You are on page 1of 22

ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 7፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

በመወሰኛዎችና በሥዕሎች ወይም ግራ ቀኝ ወገኖች በጽሑፍ በተስማሙበት መሠረት የቀረቡ የውሉ ልዩ ሁኔታዎች

71. የሥራዎች መጀመር


71.1 የሥራ መጀመሪያውን ቀን በውሉ ልዩ ሁኔታ ወይም መሐንዲሱ በሚያዘጋጀው የአስተዳደራዊ
ትዕዛዝ መሠረት የመንግሥት አካል ይወስናል፡፡
71.2.. ሥራዎች የሚፈጸሙበት የመጀመሪያ ቀን በግራ ቀኝ ወገኖች ስምምነት ካልተደረሰበት በስተቀር
የውል አሸናፊነት መግለጫ ከተሰጠ በኋላ ከ 120 ቀናት በላይ አይዘገይም፡፡
72. የሥራዎች መፈጸሚያ ጊዜ
72.1. የሥራዎች መጀመሪያ ቀን የሚወሰነው በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 71.1 በተጠቀሰው
የመጀመሪያ ቀን መሠረት ሲሆን በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 73 ከቀረበው የሥራዎች
ማራዘሚያ ጊዜ የተለየ አይሆንም፡፡
72.2. ተቋራጩ ሥራዎችን ተቋራጩ ባስረከበውና መሐንዲሱ ባጸደቀቀለት የትግበራ መርሐ ግብር
መሠረት በማከናወን በታሰበው የማጠናቀቂያ ጊዜ ውስጥ ያጠናቅቃቸዋል፡፡
72.3. ልዩ የትግበራ ጊዜን በተመለከተ ድንጋጌ ካለና ለተለያዩ የሥራ ክፍሎች አንድ ተቋራጭ በአንድ
ውል ውስጥ ከአንድ በላይ ለሆነ የሥራ ክፍል ውል ከገባ ለተለያዩ ክፍሎች የተመደበ የትግበራ
ጊዜ ሊጠራቀም አይችልም፡፡
73. የታሰበው የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ መራዘም
ተቋራጩ ውሉን ለማጠናቀቅ የሚዘገይ ወይም የዘገየ እንደሆነ የታሰበው የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ
እንዲራዘምለት ተቋራጩን ሊጠይቅ የሚችለው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡
(ሀ) በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የተከሰተ ልዩ የአየር ሁኔታ
(ለ) ልምድ ባለው ተቋራጭ ቀድመው ሊገመቱ የማይችሉ ሰው ሠራሽ ወይም አካላዊ ሁኔታዎች
(ሐ) ሥራው በታቀደው የማጠናቀቂያ ጊዜ እንዳይጠናቀቅ የሚያደርግ የካሣ አጋጣሚ ከተከሰተ ወይም
የለውጥ ወይም ማስተካከያ ትዕዛዝ ከተሰጠ
(መ) አስተዳደራዊ ትዕዛዞች ከተቋራጩ ጉድለት በስተቀር በስሥራው ማጠናቀቂያ ጊዜ ላይ ተጽዕኖ ካደረሱ
(ሠ) የመንግሥት አካል በውሉ የተጠቀሰውን ግዴታውን መወጣት ካልቻለ
(ረ) በተቋራጩ ጉድለት ምክንያት ያልሆኑ ማናቸውም የሥራ መቋረጦች
(ሰ) ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት
(ሸ) በውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች የተጠቀሱ በተቋራጩ ጉድለት ምክንያት ያልሆኑ ማናቸውም ምክንያቶች
73.2. ተቋራጩ የሥራ መዘግየት እንደሚያጋጥም ባወቀ በ 15 ቀናት ውስጥ የታቀደውን የሥራ ማጠናቀቂያ
ጊዜ ለማራዘም ተገቢውን ጥያቄ ለማቅረብ እንዳቀደ መሐንዲሱን የሚያሳውቅ ሲሆን በመሐንዲሱና
በተቋራጩ መካከል ስምምነት ላይ እስካልተደረሰበት በስተቀር መግለጫ በደረሰው በ 21 ቀናት ውስጥ
ጥያቄው በጊዜው መመርመር ይችል ዘንድ ለመሐንዲሱ የጥያቄውን ሙሉና ዝርዝር መረጃ ያቀርባል፡፡
73.3. የተቋራጩ ዝርዝር ጥያቄ በደረሰው በ 21 ቀናት ውስጥ መሐንዲሱ መሐንዲሱ ከመንግሥት አካል ጋር
ወይም አግባብ ከሆነ ከተቋራጩ ጋር ከተመካከረ በኋላ ለተቋራጩ የጽሑፍ መግለጫ በመስጠት
የታሰበውን የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ያራዝማል፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ የተቋራጩ የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ
እንደማይራዘም ያሳውቀዋል፡፡
ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 7፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

73.4. ተቋራጩ መዘግየት ማጋጠሙን ቀደም ብሎ ማሳወቅ ካልቻለ ወይም የመዘግየት ችግር እንዲቀረፍ
መተባበር ሳይችል ቢቀር በዚህ ችግር የተነሳ ያጋጠመ መዘግየት አዲስ የታሰበውን የሥራ ማጠናቀቂያ
ጊዜ ለመገምገም ግምት ውስጥ አይገባም፡፡
74. የጊዜ መራዘም እንዲኖር የሚያስችሉ የካሣ ሁኔታዎች
74.1. የጊዜ ማራዘም እንዲኖር የሚያስችሉ የካሣ ገጠመኞች የሚከተሉት ናቸው፤
(ሀ) የመንግሥት አካል በተቋራጩ ተዘጋጅቶ በጸደቀው የሥራ መርሐ ግብር በተጠቀሰው ቀን ውስጥ የሥራ
ቦታውን ክፍል ማቅረብ ካልቻለ፤
(ለ) የመንግሥት አካል የሌሎችን ተቋራጮች የሥራ መርሐ ግብርን በውሉ በተጠቀሰው የውሉ ሥራ ላይ
ተጽዕኖ በሚያሳድር ሁኔታ ካስተካከለው፤
(ሐ) መሐንዲሱ ሥራው እንዲዘገይ ትዕዛዝ ካስተላለፈ ወይም ሥራው በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የሆኑ
ሥዕሎችን፣ መወሰኛዎችን ወይም መመሪያዎችን ማቅረብ ካልቻለ፤
(መ) ተቋራጩ ሥራውን ክፍት እንዲያደርግ ወይም ተጨማሪ ፍተሻዎችን እንዲያካሂድ በመሐንዲሱ ከታዘዘና ይህም ከሆነ
በኋላ በሥራው ላይ ጉድለት ካልተገኘ፤
(ሠ) መሐንዲሱ ያለምክንያት ንዑስ ውል የማያጸድቅ ከሆነ
(ረ) በመንግሥት አካል ምክንያት ወይም ለደህንነት ሲባል በሚፈለግ ተጨማሪ ሥራ ወይም ሌሎች ምክንያቶች ግምት ውስጥ
ያልገቡ ሁኑታዎች እልባት እንዲሰጥባቸው መሐንዲሱ ትዕዛዝ ካስተላለፈ፤
(ሰ) ሌሎች ተቋራጮች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ሌሎች የመንግሥት ክፍሎች፣ ወይም የመንግሥት አካል በውሉ
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ሥራቸውን ማከናወን ካልቻሉና ይህም መዘግየት ካስከተለ፤
(ሸ) ቅድመ ክፍያው ከዘገየ
(ቀ) መሐንዲሱ የጊዜያዊ ክፍያ ምሥክር ወረቀቶችን ያለምክንያት ካዘገየ
(በ) በውሉ ልዩ ሁኔታ የተጠቀሱ ወይም በመንግሥት አካል የተወሰኑ ሌሎች የካሣ ገጠመኞችና ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎች
74.2. የካሣ ገጠመኝ ሥራው ከታሰበለት የማጠናቀቂያ ጊዜ በፊት እንዳይጠናቀቅ የሚያደርግ ከሆነ የታሰበው የሥራ
ማጠናቀቂያ ጊዜ ይራዘማል፡፡ የታቀደው የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ መራዘም የሚችለውና የቀናቱ ብዛትም የሚወሰነው
በመሐንዲሱ ነው፡፡
74.3. ተቋራጩ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ባለመስጠቱ የተነሳ የሕዝብ ጥቅም ጉዳት የሚደርስበት እንደሆነ ተቋራጩ ካሣ
የማይገባው ይሆናል፡፡
75. ሥራን ማፍጠን
75.1. ተቋራጩ ሥራውን ከታሰበው የማጠናቀቂያ ጊዜ በፊት እንዲያጠናቅቅ የመንግሥት አካል ከፈለገ ተፈላጊው የሥራ
ፍጥነት እንዲከናወን ለማስቻል ተቋራጩ ለመሐንዲሱ የዋጋ ዝርዝር ዕቅድ እንዲያቀርብ ይደረጋል፡፡ የመንግሥት አካል
የቀረበውን የዋጋ ዝርዝር ዕቅድ ከተቀበለው የታቀደው የማጠናቀቂያ ጊዜ በአግባቡ የሚስተካከልና በሁለቱም ማለትም
በመንግሥት አካልና በተቋራጩ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
75.2. ሥራውን ለማፍጠን በተቋራጩ የቀረቡ የዋጋ ዝርዝር ዕቅዶች በመንግሥት አካል ተቀባይነትን ካገኙ በውሉ ዋጋ
የሚካተቱና እንደማስተካከያ የሚቆጠሩ ይሆናሉ፡፡
76. የሥራ አመራር ስብሰባ
76.1. መሐንዲሱ ወይም ተቋራጩ አንዱ ሌላውን በውሉ የተየቀሱ ሥራዎችን ክንዋኔ በተመለከተ የመንግሥት አካል ባለው
የእርካታ መጠን ላይ ለመወያየት፣ የቀሪ ሥራዎችን ዕቅድ ለመገምገምና የእርካታ መጓደልን ለመቅረፍ በሚወሰዱ ማናቸውም
ተፈላጊ እርምጃዎች
ክፍል 3፡ ውልላይ ለመስማማት በመደበኛ ስብሰባ ላይ እንዲገኝ ሊጋብዘው
ንዑስ ክፍል ይችላል፡፡
7፡ የውሉ አጠቃላይበእነዚህ ስምምነቶች ላይ
ሁኔታዎች
ተቋራጩ ሊያፈነግጥ ወይም እንቅፋት ሊሆን አይገባም፡፡
እነደነዚህ ዓይነት ስብሰባዎች የሚከናወኑት በመንግሥት አካልና በተቋራጩ የሚላኩ ሙሉ ሥልጣንና በቂ ልምድ ያላቸው
ማኅተሞች
ሠራተኞች በተገኙበትና ከሌሎች አግባብነት ካላቸው ተሳታፊዎች ጋር ነው፡፡ ለግምገማው -አስፈላጊ መመ በሆኑ ቋሚ አጀንዳዎች
ላይ ግራ ቀኝ ወገኖች የሚስማሙ
SlTRg#Ñ TKKl¾nTይሆናል፡፡ - መመ
76.2. መሐንዲሱ የሥራ አመራር ስብሰባ ቃለ ጉባዔ ከያዘ በኋላ ቅጅውን ለስብሰባው ተሳታፊዎችና ለመንግሥት አካል
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT
ያቀርባል፡፡ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ የግራ ቀኝ ወገኖች ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት መሐንዲሱ በሥራ አመራር
ስብሰባ ወቅት ይወስናል ወይም ከስብሰባው በኋላ ስብሰባው ላይ ለተሳተፉ በሙሉ በጽሑፍ ያሳውቃል፡፡
77. ቅድመ ማስጠንቀቂያ

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
77.1. በሥራዎች ጥራት ላይ ጎጅ ተጽዕኖ የሚያደርሱ ወይም የውሉን ዋጋ የሚጨምሩ ወይም የሥራዎችን አፈጻጸም
የሚያዘገዩ ወደፊት የሚያጋጥሙ ክስተቶች ወይም ገጠመኞች ሲኖሩ ተቋራጩ ባለው ፈጣን አጋጣሚ መሐንዲሱን
ያስጠነቅቃል፡፡ መሐንዲሱ ተቋራጩ የወደፊት ክስተቶች ወይም አጋጣሚዎች በውሉ ዋጋና በሥራው ማጠናቀቂያ ጊዜ
ላይ የሚኖረውን የሚጠበቅ ተጽዕኖ ግምት እንዲያቀርብ ይጠይቀዋል፡፡ ተቋራጬ ተፈላጊውን ግምት በተቻለው
ፍጥነት ያቀርባል፡፡
77.2. ተቋራጩ እንደነዚህ ዓይነት ክስተት ወይም ገጠመኝ በሥራው በሚሳተፍ በማናቸውም ግለሰብ እንደምን ሊወገድ
ወይም ሊቀነስ እንደሚችል ዕቅዶችን ለማዘጋጀትና ግምት ውስጥ ለማስገባት ብሎም ከዚህ የሚመነጩ ሌሎች
የመሐንዲሱን ትዕዛዞችን ለማከናወን ከመሐንዲሱ ጋር ይተባበራል
78. ሥራዎችን ለመተግበር የሚኖር መዘግየት
78.1. ተቋራጩ በውሉ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሥራዎችን ማጠናቀቅ ካልቻለ የመንግሥት አካል ያለምንም
ቅድመ ማስጠንቀቂያና በውሉ የተጠቀሱት ሌሎች ማስተካከያዎች እንደተጠበቁ ሆነው በሥራዎች መጠናቀቂያ ጊዜና
ተግባራዊ በሆኑበት ቀን መካከል ላሉት ለእያንዳንዱ ቀን ወይም በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 72 የተጠቀሰው
የሥራዎች ማጠናቀቂያ ቀን ለተራዘመበት የጊዜ መጠን ካሣ የሚገባው ሲሆን የካሣው መጠንም በውሉ አጠቃላይ
ሁኔታ ሐረግ 27 የተጠቀሰው ይሆናል፡፡ ሥራዎች በውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች ሐረግ 86 መሠረት በከፊል ተቀባይነት
ካገኙ በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 27 የተጠቀሰው የጉዳት ካሣ ተቀባይት ያገኘው የሥራ ክፍል የሥራውን አጠቃላይ
ዋጋ ግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ በሚኖር ምጣኔ ይቀንሳል፡፡
78.2. የመንግሥት አካል በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 78.1 የተጠቀሰው ከፍተኛ ካሣ የሚገባው ከሆነ ለተቋራጩ
መግለጫ በመስጠት የሚከተሉትን ሊያደርግ ይችላል፤
(ሀ) የአፈጻጸም ዋስትናውን ሊሰርዝ እንዲሁም/ወይም
(ለ) ውሉን ሊያቋርጥና
(ሐ) ሥራዎችን በሚዛናዊነት ለማከናወን በተቋራጩ ወጭ ከሦስተኛ ወገን ጋር ውለታ ሊገባ ይችላል፡፡
79. የሥራ መዝገብ
79.1. የሥራ መዝገብ በውሉ ልዩ ሁኔታ ካልተጠቀሰ በስተቀር በመሐንዲሱ አማካይነት በሥራ ቦታው የሚቀመጥ ሲሆን
የሚመዘገብበትም የሚከተለው መረጃ ነው፤
(ሀ) የአየር ሁኔታ፣ በአየር ሁኔታው የተነሳ የሥራ መራዘም፣ የሥራ ሰዓት፣ በሥራ ቦታው የሚሠሩ ተቀጣሪዎች ብዛትና
ዓይነት፣ የቀረቡ ጥሬ ዕቃዎች፣ በጥቅም ላይ የዋለ ቁሳቁስ፣ ለሥራ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቁሳቁስ፣ የተከናወኑ
ሙከራዎች፣ የተላኩ ናሙናዎች፣ ያልተጠበቁ ገጠመኞችና ለተቋራጩ የተላለፉ ትዕዛዛት ናቸው፡፡
(ለ) በሥራ ቦታው ላይ ሊፈተሸ የሚችልና ለተቋራጩ ክፍያ ሲሰላ ፋይዳ ያለው የተከናወነው ሥራና ቀርበው ጥቅም
ላይ የዋሉ ግብዓቶች ብዛትና ጥራት ዝርዝር መግለጫ፡፡ ማኅተሞች
ክፍል 3፡ ውል - ሁኔታዎች
ንዑስ ክፍል 7፡ የውሉ አጠቃላይ መመ
- መመ
SlTRg#Ñ TKKl¾nT
79.2. መግለጫው የሥራው መዝገብ ዋና አካል የሚሆን ቢሆንም ቅሉ አግባብነት እስካለው ድረስ በተለየ ሠነድ
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT
ሊመዘገብ ይችላል፡፡ መግለጫውን ለማዘጋጀት የሚረዳው ቴክኒካዊ ሕግ በውሉ ልዩ ሁኔታ የተጠቀሰው ይሆናል፡፡
79.3. ተቋራጩ በተከታታይ ሊለካና ሊረጋገጥ የማይችል ሥራን አገልግሎቶችንና ግብዓቶችን በተመለከተ
የሚያረጋግጠው ነገር መግለጫዎች በተገቢ ጊዜና በውሉ ልዩ ሁኔታ መሠረት መዘጋጀታቸውን ሲሆን ይህን ሳያደርግ
ቢቀር ግን የመሐንዲሱን ውሳኔ ይቀበላል፣ አለበለዛም በራሱ ወጭ ማስረጃ ያቀርባል፡፡
79.4. ሥራው እየተካሄደ እያለ በሥራ መዝገብ ውስጥ የሚመዘገቡ መረጃዎች በመሐንዲሱና በተቋራጩ ወይም
በተወካዩ የሚፈረምባቸው ይሆናል፡፡ ተቋራጩ ተቃውሞ ካለው የተቃወመው መረጃ በተመዘገበ በ 15 ቀናት ውስጥ
ቅሬታውን ለተቋራጩ ያቀርባል፡፡ ተቋራጩ መፈረም ወይም ቅሬታውን በፈቀደው ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ካልቻለ
በመዝገቡ ላይ በሰፈሩ መረጃዎች ላይ ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ተቆጥሮ ይወሰዳል፡፡ ተቋራጩ የሥራ መዝገቡን
በማንኛውም ጊዜ መመርመር የሚችል ሲሆን ከሠነዱ ላይ ሳይቀድ ለግል መረጃው አስፈላጊ ሆኖ ያገኘውን የመረጃ
ቅጅ ማግኘት ይችላል፡፡
79.5. ተቋራጩ ሲጠየቅ የሥራው መዝገብ በጥሩ ሁኔታ እንዲሆን የሚያስችል መረጃን ለመሐንዲሱ ያቀርባል፡፡
80. የሥራዎችና ጥሬ ዕቃዎች ምንጭና ጥራት

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
80.1. በውሉ መሠረት የተገዙ ሁሉም ዕቃዎች በጨረታ ሠነዱ ክፍል 5 መሠረት የተጠቀሱ ምንጭና ሀገር ይኖራቸዋል፡፡
80.2. ሥራዎች፣ ክፍሎችና ጥሬ ዕቃዎች ከመወሰኛዎች፣ ሥዕሎች፣ ቅኝቶች፣ ሞዴሎች፣ ናሙናዎች፣ ሂደቶችና
ሥራዎች በሚፈጸሙበት ጊዜ ውስጥ የመለየት ሥራ ለማከናወን ይቻል ዘንድ በመንግሥት አካል ወይም በመሐንዲሱ
ሊያዙ ለሚችሉ በውሉ ልዩ ሁኔታ ለተጠቀሱ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
80.3. በውሉ ልዩ ሁኔታ የተጠቀሰ ማናቸውም ቅድመ የቴክኒክ ተቀባይነት ተቋራጩ ለመሐንዲሱ በሚያቀርበው
መጠይቅ መሠረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡ መጠይቁ የሚያካትተው የውሉን መለያ ቁጥር፣ የሥራ ክፍሉን ቁጥር፣ አግባብ
ከሆነ ይህ ተቀባይት ተፈጻሚ የሚሆንበትን ቦታ ነው፡፡ በጥያቄው የተጠቀሱ ክፍሎችና ጥያቄዎች የሥራዎች አካል
ከመሆናቸው በፊት ለተቀባይነታቸው መሥፈርት እንዳሟሉ በመሐንዲሱ የምሥክር ወረቀት ሊሰጥባቸው ይገባል፡፡
80.4. በሥራዎች ወይም በምርት ክፍሎች ውስጥ የሚካተቱ ጥሬ ዕቃዎች ወይም ግብዓቶች በቴክኒክ በዚህ መልኩ
ተቀባይትን ቢያገኙም ውድቅ ሊደረጉ የሚችሉና ቀጣይ ምርመራ ጉድለት ወይም ብልሽት ካገኘባቸው ወዲያውኑ
በተቋራጩ ሊተኩ ይገባል፡፡ ተቋራጩ ውድቅ የተደረጉ ጥሬ ዕቃዎችን የመጠገንና በመልካም ሁኔታ ላይ እንዲገኙ
የማድረግ ዕድል ቢሰጠውም ቅሉ እነዚህ ጥሬ ዕቃዎች በሥራዎች ለመካተት ተቀባይነት ሊያገኙ የሚችሉት በተጠገኑና
በተስተካከሉ ሥራዎች መሐንዲሱ ከረካ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
81. ፍተሻና ሙከራ
81.1. ተቋራጩ የሚያረጋግጠው ነገር መሐንዲሱ ጥሬ ዕቃዎችንና የሥራ ክፍሎችን እንዲቀበላቸው ወደ ሥራ ቦታው
በጊዜ መላኩን ነው፡፡ በዚህ ረገድ ተቋራጩ የሚያጋጥሙትን ውጣ ውረዶች በቅጡ ሙሉ በሙሉ እንደተረዳቸው
የሚወሰድ ሲሆን ግዴታውን ለመወጣት ለዘገየበት ጊዜ ቅድመ ክፍያ አይፈቀድለትም፡፡
81.2. መሐንዲሱ በራሱ ወይም በተወካዩ ሥራዎችን፣ ክፍሎችንና አሠራሮችን የመፈተሽ፣ የመመርመርና የመለካትና
የሥራ ክፍሎች፣ ጥሬ ዕቃዎችና አሠራሮች ተገቢው ጥራትና ብዛት እንዳላቸው ለማረጋገጥ በውሉ መሠረት የዝግጅት
ሂደትንና አመራረትን የመፈተሽ መብት አለው፡፡
ማኅተሞች
- መመ
- መመ
ክፍል 3፡ ውል
SlTRg#Ñ TKKl¾nT ንዑስ ክፍል 7፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT
81.3. ለእነዚህ ሙከራዎችና ፍተሻዎች ተቋራጩ የሚከተሉትን ያከናውናል፤
(ሀ) ለመሐንዲሱ ድጋፍ፣ የሙከራ ናሙና፣ ክፍሎችን፣ ማሽኖችን፣ ቁሳቁስ፣ መሣሪያ ወይም ጥሬ ዕቃና
ጉልበት ለፍተሻና ሙከራ በሚያስፈልጉበት ሁኔታ ለጊዜውና ያለክፍያ ያቀርባል፡፡
(ለ) ለሙከራዎች በሚመደብ ቦታና ጊዜ ከመሐንዲሱ ጋር ይስማማል፤
(ሐ) ሙከራዎች የሚከናወኑበት ቦታ ተቀባይነት ባለው ጊዜ ለመሐንዲሱ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
81.4. መሐንዲሱ ፍተሻው እንዲካሄድ በተስማሙበት ቀን መገኘት ካልቻለ ተቋራጩ በመሐንዲሱ ካልታዘዘ በስተቀር
መሐንዲሱ እንዳለ በመቆጠር ተቋራጩ ፍተሻውን ያከናውናል፡፡ ተቋራጩ የተረጋገጡ የፍተሻ ውጤት ቅጅዎችን
ለመሐንዲሱ የሚያቀርብ ሲሆን መሐንዲሱም በበኩሉ በፍተሻው ጊዜ ባይገኝም ለውጤቱ ግን ተገዥ ይሆናል፡፡
81.5. የሥራ ክፍሎችና ጥሬ ዕቃዎች በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ የተጠቀሱ ፍተሻዎችን ካለፉ መሐንዲሱ ተቋራጩን
ያሳውቀዋል ወይም የሥራ ሂደቱን ምሥክር ወረቀት ይቀበለዋል፡፡
81.6. መሐንዲሱና ተቋራጩ በፍተሻ ውጤቱ ካልተስማሙ እያንዳንዳቸው አንዱ ለሌላው ይህ አለመግባባት በተከሰተ
በ 15 ቀናት ውስጥ አመለካከቱን ይገልጣል፡፡ መሐንዲሱ ወይም ተቋራጩ ፍተሻዎች በተመሳሳይ ደንብና ሁኔታ ወይም
ከግራ ቀኝ ወገኖች አንዱ ከጠየቀ በጋራ ስምምነት በሚመረጥ ባለሙያ እንዲደገሙ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ሁሉም የፍተሻ
ሪፖርቶች ለመሐንዲሱ የሚቀርቡ ሲሆን መሐንዲሱም የእነዚህን ፍተሻዎች ውጤት ለተቋራጩ ይልክለታል፡፡ የድጋሚ
ፍተሻዎች ውጤት ማጠቃለያ ይሆናል፡፡ የእንደገና ፍተሻዎች ወጭ የሚሸፈነው ድጋሚ ፍተሻው ሲካሄድ ቀድሞ ይዞት
የነበረው አመለካከት ውድቅ በተደረገበት ወገን ነው፡፡
81.7. መሐንዲሱና እርሱ ሥልጣን የሰጣቸው ግለሰቦች ተግባራቸውን ሲፈጽሙ የምርት ዘዴንና አተገባርን በተመለከተ
የሚኖርን የፍተሻና ምርመራ መረጃን ማወቅ ለሚገባቸው ግለሰቦች ብቻ ያቀርባል፡፡
82. ውድቅ መደረግ

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
82.1. የተጠቀሰው ጥራት የሌላቸው የሥራ ክፍሎችና ጥሬ ዕቃዎች ውድቅ ይደረጋሉ፡፡ ውድቅ በተደረገው የሥራ ክፍል
ወይም ጥሬ ዕቃ ላይ ልዩ ምልክት ሊደረግበት ይችላል፡፡ ይህ የሚደረገው ከሌላ ዕቃ ጋር እንዳይቀላቀሉና ዋጋቸውን
እንዳያጡ ለማድረግ ነው፡፡ ውድቅ የተደረጉ የሥራ ክፍሎችና ጥሬ ዕቃዎች ከሥራ ቦታው በተቋራጩ የሚወገዱት
መሐንዲሱ በሚያሳውቀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሲሆን ይህ ተግባራዊ የማይሆን ከሆነ ግን መሐንዲሱ በተቋራጩ ወጭና
ኃላፊነት ያስወግዳቸዋል፡፡ ውድቅ የተደረጉ የሥራ ክፍሎችና ጥሬ ዕቃዎች የተካተቱበት ማናቸውም ሥራ ውድቅ
ይረደጋል፡፡
82.2. መሐንዲሱ ሥራዎች እየተከናወኑ እያለና ሥራዎች ከመጀመራቸው በፊት በሚከተሉት ላይ የመወሰን ሥልጣን
አለው፤
(ሀ) በመሐንዲሱ አስተያየት በውሉ መሠረት ያልቀረቡ የሥራ ክፍሎችንና ጥሬ ዕቃዎችን በእነዚህ የጊዜ
ገደቦች ውስጥ ከሥራ ቦታው ማስወገድ፤
(ለ) አግባብነት ያላቸውና ምቹ የሆኑ የሥራ ክፍሎችንና ጥሬ ዕቃዎችን መተካት ወይም
(ሐ) በፊት ያለ ፍተሻ ወይም ቅድመ ክፍያ እንደተጠበቀ ሆኖ እርሱ ኃላፊነት የወሰደባቸው በተቋራጩ
የተከናወኑ የሥራ ክፍሎች፣ ጥሬ ዕቃዎች፣ አሠራሮችና ዲዛይን በመሐንዲሱ አስተያየት በውሉ
መሠረት ያልሆነ እንደሆነ ማንኛውንም ሥራ የማፍረስና በአግባቡ መልሶ የመሥራት ወይም በበቂ
ሁኔታ የመጠገን መብት አለው፡፡

ማኅተሞች
- መመ
ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 7፡ የውሉ- አጠቃላይ
መመ ሁኔታዎች
SlTRg#Ñ TKKl¾nT
82.3. መሐንዲሱ በተቻለ ፍጥነት የተባለውን h#lT
ጉድለት ዝርዝርðR¥ãC
y¥Ynbb# ሁኔታxl#bT
በመግለጽ ውሳኔውን በጽሑፍ ለተቋራጩ
ያቀርባል፡፡
82.1. ተቋራጩ ባለበሌለ ፍጥነትና በራሱ ወጭ የተጠቀሱ ጉድለቶችን በመልካም ሁኔታ ላይ እንዲገኙ ያደርጋል፡፡
ተቋራጩ ለዚህ ትዕዛዝ ተገዥ ካልሆነ ይህን ተመሳሳይ ሥራ ለማሠራት የመንግሥት አካል ሌላ ግለሰብ የመቅጠርና
ለተቋራጩ ሊከፈል ከነበረው የገንዘብ መጠን ላይ የመቀነስ መብት አለው፡፡
82..5. የዚህ ውል አጠቃላይ ሁኔታ ድንጋጌ በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ 19 ና 78 በተጠቀሰው የመንግሥት አካል ይገባኛል
መብት ላይ ተጽእኖ አያደርስም፡፡
83. የማሽንና ጥሬ ዕቃ ባለቤትነት
83.1 በተቋራጩ የቀረቡ ሁሉም ቁሳቁሶች፣ ጊዜያዊ ሥራዎች፣ ማሽንና ጥሬ ዕቃ ወደ ሥራ ቦታው ሲመጡ ሙሉ
በሙሉ ሥራውን ለማጠናቀቅ ብቻ ታስበው መሆን የሚገባ ሲሆን ከአንድ የሥራ ቦታ ወደሌላ ከማንቀሳቀስ በስተቀር
መሐንዲሱ ሳያውቀው እዚህ የተጠቀሱትን ንብረቶች ተቋራጩ ማንሳት አይችልም፡፡ የመሐንዲሱ እውቅና ድጋፍ ሰጭ
ሠራተኞችን የጉልበት ሠራተኞችን፣ ቁሳቁስ፣ ጊዜያዊ ሥራዎች፣ ወደ ሥራ ቦታው የሚመጡና ከሥራ ቦታው
የሚወጡ ማሽኖችንና ጥሬ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን አይመለከትም፡፡
83.2. የውሉ ልዩ ሁኔታ እዚህ ሊያቀርብ የሚችለው ነገር ሁሉም ቁሳቁሶች፣ ጊዜያዊ ሥራዎች፣ በተቋራጩ ወይም
በእርሱ ከፍተኛ ይዞታ በተያዘ ኩባንያ ባለቤትነት ያሉ ማሽኖችንና ጥሬ ዕቃዎችን ሥራው እስከሚጠናቀቅ ባለው ጊዜ
ውስጥ ሲቀርቡ፤
(ሀ) ኃላፊነቱ የመንግሥት አካል ይሆናል ወይም፣
(ለ) ለመንግሥት አካል ጥቅም ሲባል ውለታ ሊገባባቸው ይችላል ወይም
(ሐ) የፍላጎት ቅደም ተከተል ወይም ደኅንነትን በተመለከተ ለሌላ ቅድመ ዝግጅት የተዳረጉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
83.3. በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 21 መሠረት ተቋራጩ ውሉን በመተላለፉ የተነሳ ውሉ በሚቋረጥበት ጊዜ
የመንግሥት አካል ሥራውን ለማጠናቀቅ በሥራ ቦታው የሚገኙ ቁሳቁሶችን፣ ጊዜያዊ ሥራዎችን፣ ማሽኖችንና ጥሬ
ዕቃዎችን የመጠቀም መብት አለው፡፡
83.4. ተቋራጩ ወደ ሥራ ቦታው የመጡ ቁሳቁሶችን፣ ጊዜያዊ ሥራዎችን፣ ማሽንና ጥሬ ዕቃዎችን ለመከራየት የተገባ
ማናቸውም የውል ስምምነት ሊኖረው የሚገባ ድንጋጌ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 21 ተግባራዊ ከሆነበት ቀን

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ጀምሮና የመንግሥት አካል ሁሉንም የኪራይ ክፍያዎች መፈጸም ከጀመረበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ
የመንግሥት አካል በሚያቀርበው የጽሑፍ ጥያቄ መሠረት የንብረቶች ባለቤት ከተቋራጩ ጋር በገባው ውል ደንብና
ሁኔታዎች መሠረት ቁሳቁሶችን፣ ጊዜያዊ ሥራዎችን፣ ማሽን ወይም ጥሬ ዕቃዎችን ለመንግሥት አካል የሚያቀርብ
ሲሆን ይህ ግን የማይመለከተው በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 21.5 መሠረት የተጠቀሰው ሥራ እንዲጠናቀቅ
የመንግሥት አካል የቀጠረው ግለሰብ እንዲጠቀምባቸው የማድረግ መብቱን ነው፡፡
83.5. ሥራዎች ሳይጠናቀቁ ውሉ በሚቋረጥበት ጊዜ ተቋራጩ ለመንግሥት አካል ማቅረብ ያለበት ማናቸውንም
ማሽን፣ ጊዜያዊ ሥራዎች፣ ቁሳቁስ ወይም ጥሬ ዕቃ ወይም መንግሥት ኃላፊነት የወሰደባቸውን ወይም በውሉ
አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 83.2 መሠረት ውለታ የተገባባቸውን ንብረቶች ነው፡፡ ተቋራጩ ይህን መፈጸም ሳይችል ቢቀር
የምንግሥት አካል የተባሉት ማሽኖች፣ ጎዜያዊ ሥራዎች፣ ቁሳቁስና ጥሬ ዕቃዎችን ለመያዝና የወጣውን ወጭ
ተቋራጩ እንዲከፍል ለማድረግ የሚመጥን መስሎ እስከታየው አግባብነት ያለውን እርምጃ ይወስዳል፡፡

ማኅተሞች
- መመ
SlTRg#Ñ TKKl¾nT
- መመ

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 7፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

ሰ. ተቀባይነትና የጉድለት ባለዕዳነት


84. አጠቃላይ መርሆዎች
ሥራዎችን በጊዜያዊነትም ሆነ ለመጨረሻ ጊዜ ለመቀበል ሲባል በመሐንዲሱ የሚደረግ ሥራዎችን የማረጋገጥ ሥራ
የሚፈጸመው ተቋራጩ ባለበት ነው፡፡ የተቋራጩ አለመኖር ሥራዎችን ለማረጋገጥ እንቅፋት የማይሆነው ሥራዎችን
የማረጋገጥ ተግባር ከመፈጸሙ ከ 30 ቀናት በፊት በጉዳዩ ዙሪያ ከተቋራጩ ጋር በአግባቡ ውይይት ተደርጎ ከሆነ ብቻ
ነው፡፡
84.2. ልዩ አጋጣሚዎች የሥራዎችን ሁኔታ ለማረጋገጥ የማይቻል ካደረገው ወይም ለጊዜያዊነትም ሆነ ለመጨረሻ ጊዜ
ተቀባይነት በተመደበው ጊዜ ውስጥ ተቀባይነት እንዳላቸው ወስዶ ለመቀጠል ይህን አለመቻል የሚያረጋግጥ መግለጫ
መሐንዲሱ ከተቻለ ከተቋራጩ ጋር ከመከረ በኋላ ያዘጋጃል፡፡ ሥራዎችን የማረጋገጥ ተግባር የሚከናወነውና
በመሐንዲሱ የተቀባይነትና ውድቅ ማድረጊያ መግለጫ የሚዘጋጀው ይህ አለመቻል በተወገደ በ 30 ቀናት ውስጥ ነው፡፡
ተቋራጩ ሥራዎችን ለተቀባይነት ምቹ በሆኑበት ሁኔታ ለማቅረብ ያለበትን ግዴታ ለመወጣት እነዚህን አጋጣሚዎች
ውድቅ ማድረግ አይችልም፡፡
85. ሥራዎች ሲጠናቀቁ የሚኖር ፍተሻ
85.1. የተጠቀሱት ማረጋገጫዎችና ፍተሻዎች በተቋራጩ ወጭ እስከሚከናወኑ ድረስ ሥራዎች ተቀባይነት አያገኙም፡፡
ተቋራጩ እነዚህ ማረጋገጫዎችና ፍተሻዎች መካሄድ የሚጀምሩበትን ጊዜ ለመሐንዲሱ ያሳውቃል፡፡
85.2. የውሉን ደንቦችና ሁኔታዎች የማያሟሉ ሥራዎች ወይም ከውሉ ደንቦችና ሁኔታዎች ውጭ የተከናወኑ ሥራዎች
ወይም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የንግድ ተሞክሮ ውጭ የተከናወኑ ሥራዎች አስፈላጊ ሆኖ
ከተገኘ በተቋራጩ ፈርሰው እንደገና ሊገነቡ ወይም መሐንዲሱ እስኪረካ ድረስ ሊጠገኑ የሚገባ ሲሆን ይህ የሚሆነው
ግን መሐንዲሱ በሚያስተላልፈው ትዕዛዝ በተቋራጩ ወጭ ከሚዘጋጅ መግለጫ በኋላ ወዲያውኑ ነው፡፡ መሐንዲሱ
እዚህ በተጨማሪነት ሊጠይቅ የሚችለው ነገር
ተቋራጩ ሥራዎችን አፍርሶ መልሶ እንዲሠራ ወይም ተቀባይት የሌላቸው ጥሬ ዕቃዎች ግልጋሎት ላይ ውለው ከሆነና
የተከናወኑትም በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 20 መሠረት በቀረቡት የማቋረጫ ጊዜ ውስጥ ከሆነ በተመሳሳይ የሥራ
ሁኔታዎች ውስጥ መሐንዲሱ እስኪረካ ድረስ እንዲጠገኑ ነው፡፡
86. በከፊት ተቀባይነት ማግኘት
86.1. የሕዝብ አካል የተለያዩ መዋቅሮችን፣ የመዋቅር ክፍሎችን፣ ሲጠናቀቁ የውሉ አካል የሚሆኑ ሥራዎችን
ሊገለገልባቸው ይችላል፡፡ በመንግሥት አካል የሚደረግ ማናቸውም መዋቅሮችን፣ የመዋቅር ክፍሎችንና የሥራ ክፍሎችን
በባለቤትነት የመያዝ ጉዳይ በቀጥይነት ደግሞ በጊዜያዊነት ተቀባይነት እንዲያገኙ ሊያደርጋቸው ይገባል፡፡ ነገር ግን
በአስቸኳይ ሁኑታ ሥራዎች ተቀባይነት ከማግኘታቸው በፊት በመንግሥት አካል ይዞታነት ሊወሰዱ የሚችሉት ውዝፍ
ሥራዎችን መሐንዲሱ ቆጥሮ ከለየና በዚህም ተቋራጬና መሐንዲሱ ቀደም ብለው ከተስማሙ ብቻ ነው፡፡ አንድ ጊዜ
የመንግሥት አካል መዋቅሮችንና የሥራ ክፍሎችን በይዞታነት ከወሰደ ተቋራጬ ከብልሹ አሠራር በስተቀር
ማናቸውንም ጉዳት የማስተካከል ግዴታ የለበትም፡፡
86.2. መሐንዲሱ ተቋራጬ በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረትና የሥራው ባሕሪ የሚፈቅድ ከሆነ የከፊል ተቀባይነትን
ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችል ግን መዋቅሮች፣ የመዋቅር ክፍሎች ወይም የሥራ ክፍሎች በውሉ በተገለጠው
ሁኔታ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ምቹ ከተደረጉ ብቻ ነው፡፡
86.3. በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረጎች 86.1 ና 86.2 የተጠቀሱትን ጊዜያዊ የከፊል ተቀባይነትን በተመለከተ የውሉ ልዩ
ሁኔታ በተለየ ሁኔታ ካላስቀመጠው በስተቀር በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 88 የተጠቀሰው የጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ
የሚጀምረው ጊዜያዊ ተቀባይነት ከተካሄደበት ቀን በኋላ ነው፡፡
ማኅተሞች
- መመ
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT - መመ
SlTRg#Ñ TKKl¾nT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 7፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

87. ጊዜያዊ ተቀባይነት


ሥራዎች የመንግሥት አካል ንብረት የሚሆኑት በማጠናቀቂያ ጊዜ የሚኖረውን ፍተሻ በአመርቂነት ካለፉና የጊዜያዊ
ተቀባይነት የምሥክር ወረቀት ከተሰጣቸው ነው፡፡
87.2. ተቋራጩ ለመሐንዲሱ መግለጫ በመስጠት የጊዚያዊ ተቀባይነት የምሥክር ወረቀት እንዲሰጠው ማመልከት
የሚችለው በእርሱ አስተያየት ሥራዎች ከመጠናቀቃቸውና ለጊዜያዊ ተቀባይነት ዝግጁ ከመሆናቸው ከ 15 ቀናት በፊት
ነው፡፡ መሐንዲሱ ደግሞ የተቋራጩ ማመልከቻ በደረሰው በ 30 ቀናት ውስጥ የሚከተሉትን ያከናውናል፤
(ሀ) ለተቋራጩ የጊዜያዊ ምሥክር ወረቀት ይሰጣል እንዲሁም ለመንግሥት አካል ቅጅውን የሚልክ ሲሆን
ይህን ሲያደርግ አግባብነት ካለው ቅሬታውን፣ ሥራዎች በውሉ መሠረት የተጠናቀቁበትንና ለጊዜያዊ
ምሥክር ወረቀት ዝግጁ የሚሆኑበትን ቀን ይጠቅሳል፡፡
(ለ) ምክንያት በማቅረብና የምሥክር ወረቀቱ እንዲሰጠው ሊያከናውነው የሚገባውን እርምጃ በመዘርዘር
ማመልከቻውን ውድቅ ማድረግ ናቸው፡፡
87.3. መሐንዲሱ በ 30 ቀናት ውስጥ የጊዜያዊ ተቀባይነት የምሥክር ወረቀት መስጠት ወይም የተቋራጩን ማመልከቻ
ውድቅ ማድረግ ካልቻለ በተጠቀሰው ቀን መጨረሻ የምሥክር ወረቀት እንደሰጠ ይቆጠራል፡፡ የጊዜያዊ ተቀባይነት
ምሥክር ወረቀት ተሰጠ ማለት ሥራዎች ሁሉ በአግባቡ ተከናወኑ ማለት አይደለም፡፡ ሥራዎች በውሉ ወስጥ በተለያዩ
ክፍሎች ከተከፈሉ ተቋራጩ ለእያንዳንዱ ክፍል የምሥክር ወረቀት እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፡፡
87.4. ሥራዎች የጊዜያዊ ተቀባይነት እንዳገኙ ተቋራጩ ጊዜያዊ መዋቅሮችንና ከውሉ አፈጻጸም ጋር ተያያዥ የሆኑና
አላስፈላጊ የሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን ያፈርሳል፣ ከሥራ ቦታውም ያስወግዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማናቸውንም እንቅፋት
በማስወገድ በውሉ በሚፈለገው መጠን የሥራ ቦታው ሁኔታ እንዲለወጥ ያደርጋል፡፡
87.5. የጊዜያዊ ተቀባይነት እንደተሰጠ ወዲያውኑ ሁሉንም የተጠናቀቁ ሥራዎችን የመንግሥት አካል ሊገለገልባቸው
ይችላል፡፡
88. የጉድለት ባለዕዳነት
88.1. ተቋራጩ በጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ ውስጥ በሥራዎች ማናቸውም ክፍል ላይ ያጋጠሙ ጉድለቶችንና ጉዳቶችን
ወደ መልካም ሁኔታ የመመለስ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን የጉድለቱ ምክንያቶችም የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፤
(ሀ) በተቋራጩ የቀረበ ብልሽት ያለበት ማሽን ወይም እንከን ያለበት አሠራር ወይም ዲዛይን
(ለ) በጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ ውስጥ ተቋራጩ ማናቸውንም የማለፍ ተግባራት ካከናወነ
88.2. ተቋራጩ በራሱ ወጭ በተቻለው ፍጥነት ጉድለቶችን ወይም ጉዳቶችን ወደ መልካም ደረጃ ማስተካከል አለበት፡፡
ለሁሉም ለተተኩ ወይም ለታደሱ ዕቃዎች የሚኖር የጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ እንደገና የሚጀምረው የመተካት ወይም
የማደስ ተግባር ለመሐንዲሱ አመርቂ ሆነው ከተገኙ ነው፡፡ ውሉ የከፊል ተቀባይነት እንዲኖር የሚያደርግ ከሆነ
የጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ የሚሠራው በምትኩ ወይም እድሳቱ ምክንያት ተጽዕኖ በደረሰባቸው የሥራዎች ክፍል ላይ
ነው፡፡
88.3. እንደዚህ ዓይነት ጉድለት ወይም ብልሽት በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 88.1 በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ሲከሰት
የመንግሥት አካል ወይም መሐንዲሱ ተቋራጩን ያሳውቀዋል፡፡ ተቋራጩ በመግለጫው ውስጥ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ
ጉድለት ወይም ጉዳት እንዲስተካከል ማድረግ ካልቻለ የመንግሥት አካል የሚከተሉትን ያከናውናል፤
(ሀ) በተቋራጩ ኃላፊነትና ወጭ ሥራዎችን ራሱ ማከናወን ወይም ሌላ ግለሰብ በመቅጠር ማከናወን
የሚችል ሲሆን በዚህ ሁኔታም የመንግሥት አካል ያወጣው ወጭ ለተቋራጩ ሲባል ከተያዘው
የዋስትና ገንዘብ ላይ ተቀናሽ ይሆናል፡፡ ማኅተሞች
ክፍል 3፡ ውልTKKl¾nT
SlTRg#Ñ - መመ
ንዑስ ክፍል 7፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
- መመ
(ለ) ውሉን ማቋረጥ h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT
88.4. የደረሰው ጉድለት ወይም ጉዳት የመንግሥት አካል ከሥራዎች የሚያገኘውን ጥቅም ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል
እንዲያጣ ካደረገው የመንግሥት አካል ማናቸውም የመፍትሔ አማራጭ እንደተጠበቀ ሆኖ የሥራ ክፍሎችን
ለማጠናቀቅና ጉድለት ያለባቸውን አፍርሶ ከቦታው ለማስወገድ ሲባል ያወጣውን ወጭ የማስመለስ መብቱ የተጠበቀ
ነው፡፡

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
88.5. በድንገተኛ ጊዜ ተቋራጩን በፍጥነት ማግኘት ሳይቻል ከቀረና ተገኝቶም ቢሆን ተገቢውን እርምጃ መውሰድ
ካልቻለ የመንግሥት አካል ወይም መሐንዲሱ ሥራውን በተቋራጩ ወጭ ሊያስቀጥሉት ይችላሉ፡፡ ይህ ሲሆን ግን
የመንግሥትም አካል ሆነ መሐንዲሱ ያከናወኑትን ተግባር ወዲያውኑ ለተቋራጩ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡
88.6. በውሉ ልዩ ሁኔታ የተጠቀሰው በተለደ ማርጀትና ማፍጀት ምክንያት የሚኖር የጥገና ሥራ በተቋራጩ ይከናወናል
የሚል ሲሆን ይህም ሥራ ያስከተለው ወጭ ለጊዜያዊ ክፍያ ተብሎ ከተያዘ የበጀት መደብ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ በውሉ
አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 44 በተጠቀሰው አጋጣሚ የሚደርስ የንብረት ማርጀት ወይም ጤናማ ያልሆነ አጠቃቀም በውሉ
አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 88 መሠረት የጥገና ወይም ምትክ ጥያቄ ካላስነሳ በስተቀር ከዚህ ግዴታ ውጭ የሚታይ
ይሆናል፡፡
88.7. የጉድለት ባለዕዳለት በውሉ ልዩ ሁኔታ በተጠቀሰው መልኩ የሚታይ ይሆናል፡፡ የጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ
በምክንያታዊነት ግልጽ ካልተደረገ 365 ቀናት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ የጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ የሚጀምረው ጊዜያዊ
ተቀባይነት ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
88.8. ጊዜያዊ ተቀባይነት ከተሰጠ በኋላና በዚህ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ የተጠቀሰው የጉድለት ተጠያቂነት
እንደተጠበቀ ሆኖ በሥራ ላይ ተጽእኖ ለሚያሳድሩ አደጋዎችና በእርሱ ችግር ላልተከሰቱ ምክንያቶች በሙሉ ተቋራጩ
ኃላፊነትን አይወስድም፡፡ ነገር ግን ተቋራጩ ኃላፊነት ያለበት ጊዜያዊ ተቀባይነት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ
ሕግ ባስቀመጠው መልኩ ግንባታው በትክክለኛነት ለመካሄዱ ነው፡፡
89. የመጨረሻ ተቀባይት
89.1. የጉድለት ተጠያቂነት ጊዜ ሲያበቃ ወይም ከአንድ በላይ የጉድለት ተጠያቂነት ጊዜ ካለ ይህ ጊዜ ሲያበቃና
ሁሉም ጉድለቶችና ጉዳቶች ከተስተካከሉ መሐንዲሱ የመጨረሻ ተቀባይነት የምሥክር ወረቀት ለተቋራጩ ቅጅ ደግሞ
ለመንግሥት አካል ይሰጣል፡፡ ይህን ሲያደርግ መሐንዲሱ በውሉ መሠረት በረካበት ሁኔታ ተቋራጩ ግዴታውን
ያጠናቀቀበትን ቀን በመጥቀስ ይሆናል፡፡ የመጨረሻ ተቀባይነት የምሥክር ወረቀት በመሐንዲሱ የሚሰጠው እላይ
የተጠቀሰው ቀን በተጠናቀቀ በ 30 ቀናት ውስጥ ወይም በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ሐረግ 88 መሠረት የታዘዙ ሥራዎች
መሐንዲሱ በረካበት ሁኔታ ከተጠናቀቁ ነው፡፡
89.2. መሐንዲሱ የመጨረሻ ተቀባይነት የምሥክር ወረቀት ፈርሞ ለመንግሥት አካልና ቅጅውን ደግሞ ለተቋራጩ
ካልሰጠ በስተቀር ሥራዎች እንደተጠናቀቁ አይቆጠሩም፡፡
89.3. የመጨረሻ ተቀባይት የምሥክር ወረቀት ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ተቋራጩና የመንግሥት አካል የመጨረሻ
የምሥክር ወረቀት ሲዘጋጅ ላልተሠሩ ማናቸውም ግዴታዎች ባለዕዳ ይሆናሉ፡፡ የእንደዚህ ዓይነት ግዴታ ባህሪና መጠን
የውሉን ድንጋጌዎች በመጥቀስ መወሰን ይቻላል፡፡

ማኅተሞች
SlTRg#Ñ TKKl¾nT - መመ
- መመ

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 8፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

ክፍል 8. የውሉ ልዩ ሁኔታዎች


የሚከተሉት የውሉ ልዩ ሁኔታዎች (ውልሁ) የውሉን አጠቃላይ ሁኔታዎች (ውአሁ) የሚያግዙ ይሆናል፡፡ በሁለቱ መካከል
መጣረስ ካጋጠመ እዚህ ያለው ድንጋጌ በውሉ አጠቃላይ ሁኔታ ካለው ድንጋጌ በላይ ይሆናሉ፡፡
የውአሁ ሐረግ ክፍል 8. የውሉ ልዩ ሁኔታዎች
ቁጥር
ሀ. አጠቃላይ ድንጋጌዎች
የውል ቁጥር፡
ውአሁ 1.2 (መ) የመንግሥት አካል፡ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ውአሁ 1.2 (ረ) ውሉ የአድሜዠርመንት ውል ነው
ውአሁ 1.2 (ሰ) ተቋራጩ፡ አሸናፊው ተቋራጩ ነው
ውአሁ 1.2 (ቀ) የጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ 365 ቀናት ናቸው
ለ. ውሉ
ውአሁ 7.1 (ኀ) በውአሁ ሐረግ 7.1 ከተዘረዘሩት ሠነዶች በተጨማሪ የሚከተሉት ሠነዶች የውሉ አካል ይሆናሉ፡
የለም
ውአሁ 8.1 የመንግሥት ሕግ፡ የኢትዮጵያ ሕግ ነው
ውአሁ 9.1 የውሉ ቋንቋ፡ እንግሊዝኛ
ውአሁ 10.2 ለመግለጫ፤ የመንግሥት አካል አድራሻ የሚከተለው ነው
የመንግሥት አካል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
በተለይ፡
ፎቅ/ክፍል ቁጥር
የመ.ሣ.ቁ፡ 79
ጎዳና
ከተማ ባሕር ዳር
ፖስታ መለያ
ሀገር ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር 058-205949
ፋክስ ቁጥር
ኢ-ሜይል አድራሻ

ለመግለጫ፤ የመንግሥት አካል አድራሻ የሚከተለው ነው


ተቋራጭ
በተለይ
ፎቅ/ክፍል ቁጥር
የመ.ሣ.ቁ፡
ጎዳና
ከተማ
ፖስታ መለያ

ማኅተሞች
- መመ
SlTRg#Ñ TKKl¾nT - መመ

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT


የውአሁ ሐረግ ክፍል 8. የውሉ ልዩ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል
ቁጥር ንዑስ ክፍል 8፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ሀገር ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር 058-205949
ፋክስ ቁጥር
ኢ-ሜይል አድራሻ
ውአሁ 11.1 ኃላፊነት ያለበት አባል (የአባሉን ስም ይጻፉ)
ውአሁ 12.1 የመንግሥት አካል መሐንዲስ
መሐንዲስ አልቲሜት ፕላን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር፣ አማካሪ
አርክቴክቶችና መሐንዲሶች
የመ.ሣ.ቁ፡ 17195
ጎዳና ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና፣ ባምቢስ መገናኛ፣ ምንትዋብ ሕንፃ
3 ኛ ፎቅ
ከተማ አዲስ አበባ
ፖስታ መለያ
ሀገር ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር 0115522925
ፋክስ ቁጥር 0115522928
ኢ-ሜይል አድራሻ

በተቋራጩ ሥልጣን የተሰጠው ኃላፊ


ሥልጣን የተሰጠው ኃላፊ ሥልጣን የተሰጠው ተወካይ
የመ.ሣ.ቁ፡ 17195
ጎዳና ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና፣ ባምቢስ መገናኛ፣ ምንትዋብ ሕንፃ
3 ኛ ፎቅ
ከተማ
ፖስታ መለያ
ሀገር ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር
ፋክስ ቁጥር
ኢ-ሜይል አድራሻ

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የውአሁ ሐረግ ክፍል 8. የውሉ ልዩ ሁኔታዎች
ክፍል
ቁጥር 3 ፡ ውል ንዑስ ክፍል 8፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የውአሁ 15.1 የሐረጉን ጽሑፍ ይሰርዙና የሚከተለውን ይተኩ
መሐንዲሱ በቀጣሪውና መተቋራጩ መካከል ባሉ የውሉ ጉዳዮች ዙሪያ ያለአድልዖ በውሉ
ደንቦች መሠረት ሁሉንም አጋጣሚዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡
እነዲዚህ ዓይነት ማናቸውም ውሳኔ፣ አስተያየት፣ ፍቃድ፣ የእርካታ መግለጫ፣ መጽደቅ፣ የዋጋ
ወይም ተግባር ግምት፣ ግልጽ ሊደረግ ወይም ሊከለስ ይችላል፡፡
የቀጣሪው ልዩ ማጽደቅ የሚፈለገው ለሚከተለው ነው፤
(ሀ) ከውሉ ዋጋ 15% በላይ ለሆኑ ሁሉም ተጨማሪ ወጭዎች ማረጋገጫ መስጠት
(ለ) ከውሉ ጊዜ 25% በላይ ለሆነ የታቀደ የፕሮጀክት ማራዘሚያ ቀን ማረጋገጫ መስጠት
(ሐ) በመሐንዲሱ ከሚወሰን ከድንገተኛ ሁኔታ በስተቀር ወይም የሁሉም ልዩነቶች ድምር የውሉን
ዋጋ ከ 10% በላይ ከጨመረው የልዩነት ትዕዛዝ መስጠት
(መ) ተቋራጩ ሥራ እንዲጀምር ወይም እንዲያዘገይ መመሪያ መስጠት
የውአሁ 16.1 የጨረታ ውል ዋጋ ከሚቀርብበት ቀነገደብ በኋላ የሕግና ደንብ መለወጥ የሚጨምር ወይም
የሚቀንስ ከሆነ ወይም ተቋራጩ በውሉ የተጠቀሰውን ግዴታውን ሲወጣ በደረሰበት ተጽእኖ ልክ
የማቅረቢያ ቀን የሚስተካከል ከሆነ፡፡
የውአሁ 17.1 ተቋራጩ፣ ንዑስ ተቋራጮችና ሠራተኞቻቸው
(ቀ)  የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት ከሚጥላቸው ቀረጦችና
ቀጥተኛ ያልሆኑ ግብሮች ነፃ መሆን አይችልም፡፡
የውአሁ 22.1 ላልተጠናቀቁ ሥራዎች የሚቀርብ የመቶኛ ማመልከቻ የመንግሥት አካል ሥራዎችን ለማጠናቀቅ
የሚያወጣቸውን ተጨማሪ ወጭዎች ግምት ውስጥ በማስገባት 10% ይሆናል፡፡
የውአሁ 26.1 አለመግባባት
የሐረጉን ጽሑፍ ይሰርዙና የሚከተለውን ይተኩ
ሥራዎች በሚፈጸሙበት ወቅት ወይም ከተጠናቀቁ በኋላ ወይም ከውል መቋረጥ፣ መተው፣
ወይም የውል ጥሰት በኋላ ሊኖር የሚችል ከውሉ ወይም ከሥራዎች አፈጻጸም ጋር በተያየዘ
የሚነሳ በቀጣሪውና በተቋራጩ መካከል የአስተያየት፣ መመሪያ፣ ውሳኔ፣ ማረጋገጫ ወይም የዋጋ
አገማመት ግጭት የሚያጋጥም ከሆነ የግጭቱ ጉዳይ በቅድሚያ በጽሑፍ ለመሐንዲሱና ቅጅው
ደግሞ ለሌላው ወገን የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ውሉ ቀደም ብሎ ተሰርዞ ካልሆነ በስተቀር ተቋራጩ በማንኛውም ሁኔታ ተገቢውን ጥንቃቄ


በማድረግ ሥራውን የሚቀጥል ሲሆን በግልግል አቅርቦት መልኩ ማስተካከያ የማይኖር ከሆነ
ተቋራጩና ቀጣሪው ለመሐንዲሱ ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
የውአሁ 26.2 የግጭት አፈታት ስነ ሥርዓት
የሐረጉን ጽሑፍ ይሰርዙና የሚከተለውን ይተኩ
መሐንዲሱ ግጭት መኖሩ በተገለጠለት በ 60 ቀናት ውስጥ ውሳኔውን በጽሑፍ ያሳውቃል፡፡

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT
የውአሁ ሐረግ ክፍል 8. የውሉ ልዩ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል
ቁጥር ንዑስ ክፍል 8፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የውአሁ 26.3 የሐረጉን ጽሑፍ ይሰርዙና የሚከተለውን ይተኩ
ቀጣሪውም ሆነ ተቋራጩ በመሐንዲሱ ውሳኔ ከሁለቱ አንዱ መርካት ካልቻለ ወይም መሐንዲሱ
ግጭት አለ የሚል መግለጫ በደረሰው በ 60 ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ማሳወቅ ሳይችል ቢቀር
ከግራ ቀኝ ወገኖች አንዱ የመሐንዲሱ የጽሑፍ ውሳኔ በደረሰ በ 30 ቀናት ውስጥ ወይም

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የተባለው 60 ቀን በተጠናቀቀ በ 30 ቀናት ውስጥ ጉዳዩን ለአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ያቀርባል
የመረጃውንም ቅጅ ለመሐንዲሱ ይሰጣል፡፡ ሁለቱም ግራ ቀኝ ወገኖች እላይ በተጠቀሱት 30
ቀናት ውስጥ ግጭቱን ለገላጋይ የማያቀርቡ ከሆነ የመሐንዲሱ ውሳኔ የመጨረሻና ቀያጅ
ይሆናል፡፡

ግጭቱን በተመለከተ ውሳኔ እንዲሰጥበት የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የሚጠየቀው በቅድሚያ
ግራ ቀኝ ወገኖች ግጭቱን በስምምነት ለመፍታት ከሞከሩ በኋላ ነው፡፡
የውአሁ 26.4 ለዚህ ውል ምንም ገላጋይ አይመደብም፡፡ በመሐንዲሱ ውሳኔ መርካት አለመቻል ካጋጠመ ጉዳዩን
የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ውሳኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡ በውሳኔው ያልረካ አካል ሥልጣን
ላለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሊል ይችላል፡፡
የውአሁ 26.5 "በዚህ ውል ምንም ፍርድ ሰጭ አካል አይሰየምም"
የውአሁ 27.1 የሁሉም ሥራዎች የጉዳት ካሣ በቀን ተቀባይነት በሌለው መዘግየት ከመጨረሻ የውል ዋጋ 0.1%
ነው፡፡ ለአጠቃላይ ሥራው የጉዳት ካሣ ከፍተኛ መጠን ከመጨረሻ የውሉ ዋጋ 10% ይሆናል፡፡
የውአሁ 50.1 ተግባራዊ አይሆንም
ሐ. የመንግሥት አካል ግዴታዎች
የውአሁ 30.2 የመንግሥት አካል ለተቋራጩ የሚከተሉትን ተጨማሪ ድጋፎች ያደርጋል፤
ቦታውን መጎብኘት፣ የፕሮጀክት ግምገማ ስብሰባዎችን ማቀናጀት፣ ዲዛይኑንና የተጠየቀውን
መረጃ ማብራራት፡፡
የውአሁ 30.3 በመንግሥት አካልና በመሐንዲሱ የሚቀርቡ ሠነዶች የሚከተሉት ናቸው፤
ባለ ዋጋ ዝርዝር የጨረታ ሠነድ፣ የመሐንዲስ ዲዛይን (የኤሌክትሮ ማካኔካል) ብሉ ፕሪንት
መ. የተቋራጩ ግዴታዎች
የውአሁ 31.1 ተቋራጩ የተቀባይነት ደብዳቤ/የተፈረመ ውል በደረሰው በ 15 ቀናት ውስጥ የሥራዎች የተከለሰ
መርሐ ግብር ያቀርባል
የውአሁ 34.5 (ለ) የመንግሥት አካል ቅድመ ማጽደቅ የሚፈለገው ለሚከተሉት ነው፤ ልዩ ንዑስ ተቋራጮችን
ለመምረጥ፣ የጥሬ ዕቃ ጥራት ማጽደቅና የፍተሻ ውጤት መፈተሽ ወዘተ ናቸው፡፡
የውአሁ 30.3 የሌሎች ተቋራጮች የድርጊት መርሐ ግብር የውሉ አካል አይሆንም
የውአሁ 38.3 በቅድመ ሁኔታዎች ድርጊት መርሐ ግብር የተጠቀሰው ሥራውን ለማከናወን የተቀጠሩ
ሠራተኞች የድርጊት መርሐ ግብር የሚከተለው ነው፡ የውሉ አካል ይሆናል፡፡

ማኅተሞች
- መመ
- መመ
SlTRg#Ñ TKKl¾nT
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT
የውአሁ ሐረግ ክፍል 8. የውሉ ልዩ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል
ቁጥር ንዑስ ክፍል 8፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የውአሁ 39.2(ለ) የባለዕዳነት ጠቅላላ ድምር፡ የውሉን ዋጋ ሊበልጥ አይችልም
የውአሁ 40.1 ዝቅተኛው የመድን ዋስትና ሽፋንና ተቀናሾች የሚከተሉት ናቸው፤
(ሀ) ለሥራዎች፣ ማሽኖችና ጥሬ ዕቃዎች የሚኖር የመድን ዋስትና ከፍተኛው መጠን
ከአጠቃላይ የውሉ ዋጋ 110% ይሆናል፤
(ለ) ለሥራዎች፣ ማሽኖችና ጥሬ ዕቃዎች የሚኖር የመድን ዋስትና ተቀናሽ ብር
500,000 ሲሆን ይህም ለቁሳቁስ ኪሣራና ጉዳት ሽፋን ይሆናል፤
(ሐ) ለቁሳቁሶች የሚኖር ዝቅተኛው የመድን ዋስትና ሽፋን ውሉን ለመፈጸም ከሚፈለገው
የቁሳቁስ ዋጋ 100% ነው፡፡
(መ) ለቁሳቁሶች የሚኖር የመድን ዋስትና ተቀናሽ ብር 250,000 ሲሆን ይህም ለቁሳቁስ
ኪሣራና ጉዳት ሽፋን ይሆናል፤

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
(ሠ) ለንብረት የሚኖር ዝቅተኛው የመድን ዋስትና ሽፋን ባልተገደበ ክስተት ውስጥ
በክስተት (ረ) ብር 2,000,000 ነው፡፡
(ሰ) ለንብረት የሚኖር የመድን ዋስትና ተቀናሽ ብር 250,000 ነው፡፡
(ረ) ለግለሰብ አካል ጉዳት ወይም ሞት የሚኖር ዝቅተኛው የመድን ዋስትና ሽፋን ያለተቀናሽ
ባልተገደበ ክስተት ውስጥ በክስተት ያለተቀናሽ ብር 50,000 ነው፡፡
የውአሁ 40.3 አደጋዎችንና የፍታብሔር ባለዕዳነት ዋስትናን በተመለከተ የመድን ዋስትና ሽፋን ባለዕዳነት መጠን
የሚሆነው  ያልተገደበ፣ በክስተትች ብዛት፣ 10/በክስተት
(2)  በገደብ
የውአሁ 41.1 ተቋራጩ የተቀባይነት መግለጫ በደረሰው በ 7 ቀናት ውስጥ የአተገባበር መርሐ ግብር የሚያቀርብ
ይሆናል፡፡
የሥራዎች አተገባበር ድርጊት መርሐ ግብር ዝርዝር ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፤
የሰው ኃይል ዝርዝር ስምሪት፣ የገንዘብ ዕቅድ፣ የጥሬ ዕቃ ዝርዝር፣ የማሽን ዕቅድ ወዘተ ናቸው
የውአሁ 41.4 በድርጊት መርሐ ግብር መካከል ያለ ጊዜ 120 ቀናት ናቸው፡፡
የተሻሻለ የድርጊት መርሐ ግብርን ዘግይቶ በማስገባት የተነሳ የሚያዝ የገንዘብ መጠን
ለእያንዳንዱ መዘግየት ከውል ዋጋ 1% ነው፡፡
የውአሁ 50.1 ተግባራዊ አይሆንም
የውአሁ 58.1 የአፈጻጸም ዋስትና የገንዘብ መጠን፡ ከውሉ ዋጋ 10% ነው፡፡
የውአሁ 58.4 ተቀባይነት ያላቸው የአፈጻጸም ዋስትና ዓይነቶች፡ የመድን ወይም የባንክ ዋስትና፡፡
የገንዘብ መጠን፡ የኢትዮጵያ ብር
የውአሁ 58.8 የአፈጻጸም ዋስትና የሚለቀቀው፡ 50% የጊዜያዊ ተቀባይነት ሲያበቃና 50% የመጨረሻ ዋስትና
ሲያበቃ ነው፡፡

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የውአሁ ሐረግ ክፍል 8. የውሉ ልዩ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል
ቁጥር ንዑስ ክፍል 8፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ሠ. ለተቋራጩ የሚፈጸሙ ክፍያዎች
የውአሁ 59.1 በዚህ ውል ውስጥ የሚኖሩ ለተቋራጩ የሚፈጸሙ ሁሉም ክፍያዎች በብር የሚከፈሉ ሲሆን
ተቋራጩ ከዚህ ውል ጋር ተያያዥ ለሆኑ የቀረጥ ቴምብር ክፍያዎች ኃላፊነትን ይወስዳል፡፡
የውአሁ 60.1 ለተቋራጩ የሚቀርብ ቅድመ ክፍያ በራሱ ጥያቄ የሚወሰን ይሆናል፡፡
የውአሁ 60.2 የቅድመ ክፍያው የገንዘብ መጠን የሚሆነው የሚከተለው ነው፡- ከተእታ ጋር የውሉን ዋጋ 10%
ሲሆን የሚከፈለውም ሥራ ከተጀመረበት ቀን 30 ቀናት በላይ ሳይዘገይ 10% የአፈጻጸም ዋስትና
እንዲሁም ተፈላጊ የባንክ ዋስትና በማቅረብ ይሆናል፡፡
የውአሁ 60.9 የሚከተሉት ድንጋጌዎች ቅድመ ክፍያንና የቅድመ ክፍያ ዋስትናን ይመለከታሉ
(ሀ) የቅድመ ክፍያ ዋስትና አስፈላጊ ነው
(ለ) የቅድመ ክፍያ በሥራ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ የቅድመ ክፍያው
የሚፈጸመው ከሥራዎች የመጀመሪያ ወራት መግለጫ ጋር ሲነጻጸር ከሚኖር እኩል
የገንዘብ መጠን የቅድመ ክፍያው ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ በመንግሥት አካል
ይፈጸማል፡፡

የቅድመ ክፍያው ዋስትና ከቅድመ ክፍያው የገንዘብ ዓይነትና መጠን ጋር ተመሳሳይ ይሆናል፡፡
(ሐ) የቅድመ ክፍያ ተመላሽ ክፍያዎች በወርሐዊ የክፍያ ጥያቄዎች መሠረት በተቀናሽ
መልክ ይፈጸማሉ፡፡
(1) የቅድመ ክፍያው (ከፍተኛው 30%) ከተከታታይ ክፍያው በተቀናሽ መልክ ወይም
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከተቋራጩ ቀሪ የገንዘብ መጠን ላይ የሚፈጸም ይሆናል፡፡ ተመላሽ
ክፍያው የሚጀምረው የመጀመሪያው ተከታታይ ከፍያ ሲፈጸምና የሚጠናቀቀውም
የውሉ 80% ዋጋ ሲከፈል ይሆናል፡፡
ተመላሽ ክፍያው የሚፈጸመው ቅድመ ክፍያው በተፈጸመበት የገንዘብ ዓይነት ነው፡፡
ከእያንዳንዱ ተከታታይ ክፍያ የሚቀነስ የገንዘብ መጠን በሚከተለው ቀመር ይሰላል፤
n አቅ × ተክመ
ተክ=
መዋ× 0.8

ተክ -- ተመላሽ ክፍያ
አቅ-- አጠቃላይ ቅድመ ክፍያ
መዋ--- መነሻ የውሉ ዋጋ
ተክመ--- ተከታታይ ክፍያ የገንዘብ መጠን
ውጤቱ በሁለት ዐሥርዮሽ ይጠጋጋል

የውአሁ 61.1 የተያዙ ክፍያዎች ምጣኔ ካሉ ተቀናሾችን ሳይጨምር አጠቃላይ የተፈጸሙ ሥራዎች ዋጋ 5%
ነው፡፡

ማኅተሞች
- መመ
- መመ
SlTRg#Ñ TKKl¾nT
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የውአሁ ሐረግ ክፍል 8. የውሉ ልዩ ሁኔታዎች
ክፍል
ቁጥር 3 ፡ ውል ንዑስ ክፍል 8፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የውአሁ 62 በመንግሥት አዋጅና መመሪያ የሚለወጡ ቀረጦች፣ ግብሮችና ሌሎች ክፍያዎች በውሉ ዋጋ ላይ
ተጽእኖ የሚያሳድሩ ከሆነ መሐንዲሱ በውሉ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ያደርጋል፡፡
የውአሁ 62 በዚው ውል ውስጥ ምንም የዋጋ ማስተካከያ ግምት ውስጥ አይገባም፡፡
የውአሁ 63.1 የሥራዎችን ዋጋ ለመተመን የሚከተሉት ዘዴዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፤
(ሀ) ለአንዱ ዋጋ (የአድሜዠርመንት) ውሎች
(1) በውሉ የሚፈጸም ክፍያ የሚሰላው ለእንዱ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን ከተፈጸመው
የሥራ ብዛት ጋር በማባዛት ሲሆን ይህም ውሉ በሚያስቀምጠው አቅጣኛ ይከናወናል፡፡
(2) በዋጋ ዝርዝር የሚጠቀሱ የሥራ ብዛቶች የሥራዎች ግምታዊ መጠን ሲሆን ይህም
ተቋራጩ በውሉ የተጠቀሰውን ግዴታውን ለመፈጸም እንደፈጸማቸው ትክክለኛና ነባራዊ
መጠኖች ተደርገው አይወሰዱም፡፡
(3) ተቋራጩ በትክክለኛነት የፈጸማቸውን ሥራዎች ብዛት መሐንዲሱ በመለካት የሚወስን
ሲሆን ክፍያቸው የሚፈጸመውም በውአሁ ሐረግ 64 መሠረት ነው፡፡ በውልሁ ካልተደነገገ
በስተቀር በዋጋ ዝርዝር ውስጥ ምንም ተጨማሪ ነገር አይጨመርም፡፡ ይህ የማይመለከተው
ግን በውአሁ ሐረግ 15 መሠረት የሚኖር ማስተካከያና ተቋራጩን ለተጨማሪ ክፍያ ባለ
ሙሉ መብት የሚያደርጉ ሌሎች ድንጋጌዎች ናቸው፡፡
(4) መሐንዲሱ የሥራዎች ማናቸውም ክፍል እንዲለካ ሲፈልግ ተቋራጩ እንዲገኝ ወይም
እንዲወክለው ብቁ ወኪል እንዲልክ መግለጫ ይሰጣል፡፡ ተቋራጩ ወይም ወኪሉ መሐንዲሱ
እነዚህን ልኬቶች እንዲያከናውን ሁሉንም ዝርዝር መረጃዎችን በማቅረብ ለመሐንዲሱ
ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ ተቋራጩ ሲጠራ መገኘትና ወኪሉን መላክ ካልቻለ በመሐንዲሱ
የሚከናወንና የሚጸድቅ ልኬት በውሉ ቀያጅ ይሆናል፡፡
የውአሁ 64.1 የጊዜያዊ ክፍያ ቅድመ ዝግጅቶች ከሚከተሉት በመቀጠል ይዘጋጃሉ፡ በወር አንድ ጊዜያዊ ክፍያ፡፡
ዝቅተኛው ጊዜያዊ የገንዘብ መጠን ከውሉ ዋጋ 5% ይሆናል፡፡
የውአሁ 64.2 (ሐ) በውአሁ ሐረግ 83 የተጠቀሱት ማሽኖችና ጥሬ ዕቃዎች ይዞታ የሕዝብ አካል ይሆናል፡፡
የጊዜያዊ ክፍያ ብዛት የሚሆነው፡ አንድ ጊዜያዊ ክፍያ በወር ነው፡፡ ዝቅተኛው የጊዜያዊ ክፍያ
የውአሁ 64.7 መጠን የውሉ ዋጋ 5% ይሆናል፡፡
የውአሁ 65.1 የመጨረሻ የሒሳብ መግለጫ ንድፍ የሚቀርበው ተቋራጩ የጊዜያዊ ተቀባይነት የምሥክር
ወረቀት በቀረበበት የቅርብ ጊዜ ነው፡፡
የውአሁ 65.2 መሐንዲሱ የመጨረሻ የሒሳብ መግለጫ አዘጋጅቶ የሚፈርመው በውአሁ ሐረግ 89 የተጠቀሰው
የመጨረሻ የምሥክር ወረቀት በቀረበ በ 30 ቀናት ውስጥ ነው፡፡

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT
h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ረ. የውሉ አፈጻጸም
ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 8፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የውአሁ 70.1 የሥራዎች ጽንፍ የሚብራራው፡ በባሕር ዳር ከተማ የባሕር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል የኤሌክትሮ
ሜካኒካዊ ሥራዎች ግንባታ የሚጠቀስ ይሆናል፡፡
የውአሁ 70.2 ተቋራጩ በሚከተሉት ቦታዎች ሥራዎችን ያከናውናል፤ በባሕር ዳር ከተማ፣ የሥራ ቦታዎች በሥዕል
ቁጥር -- የሚመላከቱ ይሆናል፡፡
የውአሁ 71.1 የሥራ መጀመሪያው ቀን፡ የሥራ ቦታው ርክክብ ከተደረገ ባሉት 21 ቀናት በኋላ ነው፡፡
የውአሁ 72.1 የሁሉም ሥራዎች የታቀደው የማጠናቀቂያ ጊዜ 365 ቀናት ይሆናል፡፡
የውአሁ 74.1 (በ) የሚከተሉት የካሣ አጋጣሚዎች ናቸው፤ የሚከተሉት ይደመሩ፡- 74.1 (በ) በኢትዮጵያ ፍትሐ
ብሔር ሕግ 1960 አንቀጽ 1792 ና 1793 መሠረት
የውአሁ 79.1 የሥራው መዝገብ፡  ይፈለጋል ወይም፤
የውአሁ 79.2 መግለጫዎችን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የሚውሉ የቴክነክ ሕጎች፡ በሥራ ቦታው ያለ መዝገብ
ወይም በመሐንዲሱ ትዕዛዝ የሚዘጋጅ ይሆናል
የውአሁ 80 በሥራ ቦታው የሚገኝ ማናቸውም ጥሬ ዕቃ ለክፍያ ግምት ውስጥ አይገባም
የውአሁ 80.2 በግንባታ ወቅት ጥቅም ላይ የዋሉ ሥራዎች፣ ክፍሎች፣ ቁሳቁሶችና ጥሬ ዕቃዎች ለሚከተለው
ተገዥ ሊሆኑ ይገባል፤
(ሀ) ለሚከተሉት መወሰኛዎች፡ ሥዕሎች፣ ቅኝቶች፣ ናሙናዎች ወዘተ
(ለ) በሥራ አፈጻጸም ሂደት ውስጥ ለመለየት ሲባል ጥቅም ላይ ለሚውሉ ቅድመ ሁኔታዎች

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 9፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

ለ. የውል ማስፈጸሚያ ዋስትና


(የባንክ ዋስትና)

ቀን፡
የውል ቁጥር፡

ለ፡

ስለዚህ (ከዚህ በኋላ "ተቋራጭ" ተብሎ የሚጠራው) በውል ቁጥር ቀን መሠረት (ከዚህ በኋላ "ውል" ተብሎ
የሚጠራውን) ለማቅረብ ተንቀሳቅሷል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በፊት በተጠቀሰው ውል ተቋራጩ በውሉ ለገባው ግዴታ ተገዥ ይሆን ዘንድ እንደ ዋስትና የሚያገለግልና
እዚሁ ለተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ልክ ተቋራጩ መልካም ስም ካለው ዋስትና ሰጭ የውል ማስፈጸሚያ ዋስትና
አውጥቶ እንደሚያቀርብ በእርስዎ ተገልጧል፡፡

ስለዚህ እዚህ እታች የፈረመው (ከዚህ በኋላ "ዋስትና ሰጭ" ተብሎ የሚጠራው ) ሕጋዊ ነዋሪ የሆነው (የዋስትና
ሰጭውን ሙሉ አድራሻ ያስገቡ) ለተቋራጩ የውል ማስፈጸሚያ ዋስትና ለመስጠት ተስማምቷል፡፡

ስለዚህ እዚህ እኛ የምናረጋግጠው ነገር እኛ ዋስትና ሰጭ መሆናችንንና ለተቀመጠው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን
ተቋራጩን ወክለን ለእርስዎ ኃላፊነቱን እንደምንወስድ ሲሆን ተቋራጩ ውል ማፍረሱን በመግለጥ የመጀመሪያ
የጽሑፍ ጥያቄ እንዳቀረቡ ለጥያቄዎ ወይም ለጠየቁት የገንዘብ መጠን ምንም ማረጋገጫ ወይም ምክንያት ማቅረብ
ሳያስፈልግዎ ያለምንም ማማረርና ክርክር እላይ እስከተጠቀሰው ወሰን ድረስ ማንኛውንም የገንዘብ መጠን ለመክፈል
ቃል እንገባለን፡፡

ይህ ዋስትና ሥራ ላይ የሚውልበት ቀን እስከ…

ይህ ዋስትና በአይሲሲ ዕትም ቁጥር 458 ለተጠቀሰው የዋስትና ጥያቄ ተመሳሳይ ሕግጋት ተገዥ ይሆናል፡፡

ስም፡

ፊርማ

ዋስትናውን ለመፈረም ሥልጣን የተሰጠው ወገን


ቀን፡--------------------------- ቀን--------------------,---------- ማኅተሞች
- መመ
- መመ

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ክፍል 3፡ ውል ንዑስ ክፍል 9፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

ሐ. የቅድመ ክፍያ ዋስትና


SlTRg#Ñ TKKl¾nT
(የባንክ ዋስትና)

ቀን፡
የውል ቁጥር፡

ለ፡

ቅድመ ክፍያዎችን በተመለከተ በውሉ በተካተተው የክፍያ ድንጋጌ መሠረት (ከዚህ በኋላ "ተቋራጭ" ተብሎ
የሚጠራው) በውሉ በተጠቀሰው ሐረግ የተጣለበትን አግባብነት ያለውንና በቅን ልቦና ያከናወነውን አፈጻጸም
መተማመኛ ለመስጠት ዋስትና በመንግሥት አካል ሥር ተቀማጭ የሚያደርግ ሲሆን የገንዘብ መጠኑም… ነው፡፡

እኛ እዚህ እታች የፈረምነው (ከዚህ በኋላ "ዋስትና ሰጭ" ተብለን የምንጠራው ) ሕጋዊ ነዋሪ የሆንነው በተቋራጩ
እንደታዘዝን ያለቅድመ ሁኔታና በማይቀለበስ መልኩ እንደ ተራ ዋስትና አቅራቢ ሳይሆን እንደ ዋና ግዴታ ገቢ ዋስትና
ለመስጠት ተቋራጩን የመጀመሪያ ክፍያ ሳይጠይቅ ለመንግሥት አካል በመጀመሪያ ጥያቄው ያለአንዳች የመቃወም
መብት ክፍያ ለመፈጸም በእኛ በኩል የምንስማማ ሲሆን የክፍያ መጠኑም ከዚህ አይበልጥም፡፡

ይህ ዋስትና ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ የሚውለው በውሉ መሠረት ተቋራጩ የቅድመ ክፍያ ከተቀበለበት ቀን አንስቶ
ሲሆን የሚቆየውም (ዓመተ ምኅረቱን ያስገቡ)

ስም፡

ፊርማ

ዋስትናውን ለመፈረም ሥልጣን የተሰጠው ወገን


ቀን፡--------------------------- ቀን--------------------,----------

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የግንባታ ስምምነት ሐረጎች ተቀጽላ

የጨረታ ገንዘብ መጠን ብር

የውል ማስፈጸሚያ ዋስትና የገንዘብ ወሰን ከውሉ ዋጋ 10%

ቅድመ ክፍያ ከውሉ የገንዘብ መጠን 20%

የሥራዎች መጀመሪያ ጊዜ 21 ቀናት

የሥራዎች ማጠናቀቂያ ጊዜ 365 ቀናት

የጉዳት ካሣ ገንዘብ መጠን በቀን ከውሉ ዋጋ 1/1000

የጉዳት ካሣ ወሰን ከውሉ ዋጋ 10%

የጉድለት ባለዕዳነት ጊዜ 365 ቀናት

የመሐንዲሱ ልዩነት የማድረግ ሥልጣን በውሉ ልዩ ሁኔታ መሠረት

የጊዜያዊ ገንዘብ መጠኖች ማስተካከያ መቶኛ 10%

የሚያዝ ገንዘብ መጠን መቶኛ ከውሉ የገንዘብ መጠን 5%

የጊዜያዊ ምሥክር ወረቀት ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን 5%

ላልተከፈሉ የገንዘብ መጠኖች የሚኖር የወለድ ምጣኔ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ምጣኔ

የውጭ ምንዛሬ (ካለ) የለም

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
የዋጋ ዝርዝር

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች
ሥራዎች ኤሌክትሮ - ሜካኒካል
የሥራው ቦታ ባሕር ዳር
ፕሮጀክት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
የሥራው ቋሚ ቦታ
የዋጋ ዝርዝር ዓይነት ውል
ዝርዝር
የዋጋ ዝርዝር ባሕሪ ዋጋው የተተመነ

ማጠቃለያ

1. የሕሙማን መኝታና ቤተ ሙከራ

ማናፈሻ ብር 2,062,992.50

2. ኩሽና ብር 790,919.50

3. የማናፈሻ መትከያ ቦታ አዳራሽ ብር 5,401,103.00

ጠቅላላ…………………………………. ብር 8,255,015.00

ተመላሽ (%) ብር --

15% ተእታ…………………………… ብር 1,238,252.25

ጠቅላላ ድምር………………………… ብር 9,493,267.25

ማኅተሞች
- መመ
- መመ

SlTRg#Ñ TKKl¾nT

h#lT y¥Ynbb# ðR¥ãC xl#bT

ኤስቢዲ- ሥራዎች(ኤንሲቢ)- በኤፍፒፒኤ ተዘጋጀ (ዕትም 1 ኅዳር 2006)


ሠነድ፡ የውሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች

You might also like