You are on page 1of 8

ኢንፊንቲ ቲች ኮምፒዮቲንግ ሶልሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር

INFINT TECH COMPUTING SOLUTION PLC


የመተዳደሪያ ደንብ
አንቀጽ አንድ
ጠቅላላ
ይህ የመተዳደሪያ ደንብ ኢንፊንቲ ቲች ኮምፒዮቲንግ ሶልሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር (INFINT
TECH COMPUTING SOLUTION PLC) የመመስረቻ ጽሑፍ ጋር በአንድነት የማይነጣጠል አካል
ሆኖ ያገለግላል፡፡

1.1 ማህበሩ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ሁለተኛ መጽሐፍ ከቁጥር 314 እስክ 509 በተመለከቱት ድንጋጌዎች
መሠረት የተቋቋመና በዚሁ መተዳደሪያ ደንብ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የመመስረቻ ጽሑፍ
ያልተሸፈኑ ጉዳዮችን በሚያጋጥሙበት ወቅት በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ውስጥ ስለ አክሲዮን ማህበር
የተመለከቱት ድንጋጌዎች እና በፍትሐብሔር ሕጋችን መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
አንቀጽ ሁለት
ካፒታል ስለመጨመር
2.1 የማህበሩ ካፒታል በጥሬ ገንዘብ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ነው፡፡ ይኸውም በጥሬ
ገንዘብ በአጠቃላይ በአባላቱ ተከፍሏል፡፡
2.2 ይህ መተዳደሪያ ደንብ የማህበሩ ሦስት አራተኛ እና ከዚህ በላይ አክሲዮን በያዙ አባላት ስምምነት
መሠረት ሊሻሻል ይችላል፡፡ የካፒታል ጭማሪ የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ በሚፈቅደው በማንኛውም
መንገድ መሆን ይችላል፡፡

አንቀጽ ሦስት
አክሲዮኖች
3.1 አክሲዮኖች በአባላት መካከል ያለምንም ገደብ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ለሟች ሚስት ወይም
ባል እና ሕጋዊ ወራሾች አክሲዮኖች ካለምንም ገደብ ወራሽነታቸው በፍ/ቤት አረጋግጠው ሲገኙ
ይተላለፍላቸዋል፡፡
3.2 አክሲዮኖችን ከማህበሩ ውጭ ሌላ ሰው ማስተላለፍ የሚቻለው በቅድሚያ ቢያንስ ከማህበሩ ካፒታል
75 ፐርሰንት የያዙትን አባላት ስምምነት ማግኘት ሲቻል ነው፡፡ የአባላቱ ስምምነት ካልተገኘና
አክሲዮኑን ማስተላለፍ የፈለገው አባል በሀሳቡ ከፀና ለሽያጭ የቀረበውን አክሲዮን የመግዛት
ቅድሚያ የሚሰጠው ለአባላቱ ይሆናል፡፡ ከአንድ በላይ ቀደምትነት ያላቸው ሰዎች አክሲዮን ለመግዛት
ያላቸውን ቅድሚያ መብት ለመጠቀም የፈለጉ እንደሆነ በመካከላቸው በጨረታ አሸናፊ ለሚሆነው
የማህበሩ አባል ይሸጣል፡፡
3.3 ከላይ በተመለከተው ሁኔታ የተደረገ የአክሲዮን ማስተላለፍ በጽሁፍ መሆን ያለበት ሲሆን በአክሲዮን
መዝገብ ካልተመዘገበ ዋጋ አይኖረውም የምዝገባ አስፈላጊ አክሲዮኑን በሚመለከት በተደነገጉ ሕጐች
መሠረት ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ አራት
የአክሲዮኑ ማህበር አባላት መብትና ግዴታዎች
4.1 እያንዳንዱ አባል የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፡፡
4.1.1 በማናቸውም የአባላት ስብሰባ ላይ የመካፈል፡፡
4.1.2 በማናቸውም ስብሰባ ላይ በያዘው የአክሲዮኖች መጠን ብዛት መጠን ድምጽ የመስጠት፡፡
4.1.3 በዋናው መ/ቤት ውስጥ ያሉ የቆጠራ ውጤቶችን ወጪና ገቢ ምዝገባዎችንና የኦዲተር
ሪፖርቶች የመመርመርና መዝግቦ የመያዝ
4.1.4 በንግድ ሕጉና በማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ እንዲሁም በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ
የተመለከቱትን መብቶች የመጠቀም፡፡
4.2 ከላይ የተገለጸው የማህበሩ አባላት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ
4.2.1 አክሲዮኖቹ የማይከፋፈሉ ናቸው፡፡
4.2.2 ብዙዎች ሰዎች የአክሲዮኖች የጋራ ባለሀብት የሆኑ እንደሆነ የማህበ ርተኛነት መብት
ሊሰራባቸው እንዲችል ለሁሉም እንደራሴ የሚሆን መሾም አለባቸው፡፡
4.2.3 ለሁሉም እንደራሴ የሚሆን ያልተሾመ እንደሆነ ለአንዱ ባለሀብት ማህበሩ የሚሰጣቸው
ማስታወቂያዎችና መግለጫዎች በሁሉም ላይ የሚፀኑ ናቸው፡፡
4.2.4 የጋራ ባለሀብቶች ከባለአክሲዮንነት የተነሳ ያላቸው ግዴታዎች በአንድነት ሳይከፋፈሉ ሁሉም
ኃላፊ ናቸው፡፡
አንቀጽ አምስት
ያለ ስብሰባ ስለሚተላለፉ ውሣኔዎች
ጉባዔ እንዲሰበሰብ ሕግ ወይም የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ በማያስገድድበት ጊዜ የማህበሩ ሥራ
አመራር አባላት ድምጽ ሊሰጡበት የፈለገውን ጉዳይ ለእያንዳንዱ አባላት በጽሑፍ በመላክ በጉዳዩ ላይ
አባላት በቃለ-ጉባዔ ድምጽ እንዲሰጡበት መጠየቅ አለበት፡፡
አንቀጽ ስድስት
ስብሰባዎች
6.1 የማህበሩ የሂሣብ ዓመት ከተዘጋ 4 ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ መጠራት
አለበት፡፡
6.2 ዋናው የጠቅላላ ጉባዔ ዓመታዊ ማህበርተኞች ስብሰባ ከመደረጉ በፊት ከ 30 ቀን ባነሰ ጊዜ አስቀድሞ
ለአባላት በአደራ ደብዳቤ የስብሰባውን ጥሪ ማሳወቅና ለውሣኔ ወይም ለውይይት ያቀረበው ሀሳብ
ምን እንደሆነ በግልጽ ማስረዳት አለበት፡፡
6.3 ኦዲተር ወይም ዋናው ገንዘብ 51 ፐርሰንት በላይ ማህበርተኞች በማንኛውም ጊዜ የማህበሩ ጠቅላላ
ጉባዔ እንዲሰበሰብ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
አንቀጽ ሰባት
ምልአተ ጉባዔ
7.1 የማህበሩ ስብሰባ ሊካሄድ የሚችለው ከዋናው ገንዘብ 50% በላይ ያለውን የሚወክሉ ማህበርተኞች
ስብሰባው ላይ ሲገኙ ነው፡፡
7.2 በዚህ ዓይነት ስብሰባዎች ላይ ውሣኔዎች የሚተላለፉት በአክሲዮኑ የድርሻ መጠን መሠረት በድምጽ
ብልጫ ይሆናል፡፡
አንቀጽ ስምንት
ዋና ሥራ አስኪያጅ
ከማህበሩ ዓላማ ጋር በተያያዘ መልክ በማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ መተዳደሪያ ደንብና በማህበሩ
ጠቅላላ ጉባዔ ውሣኔዎች መሠረት የሚከተሉትን ተግባራት የማከናወን ሥልጣን አለው፡፡
8.1 የዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ይሾማል፣ ይሽራል፣ ተግባራቸውን ዘርዝሮ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፡፡
8.2 ማህበሩን በመወከል ይፈርማል፡፡
8.3 ለማህበሩ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነው፡፡
8.4 የጠቅላላ ጉባዔዎችና የቦርዱ ውሣኔዎችን ሥራ ላይ ያውላል፡፡
8.5 ለማህበሩ የሚከፈል ገንዘብ መቀበል፣ የማህበሩን ዕዳዎች መክፈል፣ ማንኛውንም የሀዋላ ወረቀት
የተስፋ ሰነድ የባንክ ሰነድ ማዘጋጀት፣ መፈረም፣ ማደስና መክፈል እንዲሁም የጭነት
ማስታወቂያ ደረሰኞችን የቦንድ ሠርተፍኬቶችን ወይም ማናቸውንም ሰነዶች ማጽደቅና
ከጀርባው መፈረም፡፡
8.6 የማህበሩን ወኪል ወይም ሠራተኛ ይቀጥራል፣ ያሰናብታል፣ ክፍያውን፣ ደመወዙን፣ ጉርሻና
ሌሎችም ከመቀጠርና ከማሰናበት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን ይወስናል፡፡
8.7 በማህበሩ ስም የባንክ ሂሳቦች ከፍቶ ገንዘብ ገቢ ወጪ ያደርጋል፡፡ በማህበሩ ስም የተከፈለውን
የባንክ ሂሣብ በፊርማ ወጪና ገቢ በማድረግ ያንቀሳቅሳል፡፡ ቼኮችን ፈርሞ መስጠትም ሆነ
መቀበል ይችላል፡፡
8.8 ለማህበሩ ዓላማ በመልካም ሁኔታ መካሄድ የሚጠቅም የግዢዎች ሽያጭና የነዚህን ማዘዣዎች
ይወስናል፡፡
8.9 ከማህበሩ ዓላማ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ሥራዎች በተመለከተ ከሌላ 3 ኛ ወገኖች ጋር ውል
ይዋዋላል፡፡ በማህበሩ ስም የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመግዛትና ንብረት
መሸጥ መለወጥ ይችላል፡፡
8.10 በማንኛውም ፍ/ቤት ማህበሩ ከሳሽ፤ተከሳሽ ወይም ጣልቃ ገብ በሚሆ ንበት ጉዳይ ሁሉ
ማህበሩን በመወከል አስፈላጊውን ይፈጽማል፡፡
8.11 ማህበርተኞች ሊቀበሉትና ሊያፀድቁት እንዲችሉ የሂሣብ ወጪና የገቢ መዝገብ በደንቡ
መሠረት እንዲገዛ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡ የማህበሩ ዓላማ ግቡን እንዲመታ
አስፈላጊ መስሎ በታየው ጊዜ ከላይ ከተገለጹት ተግባራት መካከል ማናቸውንም በሌላ ሦስተኛ
ሰው እንዲፈጸም በማህበሩ ስም ውክልና መስጠትም ይችላል፡፡
8.12 በማህበሩ ስም ተመዝግቦ የሚገኙትን ንብረቶች በዋስትና በማስያዝ ከባንክ፣ ከግለሰቦች፣
ከአበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ ይበደራል፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ
የጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣን
9.1 በደንበኛው ጠቅላላ ጉባዔ የሂሣቡ ሚዛን የኪሣራውን፤ የትርፍ ሂሣብ የአስተዳዳሪዎቹና
የተቆጣጣሪዎቹ ሪፖርት ይነበባል፡፡ ባለፈው የሂሣብ ማጠቃለያ ዘመን ጊዜ የተሰራውን ሂሣብ
ያፀድቀዋል ወይም ይሽረዋል፡፡ አስፈላጊ ሲሆን የትርፍን አመዳደብና አከፋፈል በጠቅላላው
ባለፈው ሂሣብ ዘመን ማጠቃለያ ጊዜ ውስጥ ባሉት የሂሣብ ጉዳዮች ሁሉ ውሣኔ ይሰጣል፡፡
አንቀጽ አስር
የማህበሩ በጀት የሂሣብ መግለጫና ሕጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ
10.1 የማህበሩ የሂሣብ ዓመት በየዓመቱ ሐምሌ 01 ቀን ተጀምሮ በቀጣዩ ዓመት ሰኔ 30 ቀን
ይፈፀማል፡፡ ስለሆነም የመጀመሪያው ሂሣብ ዓመት የመመስረቻው ጽሑፍና ይህ የመተዳደሪያ
ደንብ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ይሆናል፡፡
10.2 በየሂሣቡ ዓመት መጨረሻ የማህበሩን ንብረቶች ዕቃዎች የሚያሳይ ሪፖርት በዋናው ሥራ
አስኪያጅ ይዘጋጃል፡፡ ይህም ሪፖርት እንዲፀድቅና እንዲመረመር ለኦዲተሮችና ማህበርተኞች
ይተላለፋል፡፡
10.3 የማህበሩን ዓመታዊ ሁኔታ፣የሂሣብ ሚዛን፣የትርፍና የኪሣራ ሁኔታ፣ የንብረት ቆጠራዎችና
የዋና ሥራ አስኪያጅ /ወይም/ የኦዲተሮች ሪፖርት የሚያሳዩ ሰነዶች በየጊዜው ለአባላት
ይላካሉ፡፡
1.4 በንግድ ሕጉ አንቀጽ 539 እንደተደነገገው በተጣራው ትርፍ ላይ በየዓመቱ መጠባበቂያ የሚሆነው
በንግድ ሕጉ መነሻ መሠረት በማድረግ እየተቀነሰ ይቀመጣል፡፡ ይኸው መጠባበቂያ ከማህበሩ
ዋና ገንዘብ አንድ አስረኛ እጅ ሲደርስ ግዴታ መሆኑ ይቋረጣል፡፡
አንቀጽ አስራ አንድ
ስለ ማህበሩ መፍረስ
ማህበሩ በንግድ ሕግ ቁጥር 217፣ 218፣ 511፣ 542፣ እና 543 መሠረት በቂ በሆኑ ምክንያቶች በፍርድ
ቤት ውሣኔ ይፈርሳል፡፡
መሥራች አባላት
ስም ፊርማ

1. አቶ ቴዎድሮስ ዘርኡ በርሄ ------------------------

2. አቶ መርሻ ዓይነኩሉ መርሻ ------------------------

ቨርቲጎ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኃ/የተ/የግል ማህበር


VERTIGO ELECTRO MECHANICAL PLC
የማህበሩ የመመስረቻ ጽሑፍ
በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ላይ ስለተወሰነ የንግድ ማህበር እና አጠቃላይ ስለማህበራት ማቋቋሚያና
አሠራር ሁኔታ በተደነገገው ድንጋጌ መሠረት ቨርቲጎ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኃ/የተ/የግል ማህበር ከዚህ በታች
በተጠቀሱት የማህበሩ መሥራቾች ስም፣ዜግነትና አድራሻቸው በተገለጸው መሠረት የአክሲዮን ማህበሩን
ለማቋቋም ተስማምተናል፡፡

አንቀጽ አንድ
የማህበሩ መሥራች አባላት ስም፣ ዜግነትና አድራሻ
አድራሻ

ክ/ከተማ

የቤ.ቁ.
ተ.ቁ. ስም ከነአያት ዜግነት

ከተማ

ወረዳ
/ዞን/
1. አቶ ቴዎድሮስ ዘርኡ በርሄ ኢትዮጵያዊ አ/አ ቦሌ 13 አዲስ
2. አቶ መርሻ ዓይነኩሉ መርሻ ኢትዮጵያዊ አ/አ ልደታ 2 273

አንቀጽ ሁለት
የማህበሩ ስያሜ
ቨርቲጎ ኤሌክትሮ ሚካኒካል ኃ/የተ/የግል ማህበር

አንቀጽ ሦስት
የማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ፡- አ/አ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤ.ቁ. አዲስ ሱቅ ቁጥር 36/3
ሲሆን ሌሎች ቅርንጫፍ መ/ቤቶች እንደአስፈላጊነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ክልሎችና በውጭ ሀገርም
ሊሆን ይችላል፡፡
አንቀጽ አራት
ማህበሩ የተቋቋመበት ዋና ዋና ዓላማዎች
4.1 የማህበሩ ሥራ በአጠቃላይ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ላይ የተመሠረተ እንደመሆኑ መጠን፡-
ማህበሩ የተቋቋመበት ዋና ዋና ዓላማዎች

4.1 የማህበሩ ሥራ በአጠቃላይ የእንጨት ሥራዎች ላይ የተመሠረተ እንደመሆኑ መጠን፡-


4.1.1 ማንኛውንም የእንጨት ሥራዎችን ማምረትና መግጠም፡፡
4.1.2 ለእሪል እስቴቶች፣ ለሆቴል፣ ለትላልቅ ህንፃዎች፣ ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለት/ቤቶች እና
ለማንኛውም የመንግሥት ሆነ የግል ድርጅቶ በሚያዙት መሠረት አዘጋጅቶ ማቅረብ፣
4.1.3 ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የእንጨት ምርቶችን ለተጠቃሚው ማስገባትና መሸጥ፣
4.1.4 ከአገር ውስጥ ወደውጪ የተለያዩ የእንጨት ምርቶችን መላክ፣
4.1.5 ወደፊት ከእንጨት ሥራዎቹ በተጨማሪ ማንኛውንም የብረትና የአልሙኒየም ምርቶችን
ማቅረብና በሚፈለገው ዲዛይን ሰርቶ መሸጥ፡፡
4.1.6 በተጨማም ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ሥራዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ማንኛውንም
ሥራዎች መሥራት፡፡
4.1.5 የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ከውጪ አገር ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ለገበያ በማቅረብ
መሸጥ፣ ማሽኖችን መትከልና ጥገናዎችን ማድረግ፣
አንቀጽ አምስት
የማህበሩን ካፒታል በተመለከተ
5.1 የማህበሩ ካፒታል ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ የሆነ፣

5.2 የማህበሩን ጠቅላላ ካፒታል እያንዳንዱ የአክሲዮን ዋጋ 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ የሆነ 400 አክሲዮን
ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ በሙሉ የተከፈለ ነው፡፡

በመሥራቾች አባላት የተያዘው የአክሲዮን መጠንም እንደሚከተለው ነው፡፡

ይኸውም:-

ተ. የተያዘው የአንድ የአክሲዮን


ቁ. የአክሲዮን ማህበርተኛው ስም አክሲዮን ጠቅላላ አክሲዮን ጠቅላላ ዋጋ
መጠን ዋጋ መጠን
1. አቶ ቴዎድሮስ ዘርኡ በርሄ 200 1,000.00 200,000.00
2. አቶ መርሻ ዓይነኩሉ መርሻ 200 1,000.00 200,000.00
ጠቅላላ ድምር 400 400,000.00

አንቀጽ ስድስት
እያንዳንዱ የማህበሩ አባላት ከዚህ በላይ በሠንጠረዡ ላይ የተገለጸውን የካፒታል ድርሻ መጠን ሁሉም
አባላት በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉ ሲሆን የኃላፊነት እና መብትም በማህበሩ ውስጥ ባላቸው የአክሲዮን
መጠን መሠረት ይሆናል፡፡
አንቀጽ ሰባት
የሥራ አመራርን በተመለከተ
ማህበሩ በዋና ሥራ አስኪያጅነት እና በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሊመራ ይችላል፡፡ የማህበሩ ዋና ሥራ
አስኪያጅ አቶ መርሻ ዓይነኩሉ መርሻ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡
አንቀጽ ስምንት
የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር
የዋና ሥራ አስኪያጅ ሥልጣን
8.1 ጠቅላላ ጉባኤውን በመወከል የማህበሩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል፣
8.2 በሕግ ፊት በማናቸውም የማህበሩ ጉዳይ ሙሉ ወኪል ናቸው፡፡
8.3 በማህበሩ ስም መክሰስና መከሰስ ወይም ጠበቃ በመወከል፣ ወኪሎችንም መሾምና መሻር
ቅርንጫፍችን መክፈትና መዝጋት፣
8.4 በማህበሩ ስም ከማናቸውም ሦስተኛ ወገን ጋር ማንኛውንም ዓይነት ውል በመዋዋል፣ ከባንክ ከገንዘብ
ተቋማት ጋር በመዋዋልና በማህበሩ ስም ገንዘብ መበደር የባንክ ሂሣብ መክፈት ሂሳቡን ማንቀሳቀስ፣
8.5 በማህበሩ ስም የማህበሩን የሚንቀሳቀሱትን እና የማይንቀሳቀሱትን ንብረቶች መግዛት መሸጥ፣
መለወጥ ስም ማዞር እና በዋስትና ማስያዝ ሠራተኛ መቅጠር ማስተዳደር ማሰናበት፣
8.6 ከዚህ በላይ የተፃፉትን ጠቅላላ አነጋገሮች እንዳሉ ሆነው ማንኛውንም የማህበሩን ጥቅም
የሚያስጠብቁ ጉዳዮችን ያከናውናሉ ይፈጽማሉ፡፡ አጠቃላይ ማህበሩን የሥራ እንቅስቃሴ ይመራሉ፤
የጠቅላላ ጉባዔውን ውሣኔ ያስፈጽማሉ፡፡
8.7 ከላይ የተገለጹትን ተግባሮች በሙሉም ሆነ በከፊል ለመፈጸም ሌላ ሦስተኛ ሰው መወከል ይችላል፡፡
8.8 በማህበሩ ላይ የሚነሱ የፍትሐብሔር እና ሌሎች ጉዳዮች ማህበሩን ወክሎ ለመከራከር የሚችል
ባለሙያ ይወክላል እንደ አስፈላጊነቱ ለመሻር ይችላል፡፡
አንቀጽ ዘጠኝ
ኦዲተሮች
የማህበሩ ኦዲተሮች ከማህበሩ አባላት ሊመረጡ የሚችሉ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ ከማህበሩ ውጭ
ኦዲተር ቀጥሮ የማህበሩን ሂሣብ ሊያሰራ ይችላል፡፡ የማህበሩ ዓመታዊ የሂሣብ ውጤትን በዓመቱ የሂሣብ
መዝጊያ ጊዜ ለአባላቱ ይቀርባል፡፡
አንቀጽ አስር
ስለትርፍ አከፋፈል
ከማህበሩ ከሚገኘው ትርፍ ውስጥ የንግድ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ለካፒታሉ ዕድገት
በፐርሰንት በመተው ቀሪውን ትርፍ እያንዳንዱ የባለአክሲዮን አባላት ባላቸው ድርሻ መሠረት ይከፍላሉ፡፡
አንቀጽ አስራአንድ
ማህበሩ የሚቆይበት ጊዜ
ማህበሩ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ሲሆን ነገር ግን በኪሣራ እና በባለአክሲዮኖች ስምምነት
እንዲሁም በሕግ ብቻ ሊፈርስ ይችላል፡፡
አንቀጽ አስራሁለት
የመመስረቻ ጽሑፉን ስለማሻሻል
ይህ የመመስረቻ ጽሑፍ የማህበሩ ሦስት አራተኛ እና ከዚህ በላይ አክሲዮን በያዙ አባላት
ስምምነት መሠረት ሊሻሻል ይችላል፡፡
ይህ የመመስረቻ ጽሑፍ በአባላት ተነቦና ጸድቆ ዛሬ የካቲት 01 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ
ከተማ ተፈርሟል፡፡
የአባላት ስም ፊርማ

1. አቶ ቴዎድሮስ ዘርኡ በርሄ ------------------------


2. አቶ መርሻ ዓይነኩሉ መርሻ

You might also like