You are on page 1of 6

ቁጥር-------------------------

ቀን--------------------

የግል ህክምና አገልግሎት ስምምነት ውል

ውል ሰጭ፡-የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ

አድራሻ አዲስ አበባ ክ/ከ አራዳ ወረዳ 6

 ውል ተቀባይ፡-በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ


 አድራሻ አዲስ አበባ ክ/ከ አራዳ ወረዳ 6

አድራሻ አ.አ

አንቀፅ አንድ

የውሉ አላማ

ይህ ውል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መሰረት በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
የአዋሽ መልካሳኬሚካል ፋብሪካ ከዚህ በሀኋላ ውል ተቀባይ እና በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከዚህ
በኋላ ውል ሰጭ መካከል ወል ተቀባ ለውል ሰጭ በሚልከው የሰራተኞች ስም ዝርዝር በሚቀርቡለትንመሰረት
ውል ሰጭበግሉ የህክምና ክፍል የዱቤ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት እና ከውል ሰጭ ህክምና ተቋምላገኙ
የህክምና አገልግሎት ወል ተቀበይ ከውል ሰጭ በሚቀርብለት የሂሳብ መጠየቂያ ሰነድ መሰረት ክፍያለመፈፀም
እንዲያስችል የተደረገ የጋራ የአስተዳደር የዱቤ ህክምና ውል ስምምነት ነው፡፡

አንቀፅ ሁለት

የውልሰጭ ግዴታወች

1. ውል ተቀባይ ለውል ሰጭበሚልከው የሰራተኞች ስም ዝርዝር በሚመለከተው በማዕከሉ


የበላይ ሃላፊ ፊርማ እና በውል ተቀባ መስሪያቤት ማህተም በተረጋገጠ ሰነድ ለውል ሰጪ በቅድሚያ
ባሳወቀው መሰረት ውል ሰጭበግሉ የህክምና ክፍል አስፈላጊ የህክምና አገልግሎቶችን
የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
2. ውልሰጭ በውሉ ላይ ለተጠቀሱት የውል ተቀባይ መ/ቤት ታካሚወችን የህክምና ሚስጥር
የመጠበቅ ሙያዊ ግዴታ እንዲሁም መረጃውን ለ 3 ኛ ወገን አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ አለበት ፡፡

1
3. ውል ሰጭ የህክምና አገልግሎት ለሚፈልጉበውሉ ውስጥ የተገለፁት የውል ተቀባይ መስሪያቤት
ሠራተኞች /ታካሚወች/ በውሉ መሰረት አስፈላጊውን ህክምና በሚሰጥበት ወቅትየህክምና ስነ-
ምግባርን ብቻ ተከትሎ ባለሙያው ሙያዊይ ግዴታውን ባግባቡ የመወጣት ሃላፊነት እና ግዴታ
አለበት፡፡
4. ውል ሰጭ ለሚሰጠው በግሉ የህክምና አገልግሎት ወር በገባ በአምስት ተከታታ የሥራ ቀናት ውስጥ
የታከሙትን ታካሚዎችና ጠቅላላ ሂሳቡን ለውል ተቀባይ እንዲከፍለው ያሳውቃል፡፡
5. ውል ሰጭ የሂሳብ መጠየቂያውን በየወሩ በሚያቀርቡበት ጊዜ ስለሰጠው የዱቤ ህክምና አገልግሎት
የሠጠውን የህክምና አይነትና ምርመራ በዋጋ ዝርዝር የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
6. ውል ሰጭ በግሉ ህክምና አገልግሎት ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት ከጨረሱ በኋላ አስፈላጊ ሆኖ
ሲገኝ የህክምና የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡
7. የውል ተቀባይ መስሪያ ቤት ታካሚዎች በመጡበት ቅደም ተከተል ህክምና አሰጣጥ
ከመንግስት የሰራ ስአት ወጭ በአግባቡ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
8. ውል ተቀባይ በማንኛውም ጊዜ የሚመጡ ዝርዝር የህክምና ሁኔታወች በአግባቡ
ስለመሰጠታችሁ ለማጣራት ቢፈልግ ውል ሰጭ ፍቃደኛ ወይም እንዲጣራ የመተባበር ግዴታ
አለበት ፡፡
9. ውል ሰጭ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሌሉ የምርመራ አይነቶችንና መድሃኒቶችን የመስጠጥ ግዴታ
የለበትም፡፡ የሌሉ ምርመራዎችን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ታካመዎች ሌላቦታ አሰርተዎ እንዲመጡ
ባለሙያው/ሃኪሙ/ ሊያዝ ይችላል፡፡
10. ውል ሰጭ ለውል ተቀባይ ሠራተኞች የሚሰጠው አገልግሎት በውል ተቀባይ በተመረጠባቸው የህክምና
አይነቶች ብቻ ነው፡፡

አንቀፅ ሦሥት

የውል ተቀባይ ግዴታ

1. ውል ተቀባይ በዱቤ ህክምና ህክምና አገልግሎት ለማግኘት ይችል ዘንድ ቅድሚያ በውል ተቀባይ
አካውንት ብር 50¸000/ሃምሳ ሽብር/ ማስገባት ግዴታአለበት፡፡
2. ውል ተቀባይ በግሉ የህክምና ክፍል በዱቤ ህክምና ተጠቃሚ የሆኑትን በውሉ ውስጥ የተጠቀሱት
ሃላፊወች እና ሰራተኞች ስም ዝርዝር በሚመለከተው የመስሪያ ቤት የበላይ ሃላፊ ፊርማና
በመሰሪያ ቤቱ ማህተም በተረጋገጠ ሰነድ ለውል ሰጭ በቅድሚያ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

2
3. ውልተቀባይ በማንኛውም ምክንያት በውሉ መሰረትህጋዊ የሆኑ የአገልግሎቱ ተጠቃሚወች
ከመስሪያቤቱ ሲቀነሱ/ሲለቁ/ወይም ሲጨመሩ/ሲቀጠሩ/ ዝርዝራቸውን ለውል ሰጭ የማሳወቅ
ግዴታ አለበት፡፡
4. ውልተቀባይ በግሉ ህክምና አገልግሎት የተጠቀሙየውል ሰጭ ሠራተኞችን
/ታካሚወች/በተጠቀሙበት ባሳወቀው መሰረት ውል ተቀባይ የሂሳብ መጠየቅያው ከደረሰው ጊዜ
ጀምሮ በሚታሰብ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በውል ሰጪ የሂሳብ አካውንት ገቢ
የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
5. የውል ተቀባይ የግል ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ሰራተኛ የዱቤ ህክምና አገልግሎት

እንዲያገኝ ወደ ውል ሰጭ ተቋም ሲመጡ እንደማንኛውም ታካሚ ወረፋቸውን ጠብቀው

ይስተናገዳል::

6. የውል ተቀባይ ሠራተኞች ወደ ውል ሰጭ ተቋም በሚሄዱበት ወቅት የመስሪያቤታቸውን መታወቂ

የማሳየት ግዴታ አለባቸው፡፡

አንቀፅ አራት

የውሉ አካል የሆኑ ሰነዶች

1. ውል ተቀባይ ውል ሰጭን ተመራጭ ያደረገበትና ከዚህ ቀደም የተለዋወቷቸው ሰነዶች የዚህ ውል


አካል ይሆናሉ፡፡
2. የሒሳብ መጠየቂያ ሰነድ
3. ውል ተቀባይ የሚልከቸው የዱቤ ታካሚዎች ስም ዝርዝር ማረጋገጫ ደብዳቤዎች የዚህ ውል
አካል የሆኑ ሰነዶች ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡

አንቀፅ አምስት

ክፍያ ሁኔታን በተመለከተ

1. ውል ተቀባይ የህክምና አገልግሎት ክፍያውን ለውል ሰጭ የባንክ አካውንት ሂሳብ ቁጥር ገቢ


ማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

አንቀፅ ስድስት

ውልን ስለማሻሻልና ስለማቋረጥ

3
1. ከሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች አንዱ ውሉን ማቋረጥ ቢፈልግ ቢያንስ ከ 30 ቀናት በፊት አስቀድሞ
የምስሪያ ቤቱ ማኅተም ባለበት ደብዳቤ በማሳወቅ ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡
2. በዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 1 ላይ ያለው የጊዜ ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ ውሉ ከመቋረጡ በፊት ውል
ተቀባይ ያልተጠናቀቁ የግል ህክምና አገልግሎቶች ክፍያዎች አጠናቆ መክፈል ይገባቸዋል፡፡
3. ከተዋዋይወገኖችአንዱበዚህውልላይየተቀመጡትንግዴታዎችመወጣትሳይችሉሲቀርበሌላኛው ተዋዋይ ሥራ ላይ
ችግሮች የሚፈጥር ከሆነ ውሉ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
4. የውል ተቀባይ ከሌላ ድርጅት ጋር ቢቀላቀል አሊያም ህጋዊ ሰውነቱን ቢያጣ በህጋዊ መንገድ የግል ህክምና
ማእከሉ ለሰጠው አገልግሎት የሚፈለግበትን ሂሳብ ሙሉ በሙሉ በመክፈል ውሉ እንዲቋረጥ ማድረግ
ይኖርበታል፡፡
5. ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛው ወይም ሁለቱም ውሉ እንዲሻሻል ጥያቄ ቢያቀርቡና የጋራ ስምምነት ላይ ሲደርሱ
ውሉ በፅሁፍ ሊሻሻል ይችላል፡፡
6. ውል ተቀባይ ለውል ሰጭ ለማስያዥያ ያስቀመጠውን ብር 50¸000 (ሃምሳ ሽ ብር) ውለ ሰጭ የመመለስ ግዴታ
አለበት፡፡ ሆኖም ግን ውሉ በሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች የሚቋረጥ በስምምነት ሂሳቡን ማቻቻል ይችላሉ፡፡

አንቀፅ ሰባት

አለመግባባት የሚፈታበት ሁኔታ

1. የግል ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ችግሮች ቢፈጠሩ ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች በመቀራረብ
ልዩነት በውይይት እንዲፈታ ጥረት ይደርጋል፡፡
2. ከዚህ ውል ጋር ተያይዞ የሚነሳ ያለመግባባት ተዋዋይ ወገኖች በሚያደርጉት ውይይት ያልተፈታ
እንደሆነ ተበዳይ ነኝ የሚለው ተዋዋይ ወገን ጉዳዩን ስልጣን ባለው ፍ/ቤት እንዲታይ አቤቱታ
ማቅረብ ይችላል፡፡
አንቀፅ ሰምንት
የውሉ ጊዜ
ይህ ውል በፍ/ብ/ሔ/ር ህግ ቁ 1731 2005 .3131 እና በተካታዮቹ ህግ መሰረት በተዋዋይ ወገኖች
መካከል ከ መስከረም------ /2015 ጀምሮ እስከ ------- /2016 ዓ.ምለአንድ አመት የፀና ይሆናል፡፡
ይህ ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ፊርማ እና ማህተም ዛሬ መስከረም -------------ቀን 2015 ዓ/ም
ተፈረመ፡፡

ስል ዉል ሰጪ ተቋም ህጋዊ ተወካይ፤ ስለ ዉል ተቀባይ ድርጅት ህጋዊ ተወካይ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ

ስም ስም -

4
ሀላፊነት ሀላፊነት

ፊርማ ፊርማ

ቀን ቀን

ይህንን የጋራ ዉል ስምምነት ሲፈራረሙ በሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች የተቆጠሩ የሰዉ ምስክሮች

ሙሉ ስም ክ/ክወረዳየቤት ቁጥርፊርማ

1--------------------- ----------- --------- --------------- ----------

2------------------- ------------- ---------- --------------- ----------

3------------------- ------------- ----------- --------------- ----------

5
6

You might also like