You are on page 1of 17

በንጋት ኮርፖሬት የዘለቄታ በጎ አድራጎት

ድርጅት ማዕከል የመዝናኛ ክበብ


አገልግሎት አሰጣጥ ለማጠናከር የተዘጋጀ
መነሻ ሃሳብ

አዘጋጅ ኮሚቴ
አቶ ሙላቱ አበበ-----------------------------
ሰብሳቢ
ወ/ሮ በላይነሽ ወረኛ-------------------------
አባልና ጸሐፊ
አቶ አበባው መኮነን------------------------ አባል
ባህር
ወ/ሮ መልሽው ምህረቴ-------------------- "ኦገስት
አቶ ጌታቸው አስረስ------------------------ "
i|Page
ማውጫ
1. መግቢያ..................................................................................................................................................1
2. አላማ.....................................................................................................................................................1
2.1. አጠቃላይ አላማ................................................................................................................................1
2.2. ዝርዝር አላማዎች.............................................................................................................................1
3. የውሳኔ ሃሳብ ለማዘጋጀት መነሻ የሆኑ ሁኔታዎች...............................................................................................2
4. የካፍቴሪያ አገልግሎቱ በተሟላ ሁኔታ መጀመሩ ያለው ጠቀሜታ...........................................................................2
4.1. ለተቋሙ.........................................................................................................................................2
4.2. ለሰራተኞች......................................................................................................................................3
4.3. ለመረዳጃ ማህበሩ..............................................................................................................................3
5. በተቋሙ ግቢ ውስጥ የተሟላ የካፍቴሪያ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችል የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ የታዩ ጉዳዮች........3
5.1. የተለያዩ ተቋማትን ልምድ መወሰድ.......................................................................................................4
5.2. ንጋት ኮርፖሬት የሻይ ቡና መስተንግዶ ሁኔታ............................................................................................5
5.3. የንጋት ኮርፖሬት የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት የሰራተኞች መረዳጃ ማህበር ሁኔታ.........................................6
5.4. የንጋት ኮርፖሬት ማዕከል የሰራተኞች በካፍቴሪያ እንዲኖር የሚፈለግ አገልግሎት የዳሰሳ ጥናት ውጤት...................6
6. በጥናቱ የተገኘ መልካም ልምድና ተግደሮት......................................................................................................7
6.1. የተገኘው መልካም ልምድ....................................................................................................................7
6.1.1. መዝናኛ ክበቡን አከራይቶ በማሰራት..............................................................................................7
6.1.2. መዝናኛ ክበቡን በተቋሙ ባሉ ማህበራት (መረዳጃ ማህበር) በማሰራት...................................................8
6.2. ያጋጥሙ ተግዳሮቶች..........................................................................................................................8
6.2.1. መዝናኛ ክበቡን አከራይቶ በማሰራት..............................................................................................8
6.2.2. መዝናኛ ክበቡን በተቋሙ ባሉ ማህበራት በማሰራት............................................................................8
7. የኮሚቴው መነሻ የውሳኔ ሃሳብ.....................................................................................................................9
7.1. አማራጭ አንድ ማህበሩ አከራይቶ ቢጠቀምበት.........................................................................................9
7.1.1. የሚኖረው ጠቀሜታ...................................................................................................................9
7.1.2. የሚኖረው ተግዳሮት..................................................................................................................9
7.1.3. ትኩረት የሚሹ ጉዳዩች...............................................................................................................9
7.2. አማራጭ ሁለት በማህበሩ ራሱ ቢጠቀምበት..........................................................................................10
7.2.1. የሚኖረው ጠቀሜታ.................................................................................................................10
7.2.2. የሚኖረው ተግዳሮት.................................................................................................................10
7.2.3. ትኩረት የሚሹ ጉዳዩች.............................................................................................................10
8. አባሪ.......................................................................................................................................................1

ii | P a g e
1. መግቢያ

ንጋት ኮርፖሬት ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር አኳያ ሻይ ቡና በማቅረብ ሰራተኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ
ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬቱ የተከራየው ህንጻ ይህን የሻይ ቡና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ጨምሮ
ለሰራተኛው ለማቅረብ የመዝናኛ ክበቡ አመች በመሆኑ የተቋሙ ሰራተኞች በመወያየት አገልግሎቱን
በተጠናከረ ሁኔታ መስጠት የሚያስችል መነሻ ሃሳብ እንዲቀርብ ኮሚቴ መርጠዋል፡፡

ስለሆነም ኮሚቴው የተለያዩ ተቋማትን ልምድ፣ ከአሁን በፊት የነበረውን የንጋትን የሻይ ቡና መስተንግዶ
ሁኔታ፣ የንጋት ኮርፖሬት የሰራተኞች መረዳጃ ማህበር ሁኔታን በማጥናት የተሻለውን የውሳኔ ሃሳብ መነሻ
የሚሆን አዘጋጅቷል፡፡

2. አላማ
2.1. አጠቃላይ አላማ
የተቋሙን መዝናኛ ክበብ ምቹ በማድረግ፣ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ሰፋ ባለ እና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ
ለሰራተኛው ማቅረብ የሚቻልበትን አመራጭ የውሳኔ ሃሳብ መነሻ ማቅረብ፡፡

2.2. ዝርዝር አላማዎች


1. መዝናኛ ክበብ ለሰራተኞች ምቹ አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
2. በተቋሙ እስካሁን ከሚሰጡ የሻይና ቡና መስተንግዶ በተጨማሪ የምግብ፣ ለስላሳ መጠጦች እና ትኩስ መጠጦች
የሚቀርቡበትን ሁኔታ መፍጠር፣
3. ሰራተኛው የሚፈልገውን አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በጥራትና በአጠረ ጊዜ እንዲያገኝ በማድረግ የተቋሙን
የስራ ስዓት በአግባቡ ተጠቅሞ በስራው ውጤታማ መሆን እንዲችል ለማስቻል፣
4. የሻይና ቡና መስተንግዶ በተደራቢነት የሚሰሩ የተቋሙ ሰራተኞች ሙሉ ጊዜያቸውን በሌሎች የስራ አካባቢን
ምቹ የማድረጉ ስራ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማድረግ፣
5. የተቋሙ ሰራተኞች የመረዳጃ ማህበር በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮና ተጨማሪ የገቢ ምንጭ አግኝቶ የሰራተኛውን
ማህበራዊ ትስስር የበለጠ እንዲጠናከር ለማድረግ፣

3. የውሳኔ ሃሳብ ለማዘጋጀት መነሻ የሆኑ ሁኔታዎች


1. ግቢው ሰፊና የካፍቴሪያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሰፊ የካፍቴሪያ ህንጻ ያለው መሆኑ፣
2. ንጋት ለሠራተኛው በእረፍት ስዓት የሻይና ቡና መስተንግዶ በተቋሙ የሚቀርብ መሆኑ፣
3. አዲስ በኪራይ የተገባበት ህንጻ ከከተማው መዕከል የራቀ በመሆኑ የምሳ ሥዓትን በቢሮ ግቢ ለሚቆዩ ሠራተኞች
የሻይ ቡና እና የምሳ አገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣

1|Page
4. በተቋሙ የለውን የሠራተኞች የመረዳጃ ማህበር አሁን ካለው በተሻለ የሰራተኛውን ማህበራዊ ትስስር የበለጠ
አጠናክሮ እንዲሰራ ማድረግ በማስፈለጉ፣
5. በንጋት የሚቀርበው የሻይ እና ቡና አገልግሎት በተደራጀ ካፍቴሪያ ሆኖ ለዚህ አገልግሎት የሚሰማሩ ሠራተኞች
በሌሎች የተቋሙ ስራ ላይ የበለጠ ተጠናክረው እንዲሰሩ ማድረግ ጥሩ አማራጭ በመሆኑ፤

4. የካፍቴሪያ አገልግሎቱ በተሟላ ሁኔታ መጀመሩ ያለው ጠቀሜታ


4.1. ለተቋሙ
1. ሰራተኛው በስራ ቦታ ላይ የሚፈልጋቸውን የካፍቴሪያ አገልግሎት እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር
የስራ ስዓቱን በተሟላ ሁኔታ በመጠቀም የተቋሙን ግቦች የሚያሳኩ ተግባራት ላይ የበለጠ ትኩረት
እንዲያደርግ ያደርገዋል፣
2. በሻይ እና በምሳ ስዓት ሠራተኛው በስፋት እንዲገኛኝ በማድረግ ማህበራዊ መስተገብሩ እንዲጎለበት፤
በስራ እና በተቋሙ ጉዳይ እንዲወያይ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤
3. ሰራተኛው በአቅራቢያው የሚፈልገውን አገልግሎት አገኝቶ የእረፍት ስዓቱን በአግባቡ ዘና ብሎ
እንዲያሳልፍ፤ በውስጥ በሚቀርብ አገልግሎት ደህንነቱ እንዲጠበቅ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል በዚህም
ተቋሙ ውጤታማነት ይጨምራል፣
4. በተቋሙ የካፍቴሪያ አገልግሎት መጀመሩ ለሌሎች የስራ እድል መፍጠር ያስችለዋል፣

4.2. ለሰራተኞች
1. የሚፈልጉትን አገልግሎት በቅርበት በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ማግኘት ያስችለዋል፣
2. ትኩስ ምግብ መመገብ እና ጤናማ አምራች እንዲሆን ያደርገዋል፣
3. የስራ ሰዓት ሳያባክን ሙሉ የስራ ስዓቱን ስራ ላይ እንዲያሳልፍ ያደረገዋል፣
4. በሻይ ቡና፣ በምሳ ስዓት በከፌው በሚኖረው ቆይታ የሰራተኛውን ማህበራዊ ግንኙነት የበለጠ
እንዲያጠናከር ያደርገዋል፣

4.3. ለመረዳጃ ማህበሩ

1. የሰራተኛውን ማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክርበት አንዱ መንገድ አድርጎ ይጠቀምበታል፣


2. የማህበሩን ገቢ ለማሳደግ አማራጭ የገቢ ምንጭ ሆኖ ያገለግለዋል፣
3. ሰራተኛው እርስ በርስ በማማር እና የመተጋገዝ ባህሉን በማሳደግ አንድነቱን በማጠናር የማህበሩን አላማ
ያሳካል፡፡

2|Page
5. በተቋሙ ግቢ ውስጥ የተሟላ የካፍቴሪያ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችል

የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ የታዩ ጉዳዮች


 የተለያዩ ተቋማትን ልምድ መወሰድ፡
 ከአሁን በፊት የነበረውን የንጋትን የሻይ ቡና መስተንግዶ ሁኔታ ማየት፡
 የንጋት የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት ባህር ዳር የሰራተኞች መረዳጃ ማህበር ሁኔታ፡
 የባህር ዳር ንጋት ሰራተኞች የካፍቴርያ አገልግሎቶች የፍላጎት መረጃ ማሰባሰብ፡

ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች የተገኘው ውጤት ወይም በእይታው የተገኘው መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፤

5.1. የተለያዩ ተቋማትን ልምድ መወሰድ


እንደ ንጋት በእረፍት ስዓት ለሠራተኛው የሚቀርበው የሻይ እና ቡና አቅርቦት ራሱን ችሎ በተቋቋመ ካፍቴሪያ

ሲሆን አተገባበሩ ከዚህ በፊት ይፈጸምበት ከነበረው የተለየ በመሆኑ በባህር ዳር ከተማ ያሉ መሰል ተቋማት ላይ

ያለውን ተሞክሮ መውሰድ የግድ ሆኖአል፡፡ ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችል ቼክሊስት በማዘጋጀት ከ 5

የልማት ድርጅቶች እና ከ 3 የመንግስት ተቋማት ውስጥ ተሞክሮ የማሰባሰብ ስራ ተሰርቷል፡፡

የእያንዳንዱን ተቋማት የካፍቴሪያ ግልጋሎት ተሞክሮ በስራ ቦታ ያለን ካፍቴሪያ ህንጻ እና ቁሳቁስ
የሚጠቀሙበት መንገድ፤ በካፍቴሪያው የሚያቀርቡ አገልግሎቶች፣ ተቋማቱ ለካፍቴሪያው የሚሰጡት
ድጋፍ በአጭር ተጠቃሎ ሲታይ በሚከተለው ሠንጠረዥ የቀረበ ሲሆን ዝርዝር ጉዳዮች ደግሞ በአባሪ
ተቀምጧል፡፡

ሠንጠረዥ 1፡ አጠቃላይ የእያንዳንዱን ተቋማት ተሞክሮ በዋና ዋና ጉዳዮች

ተ.ቁ ልምድ የተገኘባቸው መዝናኛ ክበብ ውን የሚጠቀሙበት የሚያቀርቧቸው አገልግሎቶች ተቋሙ ለመዝናኛ ክበብ ምርመራ
ተቋማት መንገድ የክትትልና ቁጥጥር ሁኔታ ው ያው የሚያደርገው
ድጋፍ
በተቋሙ በኪራይ በመረዳጃ/ ትኩስ ምግብ ለስላሳ በገንዘብ በአይነት
ሰራተኛ ነገሮች መጠጠች
ማህበር
1 አህስኮድ √ √ √ √ √ √ በጨረታ
2 አውስኮድ √ √ √ √ √ √ በጨረታ
3 አዲቁድ √ √ √ √ √ በጨረታ
4 አመልድ √ √ √ √ √ √ መረዳጃ
ማህበሩ

3|Page
5 አማራ ፓይፕ √ √ √ √ √ √ √ በጨረታ

መገጣጠሚያ
6 የአ/ብ/ክ/መ ት/ት ቢሮ √ √ √ √ √ √ በጨረታ
7 የአ/ብ/ክ/መ/ሲ/ሰ ቢሮ √ √ √ √ √ በጨረታ
8 የአ/ብ/ክ/መ/ዋ/ኦ/ ቢሮ √ √ √ √ √ መረዳጃ
ማህበሩ
ማብራሪያ፡- ከላይ በሰንጠረዡ በኪራይና በመረዳጃ ማህበሩ በሚል ምልክት የተደረገበት ሁኔታ ምንም
እንኳን መዝናኛ ክበቡን አከራይተው የሚጠቀሙበት ቢሆንም መረደጃ ማህበራቸውም ከኪራይ ገቢ
እና ከመከታተልና ከመቆጣጠር አኳያ ድርሻ ስላለው የተቀመጠ መሆኑ ይታወቅ፡፡

ከላይ በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሰረት 6 ተቋማት መዝናኛ ክበቡን በማከራየት እና ገቢው ለሰራተኛ መረደጃ ማህበር
እንዲሆን፣ 2 ተቋማት ደግሞ ገቢውንም የማስተዳደር ስራውንም ሙሉ በሙሉ በሰራተኛ ማህበሩ/መረዳጃ ሆኖ
እንዲመራ አድርገዋል፡፡ ሁሉም ተቋማት መዝናኛ ክበብ ውን በማከራየት አገልግሎት እንዲሰጥ ቢያደርጉም ቋሚ
እቃዎችን (ፍሪጅ፣ ወንበር፣ጠረጴዛ፣ ሰቶቭ ወዘተ) እና መብራትና ውሃ በተቋማት የሚሸፈን መሆኑን አይተናል፡፡

ሰራተኛ/መረዳጃ ማህበር የሚያስተዳድሩት ተቋማት የፋይናንስና የንብረት ምንጫቸው ተቋማቱ ሲሆኑ አመልድ መነሻ
መንቀሳቀሻ ካፒታል እና አማራ ፓይፕ ደግሞ የምግብ ክፍያ እንደሚከፍል አይተናል፡፡ በአጠቃላይ ከተቋማቱ የተገኘው
ልምድ የመዝናኛ ክበብ ስራ በውስጥ አቅምም ተሰራ በውጭ አካላት በጣም ጠንካራ የማኔጅመንት ስራ የሚጠይቅ
መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

5.2. ንጋት ኮርፖሬት የሻይ ቡና መስተንግዶ ሁኔታ

ንጋት ኮርፖሬት የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት ባለፉት አመታት ጀምሮ የሻይና ቡና መስተንግዶ በራሱ ወጭ
ለሰራተኞቹ እያቀረበ ያለ ሲሆን በዚህም ከአማራ ፓይፕ በመቀጠል ከሌሎች ተቋማት የተሻለ ልምድ ያለው
መሆኑን ተመልክተናል፡፡ በዚህ የሰራተኛ ደመወዝን ሳይጨምር ለሻይ ቡና ብቻ ብር 67,729.86 በላይ በየአመቱ
ወጭ ያደርጋል፡፡

ስለሆነም አሁን ያለው የካፍቴሪያ ቦታ ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ምቹ በመሆኑ ቢያንስ
ለሻይና ቡና የሚያወጣው ወጭ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዚሁ አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞች በሌሎች ስራዎች
ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ትኩረት እንዲያደርጉ አድርጎ እና የማስተዳደር ስራውን
ከተቋሙ ውጭ ማድረግ የተሻለ እንደሆነ ከሌሎች ተቋማት የተገኘው ልምድ ያሳያል፡፡ ኮሚቴውም ይህ
አማራጭ የተሻለ መሆኑን በጥናቱ ባገኘው ልምድና ተሞክሮ ለመገንዘብ ችለናል፡፡

በተቋሙ ውስጥ ለመዝናኛ ክበቡ አገልግሎት የሚሰጡ ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ የሻያና ቡና ሰኒ፣ ስቶቭ የመሳሰሉት
ንብረቶች ያሉት ሲሆን ተጨማሪ የሚያስፈልጉ ንብረቶች ማሟላት የሚጠበቅ ይሆናል፡፡

4|Page
5.3. የንጋት ኮርፖሬት የዘለቄታ በጎ አድራጎት ድርጅት የሰራተኞች መረዳጃ ማህበር ሁኔታ
የንጋት ኮርፖሬት የዘለቄታ በጎ አድራት ድርጅት የሰራተኞች መረዳጃ ማህበር 90 አባላት ያሉት ሲሆን
ከእያንዳንዱ ሰራተኛ ብር 30 ወርሃዊ መዋጮ በአመት ብር 32,400 በመሰብሰብ ለሰራተኛውም በሃዘን፣
በደስታ (ለጋብቻ፣ ወላድ መጠየቅ፣ ምረቃ፣ ሽኝት) ፣ በችግር (ጡረታ ሲወጣ፣ ከፍተኛ ህመም/አዳጋ
ሲያጋጥም፣ ከስራ ሲታገድ) በመተደዳደሪያ ደንቡ በተቀመጡ የዝምድና ሐረጋትና አሰራር መሰረት ድጋፍ
ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህ ፕሮፖዛል በሚሰራበት ወቅት ከወጭ ቀሪ ብር 107,000 አለው፡፡

ሆኖም ማህበሩ ከዚህ ቀደም ከሚሰጠው አገልግሎት በተጠናከረ ሁኔታ ስራውን እንዲሰራ እና የሰራተኛውን
ማህበራዊ ትስስር የበለጠ ለማጠናከር የአባላት መዋጮ ከማሻሻል ጀምሮ ተጨመሪ ገቢ የሚያገኝባቸውን
አማራጮችን ማየት ተገቢ ነው፡፡ ከዚህም አንዱ የተቋሙን የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት በበላይነት
በማስተዳደር ገቢ እንዲያገኝ ማድረግ አንዱ ነው፡፡

5.4. የንጋት ኮርፖሬት ማዕከል የሰራተኞች በካፍቴሪያ እንዲኖር የሚፈለግ አገልግሎት የዳሰሳ

ጥናት ውጤት

ኮርፖሬቱ በማዕከሉ ጠቅላላ 90 የስራ መሪዎችና ሰራተኞች ያሉት ሲሆን በተለያዩ የስራ ምክኒያቶች ከስራ ቦታ
የለሉትን ሳይጨምር ለ 54 ሰራተኞች መጠይቁ ተበትኖ በመዝናኛ ክበብ አጠቃቀም ዙሪያ ያላቸውን ፍላጎት ለማዎቅ
ዳሰሳ ጥናት ተደርጓል፡፡ መጠይቁ ከተበተነላቸው ውስጥ ወንድ 28 ሴት 17 በድምሩ 45 ሰራተኞች ማለትም 83 በመቶ
መጠይቁን ሞልቶ መልሰዋል፡፡

በመጠይቁን እንዲሞሉ የተሰጣቸው ሰራተኞች በደመወዝ መጠን ሲታይ ደግሞ፡-

ተ.ቁ የደመወዝ መጠን ወ ሴ ድ


1 2000-5000 2 9 11
2 5001-8000 2 4 6
3 8001-15000 17 6 23
4 ከ 15000 በላይ 4 1 5
ጠ/ድምር 45

በኮርፖሬቱ ውስጥ ከሚሰሩ እና መጠይቁን ከሞሉት ሰራተኞች ውስጥ በተቋሙ የደመወዝ እርከን እና በኮሚቴው
በወጣው ደረጃ መሰረት 24 በመቶ የሚሆኑት ከ 2000 እስከ 5000፣ 13 በመቶ ከ 5001 እስከ 8000፣ 52 በመቶ
ከ 8001 እስከ 15000 እና 11 በመቶ ደግሞ ከ 15000 በላይ ናቸው፡፡

መጠይቁ ከሞሉት ውስጥ 97 በመቶ በመዝናኛ ክበብ ው የሚሰጡ አገልግሎቶችን የመጠቀም ፍላጎት ያላቸው
መሆኑን የገለጹ ሲሆን 3 በመቶው ደግሞ ፍላጎት የሌላቸው መሆኑን ገልጻዋል፡፡

5|Page
በመዝናኛ ክበቡ እስካሁን ይቀርቡ ከነበሩ ትኩስ መጠጦች በተጨማሪ በትእዛዝ የሚዘጋጁ እና ለብልሽት
የማይዳረጉ ቁርሳና ምሳ አቅርቦቶች እንዲሁም ለስላሳ መጠጦች እንዲቀርቡ ሁሉ ሰራተኛ ይፈልጋል፡፡

አገልግሎቱም በተመጣጠኝ ዋጋ እና በጥራት መቅረብ የሚኖርበት መሆኑን ገልጸው ካፌውን የሚያስተዳድረው


አካል ደግሞ መረዳጃ ማህበሩ ቢሆን ያሉት 22 ሰራተኞች ማለትም 48 በመቶ፣ ለውጭ ተከራይ 14 ሰራተኞች
ማለትም 32 በመቶ እና በተቋሙ በነበረው ሁኔታ እንዲቀጥል በማለት ደግሞ 9 ሰራተኞች ማለትም 20 በመቶ
ምለሽ ሰጥተዋል፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ አገልግሎቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በጥራት፣ በጠንካራ የሃላፊነት ስሜትና የክትትልና


ቁጥጥር ስርዓት ከተመራ የሰራተኛው በመዝናኛ ክበብ ው የመጠቀም ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

6. በጥናቱ የተገኘ መልካም ልምድና ተግደሮት


6.1. የተገኘው መልካም ልምድ

6.1.1. መዝናኛ ክበቡን አከራይቶ በማሰራት


1. መዝናኛ ክበቡን የማስተዳደር ሙሉ ሃላፊነት ተከራዩ የሚወስድ መሆኑና ይህን መዝናኛ ክበብ
በማስተዳደርን ለመዝናኛ ክበብ ው የሚያስፈልገውን አስቤዛ ለመግዛት የሚባክነውን ጊዜ
በመቆጠብ የሰራተኛውን የስራ ጊዜ የማይሻማ መሆኑ፣
2. ለመዝናኛ ክበብ ው አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ለመግዛት ወይም ለማሟላት የሚወጣዉን
ወጭ የመቀነስ፣
3. ለመዝናኛ ክበቡን አገልግሎት የሚውሉ የተቋማችን ንብረቶች ከብክነት እና ከመሰበር በአግባቡ
ተጠብቀው ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ የሚያስችል በመሆኑ፣
4. የመረዳጃ ማህበሩን ሙሉ ለሙሉ ሊመጣ ከሚችል ኪሳራ የሚያድን በመሆኑ፣
5. ተቋማቱ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች እና የመብራት እና ውሃ ወጭ የሚሸፍን በመሆኑ ለሰራተኛው
በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ መሆኑ፣
6. ሌሎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉ፣
7. ከመዝናኛ ክበብ የኪራይ ገቢ የሚገኝ መሆኑ፣

6.1.2. መዝናኛ ክበቡን በተቋሙ ባሉ ማህበራት (መረዳጃ ማህበር) በማሰራት

1. ለሰራተኛው በተሻለ ጥራትና ዋጋ አገልግሎቶችን ማቅረብ እና የሰራተኛው እርካታ በተሻለ

መልኩ ማምጣት መቻሉ፣

2. ተቋማቱ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች እና የመብራት እና ውሃ ወጭ የሚሸፍኑ በመሆኑ ለሰራተኛው


በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ መሆኑ፣
3. ሌሎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉ፣

6|Page
4. ማህበራቱ/ኮሚቴው በቁርጠኛነትና በሃላፊነት ስሜት ከሰራ የተሻለ ትርፍ የሚያስገኝ መሆኑ፣

6.2. ያጋጥሙ ተግዳሮቶች

6.2.1. መዝናኛ ክበቡን አከራይቶ በማሰራት


1. አገልግሎቶች በሚፈለገው ጥራትና ዋጋ ለሰራተኛው ያለመቅረብ፣
2. ሰራተኛው በሚፈለገው ቁጥር የሚጠቀም አለመሆኑ፣
3. የመዝናኛ ክበብ ለውጭ ተጠቃሚዎች አመች ባለመሆኑ ተጨማሪ ገበያ ባለመኖሩ በየጊዜው ተከራዮች
መልቀቅ፣
4. በየወቅቱ ባለው የገበያ መናር ምክንያት የወጋ ይሻሻልልኝ ጥያቄዎች ከተከራዩ መነሳት፣

6.2.2. መዝናኛ ክበቡን በተቋሙ ባሉ ማህበራት በማሰራት


1. ከመደበኛ ስራ በተጨማሪ የሚሰራ ስራ በመሆኑ ስራውን በማስተዳርና በመምራት ውጤታማ ማድረግ
የማይቻል መሆኑ፣
2. ሁሉም የኮሚቴው አበላት ለስራው እኩል በባለቤትነትና በሃላፊነት ስሜት ፣
3. የፋይናንስና ሃብት ብክነት መኖሩ፣
4. በየወቅቱ ያለው የገበያ መኖር፣

7. የኮሚቴው መነሻ የውሳኔ ሃሳብ


7.1. አማራጭ አንድ ማህበሩ አከራይቶ ቢጠቀምበት
7.1.1. የሚኖረው ጠቀሜታ
1. መዝናኛ ክበቡን የማስተዳደር ሙሉ ሃላፊነት ተከራዩ የሚወስድ ስለሆነ የሰራተኛውን የስራ ጊዜ
የማይሻማ መሆኑ፣
2. ለመዝናኛ ክበቡን አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ለመግዛት የሚወጣዉን ወጭ መቀነስ
የሚያስችል መሆኑ፣
3. የመረዳጃ ማህበሩን ሙሉ ለሙሉ ሊመጣ ከሚችል ኪሳራ የሚያድን በመሆኑ፣
4. በተቋማችን ያሉ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች እና የመብራት እና ውሃ ወጭ አከራዩ ስለሚሸፍን
ተከራዩ አገልግሎቶችን ለሰራተኛው በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብበት እድል ስለሚኖረው፣
5. ሌሎች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑ፣
6. ከመዝናኛ ክበቡ የኪራይ ገቢ የሚገኝ መሆኑ፣

7.1.2. የሚኖረው ተግዳሮት


1. አገልግሎቶች በሚፈለገው ጥራትና ዋጋ ለሰራተኛው ያለመቅረብ፣
2. ሰራተኛው በሚፈለገው ቁጥር ላይጠቀም ስለሚችል ተከራዩ አዋጭ አይደለም በሚል በየጊዜው
የመልቀቅ ሁኔታ የሚያጋጥም መሆኑ፣

7|Page
3. በየወቅቱ ባለው የገበያ መናር ምክንያት የዋጋ ይሻሻልልኝ ጥያቄዎች ከተከራዩ መነሳት፣

7.1.3. ትኩረት የሚሹ ጉዳዩች


1. ተከራዩ አገልግሎቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንዲችል በጨረታ እና በውል
አያያዝ ወቅት ማሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች ማለትም የግብዓቶ አቅርቦት ጥራት፣
ሊያሟላቸው የሚገቡ ማቴሪያሎችና የሰው ሃይል ፣ ለሚያቀርባቸው አገልግሎቶች የሚከፍል
መነሻ ዋጋ፣ የኪችንና የመመገቢያ እቃዎች ንጽህና አጠባበቅ ወዘተ በቅድሚያ በዝርዝርና
በትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲታዩ ማድረግ፣
2. የመዝናኛ ክበቡን አጠቃቀም፣ የአቅርቦት ጥራት እና በአከራይና ተከራይ መካከል ሰለሚኖረው
ግንኙነት በትኩረት የሚሰራ ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ኮሚቴ መቋቋም፣

7.2. አማራጭ ሁለት በማህበሩ ራሱ ቢጠቀምበት


7.2.1. የሚኖረው ጠቀሜታ

1. ማህበሩንና የመዝናኛ ክበቡን በተመለከተ ጠንካራ እና የባለቤትነት ስሜት የሚሰማቸው

ሰራተኞች በኮሚቴው እንዲካተቱ ከተደረገ እና በአሰራር ስርዓት በአግባቡ ከተመራ ለሰራተኛው

በተሻለ ጥራትና ዋጋ አገልግሎቶችን በማቅረብ የሰራተኛው እርካታ በተሻለ መልኩ ማምጣት

የሚያስችል መሆኑ፣

2. ማህበራቱ/ኮሚቴው በቁርጠኛነትና በሃላፊነት ስሜት ከሰራ ከኪራይ ገቢው በተሻለ ሁኔታ

ተጨማሪ ገቢ ሊያስገኝ የሚችል መሆኑ፣

3. ተቋማቱ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች እና የመብራት እና ውሃ ወጭ የሚሸፍኑ በመሆኑ ለሰራተኛው


በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ይቻላል፣
4. ሰራተኛው የመዝናኛ ክበቡን በተመለከተ የተሻለ የባለቤትነት ስሜት የሚፈጥር መሆኑ፣

5. ከኮሚቴው ባለፈ የእለት ከእለት የመዝናኛ ክበቡን ስራ የሚያከናውኑ ቋሚ ሰራተኞች የሚቀጥር

በመሆኑ ለሌሎች የስራ እድል መፍጠር ያስችላል፣

7.2.2. የሚኖረው ተግዳሮት


1. ከመደበኛ ስራ በተጨማሪ የሚሰራ እና ስራው ውስብስብ በመሆኑ ስራውን በማስተዳርና በመምራት
ውጤታማ ለማድረግ የማይቻል መሆኑ፣
2. ሁሉም የኮሚቴው አበላት ለስራው እኩል በባለቤትነትና በሃላፊነት ስሜት ያለመስራት፣
3. መነሻ የስራ ማሰኬጃ ገንዘብ እጥረት፣
4. ማህበሩ የሰራተኞች የመዝናኛ ክበብ ስራ ላይ ልምድ የለለው በመሆኑ ስራውን አስቸጋሪ ሊያደርገው
ይችላል፡

8|Page
5. የፋይናንስና ሃብት ብክነት ሊያጋጥም የሚችል መሆኑ፣
6. በየወቅቱ የሚያጋጥመው የገበያ አለመረጋጋትና መናር፣

7.2.3. ትኩረት የሚሹ ጉዳዩች


1. ጠንካራ፣ የባለቤትነት እና ሃላፊነት ስሜት ያላቸው የአስተዳደርና የክትትልና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲኖረው
ማድረግ፣
2. በየጊዜው የሌሎችን ተቋማት ልምድና ነባራዊ ሁኔታውን እየተገነዘቡ መምራት ይጠበቃል፣
3. አማረጭ የገንዘብ ምንጮችን በማፈላለግ የስራ ማስኬጃ እጥረትና ሰራተኛው በተሻለ ዋጋ ተጠቃሚ
የሚሆንበትን የድጎማ ስርዓት እንዲኖር ማድረግ፣
4. ከውስጥ ደንበኛው በተጨማሪ የውጭ ደንበኞችን መሳብ የሚያስችል የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር
ማድረግ፣

የኮሚቴው ምክረ ሃሳብ

መዝናኛ ክበቡ በሁለቱም አማራጮች አገልግሎት ቢሰጥ ሰራተኛውን ለማበረታታት፣ እርካታውን ለመጨር እና
በመዝናኛ ክበቡ የተሸለ ተጠቃሚ መሆን እንዲችል ተቋሙ ከሻይ ቡና በተጨማሪ የምግብ ድጎማ የሚያደረግት ሁኔታ
ቢኖር መልካም ነው፡፡

የኮሚቴው ውሳኔ

በአጠቃላይ ከላይ በተቀመጡት አማራጫ የውሳኔ ሃሳብ መነሻዎች መሰረት እና ከተለያዩ ተቋመት ከተገኘው ልምድ
አኳያ የሰራተኛ መዝናኛ ክበቡን መረዳጃ ማህበሩ የሚከታተለውና የሚቆጣጠረው ሆኖ ለውጭ ተከራዮች በጨረታ
አወዳድሮ አገልግሎት እንዲሰጥ ቢደረግ እና የክራዩ ገቢው ለማህበሩ እንዲሆን በሚል ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ መነሻውን
ያቀርባል፡፡

9|Page
8. አባሪ
ተሞክሮ የተወሰደባቸው ተቋማት ዝርዝር መረጃ

1. አማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት(አህስኮድ)


 ይህ ተቋም መዝናኛ ክበብ የሚጠቀምበት ሁኔታ ለውጭ አካላት አከራይቶ ሲሆን የሚሰጠውን
አገልግሎት በመከታተልና በቆጣጠር እንዲሁም የኪራዩ ገቢ የመረዳጃ ማህበሩ የሚመለከት ነው፡፡
 መዝናኛ ክበብ ውን የሚሰራበት ድርጅት ጨረታ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን ከተቋሙም ቋሚ እቃዎች
ማለትም ፍሪጅ፣ የሻይ ማሽን፣ ወንበር ጠረጴዛ፣ በተቋሙ የነበሩ የመስተንግዶ እቃዎች በሙሉ
እንዲሁም የመብራትና የውሃ ወጭ ተሸፍኖለቸዋል፡፡
 በጨረታ ወቅት የሚቀርቡ አገልግሎቶችን መነሻ ዋጋ በድርጅቱ ቀርቦላቸው ከመነሻ ዋጋው በታች የሞሉ
እና በቀረበው ዝርዝር መሰረት በአጠቃላይ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረቡ ተጫራቾች እንዲያሸንፉ ተደርጓል፡፡
 የሰራተኛው በመዝናኛ ክበብ ው ከትኩስ መጠጦች ውጭ የመጠቀም ልምዱ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
 በተቋሙ ያሚኖሩ ማንኛውንም ዝግጅቶች አቅርቦት ያቀርባሉ፡፡ የክፍያ ሁኔታ ለተቋማት ሃላፊዎች ከሆነ
በየወሩ ለሰራተኞች ደግሞ በየቀኑ ገንዘቡ ይሰበሰባል፡፡
 የመዝናኛ ክበብ ው የክራይ ዋጋ ብር 2000 ነው፡፡
2. የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት(አውስኮድ)
 ይህ ተቋማ መዝናኛ ክበብ ን የሚጠቀምበት ሁኔታ ለውጭ አካላት አከራይቶ ሲሆን የሚሰጠውን
አገልግሎት በመከታተልና በቆጣጠር እንዲሁም የኪራዩ ገቢ የመረዳጃ ማህበሩ የሚመለከት ነው፡፡
 መዝናኛ ክበብ ውን የሚሰራበት ድርጅት ጨረታ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን ከተቋሙም ቋሚ እቃዎች
ማለትም ፍሪጅ፣ የሻይ ማሽን፣ ወንበር ጠረጴዛ፣ በተቋሙ የነበሩ የመስተንግዶ እቃዎች በሙሉ
እንዲሁም የመብራትና የውሃ ወጭ ተሸፍኖለቸዋል፡፡
 በጨረታ ወቅት በቀረበው የምግብ ዝርዝር መሰረት በአጠቃላይ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረቡ ተጫራቾች
እንዲያሸንፉ ተደርጓል፡፡
 የሰራተኛው በመዝናኛ ክበብ ው ከትኩስ መጠጦች ውጭ የመጠቀም ልምዱ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
 በተቋሙ ያሚኖሩ ማንኛውንም ዝግጅቶች አቅርቦት አያቀርቡም፡፡ የክፍያ ሁኔታ ለተቋማት ሃላፊዎች
ከሆነ በየወሩ ለሰራተኞች ደግሞ በየቀኑ ገንዘቡ ይሰበሰባል፡፡
 የመዝናኛ ክበብ ው የክራይ ዋጋ ብር 2000 ነው፡፡
3. የአማራ ዲዛይን ቁጥጥር ድርጅት
 ይህ ተቋማ መዝናኛ ክበብ ን የሚጠቀምበት ሁኔታ ለውጭ አካላት አከራይቶ ሲሆን የሚሰጠውን
አገልግሎት በመከታተልና በቆጣጠር እንዲሁም የኪራዩ ገቢ የመረዳጃ ማህበሩ የሚመለከት ነው፡፡
 መዝናኛ ክበብ ውን የሚሰራበት ድርጅት ጨረታ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን ከተቋሙም ቋሚ እቃዎች
ማለትም ፍሪጅ፣ የሻይ ማሽን፣ ወንበር ጠረጴዛ፣ በተቋሙ የነበሩ የመስተንግዶ እቃዎች በሙሉ
እንዲሁም የመብራትና የውሃ ወጭ ተሸፍኖለቸዋል፡፡

1|Page
 በጨረታ ወቅት የሚቀርቡ አገልግሎቶችን መነሻ ዋጋ በድርጅቱ ቀርቦላቸው ከመነሻ ዋጋው በታች
መሙላት አይቻልም ምክኒያቱ ተጫራቹ በብዛት ተጠቃሚ የሌላቸውን አቅርቦቶች ሞልቶ አሸናፊ
እንዳይሆንና ስራ እንዳይበደል በማሰብ፣
 አብዛኛው ሰራተኛው በመዝናኛ ክበብ ው የመጠቀም ልምዱ የተሻለ ነው፡፡
 በተቋሙ ያሚኖሩ ማንኛውንም ዝግጅቶች አቅርቦት ያቀርባሉ፡፡ የክፍያ ሁኔታ ለተቋማት ሃላፊዎች ከሆነ
በየወሩ ለሰራተኞች ደግሞ በየቀኑ ገንዘቡ ይሰበሰባል፡፡
 የመዝናኛ ክበብ ው የክራይ ዋጋ ብር 1000 ነው፡፡
4. አመልድ
 ይህ ተቋማ መዝናኛ ክበብ ን የሚጠቀምበት ሁኔታ በመረዳጃ ማህበሩ ሲሆን የሚሰጠውን አገልግሎት
በመከታተልና በቆጣጠር እንዲሁም ሰራኞችን በቅጠር እን አቅርቦቶችን በማቅረብ የመረዳጃ ማህበሩ
የሚመለከት ነው፡፡
 መዝናኛ ክበብ ው የሚመሩ ሰራተኞች ቋሚ ተቀጣሪ ያለውና የራሱ አደራጀጀት አለው፡፡ የሰው ሃይልም
ስራ አስኪያጅ፣ ሸፍ፣ ረዳት ሸፍ፣ ካሸር፣ 2 አስተናጋጅ እና የጀበና ቡና ሰራተኛ አላቸው፡፡ ለሰራተኞችም
ከብር 1200 እሰከ ብር 3500 ድረስ ይከፍላሉ፡፡
 መዝናኛ ክበብ ውን የሚሰራበት እቃዎች በሙሉ፣ የካፍተሪ እድሳት ወጭ እና መነሻ ካፒታል በድጋፍ
መልክ ከድርጅት የተበረከተላቸው ሲሆን በአጠቃላይ ከብር 600000 በላይ ወጭ ተደርጎላቸዋል፡፡
የመብራትና የውሃ ወጭ ይሸፈንላቸዋል፡፡
 ለሰራተኛው የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ዋጋ ተመን ጥናት በማድግ በማህበሩ በኩል ተቀምጧል፡፡ ለውጭና
ለውስጥ ሰራተኛም መተለያየ ዋጋ ተቀምጧል፡፡
 ከ 300 በላይ ሰራተኛ ያለ ሲሆን አብዛኛው ሻይ ቡና፣ 50% የሚሆነው ምግብ በመዝናኛ ክበብ ው
የመጠቀም ልምዱ አለው ነው፡፡ የውጭ ደንበኛም ይጠቀማል፡፡
 በተቋሙ ያሚኖሩ ማንኛውንም ዝግጅቶች አቅርቦት ያቀርባሉ፡፡ የክፍያ ሁኔታ ለተቋማት ሃላፊዎች ከሆነ
በየወሩ ለሰራተኞች ደግሞ በየቀኑ ገንዘቡ ይሰበሰባል፡፡
 ካፌውን የማስተዳደርና የመምራት ጉዳይ በጣም አስቸጋሪና ከተጨማሪ ስራ ጋር የሚሄድ ባለመሆኑ
በቀጣይ ሌላ አማራጭ ሊያሱቡ እንደሚችሉ ተረድተናል፡፡
5. አማራ ፓይፕ
1. ይህ ተቋማ መዝናኛ ክበብ ን የሚጠቀምበት ሁኔታ ለውጭ አካላት አከራይቶ ሲሆን የሚሰጠውን
አገልግሎት በመከታተልና በቆጣጠር የሰራተኛ ማህበሩ የሚመለከት ነው፡፡
2. መዝናኛ ክበብ ውን የሚሰራበት ድርጅት ጨረታ እንዲገባ የተደረገ ሲሆን ከተቋሙም ቋሚ እቃዎች
ማለትም ፍሪጅ፣ የሻይ ማሽን፣ ወንበር ጠረጴዛ፣ በተቋሙ የነበሩ የመስተንግዶ እቃዎች በሙሉ
እንዲሁም የመብራትና የውሃ ወጭ ተሸፍኖለቸዋል፡፡
3. በጨረታ ወቅት በቀረበው የምግብ ዝርዝር መሰረት በአጠቃላይ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረቡ ተጫራቾች
እንዲያሸንፉ ተደርጓል፡፡ የሚያቀርቧቸውን የምግብ ዝርዝር የተመረጡና የተወሰኑ ናቸው፡፡

2|Page
4. አብዛኛው ሰራተኛው በመዝናኛ ክበብ ው የመጠቀም ልምዱ የተሻለ ነው፡፡ ምክንያም ሰራተኛው 600
ብር የምግብ አበል ያለው በመሆኑ ነው፡፡ በቀጣያም 75% በተቋሙ 25% በሰራተኛው ተሸፍኖ
ተጠቃሚ እንዲሆን ውሳኔ ላይ የተደረሰ እና ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ነው፡፡
5. በተቋሙ ያሚኖሩ ማንኛውንም ዝግጅቶች አቅርቦት ያቀርባሉ፡፡ የክፍያ ሁኔታ ለተቋማት ሃላፊዎች
ከሆነ በየወሩ ለሰራተኞች ደግሞ በየቀኑ ገንዘቡ ይሰበሰባል፡፡
6. የመዝናኛ ክበብ ው የክራይ ዋጋ በነፃ ነው፡፡
6. ኦዲት ቢሮ
 ይህ ተቋም መዝናኛ ክበብ ን የሚጠቀምበት ሁኔታ በመረዳጃ ማህበሩ ሲሆን የሚሰጠውን አገልግሎት
በመከታተልና በቆጣጠር እንዲሁም ሰራተኞችን በቅጠር እን አቅርቦቶችን በማቅረብ የመረዳጃ ማህበሩ
የሚመለከት ነው፡፡
 መዝናኛ ክበብ ው የሚመሩ ሰራተኞች ማህበሩ የሚመርጣቸው ኮሚቴዎች ሲሆኑ የተቋሙ ቋሚ
ተቀጣሪ ናቸው፡፡ ለካፌው ስራተኛ 2 የሰው ሃይል አንድ ምግብ አዘጋጅ እና አንድ አስተናጋጅ ቀጥረው
ያሰራሉ፡፡ ለሰራተኞችም ደመወዝ ለእያንዳንዳቸው ብር 1500 ይከፍላሉ፡፡
 መዝናኛ ክበብ ውን የሚሰራበት እቃዎች በሙሉ፣ የተቋሙ ሲሆን የመብራትና የውሃ ወጭ
ይሸፈንላቸዋል፡፡
 ለሰራተኛው የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ዋጋ ተመን ጥናት በማድግ በማህበሩ በኩል ተቀምጧል፡፡
 ሰራተኛ በመዝናኛ ክበብ ው የመጠቀም ልምዱ ዝቅተኛ ነው፡፡ የውጭ ደንበኛ የለውም፡፡
 በተቋሙ የሚኖሩ ማንኛውንም ዝግጅቶች አቅርቦት ያቀርባሉ፡፡ የክፍያ ሁኔታ ለተቋማት ሃላፊዎች ከሆነ
በየወሩ ለሰራተኞች ደግሞ በየቀኑ ገንዘቡ ይሰበሰባል፡፡
 ካፌውን የማስተዳደርና የመምራት ጉዳይ በጣም አስቸጋሪና ከተጨማሪ ስራ ጋር የሚሄድ ባለመሆኑ
በቀጣይ ሌላ አማራጭ ሊያሱቡ እንደሚችሉ ተረድተናል፡፡
7. ት/ት ቢሮ
 መዝናኛ ክበብ ውን በጨረታ ለውጭ ባለሀብት አከራይተው የሚጠቀሙ ሲሆን ገቢው ለተቋሙ
የመረዳጃ ማህበር የሚውል ነው፡፡

 ተከራዩ ምግብ የሚሸጥበት ዋጋ የተጋነነ እና ከተማ ላይ በውድ ቤት ተከራይቶ የሚሰራ የሚመስል ነው፡፡
 የውጭ ተጠቃሚም ገብቶ ከካፌው ይጠቀማል፡፡

8. ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ
 ካፌውን በጨረታ ለነጋዴ አከራይተው እየተጠቀሙ ይገኛሉ፣
 የኪራዩ መጠንም ብር 4400 ነው፣
 የኪራዩ ገንዘብ ለመረዳጃ ማህበሩ ማጠናከሪያነት ይውላል፣

3|Page
 ወምበር፣ ጠረጴዛ ፍሪጅ እና መሰል ቁሳቁሶች የተቋሙ ሲሆኑ የጎደሉትን ቁሳቁሶች ተከራዩ አሟልቶ
ይጠቀማል፣

 የተቋሙን የሚወገዱ ንብረቶች መረዳጃ ማህበሩ ሽጡ እንዲጠናከርበት ይደረጋል፤


 አባሉ የአባልነት መዋጮ ብር 20 በየወሩ ያዋጣል፣
 የመዝናኛ ክበብ ው ክራይ ብር 4400

ከተለያዩ ድርጅቶች ያለዉን ልምድ እንደመነሻ ለመጠቀም የተዘጋጀ ቸክሊስት፣

1. በጥናቱ የተካተቱ የግል ድርጅቶችና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ዝርዝር


1.1. የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት(አህስኮድ)
1.2. የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት(አውስኮድ)
1.3. የአማራ ዲዛይን ቁጥጥር ድርጅት
1.4. አመልድ
1.5. ቧንቧ መገጣጠሚያ
2. በጥናቱ የተካተቱ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዝርዝር
2.1. የአማራ ክልላዊ መንግስት ት/ት ቢሮ
2.2. የአማራ ክልላዊ መንግስት ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ
2.3. የአማራ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲት ቢሮ
2.4. መብራት ሃይል
3. ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያላቸዉን የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት በምን መልኩ ነው የሚጠቀሙት፤
3.1. መዝናኛ ክበቡን በማከራየት
3.2. በድርጅቱ ሰራተኞች በመቅጠር
3.3. በሰራተኛ ማህበር/መረዳጃ ማህበር ሆኖ ሰራተኞችን ቀጥሮ በማሰራት
4. በተራ ቁጥር 3 መልሱ 3.2 እና 3.3. ከሆነ የሰው ሃይል ብዛቱ፣ አይነት እና ሁኔታው በምንና እንዴት እንደሆነ
ማብራሪያ ካለ ይገለፅ
4.1. ሥራ አስኪያጅ ብዛት ……….…. ደሞዝ…….
4.2. የወጥ ቤት ሰራተኛ ብዛት…………. ደሞዝ…….
4.3. ተቆጣጣሪ እና አሰተባባሪ ብዛት ……… ደሞዝ……...
4.4. አስተናጋጅ እና ጽዳት ሰራተኛ ብዛት…… ደሞዝ………
4.5. ሎሎች ካሉ ይገለጽ

መዝናኛ ክበብ ው በተቋሙ ወይም በተቋሙ ባሉ ማህበራት (በሰራተኛ ማህበር/መረዳጃ ማህበር) የሚሰራ ከሆነ
አጠቃላይ አደረጃጀቱ እና የአሰራር ስርዓቱ ምን ይመስላል

4|Page
5. መዝናኛ ክበብ ው በተቋሙ ባሉ ማህበራት (በሰራተኛ ማህበር/መረዳጃ ማህበር) የሚሰራ ከሆነ ስራ ለማስጀመር
የሚያስችል የበጀት ምንጭ እንዴት እና ከማን ተሟላ
6. መዝናኛ ክበብ ውን ተከራይቶ የሚሰራ ከሆነ ድርጅቱ ስንት ተከራየው እንዲከራዩ የተጋበዛሁበት ሁኔታ፣ የውሃና
የመብራት አጠቃቀም ሁኔታ፣
7. ተከራይተዉ የሚሰሩ ድርጅቶች ከአከራዩ ድርጅት የሚያገኙት ወይም የሚሟላላቸዉ ቅድመ ሁኔታ ካለ ቢዘረዘር
8. አከራዩ ተቋም ከተከራዩ ድርጅት እንዲሟሉለት የሚፈልጋቸው ቅድመ ሁኔታዎች ካሉ ቢዘረዘሩ
9. መዝናኛ ክበብ ው ተከራይቶ ከሆነ የሚሰራው የሚያቀርቡት አገልግሎቶች በምን እና እንዴት ባለ ሁኔታ ነው
9.1. ድርጅቱ በሚፈልገዉ አጠቃቀም መነሻ በማድረግ
9.2. በተከራይታዉ እና በድርጅቱ ስምምነት መነሻ በማድረግ
9.3. በተከራይታዉ በሚያቀርበዉ አጠቃቀም መነሻ በማድረግ
9.4. የተጣሉ ግዴታዎችስ አሉ ወይ
10. በመዝናኛ ክበብ የሚቀርቡ የምግብ፣ የመጠጥና ትኩስ ነገሮች ምን ምን ናቸዉ ለማን ለማን ይቀርባሉ ዋጋቸዉ
ቢገለፅ
11. በመዝናኛ ክበቡ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ሰራተኛው የመጠቀም ባህሉ እንዴት ነው ? ምን ያህል የድርጅቱ
ሰራተኞች በመዝናኛ ክበብ ዉ በአማካይ ይጠቀማሉ
12. ከድርጅቱ ሰራተኞች ዉጭ የሚጠቀሙ ካሉ በአማካይ ምን ያህል ይሆናሉ
13. የድርጅቱ ሰራተኞች ከመዝናኛ ክበቡን ሲጠቀሙ የአከፋፈል ሁኔታ እንዴት ነዉ
13.1. በየቀኑ በተጠቀሙት መጠን
13.2. በየሳምንቱ የተጠቀሙትን በመደመር
13.3. በወር የተጠቀሙትን በመደመር
13.4. ሌላ ካለ ይገለፅ
14. ለመዝናኛ ክበብ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን የአቅርቦት ሁኔታ (ከማን፣ እንዴት፣ በምን ያህል ጊዜ ወዘተ) ምን
ይመስላል?
15. የመዝናኛ ክበብ ው የፋይናንስ፣ የንብረትና የሰው ሃይል አስተዳደሩ ምን ይመስላል?
16. በተቋማችሁ ለሰራተኛው የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት በመኖሩ ለሰራተኛውና ለተቋሙ ያለውን ጠቀሜታ እንዴት
ታዩታላችሁ?
17. በተቋማችሁ የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት ስትሰጡ ያጋጠማችሁ ተግዳሮት ካለ ቢገለጽልን
18. በአጠቃላይ የመዝናኛ ክበብ አገልግሎት ላይ የምትሰጡን አስተያየት ካለ?

እናመሰግናለን!

የሰራተኛ የፍላጎት ማሰባሰቢያ መጠየቅ

5|Page
ንጋት ኮርፖሬት ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር አኳያ ሻይ ቡና በማቅረብ ሰራተኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ
ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬቱ የተከራየው ህንጻ ይህን የሻይ ቡና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ጨምሮ
ለሰራተኛው ለማቅረብ የመዝናኛ ክበቡን አመች በመሆነ መልኩ መጠቀም እንዲቻል የተቋሙ ሰራተኞች
ፍላጎት ማሰባሰብ አስፈልጓል፡፡

ስለሆነም እርሰዎ በመዝናኛ ክበቡን አገልግሎት ዙሪያ የሚኖረዎትን ሃሳብ ማወቅ በማስፈለጉ መጠይቁን
ጊዜዎትን ሰጥተው በአግባቡ እንዲሞሉልን በአክብሮት እየጠየቅን በቅድሚያ እናመሰግናልን፡፡

1. የመረጃ አሞላል

 ስም መጻፍ አያስፈልግም፣

 በተቀመጠው ሳጥን ላይ √ ወይም × ምልክት በማስቀመጥ እና በክፍት ቦታዎች ደግሞ

ሃሳባዎን በማስቀመጥ ምላሻዎን ይስጡን!

2. መሰረታዊ መረጃ
1. ጾታ ወንድ ሴት
2. የደመወዝ መጠን ከ -------- እስከ ------------ ከ ----------- እስከ -------- ከ ----------- እስከ
------------ ከ ----------- እስከ ------------ ከ ---------እስከ ------------
3. በመዝናኛ ክበብ ው የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለመጠቀም ፍላጎት አለዎት
አወ የለኝም

4. በመዝናኛ ክበብ ው ውስጥ ምን ምን አገልግሎቶች ቢቀርቡ ይመርጣሉ


o ትኩስ ነገሮች-----------------------------------------------------------------
o ቁርስና ምሳ-----------------------------------------------------------------
o ለስላሳ መጠጦች----------------------------------------------------------
5. መዝናኛ ክበቡን በምን መልኩ ቢተዳደር/ቢመራ ይርጣሉ
o በመረዳጃ ማህበሩ
o ለውጭ ተከረይቶ
o በተቋሙ

እናመሰግናለን!

6|Page

You might also like