You are on page 1of 6

የካት ኮንስትራክሺን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መተዳደሪያ ደንብ

አንቀጽ አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
1. ይህ መተዳደሪያ ደንብ የካት ኮንስትራክሺን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
መመስረቻ ጽሑፍ ጋር የማይነጣጠል አካል ሲሆን ሁለቱም ማህበሩ የሚመራባቸው
መሰረታዊ ሰነዶች ናቸው፡፡
2. ማህበሩ በኢትዩጽያ የንግድ ህግ ሁለተኛ መጽሐፍ ከቁጥር 51ዐ-543 በተመለከቱት
ድንጋጌዎች እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ህጎች መሠረት የተቋቋመና በዚህ
መተዳደሪያ ደንብና ተያይዞ በሚገኘው የመመሥረቻ ጽሑፍ የሚገዛ ኃላፈነቱ
የተወሰነ የግል ማህበር ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ሳይጠቀሱ የታለፉ
ጉዳዩች ሲያጋጥሙ በኢትዩጽያ ንግድ ህግ ውስጥ ኃላፈነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን
የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
አንቀጽ ሁለት
የማህበርተኞች መብት
እያንዳርዱ የማህበሩ አባል የሚከተሉት መብቶች አሉት፡
1. በማናቸውም የማህበርተኞች ጉባኤ በመገኘት የመሳተፍ፤
2. በማናቸውም የማህበርተኞች ጉባኤ ላይ በመገኘት በያዘው/በያዘችው የአክስዮን
መጠን መሰረት ድምጽ የመስጠት፤
3. በማህበሩ መስሪያ ቤትም ሆነ በቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች የሚገኙትን የማህበሩን
የሂሳብ ሪፖርቶች እና የኦዲት ሪፖርቶች የመመልከት እና ኮፒ አድርጎ
የመውሰድ፤ እና
4. በህግ፣ በማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ እና በዚህ የመተዳደሪያ ደንብ ያለው
ማናቸውም መብቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰደድ፤

አንቀጽ ሶ ስት
ካፒታልና አክሲዮን ስለመጨመር
1. የማህበሩ ካፒታል 1,000,000 ብር ሲሆን ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ
በአባላት ተከፍሏል፡፡
2. ከማህበሩ አባላት የማህበሩን ካፒታል ሶስት አራተኛ ድርሻ ያላቸው አባላት
ሲስማሙ የማህበሩን ካፒታል አንዴ ወይም ብዙ ጊዜ ለማሣደግ ይቻላል፡፡ በዚህ
ጊዜ ተጨማሪዎቹ አክስዩኖች በአባላት መሀከል የሚደለደሉት ማህበርተኞች ቀደም
ሲል በነበራቸው የአክስዩን መጠን መሰረት ይሆናል፡፡

አንቀጽ አራት
ስለማህበሩ አክስ ዩኖች እና የአክስዮኖች መ ዝገብ፣
1. የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ በንግድ ህጉ አንቀጽ 522(1) መሰረት አንድ የአክስዮን
መዝገብ በዋናዉ መ/ቤት እንድያዝ ያደርጋል፡፡
2. የአባላት ስም እና አድራሻ፣ የአክስዮን ድርሻ፣ እና ማናቸዉም የአክስዮን ማስተላለፍ
የንግድ ህጎቹ በሚደነግገዉ መሰረት አግባብነት ካላቸው ሌሎች መረጃዎች ጋር
በመሆን በመዝገቡ ውስጥ ይሰፍራሉ፡፡
3. የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ተያይዞ የሚገኘው መመሥረቻ
ጽሑፍ(ከማሻሻያዎች) ጋር በአንድነት ሲቀርብ ማህበርተኞቹ ማህበሩ ውስጥ
የተመለከቱት አኪሲዩኖች ባለንብረት ለመሆናቸው ማስረጃ ሆነው ያገለግላሉ፡፡
4. ማንኛውም ማህበረተኛ ባለንብረትነቱን ለማስረዳት የአክሲዩን ምስክር ወረቀት
እንዲያቀረብ አይገደድም፡፡
5. ከማህበሩ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ሁሉ አክሲዩኖች የማይከፋፈሉ በመሆናቸው ኩባኒያው
ለአንድ አክሲዩን በአክሲዮኑ ከተመዘገበው አካል ውጭ ባለንብረት አያውቅም::
ስለሆነም የአክሲዩን የጋራ ባለንብረቶች ቢኖሩ መብታቸውን ሊጠቀሙ የሚችሉት
በመካከላቸው አንድ እንድራሴ በመሰየም ብቻ ነው ፡፡

አንቀጽ አምስ ት
አ ክስዮኖችን ስለማስተላ ለፍ
1. አክስዮኖቹ በአባላት መካከል ያለምንም ገደብ ሊተላለፍ ይችላል፡፡
2. በዚህ መተዳደሪያ ሰነዶች መሠረት የሚፈጸም አክሲዩን የማስተላለፍ ተግባር
የሚከናወነው በጽሑፍ እና በንግድ ህግ ቁጥር 522 መሠረት ነው፡፡
3. ከማህበሩ ውጪ ላሉ ሰዎች አክሲዮን ማስተላለፍና መሸጥ የሚቻለው ቢያንሰ የዋናው
ካፒታል ሶስት ሩብ ያላቸው የማህበርተኛቹ አብዛኛው ቁጥር ሲስማሙ ብቻ ነው፡:
4. በቁጥር 3 በተመለከተው መሠረት አክስዮን ለመሸጥ የሚያስችል ሁኔታ ሲኖር
አባላቱ የግዥ ቅድሚያ መብት ይኖራቸዋል፡፡ ሆኖም ቁጥራቸው ከአንድ በላይ የሆኑ
አባላት የግዥ ቅድሚያ መብታቸውን ለመገልገል በፈለጉ ጊዜ፣ ከፍተኛ ዋጋ
ለሚከፍለው ማህበርተኛ ይሸጥለታል፡፡ የግዢ ቅድሚያ መብት ያላቸው አባላት
እኩል የሆኑ ዋጋዎች ያቀረቡ እንደሆነ በጨረታ አሸናፈ ለሆነው ይሸጣል፡፡
አንድ ማህበረተኛ ከማህበሩ ውጭ ለሌላ አዲስ ሰው አክሲዮኖችን ወይም አክስዮንን
5. ለማስተላለፍ የፈለገ እንደሆነ የሚተላለፍለትን ሰው ስም፣ አድራሻ እንዲሁም
የሚተላለፋትን አክሲዩን ብዛት በማመልከት ለስራ አስኪያጅ ማስታወቅ
አለበት፡፡ሥራ አስኪያጁ ማመልከቻው በቀረበ በሰላሣ ቀናት ውስጥ በመተዳደሪያ
ደንቡ መሠረት ለአባላት ውሣኔ ያቀርባል፡፡

አንቀጽ ስድስ ት
ስለጉባዔዎ ች
የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ቢያንስ በማህበሩ የበጀት አመት አንድ ጊዜ ይካሄዳል፡፡
የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ከመድረሱ 15 ቀን በፊት የማህበሩ ስራ አስኪያጅ በተመዘገበ
ደብዳቤ ጉባኤው መቼ እና የት እደሚደረግ ለማህበሩ አባላት ያሳውቃል፡፡
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ በማይኖርበት ጊዜ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማህበሩ ኦዲተር
1. ሊጠራ ይችላል፡፡
2. ከማህበሩ አባላት መሀከል ከማህበሩ ካፒታል እኩሌታ በላይ ያላቸው ማህበርተኞች
የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ሊጠሩ ይችላሉ፡፡
3. በንግድ ህጉ መሰረት የማህበሩ ዋና ዋና ጉዳዩች በማህበርተኞቹ ጠቅላላ ጉባዔ
ይወሰናሉ፡፡
4.

5.
አንቀጽ ሰባ ት
ሙልዓተ -ጉባኤ
ከማህበሩ ካፒታል እኩሌታ በላይ ድርሻ ያላቸው የማህበሩ አባላት በጉባኤው ሲገኙ
የማህበሩ ጉባኤ ሊካሄድ ይችላል፡፡
አንቀጽ ስምንት
ስለውሣኔዎ ች
1. በንግድ ህጉ በልዩ ሁኔታ ከተደነገጉት ጉዳዮች ውጪ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ
ውሳኔዎች የሚወስነው ከማህበሩ ካፒታል እኩሌታ በላይ ድርሻ ባላቸው አበላት
ድምጽ ነው፡፡
2. የመተዳደሪያ ደንቡን ለማሻሻል፣ ማህበሩ ከሌላ የንግድ ድርጅት ጋር ለማዋሃድ፣
የማህበሩን ህጋዊ አቋም ለመለወጥ፣ ካፒታሉን ለመጨመር፣ አዲስ አባል ለመቀበል
ወይም የማህበሩ አባል ላልሆነ ሰው አክሰዩን ለማስተላላፍ የሚወሰን ውሳኔ ቢያንስ
ከማህበሩ ካፒታል ሶስት ሩብ ድርሻ ያላቸው ባለአክሰዩኖችን ድጋፍ ማግኘት
አለበት፡፡
3. የማህበሩን ዜግነት ለመለወጥ የሚቻለው በማህበርተኞቹ ሙሉ ድምጽ ብቻ ነው፡፡

xNq{ ዘጠኝ
yg#Æ›@ xm‰R
1. ¥ÂcWM y¥?brt®C -Q§§ g#Æ›@ bg#Æ›@W btgß# ¥?brt®C
bDM{ BLÅ b¸mr_ l!qmNbR Ym‰LÝÝ
2. ¥?b„ b¥ÂcWM y¥?brt®C -Q§§ g#Æ›@ bmgßT
b?g#½
b¥?b„ ymmSrÒ {/#F½ bz!H ymtÄd¶Ã dMB XÂ
b¥?brt®C -Q§§ g#Æ›@ãC bts-# Wœn@ãC m\rT mmZgB
ÃlÆcWN /úïC½ yWœn@ /úïC½ Wœn@ãC XÂ b{/#F mÃZ
ÃlÆcWN l@lÖC g#Ä×C h#l# mZGï bmÃZ y¸ÃSqM_ i/ð
YñrêLÝÝ

አንቀጽ አ ስር
ስለማህበሩ ሥራ አስክያጅ አሿ ሿም እና የስልጣን ዘመን
1. የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ከማህበሩ አባላት መሀከል ወይም ከማህበሩ አባላት ውጪ
በማህበሩ አባላት ውሳኔ ይሾማል፡፡ በዚሁ መሰረት የማህበሩ አባል የሆኑት አቶ
አሸናፊ ቢተውልኝ ሙሉነህ የማህበሩ የመጀመሪያ ስራ አስኪያጅ ሆነው
ተሹመዋል፡፡
2. የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የስራ ዘመን ሁለት አመት ሆኖ በድጋሚ ሊመረጥ ይችላል፡፡
3. በንግድ ህጉ በተገለጸው መሰረት የማህበሩ አበላት የማህበሩን ስራ አስኪያጅ የስራ
ዘመኑ ከማለቁ በፊት ከስልጣን ሊያወርዱ እና በሌላ ስራ አስኪያጅ ሊተኩ
ይችላሉ፡፡
አንቀጽ አ ስራ አንድ
የሥራ አስኪያ ጅ ሥልጣንና ተግባር
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የሚከተሉት ዋና ዋና ስልጣን እና ሀላፊነቶች አሉት፡፡
1. የማህበሩን አመታዊ የስራ እቅድ ያዘጋጃል፣ ያስፈጽማል እንዲሁም ወቅታዊ
ሪፖርቶችን ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል፣
2. የማህበሩን አላማ ለማሳካት አስፈላጊ ውሳኔዎችን ይወስናል እንዲሁም የማህበሩን
እንቅስቃሴ ይመራል፣
3. የማህበሩን አላማ ለማሳከት በጠቅላላ ጉባኤ የሚወሰኑ ውሳኔዎችን ያስፈጽማል፣
4. ማህበሩን በማንኛዉም የመንግስት ባለስልጣን' አስተዳድር አካላት 'የQዝባዊ
ድርጅቶች፣ በገንዘብ ተቋሞችና ባንኮች ይወክላል እንዲሁም አስፈላጊዉን ሁሉ
ይፈጽማል፣
5. የማህበሩን አላማ ለማስፈጸም የሚረዱ የተለያዩ ውሎችን ከሶስተኛ ወገኖች ጋር
ይዋዋላል፣
6. ማህበሩን በሚመለከቱ ጉዳዮች ማህበሩን በመወከል ክስ ይመሰርታል፣ ጣልቃ
ይገባል፣ ማህበሩ በተከሰሰባቸው ጉዳዩች መልስ ይሰጣል እንዲሁም ጠበቃ ቀጥሮ
ይከራከራል፣
7. የማህበሩን የተለያዩ ክፍሎች የሚመሩ አመራሮችን መርጦ በጠቅላላ ጉባኤ
አጽዳቂነት ያሾማል፣
8. የማህበሩን ሰራተኞች ይቀጥራል፣ ውል ያቋርጣል፣ ደሞዝና ሌሎች ጥቅማ
ጥቅሞችን ይወስናል፣
9. ለማህበሩ የሚከፈሉ ክፍያዎችን ይቀበላል፣ የማህበሩን እዳ ይከፍላል፣ በማህበሩ
ስም የባንክ አካዉንት ይከፍታል እንዲሁም ወጪና ገቢ ያዛል፣
10. በዚህ መመስረቻ ጽሁፍ እና በመተዳደሪያ ደንብ የተሰጠውን ስልጣንና ሀላፊነት
ለሌላ የማህበሩ አባላትም ሆነ ሌሎች ሰዎች ይወክላል፡፡

አንቀጽ አ ስራ ሁለት
ስለ ሥራ አስ ኪያጅ የሥራ ዋጋና ኃላ ፊነት
1. ለሥራ አስኪያጁ ለሚከፈለው የሥራ ዋጋ ክፍያ መጠን በማህበሩ አባላት ጠቅላላ
ጉባዔ ይወሰናል፡፡
2. ሥራ አስኪያጁ ከተሰጠው ስልጣን በላይ ለሚፈጽመውና ከቅንልቦና ውጭ በሆነ
ምክንያት ለሚፈጽማቸው ጥፋቶች ኃላፊ ነው፡፡

አንቀጽ አ ስር ሶስት
ስለተጨማሪ ሥራ አስኪያ ጅና ስለተቆጣጣሪዎ ች
እንደ ማህበሩ የካፒታል መጨመር ፣ የስራ ስፋትና ብዛት ተጨማሪ ሥራ አስኪያጆችና
ተቆጣጣሪዎች በጠቅላላ ጉባኤ ሊሾሙይችላሉ፡፡
አንቀጽ አ ስራ አራት
የማህበሩ ኦ ዲተር
1. የማህበሩ ኦዲተር በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ለአንድ አመት ይሾማል፡፡ የስራ ዘመኑ
ለተጨማሪ ጊዜ ሊራዘም ይችላል፡፡
2. ኦዲተሩ በበቂ መክንያት ከሀላፊነቱ እንዲነሳ ሊደረግ ይችላል፡፡
3. ኦዲተሩ ስራውን በሚያከናውንበት ወቅት ለሚሰራው ጥፋት ለማህበሩ እና ለሶስተኛ
ወገኖች ሀላፊነት አለበት፡፡
አንቀጽ አ ስራ አምስት
የማህበሩ ሒሣብ ዘመን
የማህበሩ የሂሣብ ዘመን የኢትዩጽያ መንግሥት ሂሣብ ዘመን ነው፡፡ ይህም ከሐምሌ 1
እስከ ሰኔ 3ዐ ነው፡፡
አንቀጽ አ ስራ ስድስት
ስለማህበሩ ባላ ንስሺትና ኢንቨንተሪ
1. የማህበሩ ባላንስሺትና ኢንቨንተሪ የሚደረገው በማህበሩ የበጀት ዘመን ሲሆን ሥራ
አስኪያጁ ባላንስሺት አዘጋጅቶ ማህበርተኞቹ እንዲያፀድቁት ያቀርባል፡፡
2. እያንዳንዱ ማህበረተኛ የባላንሺትና ኢንቨንተሪውን ግለባጭ ከዋናው መሥሪያ ቤት
ለመውሰድ ይችላል፡፡

አንቀጽ አ ስራ ሰባት
የመጠባበቂያ ገንዘብ
1. ማህበሩ በየዓመቱ ከሚያገኘው የተጣራ ትርፍ 5% (አምስት በመቶ) የመጠባበቂያ
ፈንድ ያስቀምጣል፡፡ይህም የሚደረገው የመጠበቂያው ፈንዱ የማህበሩን ካፒታል
አንድ አሥረኛ እጅ ያህል እስከሚሆን ነው፡፡
y¥?b„ mdb¾ -Q§§ g#Æ›@ s!wSN |‰ xSk!ð t=¥¶ ym-ÆbqEà gNzB
2. ÃÌq$¥ል#ÝÝ
አንቀጽ አ ስራ ስምንት
የተጣራ ትርፍ እና የትርፍ ክፍ ፍል
yTRF DRšN l¥?brt®C l¥kÍfL ytȉ TRF xl y¸ÆlW y¥?b„ -
Q§§ wÀ tkFlÖ ¥?b„ ÃSgßW TRF s!ñR X ÆSgßW TRF m\rT
1. y¸kFlW yTRF GBR lm-ÆbqEà mÃZ ÃlbT gNzB ktqns b“§
y¸tRF gNzB s!ñR nWÝÝ
ከላይ በቁጥር 1 የተገለጸው የተጣራ ትርፍ ሲኖር ለማህበርተኞቹ

2.
አንደየአክሰዩናቸው መጠን ይከፋፈላል፡፡

አንቀጽ አ ስራ ዘጠኝ
የማህበሩ መ ፍረስ
1. ማህበሩ በአባለት ውሳኔ፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም በንግድ ህጉ በተቀመጡት
ምክንያቶች ሊፈርስ ይችላል፡፡
2. ከማህበሩ ጠቅላላ ካፒታል ውስጥ ሶስት እሩብ የሚሆነው በከሰረ ጊዜ፣ ሥራ
አስኪያጁ ማህበሩ መፍረስ የሚገባው ወይም መቀጠል የሚኖርበት እንደሆነ
የማህበርተኞችን ውሣኔ መጠየቅ አለበት፡፡
አንቀጽ ሀያ
ስለ ሂሳብ አ ጣሪ
1. ማህበሩ የሚፈርስ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ማህበርተኞቹ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ
የሂሣብ አጣሪዎችን ከማህበሩ አባላት መሀከል ወይም ከአባላት ውጪ ይመርጣሉ፡፡
2. ለዚህ ጉዳይ የተመረጡት የሂሣብ አጣሪዎች የማህበሩን መፍረስ የሚመለከቱ
ጉዳዩቹን ሁሉ የማከናወን ሙሉ ስልጣን አለው፡፡
3. የሂሣብ አጣሪው የኩባኒያውን ንብረቶች በመሸጥ የኩባኒያውን ዕዳዎች ለመክፈል
ይችላሉ፡፡
አንቀጽ ሀያ አንድ
ማ ሻሻያ
ይህ የካት ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመተዳደሪያ ደንብ በንግድ ህጉ
መሰረት በአባላት ውሳኔ ሊሻሻል ይችላል፡፡

የማህበርተኞቹ ስም ፊርማ

1. ___________________ __________________
2. ___________________ __________________
3. ___________________ __________________

You might also like