You are on page 1of 1

ቀን፡-

የንግድ ቤት ኪራይ ውል ስምምነት


አከራይ ፡- አቶተፈሪ /ዜግነት አትዮጵያዊ/
አድራሻ፡- አ.አ.የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤ/ቁጥር አዲስ
ተከራይ፡- ብሩክ እሸቱ/ ዜግነት ኢትዮጵያዊ/
አድራሻ፡- አ.አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤ/ቁጥር አዲስ
አከራይና ተከራይ ተብለን በዚህ ውል የምንጠራ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1711/1731/2005 መሰረት የኪራይ ውል ስምምነት
አድርገናል፡፡
እኔ አከራይ በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘውን ግቢ አድራሻው የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ቀጠና 6 ከመኖሪያ ቤቴ ላይ ግማሹን
ቆርጬ ለጋራዥ ሊገለገሉበት ያከራየኋቸው ሲሆን ይህንን ገራዥ ሳከራያቸው በወር /
/ሊከፍለኝ እንዲሁም ቅድሚያ የሶስት ወር ክፍያ /
/የከፈለ ሲሆን እና ከሁለት ወር ክፍያ በኋላ በየወሩ እየከፈሉ በስማቸው የንግድ ፍቃድ አውጥተው ሊገለገሉበት
ለአንድ ዓመት ኮንትራት ሰጥቼ ያከራየኋቸው ሲሆን መብራትን በተመለከተ ተከራይ የቆጠረውን ሊከፍሉ ተስማምተን ቤቱን
ለማስለቀቅ ስፈልግ የቅድሚያ የሶስት ወር ማስጠንቀቂያ የምንሰጣቸው መሆኑን አውቄ ያከራየኋቸው መሆኔን በፊርማዬ
አረጋግጣለሁ፡፡
እኔም ውል ተቀባይ/ ተከራይ ከላይ በውል ሰጭ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ግቢ አድራሻው የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ቀጠና 6
ከመኖሪያ ቤት ላይ ግማሹን ቆርጬ ከጋራዥ ልገለገልበት የተከራየኋቸው ሲሆን ይህንን ገራዥ ስከራያቸው በወር
/ / ልከፍላቸው እንዲሁም ቅድሚያ የሶስት ወር ክፍያ /
የከፈልኩ ሲሆን እና ከሁለት ወር ክፍያ በኋላ መብራትን በተመለከተ እኔ ተከራይ
የቆጠረውን ልከፍል የተስማማን ሲሆን ቤቱን መልቀቅ ስፈልግ የቅድሚያ የሶስት ወር ማስጠንቀቂያ የምንሰጣቸው መሆኑን
አውቄ የተከራየሁ መሆኔን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡ ተከራይ የተከራዩትን ቤት በሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይችሉም፡፡
ውሉም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1889/1890 መሰረት በሕግ ፊት የፀና ነው፡፡ ውሉን ለማፍረስ ወይም እንደ ውሉ ለመፈፀም
እንቅፋት የፈጠረ ለመንግስት ብር 2000/ሁለት ሺህ ብር ለውል አክባሪ ወገን ኪሳራ ብር 2000(ሁለት ሺህ ብር) ከፍሎ
ውሉ የፀና ይሆናል እንጂ አይፈርስም፡፡
ይህንን ውል ስንዋዋል የነበሩ ምስክሮች
1. አድራሻ
2. አድራሻ
እኛም ምስክሮች አከራይ ተከራይ ከላይ በተገለፀው መሰረት ተስማምተው ሲዋዋሉና ሲፈራረሙ አይተን በውሉ ላይ
በምስክርነት ፈርመናል፡፡
የውል ሰጭ ስምና ፊርማ የውል ተቀባይ ስም ፊርማ

የምስክሮች ስምና ፊርማ


1.
2.
3.

You might also like