You are on page 1of 3

ቀን 04/07/2013 ዓ/ም

ለአሶሳ ዞን ጠቅላይ ዐ/ህግ መምሪያ

አሶሳ

ጉዳዩ፡-አብሮ በጋራ የመስራት የሥራ ዉል ስምምነት ስለማድረግ ይሆናል፡፡

ዉል ስጪ፡- ሄራላ ልዩ አነስተኛ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር(አቶ እስማኤል ሙባረክ አማካኝነት)


አድራሻ፡- ቤ/ጉ/ክ/አሶሳ ዞን ሽርቆሌ ወረዳ ሀልሙ ቤቤ ቀበሌ ነዋሪ ስልክ 0939057090

የዉል ተቀባይ፡-
1. ባላቶሪይ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግል ኩባኒያ
አድራሻ፡-አሶሳ ከተማ ወረዳ 1 ቀጠና 1 ነዋሪ የቤ.ቁ አድስ ስልክ -------------------------
ዉል ሰጭ እና ዉል ተቀባይ ወገን ተብለን የምንጠራዉ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ቁጥር 212/ሀ እና በፍትሀብሔር
ህግ ቁጥር 1711 እና 1731 መሠረት ከዚህ የሚከተለዉ በጋራ አብሮ የመስራት ዉል ወደንና ፈቅደን ማንም
ሳያስገድደን በገዛ ፍቃዳችን ተስማምተን ተፈራርመናል፡፡

አንቀጽ አንድ

ዓላማ

ዉል ሰጪ ሄራላ ልዩ አነስተኛ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማዕድን ኤጀንሲ
በተፈቀደላቸዉ መሠረት በአሶሳ ዞን ሽርቆሌ ወረዳ ሀልሙ ቤቤ ቀበሌ በተስጠዉ የወርቅ ማዕድን ለማምረት
ማህበሩ በህግ ስልጣን የተሰጠዉ አካል ህጋዊ ስዉነት ያገኘ ሲሆን በአንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ ‘’9’’ መሠረት
በተስጠዉ ሥልጣን በአሶሳ ዞን ሽርቆሌ ወረዳ ሀልሙ ቤቤ ቀበሌ በተስጠዉ የወርቅ ማዕድን ማምረት ሥራ
ለመስራት በተፈቀደልኝ መሠረት እኔ ሄራላ ልዩ አነስተኛ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር በወርቅ በማዕድን
ፍለጋ ንግድ ድርጅቱ ዉስጥ ባለን 100%/መቶ ፐርስንት/ሥራዉን ለመስራት ፍላጎት ያላቸዉ ግለስቦች ወይም
ድርጀቶች ማለትም ለዉል ተቀባይ 60% በመስጠት ለመስራት በቅድሚያ ለመንግስት የሚከፈለዉ ዓመታዊ
የሮያሊቲ ገቢ ግብር ጨምሮ በዉል ተቀባይና እንዲሸፈን በሙሉ ፍላጎታችን ተስማምተናል፡፡

የዉል ተቀባይ ባላቶሪይ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግል ኩባኒያ ከላይ ዉል ስጪ ሄራላህ ልዩ አነስተኛ የወርቅ
አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህ ጋር የተስማማንበት ነጥቦች ማንም ሳያስገድድን በገዛ ፍቃዳችን ተስማምተናል፡፡

ተ.ቁ የተስማሚዎች ስም የክፍፍል


ፐርስንት
1 ባላቶሪይ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግል ኩባኒያ 60%
2 ሄራላህ ልዩ አነስተኛ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር 40%

አንቀጽ ሁለት
የተስማሚዎች በመብትና ግዴታ

2.1. ይህ ዉል ሰጪ እና ዉል ተቀባይ የስምምነት ዉል ሲደረግ ዉል ሰጪና ዉል ተቀባይ ወገኖች የጋራ የሆነ


ንብረት የሌላቸዉ ሲሆን ወጪዉም እንደባለድረሻዎች መዋጮ ተዋፅኦ የሚወስን ሲሆን ሁለቱም ወገኖች
በሥራ በኩል ለሚመጣዉ ግብርም ሆነ ማንኛዉም መንግስታዊ ክፊያዎች በዉል ተቀባይና የሚሽፈን ይሆናል፡፡

2.2. በኢትዮጵያ ህግ መሠረት የሚከፈሉ ማናቸዉም ታክሲዎችና ሥራዉን የሚመለከቱ ልዩ ልዩ ወጪዎች


በዉል ተቀባይ የሚሽፈን ይሆናል፡፡

2.3. ዉል ተቀባይ በሥራዉ የሚያስፈልገዉ ልዩ ልዩ ወጪዎች በመሸፈን ዉጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ትጋት
የማድረግ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ይህ ግዴታ ካልተወጣ ዉል ስጪ በቅድሚያ ባልተፈፀሙ ጉዳዮች ላይ በጋራ
በመወያየት መግባባት ላይ ካልተደረስ ዉሉን በስምምነት በፍርድ ቤት የማፍርስ መብት የተጠበቀ ነዉ፡፡

አንቀጽ ሦስት

የተዋዋይ ወገኖች ተግባርና ኃላፊነት

3.1. የዉል ስጭ ተግባርና ኃላፊነት

 የማህበሩ ህገዊ ስርተፊከት ለሥራ ዝግጁ በማድረግ ማቅረብ


 ለሥራዉ የሚያስፈልጉ መንግስታዊ ማዋቅር ጋር ግንኙነት በማድረግ ምቹ ሁኔታ መፈጠር
 ለድርጀቱ የሚያስፈልጉ ሠራተኞች በመለየት እና በማዘጋጀት ማቅረብ

3.2. የዉል ተቀባይ ተግባርና ኃላፊነት

 የሳይት ሥራዎች ማዘጋጀት(በሳይት ላይ የሚገናቡ ግንባታዎች ጨምሮ)


 ለሥራዉ የሚያስፈልጉ የሥራ ማቴሪያል በሙሉ የማቅረብ
 የባለሙያዎች ቅጥር መፈጸም(ጂኦሎጀስት እና ሌሎች ድጋፍ ስጭ ሠራተኞች)
 ለሥራዉ የሚያስፈልግ ካፕታል ማዘጋጀት
 በየጊዘዉ የድርጀቱ የሥራ እንቅስቃሴ እየተከታተለ የአካባቢ ሥነ ምህዳር እና ሌሎች ተፅዕኖ
እንዳይፈጠር የሚከታተል አማካሪ ድርጀት መቀጠር

አንቀጽ አራት

ዉሉን የሚያስፈጽሙ ኃላፊነት ያላቸዉ

እኔ ዉል ሰጪና ዉል ተቀባይ ወገኖች በተስማማነዉ ዉል መሠረት ባለድረሻ በኃላፊነት ሥራዉን በጋራ


ለማስተባበር ተሰማምተናል፡፡

አንቀጽ አምስት

የትረፍና ኪሳራ ከፍፍል


ተዋዋይ ወገኖች በተለየ ሁኔታ ካለተስማሙ በስተቀር ከጠቅላላው ዓመታዊ ትርፍ ህጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ
በአባላቱ መካከል እንደ አክሲዮን ይዞታቸው ይከፋፈላል፡፡ ነገር ግን ሥራዉ ለመከናወን የወጡ ሌሎች ጠቅላላ
ወጪዎች በዉል ተቀባይ የሚሽፈን ይሆናል፡፡ ሆኖም በማንኛውም ሁኔታ አባላቱ በማህበሩ ውስጥ ካለው
የአክሲዮን ካፒታል በላይ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም፡፡
አንቀጽ ስድስት

የገንዘብ ሥርጭት፣አካፋፍል ወይም አለቃቅ በተመለከተ

የገንዘብ ወጪና ገቢ እንቅሳቃሴ በዉል ተቀባይ እና በዉል ስጪ በጋራ የሚከናወን ይሆናል፡፡

አንቀጽ ስባት

ዉሉ ጽንቶ የሚቆይበት ጊዜ

ይህ ዉል በአሶሳ ዞን ጠቅላይ ዐቃበ ህግ መምሪያ ዛሬ 04/07/2013 ዓ/ም ጀምሮ በፍትሃብሔር ህግ


ቁጥር 1731/2005 እና 2266 መሠረት በህግ ፊት ለ 5 ዓመት የጸና መሆኑንና እንደሁኔታዉ ዉል
በማሻሻል የሚቻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በዉሉ መሠረት የማይፈጽም ወገን ቢኖር ለዉል አክባሪዉ
ያወጣቸዉን ወጪዎች እና ብር 50.000/ሀምሳ ሺህ ብር ብቻ/ ለመንግስት ብር 50.000/ሀምሳ ሺህ
ብር ብቻ/ ገደብ ከፍሎ ዉሉና ገደቡ በህግ ፊት የጸና ይሆናል፡፡

እኛ ምስክሮች ተዋዋዮች ይህን አብሮ በጋራ የመስራት ዉል ሲዋዋሉ ያየን መሆናችን በፊርማችን
እናረጋግጣለን፡፡

የነበሩ ምስክሮች

1 ኛ ----------------------------------- አድራሻ------------------------------ፊርማ-------------

2 ኛ ----------------------------------- አድራሻ --------------------------- ፊርማ-------------

3 ኛ ------------------------------------አድራሻ --------------------------- ፊርማ-------------

ዉል ሰጪና ተቀባይ ስም

ዉል ሰጪ ፡- ሄራላ ልዩ አነስተኛ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር (አቶ እስማኤል ሙባረክ


አማካኝነት)ፈርማ -------------------

ዉል ተቀባይ፡-

1. ባላቶሪይ የወርቅ አምራች ኃ/የተ/የግል ኩባኒያ(አቶ ------------------ አማካኝነት) ፈርማ


-------------------

You might also like