You are on page 1of 4

የአምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር የፐርፎርማንስ ኦዲት ስራ ዕቅድ፣

1. መግቢያ

የንጋት ኮርፖሬት ኦዲትና ኢንስፔክሽን በ 2022 እ.አ.አ በጀት ዓመት የሚያከናውናቸውን የኦዲት ስራዎች በማቀድ
እና በንጋት ስራ አመራር ቦርድ በማጸደቅ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ የስራ ክፍሉ በ 2022 እ.አ.አ. በጀት ዓመት በእቅድ
ከያዛቸው ተግባራት ውስጥ አንዱ በአምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር ላይ የፐርፎርማንስ ኦዲት

በማድረግ ኩባንያው የተቋቋመበትን ዓላማ ወጪ ቆጣቢ፣ ብቃት ባለው እና ውጤታማ በሆነ መንገድ እየፈጸመ

መሆኑን ገለልተኛ በሆነ መንገድ በመገምገምና በማረጋገጥ አሉታዊ አፈፃፀሞች ለወደፊቱ እንዲሻሻሉና

እንዳይደገሙ፤ ጥሩ ተሞክሮዎች የበለጠ እንዲጎለብቱና እንዲስፋፉ ለውሳኔ አጋዥ የሚሆን የተደራጀ ሪፖርት
ለንጋት አመራር ማቅረብ የሚል ይገኝበታል፡፡
ስለሆነም የክዋኔ ኦዲት ስራውን ማከናወን እንዲቻል ዝርዝር የኦዲት እቅድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
2. የኦዲቱ ዓላማ፡- ኩባንያው ያከናወናቸዉ ተግባራት ወጪ ቆጣቢ፣ ቀልጣፋና ዉጤታማ በሆነ አሰራር

መከናወናቸውን በክዋኔ /ፐርፎርማንስ/ ኦዲት በመገምገም የሚታዩ የአሰራር ግድፈቶች ካሉ እንዲስተካከሉ

ለማድረግና ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እንዲቻል ለማኔጅመንቱ/ ለባለሀብቱ ውሳኔ አጋዥ የሆኑ አስተያየቶችን

ለማቅረብ ነው፡፡

3. የኦዲት ወሰን፡- ከ 2019 እስከ 2021 እ.አ.አ ድረስ ያለው የኩባንያው የስራ አፈጻጸም ይገመገማል፤
4. የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴ፡
 መረጃዎችን መከለስና መተንተን
 ከኩባንያው ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የጽሁፍና የቃል መጠይቅ ማድረግ፤
 በቦታው ተገኝቶ በአካል የማረጋገጥ /physical verification/ ስራ ይሰራል፡፡
 እንደ አስፈላጊነቱ በፎቶ ግራፍ የማስደገፍ ስራ ይሰራል፤
5. ዝርዝር ተግባራትና የመፈጸሚያ ጊዜ

ፈጻሚ
የሚወስደው የሰው
ተ.ቁ ዝርዝር ተግባራት የመፈፀሚያ ጊዜ
ጊዜ በቀናት ሀይል
ብዛት

የመስክ ጉዞ፤ የቢሮ ዝግጅትና የክዋኔ ኦዲት ስራ የመግቢያ ስብሰባ በማድረግ ትውውቅ 1 4
1 19/06/2022
መፍጠር፤

 በዋና ስራአስኪያጅና በየመምሪያው ያሉ የስራ አፈጻጸም ፋይሎችን /ገቢና ወጪ/


መለየት፤ መከለስ፤ የኦዲት ማስታወሻ መያዝ፤ ማጣራትና መተንተን
2 20-22/06/2022 3 4
 የኩባንያዉን መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም የተቋቋመበትን ዋና
ዋና አላማዎችን መረዳትና መገንዘብ

1
የማኔጅመንት ቃለ-ጉባኤዎችን በማየት ዋና ዋና የውሳኔ አቅጣጫዎችን መለየት፤ 2 4
3 23-24/6/2022
በኦዲት ማስታወሻ መያዝና አፈጻጸማቸውን መገምገም

4 ለኩባንያው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መጠይቆችን ማዘጋጀት፣ ማቅረብ፤ 25/10/2022 1 4


መሰብሰብና መተንተን፤
5 የኩባንያው የግዥ አፈጻጸም ወጪ ቆጣቢ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን 26-27/10/2022 2
መገምገም፤
 የአገር ውስጥ ግዥ አፈጻጸም ወጪ ቆጣቢ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን
ማረጋገጥ፤
 የኩባንያው የውጭ አገር ግዥ ወጪ ቆጣቢ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን
ማረጋገጥ፤
 የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዥዎችን ለማከናወን የሚያስችል የግዥ መመሪያ
መኖሩንና በመመሪያው መሰረት እየተሰራ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዥዎች በጨረታ (በውድድር) የሚፈጸሙ መሆኑን
ማረጋገጥ፤
 የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዥ መጠየቂያ እየቀረበ፤ በሚመለከተው
እየተፈቀደ፤ እየጸደቀ እና እየተረጋገየጠ የሚፈጸም መሆኑን ማረጋገጥ፤
6 የገቢ (ኢምፖርት) ሸቀጦች አቅርቦትና ሽያጭ እንዲሁም የወጪ (ኤክስፖርት) 28-30/06/2022 3 4
ሸቀጦች አቅርቦትና ሽያጭ ወጪ ቆጣቢ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ አሰራር
እየተከናወነ መሆኑን መገምገም፤
 የሸቀጦች ሽያጭ መመሪያን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 የሸቀጦች ሽያጭ በደንበኞች ላይ ቅሬታን በማይፈጥር መንገድ የመፈጸም
መሆኑን ማረጋገጥ፤
 ኩባንያው የአገር ውስጥና የውጭ ገበያ ድርሻውን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ
መሆኑን ማረጋገጥ፤
 የውጭ ምንዛሬ በሚፈለገው መጠንና በወቅቱ እንዲገኝ የሚሰራው ስራ
ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 የተደራጀና ቀልጣፋ የትራንዚትና ሎጂስቲክስ ዶክመንቶች አያያዝ መኖሩን
ማረጋገጥ፤
 ወጪ ቆጣቢ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ የትራንዚትና ሎጂስቲክስ አፈጻጸም
(ፖርትሃንድሊግና ከስተምስ ክሊራንስ) መኖሩን ማረጋገጥ፤

7 የኩባንያው የክምችት (ስቶክ) አስተዳደር ስርዓት ወጪ ቆጣቢ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ 01-02/7/2022 2 4


በሆነ አሰራር እየተከናወነ መሆኑን መገምገም፤
 ሸቀጦች ፈጣን እንቅስቃሴ ያላቸው፤ መካከለኛ እንቅስቃሴ ያላቸው እና
እንቅስቃሴ የሌላቸው በሚል እየተለዩ አስፈላጊው እርምጃ በወቅቱ
የሚወሰድ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 የሸቀጦች የመጠቀሚያ ጊዜ እንዳያልፍ አስፈላጊው ክትትልና ቁጥጥር
የሚደረግ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 ወጪ ቆጣቢ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ የመጋዘን አስተዳደር መኖሩን ማረጋገጥ
(የካይዘን ትግበራ)፤
 የገቢና የወጪ ሸቀጦች ከፍተኛ የዲሜሬጅ እና የስቶሬጅ ወጪ እንዳያስከትሉ

2
ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግ መሆኑን ማረጋገጥ፤

8 የኩባንያው የፋይናንስ አያያዝና አስተዳደር ወጪ ቆጣቢ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ


መሆኑን መገምገም፤
 ከሸቀጦች ሽጭና ከሌሎች ምንጮች የሚያገኘውን ገቢ በወቅቱ የሚሰበስብ
3-4/7/2022 2 4
መሆኑን መገምገም፤
 ተሰብሳቢ ሂሳቦች በወቅቱ የሚሰበሰቡ መሆኑን፤ ተከፋይ ሂሳቦች በወቅቱ
ለሚመለከተው የሚከፈሉ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 በተለያዩ ተቋማት ኢንቨስት ካደረገው ሀብት ተገቢውን ሪተርን እያገኘ መሆኑን
መገምገም፤
 ተገቢውን አሰራር ተከትሎ ወቅታዊ የሆነ የሂሳብ ሪፖርት የሚያቀርብ መሆኑን
ማረጋገጥ፤
 ኩባንያውን ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ጥምርታ
ስታንዳርዶች /Financial Ratio Standards/ ተጠቅሞ ራሱን የሚገመግም
መሆኑን ማረጋገጥ፤
 የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓቱ በኩባንያው የፋይናንስ ማኑዋልና መመሪያ መሰረት
መሆኑን ማረጋገጥ፤
9 የኩባንያው የሰው ሀብት አስተዳደር ስርዓት ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን
መገምገም፤
5-6/7/2022 2 4
 የሰራተኛ ቅጥር፤ ዝውውር፤ የደረጃ እድገት፤ ስንብት ወዘተ መመሪያን ተከትሎ
የሚፈጸም መሆኑን ማረጋገጥ፤
 የሰራተኛውን የስነ-ምግባር ሁኔታ መገምገም፤
 የፐርፎርማንስ ማኔጅመንትና ሌሎች የአፈጻጸም መገምገሚያ ዜዴዎችን
አተገባበር ማረጋገጥ፤
10 የቋሚና አላቂ ንብረቶች አስተዳደርና አጠቃቀም ውጤታማ መሆኑን መገምገም፤
 ኩባንያው በተለያዩ ቦታዎች ያስገነባቸው ህንጻዎች አጠቃቀምና እያስገነባቸው
7-8/7/2022 2 4
ያሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ውጤታማ መሆናቸውን ማረጋገጥ፤
 ቋሚ ንብረቶች ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ማረጋገጥ፤
 የሰርቪስ ተሸከርካሪዎች፤ የቢሮ መገልገያ እቃዎችና ቁሳቁሶች አጠቃቀም
ውጤታማነትን ማረጋገጥ፤
 በስቶር ውስጥ ያሉ ንብረቶች አቀማማጥና አያያዝ በተገቢው መንገድ መሆኑን
ማረጋገጥ፤
 የተሸከርካሪዎች ጥገና፤ የነዳጅ አጠቃቀም ክትትልና ቁጥጥር ስርዓቱ ወጪ
ቆጣቢና ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጥ፡
 የሸቀጦች መያዛ ኮንቴይነሮች አስተዳደር ውጤታማነትን መገምገም፤
11 ኩባንያው የተደራጀና ቀልጣፋ የሆነ የመረጃ አያያዝና ልውውጥ ስርዓት የዘረጋ
መሆኑን መገምገም፡
 በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ስርዓት መኖሩን ማረጋገጥ፤ 09/7/2022 1 4
 የተዘጋጁና የጸደቁ የስራ መመሪያዎች ማለትም የግዥ፤ የንብረትና የሰው ሀብት
አስተዳደር፤ የሽያጭና የማርኬቲንግ እንዲሁም የፋይናንስ አስተዳደር፣ ወዘተ
መመሪያዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ
 ግልጽና ወጥ የሆነ የሪፖርት አቀራረብ ስርዓት መኖሩን መገምገም
12 በኩባንያው የውስጥ ኦዲት ክፍል የሚሰጡ አገልግሎቶች ውጤታማነትን መገምገም 10/7/2022 1 4

3
13 በሕግ አገልግሎት ክፍል የተያዙ ጉዳዮች ውጤታማነትን መገምገም 11/7/2022 1 4
መገምገም (የፍርድ ቤት ክትትል)

14 የተያዙ ማስታወሻዎችን ማጣራት፤ የእውነታዎች ማጠቃለያ ማዘጋጀትና 11-14/7/2022 3 4


መፈራረም
የኦዲት ስራው የሚፈጀው ጠቅላላ ቀናት 26

ማስገንዘቢያ፡-በሰንጠረዡ የተገለጸው ዝርዝር የኦዲት ስራ የሚከናወንባቸው ቦታዎች፤ አዲስ አበባ ዋናው


መ/ቤት፤ ማእከላዊ ቅርንጫፍ፤ ደሴ አብይ ቅርንጫፍ ባህር ዳር እና ጎንደር አብይ ቅርንጫፎች
መሆናቸው ይታወቅ፤

6. ማስፈጸሚያ በጀት

የባለሙያ ውሎ አበል (4 ሰው*ብር 400*26 ቀን = 41,600.00


የባለሙያ የመኝታ ወጪ (4 ሰው*ብር 400*24 ቀን) = 38,400.00
ድምር 80,000.00
7. ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና የመፍትሄ ሀሳቦች
7.1 ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች
 የሚፈለጉ ማስረጃዎች /ሰነዶች/ በሚፈለገው ጊዜ ላይቀርቡ ይችላሉ፤
 ጉዳዩ የሚመለከተው ባለሙያ /ኃላፊ በሚፈለገው ጊዜና ቦታ ላይገኝ ይችላል፤
 የመስክ ስራውን ለማከናወን አስፈላጊው ትራንስፖርት በሚፈለገው ጊዜ ላይገኝ ይችላል፤
7.2 የመፍትሄ ሀሳቦች
 የሚያስፈልጉ ሰነዶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አስቀድሞ ማሳወቅ፤
 ጉዳዩ የሚመለከተው ባለሙያ /ኃላፊ እንዲገኝ ቀድሞ ማሳወቅ፤
 ኩባንያው የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲመደብ አስቀድሞ ማሳወቅ፤

You might also like