You are on page 1of 1

. . . . . . . .

ቀን 2012 ዓ/ም
የቤት ኪራይ ውል ስምምነት
እኔ አቶ . . . . . . . . . . . . . . . . .. . ወ/ሮ (ወ/ሪት) . . . . . . . . . . . .
የአቶ ንጋቱ ዶሪ ቤትን ለመኖሪያነት ለኪራይ በዚህ የኪራይ ውል ስምምነት መሰረት በቤታቸው ግቢ ውስጥ ለተከራዮች
የተቀመጠውን ውል እንክብካቤው በመረዳትና በማመን እኔም አቶ . . . . . . . . . . . . . . . . የቅድሚያ ክፍያ ብር
. . . . . . . . . . . . . . . በመክፈል ተስማምቼ የተከራየሁ መሆኔን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡
1. ይህን የተከራየሁትን ቤት ምሽት ወደ ግቢው መግባት የሚቻለው እስከ ምሽቱ 3 (ሶስት) ሰዓት ብቻ መሆኑን
ተረድቼ በማመን ነው፡፡
2. እኔ ስሜ በዚህ ውል ከተገለፀው በስተቀር ሌላ ሰው በደባልነት ያለማስገባት በዚህ ውል ተስማምቻለሁ፡፡
3. በቤቱና በግቢው ውስጥ ምንም አይነት የሱስ ነገሮችን ያለማስገባትና ያለመጠቀምም በዚህ ውል ተስማምቻለሁ፡፡
4. መኖሪያየ ስለሆነ የምኖርበትን የቤቱን የውስጥ ንፅህናን ለመጠበቅና ለቅቄውም እንኳ ብወጣ አጽድቼው ልወጣ
በዚህ ውል ተስማምቻለሁ፡፡
5. የቤቱም ኪራይ በቅድሚያ ክፍያ የተከራየሁ ሲሆን የተከራየሁበት ቀኑ ወይም ወሩ ሲደርስ በአምስት (5) ቀናት
ውስጥ ኪራይን ልከፍል የተስማማሁ ሲሆን ይህንን ያለመፈጸም ኪራዩን ከ 10 (አስር) ቀናት በላይ ባሳልፍ ይህን
የተስማምቼ የፈረምኩት ውል በቂ ማስረጃ ሆኖ ያለ አንዳች የሰው ማስረጃ (ምስክርነት) በወረዳው ማህበራዊ
ፍ/ቤት ወይም በክ/ከተማው መደበኛ ፍ/ቤት አከራይ አቶ ንጋቱ ዶሪ ወይም ወኪላቸው ሊከሱኝ መቻላቸው በዚህ
ውል መስማማቴ በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡
6. ኪራይውን ያለመክፈል ለመሸሽ (ለመሰወር) አስቤ ቤት ውስጥ ያለሁበት በማስመሰል ከኪራዩ መከፈያ ጊዜ ከ 10
(ከአስር) ቀናት በላይ ቤቱን ቆልፌው እንኳን ብሰወር በቤቱ ውስጥ ምንም ዓይነት እቃ ወይም ንብረት እንደሌለኝ
ያመንኩት መሆኑ ታውቆ አከራዩ አቶ ንጋቱ ዶሪ ወይም ወኪላቸው የተቆለፈውን ቤት ቁልፉን ሰብረው ከፍተው
ቤታቸውን ለሌላ ሰው ማከራየት የሚችሉ መሆናቸውን በዚህ ውል ተስማምቼ መከራየቴን በፍርማዬ
አረጋግጣለሁ፡፡
የአከራይ ፊርማ የተከራይ ፊርማ
. . . . . . .. … . . . . . . .. . . . . .

You might also like