You are on page 1of 6

የተሟላ ሰነድ የሌላቸውና ሰነድ አልባ ይዞታዎችን በማጣራት የቦታ መጠናቸውን

በመወሰን ህጋዊ የይዞታ


ማረጋገጫ ሰነድ/ካርታ ለመስጠት በወጣው የአፈጻጸም መመሪያ
ቁጥር 2/2005 ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች

መግቢያ
የተሟላ ሰነድ የሌላቸውና ሰነድ አልባ ይዞታዎችን ስርአት ለማስያዝና ዜጎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲያገኙ ለማድረግ
የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ መመሪያ ቁጥር 2/2005 በማጽደቅ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን የክልሉ ከተሞችም
መመሪያውን መሰረት በማድረግ የይዞታዎችን መረጃ በመሰብሰብ አጣርቶ ሰነድ የመስጠት ሰራ በስፋት እያከናወኑ መሆኑ
ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በመመሪያው ላይ በግልጽ ያልተቀመጡ እና በአፈጻጸም ሂደት እያጋጠሙ ያሉ በርካታ ችግሮች እንዳሉ
ከከተሞችና ከዞኖች ከሚቀርቡት የማብራሪያና የአፈጻጸም ሪፖርቶች መገንዘብ ይቻላል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ከተሞች
ተግባሩን በተሟላ ሁኔታ ለማከናወን እንዲችሉ በትግበራ ወቅት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን/በዝርዝር በማየት እንደአስላጊነቱ
ተጨማሪ መካተት ያለባቸውን ጉዳዮች በመለየትና በማሻሻል ሁሉም ከተሞች የሰነድ አልባ ይዞታዎች መስተንግዶ በአዋጁ
አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 5 በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠናቀው ሰነድ እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በመሆኑም በመመሪያው አፈጻጸም ዙሪያ ያጋጠሙ ተጨባጭ ችገሮች በመለየት ዘላቂ መፍትሄ
ለመስጠት፤ ቀደም ሲል ያልታዩ ሆነው ነገር ግን ተጨማሪ የመመሪያው አካል መሆን የሚገባቸውን መስፈርቶች
በማካተት የነዋሪዎችን የይዞታ ባለቤትነት መብት ለማረጋገጥ እና የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነትን በማስፈን
የመስተንግዶ ስራውን ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ለአፈጻጸም መመሪያው አካል የሆነ ተጨማሪ
መስፈርት ተዘጋጅቷል፡፡

1. አጭር ርዕስ-

ይህ መመሪያ የተሟላ ሰነድ የሌላቸውና ሰነድ አልባ ይዞታዎች አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 2/2005 ማሻሻያ መመሪያ
ቁጥር 1 ሊባል ይችላል፡፡

1. በአፈጻጸም መመሪያው ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች

በክፍል ሁለት ላይ የተካተቱ


4.2. የሰነድ አልባ ይዞታዎች በተመለከተ የተካተቱ ተጨማሪ ሰነዶችና ማስረጃዎች፡-
4.2.8.ከተሞች የከተማ ዕውቅና ካገኙበት ጊዜ ጀምሮ ተይዘው ቤት የተገነባባቸውና አሁንም አገልግሎት
በመስጠት ላይ ያሉ ይዞታዎች በቀበሌው አስተዳደር የተረጋገጠበት የጽሁፍ ማስረጃ ማቅረብ
የሚችሉ ባለይዞታዎች፣በህጋዊ መንገድ ምሪት ከተመሩ በኋላ ግንባታ እንዳይገነቡ ታግደዉ የቆዩ
እና በአሁን ሰዓት ለመገንባት ፈቃድ ያገኙ ከሆነ፡፡

4.2.9 በከተማው ፕላን ክልል ውስጥ የሚገኝና የፕላን ምደባ የተሰጠው የአርሶ አደር ባለይዞታዎች፣ሆነው
ይዞታውን በመኖርያነት እየተጠቀሙበት ያለና በህጋዊ ባለይዞታው ብቻ ቤት የተገነባ ከሆነ፣

4.2.10. ቦታው በልማትና በተለያዩ አደጋዎች ተነሺ ለሆኑ ግለሰቦች በህጋዊ መንገድ የተሰጠ ሆኖ ለሶስተኛ
ወገን የተላለፈ ስለመሆኑ የባህላዊ የግዥና ሽያጭ ወይም የስጦታ ውል ማስረጃ/ውሉ በፍትህ
የጸደቀ ሆኖ/ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ቤት የተሰራባቸው ይዞታዎች፡፡

4.2.11. በከተማው ማ/ቤት ከመቋቋሙ በፊት ተይዘው ቤት የተገነባባቸው እና የባህላዊ ግዥና ሽያጭ
ውል/የሀገር ሽማግሌ/ ወይም የስጦታ ውል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ቤት የተሰራባቸው
ይዞታዎች፣ወይም ቦታዉ በዋስትና ተይዞ በፍርድ ቤት ክርክር ተደርጎበት ዉሳኔ ያገኘ ከሆነ ማስረጃ
ማቅረብ የሚችሉ ባለይዞታዎች

5. የተሟላ ሰነድ የሌላቸውና ሰነድ አልባ ይዞታዎች የቦታ መጠን ስለመወሰን

 የመኖሪያ ይዞታ ሰነድ አልባ በተመለከተ


ሀ/መንግስት በሰፈራ መልክ ያሰፈራቸው ነዋሪዎች የመኖሪያ ይዞታቸው በያዙት ልክ የሚስተናገድ ይሆናል
 የሰነድ አልባ የድርጅት ቦታዎችን መጠን በተመለከተ

ሀ/ 500 ካሜ የቦታ መጠን እና በታች የሆኑ ይዞታዎች በልኬት በተገኘው የቦታ መጠን መሰረት እንዲጸድቅ
ይደረጋል፡፡

ለ/ ከ 501 እስከ 1000 ካ.ሜ የሆኑ ይዞታዎች ቦታውን በፕላን ምደባ መሰረት ለማልማት አቅሙ ያላቸው ለመሆኑ
በቦታው ላይ ሊገነባ የሚፈለገውን ግንባታ ፕሮጀክት እንዲያቀርቡ ተደርጎ በ 9 ወራት ውስጥ መገንባት
የሚችሉ መሆኑ ተረጋግጦ እንዲጸድቅላቸው ይደረጋል ፡፡

ሐ/ ከ 1001 እስከ 2000 ካ.ሜ በቦታው ላይ ሊገነባ የሚፈለገውን ግንባታ ፕሮጀክት እንዲያቀርቡ ተደርጎ በ 9 ወራት
ውሰጥ መገንባት የሚችሉ መሆኑ ተረጋግጦ እንዲጸድቅላቸው ይደረጋል

መ/ ከ 2001-3000 ካ.ሜ በቦታው ላይ ሊገነባ የሚፈለገውን ግንባታ ፕሮጀክት እንዲያቀርቡ ተደርጎ በ 9 ወራት ውሰጥ
መገንባት የሚችሉ መሆኑ ተረጋግጦ እንዲጸድቅላቸው ይደረጋል

ሠ/ ከ 3000 በላይ ያሉ የሰንድ አልባ የድርጅት ይዞታዎች ትርፍ ቦታው ተቀናሽ ተደርጎ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ
ይደረጋል፡

ረ/ ከላይ ከፊደል ተራ ለ እስከ መ የተገለጸው ቢኖርም ባለይዞታው ከላይ በተገለጸው መሰረት የመገንባት አቅም ከሌለው
የመገንባት አቅም ላለው ልጀ ማስተላልፍ ይችላል፡፡
ሰ/ ከላይ የተገለጹት ድንጋጌዎች ተግባራዊ የሚሆኑት በህጋዊ መንገድ ለቴዙ ሰነድ አልባ ይዞታዎች ብቻ እንጂ
በህገወጥነት ተስፋፍተው የተያዙ ይዞታዎችን አይመለከትም

8.4.1 ከስታንዳርድ በላይ ሆነው በተቀነሱ ይዞታዎች ላይ የሚገኙ ግንባታዎች እና የቦታ አጠቃቀም በተመለከተ፡

8.4.1.1 ግንባታዎቹ በሚመለከተው አካል የእድሳት ወይም የግንባታ ፈቃድ ተሰጥቶአቸው የተሰሩ ከሆኑ
ተገምተው ለባለ ይዞታዎቹ ካሳ እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡

8.4.1.2 የግንባታ ፈቃድ የሌላቸውና የተቀነሰው ቦታ በአቀማመጡና በቦታ መጠኑ ራሱን ችሎ የማይለማ ከሆነ
የተቀነሰው ቦታ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ እንዲረግና ቦታውን በጊዜያዊ ውል እንዲጠቀምበት
ይደረጋል፡፡

8.4.1.3 የግንባታ ፈቃድ የሌላቸውና የተቀነሰው ቦታ በአቀማመጡና በቦታ መጠን ራሱን ችሎ የሚለማ
ከሆነም ግንባታው ፈርሶ ወደ መሬት ባንክ በማስገባት ቦታው በጨረታ ወይም በምደባ አግባብ
መሰረት ለተጠቃሚ እንዲተላለፍ ይደረጋል፡፡

8.4.1.4 ከላይ የተገለጸው ቢኖርም በሚቀነሰው ቦታ ላይ ምንም ዓይነት ግንባታ ሌለበት ከሆነ በቀጥታ ቦታው
ከይገባኛል ወገን ነጻ በማድረግ ወደ መሬት ባንክ ገቢ ይደረጋል፡፡

9.6.1 ሁለት እና በላይ ሰነድ አልባ እና የተሟላ ሰነድ የሌላቸው ይዞታዎች ያላቸውን ግለሰቦች
መስተንግዶን በተመለከተ፡-

9.6.1.1. በህጋዊ መንገድ በተመራ እና ግንባታ የተከናወነበት ይዞታ በግዥ በሽያጭ ወይም በስጦታ
ወይም በፍ/ቤት/ ትዕዛዝ የተገኘ ከሆኑ ለሁሉም ይዞታዎች ሰነድ እንዱያገኙ እየተደረገ
ተገቢን ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል ፡፡

9.6.1.2 አንድ የተሟላ ሰነድ የሌለው እና አንድ ሰነድ አልባ ይዞታ ያለው ባለይዞታ አገልገሎቱ
ተመሳሳይ ካልሆነ ይጸድቅለታል ተመሳሳይ ከሆነ ግን ቤተሰቦ ተስማምቶ በሚያቀርበው አንድ ለአቅመ
አዳም በደረሰ ልጅ ስም ይፀድቃል

9.6.1.3 በውርስ የተገኙ ሁለትና ከዚያ በላይ ይዞታዎች የውርስ ሃብት ክፍፍል ማስረጃ ሲያቀርቡ በውርስ
ሃብት ክፍፍላቸው መሰረት ይዞታው እንዲጸድቅላቸውና ሰነድ እንዲያገኙ ይደረጋል፣ይህ የሚሆነው
ግን ክፍፍሉ የፕላን ህግጋትን የማይጻረር ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው

9.6.1.4. ሁለትና ከዚያ በላይ ሰነድ አልባ ባለይዞታዎች ሲሆኑ፡-

ሀ/ ተመሳሳይ አገልግሎት ሲሆን ከሁለት ይዞታዎች አንዱ ብቻ ይጸድቅለታል ሌለው 18(ለአቅመ አአዳም
ለደረሰ) አመት ለሞላው ልጅ በስጦታ እንዲያስተላልፈ ይደረጋል፤
ለ/ በመመሪያው መሰረት አስፈላጊው ማጣራት እንደተጠበቀ ሆኖ የተለያየ የቦታ አገልግሎት ያላቸው
ባለይዞታዎች እስከ ሁለት ይዞታ እንዲጸድቅ ተደርጎ ሰነድ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ከዚህ ውጪ ያለ ይዞታ
ግለሰቡ 18 አመት እና በላይ ለሆነ(ለአቅመ አዳም ለደረሰ) ተመሳሳይ ይዞታ ለሌለው ልጁ በስጦታ
እንዲያስተላልፍ ይደረጋል፡፡

ሐ/ ከላይ በ ሀ እና በ ለ የተጠቀሰው ቢኖርም በተመሳሳይም ሆነ በተለያየ አገልግሎት አንድ ግለሰብ ከሁለት


በላይ ይዞታዎች ለልጆቹ ማስተላለፍ አይችልም፡፡

ቁጥር

ቀን

ለ----------------ዞን ኢ/ከ/ል/መምሪያ

ለ----------------ከተማ ሜትሮፖሊታን ከተማ አስተዳደር

-----------------

ጉዳዩ፣የመመሪያ ማሻሻያ ስለመላክ

የተሟላ ሰነድ የሌላቸውና ሰነድ አልባ ይዞታዎችን አጣርቶ ሰነድ እንዲያገኙ በማድረግ ሂደት ከመመሪያ 2/2005 ጋር
ተያይዞ ከከተሞችና ዞኖች ለቀረቡ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው የህግ ጉዳዮችን ቢሮው መፍትሄ ይሆናሉ ብሎ
ያመነባቸውን የማሻሻያ ግብአቶችን በመጠቀም ከዚህ ደብዳቤ ጋር ----ገጽ አባሪ አድርጎ የላከ መሆኑን እየገለጽን
የተሟላ ሰነድ የሌላቸውና ሰነድ አልባ ይዞታዎችን አጣርቶ ሰነድ የመስጠት ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እናሳስባለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

ግልባጭ

You might also like