችን ሥነ-ምግባር ለማነፅ፣ ጠንካራ ጎናቸውን ለማጎልበት፣ ድክመቶቻቸውን ለማረም፣ የሥራ
ችሎታንና የግል ሙያን ለማዳበር ፤ ከዚህም አንፃር የሠራተኛው መልካም ውጤት የሚሰራበትን ክፍል እና
የባንኩን ዓላማ በማሳካት ውጤታማና ትርፋማ በማድረግ የሥራ ውጤቱ ያለማቋረጥ ዕድገት እንዲያሳይ
ለማድረግ፤
2.2. ሠራተኞች የራሳቸውን የሥራ ውጤት ደረጃ ለመገምገም እንዲረዳቸው ለማድረግ እና በሥራ ውጤታቸዉ
መሠረት ተገቢዉን ሥልጠናዎች ለማዘጋጀት፤
2.3. የሠራተኛዉ የሥራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት ለሠራተኛዉ የደረጃ ዕድገት፣ ለደመወዝ ጭማሪ እና ለተለያዩ
የማበረታቻ ሽልማቶች እንዲሁም የውድድር መንፈስ በሠራተኞች መካከል ለመፍጠር እና አጠቃላይ የሥራ
ውጤት ማሳደግን ያካትታል፡፡
2.4. ከፍተኛ የሥራ ውጤት ያስመዘገቡና የሥራ ችሎታና ብቃት ያላቸውን ሠራተኞች ለይቶ ለማወቅና ተገቢውን
ሥልጠና በመስጠት ለከፍተኛ ኃላፊነት ለማዘጋጀት፤
2.5. ባንኩ ለሚፈልጋቸው የተለያዩ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች እንደ ግብዓትነት ለመጠቀም ነው፡፡

3. የሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም አስተዳደር ሂደት፡-

16
3.1. የሥራ ምዘና ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ ከእያንዳንዱ የባንኩ ክፍሎች ማህበሩ እና ባንኩ በጋራ
በሚወክሏቸው ልምድ ያላቸው ሠራተኞች ፣ የሠው ኃይል አስተዳደር እንዲሁም ከሠራተኞች የሥራ ምዘና
መኮንኖች ጋር በመሆን የባንኩን ግቦች ባማከለ መልኩ ለእያንዳንዱ ክፍል ከሚሰራው ስራ ጋር የሚሄድ
የሥራ ግብ (goal) ያስቀምጣሉ፤
3.2. ባንኩ ከሰራተኞች የስራ መዘርዝር ጋር የሚጣጣም የስራ ውጤት መመዘኛ መስፈርቶችን ሲያዘጋጅ ግልፅ ፤
የሚለኩ ፤ ሊሳኩ የሚችሉ ፤ ተጨባጭ እና በጊዜ የተወሰኑ (Smart) መሆን ይኖርባቸዋል፡
3.3. ሠራተኛው የሚመዘነው አስቀድሞ ፈርሞ በተቀበላቸው የሥራ ግቦችና ዕቅዶች መሰረት ሆኖ በተጨማሪም
የባንኩን መሠረታዊ እሴቶች ያካትታል፡፡
3.4. የተቀመጡት የሥራ ግቦች አፈፃፀም ምዘና የሚካሄደው በየሩብ ዓመቱ ወይም በየዓመቱ ሆኖ ባንኩ
ባስቀመጠው ጊዜ እና መገልገያ ስርዓት (Oracle Self-service) በመጠቀም ይካሄዳል፤ የመመዘኛ ነጥቦች
ውጤት ትርጉም ከሥራ ግብ መመሪያ (Operationalization Document) ጋር ተካቶ ተፈፃሚ ይሆናል።
3.5. የባንኩ ዕቅድ እና ግቦች አዲሱ ሩብ ዓመት እንደገባ በአስር ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት፡፡ የቅርብ የሥራ
ሀላፊው ዕቅድና ግቦቹ እንደደረሱት በሦስት የሥራ ቀናት ውስጥ ለሠራተኛው መላክ አለበት፡፡
ሠራተኛውም ዕቅድና ግቦቹ በደረሱት በሁለት የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቅዱን አይቶ አስተያየቱን ለቅርብ
የሥራ ሀላፊው መመለስ አለበት፡፡
3.6. የቅርብ የሥራ ሀላፊው ከሰራተኛው የቀረበለትን አስተያየት ወይም ቅሬታ በቀረበለት በሁለት የሥራ ቀናት
ውስጥ መልስ መስጠት ያለበት ሲሆን ሰራተኛው በተሰጠሰቀው መልስ ካልተስማማ ለቀጣይ የበላይ ሃላፊ
ያቀርባል፤ የበላይ ሀላፊውም በአንድ የሥራ ቀን ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ይህም ውሳኔ የመጨረሻ
ይሆናል፡፡
3.7. ሠራተኛው የተሰጠውን ኃላፊነትና የሥራ ግብ በአግባቡ እንዲወጣ መቅረብ የሚገባቸው መሠረታዊ
ግብዓቶችና አቅርቦቶች መሟላት አለባቸዉ፡፡
3.8. ባንኩ አዳዲስ አገልግሎቶችን (products) በሥራ ላይ ሲያውል እና ለሠራተኛው እንደ ግብ ሲሰጥ ወይም
ሠራተኛዉ ለቦታዉ አዲስ ከሆነ የቅርብ የሥራ ሀላፊው አስቀድሞ ለሠራተኛው በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ
(orientation) ወይም ስልጠና ሊሰጠዉ ይገባል::
3.9. አንድ ሠራተኛ በሩብ ዓመቱ ውስጥ በኦራክል ሲስተም ከተሰጠው ግብ እና ዕቅድ ውጪ ሌላ ግብ እና ዕቅድ
ከተሰጠው እና ከሰራ ሥራዎቹ ለምዘና እንዲያዙለት ለማስቻል ባንኩ ቀጣይነት ያለው የሲስተም ማሻሻያ
ሥራዎችን ይሰራል፡፡
3.10. በኮርፖሬት ደረጃ ለእያንዳንዱ የስራ መደብ የሥራ እቅድ ወይም ግብ ሲዘጋጅ የሠራተኛ ማህበሩ መሳተፍ
አለበት፡፡

4. የሥራ ምዘና፡-
17
4.1. የሰራተኞች የስራ ምዘና የሚከናወነው በየሶስት ወር ሲሆን አንድ ሰራተኛ በነዚህ ወራት የሚመዘንበት የስራ
መደብ ላይ ቢያንስ ለሁለት ወራት መስራት አለበት፡፡
4.2. ሠራተኛው በተለያዩ ምክንያቶች ያለው የምዘና ውጤት የሁለት ሩብ ዓመት ብቻ ከሆነ ለዓመታዊ ምዘና
ይካተትለታል፡፡ ሆኖም የሠራተኛው ውጤት የአንድ ሩብ ዓመት ብቻ ከሆነ ዓመታዊ የሥራ ምዘና
አይኖረውም፡፡
4.3. የሥራ ኃላፊው ወይም የቅርብ ኃላፊው ከተመዛኙ፣ ሠራተኛ ጋር ባለው የግል ትውውቅ ወይም ጥላቻ፣
የጥቅም ግንኙነት ወይም የቀድሞ የምዘና ውጤትን መሠረት በማድረግ ብቻ የተመዛኙን ሠራተኛ ውጤት
ከፍ ወይም ዝቅ ማድረግ አይችልም፡፡
4.4. ሠራተኛው የስራ ምዘና ውጤቱን በመገልገያ ስርዓት (Oracle Serf-service) ከተመለከተ በኋላ ለሥራ
ኃላፊው ወይም ለቅርብ ኃላፊው አስተያየት ካለው አስተያየቱን አካቶ ይመልሳል፡፡ የቅርብ የሥራ ኃላፊው
የሠራተኛው የስራ ምዘና ውጤቱን ያፀድቃል። የሠራተኛው የስራ ምዘና ውጤትም ባንኩ ባስቀመጠው
የመረጃ ቋት (Database) ውስጥ ይቀመጣል።
4.5. ሠራተኛዉ ተማምኖ ከተቀበለዉ ዕቅድ አንፃር ተመዝኖ ያገኘዉ ውጤት ሩብ ዓመቱ አልቆ በሃያ ቀናት
ውስጥ ያገኘው ነጥብ ክፍልፋዩ ሳይጠጋጋ ውጤቱ ይሰጠዋል፡፡
4.6. ሠራተኛው ሳያውቅ የስራ ምዘና ግብ እና ውጤት አይሰጥም ሆኖም ሠራተኛው ካልተስማማ ውጤቱን
ተቀብሎ ቅሬታ ማቅረብ ይችላል፡፡
4.7. ሠራተኛው የሥራ አፈፃፀም ውጤቱን በተመለከተ ስለ ምዘናው ቅሬታ ሲኖረው ባንኩ ባስቀመጠው
የመገልገያ ስርዓት (Oracle Serf-service) በመጠቀም ቅሬታውን ይመዘግባል ፤ የሥራ ኃላፊው ወይም
የቅርብ ኃላፊው የተመዘገበውን ቅሬታ መርምሮ ያስተካክላል ወይም የውጤት ለውጥ ከሌለ ለሠራተኛው
በሶስት ቀን ውስጥ ያሳውቃል። ሆኖም ሠራተኛው በውሳኔው ቅሬታ ቢኖረው ሠራተኛው ቅሬታውን
ለሚቀጥለው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ያቀርባል። ኃላፊውም አለመግባባቱን ለማስወገድ ሁለቱንም በማነጋገር
ጉዳዩን መርምሮ ምዘናውን ያስተካክላል ወይም ያፀድቃል። ለሁለተኛ ጊዜ ለቀረበው ቅሬታ የተሰጠው
መልስ የመጨረሻ ይሆናል ።

5. የማበረታቻ ሽልማት፡-

5.1. ባንኩ ሁሉንም ሠራኞች በማወዳደር የተለየ የአፈፃፀም ብቃት እና ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ሠራተኞች ለይቶ
በየዓመቱ ሽልማት ይሰጣል፡፡
5.2. የሚሸለሙ ሠራተኞችን እና የሽልማቱን ዓይነት የመለየት ሂደት ላይ ማህበሩን በማሳተፍ ባንኩ የሚወስን
ሆኖ ዋንጫ ፣ ገንዘብ ፣ ቁሳቁስ ፣ የትምህርት ዕድል ፣ ማኔጅመንት ትሬይኒ የመስጠት ወይም ሌላ ሊሆን
ይችላል፡፡

18
5.3. የውድድሩ መስፈርቶች ወጥ ፣ ግልፅ እና የሚለኩ (Measurable) ሆነዉ ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያዉን
ባንኩ እና ማህበሩ በጋራ ያወጣሉ፡፡

አንቀፅ - አሥራ ሰባት

የሠራተኛው የሥራ ደረጃ እድገት


1. የሠራተኛው የሥራ ደረጃ ዕድገት ማለት አንድ ሠራተኛ ከነበረበት ዝቅተኛ የስራ ደረጃ ወደ ከፍተኛ የሥራ ደረጃ
በመሸጋገሩ ምክንያት የሚያገኘው የሥራ ደረጃ ዕድገት ነው፡፡ አንድ ሠራተኛ የስራ እድገት አገኘ የሚባለው
ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡

2. በመርህ ደረጃ የሠራተኛው የሥራ ደረጃ ዕድገት የሚሰጠዉ በውድድር ብቻ ነዉ፡፡

3. ክፍት የሥራ ቦታ በባንኩ ውስጥ በሚኖርበት ወቅት ይህንኑ የሚያስታውቀው አግባብ ያለው የባንክ አካል ሲሆን
የስራዉ ቦታ (ዲስትሪክት ፤ ቅርንጫፍ ፤ የሥራ ክፍል) ፣ የስራዉ ደረጃ ፣ የስራዉ መለያ ቁጥር ፣ የስራዉ
መዘርዝር ፣ ስራው የሚፈልገው የትምህርት ዝግጅት እና የስራ ልምድ እንዲሁም ሰራተኛው በምን መልኩ
ማመልከት እንደሚጠበቅበት በዝርዝር ተጠቅሶ የሥራ የደረጃ ዕድገት ማስታወቂያ ይወጣል፡፡

4. ክፍት የሥራ ቦታዉን መስፈርት የሚያሟላ ባንኩ በሚያወጣው መመዘኛ መስፈርት እና በሚሰጠው የችሎታ
መለኪያ ፈተና ተወዳድሮ በንፅፅር የተሻለ ውጤት ያገኘ ፀሐፊ ያልሆነ ሠራተኛ በፀሐፊነት የሥራ መደብ ላይ
ይመደባል፡፡

5. በአንድ የሥራ ቦታ እና የሥራ መደብ ላይ ምደባ የሚደረገው ከተወዳደሩት ሠራተኞች መካከል በንፅፅር የተሻለ
ውጤት ላላቸው ቅድሚያ በመስጠት ሆኖ ተጠባባቂ ለሆኑት እስከ ሦስት ወር የፀና ይሆናል፡፡

6. ማንኛዉም ሰራተኛ ተወዳድሮ ሲያድግ ደመወዙ ለአዲሱ የሥራ ቦታ በተመደበው መነሻ መጠን ይስተካከላል፡፡
ሆኖም በማንኛውም ሁኔታ ሠራተኛው ቀደም ሲል በነበረው የሥራ መደብ ከሚከፈለው ደመወዝ የተሻለ
ይሆናል፡፡

7. ሁለትና ከሁለት የሚበልጡ ሠራተኞች በባንኩ የምርጫ መስፈርት መሠረት ውጤታቸው እኩል ሆኖ ከተገኘ
የዕድገት ቅድሚያ የሚሰጠው ለአካል ጉዳተኛ እና ለሴት ሠራተኞች ይሆናል፡፡ ሆኖም አመልካቾቹ ሠራተኞች
ተመሳሳይ ጾታ ከሆኑ እንዲሁም ተመሳሳይ የአካል ጉዳት ካለባቸው በማህደር ጥራት ይወሰናል፡፡

8. በባንኩ ፕሬዝደንት የሚሰጥ ልዩ ውሳኔ እና በኦራክል ሲስተም የሚሰሩ ሥራዎች እንደ ተጠበቁ ሆነዉ
የሠራተኛዉ የደረጃ ዕድገት የሚፀድቀዉ በሦስት የኮሚቴ አባላት ሆኖ ሁለት ከባንኩ እና አንድ ሠራተኛ ማህበሩ
ያለበት የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ ሲፈርም ብቻ ነዉ፡፡

19
9. የሥራ ዕድገት ተሰጥቷል የሚያሰኘው የሠራተኛው ዕድገት በደረጃ ዕድገት ኮሚቴ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ
በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ሠራተኛው ለቦታው መመረጡን፣ የሚያገኘው ደመወዝና ጥቅማ-ጥቅም እንዲሁም
የዕድገት ቦታው ተገልፆ በሚመለከተው የባንኩ የሰው ሀይል አስተዳደር ሲፃፍለት ወይም ባንኩ በሚጠቀምባቸው
የመረጃ መረቦች አማካኝነት ሲገለጽለት ነው፡፡

10. የዕድገት ደብዳቤው በፅሑፍም ሆነ በሲስተም የተሰጠው ሠራተኛ ደብዳቤው ከደረሰው ቀን አንስቶ ከአንድ ወር
በላይ በቀድሞ ሥራው ላይ እንዲቆይ አይደረግም ፤ ሠራተኛዉ በባንኩ ምክንያት በአዲሱ የዕድገት ቦታ ላይ
ሥራውን መጀመር ካልቻለ ለአዲሱ የሥራ መደብ የተመደበውን ደመወዝ እና ጥቅማ-ጥቅም ያገኛል ፤ ሆኖም
ሠራተኛው በማንኛዉም ሁኔታ በአዲሱ የሥራ መደብ ላይ ሥራ ሳይጀምር ከሁለት ወር በላይ መቆየት
የለበትም፡፡

11. አዲስ የተቀጠረ ሠራተኛ ለደረጃ ዕድገት ውድድር ብቁ የሚሆነዉ በባንኩ ውስጥ ቢያንስ ለአንድ ዓመት ካገለገለ
በኋላ ነዉ፤ እንዲሁም በአንድ የሥራ መደብ ላይ ዕድገት ያገኘ ሠራተኛ በሌላ መደብ ላይ ለዕድገት ለመወዳደር
በያዘው የሥራ መደብ ላይ ቢያንስ አንድ ዓመት ማገልገል አለበት፡፡

12. በግል ማኅደር ውስጥ የሚገኙ የጊዜ ገደባቸው ያለፈባቸው የጽሑፍ ማስጠንቀቂያዎች ወይም የዲሲፕሊን
እርምጃዎች ለዕድገት ውድድር አይከለክሉም፡፡

13. በውድድሩ ውስጥ ለተሳተፉ ሰራተኞች በሙሉ ውጤታቸዉ ወይም ማለፍ አለማለፋቸዉ ፈተናውን ከወሰዱበት
ቀን ጀምሮ በ 15 ቀናት ውስጥ ይገለጽላቸዋል፡

14. የሠራተኛዉ የደረጃ ዕድገት ሂደት የሚከናወነው እንደ ባንኩ አሰራር በዲስትሪክት እና/ወይም በዋናዉ መስሪያ
ቤት ሊሆን ይችላል፡

15. ማንኛውም ሠራተኛ ለደረጃ ዕድገት የሚወዳደረው በሚከተሉት ነጥቦች መሠረት ይሆናል፡፡

ሀ - የስራ አፈፃፀም ውጤት - 50%


ለ - የተግባር ወይም የጽሑፍ ፈተና - 35%
ሐ - የሥራ ልምድ - 10%
መ - የአገልግሎት ዘመን - 5%
ድምር - 100%

16. የስራ ልምድ ማለት አንድ ሠራተኛ በዕድገት ማስታወቂያ ላይ በመስፈርትነት በተጠየቀው የሥራ ደረጃ ላይ
የሠራበት ዓመት ማለት ነው፤ በዚህ መሠረት ዝቅተኛ መስፈርቱን ብቻ የሚያሟላ ተወዳዳሪ ነጥብ የማይሰጠው

20
እና ከተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ የሥራ ልምድ ያለው ሙሉ ነጥብ የሚያገኝ ሲሆን በመካከል ያሉ
ተወዳዳሪዎች እንደቆይታቸው ተሰልቶ ነጥብ ይሰጣቸዋል፡፡

17. የአገልግሎት ዘመን ማለት በዚህ ሕ/ስምምነት አንቀፅ 14 ንዑስ አንቀፅ 12 ላይ የተጠቀሰዉ እንደተጠበቀ ሆኖ
ሠራተኛዉ አጠቃላይ በባንኩ ውስጥ የሰራበት ጊዜ ማለት ነዉ፤ በዚህ መሠረት ከተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ
የአገልግሎት ዘመን ያለው ሙሉ ነጥብ የሚያገኝ ሲሆን ሌሎች ተወዳዳሪዎች እንደቆይታቸው መጠን ተሰልቶ
ነጥብ ይሰጣቸዋል፡፡

18. የተግባር ወይም የጽሑፍ ፈተና ማለት ባንኩ ለተወዳዳሪዎች ለወጣዉ ክፍት የሥራ ቦታ ያላቸዉን ዕዉቀት
ለመገምገም የሚፈትናቸዉ ፈተናዎች ሆነዉ ፈተናዎቹም ወቅታቸዉን የጠበቁ፣ ጥያቄዎቹም ግልፅ እና
ያልተደጋገሙ፣ እንዲሁም ፈተናው በጥብቅ ቁጥጥር የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡

19. የአገልግሎት ዘመንና የስራ ልምድ እንዲሁም የስራ አፈፃፀም ውጤት ለውድድር ወይም ለምልመላ
በሚያስፈልግበት ወቅት ለመጠቀም እንዲያመች በባንኩ ኦራክል ሲስተም ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡

20. የዕድገት ደብዳቤ በፅሁፍም ሆነ በኦራክል ሲስተም የደረሰው ሠራተኛ ያለ በቂ ምክንያት የሚሰርዝ ከሆነ ለቀጣይ
ስድስት ወራት ለሌላ ዕድገት መወዳደር አይችልም፡፡

21. የባንኩ የሥራ ቤተሰብ (Job family) እና ሠራተኛው ማሟላት ያለበት መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው
ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ሠራተኛው ከአንድ የሥራ ቤተሰብ (Job family) ወደ ሌላ የሥራ ቤተሰብ (Job family)
ተወዳድሮ ማደግ ይችላል፡፡

22. የባንኩ የዕድገት ማለፊያ ነጥብ ከ100 ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ ይሆናል፡፡

አንቀፅ - አሥራ ስምንት

ከሥራ ደረጃ ዝቅ ስለመደረግ

1. ከደረጃ ዝቅ (Demotion) ማለት በሥነ ሥርዓት እርምጃ ወይም በሥራ አፈፃፀም ውጤት ከደረጃ (standard)
በታች በመቀነስ ምክንያት አንድ ሠራተኛ ከነበረበት የስራ መደብ ወይም ደረጃ እና ደመወዝ ወደ አነሰ የሥራ
ደረጃ እና ደመወዝ ዝቅ እንዲል ሲደረግ ነው፡፡

2. አንድ ሠራተኛ ከደረጃ ዝቅ የሚደረገዉ በሁለት ምክንያት ብቻ ሆኖ አንደኛዉ በሥነ-ሥርዓት እርምጃ ሲሆን
ሁለተኛዉ በሥራ አፈፃፀም ውጤት ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት ነዉ፡፡

21
3. አንድ ሠራተኛ በሥራ አፈፃፀም ውጤት መቀነስ ምክንያት ከደረጃ ዝቅ የሚደረገዉ በቅርብ የሥራ ሀላፊው
በየሩብ ዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ማሻሻያ ድጋፍ (አቅም ግንባታ) እና ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለተከታታይ
ስድስት ሩብ ዓመት ማሻሻል ካልቻለ ነው፡፡

4. በዚህ ንዑስ አንቀፅ መሰረት ከስራ ደረጃ ዝቅ የተደረገ ሠራተኛ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ለማንኛውም የእድገት
ውድድር መቅረብ አይችልም፡፡

5. በስራ አፈፃፀም ምክንያት አንድ ሠራተኛ ከደረጃው ቢያንስ ሁለት ጊዜ በተከታታይ አራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ዝቅ
ተደርጎ ሳያሻሽል በተጨማሪ ዝቅ የሚያስደርግ ሁኔታ ውስጥ ከተገኘ ባንኩ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011
መሰረት ከስራ እስከማሰናበት የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡

6. ሠራተኛዉ ከደረጃዉ ዝቅ ሲደረግ ከነበረበት የስራ ደረጃ ከሙያው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ወይም ሲሰራ ከነበረው
የሥራ መደብ ጋር ተዛማጅነት ወደ አለው ቀጣይ አነስተኛ የስራ መደብ ዝቅ ተደርጎ እንዲሰራ ይደረጋል፡፡

7. አንድ ሠራተኛ በሥነ-ሥርዓት እርምጃ ምክንያት ከደረጃ ዝቅ የሚደረገዉ በዚህ ሕብረት ስምምነት ውስጥ
ከተቀመጡት ሠራተኛዉን ከደረጃ ዝቅ የሚያስደርግ ጥፋትን ሲያጠፋ እና በአስተዳደር ኮሚቴ ሲወሰን
ይሆናል፡፡

አንቀጽ - አሥራ ዘጠኝ

በተተኪነት (Acting) የሚመደብ ሠራተኛ

1. ክፍት የሆነ የሥራ መደብ በሚኖርበት ጊዜ ቦታው በዕድገት ወይም በዝውውር እስኪሟላ ድረስ የቅርብ ኃላፊዉ
ከበላይ ኃላፊዉ ጋር በመነጋገር በትምህርት ደረጃው፣ በአገልግሎት ዘመን፣ በሥራ ልምድ እና በስራ አፈፃፀሙ
ውጤት የተሻለ ሠራተኛን መርጦ በጽሑፍ ወይም በኦራክል ሲስተም በተተኪነት እንዲሰራ ይመድባል፡፡
2. በተተኪነት ምደባ የሚሰጠው ከፍ ወደ አለዉ የሥራ መደብ ሆኖ የሥራ መሪነት ወይም የሠራተኛ የሥራ መደብ
ላይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
3. በተተኪነት የሚመደብ ሠራተኛ የአዲሱን የሥራ መደብ የሥራ መዘርዝርና የሥራ ግቦች (goals) እንዲሁም
ለጊዜው በቦታው ላይ መመደቡን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሁፍ ወይም በኦራክል ሲስተም ይደርሰዋል፡፡
4. አንድ ሰራተኛ በተተኪነት ከፍ ባለ ደረጃ ሲመደብ የተመደበበትን ቦታ ሙሉ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር ወስዶ
ስለሚሰራ ከተመደበበት ቀን ጀምሮ በሠራባቸው ጊዜያት ውስጥ ቀደም ሲል በያዘው የሥራ ደረጃ ላይ ሲያገኝ
የነበረው እና በተተኪነት በተመደበበት የሥራ ደረጃ መካከል ያለው የደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ልዩነት
ይከፈለዋል፡፡ ሆኖም የሚያገኘው ደመወዝ ለደረጃው ከተቀመጠዉ መነሻ ደመወዝ እኩል ወይም የሚበልጥ
ከሆነ በደመወዙ ላይ አንድ እርከን ተጨምሮ ይከፈለዋል።

22
5. አንድ ሠራተኛ በተተኪነት ተመድቦ የሚሰራዉ ቢበዛ ለሶስት ወራት ብቻ ነዉ፤ ባንኩ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ
ለቦታው ማስታወቂያ አዉጥቶ ሠራተኛን አወዳድሮ መተካት አለበት ፤ ሆኖም በማንኛዉም ምክንያት ባንኩ
በሦስት ወራት ውስጥ አወዳድሮ ሠራተኛን መመደብ ካልቻለ ሌላ ሠራተኛ በተተኪነት ይመደባል፡፡
6. አንድ ሠራተኛ በሥራ መሪ መደብ ላይ በተተኪነት በሚያገለግልበት ወቅት ከደመወዝ ልዩነት፣ ከአበልና ጥቅማ-
ጥቅም በስተቀር የትርፍ ሰዓት ክፍያ አይከፈለዉም፡፡
7. አንድ ሠራተኛ ተመሳሳይ ደረጃ የሆነን ሥራ ከራሱ ሥራ ጋር ደርቦ እንዲሰራ ሲፈለግ በጽሑፍ ወይም በኦራክል
ሲስተም ይሰጠዋል ሆኖም ከሰላሳ ተከታታይ ቀናት በላይ እንዲሰራ አይደረግም፡፡

አንቀፅ - ሃያ

ዝውውር

1. ዝውውር ማለት ከአንድ የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ወይም ከአንድ የሥራ ክፍል ወይም ዘርፍ ወደ ሌላ የሥራ
ክፍል ወይም ዘርፍ የሚፈጸም የሠራተኛ ዝውውር ነው፡፡

2. ዝውውር በሦስት ምክንያች ሊፈፀም ይችላል እነሱም፡- በባንኩ ፍላጎት የሚደረግ ዝውውር፣ በሠራተኛዉ
ፍላጎት የሚደረግ ዝውውር እና በሕክምና ቦርድ ትዕዛዝ የሚደረግ ዝውውር ናቸዉ፡፡

3. በባንኩ ፍላጎት የሚደረግ ዝውውር ፡-

3.1. ሠራተኛው ቀድሞ የሚያገኘውን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲሁም ደረጃ ሳያጓድል ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ወይም ክፍል
አዘዋውሮ ለማሠራት ይችላል፡፡
3.2. ባንኩ የሚያደርገዉ ዝውውር ጊዜያዊ ወይም ቋሚ ሊሆን ይችላል፤ በጊዜያዊነት እንዲዛወር የተደረገ ሠራተኛ
በተዛወረበት የሥራ ቦታ ወይም ክፍል የሚቆይበት ከፍተኛ ጊዜ ስድስት ወር ብቻ ይሆናል።
3.3. በቋሚነት እንዲዛወር የተደረገ ሠራተኛ በራሱ ስምምነትና ፍቃድ ካልሆነ በስተቀር በተዛወረበት ቦታ የሚቆይበት
ከፍተኛ ጊዜ በደጋ አካባቢ 3½ (ሶስት ተኩል) ዓመት በቆላ አካባቢ ደግሞ 1 (አንድ) ዓመት ይሆናል፡፡
3.4. ባንኩ የሚያደርገዉ ማንኛዉም የሠራተኛ ዝውውር ሆነ ብሎ ሠራተኛዉን ለመጉዳት ወይም ለማጥቃት አይደረግም፤
ሆኖም ይህ ተፈፅሞ ሲገኝ እና ሲረጋገጥ ይህን የፈፀመ የሥራ መሪ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል፤ ሠራተኛዉም
ወደ ነበረበት ይመለሳል፡፡
3.5. የሚሰጠዉ ዝውውር በቋሚነት ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ከሆነ የዝውውሩ ደብዳቤ ቢያንስ ከ 20 ቀናት ቀድሞ
በጽሑፍ ወይም በኦራክል ሲስተም ለሠራተኛው እንዲደርሰው ይደረጋል ፤ በደብዳቤው ላይም የዝውውሩ ምክንያት፣
የተዛወረበት ቦታ፣ የሚከፈልው ደመወዝ፣ አበል እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በግልጽ ተዘርዝረው ይጻፋሉ፡፡

4. በሠራተኛው ፍላጎት የሚደረግ ዝውውር፡-

23
4.1. ሠራተኛው በማህበራዊ ችግሮቹ ምክንያት ዝውውር ሲጠይቅ ባንኩ የሚከተሉትን መስፈርቶች ግምት ውስጥ በማስገባት
ባለዉ ክፍት የሥራ ቦታ ዝውውር ሊሰጥ ይችላል፡

ሀ. የትዳር ወይም የቤተሰብ ሁኔታ

ለ. የአገልግሎት ዘመን ወይም ዕድሜ

ሐ. ሠራተኛዉ እየሰራበት ያለው ቦታ አስቸጋሪነት

4.2. መ. በሌሎች አሳማኝ ምክንያቶችአካል ጉዳተኛ ሠራተኛ የሚሰራበት ቦታ አመቺ አለመሆኑ ሲረጋገጥና ዝውውር
ሲጠይቅ ከጉዳቱ ጋር በተያያዘ አመቺ ወደ ሆነ ቦታ ዝውውር ይሰጠዋል።
4.3. በተመሳሳይ ደረጃ እና የሥራ መደብ ላይ ያሉ ሠራተኞች የእርስ በእርስ ዝውውር ጥያቄ ሲያቀርቡ ዝውውሩ በአስር ቀናት
ውስጥ ሊያልቅላቸዉ ይገባል፡፡

5. በሕክምና ቦርድ ትዕዛዝ የሚደረግ ዝውውር፡-

5.1. ሠራተኛው በሕመም ምክንያት ቀድሞ ከሚሠራው ሥራ የተለየ ሥራ እንዲሠራ ወይም ካለበት የሥራ ቦታ ወደ ሌላ
የሥራ ቦታ እንዲዛወር በሕክምና ቦርድ /Medical Board/ ትዕዛዝ ሲሰጥ ባንኩ ሠራተኛውን አመቺ ወደሆነ ሥራ ወይም
ቦታ ያዛውረዋል፡፡
5.2. ከላይ በንዑስ አንቀፅ አንድ የተጠቀሰው ቢኖርም ሠራተኛዉ ከባንኩ ጋር ስምምነት ካላቸዉ ሆስፒታሎች ለዝውውር
ጥያቄ የሕክምና ቦርድ ሲያመጣ ባንኩ የማጣራት ወይም ራሱ በመረጠዉ ሆስፒታል የማስመርመር መብት አለዉ፤
በመሆኑም የተሳሳተ መረጃ ያቀረበ ሠራተኛ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል፤ ዝውውሩም አይሰጠዉም፡፡
5.3. ነፍሰጡር የሆነች ሴት ሠራተኛ እስክትወልድ ድረስ ቀድሞ ትሠራ የነበረውን ሥራ አሁን ለመሥራት የሚያቅታት
መሆኑ በሐኪም ማስረጃ ሲረጋገጥ ባንኩ ለሠራተኛዋ ጤና አመቺ የሆነ ተመጣጣኝ ሥራ ይሰጣታል፡፡

6. በዲስትሪክትም ሆነ በዋናዉ መ/ቤት ደረጃ የሚደረግ ማንኛዉም የሰራተኛ ዝውውር ሲከናወን የሰራተኛ ማህበሩ
ተሳታፊ ይሆናል፡፡

7. ማንኛዉም ዝውውር የማሕበሩን ተግባራዊ እንስቅቃሴ በሚጎዳ እና በሚያዳክም መንገድ መፈጸም የለበትም፡፡

8. አንድ ሠራተኛ የማሕበሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወይም ኦዲት ኮሚቴ አባል ሆኖ ከተመረጠ እና ማህበሩ ከጠየቀ
ባንኩ ወደ አዲስ አበባ ዝውውር ይሰጠዋል፤ የማሕበሩን ሥራ ለመስራት በሚያመች የሥራ መደብ ላይም
ይመድበዋል።

9. ማንኛውም የማሕበሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወይም የኦዲት ኮሚቴ አባል ሠራተኛ ማህበሩ ሳያውቀው
እና/ወይም እራሱ በጽሑፍ ካልጠየቀ በስተቀር ከሚሠራበት ከተማ ውጭ አይዛወርም፡፡

24
10. አንድ ሠራተኛ የዲስትሪክት ተወካይ ሆኖ ሲመረጥ እና ማህበሩ ሲጠይቅ ባንኩ የዲስትሪክቱ ጽ/ቤት
ወደሚገኝበት ከተማ ዝውውር ይሰጠዋል፤ የሰራተኛ ማህበሩ ካልጠየቀ ወይም ሰራተኛው ራሱ በፅሑፍ ካልጠየቀ
በስተቀር የዲስትሪክቱ ጽ/ቤት ካለበት ከተማ ውጪ እንዲዛወር አይደረግም፡፡

11. ሠራተኛው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም 2 ኛ ዲግሪ እየተማረ ከሆነ እና ለማጠናቀቅ
አንድ ዓመት የሚቀረዉ ከሆነ በራሱ ፍቃድ ካልሆነ በስተቀር ካለበት ከተማ ውጪ እንዲዛወር አይደረግም፡፡

አንቀፅ - ሀያ አንድ

የሥራ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ

1. የሥራ ውል የሚቋረጠው በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በተደነገጉት ሁኔታዎች መሠረት
በአሰሪው ወይም በሰራተኛው አነሳሽነት ወይም በሕግ በተደነገገው መሠረት ወይም በህብረት ስምምነት ወይም
በተዋዋይ ወገኖች በሚደረግ ስምምነት ሆኖ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

2. አሠሪው ሠራተኛው ላይ ኢሠብአዊ ክብሩን እና ሞራሉን የሚነካ ወይም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት
የሚያስቀጣ አድራጎት በመፈፀሙ የተነሣ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ሲያቋርጥ፤

3. አሠሪው ለሠራተኛው ደህንነት ወይም ጤንነት የሚያሠጋ አደጋ እንዳይደርስ ማስጠንቀቂያ ተሠጠቶት እርምጃ
ባለመውሰዱ የተነሣ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ሲያቋርጥ፤

4. በኅብረት ስምምነቱ መሠረት ሠራተኛው ከሥራ የሚያስወጣው ጥፋት ሲፈፅም፤

5. በአሰሪው ወይም በስራ መሪው ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ ሲፈፀምበት ሰራተኛዉ ያለማስጠንቀቂያ የስራ
ውሉን ሲያቋርጥ፡፡

አንቀፅ - ሃያ ሁለት
የሥራ ስንብት ክፍያ መጠን
1. አንድ ሠራተኛ የሥራ ውሉን ሲያቋርጥ የሥራ ስንብት ክፍያ ማግኘት የሚችለው በአዋጅ ቀጥር 1156 አንቀፅ 39
ሥር በተደነገጉት ሁኔታዎች ይሆናል፡፡

2. ማንኛውም ሠራተኛ በዚህ ህብረት ሥምምነት አንቀፅ 21 ንዑስ አንቀፅ 4 እና አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ 3 ላይ
ከተመለከቱት ምክንያቶች በስተቀር በዚህ ህብረት ሥምምነት በአንቀፅ 21 ሥር በተዘረዘሩት ምክንያቶች የስራ
ውል ሲቋረጥ በሚከተለው አኳኋን የሥራ ስንብት ክፍያ ይከፈላል።

የአገልግሎት ዘመን የክፍያመጠን


ሀ. 1 (አንድ) ዓመት 1 (አንድ) ወር ደመወዝ
ለ. 2 (ሁለት) ዓመት 2 (ሁለት) ወር ደመወዝ
25
ሐ. 3 (ሦስት) ዓመት 3 (ሦስት) ወር ደመወዝ
መ. 4 (አራት) ዓመት 4 (አራት) ወር ደመወዝ
ሠ. 5 (አምስት) ዓመት 5 (አምስት) ወር ደመወዝ
ረ. 6 (ስድስት) ዓመት 6 (ስድስት) ወር ደመወዝ
ሰ. 7 (ሰባት) ዓመት 7 (ሰባት) ወር ደመወዝ
ሸ. 8 (ስምንት) ዓመት 8 (ስምንት) ወር ደመወዝ
ቀ. 9 (ዘጠኝ) ዓመት 9 (ዘጠኝ) ወር ደመወዝ
3. ከዚህ በተጨማሪ አሥር ዓመትና ከዚያ በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት
የደመወዛቸው 1/3 ኛ እየታሰበ በተጨማሪ ይከፈላቸዋል፡፡ ሆኖም ጠቅላላ ክፍያው ከሠራተኛው የ 12 ወራት
ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡

4. በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በአንቀጽ 24/4፣ 24/5፤ 32(1)(ለ) 32(1)(ሐ) እና በአንቀጽ
29 ድንጋጌዎች መሠረት የስራ ውል ሲቋረጥ በዚህ ህብረት ሥምምነት አንቀፅ 22 ንዑስ አንቀጽ 2 ሥር
ከተመለከተው በተጨማሪ የሠራተኛው የመጨረሻ ሳምንት አማካይ የቀን ደመወዝ በ 60 ተባዝቶ ይከፈለዋል።

5. የሥራ ውል ከህግ ውጭ ሲቋረጥ በአዋጅ ቁጥር 1156/11 አንቀፅ 32፤42፤43 44 እና አንቀፅ 45


ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውልን በማቋረጥ ምክንያት የሚያስከተሉት ኃላፊነቶች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

አንቀፅ - ሃያሦስት

ሠርተፍኬት

1. ሠራተኛው ሥራ ላይ እያለ በማንኛዉም ጊዜ ሲፈልግ ወይም በማናቸውም ምክንያት ከባንኩ ጋር ያለው የሥራ
ውል ሲቋረጥ የሠራተኛውን ፎቶግራፍ የያዘ ሕጋዊ የባንኩ ኃላፊ ፊርማ እና የባንኩ ማህተም ያረፈበት
የአገልግሎት የምስክር ወረቀት (Certificate of service) ይሰጠዋል፤ የምስክር ወረቀቱ ይዘትም የሚከተሉትን
ሊያካትት ይችላል፡-
1.1. የሠራተኛው ሙሉ ስም
1.2. በአገልግሎት ዘመኑ የሰራቸው የሥራ ዓይነቶችና የሰራባቸውን ቦታዎች
1.3. አሁን ያለበት የሥራ ደረጃ እና የመጨረሻ ደመወዝ
1.4. ተገቢውን የሥራ ግብር መክፈሉን
1.5. ሌሎች ሠራተኛዉን የሚጠቅሙ መረጃዎችን ሊያካትት ይችላል፡
2. ሰራተኛው የአገልግሎት ምስክር ወረቀቱን ከጠየቀበት ቀን ጀምሮ ቢዘገይ በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ ማግኘት
አለበት፡፡

26
3. የስንብት ምስክር ወረቀት (Clearance) ሥራ ማቋረጡ ሲረጋገጥ እና የሚፈለግበትን የክሊራንስ ፎርማሊቲ
ሲያሟላ ቢዘገይ በሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ መሰጠት አለበት።
4. ከምስክር ወረቀት በተጨማሪ ሠራተኛው ከፈለገ ሠራተኛው ስላሳየው የሥራ አፈፃፀም ውጤት በጽሑፍ ማስረጃ
ይሰጠዋል፡፡
5. ሠራተኛው በሥራው ላይ እያለ ለዋስትና ወይም ለመሳሰሉት ጉዳዮች ከባንኩ የድጋፍ ደብዳቤ እንዲሰጠው
በጽሑፍ ሲጠይቅ በጠየቀዉ መሠረት ደመወዙ ተጠቅሶ ቋሚ ሠራተኛ መሆኑንና ባንኩንም ሲለቅ የሚያሳውቅ
መሆኑን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ይሰጠዋል፡፡

አንቀጽ - ሃያ አራት
ጡረታ
1. ማንኛውም በሙከራ ላይ ያለ ወይም ቋሚ ሠራተኛ የደመወዙን ሰባት በመቶ (7%) ባንኩ ደግሞ አስራ አንድ
በመቶ (11%) የጡረታ መዋጮ ይከፍላል፡፡ የጡረታ መዋጮ የሚቋረጠው ሠራተኛው ከባንኩ ጋር ያለው የሥራ
ውል ሲቋረጥ ነው፡፡

2. የአደጋ ኢንሹራንስ ክፍያ ማግኘት የጡረታ መብትንና ጥቅምን አያስቀርም፡፡

3. 5 (አምስት) ዓመት እና ከዚያ በላይ በባንኩ ውስጥ አገልግለው በዕድሜ ጣሪያ፣ በቅድመ ጡረታ እና በህክምና
ጡረታ የሚወጡ ሰራተኞች ባንኩ የመጨረሻ ወር ደመወዛቸውን መሰረት በማድረግ የሃያ አራት (24) ወራት
ደመወዝ በድጐማ መልክ ይሰጣቸዋል፡፡

4. ባንኩ የሰራተኛው ጡረታ መውጫ ከመድረሱ ሶስት አመት ቀደም ብሎ ሠራተኛዉ እንዲያዉቀዉ ያደርጋል።

5. ጡረታ በመውጣቱ የ 24 ወራት ደመወዝ በድጎማ የተከፈለው ሠራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያ አያገኝም፡፡

6. በጡረታ ለሚሰናበት ሠራተኛ በባንኩ ፕሬዝደንት የተፈረመ የምስጋና ሠርቲፍኬት ይሰጠዋል።

ምዕራፍ - አራት

ደመወዝ፣ ቦነስ እና ጥቅማጥቅሞች

አንቀፅ - ሃያ አምስት

ደመወዝ እና ቦነስ

1. ደመወዝ ማለት አንድ ሠራተኛ በሥራ ውል መሠረት ለሚያከናውነው ሥራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ነው፡፡
ሆኖም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 ሥር የተጠቀሱ ክፍያዎች
እንደ ደመወዝ አይቆጠሩም፡፡

27
2. የባንኩ የደመወዝ አከፋፈል ወይም አወሳሰን የሥራ ደረጃን መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ባንኩ በአዲስ
መልክ መዋቅር በሚያስጠናበት ወቅት የሥራ ደረጃው ዝቅ ወይም ከፍ ሊል ቢችልም አጠቃላይ የባንኩ የሥራ
ደረጃ (Job grade) ለውጥን የሚመለከት ካልሆነ በስተቀር የሠራተኛው ደረጃና ደመወዝ ዝቅ ሊደረግ
አይችልም፡፡
3. ባንኩ የሠራተኛውን ደመወዝ እ.ኤ.አ ወር በገባ ከ 25 እስከ 28 ባሉት ቀናት ውስጥ ይከፍላል፡ ሠራተኛውም
በፅሑፍ ወይም በኦራክል ሲስተም የሰዓት መቆጣጠሪያ (Time card) ይሞላል፤የክፍያ መረጃ (pay slip) በወቅቱ
ለሠራተኛው እንዲደርስ ይደረጋል፤ ሠራተኛው የደመወዝ አከፋፈሉ ላይ ጥያቄ ወይም ቅሬታ ካለው ባንኩ
በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ መልስ ይሰጠዋል ለዚህም ግልፅ አሰራር ይዘረጋል፡፡
4. በሕዝብ በዓላት ወቅት ባንኩ ከሠራተኞች ደመወዝ ተቀናሽ የሚሆን ሀያ በመቶ (20%) ከሦስት ቀን በፊት
በቅድሚያ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ይህ ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖረው በዓሉ ደመወዝ ከተከፈለ ከ 15 ቀናት በኋላ
የሚውል ሲሆን ነው፡፡
5. ደመወዝ የሚከፈለው ለተሰራ ሥራ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 54/2 መሠረት
ሠራተኛው ለመስራት ዝግጁ ሆኖ ሳለ በሠራተኛው ጉድለት ባልሆነ ምክንያት ባንኩ ሳያሰራው ቢቀር ሠራተኛው
ደመወዙን የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
6. በባንኩ አጠቃላይ ትርፋማነት እና የሥራ እቅድ አፈጻጸም እንዲሁም ባንኩ እና እያንዳንዱ ሠራተኛ በበጀት
ዓመቱ በየጊዜው በሚስማሙት የሥራ ግብ /goals/ አፈፃፀም ውጤት መሠረት የወቅቱን የዋጋ ግሽበት ታሳቢ
በማድረግ በየዓመቱ እ.አ.አ ከሐምሌ አንድ ቀን ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙም ባንኩና ማህበሩ
በጋራ በሚያወጡት መመሪያ ይሆናል፡፡
7. ባንኩ በጋራ ጥያቄና ውይይት ላይ በመመስረት በየጊዜው የደመወዝ ክለሳ ያደርጋል፡፡ ረቂቅ ጥናቱን
በሚያደርግበት ወቅት ማሕበሩን ያሳትፋል፡፡
8. አንድ ሠራተኛ ከባንኩ ስራ ጋር በተገናኘ ያለጥፋቱ ወይንም በጥርጣሬ ታስሮ ቢቆይና ጉዳዩን የያዘው ፍርድ ቤት
በነፃ ወይም ፖሊስ በዋስትና ቢያሰናብተው የሠራተኛው ማመልከቻ በማህበሩ ወይም በባንኩ የሰው ሐይል
አስተዳደር በኩል ለአስተዳደር ኮሚቴ ቀርቦ ሲወሰን ባንኩ ወደ ስራው ይመልሰዋል ፤ የደመወዙን እና የጥቅማ
ጥቅሙን ውዝፍ ይከፍለዋል፡፡
9. አንድ ሰራተኛ ከባንኩ ሥራ ውጪ በሆነ ምክንያት ታስሮ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ለመመለስ
ጥያቄውን በማህበሩ ወይም በባንኩ የሰው ሀይል አስተዳደር በኩል ካቀረበ የባንኩ የአሰተዳደር ኮሚቴ ወደ ሥራው
ሊመልሰው ይችላል፡፡
10. በማኛዉም ሁኔታ አንድ ሰራተኛ በባንኩ የሥራ መሪዎች ከሥራ ታግዶ ከአንድ ወር በላይ መቆየት የለበትም፤
ነገር ግን ዉሳኔ ሳይሰጠዉ አንድ ወር ካለፈዉ ታግዶ የቆየበት ደመወዙ እና ጥቅማ ጥቅሙ በባንኩ ተከፍሎት ወደ
ስራዉ ይመለሳል፡ ጉዳዩ ያላለቀ እንደ ሆነም ሥራዉ ላይ ሆኖ ይከታተላል፡፡

28
11. የባንኩን ትርፋማነት ፣ የሠራተኛውን የሥራ ዕቅድ አፈፃፀምና ውጤታማነትን በመገምገም ለተጨማሪ የሥራ
ውጤት እና ሠራተኛውን ለማትጋት ባንኩ ቦነስ ይሰጣል፡፡ አፈፃፀሙም ባንኩ እና ማህበሩ በጋራ በሚያወጡት
መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡

አንቀፅ - ሃያ ስድስት

ልዩ ልዩ አበሎች

1. የውሎ አበል

1.1. የውሎ አበል የሚከፈለው ሠራተኛው ለባንኩ ሥራ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ከ 25 ኪ.ሜ. በላይ ሲሰማራ ብቻ
ነው፡፡
1.2. ሠራተኛው ለሥራ ሄዶ ሳያድር የሚመለስ ከሆነ በቀን የተተመነውን የውሎ አበል ግማሸ ይከፈለዋል። ሆኖም
ሠራተኛው አድሮ ወደ መደበኛ የሥራ ቦታው የሚመለስ ከሆነ የገባበት ሠዓት ከግምት ሳይገባ የሚከፈለው የአንድ ቀን
ተኩል ይሆናል።
1.3. በውሎ አበል የሚከናወን ሥራ በማንኛውም ሁኔታ ከ 15 ተከታታይ ቀናት መብለጥ የለበትም፡፡ ሆኖም ሠራተኛዉ
ከመደበኛ የሥራ ቦታው ወደሌላ ቦታ በመስክ ሥራ ሲላክና ሥራው ከ 15 ተከታታይ ቀናት በላይ የሚያቆየው ሆኖ ሲገኝ
ለሚራዘመው ተጨማሪ ጊዜ በቅርብ የሥራ ሀላፊው የበላይ ሀላፊ ሊፈቀድ ይገባል፡፡
1.4. ለመስክ ስራ የታዘዘ ሠራተኛ ወደ መስክ ስራው ከተንቀሳቀሱበት ቀን ጀምሮ የተወሰነውን የውሎ አበል ያገኛል፡፡
1.5. ለሠራተኞች የሚከፈለው የውሎ አበል በመመሪያው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

2. የነዳጅ ወይም የትራንስፖርት አበል (Fuel or Transportation Allowance)፡-

2.1. የነዳጅ ወይም የትራንስፖርት አበል ለሁሉም የባንኩ ሠራተኞች እንደየሥራ መደባቸው ወይም ደረጃቸው ሆኖ
በወቅታዊው የሐገሪቱ የነዳጅ ዋጋ ተመን መሠረት ተሰልቶ በየወሩ ከደመወዝ ጋር የሚከፈል ይሆናል፡፡

29
2.2. መልዕክተኞች በሥራ ፀባያቸው ምክንያት ለባንኩ ሥራ ሲንቀሳቀሱ የታክሲ ወጪ በባንኩ ይሸፈናል፡፡
2.3. በሥራቸው ባህሪ ምክንያት ወይም ሠራተኛው ከመደበኛው የሥራ ሰዓት ውጪ እንዲሰራ የሚያስገድድ ሁኔታ ሲፈጠር
እና በቅርብ ሀላፊ ሲታዘዝ ባንኩ የትራንስፖርት አገልግሎት ያመቻቻል፡፡
2.4. በወረርሽኝ ወይም የፀጥታ ችግር ምክንያት የሕዝብ ትራንስፖርት ሲቋረጥ እና ሠራተኛዉ ሥራ እንዲገባ ሲፈለግ ባንኩ
እና ማህበሩ በጋራ ምክክር ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ያመቻቻል፡፡

3. የበረሐ እና ወይም የኑሮ ውድነት አበል (Hardship Allowance)

3.1. ሠራተኛዉ በኑሮ ውድነት እና/ወይም አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ውስጥ በመኖሩ ምክንያት የሚደርስበትን አስቸጋሪ
ሁኔታዎች እንዲቋቋም ባንኩ ለሁሉም ሠራኞች እንደተመደቡበት የሥራ ሁኔታ የበረሐ እና ወይም የኑሮ ዉድነት አበል
ይከፍላል አፈፃፀሙም በመመሪያ ይወሰናል፡፡
3.2. በአንድ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ቅርንጫፎች ነባርም ሆኑ አዲስ የሚከፈቱ ተመሳሳይ የአበል ምጣኔ ይኖራቸዋል፤ አበል
ባልተወሰነባቸው ከተሞች አዲስ ቅርንጫፍ ሲከፈት የክፍያ ምጣኔውን ባንኩ ይወስናል፡፡
3.3. ባንኩ የሚከፍለዉ የበረሃ እና ወይም የኑሮ ዉድነት አበል በማንኛዉም ሁኔታ በመንግስት ከተቀመጠዉ ምጣኔ በታች
አይሆንም፡፡

4. የቤት ኪራይ አበል

4.1. ባንኩ የቤት ኪራይ አበል ለሁሉም ሠራተኞች እንደተመደቡበት የሥራ ደረጃ በየወሩ ከደመወዝ ጋር ይከፍላል፡፡ ነገር
ግን ባንኩ የመኖሪያ ቤት የሚሰጥ ከሆነ እና ሠራተኛው በተሰጠው ቤት ውስጥ ለመኖር ከወሰነ ለቦታው የተመደበው
የቤት ኪራይ አበል አይከፈለውም፡፡
4.2. ባንኩ ለሠራተኛው የሚከፍለው የቤት ኪራይ አበል የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያገናዘበ እንዲሆን በየጊዜው ይከልሰዋል፡፡
4.3. ባንኩ የመኖሪያ ቤት በሚሰጥበት የሥራ ቦታ ለተዛወረ ሠራተኛ የርክክቡ ጊዜ አልቆ በተመደበለት የመኖሪያ ቤት
እስከሚገባ ድረስ ላለው ጊዜ ሠራተኛው ቀደም ሲል ይከፈለው በነበረው የቤት ኪራይ አበል መጠን ልክ ተሰልቶ
ይከፈለዋል፡፡ ከ 15 ቀናት በኋላ ባንኩ ከቁጥጥሩ ውጪ በሆነ ምክንያት ቤቱን ለሠራተኛው ማስረከብ ሳይችል ቢቀር
ሠራተኛው ባለው የሥራ ደረጃ የተመደበውን የቤት ኪራይ አበል ይከፍለዋል፡፡

5. ባንኩ ለሠራተኞቹ የሚሰጣቸው የነዳጅ እና ወይም ትራንስፖርት፣ የበረሐ እና/ወይም የኑሮ ውድነት እና የቤት
ኪራይ አበሎች የሠራተኛው የደመወዝ ክፍያ እስካልተቋረጠ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል፡፡

6. በአንድ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ቅርንጫፎች ነባርም ሆኑ አዲስ የሚከፈቱ ተመሳሳይ የአበል ምጣኔ ይኖራቸዋል ፤
ከተጠቀሰው ውጪ በተለየ ሁኔታ አዲስ ቅርንጫፍ ሲከፈት የክፍያ ምጣኔዉን ባንኩ ይወስናል::(3.2 ጋር
ተመሳሳይ ነዉ)በመሆኑም ይሄ በ 3.2 የተካል፡፡

7. የመነቃነቂያ አበል

30
7.1. የመነቃነቂያ አበል የሚከፈለው ሠራተኛው በማንኛውም ምክንያት ከተቀጠረበት ቦታም ይሁን ወደ
ተቀጠረበት ቦታ አንድ የባንኩ ቅርንጫፍ ከሚገኝበት ከተማ ወደ ሌላ የባንኩ ቅርንጫፍ ወደሚገኝበት ከተማ
ሲዘዋወር ብር 5,000.00/አምስት ሺህ/ ይከፈለዋል፡፡
7.2. በአንድ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች መካከል የሚደረግ ዝውውር የመነቃነቂያ አበል
አያስከፍልም፡፡

8. የመጓጓዣ ወጪ (Transportation Expense)

8.1. በዝውውር ጊዜ ባንኩ በራሱ መኪና ሠራተኛውን፣ ቤተሰቡን እና የቤት ቁሳቁሱን ሠራተኛዉ ወደ ተዛወረበት
ቦታ ያደርሳል፤ ወይም የመጓጓዣ ወጪን ይሸፍናል፡፡
8.2. የተዛወረ ሠራተኛ በአውቶብስ ፣ በባቡር እና በመኪና መጓጓዝ አለበት ፡፡ በየብስ መጓጓዝ የማይችልበት
ሁኔታ ሲፈጠር ወይም ከአምስት መቶ ሃምሳ (550) ከ.ሜ በላይ የሚጓዝ ከሆነ ሠራተኛው በአየር እንዲጓዝ
ይደረጋል ፤ ለራሱ እና ለቤተሰቡ ከሃምሳ (50) ኪ.ግ ለማይበልጥ ዕቃ የአየር መጓጓዣ ወጪን ባንኩ
የሚሸፍን ሆኖ ቀሪውን ቁሳቁስ ደግሞ ሠራተኛው ጉዞ ከመጀመሩ በፊት እንዲጫን ይደረጋል ፤ ይህ
ካልተቻለ ግን አንድ ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሠራተኛው ወደተዛወረበት ቦታ ባንኩ ያደርስለታል፡፡
8.3. የዕቃው ወይም የባንኩ ሠራተኛ እና ቤተሰቦቹ ጉዞ በኪራይ መኪና የሚደረግ ከሆነ የኪራዩን ዋጋ የሚዋዋለው
የባንኩ ተወካይ ይሆናል ፤ ሆኖም ይህ እንዲደረግለት ሠራተኛዉ የቅርብ ኃላፊዉን በፅሑፍ አሳዉቆ እስከ
አምስት ተከታታይ ቀናት የማይመቻችለት ከሆነ ሠራተኛዉ ሁለት ምስክሮችን ይዞ በራሱ በመዋዋል መኪና
ሊከራይ ይችላል ፤ ባንኩም ወጪውን ይሸፍናል፡፡
8.4. በዝውውር ጊዜ በራሳቸው መኪና ለሚጓጓዙ ሠራተኞች ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን የነዳጅ ወጪ ብቻ ባንኩ
ይሸፍናል፡፡
8.5. በዝውውር ጊዜ የመነቃነቂያ አበሉንም ሆነ የመጓጓዣ መኪና የሚያመቻቸዉ ወይም የመጓጓዣ ወጪን
የሚሸፍነው የተዛወረዉ ሠራተኛ እስከሚዛወር ድረስ ሲሰራበት የነበረው ክፍል(ቅርንጫፍ) ይሆናል፡፡

9. የሾፌሮች ልዩ አበል (Drivers Allowance)


ሾፌሮች በመኪና ላይ አደጋ እንዳያደርሱ የማበረታቻ ልዩ አበል በየወሩ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ ክፍያ እና
በአመት ውስጥ ምንም አይነት ጉዳት ባያደርስ ሽልማትና የምስክር ወረቀት በሚሰሩበት ክፍል በኩል
ይሰጠዋል፡፡ ሆኖም በወሩ ውስጥ በሚያሽከረክሩት መኪና ላይ ጉዳት ቢደርስ በሌላ ሰው ጥፋት መሆኑን
ካላረጋገጡ በስተቀር ለዚያ ወር ብቻ አበል አይከፈላቸውም፡፡

10. የሞተረኞች ልዩ አበል (Motorist Allowance)

31
ሞተረኞች በሚያሽከረክሩት ሞተር ላይ አደጋ እንዳያደርሱ የማበረታቻ ልዩ አበል በየወሩ ብር 300.00 (ሶስት
መቶ) ይከፈላቸዋል። ሆኖም በወሩ ውስጥ አንድ ሞተረኛ በሚያሽከረክረው ሞተር ላይ ጉዳት ቢደርስ በሌላ ሰው
ጥፋት መሆኑን ካላረጋገጠ በስተቀር ለዚያ ወር ብቻ አበሉ አይከፈለውም።

11. በደንበኞች አገልግሎት ማዕከል (Contact Center) ውስጥ በስልክ ጥሪ አገልግሎት ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች
የሚከፈል አበል (Hearing Allowance)፡-

በስልክ ለደንበኞች የተለያዩ መረጃዎችን በመስጠት የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ውስጥ በስልክ ጥሪ ላይ
ለሚሰሩና የዕለት ተዕለት ግዴታቸውን እየተወጡ ላሉ ሠራተኞች ባንኩ የደንበኞች የስልክ ጥሪ አገልግሎት ክፍያ
(Hearing Allowance) 800.00 (ስምንት መቶ ብር) ይከፍላል፡፡

አንቀጽ - 27 (ሃያ ሰባት)

ብድርና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች

1. ለድንገተኛ ጉዳይ (Revolving Salary Advance)

1.1. ባንኩ ለድንገተኛ ጉዳይ (Revolving Salary Advance) የሚውል ከ 2 እስከ 6 ወራት ደመወዝ የማይበልጥ ከ 12
ወራት እስከ 36 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚያልቅ ከወለድ ነፃ የሆነ ቅድመ ደሞዝ ያለ ምንም ዋስትና
ለሠራተኛ ይሰጣል፡፡
1.2. አንድ ሰራተኛ የወሰደዉን የደመወዝ ቅድመ ክፍያ ከፍሎ ሳይጨርስ ከባንኩ የሚለቅ ከሆነ ቀሪ ሂሳቡን ወዲያውኑ
መክፈል ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ሠራተኛው ቀሪ ሂሳቡን መክፈል የማይችል ከሆነ ከሥራ መልቀቅ ጋር በተያያዘ
ከሚከፈሉት ጥቅማጥቅሞቹ ላይ እንዲሸፈን ይደረጋል፡፡ ይህም የማይበቃ ሲሆን ቀሪው ሂሳብ ወደ ብድር ተለውጦ
በባንኩ የብድር መመሪያ መሰረት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡
1.3. አንድ ሰራተኛ የወሰደዉን የደመወዝ ቅድመ ክፍያ ከፍሎ ሳይጨርስ ህይወቱ ቢያልፍ ቀሪ ሂሳቡ በባንኩ የሚሰረዝለት
ይሆናል፡፡
1.4. የደመወዝ ቅድመ ክፍያ ዝርዝር አፈፃፀም ባንኩ በሚያወጣዉ መመሪያ ይወሰናል፡፡

2. የመኖሪያ ቤት መግዣ ብድር (Staff Mortgage Loan)

2.1. ባንኩ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን እና የሠራተኛውን የመበደር አቅም ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ለመኖሪያ ቤት ግዢ፣
ለአዲስ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለተጨማሪ የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና ለመኖሪያ ቤት እድሳት ለሠራተኛዉ ብድር
ይሰጣል፡፡
2.2. የብድሩ መጠንና አከፋፈል ባንኩ በሚያወጣዉ መመሪያ መሰረት የሚወሰን ሆኖ የወለድ ምጣኔዉ ብሔራዊ ባንክ
በሚያወጣው ዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ ምጣኔ ይሆናል፡፡

32
2.3. አንድ ሠራተኛ በባንኩ ውስጥ ቆይታዉ የዚህ የመኖሪያ ቤት ብድር ተጠቃሚ የሚሆነው ቢያንስ ለሁለት ጊዜ ያህል
ይሆናል፡ እንዲሁም የደመወዝ ጭማሪ ሲኖር ለአንድ ብድር ሁለት ጊዜ የመኖሪያ ቤት ተጨማሪ ብድር
(Increamental staff mortgage Loan) ብድር ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

3. የመኪና መግዣ ብድር (Staff Automobile Loan)

ሠራተኛዉ የሥራ ሰዓቱን እንዲያከብር፣ በሥራዉ ላይ ውጤታማ እንዲሆን እና ኑሮዉን ቀላል ለማድረግ እንዲችል
የሠራተኛዉ የመበደር አቅም እስከ ቻለ ድረስ ባንኩ የመኪና መግዣ ብድር ለሠራተኛዉ ይሰጣል፤ ለአካል ጉዳተኛ
ሠራተኞችም የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመሪያ ቁጥር 41/2007 ዓላማን መሰረት በማድረግ የመኪና መግዣ
ብድር ይመቻችላቸዋል፤ አፈፃፀሙ በመመሪያ ይወሰናል፡፡

4. የግል ጉዳይ ብድር (Personal Loan)

ሠራተኛዉ የቤት እቃ የሚያሟላበት፣ የቤተሰቡን የኑሮ ጫና ማቅለያ እና ለሌሎች የግል ጉዳዮቹ የሚጠቀምበት ባንኩ
የግል ጉዳይ ብድር (personal loan) ለሠራተኛዉ ይሰጣል፤ አፈፃፀሙ በመመሪያ ይወሰናል፡፡

5. ሠራተኛዉ በባንኩ ቅርንጫፎች ወይም የስራ ክፍሎች ለመገልገል ሲመጣ ማንኛዉንም አገልግሎት ያለወረፋ
ቅድሚያ ያገኛል፡፡

6. ከላይ በተራ ቁጥር 1፣ 2፣ 3 እና 4 የተመለከቱትን የሚጠይቅ ሠራተኛ በባንኩ ውስጥ ቢያንስ አንድ ዓመት
አገልግሎት ያጠናቀቀ መሆን ይኖርበታል፡፡

7. ሠራተኛዉ ከደመወዝ መክፈያ ሂሳቡ ጋር የተጣመሩ የኤቲኤም (ATM) አገልግሎቶችን ያለ ምንም ክፍያ
ያገኛል፡፡

8. ሠራተኛዉን ለማሰባሰብ እና ለማዝናናት በየዓመቱ መጨረሻ አንድ ቀን የባንኩ ሠራተኞች ቀን ይከበራል፡፡

አንቀጽ - ሃያ ስምንት

ሕክምና፣ በሕመም ጊዜ የሚሰጡ ፈቃዶች እና ድጋፎች

1. ማንኛውም ሠራተኛ በሚታመምበት ጊዜ ባንኩ ሙሉ የህክምና አገልግሎት በነፃ ይሰጣል፡፡ ባንኩ የሕክምና
አገልግሎት የሚሰጠዉ በራሱ ክሊኒክ ሆኖ የባንኩ ክሊኒክ በሌለባቸው ከተሞች ወይም የባንኩ ሐኪም ከአቅሙ
በላይ በሆነበት እና ልዩ ምርመራ የሚያስፈልገው ሲሆን ሌሎች የተሻሉ የግልም ሆኑ የመንግስት ሕክምና ተቋማት
ጋር የቀጥታ ሕክምና ውል በመግባት ሕክምና እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ ሕክምናውም የጤንነት ምርመራ ፣

33
የመድኃኒት መግዣ ፣ የቀዶ ሕክምና ፣ የሆስፒታል አልጋና ምግብ ፣ የተለያዩ የአካል ድጋፍ መሳሪያዎች እና
ሌሎች የሕክምና ዓይነቶችን ይጨምራል፡፡

2. ሰራተኛዉ የታመመዉ ድንገተኛና አስቸኳይ እርዳታ የሚጠይቅ ወይም የባንኩ ክሊኒክ በማይሰራባቸው ቀናት
እና ሰዓታት ከሆነ እና ይህም ሲረጋገጥ በሌላ የሕክምና ተቋም ታክሞ ባንኩ ያወራርድለታል፡፡

3. ባንኩ ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ፣ ኮቪድ-19 እና ሌሎች ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በስራ ቦታ እንዳይስፋፉ
የመከላከል እና የመቆጣጠር ሥራዎችን ፕሮግራም በማዉጣት ወይም በወጣዉ ፕሮግራም መሰረት ከማሕበሩ ጋር
ይሰራል አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍም ያደርጋል፡፡

4. ባንኩ ከኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ጋር በሚኖሩ ሰራተኞች ላይ መገለልና መድሎ እንዳይደርስባቸው ክትትል ያደርጋል
፤ ምንም ዓይነት ለሌሎች ሠራተኞች የሚሰጠዉን ጥቅም አያጓድልባቸዉም፤ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችንም
አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

5. ባንኩ ለካንሰር ሕመምተኛ ሠራተኞች ከኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ሕመምተኛ ሠራተኞች በጀት ላይ ድጋፍ
ያደርግላቸዋል፡፡

6. አንድ ሠራተኛ ወይም ከባንኩ በጡረታ የተሰናበተ እና የባንኩ የህክምና ተጠቃሚ የሆነ ጡረተኛ በደረሰበት በሽታ
ወይንም አደጋ ጤንነቱን እስኪያገኝ ድረሰ ባንኩ በአገር ውስጥ ያሳክመዋል፡፡ ሆኖም በአገር ውስጥ ታክሞ
ለመዳን የማይችል ከሆነና ውጭ ሀገር ሄዶ ቢታከም ተስፋ ያለው መሆኑ በሐኪሞች ቦርድ (Medical Board)
ከተረጋገጠ እስከ 20,000 (ሀያ ሺህ) የአሜሪካን ዶላርና እና ባለው የቀጥታ መሥመር የአንድ ጊዜ ደርሶ መልስ
የታካሚውን እና አብሮት እንዲጓዝ በጤና ጥበቃ የተፈቀደለት የአንድ አስታማሚ የአየር ትራንስፖርት ወጪ
ይሸፍናል፡፡ ሆኖም ታማሚዉ እንዲመለስ ቀጠሮ ተሰጥቶት ከሆነ እና ለባንኩ ተመላሽ ያደረገው ገንዘብ ካለ
በድጋሚ እንዲጠቀመው ይደረጋል፡፡ ሠራተኛው ወይም ጡረተኛው ሕክምናውን እንዳአጠናቀቀ የሕክምና
ወጪውን፣ የመኝታ፣ የምግብ፣ የትራንስፖርት ሰርቪስ እና የመድሀኒት ሂሳቡን ካላወራረደ የተሠጠውን የውጭ
ምንዛሪ እንዲከፍል ይደረጋል። ጡረተኛ ከሆነ ሕክምና እንዳጠናቀቀ የሕክምና ወጪውን ካላወራረደ በቀጣይ
ከባንኩ ምንም ዓይነት የሕክምና አገልግሎት አያገኝም፡፡

7. ባንኩ የጆሮ ህመም ወይም የመስማት ችግር ላለበት ሰራተኛ በሐኪም ትዕዛዝ የጆሮ ማዳመጫ (Hearing Aid)
ይገዛለታል፡፡

8. ባንኩ ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች የዊል ቼር ወይም ክራንች ወይም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ የሰዉነት ድጋፍ
መሣሪያዎችን ወጪ ይሸፍናል፡፡

34
9. የዓይን መነጽር በሐኪም ለሚታዘዝላቸው ሠራተኞች ባንኩ የፍሬምን 85% (ሰማኒያ አምስት በመቶ) እና የሌንስን
100% (መቶ በመቶ) ይሸፍናል፤ እንዲሁም መነጽሩ እንዲቀየር በሐኪም ሲታዘዝ ፍሬምን በሦስት ዓመት ጊዜ
ሌንሱ በማንኛዉም ጊዜ በዚህ ምጣኔ ወጪዉን ይሸፍናል፡፡ መነፅሩ ቢሰበር ወይም ቢጠፋ ወጪውን ባንኩ
አይሸፍንም፡፡

10. ባንኩ ጥርስ ማስተካከልን ሳይጨምር የጥርስ ሕክምና ወጪን ጥርስ መተካትን ጨምሮ ይሸፍናል። ሆኖም ጥርስ
መተካትን በተመለከተ ለሴራሚክ እና ከዚያ በላይ ዋጋ ለሚያስወጡ መተኪያዎች ወጪ አይሸፍንም። አንድ
ጥርስ ከተተካ ከአምስት ዓመት በኋላ በተለያየ ምክንያት ሀኪም እንዲቀየር ካዘዘ ሙሉ ወጨውን ባንኩ
ይሸፍናል።

11. ሠራተኛው ሲታመም የህክምና ፈቃድ አሰጣጥና በህመም ላይ ላለ ሠራተኛ የሚከፈለው የደመወዝ መጠን
እንደሚከተለው ሆኖ፤ በአዲስ አበባና ዙርያው የሚገኙ ሠራተኞች የሚሰጣቸው የህክምና ፈቃድ ማስረጃ በባንኩ
ሀኪም መረጋገጥ እና የተሰጠው የሀኪም ፈቃድም በባንኩ ክሊኒክ በኦራክል ሲስተም ላይ ሲመዘገብ እንዲሁም
ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ሰራተኞች በቅርብ የሥራ ኃላፊያቸው አማካኝነት በኦራክል ሲስተም ላይ ይመዘገባል፡፡

12. ሠራተኛው ህመሙ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ወይም በተለያዩ ጊዜያት
የሚወሰድ እስከ 300 (ሦስት መቶ) ቀናት የሕመም ፈቃድ ያገኛል፡፡ ሆኖም ህመሙ በኤች.አይ.ቪ. (ኤድስ)
ወይም ኤም.ዲ.አር (መድሀኒት የተላመደ የሳንባ ህመም) ወይም ካንሰር ምክንያት ከሆነ 1 (አንድ ዓመት)
ይሆናል። የተጠቀሰውም የህመም ፈቃድ ቀጥሎ በተመለከተው ሁኔታ ይሰጣል፡፡
12.1. ለመጀመሪያው 6 (ስድስት) ወራት ሙሉ ደመወዝ፥
12.2. ለቀጣይ 2 (ሁለት) ወራት ግማሽ (50%) ደመወዝ፥
13. ለቀሪው ወራት አንድ ሦስተኛ (1/3) ደመወዝ የሚከፈልበት የህመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት
የረጅም ጊዜ የህክምና ፈቃድ የሚሰጠው ወይም የሚፀድቀው በባንኩ ሐኪም ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
14. ከዚህ በላይ በአንቀፅ 12 በተጠቀሰው አኳኋን በህክምና ሲረዳ ቆይቶ የሕክምና ፍቃዱን ያጠናቀቀ ሠራተኛ የሥራ
ውሉ ይቋረጣል፡፡ በሕመም ፈቃድ ላይ ያለ ሠራተኛ የዓመት ፈቃድ ሊጠቀም አይችልም፡፡ ሆኖም ግን
ሰራተኛው ከስራ ከተሰናበተ በኋላ ከህመሙ በመዳኑ ወደ ስራ ለመመለስ ጥያቄ ቢያቀርብና በሃኪም የተረጋገጠ
ማስረጃ ማቅረብ ከቻለ ባንኩ ወደ ስራው ሊመልሰው ይችላል፡፡
15. ድንገተኛ እና አስቸኳይ ሕመም ካልሆነ በስተቀር ሰራተኛው በቅድሚያ ለቅርብ ሃላፊው ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
16. ሠራተኛው በሥራ ላይ እያለ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ የተጠቀሰው የአካል ጉዳት
ቢደርስበት እና ቢታመም ሠራተኛው ድኖ ወደ ሥራ እስኪመለስ ወይም እስከ 12 ወራት ድረስ ባንኩ ሙሉ
ደመወዝ ይከፍለዋል፡፡ ሆኖም በደረሰበት እክል ምክንያት ከ 12 ወር በኋላም ወደ ሥራ ሊመለስ አለመቻሉ
በሃኪም ሲረጋገጥ በአዋጁ እና በዚህ ህብረት ስምምነት መሰረት ይፈጸማል፡፡

35
17. በቂ የህክምና አገልግሎት ከማይሰጥበት አስተዳደር ክልል ከፍተኛ ህክምና ወደሚሰጥበት የአስተዳደር ክልል
መሄድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና በአቅራቢያው ከሚገኘው ሆስፒታል ወይም ጤና ጣቢያ የሃኪም ትዕዛዝ ሲሰጥ ባንኩ
ለሠራተኛው የህመም ፍቃድ ይሰጣል፡፡ የትራንስፖርት ወጪውም በባንኩ ይሸፈናል፡፡ ሆኖም ወደ አዲስ አበባ
የተላከ ሠራተኛ ቀደም ሲል የተሰጠውን የሐኪም ትዕዛዝ በቅድሚያ ከባንኩ ክሊኒክ ማረጋገጫ ማግኘት
ይኖርበታል፡፡
18. የባንኩ ክሊኒኮች ባሉበት አካባቢ ያለ ማንኛዉም ታማሚ የታዘዘለትን መድሃኒት የሚወስደው ከባንኩ ክሊኒክ
ፋርማሲ ሆኖ የባንኩ ክሊኒክ ፋርማሲ መድሃኒቱ ከሌለዉ እና ይህንንም ሲያረጋግጥ ከሌሎች ባንኩ ጋር ውል
ካላቸዉ ፋርማሲዎች ይሆናል ፤ ነገር ግን መዲሃኒቱ እነሱ ጋር የማይገኝ ከሆነ ከሌሎች ሃገር ውስጥ ካሉ መድሃኒት
ቤቶች ሲገዛ ይወራረድለታል፡፡
19. የባንኩ ክሊኒኮች በሌሉበት አካባቢ ያለ ማንኛዉም ታማሚ የታዘዘለትን መዲሃኒት የሚገዛዉ ከታከመበት ሕክምና
ተቋማት ሆኖ የታከመበት ተቋም መዲሃኒቱ ከሌለዉ እና ይህንንም ሲያረጋግጥ ከሌሎች ከባንኩ ጋር ውል ካላቸዉ
ፋርማሲዎች ይሆናል ፤ ነገር ግን መዲሃኒቱ እነሱ ጋርም የማይገኝ ከሆነ ከሌሎች ሃገር ውስጥ ካሉ መድሃኒት
ቤቶች ሲገዛ ይወራረድለታል፡፡
20. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 18 እና 19 ላይ የተጠቀሰዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ሕክምናዉ ድንገተኛ እና አስቸኳይ
ከሆነ እና ይህም በሐኪም ሲረጋገጥ ታማሚዉ መድሃኒቱን ከሌሎች ፋርማሲዎች ሲገዛ ይወራረድለታል፡፡
21. አንድ ሰራተኛ ከስራ ታግዶ ባለበት ወቅት ቢታመምና ለህክምና ያወጣዉ ወጪ ካለ ሰራተኛዉ ወደ ሰራው
ሲመለስ በዕገዳዉ ጊዜ ያወጣዉ ወጪ በባንኩ ሃኪም ተረጋግጦ ይሸፈናል፡፡
22. የቤተሰብ ሕክምና
ባንኩ ለሠራተኛው ሚስት ወይም ባል እና ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ የሠራተኛው ልጆች የሕክምና አገልግሎት
ይሰጣል፤ ዝርዝር አፈፃፀሙም ተጠንቶ ባንኩ እና ማህበሩ በጋራ በሚያወጡት መመሪያ ይወሰናል፡፡

አንቀጽ - ሃያ ዘጠኝ

ኢንሹራንስ

1. ባንኩ ሃያ አራት /24/ ሰዓት የሚሸፍን የአደጋ ኢንሹራንስ ለሠራተኛው ይገባል፡፡

2. ሠራተኛው በደረሰበት አደጋ ምክንያት ቢሞት ወይም ከፊል ወይም ሙሉ ወይም ዘላቂ የአካል ጉዳት ቢደርስበት
የሚከፈለው ካሳ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በተደነገገው መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡

3. አንድ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ ስለደረሰበት አደጋ ለሚሰራበት ክፍል ሀላፊ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ
ማሳወቅ አለበት፡፡ ሠራተኛው የሚሰራበት ክፍል ሀላፊ አደጋ የደረሰበትን ሠራተኛ ሁኔታ መረጃውን በተቀበለ
በ 24 ሰዓት ውስጥ ለፋይናንስ ክፍል ማሳወቅ አለበት ፤ የባንኩ ፋይናንስ ክፍል በወቅቱ ለሚመለከተው ክፍል
በማሳወቅ የሚከፈለውን የኢንሹራንስ ካሣ አደጋ ለደረሰበት ሠራተኛ ወይም ለሕጋዊ ወራሾች ይሰጣል፡፡
36
አንቀጽ - ሠላሳ

መዝናኛ እና ስፖርት

1. ሠራተኞች በሚሰሩበት አካባቢ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራቱ የተጠበቀ የምግብና የመጠጥ አገልግሎት እንዲያገኙ
እንደአመቺነቱ ባንኩ የሠራተኞች ክበባት እንዲቋቋሙ ያደርጋል ፤ አስፈላጊዉን በጀትም በማህበሩ በኩል
ይደጉማል፡፡

2. ማህበሩ የተሰጠዉን የድጎማ በጀት በወቅቱ ለክበባቱ ያከፋፍላል፤ ከባንኩ እና ከማህበሩ የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ
አጠቃላይ የክበባቱን አሰራር እና የበጀት አጠቃቀም ይከታተለዋል ይመራዋል፡፡

3. ሠራተኞች ጤነኛ እና ደስተኛ እንዲሆኑ፣ አንድ ላይ በመሰባሰብ ማህበራዊ አብሮነታቸዉን እንዲያጎለብቱ


እንዲሁም በሥራቸዉ ላይ ቀልጣፋ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ባንኩ በየደረጃዉ የተለያዩ ውጫያዊና ውስጣዊ
ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ውድድሮች እንዲኖሩ በጀት ይመድባል ፤ ከባንኩ እና ከማህበሩ የተውጣጣ የጋራ
ኮሚቴ አጠቃላይ የስፖርቱን እንቅስቃሴ እና የበጀት አጠቃቀም ይከታተለዋል ይመራዋል፡፡

ምዕራፍ - አምስት
አንቀፅ - ሰላሳ አንድ
የሥራ ሰዓት
የሥራ ሰዓት እና ፈቃድ
1. የባንኩ የሥራ ሰዓት እንደሥራው ዓይነት ፣ እንደአካባቢው የአየር ፀባይ እና የገበያ ሁኔታ የሚለያይ መሆኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ ባንኩ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የሳምንት የሥራ ሰዓት ሳያስበልጥ በፈረቃ ሊያሰራ
ይችላል፡፡

2. በባንኩ የስልክ የጥሪ ማዕከል ውስጥ ለሚሰሩ ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን 6፡00 ሰዓት ወይም በሳምንት 36፡00
ሰዓት ሆኖ ባንኩ በፈረቃ ሊያሰራ ይችላል፡፡

3. በቅርንጫፍ እና ከገንዘብ ጋር ንክኪ ባላቸዉ ቦታዎች ለሚሰሩ ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን 7፡30 ወይም
በሳምንት 41፡30 ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
3.1. ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 – 6፡00 ወይም ከ 3፡30 - 7፡00 ሰዓት
3.2. ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከቀትር በኋላ ከ 7፡00 – 10፡30 ወይም ከ 8፡00 - 12፡00 ሰዓት
37
3.3. በተ.ቁ 3.1 እና 3.2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ሰራተኛ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ካሉት ቀናት ውስጥ
አንዱን ቀን 4፡00 ሰዓት ብቻ ይሰራል።
3.4. እንደ ዋና ገንዘብ ያዥ ያሉ እና ሌሎች በስራ ባህሪያቸው ምክንያት በሳምንቱ የስራ ቀናት ውስጥ ማረፍ
የማይችሉ ሰራተኞች በትርፍ ሰዓት አግባብ ማሰራት ይቻላል።
3.5. ከላይ የተጠቀሰው የስራ ሰዓት የሂሳብ መዝጊያን ይጨምራል።
4. በዋናው መ/ቤት፣ ሪጅንና ዲስትሪክት ፅ/ቤቶች የሚሰሩ ሰራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን 7፡00 ወይም በሳምንት
41፡30 ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
4.1. ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00 – 6፡00 ሰዓት
4.2. ከሰኞ እስከ አርብ ከቀትር በኋላ ከ 7፡00 – 10፡30 ሰዓት

5. በጥበቃ ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን 8፡00 በሳምንት 48፡00 ሰዓት ሆኖ ባንኩ በሚያወጣው
የፈረቃ ፕሮግራም መሰረት ይፈፀማል፡፡

6. የጽዳት ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን 7፡00 በሳምንት 39፡00 ሰዓት ሆኖ ባንኩ በሚያወጣው የፈረቃ ፕሮግራም
መሰረት ይፈፀማል፡፡

7. የሾፌሮች የሥራ ሰዓት በቀን 8፡00 ሰዓት በሳምንት 48፡00 ሰዓት ሆኖ ባንኩ በሚያወጣው የፈረቃ ፕሮግራም
መሰረት ይፈፀማል፡፡

8. ማንኛውም ሠራተኛ በሣምንት ቢያንስ 24፡00 ሰዓት በመደዳው ማረፍ ይኖርበታል።

9. በዚህ ሕብረት ስምምነት በተጠቀሰው የሥራ ሰዓት መካከል ጠዋትም ሆነ ከቀትር በኋላ 15 ደቂቃ የሻይ ዕረፍት
ለሠራተኞች ይፈቀዳል፡፡

10. ባንኩ ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ለሚያሰራቸው ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት
ያቀርባል፡፡

አንቀፅ - ሠላሳ ሁለት


የትርፍ ሠዓት ሥራ

1. የትርፍ ሰዓት ሥራ ማለት ሠራተኛው በዚህ ሕብረት ስምምነት አንቀፅ 31 መሰረት ከተወሰነው መደበኛ
የሥራ ሰዓት በላይ የሰራበት ሰዓት ማለት ነው፡፡

38
2. በትርፍ ሰዓት የሚሰራው ሥራ አስፈላጊነት ተገምግሞ አግባብ ያለው የክፍል ሃላፊ ወይም ሥራ
አስኪያጅ ሲፈቅድና በጽሁፍ ወይም በኦራክል ሲስተም ትዕዛዝ ሲሰጥ ብቻ ይሆናል፡፡

3. እንደ ትርፍ ሰዓት የሚቆጠረው እጅግ ቢያንስ 15 ደቂቃ ሲሆን ነው ፤ ሆኖም በማንኛውም ቀን
የሚሠራው የትርፍ ሰዓት ሥራ በቀን ከ 4፡00 በሳምንት ከ 12፡00 ሰዓት መብለጥ የለበትም፡፡

4. ከንጋቱ 12፡00 እስከ ምሽቱ 4፡00 ሠዓት ለሚሠራ የትርፍ ሠዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት
የሚከፈለው ደመወዝ በ 1.50 ተባዝቶ ይሆናል።

5. ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ሠዓት ለሚሠራ የትርፍ ሠዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት
የሚከፈለው ደመወዝ በ 1.75 ተባዝቶ ይሆናል።

6. በማንኛወም ቀን ቢውልም በሣምንት የዕረፍት ቀን እና በህዝብ በዓላት ቀን የሚሠራ የትርፍ ሠዓት ሥራ


ለመደበኛ ሥራው በሠዓት የሚከፈለው ደመወዝ 2.50 ተባዝቶ ይሆናል።

7. የትርፍ ሰዓት ክፍያ የሚታሰበው በሠራተኛው ጠቅላላ ቋሚ ደመወዝ (Basic salary) ላይ ሲሆን
አበሎችን አይጨምርም፡፡

8. በሥራ ባህሪያቸው አስገዳጅነት በሕዝብ በዓል ቀን የሚሰሩ ሠራተኞች ከሰሩ በሰዓት የሚያገኙት ክፍያ
በበዓል ቀን ለሠራበት ለዕያንዳንዱ ሰዓት የሚያገኘው ክፍያ በሰዓት የሚያገኘው ደመወዝ በ 2.50
ተባዝቶ በሠራው ሰዓት ልክ ይሆናል።

9. ማንኛውም ሠራተኛ በአንድ ጊዜ የውሎ አበል (Perdiem Allowance) እየተሰጠው የትርፍ ሰዓት
(Over Time) ክፍያ እንዲያገኝ አይደረግም፡፡

አንቀፅ - ሰላሳ ሦስት


ፈቃድ
የዓመት ፈቃድ ማለት ሠራተኛው ሥራ ላይ በመቆየቱ ምክንያት የሚፈጠረዉን የአካል እና የአዕምሮ ዝለት ለማቅለል እና
ሠራተኛው አርፎ ወደ ሥራዉ ሲመለስ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ከሥራ ቀናት ውስጥ ከደመወዝ ጋር ለሠራተኛዉ
የሚሰጥ የዓመት ዕረፍት ነዉ፡፡

ከደመወዝ ጋር የሚሰጥ ፈቃድ (Leave with pay)

39
1. ለአንድ ሠራተኛ የሚሰጠዉ የዓመት ፍቃድ መጠን በአገልግሎት ዘመኑ ይወሰናል፡፡ ይህም ማለት አንድ አመት
የአገልግሎት ዘመን ያለዉ ሠራተኛ 20 (ሃያ) የሥራ ቀናት የዓመት ፍቃድ የሚያገኝ ሲሆን ለእያንዳንዱ ተጨማሪ
ዓመት አንዳንድ ተጨማሪ ቀን እየታከለበት የዓመት ፍቃድ ይሰጠዋል።
2. አዲስ የተቀጠረ ሠራተኛ ለአመት ፍቃድ ብቁ ለመሆን በባንኩ ውስጥ ቢያንስ ያለማቋረጥ 12 (አሥራ ሁለት) ወራት
መሥራት አለበት፡፡ ሆኖም አስቸኳይ ግለሰባዊ ወይም ማህራበዊ ጉዳዮች ከገጠሙት እስከሰራበት ቀን ድረስ
የሚገባዉን ፈቃድ ያገኛል፡፡
3. የዓመት ፈቃድ ለሠራተኛው የሚሰጠዉ የቅርብ ኃላፊው ከሰራተኞው ጋር በመመካከር በሚያዘጋጀዉ የዓመት ፈቃድ
አሰጣጥ ዕቅድ ሰንጠረዥ መሠረት ይሆናል፡፡
4. ከላይ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2 የተጠቀሰዉ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለያዩ ግለሰባዊ ወይም ማህበራዊ ጉዳዮች
ምክንያት ሠራተኛዉ የዓመት ፈቃዱን ከዕቅድ ውጪ ሲጠይቅ እና የቅርብ ሀላፊው ሲያምንበት ይሰጠዋል፡፡
5. አንድ ሠራተኛ የአመት ፍቃድ ሳይሰጠው ከአንድ አመት በላይ እንዲሰራ አይደረግም፤ ሆኖም በሁኔታዎች
አስገዳጅነት የተነሳ ወደሚቀጥለዉ ዓመት እንዲተላለፍ የተደረገ የአመት ፍቃድ በማናቸውም ምክንያት ከሁለት
አመታት በላይ ሊራዘም አይችልም፡፡
6. ሠራተኛዉ የሁለት ዓመቱ ጊዜ ከማለፉ በፊት አስቀድሞ ያለውን የዓመት ፈቃድ አስልቶ በፅሑፍ ወይም በኦራክል
ሲስተም ፈቃድ መጠየቅ አለበት ፤ የቅርብ የሥራ ኃላፊውም የሁለት ዓመቱን ማለቂያ ጊዜ ታሳቢ በማድረግ
ለሠራተኛው ፈቃድ ይሰጠዋል ፤ የቅርብ የሥራ ኃላፊው ፈቃዱን ባይሰጥ ቀጥሎ ያለው የበላይ ሀላፊ ለመጨረሻ ጊዜ
ይፈቅዳል ፤ በቅርብ የሥራ ኃላፊው ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ ይወሰዳል፡፡
7. አንድ ሠራተኛ በዓመት ዕረፍት ፈቃድ ላይ እያለ ታሞ ሆስፒታል ከገባ ፣ ወይም በመንግሥት መዝገብ ከታወቀ
ሐኪም በህመም ምክንያት የሕክምና ዕረፍት ማስረጃ ከተሰጠው፣ ከጤና ጣቢያ ወይም ሐኪም በሌለበት ቦታ
ከታመመ ለአንድ ሳምንት ጊዜ ብቻ ከቆየበት አካባቢ ከሚገኝ የመንግሥት አስተዳደር አካል፣ ለመታመሙ ተገቢውን
የምሥክር ወረቀት ካቀረበ በሕመም ምክንያት ፈቃድ ተሰጥቶት ያሳለፋቸው ቀናቶች ከዓመት ፈቃዱ ላይ እንዲቀነሱ
አይደረግም፡፡
8. ሴት ሠራተኛ በዓመት ዕረፍት ፈቃድ ላይ እያለች ብትወልድ የአመት ፈቃዱ ተቋርጦ የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
የወሊድ ፈቃድዋን ካጠናቀቀች በኋላ በወሊድ ምክንያት የተቋረጠውን የዓመት ዕረፍት ፈቃዷን መቀጠል
ትችላለች፡፡
9. የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ ያልተቃጠለውና ያልተጠቀመበት እንዲሁም በባንኩ ፈቃድ የተራዘመው የዓመት
ዕረፍት ፈቃዱ በገንዘብ ታስቦ ይከፈለዋል፡፡
10. አንድ ሠራተኛ በፈቃድ ላይ እያለ ቀደም ብሎ ሊታወቅ በማይችል ምክንያት በሥራ ላይ እንዲገኝ የሚያስገድድ
ምክንያት ሲፈጠር ሠራተኛው ፈቃዱን አቋርጦ ሥራው ላይ እንዲገኝ ባንኩ ሊጠራው ይችላል፡፡ ሆኖም ከፈቃዱ
ለተመለሰ ሠራተኛ በጉዞው ያጠፋው ጊዜ ሳይቆጠር የቀረው የዓመት ፈቃድ በገንዘብ ተተምኖ ይከፈለዋል፡፡
በተጨማሪም ያወጣውን የመጓጓዣ ወጪና የውሎ አበል ባንኩ ይችላል፡፡
40
2. ለሐዘን ከደመወዝ ጋር የሚሰጥ ፈቃድ (Mourning Leave)

2.1. የሠራተኛው ባለቤት፣ ወይም የሠራተኛው ወይም የባለቤቱ አባት ፣ እናት፣ ወንድም ፣ እህት ፣ ልጅ ፣
የጉዲፈቻ ልጅ ፤ ሠራተኛው በሀላፊነት የሚያስተዳድረው ሰው የሞተ(ች) እንደሆነ፣ ወይም ከሠራተኛው
ቤት አስከሬን የወጣ እንደሆነ ለሠራተኛው ሰባት (7) የሥራ ቀናት የሀዘን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
2.2. የሠራተኛው ወይም የባለቤቱ አያት፣ የልጅ ልጅ ፣ እንጀራ አባት ወይም እንጀራ እናት የሞተ(የሞተች)
እንደሆነ ለሠራተኛው 5 (አምስት) የሥራ ቀናት የሃዘን ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
2.3. ከላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ሀዘኑ የደረሰው ሠራተኛው ከሚሰራበት ከተማ ውጪ ከሆነ ወደ ሃዘኑ
ቦታ ለመድረስና ለመመለስ የሚያስችል ከአመት ፍቃዱ ላይ የሚቀነስ ተጨማሪ ፈቃድ እንደአስፈላጊነቱ
ይሰጠዋል፤ ሆኖም ሠራተኛው የተጠራቀመ የአመት ፍቃድ ከሌለው ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ
ይሰጠዋል፡፡
2.4. አንድ የባንኩ ሠራተኛ ሲሞት ባንኩ የሃዘን መግለጫ ያወጣል፤ በቀብር ስነ ስርአቱ ላይ በተወካዮቹ
አማካይነት የአበባ ጉንጉን ያስቀምጣል፤ የባንኩ ሥራ ሳይቋረጥ የሠራተኛዉ የሥራ ባልደረቦች በቀብር ስነ
ስርአቱ ላይ እንዲገኙ ፈቃድ ይሰጣል፡፡
2.5. ሠራተኛዉ የሞተዉ ከባንኩ ሥራ ጋር ባልተገናኘ ምክንያት ከሆነ በአሠሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 አንቀፅ 39 ንዑስ አንቀፅ 2 እና 3 መሠረት ለሟች ጥገኞች የሚከፈለዉ የሥራ ስንብት ክፍያ
እንደተጠበቀ ሆኖ የአገልግሎት ዘመን ሳይገድበው ባንኩ ለቀብር ማስፈፀሚያ የሠራተኛዉን የ 2 ወር ደመወዝ
ለሟች የትዳር ጓደኛ ወይም ቤተሰብ ይከፍላል፡፡
2.6. ሠራተኛዉ የሞተዉ በባንኩ ሥራ ላይ (On Duty) ከሆነ በአሠሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 አንቀፅ 110 መሠረት ለሟች ጥገኞች የሚከፈለዉ የካሳ ክፍያ እንደተጠበቀ ሆኖ የአገልግሎት
ዘመን ሳይገድበዉ ባንኩ ለቀብር ማስፈፀሚያ የሠራተኛዉን የ 4 ወር ደመወዝ ለሟች የትዳር ጓደኛ ወይም
ቤተሰብ ይከፍላል፡፡
2.7. አንድ ሠራተኛ ሌላ ማንኛውም የቅርብ ዘመድ ወይም ወዳጅ ቢሞትበት ሠራተኛው በቀብሩ ሥነሥርዓት ላይ
እንዲገኝ የቅርብ የሥራ ሀላፊው ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
2.8. በዓመት ዕረፍት ላይ እያለ ሠራተኛው ሐዘን ቢገጥመው በንዑስ አንቀጽ 2.1 እና 2.2 የተጠቀሰው የሐዘን
ፈቃድ መጠን የዓመት ዕረፍቱ ይራዘምለታል፡፡
2.9. አንድ ሠራተኛ በማንኛውም ምክንያት ከሚኖርበት አካባቢ ውጪ ቢሞት ባንኩ የሠራተኛውን አስክሬን
ለቤተሰቡ ያደርሳል፡፡

41
3. ለጋብቻ የሚሰጥ ፈቃድ (Marital Leave)

አንድ ሠራተኛ ሲያገባ ለአንድ ጊዜ ብቻ ለ 7 (ለሰባት) የሥራ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የጋብቻ ፈቃድና ካስፈለገም
ከተጠራቀመ የዓመት ፈቃድ የሚታሰብ በተጨማሪ ይሰጠዋል፡፡

4. የወሊድ ፈቃድ (Maternity Leave)

4.1. ነፍሰ ጡር ሠራተኛ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት መውለጃዋ እስኪደርስ የ 30 ተከታታይ ቀናት
የወሊድ ፈቃድ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ ለ 120 (አንድ መቶ ሃያ) ተከታታይ ቀናት
የወሊድ ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጣታል፡፡
4.2. ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ 30 ቀን ፈቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከምትወልድበት ቀን
ድረስ እንድታርፍ ሀኪም ከፈቀደላት በሐኪም ትዕዛዝ መሠረት ከክፍያ ጋር ዕረፍት ይሰጣታል። ሆኖም የ 30
ቀኑ ፈቃድ ሳያልቅ ከወለደች የቀሩት ቀናት ከወሊድ ፈቃዷ ጋር ተጨምሮ ይሰጣታል። በማንኛዉም ሁኔታ
ሠራተኛዋ የቅድመ ወሊድ ፈቃዷን ሳትጠቀም ከወለደች በድህረ ወሊድ ፈቃዷ ላይ ተጨምሮ
ይሰጣታል፡፡
4.3. ሠራተኛዋ በእርግዝና ጊዜ ምርመራ እንድታደርግ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ
ይሰጣታል፡፡
4.4. ሠራተኛዋ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ፅንሷ የተቋረጠ ስለመሆኑ በሀኪም ሲረጋገጥ ወይም እርግዝናው
ለጤንነቷ አስጊ ሆኖ ሲገኝና በህክምና ውርጃው ቢፈጸም ሙሉ የህክምና ወጪውን ባንኩ ይችላል፡፡
በተጨማሪም ሐኪም ባዘዘው መሠረት ልዩ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡ ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ የሆነው ጽንስ
ውርጃ ካጋጠማት እንደ ወሊድ ፍቃድ ተቆጥሮ 60 (ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ፍቃድ ይሰጣታል፡፡
4.5. የባንኩ ሴት ሠራተኛ በምትወልድበት ጊዜ የባንኩ ዓርማ ያለበት የእንኳን ደስአለሽ ካርድ፣ የ 400 ብር አበባ
ይበረከትላታል፤ እነዲሁም ብር 1‚000 (አንድ ሺህ ብር) በባንኩ ይሰጣታል።
4.6. ነፍሰጡር የሆነች ሠራተኛ ከመውለዷ በፊት ሐኪም እንድታርፍ ካዘዘ ከክፍያ ጋር ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
ይህም እንደ ህመም ፈቃድ አይቆጠርም፡፡
4.7. ማንኛውም የባንኩ ሴት ሠራተኛ የባንኩ ክሊኒክ በሚፈቅዳቸው ሆስፒታሎች ወይም ክሊኒኮች በእርግዝናና
በወሊድ ጊዜ የምታወጣውን የህክምናና የሆስፒታል ወጪ በሙሉ የህፃኑን ጨምሮ ባንኩ ይችላል፡፡
4.8. ባንኩ ለሴት ሰራተኞች የጨቅላ ህጻናት ማቆያ የሚሆን ከማህበሩ ጋር በመመካከር ያዘጋጃል፡፡

5. የአባትነት ፈቃድ (Paternity Leave)

42
የባንኩ ሠራተኛ ሚስቱ ስትወልድ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ሕፃኑን እና ባለቤቱን ለመንከባከብ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት
የአባትነት ፍቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፤ ሆኖም የፅንስ ማቋረጥ ሲያጋጥምና የሐኪም ማስረጃ ያቀረበ ከሆነ 5 (አምስት)
ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፡:

6. ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ (Leave Without Pay)


ሠራተኛው ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ለማግኘት ያለው መብት ያበቃ እንደሆነ ልዩና አሳሳቢ ሁኔታ ሲያጋጥመው
በሚያቀርበው መረጃ መሠረት ባንኩ ካመነበት እስከ 30 (ሰላሣ) ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ደመወዝ የማይከፈልበት ፈቃድ
የቅርብ የሥራ ኃላፊው ይሰጠዋል፡፡ ተጨማሪ ካስፈለገ በሚያቀርበው ማስረጃና በቅርብ የሥራ ኃላፊው ሲረጋገጥና
በፅሁፍ ሲገለፅ ፤ በሚቀጥለው የሥራ ኃላፊ እስከ 30 (ሰላሣ) ተከታታይ ቀናት ፈቃድ ሊያገኝ ይችላል፡፡ ይህም ካልበቃ
ተጨማሪ እስከ 120 (አንድ መቶ ሃያ) ተከታታተይ ቀናት ድረስ በም/ፕ- የሰውኃ/አስተዳደር በኩል ፈቃድ ሊያገኝ
ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በአጠቃላይ የሚፈቀደው ደሞዝ የማይከፈልበት ፈቃድ ከስድስት ወራት አይበልጥም፡፡ ማንኛውም
ደሞዝ የማይከፈልበት ፈቃድ ሲሰጥ በኦራክል ሲስተም ላይ የቅርብ የሥራ ኃላፊው ይመዘግባል ፤ ለሠው ኃይል
አስተዳደርም በግልባጭ ያስታውቃል፡፡

7. ልዩ ልዩ ተግባራት ለማከናወን ለሠራተኛ የሚሰጥ ፈቃድ


አንድ ሠራተኛ የሥራ ክርክር ለማሰማት ማለትም ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለፍርድ ቤት ወይም ሕጎችን
ለማስፈጸም ሥልጣን ባላቸው አካላት ዘንድ ቀርቦ ቅሬታውን ለማሰማት ወይም ቃል ለመስጠት ላጠፋው ጊዜ ብቻ
ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡

8. የማህበር ተግባር ለማከናወን የሚሰጥ ፈቃድ (Trade Union Leave)


8.1. የማኅበር መሪዎች የሥራ ክርክር ለማቅረብ፣ የህብረት ስምምነት ለመደራደር፣ በሠራተኞች ማህበራት
ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽንና በኮንፌዴሬሽን በሚጠራ ስብሰባ ላይ ለመገኘት፣ በሴሚናሮች በኮንፈረንሶች ወይም
በልዩ ልዩ ሥልጠናዎች ላይ ለመካፈል እንዲችሉ ባንኩ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
8.2. ከላይ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 8.1 ላይ የሚሰጥ ፈቃድ እንደተጠበቀ ሆኖ በማህበሩ ህገ-ደንብ መሰረት
ለተመረጡ የማህበሩ አመራሮች የሥራ ዘመናቸዉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ባንኩ በሚከተለዉ አኳኋን ፈቃድ
ይሰጣል፡-
8.2.1. ለማህበሩ ፕሬዝዳንት በሳምንት 4 (አራት) ቀን ፤
8.2.2. ለማህበሩ ም/ፕሬዝዳንት ፣ ለዋና ፀሐፊ፣ ለሂሳብ ሹም እና ለኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ በሳምንት 2 (ሁለት)
ቀን፤
8.2.3. ለሌሎች የሥራ አስፈፃሚ እና ኦዲት ኮሚቴ አባላት በሳምንት 1 (አንድ) ቀን እንዲሁም፤
8.2.4. ለዲስትሪክት ተጠሪ ፅ/ቤት ተወካዮች በሳምንት 1/2 (ግማሽ) ቀን ፤
8.2.5. ለዋናው መ/ቤት ተጠሪ ተወካዮች በወር ለ 1 (ለአንድ) ቀን ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡
43
8.2.6. የማኅበሩ ሕገ ደንብ በሚደነግገው መሠረት የማኅበሩን የጠቅላይ ምክር ቤት አባላት ወይም ጠቅላላ
ጉባዔውን ለመጥራት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ባንኩ ለተሳታፊዎቹ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ
ይሰጣቸዋል፡፡

9. በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የሠራተኛ ማህበሩ ተመራጮች በማህበር ሥራ ምክንያት ለስብሰባ፣ ለስልጠና እና ለሌሎች
ጉዳዮች በመደበኛ ሥራቸው ላይ በሌሉበት ጊዜ የሚሰጥ የሥራ ውጤት ምዘና ያልነበሩበትን ጊዜ ከግምት ውስጥ
ያስገባ እና በነበሩበት ጊዜ በሰሩት ሥራ ነው፡፡

ምዕራፍ - ስድስት

የሙያ ደህንነት፣ የሥራ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ

አንቀፅ ሠላሳ አራት

የሥራ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ

1. ማንኛውም የባንኩ ሠራተኛ የባንኩን ገጽታ የሚመጥን እና ራዕይዉን መግለጽ የሚችል ደረጃዉን የጠበቀ አለባበስ
የሥራ ባህሪዉ በሚጠይቀዉ መሠረት እንዲለብስ ይገደዳል፤ ባንኩም አስፈላጊዉን ሁሉ ያመቻቻል፡፡

2. ባንኩ ከዚህ በታች በተመለከተዉ ሰንጠረዥ ላይ በተጠቀሱት የሥራ መደቦች ላይ ለሚመደቡ ሠራተኞች በሙሉ
የሥራ ልብስ እና እንደአስፈላጊነቱ የአደጋ መከላከያዎችን ወቅቱን እና ጥራቱን ጠብቆ ይሰጣል፡፡

3. ለሠራተኛዉ የሚሰጡ የደንብ ልብሶች ወይም የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች በዓመት አንድ ጊዜ እ.ኤ.አ ጁላይ ወር
ውስጥ ሆኖ እ.ኤ.አ ከጁላይ ጀምሮ እስከ ድሴምበር ባለው ጊዜ ውስጥ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች የዓመቱ ኮታ
(ድርሻ) ሙሉ የሚሰጥ ሲሆን እ.ኤ.አ ከጃኑዋሪ እስከ ጁን ባለው ጊዜ ውስጥ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ደግሞ ከዚህ
በታች በተመለከተዉ ሰንጠረዥ መሠረት የዓመቱ ኮታ ግማሽ ይሰጣቸዋል፡፡

4. ይህ ሕብረት ትስምምነት ከተፈረመ በኋላ በሚቋቋሙ ወይም በሚከፈቱ አዳዲስ ሥራዎች ምክንያት ለሚመደቡ
ወይም ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ተገቢ እና አስፈላጊ የሥራ ልብሶች እና የአደጋ መከላከያዎች መጠቀሚያ ባንኩ
ይሰጣል፡፡

44
የሥራ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ፡-

የአፍ መሸፈኛ
ክራቫት (ለወንዶች)

የዝናብ ልብስ

ጃንጥላ

የአደጋ መከላከያ ጫማ (safety Shoe) (ወይም በመምትኩ ሁለት ጫማ)


ቆዳ ጫማ

የእጅ ጓንት የፕላስቲክ

ካኪ የሥራ እና የጥበቃ ካፖርት

የእጅ ባትሪ እንደ አስፈላጊነቱ

የንፋስ መነጽር፣ የብረት ቆብ፣ የነፋስ መከላከያ መስታወት

የቆዳ ጃኬት
ነጭ ጋዋን

ጥልፍልፍ የቆዳ ጫማ

ኮፊያ ወንፊት ያለው


ቱታ

ነጭ ሱሪ እና ቶኘ /አላባሽ/

ነጭ ጫማ /ዶክተር ሹዝ/
ቆብ የጨርቅ

አቧራ መከላከያ ጭምብል


የእግር ሹራብ

የአደጋ መከላከያ ቆብ
ኮትና ሱሪ

ሰደርያ ቀሚስ እና ሱሪ

ሽርጥ
ሻሽ
ሸሚዝ

ቦቲ ጫማ የቆዳ

ቦቲ ጫማ የፕላስቲክ

የእጅ ጓንት የቆዳ

ሽርጥ የፕላስቲክ
የስራ መደብ

1 አትክልተኛ 2 4 2 4 - - 1 1 1 1 1 - - - - - - - - - - - - - - - - - - -

2 የጽዳት ሠራተኛ 2 4 2 4 2 - 1 - - 1 1 - 1 1 1 - - 2 - - - - - - - - - - - -

3 የቢሮ ተላላኪ 2 4 2 4 2 - 1 - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -

4 የገንዘብ ቤት ተላላኪ 2 4 2 4 - - - - - - 1 - - - 1 1 - - - - - - - - - - - - - -

5 የጥበቃ አባል 2 4 2 4 2 - 1 - - 2 - - - - 1 - - - - - 1 - - - - - - - - -

6 ሹፌር 2 4 2 4 2 - 1 1 1 - - - - 1 - - - - - - 1 - - - - - - - - -

7 ሞተረኛ ተላላኪ 2 4 2 4 2 1 1 - - - - 1 - - - - - - - - - 1 1 - - - - - - -

8 ግንበኛ እና የግንበኛ ረዳት 2 4 - 4 - - 1 1 1 - - 1 - - - - 1 - - - - - - - - - - - - -

9 የቧንቧ ሠራተኛ እና - - - - - - - 1 1 - - 1 - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ቀለም ቀቢ
10 የኤሌክትሪክ ሠራተኛ - - - - - - - - 1 - - 1 1 1 - - - - - - - - - - - - -

11 መዝገብ ቤት፣ የማባዣ/ - - - - - - - - - - - - - - 1 1 - - - - - - - - - - - - - -


ማተሚያ ቤት እና የዕቃ
መጋዘን ሠራተኞች
45
ቆዳ ጫማ

የእጅ ጓንት የፕላስቲክ

ካኪ የሥራ እና የጥበቃ ካፖርት

ነጭ ጋዋን

ኮፊያ ወንፊት ያለው


የአፍ መሸፈኛ

አቧራ መከላከያ ጭምብል


የእግር ሹራብ

የአደጋ መከላከያ ቆብ
ክራቫት (ለወንዶች)

የዝናብ ልብስ

ጃንጥላ

የአደጋ መከላከያ ጫማ (safety Shoe) (ወይም በመምትኩ ሁለት ጫማ)

ሰደርያ ቀሚስ እና ሱሪ

ሽርጥ
ሻሽ
ሸሚዝ

ቦቲ ጫማ የቆዳ

ቦቲ ጫማ የፕላስቲክ

የእጅ ጓንት የቆዳ

ሽርጥ የፕላስቲክ

የእጅ ባትሪ እንደ አስፈላጊነቱ

የንፋስ መነጽር፣ የብረት ቆብ፣ የነፋስ መከላከያ መስታወት

የቆዳ ጃኬት

ጥልፍልፍ የቆዳ ጫማ
ቱታ

ነጭ ሱሪ እና ቶኘ /አላባሽ/

ነጭ ጫማ /ዶክተር ሹዝ/
ቆብ የጨርቅ
ኮትና ሱሪ
የስራ መደብ

12 ገንዘብ ለየቅርንጫፎች - - - - - - - - - - - - - - 1 1 - - - - - - - - - - - - - -
የሚያሰራጩ Issue
Account ላይ የሚሰሩ
ፀሃፊ ለሆኑ የገንዘብ ቤት
ሰራተኞች
13 መካኒክ፣አናጢ እና የህንጻ - - - - - - - - 2 - - - - - 1 - 1 - 2 1 - - - - - - - - - -
ቴክኒሺያን
14 ሲቪል፣ ኤሌክትሪካል እና - - - - - - - - - - - - - - - - 1 - 2 1 - - - - - - - - - -
መካኒካል መሃንዲስ
15 ቧንቧ ሠራተኛ፣ ቀለም - - - - - - - 1 1 - - 2 - - 1 1 - 2 1 - - - - - - - - - -
ቀቢ
16 የሕንፃ ቴክኒሽያን 1 1 1 2 1
17 ፈርኒቸር ባለሙያ፣ ብረት - - - - - - - - 2 - - 1 - - 2 1 - - - - - - - - - - - - -
እና አልሙኒየም ባለሙያ፣
18 ለሕክምና ባለሙያዎች - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - 2 2 2 - - - -

19 ለሥራ አስኪያጅ፣ 2 2 2 - 2 - - - - - - - - - - - - - - - - - - 2 - - - - - -
ለምግብና መጠጥ ቁጥጥር
ሰራተኞች
20 ለምግብና መጠጥ ኦዲተር 2 2 2 - 2 - - - - - - - - - - - - - - - - - - 2 - - - - - -
እና ስቶር ኪፐር ሰራተኞች
21 ለምግብና መጠጥ ዋና 2 2 2 - 2 - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
አስተናጋጅ ሰራተኞች
22 ለምግብና መጠጥ - 2 2 - 2 - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - 2 - -
መስተንግዶ፣ ባር ቴንደር እና
46
26
25
24
23

ሰራተኞች
ካሸር ሰራተኞች
የስራ መደብ

ዳቦ ጋጋሪ ሰራተኞች

ለስጋ አዘጋጅ /ቡቸር/

አገልግሎት ሰራተኞች
ክፍል ጽዳት ሰራተኞች

ለምግብና መጠጥ ጠቅላላ


ለምግብና መጠጥ ዝግጅት
ለምግብ ዝግጅት፣ ኬክ እና

2
2
2
2
ኮትና ሱሪ

2
2
2
2
ሸሚዝ

2
2
2
2
ቆዳ ጫማ

4
2
2
2
የእግር ሹራብ

-
-
-
-
ክራቫት (ለወንዶች)

-
-
-
-
ቦቲ ጫማ የቆዳ

1
2
2
2 የዝናብ ልብስ

-
-
-
-

ቦቲ ጫማ የፕላስቲክ

-
-
-
-

ቱታ

-
-
-
-

ቆብ የጨርቅ
-

2
4
2

የእጅ ጓንት የፕላስቲክ


-
-
-
-

የእጅ ጓንት የቆዳ

47
-
-
-

ጃንጥላ
-
-
-
-

ሽርጥ የፕላስቲክ
-
-
-
-

ካኪ የሥራ እና የጥበቃ ካፖርት


-
-
-
-

የአፍ መሸፈኛ
-
-
-

የአደጋ መከላከያ ጫማ (safety Shoe) (ወይም በመምትኩ ሁለት ጫማ)


-
-
-
-

ሻሽ
-
-
-
-

አቧራ መከላከያ ጭምብል


-
-
-
-

የአደጋ መከላከያ ቆብ
-
-
-
-

የእጅ ባትሪ እንደ አስፈላጊነቱ


-
-
-
-

የንፋስ መነጽር፣ የብረት ቆብ፣ የነፋስ መከላከያ መስታወት


-
-
-
-

የቆዳ ጃኬት
-
-
-
-

ነጭ ጋዋን
-
-
-
-

ነጭ ሱሪ እና ቶኘ /አላባሽ/
-
-
-
-

ነጭ ጫማ /ዶክተር ሹዝ/
-
-
-
-

ጥልፍልፍ የቆዳ ጫማ
-
-
-
-

ሰደርያ ቀሚስ እና ሱሪ
-
2
2
2

ኮፊያ ወንፊት ያለው


-
2
2
2

ሽርጥ
ምዕራፍ - ሰባት
አንቀፅ - ሠላሳ አምስት
የሥነ-ሥርዓት ጉድለቶችና እርምጃዎች፡
1. የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ትርጉምና አፈጻጸም፡-
የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ማለት አንድ ሠራተኛ የጋራ ስምምነት በመጣስ ወይም ባንኩ የሚያወጣውን መመሪያ በትክክል
ሥራ ላይ ባለማዋል ወይም ባንኩና ማህበሩ ተስማምተው በሥራ ላይ ያዋሉትን ደንብ በመተላለፍ ለሚፈጽመው ጥፋት
የሚወሰድበት የቅጣት እርምጃ ማለት ነው፡፡

1.1. በአንድ ሠራተኛ ላይ የሥነ-ሥርዓት እርምጃ የሚወሰደው ሠራተኛውን ከጥፋት ለማረምና ሥራው እንዳይበደል
ለመቆጣጠር እንጂ በሠራተኛው ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ አይደለም፡፡
1.2. ማንኛውም ሠራተኛ ጥፋት በሚፈፅምበት ጊዜ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት አስፈላጊው ማስረጃ መቅረብ አለበት፤
እንዲሁም ቅጣት ከመወሰኑ በፊት የጥፋቱ ክብደት፣ ሠራተኛው ከጥፋቱ በፊት የነበረው ፀባይ፣ ያለፈው
መልካም አገልግሎቱ እና ለጥፋቱ መንስኤ የሆኑትን ተጨባጭ ሁኔታዎች በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው፡፡
1.3. የቃል ማስጠንቀቂያ ለመስጠትና ሠራተኛውን ለማስተማር አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ማስጠንቀቂያው በተለየ መዝገብ
ተመዝግቦ ማስጠንቀቂያውን በሰጠው ኃላፊና ማስጠንቀቂያውን በተቀበለው ሠራተኛ ይፈረምበታል፡፡

1.4. ከቃል ማስጠንቀቂያ በስተቀር ማንኛውም የሥነ-ሥርዓት እርምጃ በአንድ ሠራተኛ ላይ ሲወሰድ ባንኩ ሁኔታውን
በዝርዝር ለሠራተኛው በመግለጽ በግልባጭ ለማህበሩ በጽሑፍ ያስታውቃል፡፡

1.5. ከቃል ማስጠንቀቂያ በስተቀር ማንኛውም የሥነ-ሥርዓት እርምጃ በሚወሰድበት ወቅት ሠራተኛው ዝርዝር
ሁኔታውን በጽሑፍ እንዲያውቀውና በግልባጩ ላይ ፈርሞ እንዲቀበል ይደረጋል፡፡

1.6. ከሥራ የሚያስወጣ ከባድ ጥፋት ፈፅመዋል በሚል በተጠረጠሩ ሠራተኞች ላይ የቅርብ ኃላፊው፣ በቅርንጫፍ
ከሆነ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ የዲስትሪከት ዳይሬክተርን በማማከር ፤ በዲስትሪክት፣ በንዑስ የሥራ ሂደት፣
በዋና የሥራ ሂደት ከሆነ የሰው ኃይል አስተዳደርን በማማከር የጥፋቱ ሁኔታ እስኪጣራ ድረስ የእግድ ውሳኔ
ይሰጣል፤ የዕገዳውም ጊዜ ከሰላሳ ቀናት መብለጥ የለበትም፡፡ ይህንንም ውሳኔ በቅርንጫፍ ከሆነ ለዲስትሪክት
ዳይሬክተር፣ በዲስትሪክት እና በዋና መሥርያ ቤት ከሆነ ለሪጅን ፅህፈት ቤት እና ለሰው ኃይል አስተዳደር
በሦስት ቀን ውስጥ ያሳውቃል። በማንኛውም ደረጃ የሚሰጥ የዕገዳ ውሳኔ የሰው ኃይል አስተዳደር እና የሠራተኛ
ማህበሩ በግልባጭ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
1.7 ከሥራ የሚያስወጣ ከባድ ጥፋት በሚፈጽሙ ሠራተኞች ላይ በቅርንጫፍ ከሆነ የዲስትሪከት ዳይሬክተር፣
በዲስትሪክት ወይም በዋና መሥርያ ቤት እና በሪጅን ፅህፈት ቤቶች ከሆነ የሰው ኃይል አስተዳደር የስንብት ውሳኔ

48
ይሰጣል፡፡ በዲስትሪክት የሚሰጥ የስንብት ውሳኔ የሰው ኃይል አስተዳደር እና የሠራተኛ ማህበሩ በግልባጭ
እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
1.8. የስንብት ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት ሠራተኛው በቀረበበት ጉዳይ ላይ በጽሁፍ ሃሳቡን እንዲገለጽ እድል
ይሰጠዋል። ውሳኔ ሰጪው ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የሠራተኛ ማህበሩ ተወካይ የተሳተፈበት የአስተዳደር ኮሚቴ
የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርብ ይደረጋል፡፡

1.9. አንድ ሠራተኛ ጥፋቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የስንብት ውሳኔ ሳይሰጠው በምንም ዓይነት ከ 30 ቀናት በላይ
ሊቆይ አይችልም፡፡

1.10. ሠራተኛው በተራ ቁጥር 1.7 በተሰጠው ውሳኔ ላይ ለሰው ኃይል አስተዳደር መምሪያ ይግባኝ የማለት መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡ ሠራተኛው ጥፋተኛ አለመሆኑ ከተረጋገጠና ስንብቱ ያለአግባብ መሆኑ ከታወቀ ከሥራ
ባሰናበተው ባለሥልጣን ላይ ባንኩ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡ በእገዳው ወይም በስንብቱ
ጊዜ ውስጥ የቀረበት ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ይከፈለዋል፡፡

1.11. አንድ ሠራተኛ ላይ የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ሲወሰድ የሚወሰነው ቅጣት ስለ ጥፋቱ የሚወሰነው የቅጣት ዓይነት
በሚያስረዳው ሠንጠረዥ መሠረት ይሆናል፡፡

1.12. በሠንጠረዡ ከተዘረዘሩት የጥፋት ዓይነቶች ውጭ የሚያጋጥሙ ሌሎች የጥፋት ዓይነቶች ሲኖሩ የጥፋቶቹ
ከባድነትና ቀላልነት እየታየ በአስተዳደር ኮሚቴ ይወሰናል፤ ጥፋቱም በሰንጠረዡ ውስጥ በቋሚነት እንዲገባ
የሚያስፈልግ ከሆነ በባንኩና በማህበሩ ይወሰናል፡፡

1.13. ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ማንኛውም ሠራተኛ የማስጠንቀቂያው የጊዜ ገደብ ሳያልቅ ሌላ ማስጠንቀቂያ የሚያሰጥ
ጥፋት ቢፈጽም የሥነ-ሥርዓት እርምጃ አወሳሰዱ የቅጣት እርምጃ በሚወሰድበት አንቀጽ (በአዲሱ ጥፋት)
በሚቀጥለው ደረጃ ይሆናል፡፡

1.14. ማንኛውም ሠራተኛ በሥነ-ሥርዓት ጉድለት ምክንያት የሚሰጠው የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ፀንቶ የሚቆየው
በሚከተሉት አኳኋን ሆኖ የተሠጠው የጊዜ ገደብ ካለፈ ለተለያየ የሠራተኛው ምዘና እንደግብዓት እይወሰድም።
ሀ/ የመጀመሪያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ለሁለት ወራት
ለ/ የሁለተኛ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እና 10% የደመወዝ ቅጣት ለስድስት ወራት
ሐ/ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እና 20% የደመወዝ ቅጣት ለዘጠኝ ወራት
መ/ ከደረጃ ዝቅ የተደረገ ማስጠንቀቂያው ለአንድ ዓመት ፀንቶ የሚቆይ ሆኖ በዚሁ ጊዜ ሠራተኛው ለሽልማት
ወይም ለምስጋና የሚያበቃ የተለየ የሥራ ውጤት ካሳየ የጊዜ ገደቡ ሳያልቅ ዕገዳው ሊነሳለት ይችላል፡፡

49
1.15. ማንኛውም ሠራተኛ በአንድ ጊዜ በሥነ-ሥርዓት ማስከበሪያ እርምጃዎች ውስጥ የተዘረዘሩትን ልዩ ልዩ ዓይነት
ጥፋቶችን ፈጽሞ ሲገኝ በከባዱ ጥፋት ብቻ ይቀጣል፡፡

1.16. ማንኛውም ሠራተኛ በተመደበበት ክፍል ወይም ቅርንጫፍ ውስጥ ልዩ ልዩ ጥፋቶችን መፈጸሙ ሳይታወቅ ቆይቶ
ጥፋት መፈጸሙ ቢታወቅ ወይም ሌላ ተጨማሪ ጥፋት በመፈጸሙ የፊተኛው ጥፋት ቢገለጽ የሚወሰደው የሥነ-
ስርዓት እርምጃ ጥፋቶቹ ተጣምረው በከባዱ ጥፋት ብቻ ይቀጣል፡፡

1.17. ማንኛውም ሠራተኛ ቀደም ሲል ተመድቦበት በነበረው ክፍል ወይም ቅርንጫፍ ውስጥ ልዩ ልዩ ጥፋቶችን
መፈጸሙ ሳይታወቅ ቆይቶ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ከተዛወረ በኋላ ጥፋት መፈጸሙ ቢታወቅ የሥነ-ሥርዓት
እርምጃው ሰራተኛው ይሰራበት በነበረው ቦታ ባለው የአስተዳደር ኮሚቴ ተመርምሮ ይወሰናል፡፡

1.18. አንድ ሠራተኛ በማንኛውም ምክንያት ተጠርጥሮ ታስሮ በዋስ ቢለቀቅ የፍርድ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ወደ ሥራ
መደቡ የሚመለስ ወይም የማይመለስ መሆኑ በአስተዳደር ኮሚቴ ታይቶ በባንኩ ይወሰናል፡፡

1.19. ባንኩ በዚህ የህብረት ስምምነት የተመለከቱ የሥነ-ሥርዓት እርምጃዎችን በመቀነስ በአጥፊው ላይ እርምጃ
ሊወስድ ይችላል፡፡
1.20. ባንኩ ከዚሀ በታች በንዑሰ አንቀጽ 2.1 ስር በማጭበረበር(ማታለል) ፣ ስርቆት እና/ወይም መማለጃ (ጉቦ)
ምክንያት ከሥራ የሚያስወጡ ጥፋቶች ውጭ በሌሎች በዚህ ህብረት ስምምነት በተመለከቱ ሁኔታዎች ለስንብት
እርምጃ የሚዳርግ ጥፋት ያጠፋ ሠራተኛን ከደረጃ ዝቅ በማድረግ ሊቀጣ ይችላል።

2. የሥነ ሥርዓት እርምጃ አወሳሰድ

2.1 በመጀመሪያ ጥፋት ካለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች

2.1.1. ማጭበርበር/ማታለል፡-

2.1.1.1. የባንኩን ወይም ለባንኩ የቀረበ ማንኛውንም ሰነድ ሆነ ብሎ ያጠፋ ወይም


የደለዘ ወይም የቀየረ፣

2.1.1.2. የሐሰት መታወቂያ ወይም የምስክር ወረቀት ያቀረበ፣


50
2.1.1.3. ለራሱ ወይም ለሶስተኛ ወገን ጥቅም በባንኩ ሰነድ ላይ የሌላ ሰው ፊርማ
አስመስሎ ሥራ ላይ ያዋለ ወይም ለማዋል የሞከረ ወይም የባንኩን ማኅተም በተመሳሳይ የተጠቀመ፣

2.1.1.4. የሐሰት ሰነድ ያቀረበ ወይም የደለዘ፣

2.1.1.5. ራሱን ወይም ሶስተኛን ወገን ለመጥቀም ሲል የተሳሳተ መረጃ የሰጠ፣

2.1.1.6. አንድ ሠራተኛ ሲቀጠር የተሳሳተ መረጃ በመሥጠት ባንኩን ያጭበረበረ፡፡

2.1.2 ስርቆት/ማጭበርበር ፡-

2.1.2.1 የባንኩን፣ የሥራ ባልደረቦቹን ወይም የደንበኞችን ንብረት ወይንም ገንዘብ


የሰረቀ፣ የዘረፈ ወይም ለመስረቅ የሞከረ፣ ወይም ሆነ ብሎ ያጐደለና በእነዚህ አድራጎቶች የተባበረ፤

2.1.2.2 በኮምፒዩተርና ሌሎች ተመሳሳይ ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች በመጠቀም ለግል


ወይም ለሌላ ሦስተኛ ወገን ጥቅም በማዋል ሥርቆትና ማጭበርበር የፈጸመ ወይም እንዲፈጸም ያደረገ ወይም
የሞከረ፤

2.1.3 መማለጃ/ጉቦ፡-

የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት መገልገያ በማድረግ ከሠራተኞቹም ሆነ ከባንኩ ጋር ግንኙነት ካለው ከማንኛውም ግለሰብ
መማለጃ ሲቀበል፣ ሲያቀባብል ወይም ሲሰጥ የተገኘ፡፡

2.1.4 ምስጢር ማባከን፡-

ከባንኩ ቋሚ አሠራር ውጪ ሆን ብሎ የባንኩን እና የደንበኞችን ዕድገት ሕልውና እና ጥቅም የሚጎዳ ምስጢር ለሌላ ሰው
ወይም ድርጅት አሳልፎ ያሳወቀ ወይም የሰጠ።

2.1.5 አደጋ ማድረስ፡-

በባንኩ ንብረትና ሠራተኞች ላይ ሆነ ብሎ አደጋ የፈጸመ ወይም ያስፈጸመ፣ ወይም የሞከረ፣ ወይም ከሌላ ሦስተኛ ሰው
ጋር ተባባሪ የሆነ፡፡

2.1.6 ወንጀል፡-

በወንጀል ተፈርዶበት ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ የታሠረ ሆኖም የወንጀሉ ዓይነት ሥርቆት እና የዕምነት ማጉደልን
የሚመለከት ከሆነ ከዚህ ላነሰ ጊዜ የታሠረ ወይም በገደብ የተለቀቀ ሠራተኛ።

51
2.1.7 ክፍያ፡-

ሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ ለግሉ ወይም ለሶስተኛ ሰው ቼክ ወይም ሌላ የክፍያ ሰነድ ሰጥቶ በመመሳጠር
ወይም በማጭበርበር ወይም በተፅዕኖ እንዲከፈል ያደረገ፡፡

2.1.8 የብልጫ ክፍያ (Overdraw):-

ሆነ ብሎ ሌላውን ሰው ለመጥቀም በማሰብ ከደንበኛ ሂሣብ ውስጥ ከሚታየው ገንዘብ በብልጫ ወጪ ተደርጐ እንዲከፈል
ያደረገ፡፡

2.1.9 በከባድ ቸልተኝነት የሚፈፀም ክፍያ:-

የተንቀሳቃሽ ወይም የቁጠባ ሂሳብ ወጪ ከመደረጉ በፊት በትክክል የደንበኛው ፊርማ መሆኑን ከናሙናው ጋር ሳያስተያይ
ወይም የኤቲኤም ካርድ እና የይለፍ ቁጥሩን ትክክለኛውን ደንበኛ ሳያረጋግጥ ለሌላ ሰው አሳልፎ በመስጠት ፤ ወይም
የደንበኛውን የሞባይል ባንኪንግን አገልግሎት ለሌላ ደንበኛ በመስጠት በከባድ ቸልተኝነት ከብር 10,000.00 (አሥር ሺህ)
በላይ ገንዘብ እንዲከፈል ያደረገ።

2.1.10 የሥራ ዝውውርን አለመቀበል፡-

የሥራ ዝውውር ትዕዛዝን ሆነ ብሎ ያለ በቂ ምክንያት ያልተቀበለ፡፡

2.1.11 መደባደብ፡-

የባንኩን ደንበኛ ወይም የሥራ ኃላፊውን ራሱን ለመከላከል ካልሆነ በስተቀር በባንኩ ግቢ ውስጥ የደበደበ።

2.1.12 ከሥራ ስለመቅረት፡-

ያለበቂ ምክንያት በመደዳው ለአምስት የሥራ ቀናት ወይም በአንድ ወር ውስጥ በጠቅላላው ለአሥር የሥራ ቀናት ወይም
በአንድ ዓመት ውስጥ በጠቅላላው ለሠላሳ የሥራ ቀናት ያለበቂ ምክንያት ከሥራ መቅረት::

2.1.13 በመሣሪያ ያለ አግባብ መጠቀም፡-

ለጥበቃ ሥራ በተሰጠው መሣሪያ ከጥበቃ ጋር ባልተያያዘ ሁኔታ ሰው የገደለ ወይም ያቆሰለ ወይም ለመግደል የሞከረ፡፡

2.1.14 የክፍያ መጠየቂያ መልስ ማዘግየት፤

ከሌላ ቅርንጫፍ ክፍያ የተፈፀመበት ቼክ እና የቁጠባ ቫውቸር (Claim) ከደረሰ በኋለ ሸሽጎ የክፍያ መጠየቂያውን መልስ
ያዘገየ::

52
2.1.15 ያለ ፈቃድ ጥበቃውን ጥሎ መሄድ፡-

እንዲጠብቅ የተመደበበትን የዘብ ቦታ የቅርብ ኃላፊውን ፈቃድ ሳያገኝ ትቶ የሄደ፡፡

2.1.16 ቼክ ማንሳፈፍ (Cheque Floating).

በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ ለግሉ ወይም ለሶስተኛ ሰው ቼክ የሰጠ ወይም ያሳለፈ ወይም
ያንሳፈፈ(Cheque Floating)::

2.1.17 የሐሰት ማረጋገጫ መስጠት፡-

የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገን የብድር ሂሳብ ሳይዘጋ የተዘጋ በማስመሰል ማረጋገጫ የሰጠ፡፡

2.1.18 መሣሪያ መጣል፡-

ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት መሣሪያውን ያስወሰደ ወይም የጣለ የጥበቃ አባል በተጨማሪ የመሣሪያውን ዋጋ ይከፍላል፡፡

2.1.19 ደንብና መመሪያ መጣስ፡-

ሆን ብሎ የባንኩን ደንብና መመሪያ በመጣስ በተመደበበት ሥራ ላይ የሚፈለግበትን የሥራ ድርሻ ባለመወጣት በባንኩ ላይ
ከብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በላይ የሚገመት ጉዳት ወይም ኪሣራ ያደረሰ::

2.1.20 የሥራ ምስጢርን ያለአግባብ መጠቀም፡-

የሥራው አጋጣሚ የደረሰበትን የባንኩን ወይም የደንበኞችን ሚስጢር ሳይፈቀድለት ከባንኩ አሰራር ውጪ በሆነ መልክ
ከሚመለከታቸው ከባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ወይም ሠራተኞች ውጪ ለሆኑ 3 ኛ ወገኖች ከገለጸ፤ ወይም ለግል ጥቅም ካዋለ::

2.1.21 ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት የጥፋት ዓይነቶች ውጭ የሆነ ጥፋት በሰራተኛው ተፈፅሞ ሲገኝ እና የጥፋት አይነቱም
በመጀመሪያ ጊዜ ከሥራ ሊያስባርር የሚችል መሆኑ በአስተዳደር ኮሚቴ ከታመነበት፤ ኮሚቴው በመጀመሪያ
ጥፋት ካለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

2.2 በሁለተኛ ጥፋት ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች፡- በሁለተኛ ጥፋት ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች ማለት ከዚህ
በታች የተዘረዘሩት ሆነው የጥፋቱ ዓይነት ቢለያይም በሰንጠረዡ ውስጥ የተዘረዘሩት ጥፋቶች የቀድሞው
የመጨረሸ ማስጠንቀቂያ ጊዜ ጸንቶ ባለበት ጊዜ ውስጥ ተደግመው ሲፈጸሙ እንደ ሁለተኛ ጥፋት ይቆጠራል፡፡
የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ጥፋት ሁለተኛ ጥፋት
2.2.1 በቢሮ ወይም በባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በጠብ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
አጫሪነት የተደባደበ ተቀንሶ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ፡፡

53
የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ጥፋት ሁለተኛ ጥፋት
2.2.2 ያለበቂ ምክንያት ሆነ ብሎ ደንበኞቹን ወይም የባንኩን የወር ደመወዝ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
ሠራተኞች በመሳሪያ ያላግባብ ያስፈራራ፣ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ
2.2.3 በሂሣቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ ቢኖረውም በቼኩ ላይ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
ከሚታየው ቀን በፊት (post dated) ቼክ ለሶስተኛ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ሰው የሰጠ ወይም ለራሱ ያዘጋጀ (post dated) ለሌላ ማስጠንቀቂያ፡፡
ሰው ያስተላለፈ፣
2.2.4 ባንኩ የሰጠውን የደንብ ልብስ የሸጠ ወይም ለሶስተኛ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
ሰው የሰጠ፣ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ እና በተጨማሪም
የደንብ ልብሱን ይተካል፡፡
2.2.5 የጥቅም ግጭት ከባንኩ ጋር የሚያመጣ ሌላ ሥራ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
ሲሰራ የተገኘ፣ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡
2.2.6 ለራሱም ሆነ ለሶስተኛ ወገን ተባባሪ በመሆን ወርሃዊ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
የብድር ክፍያ እንዲታለፍ ያደረገ፣ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡
2.2.7 ገንዘብ መኖሩን ሳያረጋግጥ በስህተት በሂሣቡ ውስጥ ገንዘቡን ተክቶ የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ካለው ገንዘብ በላይ ወጪ አድርጐ እንዲከፈል ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ የመጨረሻ
ያደረገ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፡፡
2.2.8 የተንቀሳቃሽ ወይም የቁጠባ ሂሳብ ወጪ ከመደረጉ ገንዘቡን ከፍሎ የደመወዙ 20% ስንብት
በፊት በትክክል የደንበኛው ፊርማ መሆኑን ከናሙናው ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ የመጨረሻ
ጋር ሳያስተያይ በቸልተኝነት ከብር 10,000.00 የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፡፡
ያልበለጠ ገንዘብ እንዲከፈል ያደረገ፣
2.2.9 በደንበኛው ሂሳብ ውስጥ በቂ ገንዘብ ሳይኖረው የደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
እንዲከፈለው የፈቀደ (ok) ያለ ወይም ከተፈቀደው ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
የኦቨር ድራፍት ጣሪያ በላይ ያለሥልጣኑ ወጪ ማስጠንቀቂያ፡፡
እንዲሆን የፈቀደ፣
2.2.10 በንዝህላልነት ከሌላ ቅርንጫፍ ክፍያ የተፈጸመበት የደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
ቼክና የቁጠባ ሂሳብ ቫውቸር(claim) ከደረሰው በኋላ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
የክፍያ መጠየቂያውን ያዘገየ ማስጠንቀቂያ

54
የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ጥፋት ሁለተኛ ጥፋት
2.2.11 ያለበቂ ምክንያት ለ 4 የሥራ ቀናት የቀረ ያልሠራበት ቀን ደመወዙና ሰንብት
በተጨማሪ የወር ደመወዙ 20%
ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ የመጨረሻ
የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ
2.2.12 ባንኩ ሳይፈቅድለት የባንኩን ንብረት ለግል ወይም የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
ለሶስተኛ ወገን ጥቅም ያዋለ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ
2.2.13 በስካር ወይም አእምሮን በሚያደነዝዙ ዕጾች ተመርዞ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
በሥራ ቦታ የተገኘ፣ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡
2.2.14 በተመደበበት ሥራ ላይ የሚፈለግበትን የሥራ ድርሻ የወር ደመወዙ 20% አንድ ጊዜ ስንብት
ሆን ብሎ ያልተወጣ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡
2.2.15 በባንኩ ውስጥ ደንበኞችን ያመናጨቀ፣ የትዕቢት የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
ወይም የስድብ አነጋገር የሰነዘረ ወይም በአግባቡ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ያላስተናገደ፣ ማስጠንቀቂያ፡፡
2.2.16 ባንኩን የሚጐዳ ነገር ሲሰራ እያወቀ ለባንኩ ሳያሳውቅ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
የቀረ፣ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡
2.2.17 እውነተኛውን መረጃ በመደበቅ ወይም በዝምታ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
በማለፍ የተሳሳተ የሥራ አፈጻጸም እንዲደርስ ያደረገ፤ ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ
2.2.18 በኮምፒዩተር የሚስጥር ቁልፎችን በአግባቡ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
አለመያዝ፤ ወይም ለሌላ ላልተፈቀደለት ሰው ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
መስጠት ወይም ሳይፈቀድለት ኮምፒዩተርን ማስጠንቀቂያ
መክፈት፤ በባንኩ ላይ ጉዳት ሳያደርስ የቀረ እንደሆነ
2.2.19 ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት የጥፋት አይነቶች ውጭ የሆነ የወር ደመወዙ 20% ለአንድ ጊዜ ስንብት
ጥፋት በራተኛው ተፈፅሞ ሲገኝና የጥፋት አይነቱም ተቀንሶ የመጨረሻ የጽሑፍ
በሁለተኛ ደረጃ ጥፋት ስር ሊካተት የሚችል መሆኑ ማስጠንቀቂያ
በኮሚቴ ከታመነበት፤ ኮሚቴው በሁለተኛ ደረጃ
ጥፋት የሚወሰደውን እርምጃ ሊወሰድ ይችላል።

55
2.3 በሶስተኛ ጥፋት ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች ማለት፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሆነው የጥፋቱ ዓይነት
ቢለያይም በሰንጠረዡ ውስጥ የተዘረዘሩት ጥፋቶች የቀድሞው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጊዜ ጸንቶ ባለበት
ጊዜ ውስጥ ተደግመው ሲፈጸሙ እንደሶስተኛ ጥፋት ይቆጠራል፡፡
ሶስተኛ
የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ጥፋት ሁለተኛ ጥፋት ጥፋት
2.3.1 በተመደበበት ሥራ ላይ የሚፈለግበትን የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
የሥራ ድርሻ በሚገባ ያልተወጣ፣ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
የመጀመሪያ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ፡፡
2.3.2. በጥበቃ ሥራ ላይ ተመድቦ የቀረ የጥበቃ የቀረበት ቀን ደመወዝና የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ሠራተኛ፣ በተጨማሪ 10% ለአንድ ለአንዽ ጊዜ ተቀንሶ
ጊዜ ተቀንሶ የመጀመሪያ የመጨረሻ የጽሑፍ
የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ፡፡
2.3.3 ለሥራ የተሰጡትን ዕቃዎች የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
መሣሪዎችን ወይም ሰነዶች ያለአግባብ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ያባከነ ወይም ያበላሸ እንዲሁም የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ከመደበኛው አጠቃቀም ውጭ ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ፡፡
በመጠቀም ጉዳት ያደረሰ፣
2.3.4 በባንኩና በማህበሩ ወይም በባንኩ እና የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
በሠራተኛው መካከል አለመግባባት ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ አንድ ጊዜ ተቀንሶ
የሚፈጥር ሐሰተኛ ወሬ ያመነጨ የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ሐሰተኛ መሆኑን እያወቀ አሰራጭቶ ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠቀቂያ፡፡
ጠብ ያነሳ ወይም እንዲነሳ የሞከረ፣
2.3.5 በኮምፒውተርም ሆነ በሌላ መንገድ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
በባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁማር ወይም ተቀንሶ የመጀመሪያ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
በሥራ ገበታው ላይ ካርታ/ተመሳሳይ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፡፡ የመጨረሻ የጽሑፍ
ጨዋታ የተጫወተ/ ፣ ማስጠንቀቂያ፡፡
2.3.6 ያለበቂ ምክንያት ለ 3 የሥራ ቀናት ያልሠራበት ቀን ደመወዙና የቀረበት ቀን ደመወዝና ስንብት
በተከታታይ ከሥራ የቀረ፣ በተጨማሪ የወር ደመወዙ በተጨማሪ የወር ደመወዙ
10% ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ 20% ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ፡፡

56
ሶስተኛ
የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ጥፋት ሁለተኛ ጥፋት ጥፋት
2.3.7 ለጥበቃ አገልግሎት የተሰጠውን ጥይት የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
የጣለ ወይም ያጐደለ፣ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ
ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡ ይሰጠዋል። በተጨማሪም
በተጨማሪም የጥይቱን ዋጋ የጥይቱን ዋጋ
ይከፍላል፡፡ ይከፍላል፡፡
2.3.8 በኅብረት ስምምነቱ መሠረት በየጊዜው የመጀመሪያ የወር ደመወዙ የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ከባንኩ የሚሰጡትን ወይም 10% ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
የሚወጡትን ደንቦችና መመሪያዎች የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ያልፈጸመ ወይም የጣሰ፣ ማስጠንቀቂያ። ማስጠንቀቂያ፡፡
2.3.9 ከሥራ ጋር ብቻ በተያያዘ የኃላፊውን የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ትዕዛዝ ያለበቂ ምክንያት ያልተቀበለ፣ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ። ማስጠንቀቂያ፡፡
2.3.10 በጥበቃ ሥራ ላይ የተሰማራ ሠራተኛ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዝ 20% ስንብት
ከመደበኛ የባንኩ ሥራ ሰዓት ውጭ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ያለፈቃድ ሰው በባንኩ ቅጥር ግቢ የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
አስገብቶ ወይም አሳድሮ የተገኘ፣ ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ፡፡
2.3.11 በብድር አሰጣጥ ጊዜ በባንክ የብድር የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
አሰጣጥ ደንብ መሠረት ተገቢ ጥናትና ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ጥንቃቄ ያላደረገ ወይም ሆነ ብሎ የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ወይም በቸልተኝነት ወርሃዊ የብድር ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ፡፡
ክፍያ በየጊዜው እንዲሰበሰብ ያላደረገ
ወይም ተገቢውን ማስጠንቀቂያ
ለደንበኛው ወይም ለዋሱ ያልሰጠ፣
2.3.12 የተሰጠውን ኃላፊነት ወይም ሥልጣን የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ያለአግባብ የተጠቀመ፣ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ

57
ሶስተኛ
የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ጥፋት ሁለተኛ ጥፋት ጥፋት
2.3.13 ከባንኩ የተጻፈለትን ደብዳቤ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
በእንቢተኝነት ያልተቀበለ፣ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ፡፡
2.3.14 በሥራ ሰዓት ሳያስፈቅዱ ከሥራው ጋር የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ያልተያያዙ ሌሎች ሥራዎችን፣ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ተግባሮችን በቢሮ ውስጥ ማከናወን፤ የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ፡፡
2.3.15 ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት የጥፋት የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
አይነቶች ውጭ የሆነ ጥፋት በራተኛው ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ተፈፅሞ ሲገኝና የጥፋት አይነቱም የመጀመሪያ የጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
በሶስተኛ ደረጃ ጥፋት ስር ሊካተት ማስጠንቀቂያ፡፡ ማስጠንቀቂያ፡፡
የሚችል መሆኑ በኮሚቴ ከታመነበት፤
ኮሚቴው በሶስተኛ ደረጃ ጥፋት
የሚወሰደውን እርምጃ ሊወሰድ
ይችላል።

2.4 በአራተኛ ጥፋት ከሥራ የሚያሰናብቱ ድርጊቶች፡- ማለት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሆነው የጥፋቱ ዓይነት
ቢለያይም በሰንጠረዡ ውስጥ የተዘረዘሩት ጥፋቶች የቀድሞው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጊዜ ጸንቶ ባለበት
ጊዜ ውስጥ ተደግመው ሲፈጸሙ እንደአራተኛ ጥፋት ይቆጠራል፡፡

58
ተራ አራተኛ
ቁጥር የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ጥፋት ሁለተኛ ጥፋት ሶስተኛ ጥፋት ጥፋት
2.4.1 ከ 1-2 ቀናት በተከታታይ ከሥራ ያልሠራበት ቀን ያልሰራበት ቀን ያልሠራበት ቀን ስንብት
የቀረ ደመወዝ ተቆርጦ ደመወዝና ደመወዝ 20% ለአንድ
የመጀመሪያ በተጨማሪም የወር ጊዜ ተቀንሶ
የጽሑፍ ደመወዙ 10% የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ማስጠንቀቂያ
ሁለተኛ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ
2.4.2 በሥራ ሰዓት የቅርብ ኃላፊውን የመጀመሪያ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20%
ሳያስፈቅድ ከሥራ ገበታው ላይ የጽሑፍ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ስንብት
ተነስቶ ውጭ የሄደ ወይም ማስጠንቀቂያ ሁለተኛ የፅሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ያለሥራና ያለበቂ ምክንያት ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
የሥራ ቦታውን ትቶ የሌሎች
ሠራተኞች የሥራ ጊዜ ያባከነ

2.4.3 ዘግይቶ ወደ ሥራ የመጣ በወር የመጀመሪያ የወር ደመወዙ 5% የወር ደመወዙ 20%
ውስጥ የዘገየባቸው ጊዜያቶች የጽሑፍ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንዽ ጊዜ ተቀንሶ ስንብት
ተደምረው ማስጠንቀቂያ ሁለተኛ ጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
1. ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
ሰዓት
2. ከሁለት ሰዓት በላይ እስከ የግማሽ ቀን በአንደኛው ጥፋት በአንደኛው ጥፋት
አራት ሰዓት ደመወዙ ለአንድ የሚወሰደውና የሚወሰደውና ስንብት
ጊዜ ተቀንሶ በተጨማሪ የደመወዙ በተጨማሪ የደመወዙ
የመጀመሪያ 10% ለአንድ ጊዜ 20% ለአንድ ጊዜ
የጽሑፍ ተቀንሶ ሁለተኛ ተቀንሶ የመጨረሻ
ማስጠንቀቂያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ
3. ከአራት ሰዓት በላይ እስከ የአንድ ቀን በአንደኛው ጥፋት በአንደኛው ጥፋት
ስድስት ሰዓት። ሆኖም ደመወዙ ለአንድ የሚወሰደውና የሚወሰደውና ስንብት
ከስድስት ሠዓት በላይ ከሆነ ጊዜ ተቀንሶ በተጨማሪ የደመወዙ በተጨማሪ የደመወዙ
እንደ አንድ ቀን ይቆጠራል። የመጀመሪያ 10% ለአንድ ጊዜ 20% ለአንድ ጊዜ
የጽሑፍ ተቀንሶ ሁለተኛ ተቀንሶ የመጨረሻ
ማስጠንቀቂያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ
2.4.4 በገንዘብ ቤት እና/ወይም የመጀመሪያ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
በተከለከለ የኮምፒዩተር አካባቢ የጽሑፍ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ሳይፈቀድለት መግባት፤ ማስጠንቀቂያ ሁለተኛ ጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
2.4.5 የሥራ ባልደረባ ወይም ባለጉዳይ የመጀመሪያ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ላይ ጾታዊ ትንኮሳ ማድረግ፤ የጽሑፍ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ማስጠንቀቂያ ሁለተኛ ጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ

59
ተራ አራተኛ
ቁጥር የጥፋቱ ዓይነት አንደኛ ጥፋት ሁለተኛ ጥፋት ሶስተኛ ጥፋት ጥፋት
2.4.6 የባንኩ ሠራተኛ ሕገ ወጥና ብልሹ የመጀመሪያ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
የሥነ ምግባር ጉድለት የጽሑፍ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
መፈጸሙን እያወቀ ማስጠንቀቂያ ሁለተኛ ጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ለሚመለከተው የባንኩ አካል ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
ሳያሳውቅ የቀረ፤
2.4.7 በውሳኔ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር የመጀመሪያ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ወይም ከሥልጣን ጋር የሚጋጭ የጽሑፍ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ስጦታና ግብዣ የተቀበለ ወይም ማስጠንቀቂያ ሁለተኛ ጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
ለዚሁ ተግባር በስጦታ ወይም ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ
በግብዣ ለማነሳሳት የሞከረ፤
2.4.8 የገንዘብ ቤት ወይም የገንዘብ የመጀመሪያ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
ካዝና ቁልፍ የጣለ ወይም ያጠፋ የጽሑፍ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
ማስጠንቀቂያ እና ሁለተኛ ጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
የቁልፉን መቀየሪያ ማስጠንቀቂያ እና ማስጠንቀቂያ እና
ዋጋ ይከፍላል። የቁልፉን መቀየሪያ የቁልፉን መቀየሪያ
ዋጋ ይከፍላል። ዋጋ ይከፍላል።
2.4.9 ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት የጥፋት የመጀመሪያ የወር ደመወዙ 10% የወር ደመወዙ 20% ስንብት
አይነቶች ውጭ የሆነ ጥፋት የጽሑፍ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ ለአንድ ጊዜ ተቀንሶ
በራተኛው ተፈፅሞ ሲገኝና ማስጠንቀቂያ እና ሁለተኛ ጽሑፍ የመጨረሻ የጽሑፍ
የጥፋት አይነቱም በአራተኛ የቁልፉን መቀየሪያ ማስጠንቀቂያ እና ማስጠንቀቂያ እና
ደረጃ ጥፋት ስር ሊካተት ዋጋ ይከፍላል። የቁልፉን መቀየሪያ የቁልፉን መቀየሪያ
የሚችል መሆኑ በኮሚቴ ዋጋ ይከፍላል። ዋጋ ይከፍላል።
ከታመነበት፤ ኮሚቴው በአራተኛ
ደረጃ ጥፋት የሚወሰደውን
እርምጃ ሊወሰድ ይችላል።

አንቀፅ - ሠላሣ ስድስት

የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት


1. የወል የሥራ ቅሬታ ማለት የሕጎች፣ የደንቦች፣ የኅብረት ስምምነት፣ የሥራና የአስተዳደር ደንቦች ትርጉምና
በእነዚህ ውስጥ የተመለከቱት የሥራ ሁኔታዎች ወይም ጥቅሞች ወይም ሲሰራባቸው የቆዩ ልምዶች በመጓደላቸው
ወይም የሚሻሻሉበት ሁኔታ ወይም አዲስ ጥቅሞችን ለማስገኘት በማኅበሩ ወይም በባንኩ የሚቀርብ አቤቱታን
የሚመለከት የሥራ ቅሬታ ነው፡፡

2. የግል የሥራ ቅሬታ ማለት ጉዳዩ የሚመለከተው ሠራተኛ በሕግ፣ በደንብ፣ በሥራና በአስተዳደር ደንብ ወይም
በኅብረት ስምምነት አተረጓጐም ወይም በሥራ ውል ውስጥ የተመለከተውን ሁኔታ የሚሽር ወይም የሚቀንስ
እርምጃ ባንኩ በመውሰዱ በሠራተኛ ጥያቄ የሚቀርብ ማንኛውም ቅሬታ ነው፡፡

60
3. ስምምነቱ የሚመለከታቸው ሁለቱም ወገኖች የተፈጠረውን ቅሬታ በተቻለ መጠን ሳየዘገይ በፍጥነት ውሳኔ
ማግኘት እንዳለበት ያምናሉ፤ እንዲሁም ሁለቱም ወገኖች ከቅሬታ ጋር የተያያዙ ወይም ቅሬታውን የሚመለከቱ
እውነተኛ ማስረጃዎችን በሙሉ በቅሬታ ሥነ ሥርዓት መጀመሪያ ላይ ለማቅረብ ይጥራሉ፡፡

4. ባንኩ ማኅበሩና ጉዳዩ የሚመለከተው ሠራተኛ በመተባበር በቅን ልቦና የሁለቱን ወገኖች የጋራ ጥቅም በመጠበቅ
ቅሬታዎችን ሁሉ በተቻለ ፍጥነት ለማስተካከል የመጣር ግዴታ አለባቸው።

5. ቅሬታ አቅራቢው የማኅበሩ ተወካይ እንዲገኝለት ሲጠይቅ ተወካዩ ከሥራ ኃላፊው እና ከሠራተኛው ጋር በመሆን
ማንኛውንም ቅሬታ ለማስተካከል ይሞክራሉ፤ ስምምነት ላይ ሊደረስ ካልተቻለ ጉዳዩ በቅሬታ አቀራረብ ስነ-
ሥርዓት መሰረት ይመራል።

6. ማንኛውም የሠራተኛ ቅሬታ በማህበሩ ወይም በባንኩ በኩል ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ይቀርባል፡፡

7. የቅሬታ አቤቱታ በሚቀርብበት ጊዜ በሚከተለው ሥነ-ሥርዓት መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡-

7.1. ሠራተኛው ቅሬታ ሲኖረው ለሚመለከተው የቅርብ ኃላፊ ወይም ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ቅሬታ የፈጠረውን ሁኔታ
በተገነዘበ በ 10 ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ያቀርባል፡፡
7.2. ቅሬታው ከሥራ መሰናበትን ወይም ከደረጃ ዝቅ መደረግን የሚመለከት ከሆነ በየትኛውም ቦታ የሚገኝ የባንኩ ሠራተኛ
በስምንት የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለሰው ኃይል ያቀርባል፤ የሰው ኃይል ከዚህ በታች በቁጥር 7.6.1 በተገለጸው
መሠረት ይፈጽማል፡፡
7.3. ኃላፊው ወይም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጁ ቅሬታው ከቀረበበት ቀን አንስቶ ከቅሬታ አቅራቢው ጋር በመነጋገር በሶስት
የሥራ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ መልስ ይሰጣል፡፡
7.4. ኃላፊው ወይም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጁ በሚሰጠው ውሳኔ ሠራተኛው ያልተስማማ እንደሆነ ወይም ምላሽ
ካልተሰጠው ቅሬታውን ለሚቀጥለው የበላይ ኃላፊ በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡
7.5. የሚቀጥለው የበላይ ኃላፊ ቅሬታው ከቀረበበት ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ለሠራተኛው
በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፤ ሆኖም የቦታ ርቀት ባለባቸው ቅርንጫፎች በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ነገር ግን ጉዳዩን
በስፋት ማጣራት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከአሥራ አምስት የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መልስ መስጠት አለበት፡፡
7.6. አሁንም የበላይ ኃላፊው በሚሰጠው ውሳኔ ሠራተኛው ያልተስማማ እንደሆነ ወይም ምላሽ ካልተሰጠው ቅሬታውን፣
7.6.1 በዋናው መ/ቤት፣ በሪጅን ፅህፈት ቤቶች እና በዲትሪክት ፅህፈት ቤቶች የሚገኝ ሠራተኛ ለሚመለከተው
የዲስትሪክት(ሪጅን) ዋና መ/ቤት ሰው ኃይል ከአምስት የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ያቀርባል፤ የሰው ኃይል
ጉዳዩን ለሚመለከተው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አቅርቦ ኮሚቴው ቅሬታውን ከመረመረ በኋላ የውሳኔ ሃሳብ ለባንኩ
ያቀርባል፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ማህበሩ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በፅሁፍ ጥያቄ ያቀርባል በግልባጭም ለቅሬታ
ሰሚ ኮሚቴ አባላት እና ለሰው ሀይል አስተዳደር ያሳውቃል፤ ባንኩም ቅሬታው ከደረሰው ቀን አንስቶ በአስራ አምስት
የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ለሠራተኛ በፅሑፍ ያሳውቃል፣ ለማኅበሩም በግልባጭ ይገልጻል፡፡

61
7.6.2 በቅርንጫፎች የሚገኝ ሠራተኛ ለዲስትሪክት ፅ/ቤት ዳይሬክተር ከአምስት የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ
ቅሬታውን ያቀርባል፡፡ ዳይሬክተሩም የቀረበውን ቅሬታ በዲስትሪክት ውስጥ ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
አቅርቦ ኮሚቴው የቀረበለትን ቅሬታ መርምሮ የውሳኔ ሐሳብ ለባንኩ ያቀርባል፤ ባንኩም ቅሬታው ከደረሰው ቀን
አንስቶ እጅግ ቢዘገይ በአሥራ አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ለሠራተኛው በጽሑፍ ያሳውቃል፤ ለማኅበሩም
በግልባጭ ይገልጻል፡፡ ሆኖም ቅሬታው የሥራ ስንብትን የሚመለከት ከሆነ በዋናው መ/ቤት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ቀርቦ
እንዲታይ ይደረጋል፡፡
7.7. ቅሬታ አቅራቢው ሠራተኛ በሕመም ፈቃድ፣ በዓመት ፈቃድና ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ቅሬታውን ለማቅረብ
ባይችል፣ የተወሰነው ቀነ-ገደብ በማለፉ ቅሬታውን ከማቅረብ አይከለከልም፡፡ ሆኖም የተጠቀሰው ችግር በተወገደ
በአምስት ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

አንቀፅ - ሰላሳ ሰባት

ሕጐችና ልምዶች በስምምነቱ ላይ የሚኖራቸው ውጤት

1. መንግስት በአዋጅ ወይም በድንጋጌ የሚያወጣቸው ሕጎችና ደንቦች በቀጥታ በሥራ ላይ ይውላሉ፡፡

2. ሲሠራባቸው የቆዩ ልምዶች ወይም ባንኩ ሊያወጣቸው የሚችሉ ሌሎች ሕግጋትና ደንቦች እና መመሪያዎች ሁሉ
ከዚህ ስምምነት መብት እና ግዴታ ጋር የሚጋጩ ሆነው ሲገኙ ተሽረው ይህ ስምምነት እንደተተካባቸው
ይቆጠራል፡፡

አንቀፅ - ሰላሳ ስምንት

የስምምነቱ ዘመን እና ስምምነቱን ስለማሻሻል


1. ይህ የኅብረት ስምምነት በሁለቱ ወገኖች ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የፀና ይሆናል፡፡

2. ይህ የህብረት ስምምነት የአማርኛና የእንግሊዝኛ ትርጉም ይኖረዋል፤ ሆኖም በአማርኛና በእንግሊዝኛ ትርጉም
መካከል ልዩነት ቢኖር የአማርኛው ትርጉም ተፈፃሚነት ይኖረዋል።

3. ከባንኩ ወይም ከማኅበሩ አንዱ ወገን በጽሑፍ ሲጠይቅ እና ሁለቱም ወገኖች ከተስማሙ ስምምነቱን በማንኛውም
ጊዜ ለማሻሻል ይችላሉ፡፡ ማሻሻያው በሁለቱም ወገን በፊርማ ከፀደቀ በኋላ አግባብ ባለው የመንግሥት አካል
መመዝገብ አለበት፡፡

4. ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 1 (አንድ) የተጠቀሰው ዘመን ከማለቁ ዘጠና /90/ ቀናት አስቀድሞ በሁለቱም ወገኖች
አዲስ ድርድር ይደረጋል፡፡ በዚህ መሰረት አንደኛው ወገን በፅሑፍ ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወገን በአስር ቀናት
ውስጥ ለድርድር ይቀርባል፡፡

62
ይህ የኅብረት ስምምነት በባንኩ እና በማህበሩ መካከል ዛሬ ቀን 2013 ዓ.ም ተፈረመ

1. አቶ ሱራ ሳቃታ ም/ፕሬዝደንት የሕግ እና ብድር ማገገሚያ- በባንኩ ወገን----


2. አቶ ኦላኒ ሴቃታ የማህበሩ ፕሬዝደንት- በማህበሩ ወገን --------------------------
3. አቶ ሰይፉ ፀጋዬ ዳይሬክተር የሰዉ ኃይል ትራንዛክሽን- በባንኩ ወገን -----------
4. አቶ አንተነህ ግርማ የማህበሩ ም/ፕሬዝደንት- በማህበሩ ወገን -------------------
5. አቶ ስጦታዉ በላቸዉ ዳይሬክተር የሰዉ ኃይል ዴቬሎፕመንት- በባንኩ ወገን--
6. አቶ ቢኒያም ወ/ሐዋሪያት የማህበሩ ዋና ፀሐፊ- በማህበሩ ወገን ------------------
7. አቶ በፊቃዱ አበራ ዳይሬክተር የሰዉ ኃይል ታለንት አኩዚሽን- በባንኩ ወገን --
8. አቶ ተስፋ ተክሌ የማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ አባል- በማህበሩ ወገን --------------
9. ወ/ሮ ሶስና ዓለማየሁ ዳይሬክተር ኮርፖሬት አድቫይዘሪ- በባንኩ ወገን ----------
10. አቶ አወቀ ስንሻዉ የማህበሩ ኦዲት ሰብሳቢ- በማህበሩ ወገን -------------------
11. አቶ ዳምጠዉ ወ/ተክሌ የድርድሩ ፀሐፊ- ገለልተኛ -----------------------------

63

You might also like