You are on page 1of 61

መመሪያ ቁጥር 7 / 2010 ዓ.

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የገጠር መሬት


ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ለንብረት ካሣ የሚከፈልበትን እና የልማት ተነሽዎችን
በዘላቂነት ለማቋቋም ተሻሽሎ የወጣ የአፈጻጸም መመሪያ

የተሻሻለው የክልሉ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር


252/2009 እና ደንብ ቁጥር 159/2010 እንዲሁም ከፌደራል አዋጅ ቁጥር 455/1997
እና ደንብ ቁጥር 135/1999 ዓ.ም ጋር ተጣጥሞ ተግባራዊ እንዲሆን በማስፈለጉ፤

የክልሉ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 252/2009


አንቀጽ 26 ከንዑስ አንቀጽ (1-9) እና ይህንኑ ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር
159/2010 አንቀጽ 15 ከንዑስ አንቀጽ` (1) እሰከ (5) በተዘረዘሩት ድንጋጌዎች
መሰረት የገጠር መሬትን ለሕዝብ ጥቅም ለማዋል ሲባል ለማንኛውም የገጠር መሬት
ባለይዞታ በቅድሚያ ተገቢውን ካሣ እንዲያገኝ በማድረግ በተለያዩ የኑሮ አማራጭ
የስራ ዘርፎች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያስችል ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ
ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

መንግስት ለሕዝብ ጥቅም ለሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች መሬትን በመጠቀሙ


እና የክልሉ ከተሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ የነዋሪዎቹም ቁጥር እየጨመረ
በመሄዱ በከተሞች ፕላን መሠረት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለመሠረተ ልማት፣
ለኢንቨስትመንትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል የከተማ መሬትን መልሶ ማልማት
አስፈላጊ በመሆኑ፣ እንዲሁም በገጠር ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች መሬት አዘጋጅቶ
ማቅረብ በማስፈለጉ፣

1
የመሬት ይዞታ እንዲለቅ ለተደረገ ባለይዞታ የሚከፈለውን ካሣ ለመተመን እንዲቻል
ግምት ውስጥ መግባት የሚገባቸውን መሠረታዊ መርሆዎችን ለይቶ ማሻሻል
በማስፈለጉ፤

ለልማት የሚፈለገውን መሬት የማስለቀቅ፣ ካሣውን የመተመን፣ የመክፈል እና የልማት


ተነሺዎችን በዘላቂነት መልሶ የማቋቋም ሥልጣንና ኃላፊነት ያለባቸውን አካላት
በግልጽ ለይቶ ለመወሰን በማስፈለጉ፤

የአማራ ብሄራዊ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ተሻሽሎ በወጣው


የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 60
ንዑስ አንቀጽ (2) እና በደንብ ቁጥር 159/2010 በተሠጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን
መመሪያ አውጥቷል፡፡

2
ክፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌ

1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ ‘’የገጠር መሬት ይዞታ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚለቀቅበትን፣


የንብረት ካሳ የሚከፈልበትንና የልማት ተነሽዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም
እንዲቻል የወጣ መመሪያ ቁጥር 7 / 2010 ዓ/ም’’ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል::

2. ትርጓሜ

የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-


1. “ዓመታዊ ገቢ” ማለት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ በአንድ የምርት
ዘመን በይዞታ መሬቱ ላይ ከተከናወነ ከማናቸውም ሰብል ልማት፣ ቋሚ
ተክልና የመኖ ልማት በአማካይ ምርታማነት ተሰልቶ በወቅቱ የገቢያ ዋጋ
ታስቦ የሚገኝ ገቢ ነው::
2. “የወቅቱ የገበያ ዋጋ” ማለት እንደ አግባቡ ኃላፊነት በተሰጠው መንግስታዊ
ተቋም፣ በንብረት ገማች ባለሙያዎች ወይም በህጋዊ አማካሪ ድርጅት የካሳ
ግመታ በሚከናወንበት ዕለት ወይም ጊዜ የተጠና እና ጥናቱ የተደረገበትን
የገቢያ መረጃ መነሻ አድርጎ የሚወሠን የንብረት ወይም የመሬት ቋሚ
ማሻሻያ ዋጋ ነው::
3. “የገማች ባለሙያ ቡድን” ማለት በመሬት ይዞታ ላይ ቋሚ ንብረትና የለማን
ሃብት ለመቁጠር የካሳ መጠን ለመተመን የስራ ልምዱና እውቀቱ እንዳለው
ታምኖ ጉዳዩ በሚመለከተው የወረዳም ወይም የከተማ አስተዳደር የተደራጀ
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም ስር የሚሰሩ የባለሙያዎች ቡድን
ነው::
4. ‘’የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ወጪ’’ ማለት በድንግል መሬት ወይም ለረዥም ጊዜ
ከምርት ተግባር ውጭ ሆኖ በቆዬ ይዞታ ላይ ይህንኑ ለእርሻ ሥራ ለማዘጋጀት
ሲባል በምንጣሮ፣ ድንጋይ በመልቀም፣ ውሃ መከተር ሥራ፣ የግቢ ንጣፍና

3
ማስዋብ የመሳሰሉትን ሥራዎች እና መሬቱን በማስተካከል ለተከናወኑ
ተግባራት የዋለ ወጪ ነው::
5. "የህዝብ ጥቅም" ማለት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማጎልበት አግባብ ያለው የፌዴራል ወይም የክልል
አካል በመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ወይም በልማት ዕቅድ ወይም በመሠረተ
ልማት መሪ ፕላን መሠረት ለሕዝብ የተሻለ የጋራ ጥቅምና ዕድገት ያመጣል
ተብሎ የተወሰነው ነው፡፡
6. "የንብረት ካሣ" ማለት የመሬት ይዞታውን እንዲለቅ ለሚወሰንበት ባለይዞታ
በመሬቱ ላይ ለሰፈረው ንብረት በዓይነት ወይም በገንዘብ ወይም በሁለቱም
የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡
7. "የመፈናቀያ ካሣ" ማለት ባለይዞታው የመሬት ይዞታውን ሲለቅ በመሬቱ ላይ
የመጠቀም መብቱ በመቋረጡ ምክንያት የሚደርስን ጉዳት ለማካካስ የሚከፈል
ክፍያ ነው፡፡
8. "መልሶ ማቋቋም" ማለት ለልማት ተብሎ በተወሰደው መሬት ምክንያት
የሚያገኙት ጥቅም ለሚቋረጥባቸው የልማት ተነሺዎች ዘላቂ የገቢ ምንጭ
እንዲኖራቸው የሚሰጥ /የሚደረግ / ድጋፍ ነው፡፡
9. "ቀመር" ማለት ለህዝብ ጥቅም በሚለቀቅ መሬት ላይ ለሠፈረ ንብረትና ለለማ
ቋሚ ንብረትና ሃብት ወጥ የሆነ የካሣ ስሌት የሚሰራበት ዘዴ ነው፡፡
10. "የማቋቋሚያ ፓኬጅ" ማለት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከመሬት ይዞታቸው
የሚነሱ ባለይዞታዎች ከንብረት ካሣ እና መፈናቀያ ካሣ በተጨማሪ
በአካባቢያቸው ከሚካሄደው ልማት ተጠቃሚ የሚሆኑበት እና ዘላቂ የሆነ የገቢ
ምንጭ ሊኖራቸው የሚያስችል አስፈላጊ የሆነ የመስሪያ ቦታ አቅርቦት፣
የገንዘብ፣ የሥልጠና እና የማማከር አገልግሎት ተሰጥቷቸው ወደ ስራ
የሚገቡበት እና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ በፓኬጅ ተቀርጾ ተግባራዊ
የሚደረግበት ነው፡፡
11. "የጉዳት ደረጃ" ማለት የይዞታ መሬት፣ የለማ ቋሚ ንብረት ወይም ኑሮው
የተመሠረተበት የገቢ ምንጭ በተለያየ ደረጃ ለልማት ሲባል ይዞታውን
በመለቀቁ የሚደርስ ጉዳት ነው፡፡
4
12. “ማጨሻ ቦታ” ማለት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ በይዞታው ላይ
የመኖሪያ ቤት ሰርቶ በእርግጥም እየኖረበት ያለ ቦታ ነው፡፡
13. “ቢሮ” ማለት የአ.ብ.ክ.መ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ነው::
3. የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሣ


የሚከፈልበትንና ተነሺዎች መልሰው በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ሁኔታ
በሚመለከት በክልሉ ውስጥ ባሉ የከተማም ሆነ የገጠር አስተዳደር በሚገኝ የገጠር
መሬት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

4. መርሆዎች

1. የመሬት ይዞታ ለሕዝብ ጥቅም እንዲለቀቅ የሚደረገው በመሬት


አጠቃቀም ዕቅድ ወይም በከተሞች መዋቅራዊ ዕቅድ ወይም በመሠረተ
ልማት መሪ ፕላን መሠረት መሆን አለበት፡፡
2. ለሕዝብ ጥቅም መሬት ሲለቀቅ የሚከፈል ካሣና የሚሰጥ የማቋቋሚያ
ድጋፍ የተነሺዎችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሻልና የሚያስቀጥል መሆን
አለበት፡፡
3. በክልሉ መንግሥት ለሚከናወን ልማት የይዞታ መሬትና የቋሚ ንብረት
ሲነሳ የሚከፈል ካሣ ተመን ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
4. ለሕዝብ ጥቅም መሬት እንዲለቀቅ ሲደረግ አሰራሩ ግልጽ፣ ፍትሃዊ እና
ተጠያቂነትን የተላበሰ መሆን አለበት፡፡

5
ክፍል ሁለት

ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት የሚለቀቅባቸው ሁኔታዎች

5. መሬት የማስለቀቅ ሥልጣን

1. የከተማ ወይም የወረዳ አስተዳደር፣ በፌዴራል መንግሥት ወይም


በክልል መስተዳድር ምክር ቤት ለህዝብ ጥቅም ሊውል ይገባል ተብሎ
የተወሰነውን መሬት የማስለቀቅ ሥልጣን አለው፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው ቢኖርም፣ ለሕዝብ ጥቅም


ሲባል መሬት የሚለቀቀው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሻለ ልማት
ያመጣል ብሎ የፌዴራል መንግሥት፤ የክልል መንግስት፣ የከተማና
የወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት በመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ወይም
በልማት ዕቅድ ወይም በመሠረተ ልማት መሪ ፕላን መሠረት
ታምኖበት ሲወሰን መሬት እንዲለቀቅ ይደረጋል፡፡

6. የመሬት ይዞታ ባለመብትነትን ስለማጣራት

1. የልማት ተነሺዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የመሬት ባለይዞታነትን


የሚያረጋግጥ የማረጋገጫ ደብተር፣ ማስረጃ ወይም ሠነድ በሕግ ሥልጣን
የተሰጠው አካል በሚያወጣው መርሃ-ግብር መሠረት ማቅረብ
አለባቸው፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ማስረጃ የቀረበለት አካል
የልማት ተነሺዎችን ባለመብትነት ያጣራል፣ ካሣና ሌሎች ተያያዥ
መብቶችን ለሚያስፈጽም አካል ያስተላልፋል፡፡

7. መሬት እንዲለቀቅለት የሚጠይቅ አካል ኃላፊነት

1. መሬት እንዲለቀቅለት የሚጠይቅ አካል ለሥራው የሚፈለገውን


የመሬት መጠንና የሚገኝበትን ትክክለኛ ስፍራ የሚያሳይ ውሳኔ
የተሰጠበት ማስረጃ ቢያንስ ሥራው ከመጀመሩ ከአንድ ዓመት በፊት

6
በከተማው ወይም በወረዳ አስተዳደር ለሚገኜው የገጠር መሬት
አስተዳዳርና አጠቃቀም ተቋም ማቅረብ አለበት፡፡
2. የመሬት ይዞታቸውን እንዲለቁ ለሚደረጉ ባለይዞታዎች፣ በዚህ
መመሪያ መሠረት የሚከፈለው የንብረት እና የመፈናቀያ ካሣ በሌላ
አካል ካልተሸፈነ በስተቀር መሬት እንዲለቀቅለት የጠየቀው አካል
የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2 እና 3) ከተገለጸው በተጨማሪ መሬት
እንዲለቀቀለት የጠየቀው አካል በቀጥታም ይሁን በተጓዳኝ የልማት
ተነሽዎችን በዘላቂነት የማቋቋምና ድጋፍ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

8. ለህዝብ ጥቅም ወይም አገልግሎት ሲባል የገጠር መሬት ይዞታ


የሚለቀቅባቸው ሁኔታዎች
1. አግባብ ባለው የፌደራል ወይም የክልል መንግስት ውሳኔና በአካባቢው
ህብረተሰብ በተደገፈ የመሬት አጠቃቀም እቅድ መሠረት ለከፍተኛ
የህዝብ ጥቅም ወይም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ
እንደሚያበረክት የታመነበትንና ቅድሚያ የተሰጠውን የልማት
ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
2. በሚመለከተዉ ቀበሌ ህዝብ አነሳሽነት ለህዝብ አገልግሎት የሚካሄድ
ግንባታ ሲኖር፤
3. አግባብ ባለውና በታወቀ ፕላን መሠረት ለከተማ ማስፋፊያ፣ ለቀበሌ
ማዕከላት፣ ለኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የመኪና መንገዶችንና ድልድዮችን፣
የባቡር መስመሮችን፣ አውሮፕላን ማረፊያና ማኮብኮቢያ ስፍራዎችን፣
ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያያዙ የውሃ ማፋሰሻዎችን፣ ካምፖችን፣
ለመንገድ ግንባታ የሚሆኑ የአፈር፣ የገረጋንቲና ድንጋይ ማውጫ
ቦታዎችና ተለዋጭ የመሰረተ ልማት አውታሮችን መዘርጋት ወይም
መገንባት ሲያስፈልግ፤

7
4. ሕዝባዊና መንግስታዊ ተቋማትን፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን፣
የህዝብ አብያተ- መፃሕፍትን፣ የጥናትና ምርምር ማዕከላትን፤ የህብረት
ስራ ማህበራት አገልግሎቶችን ለማስፋፋት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
5. የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮችንና የማጠራቀሚያ ጋኖችን፣ የፍሳሽ
ቆሻሻ ማስተላለፊያና ማሰወገጃ ቦዮችን፣ የኤሌክትሪክ መስመሮችንና
የማከፋፈያ ጣቢያዎችን፣ የመገናኛና ቴሌኮሙኒኬሽን አውታሮችን፣
ክልላዊና ብሄራዊ ፓርኮችን፣ ልዩ ልዩ ክበባትን፣ የህዝብ መናፈሻና
መዝናኛ ስፍራዎችን ለማዘጋጀት ወይም ለመገንባት ሲያስፈልግ፤
6. በገጠር የሚከናወኑ የግብርና ልማት ስራዎችን ማለትም የመስኖ
ቦዬችን፣ የማንጣፈፊያ ቦዮች እና መሰል የአገልግሎት መስጫ
መስመሮችን ለመገንባትና ለማሳለፍ ሲባል መሬቱን ነፃ ማድረግ
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
7. የመከላከያና የፖሊሰ አገልግሎት ማሰልጠኛ ተቋማትን ለመመሥረትና
አገልግሎታቸውን ለማስፋፋት መሬት ማስፈለጉ ሲታመንበት፤
8. በአገር አቀፍና በክልል ደረጃ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን
ለማስፋፋት፤ የሠርቶ ማሣያ ጣቢያዎችን ማቋቋም ሲያስፈልግ፤
9. በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ አደጋዎች እና በድንበር አከላለል ወይም
ሽግሽግ ምክንያቶች የሚፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም መሬት
ማስፈለጉ ሲታወቅ፤
10. ለአካባቢ ደህንነት እንክብካቤ ሲባል፣ ከፕሮጀክቱ ክልል ውጭ ወደ
ምርት ተግባር እንዳይገባ የተከለለን ቦታ መጠበቅ ሲያስፈልግ፤
11. በክልሉ ውስጥ የኗሪውን ህብረተሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት
የሚያፋጥኑ የልማት ተቋማትን ለማስፋፋት በቂ መሬት ሲያስፈልግ፤
12. ከባለይዞታው ቸልተኝነት ወይም ግዴለሽነት የተነሳ በተፈጥሮ ሃብት
ላይ አስከፊ ጉዳት በመድረሱ ይህንኑ ለመከላከል ይቻል ዘንድ
አካባቢውን ከልሎ መጠበቅ ሲያስፈልግ፤
8
13. አግባብ ባለው የመንግስት አካል በሚሰጥ ፍቃድ መሠረት የእምነትና
የአምልኮ ሥፍራን ለማሰናዳት መሬት ያስፈለገ እንደሆነ፤
14. የልማቱን ሥራ ለመደገፍ በገጠሩ አካባቢ በጥቅም ላይ ሊውሉ
የሚችሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መሬት
ይለቀቃል፡፡
9. በቀበሌ ማዕከላት የመሬት ማስለቀቅ ስርዓት በሚከተለው መልኩ
ተደንግጓል፡፡
1. በገጠር የይዞታና የመጠቀም መብት የተሰጠው ማንኛውም ባለይዞታ
በቀበሌው ፕላን መሰረት ለልማት መሬት እንዲለቀቅ ሲጠየቅ
የመልቀቅ ግዴት አለበት፤
2. ለቀበሌ ማዕከላት፣ ለመንገድ መሰረተ ልማት ዝርጋታና ሌሎች የጋራ
መጠቀሚያ መሬት ማሰለቀቅን አስመልክቶ የሚከፈል ካሳ የሚሸፈነው
በቦታ ተረካቢዎች ይሆናል፤
3. በቀበሌ ማዕከላት ምክንያት የይዞታ መሬታቸዉ ለሚወሰድባቸዉ
ባለይዞታዎች በዚህ መመሪያ አንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ (32.1) በተራ
ቁጥር 1 ከፊደል ሀ እስከ ረ በተጠቀሰው አግባብ በደረሰባቸው የጉዳት
መጠን መሰረት የመስሪያና የመኖሪያ ቦታ ይመቻችላቸዋል፤
4. መሬቱን የሚያስለቅቀው አካል የሽንሸና ስራ ከመከናወኑ በፊት
ተገቢውን ካሳ ለባለይዞታው ቅድሚያ መከፍል ይኖርበታል፤ ሆኖም
ከዚህ ውጭ የሚከናውን ማንኛውም የመሬት የማስለቀቅ ሂደት በህግ
ተጠያቂ ያደርጋል፡፡
10. በአገልግሎት መስመር ባለቤቶች የተዘረጉ መስመሮች እንዲነሱና መሬቱ
እንዲለቀቅ ስለማድረግ
1. መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ወይም የልማት ድርጅቶች
ንብረት የሆነ የአገልግሎት መስመር ያረፈበት መሬት የሚለቀቅ ሆኖ
ሲገኝ፣ መሬቱን የሚፈልገው አካል መስመሩ የሚገኝበትን ትክክለኛ
9
ሥፍራ በማመልከት ባለቤት ለሆነው አካል መስመሩ እንዲነሳ
ጥያቄውን በጽሁፍ ያቀርባል፤
2. የአገልግሎት መስመር ባለቤቶች በ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ መስመሩን
ለመቀየር መከፈል ያለበትን ካሳ በማስላት የአገልግሎት መስመሩ
እንዲነሳ ለጠየቀው አካል ወይም ለአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች እና
ለከተማ ወይም ወረዳ አስተዳደር ማሳወቅ አለባቸው፤
3. የአገልግሎት መስመር ባለቤቶች ያቀረቡት የካሳ ክፍያ ጥያቄ
የአገልግሎት መስመሩ እንዲነሳ ለጠየቀው አካል ወይም ለአስፈፃሚ
መስሪያ ቤቶች በደረሰ በ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ ካሣው ለመስመር
ባለቤቶቹ መከፈል ይኖርበታል፤
4. የአገልግሎት መስመር ባለቤቶቹም የካሳ ክፍያው በተፈፀመ በ60 ቀናት
ውስጥ መስመሩን በማንሳት መሬቱን ነፃ ያደርጋሉ፤
5. ከዚህ በላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ የአገልግሎት መስመሩ
ካልተነሣ፣ መሬቱን ነጻ ባለመደረጉ በፕሮጀክት ባለቤቶች ወይም
በአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ላይ ለሚደርስ ጉዳት መስመሩን ማንሣት
የነበረባቸው ወገኖች የዕዳ ተጠያቂዎች ናቸው።
11. በሕዝብ ጥቅም ወይም አገልግሎት ሥም ስለማይለቀቁ ይዞታዎች

ከዚህ በታች የተመለከቱትን የመሬት ይዞታዎች በህዝብ ጥቅም ወይም


አገልግሎት ስም ለማስለቀቅ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በዚህ መመሪያ መሠረት
ተቀባይነት የላቸውም፡፡
1. በወረዳ ወይም በከተማ አስተዳደር በፌደራል ወይም በክልሉ መንግስት
በተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ሰው ሰራሽ ቅርስነት የተመዘገቡ
የመሬት ይዞታዎች ወይም ቅርሶቹ ያረፉበትና እነዚህኑ ለመጠበቅ
የተከለለ መሬት፤

10
2. በቱሪዝምና በተፈጥሮ መስህብነት የሚታወቁ ሥፍራዎችና እነዚህኑ
ለመጠበቅ የተከለለ መሬት፤
3. ለአካባቢ ጥበቃና ለብዝሃ ሕይወት እንክብካቤ ማለትም አእዋፋትን፣
የዱር እንሰሳትንና የተፈጥሮ ተክሎችን ዝርያ ለመጠበቅ ሲባል
በጥብቅነት የሚታወቁ መሬቶች፤
4. ብሔራዊ ወይም ህዝባዊ ፓርኮችና የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች፤
5. በፌደራልና በክልል ደረጃ ለተለያዩ የምርምር አገልግሎቶች የተከለሉ
መሬቶች፤
6. በዚሁ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ (1) እስከ (5) የተደነገገው እንደተጠበቀ
ሆኖ እነዚሁን ይዞታዎች ለመጠቀም እና ለአካባቢው ህብረተሰብ
ለሚከናወኑ የመንገድ፣ የስልክ፣ የውኃና የመብራት መሰረተ ልማቶችን
ለመዘርጋት መሬት ሲያስፈለግ ጉዳት በማያደርስ መልኩ መሬት
ሊለቀቅ ይቻላል፡፡
12. ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታቸውን ስለሚለቁ ባለይዞታዎች
ተሳትፎ አስፈላጊነት
1. የንብረት ገማች ባለሙያዎች ቡድን በቀበሌው ተገኝቶ አግባብ ባለው
የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ በመታገዝ የባለይዞታውንና
በመሬቱ ላይ ያለማውን ንብረት መረጃ በሚያሰባስቡበት ወቅት
ባለይዞታው በግንባር ተገኝቶ በስራው የመሣተፍና መረጃውን
የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
2. መረጃዎችን በማሰባሰብ ሂደት በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ኮሚቴውና በንብረት ገማች ቡድን አባላቱ ቸልተኝነት ምክንያት
ትክክለኛ ባለይዞታውን ወይም ባለይዞታዎችን የመለዬት ችግር
እንዳይከሰት ብርቱ ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል፡፡
3. ይዞታውን የመለካቱና የንብረት ቆጠራውም ሆነ ምዝገባው ተግባር
እንደተጠናቀቀ ዝርዝሩ በሰፈረበት ቅጽ ላይ ባለይዞታዎቹና የንብረት
11
ገማች ባለሙያዎች የስምምነት ፊርማቸውን ወይም የጣት አሻራቸውን
በንብረት መተማማኛ ሰነዱ እንዲያሳርፉ ይደረጋል፡፡
4. ማንኛውም ባለይዞታ መሬት የመለካቱና የለማ ንብረት ቆጠራ ሥራው
ከተጠናቀቀና መተማማኛ ከፈረመ በኋላ የመረጃ ይስተካከልልኝ ጥያቄ
ሊያቀርብ አይችልም፡፡ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በዚህ መመሪያ መሠረት
የተጠበቁትን ቅሬታ ወይም ይግባኝ የማቅረብ መብቶቹን የሚከለክል
አይሆንም።
5. የይዞታ መሬቱ ሲለካና በመሬት ላይ ያለማው ንብረት ተቆጥሮ ለዚሁ
የሚያስፈልገው መረጃ ሲያዝ እንዲገኝ ጥሪው በአግባቡ ደርሶት በአካል
ለመገኜት ፈቃደኛ ያልሆነ ባለይዞታ፣ የመሬት መለካቱና ንብረት
ቆጠራው ወይም የምዝገባ ስራው በሌለበት ይካሄድ ዘንድ ሙሉ በሙሉ
እንደተስማማ ይቆጠራል፡፡
6. በግል ይዞታ የጋራ የመጠቀም መብት ያላቸው በመሬቱ ላይ የለማ
ንብረት መረጃ፣ ሁሉም ባለይዞታዎች ወይም ተጠቃሚዎች እና የወል
መሬት መረጃ ደግሞ በወል መሬት አስተዳዳር ኮሚቴዎች ወይም
ይኼው የሚገኝበት የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ አባላት
በተገኙበት ይረጋገጣል፡፡

12
ክፍል ሦስት

ለህዝብ ጥቅም ታስቦ መሬት ሲለቀቅ ንብረት ስለሚነሳበት፣ ስለትክ አሰጣጥ፣


ስለ ካሣ አወሳሰን እና ክፍያ አፈጻጸም
13. ለህዝብ ጥቅም ታስቦ መሬት ሲለቀቅ ንብረት ስለሚነሳበት ስርዓት

1. ለልማት የሚፈለገውን መሬት የማስለቀቅ ቅደም ተከተል በተመለከተ


ቀጥሎ በተዘረዘረው መልኩ ተደንግጓል፡፡
ሀ. የልማት ተነሺዎች ከመነሳታቸው ቢያንስ ከ6 ወር በፊት
ስለልማቱ ዓይነት፣ ጠቀሜታና አጠቃላይ ሂደት በማወያየት
እንዲያውቁት ማድረግ አለበት፤
ለ. ለሕዝብ ጥቅም እንዲለቀቅ በተወሰነው ቦታ ላይ ለሚገኝ
ባለይዞታ የሚገባውን የካሣ መጠን እና ምትክ ቦታ ስፋትና
አካባቢን ወይም ቤት በመግለጽ በጽሁፍ የማስለቀቂያ ትዕዛዝ
መሰጠት አለበት፤
ሐ. የሚለቀቀው ይዞታ የመንግሥት ከሆነ የማስለቀቂያ ትዕዛዙ
የሚደርሰው ለሚያስተዳድረው አካል ይሆናል፤
መ. ለልማት ተነሺዎች ካሣ ከተከፈለ፤ ትክ ቦታ ወይም የመስሪያ
እና የመኖሪያ ቦታ እንደ ጉዳት ደረጃቸው ተለይቶ ከተሰጠ በኋላ
መሆን አለበት፡፡
2. የካሳ ግመታው እንደተጠናቀቀና ክፍያው እንደተወሰነ በቅድሚያ
ተከፍሎ በሚመለከተው የቀበሌ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ኮሚቴዎች አማካኝነት ለራሱ ወይም ለህጋዊ ወኪሉ የማስለቀቂያ ትዕዛዝ
በጽሁፍ እንዲደርሰው ይደረጋል።
3. የልማት ተነሺው የካሣ ግምት በጽሁፍ እንዲያውቅ ከተደረገበት ቀን
ጀምሮ፡-

13
ሀ. በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሣ ካልተከፈለው በመሬቱ ላይ ከቋሚ
ተክልና ግንባታ በስተቀር ሌሎች ሥራዎችን ከመስራት መከልከል
የለበትም፤
ለ. በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሣ ካልተከፈለው በመሬቱ ላይ የመሬት
አጠቃቀም ዕቅዱን መሰረት አድርጎ ማንኛውንም ሥራ ከመስራት
መከልከል የለበትም፡፡
4. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ ትዕዛዙ በደረሰው በ10 የሥራ ቀናት
ውስጥ ካሣ እና ምትክ ቦታ ወይም መስሪያ ቦታ መውሰድ አለበት፤
5. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3)
መሠረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የካሣ ክፍያውን ካልወሰደ በከተማው
ወይም በወረዳው አስተዳደር ስም በሚከፈት ዝግ የባንክ ሂሳብ ገንዘቡ
እንዲቀመጥለት ይደረጋል፤
6. ለባለይዞታ የሚሰጠው የመልቀቂያ የጊዜ ገደብ ካሣና ምትክ ከተቀበለ ወይም
ካሣው በዝግ ሂሳብ ከተቀመጠበት ቀን ጀምሮ ከ90 ቀን ያነሰ መሆን
የለበትም፤
7. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) የተደነገገው ቢኖርም በሚለቀቀው መሬት ላይ
ሰብል፣ ቋሚ ተክል ወይም ሌላ ንብረት ከሌለ ባለይዞታው የመፈናቀያ ካሣ
ከተከፈለው በኋላ በ30 ቀናት ውስጥ ይዞታውን ለወረዳው ወይም ለከተማው
አስተዳደር ማስረከብ አለበት፤
8. በሕገ-ወጥ መንገድ በተያዘ ቦታ ላይ ለሰፈረ /ለተፈራ/ ንብረት ካሣ መክፈል
ሳያስፈልግ ለሰባት የሥራ ቀናት የሚቆይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት
ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ እንዲለቀቅ ይደረጋል፤
9. የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ ወይም ባለንብረት በዚህ አንቀጽ
ንዑስ አንቀጽ (5) እና (6) በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ያለ በቂ ምክንያት
ይዞታውን ካላስረከበ የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር መሬቱን
ለመረከብ የፖሊስ ኃይል መጠቀም ይችላል፤

14
10. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (9) መሰረት በፖሊስ ኃይል እንዲለቅ የተደረገ
ባለይዞታ ግንባታ፣ በህግ አስገዳጅነት እንዲፈርስ የተደረገ እንደሆነ ግንባታውን
ለማፍረሰ የወጣውን ወጪ ባለይዞታው እንዲሸፍን ወይም ባለይዞታው
ከሚከፈለው የካሳ መጠን ላይ እንዲቀነስ ሊወሰን ይችላል፤
11. ማንኛውም ባለይዞታ በመሬቱ ላይ ያለውን የዛፍ ተክል ቆርጦ ለማንሳት
ፈቃደኛ ካልሆነ ለባለይዞታው የተወሰነው ካሳ ተከፍሎት ዛፉን መቁረጥ
አስፈላጊ ከሆነ በጨረታ እንዲሸጥ ተደርጎ ገንዝቡ በከተማ ወይም በወረዳ
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ተቋም በኩል ገቢ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
14. ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚለቀቁ መሬቶችን ስለ ማሳወቅና የለማ ንብረት
ቆጠራ ጥሪን ስለማስተላለፍ
1. በፌደራልም ሆነ በክልልም ደረጃ የሚቀርቡ የመሬት ማስለቀቅ ጥያቄዎችን
አስመልክቶ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ወይም የልማት ፕሮጀክቱ ባለቤት
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚፈለገውን መሬት ለማስለቀቅ እንዲቻል የይዞታውን
ስፋት፣ መሬቱ የሚገኝበትን ትክክለኛ ስፍራ፣ መሬቱ የተመረጠበትን አግባብና
ሌላ አማራጭ አለመኖሩን ከሚያብራራ መግለጫ ጋር መረጃዎችን በካርታ
በማስደገፍ በመሬቱ ላይ የታቀደው ስራ ከመጀመሩ ቢያንስ ከአንድ ዓመት
በፊት ለቢሮው ወይም ለተዋረድ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ተቋም እንዲታወቅ ማድረግ ይኖርበታል፤
2. በተዋረድ የሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም የቀረበውን
ጥያቄ መነሻ በማድረግ ንብረቶቹ እንዲነሱና መሬቱ እንዲለቀቅ
ለባለይዞታዎቹ ያሳውቅ ዘንድ በመሬቱ ላይ የታቀደው የልማት ስራ
ከመጀመሩ ቢያንስ ከ3 ወራት በፊት የወረዳ ወይም የከተማ አስተዳደር
እንዲያውቀው ያደርጋሉ፤
3. ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚለቀቁ መሬቶች አካባቢ ለሚገኘው ህብረተሰብ
ስለታሰበዉ ልማት፣ ስለሚለቀቁት መሬቶች ስፋት፣ መሬቱ ስለተመረጠበት
አግባብና ስለ አጠቃላይ አፈጻጸሙ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው በቅድሚያ
መደረግ ይኖርበታል፤

15
4. የሚፈለገው መሬት ለህዝብ ጥቅም መሆኑን የተወሰነበትንና የማስለቀቂያ
ትእዛዝ የከተማ ወይም የወረዳው አስተዳደር አግባብ ላለው የገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም መላክ አለበት፤
5. የገጠር መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም ተቋም ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት
ይዞታ የሚለቀቅበትንና የንብረት ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ አስመልክቶ
ለልማት የተፈለገውን መሬት ስፋት፤
6. በካርታ በማስደገፍ፣ መሬቱ የሚለቀቅበትንና ንብረቶቹ የሚነሱበትን ጊዜ፣
ሊከፈለው የሚገባውን ካሳ፣ ምትክ መሬት ስለመኖሩ ወይም ስለ አለመኖሩና
ስለ ቅሬታና ይግባኝ አቀራረብ በማብራራት ለባለይዞታው ከ90 ቀናት በፊት
በቅድሚያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ኃላፊነት አለበት፤
7. መሬቱ በወረዳ ወይም በከተማው አስተዳደር ወይም በህብረተሰቡ አነሳሽነትና
ጥያቄ እንዲለቀቅ የሚያስፈልግና ካሳ ከፋዩም ወይም ትክ መሬት የሚሰጠው
ህብረተሰቡ ራሱ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ፣ መሬቱ የሚገኝበት ቀበሌ ህዝብ በጉዳዩ
ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉ የግድ ሲሆን ይኸው ለወረዳ ወይም ለከተማ
አስተዳደር ምክር ቤት ቀርቦ ካልፀደቀ ተፈፃሚ አይሆንም፤
8. ማንኛውም ባለይዞታ ለህዝብ ጥቅም መሬቱን እንዲለቅ ውሳኔ የተሰጠበት
እንደሆነ መሬቱ በሚለካበትና የለማ ንብረቱ በሚቆጠርበት ወቅት ይህንኑ
በቦታው ተገኝቶ እንዲያስለካ፣ እንዲያስቆጥርና መተማመኛ እንዲፈርም
በአካል ሊነገረው ወይም በጽሁፍ ማስታወቂያ ወይም በግል ለባለይዞታውና
ለቤተሰቡ አባላት በሚደርስ ደብዳቤ መልእክቱ እንዲደርሰው ይደረጋል፤
9. በንብረት ቆጠራ ወቅት የምንጠቀመው የመሬት ልኬታ መረጃ ከእጅ
ጅ.ፒ.ኤስ ውጭ ባሉ የተሻሻሉ የቅየሳ መሳሪያዎች ተለክቶ የሚገኝ መረጃን
መሆን ይኖርበታል፡፡
15. ለካሳ ትመና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ስለማሰባሰብ፤
1. በዚህ መመሪያ መሰረት የንብረት ገማች ባለሙያዎች ለንብረት ግመታ
ስራው የሚሰበስቧቸው የመሬት ልኬታና የመሬት ሃብት መረጃዎች ከዚህ
በታች የተመለከቱትን ዝርዝሮች ሊይዙ ይገባል፡፡

16
ሀ. የመሬቱ ባለይዞታ/ዎች ሙሉ ስም /ከነ አያት/ እና የመኖሪያ
አድራሻ፤
ለ.የባለይዞታው የይዞታ/ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ማስረጃዎች ማለትም
የይዞታ መሬቱ መለያ ቁጥር፣ የይዞታው ስፋት፣መሬቱ የሚገኝበት ልዩ
ስፍራ ወይም አዋሳኞቹ እና ከይዞታው የሚቀነሰው መሬት በሄ/ር
የማሳ ካርታ የሚያመለክት መረጃዎች መሟላት ይኖርባቸዋል።
2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ (1) ሥር የተገለጹትን መረጃዎች ለማሟላት
ሲባል የመሬት ይዞታ ምዝገባና ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የመስጠት
ስራ የመረጃ ማሰባሰቡ ስራ ከመጀመሩ በፊት መጠናቀቅ አለበት፡፡
3. የባለይዞታው የመሬት አጠቃቀም አይነት ማለትም ለግጦሽ፣ ለመስኖ፣
ለአመታዊ ሰብል፣ ለቋሚ ተክል፣ ለደን ልማት፣ ለአግሮ ፎረስትሪ ልማት፣
ለመኖሪያ ቤትና የጓሮ መሬት መሆን አለመሆኑ መረጃው ተለይቶና
ተዳረጅቶ መያዝ አለበት፤
4. በመኸር፣ በበልግ ወይም በቀሪ ዕርጥበት የሚለማ መሬት ስፋት፣ ለአለፉት
አምስት ዓመታት መሬቱ በሚወሰድበት አካባቢ የተዘሩ እስከ ሶስት
በሚደረሱ ዋና ዋና ሰፊ ሽፋን ያላቸው ሰብሎች በሰብል ፈረቃነት የሚዘሩ
በአይነት የቅርብ አምስት ዓመታት ምርታማነትና የወቅቱ የገቢያ ዋጋ
በኩንታል ተሰልቶ መታወቅ አለበት፤
5. የሚለማ መሬት በመኸር፣ በበልግና በቀሪ ዕርጥበት፣ በመስኖ የሚያመርት
ወይም የጓሮ መሬት ከመሆኑ የተነሣ የሰብል ፈረቃው የሚለያይ ከሆነ
ይኸው ተለይቶ በስሌቱ ውስጥ ታሣቢ መደረግ ይኖርበታል፤
6. ይዞታው በመስኖ የሚለማ የእርሻ መሬት ሲሆን የዚሁ ስፋት፣ ለአለፉት
አምስት ዓመታት የተዘሩ ዋና ዋና በፈረቃ የሚዘሩ ሰብሎች አይነት፣
የየዓመቱ የምርት ድግግሞሽ /በየሰብል አይነቱ/፣ የቅርብ አምስት ዓመታት
ምርታማነትና የወቅቱ የገቢያ ዋጋ በኩንታል መሰላት ይኖርበታል፤
7. የሰብል ወይም ቋሚ ተክሉ ምርታማነት ከአምስት ዓመት ላነሰ ጊዜ የተገኘ
ከሆነ በእነዚሁ ዓመታት በተገኘው ምርታማነት መሰረት ተደርጎ ይሰራል፤

17
8. የሰብል ወይም ቋሚ ተክል የሚመረትበት ወይም የተተከለበት መሬት ምርት
መስጠት ያልጀመረ ከሆነ ሰብልን በተመለከተ በአካባቢው ባለው ተመሳሳይ
የይዞታ መጠን ከተመሳሳይ ሰብል፤ የቋሚ ተክል ማፈናቃያ ካሳው
የሚሰላው በአባባና ፍሬ በመጥለፍ ደረጃ ላይ ሁኖ ሲገኝ ከሚመለከተው
የግብርና ተቋም ተጣርቶ በሚገኝ መረጃ መሰረት እያንዳንዱ በቋሚ ተክል
አግር ተቆጥሮ ሊያስገኝ በሚችለው የሚችለው ምርት በወቅቱ የገቢያ ዋጋ
ተስልቶ ካሳው የሚሰላ ይሆናል፤
9. አካባቢውን የሚወክል የአለፉት አምስት ዓመታት ምርታማነት መሬቱ
በሚወሰድበት አካባቢ በሚገኘው የቀበሌ ግብርና ልማት ጽ/ቤቶች
የሚሰሰሰብ ሁኖ መረጃው በወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ተረጋገጦ የሚቀረብ
ይሆናል፤ ነግር ግን የምርታማነት መረጃው በማይኖርበትና አጠራጣሪ ሁኖ
ሲገኝ የመሬቱን ለምነት፣ ተዳፋትነት፣ የአፈር አይነት፣ የመሬት ገጽታና፣
የዝናብ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ በተቋሙ በሚገኘው የመሬት አጠቃቀም
ቡድንና በወረዳው ግብርና ጽ/ቤት በጋራ ተረጋግጦ በሚቀርብ መረጃ
የግመታ ስራው ይከናወናል፤
10. የግጦሽ መሬት ያለ እንደሆነ የዚሁ ስፋት፤ በአካባቢው ለአለፉት ሶስት
ዓመታት በድርቆሽ መሬቶች የተገኘ ድርቆሽ መጠን በሸክም ወይም ሌሎች
ለመኖ ልማት ሊውሉ የሚችሉ ቋሚ እፅዋት ለምሳሌ እንደ ሳስፓኒያ፣
ሉኪኒያ፣ የዝሆኔ ሳር ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉ ቅጠላቸው ቢቆረጥ ሊገኝ የሚችል
የመኖ ምርት በሸክም ብዛትና የወቅቱ የአንድ ሸክም የድርቆሽ ወይም
የሌሎች የመኖ ተክሎች የገበያ ዋጋ በስሌቱ ውስጥ ገብቶ ይታሰባል፤
11. በይዞታ መሬት ላይ ወጥ በሆነ መልኩ የተተከለና የለማ የዛፍ አይነት
በሚኖርበት ጊዜ የዛፉ ቁጥር የሚወሰነው አግባብ ባለው የግብርና ጽ/ቤት
በሚሰጥና በሳይንሳዊ መንገድ በአንድ ሄ/ር መሬት ላይ ተተክሎ ሊለማ
የሚችለውን የዛፍ ብዛት ከዕድገት ደረጃ፣ ቁመትና ውፍረት ጋር ባገናዘበ
መልኩ ይሆናል፤

18
12. በመሬቱ ላይ ያለ ተፈጥሯዊ የዛፍ አይነት፣ ብዛትና የእድገት ደረጃ የታወቀ
እንደሆነ ይህም በስሌቱ ውስጥ የሚገባ ይሆናል፤
13. በይዞታ መሬቱ ላይ የለማው ቋሚ ተክልና የአግሮ ፎረስትሪ ልማት ሲሆን
ፍሬ መስጠት ያልጀመረ ቋሚ ተክል ከሆነ አንድን ቋሚ ተክል ለማሳደግ
የወጣው ግብዓት፣ ጉልበትና ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎች አግባብ ባለው
የግብርና ጽ/ቤት በሚሰጥና በሳይንሳዊ መንገድ በአንድ ሄ/ር መሬት ላይ
ተተክሎ ሊለማ የሚችለውን ተወስዶ የሚገመት ይሆናል፤ ነገር ግን
ካሳይንሳዊ አሰራር ውጭ የተሻለ ካሳ እንዳገኝ በሚል ለተተከለ ቋሚ
ተክልም ሆነ የባህር ዛፍ ዝርያ በአንድ እግር በተቆጠረ ቆጠራ ካሳ
አይገመትም፤ ቋሚ ማፈናቀያ ካሳም አይሰራለትም፤
14. መሬቱ በቋሚነት የሚለቀቅ ሆኖ ፍሬ መስጠት የጀመረ ቋሚ ተክል ሲሆን
በግንባር በአንድ ቋሚ ተክል የሚገኝ አማካይ ምርታማነትን መሰረት
በማድረግ ያስገኘው ገቢ በታሣቢነት ይወሰዳል።
15. በአገልግሎት ላይ ያሉ ባአጥጋቢ ሁኔታ የሚገኙ የአፈርና ውሃ ጥበቃ
ስራዎች ማለትም እርከኖች፣ ክትሮች፣ የውሃ ማፋሰሻ ቦዮች፣ ለውሃ ልማትና
ማሰባሰቢያ የተሰሩ የማጠራቀሚያ ኩሬዎች፣ ጉድጓዶችና መሰል ስራዎች እ
16. ርዝመት፣ ብዛት፣ ስፋትና ደረጃም በዋጋ ስሌቱ የሚካተት ይሆናል።
17. በጊዘያዊነትም ሆነ በቋሚነት የሚለቀቅው መሬት ላይ ለባለይዞታው ጥቅም
የሚሰጥ በተለያየ ወይም በተመሳሳይ ደረጃ ባህር ዛፍ የተተከለበትን
አስመልክቶ መሬቱ ለልማት ተፍለጎ ሲወስድ፣ በንብረት ቆጠራ ወቅት
በግንባር ባህር ዛፉ ተቆርጦ ሲገኝ፣ ቀሪ ጉቶው በማቆጥቆጥ ደረጃ ከሆነና
ባህር ዛፉ ተመልሶ ጥቅም እንደሚሰጥ ከቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ማረጋጋጫ
በጹሁፍ ሲቀርብ ቀደም ብሎ በተለያየ ደረጃ በአስገኜው የምርት ዓይነት
በወቅቱ ዋጋ ተባዝቶ የማፈናቃያ ካሳ ይሰራለታል፤ ነገር ግን ተመልሶ
ለማያቆጠቁጥ የባህር ዛፍ ጉቶ ካሳ አይከፈለም፡፡
18. የወቅቱ የገበያ ዋጋ በሚሰላበት ወቅት አካባቢውን በትክክል የሚወክል
መረጃ ያልተገኜ እንደሆነ የሚገመተው ምርት፣ ቋሚ የመሬት ማሻሻያ

19
ወይም ቋሚ ንብረት በሚሸጥበት ወይም ልውውጥ በሚካሄድበት አቅራቢያ
ያለውን የገቢያ ዋጋ ቀረቤታ፣ የአካባቢው የህዝብ ብዛትና የኢኮኖሚ
ሁኔታዎችን ወ.ዘ.ተ አገናዝቦና ተጠንቶ መሠራት ይኖርበታል፤
19. እያንዳንዱን ልማታዊ ተግባር ለማከናወን የወጣ የገንዘብና የጉልበት ወጪ
እንዲሁም የፈጀው ጊዜና ማቴርያል፣ አሁን ያለበት ደረጃ በአዲስ መልኩ
ለማደስ የሚያስፈልገው ተጨማሪ ቁሣቁስና ሰብአዊ ግብዓት በወቅቱ
የሚጠይቀው የገበያ ዋጋ በስሌቱ ውስጥ መካተት ይኖርበታል፤
20. መኖሪያ ቤቶች፣ የእህል መጋዘኖች፣ የእንሰሳት መጠለያዎችና ሌሎች
ግንባታዎች ከተሰሩበት ስፋት፣ የጥሬ እቃ አይነትና ብዛት ጋር የወቅቱን
የገቢያ ዋጋ መሰረት በማድረግ መገመት አለባቸዉ፤
21. መረጃዎቹ ተሰብስበው እንደተጠናቀቁ ዝርዝራቸውን የያዘው መግለጫ
በባለይዞታው ወይም የባለይዞታዎቹ ወይም ህጋዊ ወኪላቸውና የገማች
ባለሙያ አባላት ሙሉ ስም፣ ፊርማና በቀበሌው ገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ማህተም መረጋገጥ ይኖርበታል፤
22. የግንባታዎች የጥሬ እቃ ፍጆታና የወቅቱ የገበያ ዋጋ ዝርዝር አግባብነት
ካላቸው የተቋሙ ባለሙያዎች ወይም ከሌሎች አስፈፃሚ ተቋማት
መሠብሰብ ይኖርበታል፤
23. ልዩ ግመታ የሚፈልጉትን ግንባታዎች የግብዓት ፍላጎትና የወቅቱን የገበያ
ዋጋ የሚያሳየውን ዝርዝር ከአገልግሎቱ ዘርፍ ባለቤቶችና ከሚመለከታቸው
ተቋማት ተጠይቆ የሚገኝ ይሆናል፤
24. ለተለያዩ ሰራዎች የሚያሰፈልገው እለታዊ የሰው ጉልበት ዋጋ አመልካች
መረጃ በወቅቱ መሠብሰብ ይኖርበታል።
16. የካሣ ግመታ ስለማካሄድ
1. ለህዝብ ጥቅም ሲባል ህጋዊ የመሬት ይዞታ በሚለቀቅበት ጊዜ የሚከፈለው
የካሳ ክፍያ፦

ሀ. በይዞታው ላይ የተደረገውን ቋሚ ማሻሻያ እንዲሁም ባለይዞታው


ያወጣውን የጉልበትና የገንዘብ ወጪ የሚሸፍን፤
20
ለ. በይዞታ መሬቱ ላይ ያፈራውንና አንስቶ ሊወስደው የማይችለውን
ንብረት ደግሞ ባለበት ሁኔታ ለመተካት የሚያስችል መሆን አለበት፤
2. ንብረቱ ከተነሣ በኋላ እንደገና ተተክሎ መስጠት የሚገባውን አገልግሎት
ወይም ጥቅም እንደነበር ወይም ከቀድሞው ባልተለዬ ሁኔታ መስጠት
የሚችል ሲሆን ካሳው ንብረቱን በነበረበት ሁኔታ መልሶ ለመተካት፣
ለንብረቱ ማንሻ፣ ማዛወሪያና መልሶ ለመትከያ የሚውሉትን የማቴርያል፣
የጉልበት፣ የአስተዳደርና ሌሎች ወጪዎች የሚሸፍን ይሆናል፤
3. ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱን ከአንድ ዓመት በላይ እስከ
ሚመለስበት ጊዜ እንዲለቅ የተደረገ እንደሆነ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ
(1) መሰረት አንስቶ መውሰድ ላልቻለውና በመሬቱ ላይ ላፈራው ቋሚ
ንብረት ወይም ላደረገው ቋሚ የመሬት ማሻሻያ ከሚከፈለው የካሳ ክፍያ
በተጨማሪ እስኪቋቋም ድረስ ሊያጣው ይችል የነበረውን ጥቅምና ጉዳቱን
ለማካካስ የሚያስችል የመፈናቀያ ካሣ የይዞታ መሬቱ እስኪመለስ ድረስ
በሚለቀቅባቸው ጊዜያት ልክ ተባዝቶ ይከፈለዋል፤
4. የመፈናቀያ ካሣው መጠን የቅርብ አምስት ዓመታት አማካይ ምርታማነትና
የወቅቱን የገበያ ዋጋ መሰረት ያደረገ ሆኖ በመኸር፣ በቀሪ ዕርጥበት፣ በበልግ
ወይም በመስኖ የሚለሙ መሬቶችን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ በ10
ተባዝቶ የሚፈፀም ይሆናል፤
5. በመሬት የማስለቀቅ ሂደት አንድ አነስተኛ የማሳ መጠን ሊኖረው ከሚገባው
ስፋት በታች የሆነና በቅርጽም ሆነ በመጠን እራሳቸውን አስችሎ ለማልማት
አመች ያልሆኑ ቁርጥራጭ መሬቶች ከተፈጠሩና ለባለይዞታው ጉልህ
ጠቀሜታ የሌላቸው ስለመሆኑ ከተረጋገጠ፣ በቅድሚያ ለቁርጥራጭ ይዞታዎቹ
ብቻ ለይቶ ካሳን በማስላት እንዲህ ያለው ይዞታ ወደ አጎራባች ማሳ
እንዲካተት ማድረግና የካሳ ክፍያውንም ይዞታውን በተጨማሪነት የተረከበው
ባለይዞታ አመች በሆነ የአከፋፈል ስርዓት እንዲከፍለው ይደረጋል፡፡ ሆኖም
ግን ይህንን ዓይነቱን የመሬት ይዞታ የአጎራባች ማሳዎች ባለይዞታዎች

21
ሊረከቡት ፈቃደኛ ካልሆኑ ካሳው ከተለቀቀው ይዞታ ንብረት ግምት ጋር
ተዳምሮ እንዲከፈልና ይዞታው በጋራ ሃብትነት እንዲያገለግል ይደረጋል፤
6. ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከሚለቀቀው መሬት ጋር ሲወዳደር በስፋቱ፣
በምርታማነቱ እና ከመኖሪያ ቤቱ ባለው ርቀት ተመጣጣኝ የሆነና በቀላሉ
ታርሶ ምርት ሊያሰገኝ የሚችል ትክ መሬት የሚሰጠው መሆኑ በከተማ
ወይም በወረዳው አስተዳደር እና አግባብ ባለው የገጠር/መ/አስ/አጠ/ተቋም
በኩል የተረጋገጠለት ማንኛውም ባለይዞታ፣ መሬቱ ለአንድ ዓመት
የሚያስገኘውን አማካይ ዓመታዊ ገቢ ወይም የቅርብ አምስት ዓመታት
አማካይ ምርታማነት በወቅቱ የገቢያ ዋጋ ተሠልቶ የመፈናቀያ ካሳ
እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ ትክ መሬት ካለ ወይም ከተገኘ በቀዳሚነት
የሚሰጠው መሬታቸውን በቋሚነት ለሚለቁ ባለይዞታዎች ይሆናል፤
7. በግል ይዞታ መሬት ላይ በጽሁፍ በተደረገና የኪራይ ውል ለመመዝገብ
ስልጣን ባለው አካል የተመዘገበ የኪራይ መሬት ሌላ አማራጭ መሬት
ባለመኖሩ የውለታ ዘመኑ ከማብቃቱ በፊት ለህዝብ አገልግሎት እንዲለቀቅ
የተደረገ እንደሆነ፣ ካሣው ለመሬቱ ባለይዞታ ይከፈለዋል፡፡ መሬቱን
ያከራየው ሰው ለተከራዩ በጽሁፍ በተገለጸው የኪራይ ውል መሰረት
በቅድሚያ ለተከፈለ የቀሪ የኪራይ ዘመን ብቻ በካሣ ከተገኘው ገንዘብ
ተሰልቶ ይከፈለዋል፡፡ በጽሁፍ በተደረገው ውል መሰረት ከተደረገው የኪራይ
ውል ዘመን በላይ የሚከፈለውን የመፈናቀያ ካሳ በስሌቱ መሰረት ቋሚ
ባለይዞታው እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ ሆኖም በጽሁፍ ላልተደረገና
ላልተመዘገበ የኪራይ ውል ካሳው የሚከፈለው ለባለይዞታው ብቻ ይሆናል፤
8. በሊዝ የተሰጠ መሬት የውሉ ዘመን ከማብቃቱ በፊት ሊለቀቅ የሚችለው፣
መንግሥት ላፀደቃቸው የልማት ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያነት በወረዳ ወይም
በከተማ አስተዳደር ውሳኔ ሲታመንበት በመሬቱ ላይ ላፈራው ቋሚ ንብረት
ለሊዝ ባለመብቱ ከሚከፈለው ካሳ በተጨማሪ ያልተጠቀመበት የሊዝ ክፍያ
ካለው ተመላሽ ይደረግለታል፤ ነግር ግን የቋሚ የማፈናቀያ ካሳ
አይከፈለውም፤

22
9. ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚለቀቀው መሬት ላይ የሚገኝ የሙታን መካነ
መቃብር የፈረሰ እንደሆነ ለዚሁ የሚከፈለው ካሳ መካነ መቃብሩን
ለማንሳት፣ ተለዋጭ የማረፊያ ቦታ ለማዘጋጀት፣ አጽሙን ለማዛወርና
ለማሳረፍ እንዲሁም ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለሚደረግ ሃይማኖታዊና ባህላዊ
ስርዓት ማስፈፀሚያ የሚያስፈልጉትን ወጪዎች ያጠቃልላል፡፡ ለተጠቀሱት
ወጪዎች በወቅቱ የገቢያ ዋጋ መሰረት የአካባቢውን የእቃ፣ የትራንስፖርት
አገልግሎትና የሰው ጉልበት ግምት ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል፡፡

17. በይዞታ መሬት ላይ በለማ ንብረት ዋጋ ግመታ ውስጥ ስለሚካተቱ ጉዳዮች

በዚህ መመሪያ መሰረት የሚካሄድ የንብረት ግመታ በይዞታው ላይ ለለማው ቋሚ


ንብረትና በመሬቱ ላይ የተደረጉ ቋሚ ማሻሻያዎችን መሰረት ያደረገ በመሆኑ
የሚከተሉትን ዝርዝር ጉዳዮች የሚያካትት ይሆናል፡-
1. ለመኖሪያ ቤት፣ ለሰብል መጋዘን፣ ለእንሰሳት መጠለያ ቤትና ለመሳሰሉት
አገልግሎቶች የተከናወኑ ግንባታዎች፤
2. በባለይዞታው አማካኝነት የለሙ ቋሚ ተክሎች፣ ዛፎችና ወቅታዊ ወይም
ዓመታዊ ሰብሎች፤
3. የመሬት ልማት በተደረገባቸው ድንግል መሬቶች ላይ መሬቱን ለተፈላጊው
አገልግሎት ለማዋል ሲባል የምንጣሮ፣ መሬት የማስተካከል፣ ድንጋይ
የመልቀም ወይም ይህንኑ የመሳሰለ ማናቸውም ተግባር፤
4. ቋሚነት ያለውና ከመሬቱ ጋር የተያያዘ አጥርና የእንሰሳት በረት ወይም
ጉረኖ፤
5. በአገልግሎት ላይ የሚገኝ የመስኖ አውታርና የውሃ ማፋሳሻ ቦዮች ግንባታ፣
6. ለአፈር እና ውሃ እንክብካቤ ሲባል ተሰርተው በአገልግሎት ላይ ያሉ የአፈር
ጥበቃ ሕዳጎች፣ ሌሎች ቋሚ የመሬት ማሻሻያ ስራዎች፤
7. ተቆፍረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ የውሃ ጉድጓዶች፣ የጎለበቱ
ምንጮች፣ ኩሬዎችና ሌሎች ውሃ እንዲያጠራቅሙ የተሰሩ ግንባታዎች፤

23
8. በግጦሽ መሬት ላይ የሚገኝ ሳር፣ የመኖ ዛፎችና ከንብረቶቹ ጋር
ተመሳሳይነት ያላቸው የማይንቀሳቀሱ ቋሚ ንብረቶች ወይም የተደረጉ
ማሻሻያዎች፡፡

18. በገጠር መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የመሬት


ይዞታቸው ለልማት ሲነሳ የንበረትና የቋሚ ማሻሻያ ካሳ ስለሚከፈልበት
ሁኔታ
በተሻሻለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅና ደንብ
መሰረት በክልሉ ውስጥ ሥራቸውን የሚያካሂዱ መንግስታዊ መ/ቤቶች፣
ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ
የተሰጣቸው የይዞታ መሬት ለህዝብ ጥቅምና ለሃገራዊ ልማት አስፈላጊ
ሆኖ ከይዞታቸው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲለቁ ውሳኔ የተሰጠ
እንደሆነ፣ በመሬቱ ላይ ላለሙት ቋሚ ንብረትና ላከናወኑት ቋሚ የመሬት
ማሻሻያ ወጭዎች ወደነበሩበት ሁኔታ መልሶ ለመተካት የሚያስችል ካሣ
ተከፍሏቸው እና/ወይም ትክ መሬት ተሰጥቷቸው እንዲለቁ ይደረጋል፡፡
19. የመሬት ይዞታ መብት በሚታጣበት ጊዜ ስለሚከፈል ካሣ
1. ማንኛውም ባለይዞታ በመሬት ይዞታው የመጠቀም መብቱን በህግ አግባብ
እንዲያጣ ሲወሰን ወይም የባለይዞታነት መብቱ በህግ ሲቋረጥ/ በልማት
ምክኒያት ይዞታው የተነሳበትን ባለይዞታ አይመለከትም/፣ ባለይዞታው
በመሬቱ ላይ ያለማውን ቋሚ ንብረት አንስቶ የመውሰድ ወይም አንስቶ
መውሰድ የማይችለውን ደግሞ በዚህ መመሪያ ስለቋሚ ንብረት ካሳ
አከፋፈል በተደነገገው መሰረት በቅድሚያ ተመጣጣኝ ካሳ እና የመሬቱን
ለምነት ጠብቆ ለማቆየት ያወጣውን የማሻሻያ ወጪ ያገኛል፤ ሆኖም
የመፈናቀያ ካሣ የማግኘት መብት አይኖረውም፤
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ቀደም ባሉት
አሰራሮች የገጠር መሬት ይዞታ አግኝተው ነገር ግን በተሻሻለው የገጠር
መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2010 መሰረት የይዞታ

24
መብታቸውን በህግ ሲያጡ፣ በመሬት ላይ ላፈሩትና አንስተው
ለማይወስዷቸው ቋሚ ንብረቶች ተገቢው የንብረት ካሳ በህጉ መሰረት
መሬቱን በሚረከበው አካል ክፍያ ይፈጽማል፡፡ መሬቱን የሚረከበው አካል
መክፈል የማይችል ከሆነ ወይም ፈቃደኛ ካልሆነ መክፈል ለሚችል አካል
መሬቱ ይተላለፋል/ይሰጣል/፡፡
20. መሬቱን በራሱ ፍላጎት /በፈቃደኝነት/ ለሚለቅ ባለይዞታ ስለሚከፈል ካሳ
1. ማንኛውም ባለይዞታ የመሬት ይዞታ መብቱን በራሱ ፈቃድ መተውን
በፈቃደኝነት የለቀቀው መሬት የሚገኝበትን ልዩ ሥፍራ፣ መጠኑን
ከነአዋሳኞቹ ለቀበሌው መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ ከ6 ወራት
በፊት በማመልከትና ከመቼ ጀምሮ መሬቱን እንደሚለቅ በጽሁፍ አስታውቆ
መልቀቅ ይችላል፤

2. ባለይዞታው የይዞታ መብቱን በራሱ ፈቃድ ስለመተው በጽሁፍ ካመለከተ


በይዞታ መሬቱ ላይ ያለማውን ቋሚ ንብረት አንስቶ የመውሰድ እንዲሁም
አንስቶ መውሰድ የማይችለውን ደግሞ በዚህ መመሪያ ስለቋሚ ንብረት ካሳ
አከፋፈል በተደነገገው መሰረት በቅድሚያ ተመጣጣኝ ካሳ ሊከፈለው
ይገባል፤ ነገር ግን የካሳ ክፍያውን የሚፈጸመው መሬቱን የሚረከበው አካል
ሲሆን ለመሬት ለቃቂው የመፈናቀያ ካሳ አይከፈለውም፡፡

21. የመተላለፊያ መስመር በሚዘረጋበት ጊዜ ስለሚከፈል ካሳ


1. በአንድ ባለይዞታ መሬት ውስጥ የመስኖ ቦይ ወይም መተላለፊያ መንገድ
የሚያልፍ ሆኖ ከተገኘና ይኸው ቦይ ወይም መስመር ባለይዞታው በመሬቱ
ላይ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም የሚያሳጣው መሆኑ ከወዲሁ ከታወቀ፣
ይህንኑ ለማካካስ የመተላለፊያ አገልግሎቱን የሚያገኘው በዚህ መመሪያ
መሠረት ለባለይዞታው ያጣዋል ተብሎ ከሚገመተው አገልግሎት ወይም
ጥቅም ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ካሣ ይከፍለዋል። የካሣ ክፍያው እንደሁኔታው
በቀበሌው አስተዳደር ወይም ጉዳዩ በሚመለከታቸው የባለይዞታዎች
ስምምነት ሊፈፀም ይችላል፤

25
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ(1) መሰረት ሁሉም ባለይዞታዎች የመተላለፊያ
አገልግሎቱ እኩል ተጠቃሚዎች ከሆኑና የጋራ መገልገያ ከመሆኑ የተነሣ
የሁሉንም የይዞታ መሬት የሚነካ ከሆነ በዚህ መመሪያ መሠረት የሚከፈል
ካሳ አይኖርም፡፡ ይልቁንም የተዘረጋው መተላለፊያ መስመር
የሚያስከትለውን ወጭ እንደ አጠቃቀማቸው ይጋራሉ፤
3. የመተላለፊያ መሬት አጠቃቀምን በሚመለከት በቀጥታ በተጠቃሚዎችና
በመሬቱ ባለይዞታዎች መካከል የጋራ ስምምነት ሊደረግ ይችላል፡፡
ስምምነቱም ለቀበሌው መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ቀርቦ
ይመዘገባል፤
4. ከዚህ በላይ የሠፈሩት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የሚኖራቸው ይህ መመሪያ
በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ አዲስ በሚገነቡ ወይም በሚዘረጉ የመተላለፊ
መስመሮች ላይ ይሆናል።
22. መሬትን ኩታ ገጠም በማድረግ ሂደት ስለሚከፈል ካሳ
1. ማሳን ለማቀራረብ ሲባል የመሬት ልውውጥ በሚደረግበት ወቅት አንዱ ማሳ
ከሌላው ማሳ በመብለጡ ምክንያት ወይም በመሬቱ ላይ የለማን ንብረት
ማካካስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከፍተኛውን የመሬት ይዞታ የሚረከበው ሰው
በመሬቱ ላይ የለማ ንብረት ወይም ተጨማሪ መሬት ለነበረው ባለይዞታ በዚህ
መመሪያ መሠረት ተመጣጣኝ ካሣ ይከፍለዋል፡፡

23. ከመስኖ ልማት ጋር ተያይዞ የመሬት ሽግሽግ ሲደረግ ስለሚከፈል ካሳ


1. በመስኖ መሬት ሽግሽግ ወቅት ከባለይዞታው በተቀነሰ መሬት ላይ ለለማ
ማናቸውም ቋሚ ንብረት መሬቱ የደረሰው ማንኛውም አርሶ አደር በዚህ
መመሪያ ስለ ንብረት ካሳ አከፋፈል በተደነገገው መሰረት የሚወሰነውን ካሣ
በቅድሚያ ለቀድሞ ባለይዞታው በመክፈል መሬቱን ይረከባል፤
2. በመሬት ሽግሽግ ወቅት ለሌላ ተጠቃሚ በደረሰ መሬት ላይ የለማው ቋሚ
ንብረት የተፈጥሮ ዛፍ ካልሆነ በስተቀር የቀድሞው ባለይዞታ ይህንኑ ቆርጦ
እንዲያነሳ ከተደረገ በኋላ ለባለድርሻው ይሰጠዋል፤

26
3. ቋሚ ንብረት ያለበት መሬት የደረሰው አርሶ አደር በመሬቱ ላይ ለለማው
ቋሚ ንብረት የሚከፍለውን ካሳ በአንድ ጊዜና በቅድሚያ ለመክፈል አቅም
የሌለው ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ይህንኑ ገልጾ ለወረዳዉ የመሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ጽ/ቤት በጽሑፍ ማመልከት አለበት፡፡ በዚህም መሰረት፡-

ሀ. የወረዳ ጽ/ቤቱ በጽሑፍ የቀረበለትን ማመልከቻ ተቀብሎ ባለይዞታዉ


በእርግጥም በአንድ ጊዜና በቅድሚያ ካሳዉን የመክፈል አቅም
እንደሌለዉ ካረጋገጠ፣ የካሳ ባለመበቱ ጋር በሚደረግ ውይይትና
ስምምነት መሰረት ካሳ መክፈል የሚገባው የመስኖ መሬት ተጠቃሚ
ከአንድ ዓመት ተኩል ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በሶስት ዙር ከፍሎ
እንዲያጠናቅቅ ግዴታ እንዲገባ በወረዳው ጽ/ቤት የማመቻቸት ስራ
ይሰራል፤ በዚህ መሰረት ችግሩን መፍታት ካልተቻለ የካሣ ክፍያውን
መክፈል ለሚችል በመስኖ መሬት የመጠቀም መብት ላለው ለሌላ
ተጠቃሚ መሬቱ ይሰጣል፤
ለ. ይህም ሆኖ ችግሩን መቅረፍ ካልተቻለ በወረዳው የመሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ጽ/ቤት አማካይነት የካሳ ባለመብቱንና ካሳ መክፈል
የሚገባውን አካል በማወያየት የክልሉን የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ህግ በማይጻረር መልኩ በሌላ አካባቢያዊ መፍትሄ ጉዳዩ
እልባት እንዲያገኝ ይደረጋል፤

4. በመስኖ ልማት ወቅት በተካሄደ የመሬት ሽግሽግ ምክንያት ቁርጥራጭና


የተበጣጠሱ መሬቶች አንድ አነስተኛ የማሳ መጠን ሊኖረው ከሚገባው ስፋት
በታች ሲሆኑ ወይም በቅርጽና በመጠን እራሳቸውን አስችሎ ለማልማት
አመች ካለመሆኑ የተነሣ ወደ አጎራባች ማሳ እንዲካተት በተደረገ መሬት
ላይ ለሠፈረ ንብረት በዚህ መመሪያ መሰረት መሬቱን የሚረከበው ባለይዞታ
በቅድሚያ ካሳ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ይኸው መሬት የሌላ ባለይዞታ ድርሻ
አለመሆኑ ከተረጋገጠና በትርፍነት የተያዘ ከሆነ፣ ለመሬቱ የሚከፈለው ካሳ
ለወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ወይም ስልጣን ላለው አካል
ገቢ ተደርጎ ለልማት እንዲውል ይደረጋል፡፡
27
24. በጊዚያዊነት የተለቀቁ መሬቶች አገግመው ለባለይዞታው ተመላሽ
የሚደረግበት ሁኔታ
1. በዚህ መመሪያ መሰረት ለተለዋጭ መንገድ፣ ለድንጋይ፣ ለግሪጋንቲ ማምረቻ፣
ለአሽዋና አፈር ማውጫም ሆነ ማጓጓዣ ወይም ለሌላ አገልግሎት ለተወሰነ
ወራት ወይም ዓመት በጊዜያዊነት የተለቀቀ መሬት ወደ ባለይዞታው
በሚመለስበት ወቅት መሬቱ ከመለቀቁ በፊት ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት
እንደቀድሞ መስጠትና የተፈጥሮ ሃብቱ እንዲያገግም በሚያስችለው ደረጃ ላይ
መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፤
2. በጊዚያዊነት የተለቀቀው መሬት በሚመለስበት ወቅት በደረሰበት ጉዳት
ምክንያት ለባለይዞታው የሚሰጠው ምርት እንደሚቀንስ ወይም ለተወሰኑ
አመታት ከነአካቴው ምርት እንደማይሰጥ አግባብ ባለው የመሬት አጠቃቀም
ባለሙያዎች በኩል የተረጋገጠ እንደሆነ መሬቱን ወስዶ ለልማት ያዋለው
አካል ለባለይዞታው የመፈናቀያ ካሣ ክፍያውን ይፈጽማል፡፡
3. በጊዜዊነት የተጠየቀን መሬት አስመለክቶ መሬቱ ከመወሰዱ በፊት
አመላለሱን አስመለክቶ፣ መሬቱ ስለማገገሙ ወይም የማያገግም ከሆነም ስለ
ካሳ ክፍያ መሬት ጠያቂውና መሬቱን የሚያሰለቅቀው አካል ቅድሚያ የጋራ
ስምምነት ላይ መደረስ ይኖርባቸዋል፡፡
25. ስለካሳ አተማመን

በዚህ መመሪያ መሠረት ለህዝብ ጥቅም ወይም አገልግሎት ሲባል በሚለቀቅ


የመሬት ይዞታ ላይ ለለማ ንብረትና ቋሚ ማሻሻያዎች የሚከፈለው የካሳ መጠን
አተማማን ወይም የሚሰላበት ቀመር በዚህ መመሪያ ተደንግጓል፡፡
26. ስለካሳ ስሌት ቀመር
26.1. በመሬት ላይ ለለማ ንብረት የግንባር ካሣ ግምት የሚሰላበት ዘዴ
26.1.1. የቤት፣ የመጋዘን፣ የመጠለያና ሌሎች ግንባታዎች ካሳ ግመታ አሰራር
ሀ. የቤት፣ የመጋዘን፣ የመጠለያና ሌሎች ግንባታዎች ካሣ የሚሰላው
የሚፈርሰውን ግንባታ መልሶ ለመግንባት የሚያስችል የወቅቱን የካሬ ሜትር
ወይም የነጠላ ዋጋ በማውጣት ይሆናል፡፡
28
ለ. ከቤቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የግቢ ንጣፍ፣ በረንዳ፣ ሴፕቲክ ታንክና
ሌሎች ስትራክቸሮችን ለመስራት የሚያስፈልገውን የወቅቱን የገበያ ዋጋ፤

ሐ. ቤቱ በመነሳቱ ምክንያት የተገነቡ የአገልገሎት መስመሮችን ለማፍረስ፣


ለማንሳት፣ መልሶ ለመገንባትና ለመትከል የሚያስፈልጉትን ወጪዎች ግምት
ይጨምራል፡፡

መ. በዚህ አንቀጽ በፊደል ተራ ቁጥር “ሀ” ላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ፣


በመሬቱ ላይ ላደረገው የቋሚ ማሻሻያ ያወጣውን የገንዘብና የጉልበት ወጭ
የሚተካ ካሳ ይከፈለዋል፡፡

ሠ. ቤቱ የሚፈርሰው በከፊል ከሆነና የቤቱ ባለቤት ቦታውን ለመልቀቅ ከመረጠ


ለሙሉ ቤቱ ካሣ ይከፈለዋል፡፡

ረ. ቤቱ የሚፈርሰው በከፊል ከሆነና የቤቱ ባለቤት በቀሪው ቦታ ላይ ለመቆየት


ከመረጠ ለፈረሰው የቤት አካል ብቻ ተሰልቶ ካሣ ይከፈለዋል፡፡ ሆኖም
የቤቱ ባለቤት በቀሪው የቤቱ አካል የመቆየት ምርጫ አግባብ ባለው
የከተማም ሆነ የቀበሌ ማዕከል ኘላን መስረት ተቀባይነት ያለው መሆን
አለበት፡፡

ሰ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (26.1.1) ከፊደል ተራ ቁጥር “ሀ” እስከ “ረ”
የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የቤት፣ የመጋዘን፣ የመጠለያና ሌሎች
ግንባታዎች ካሳ ግመታ አሰራር ቀመር= የወቅቱ የግንባታ ወጪ
(የማቴርያል + የጉልበት + የገንዘብ ወጪ) + በመሬት ላይ የተደረገ ቋሚ
ማሻሻያ (ምንጣሮ + መሬት ማስተካከል + ድንጋይ ለቀማ + ሌሎች
የመሬት ልማት ሥራዎች) ወጪ + የቀሪ ዘመን የመሬት ሊዝ ተመላሽ
ክፍያ ቢኖር፣

29
26.1.2. የአጥር፣ የእንሰሳት በረት ወይም ጉረኖ ስራዎች ካሣ አተማመን

ሀ. የግንብ አጥር ካሣ የሚሰላው የሚፈርሰውን አጥር መልሶ ለመስራት


የሚያስፈልገው የወቅቱ የካሬ ሜትር ወይም የነጠላ ዋጋ በማውጣት
ይሆናል፡፡
ለ. ከግንብ ውጪ ለሆነ የአጥር አይነት የወጣበትን ወጪ በወቅቱ የገበያ ዋጋ
ተሰልቶ ካሳ ይከፈለዋል፡፡

ሐ. አጥሩ ተነስቶ መልሶ ለማጠር የሚቻል ከሆነ የሚከፈለው ክፍያ ተዛውሮ


የሚተከል ንብረት እንደሚከፈለው ይሆናል፡፡ ነገር ግን የአጥሩ ባለቤት ካሳ
እንዲከፈለው ወይም መልሶ ለማጠር እንደሚፈልግ ምርጫ ይሰጠዋል፡፡

መ. የአጥር ካሣ ቀመር = የአጥሩ አጠቃላይ ርዝመት (በሜትር) የአጥሩ


ቁመት (በሜትር)  የአጥሩ ወርድ (በሜትር)

ሠ. የእንሰሳት በረት ወይም ጉረኖ ስራዎች ካሣ= የወቅቱ የግንባታ ወጪ


(የማቴርያል + የጉልበት + የገንዘብ ወጪ)

26.1.3. የሰብል ካሣ አተማመን

ሀ. የሰብል ካሣ የሚተመነው ሰብሉ ለመሰብሰብ ደርሶ ቢሆን ኖሮ ሊሰጥ


የሚችለውን የምርት መጠንና ምርቱ ሊያስገኝ ይችል የነበረውን ወቅታዊ
የገበያ ዋጋ መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡

ለ. በመሬቱ ላይ የተደረገ ቋሚ ማሻሻያ ካለ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ


(26.1.3) ፊደል ተራ ቁጥር “ሀ” ከሚከፈለው ካሳ በተጨማሪ ያሻሻለበት
የገንዘብና የጉልበት ወጭ የሚተካ ካሳ ይከፈለዋል፡፡

ሐ. ሰብሉ ለመሰብሰብ የደረሰ ከሆነ ባለንብረቱ በካሣ ክፍያ ፋንታ በተሰጠው


የጊዜ ገደብ ውስጥ ሰብሉን ሰብስቦ መውሰድ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰብሉን
ሰብስቦ ማንሳት የማይችል ከሆነም የሰብል ካሳ ተሰልቶ ይከፈለዋል፡፡

30
መ. የመኸር የሰብል አብቃይ ካሳ = [የመኸር መሬት ስፋት በሄ/ር x በአንድ
ሄ/ር መሬት የሚገኝ ምርት በኩንታል x የሰብሉ የወቅቱ የገቢያ ዋጋ ብር
በኩንታል] + የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ወጪ
ሠ. የበልግ የሰብል አብቃይ ካሳ = [የበልግ መሬት ስፋት በሄ/ር x በአንድ ሄ/ር
መሬት የሚገኝ ምርት በኩንታል x የሰብሉ የወቅቱ የገቢያ ዋጋ ብር
በኩንታል] + የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ወጪ
ረ. የቀሪ ዕርጥበት የሰብል አብቃይ ካሳ = [የቀሪ ዕርጥበት መሬት ስፋት በሄ/ር
x በአንድ ሄ/ር መሬት የሚገኝ ምርት በኩንታል (የቀሪ ዕርጥበት ለሚያለሙ
አካባቢዎች ብቻ)] x የሰብሉ የወቅቱ የገቢያ ዋጋ ብር በኩንታል] + የመሬት
ቋሚ ማሻሻያ ወጪ
ሰ. የመስኖ የሰብል አብቃይ ካሳ = [(በመስኖ የሚለማ መሬት ስፋት በሄ/ር x
ከአንድ ሄ/ር መሬት ላይ የሚገኝ ምርት በኩንታል x የሰብሉ የወቅቱ የገቢያ
ዋጋ በኩንታል) X ምርቱ በሚሰበሰብበት ጊዜ] + የመሬት ቋሚ ማሻሻያ
ወጪ (በዓመት ከ2 አስከ 3 ጊዜ ለሚያለሙ መሬቶች ብቻ)]
ሸ. የሰብል ተረፈ ምርት ካሣ = የቦታው ስፋት (በሄ/ር)የሰብሉ ተረፈ ምርት
ወቅታዊ የገበያ ዋጋበአንድ ሄ/ር ስፋት ላይ የሚገኝ ተረፈ ምርት በኩ/ል
ወይም በሸክም X ምርቱ በሚሰበሰብበት ጊዜ]
ቀ. የሰብል ተረፈ ምርት ካሣ የሚገመተው በመኸር፣ በበልግ፣ በቀሪ ዕርጥበት
ወይም በመስኖ የምርት ወቅት በሚገኜው የምርት ድግግሞሽ ታሳቢ ተደርጎ
የሚሰላ ይሆናል፡፡
26.1.4. የቋሚ ተክል ካሳ
1. የቋሚ ተክል ካሣ የሚሰላው ተክሉ ፍሬ መስጠት ያልጀመረ ከሆነ ተክሉ
በሚገኝበት ደረጃ ለማድረስ የሚያስፈልገውን ወጪ ግምት በማስላት እና
በመሬቱ ላይ ያደረገው ቋሚ ማሻሻያ ካለ ያሻሻለበት የገንዘብና የጉልበት
ወጭዎች የሚተካ ካሳ ይከፈለዋል፡፡ ፍሬ መስጠት ያልጀመረ የተባለው
ተዛውሮ ተተክሎ የጸደቀ ችግኝን ይጨምራል፡፡

31
ሀ. ፍሬ መስጠት ያልጀመረ የቋሚ ተክል ካሳ = [የተክል ብዛት
(በእግር) X በአንድ እግር ለጉልበትና ለማቴሪያል የወጣ ወጪ
ግምት] + የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ወጪ
2. ፍሬ መስጠት የጀመረ የቋሚ ተክል ካሳ የሚሰላው ወቅታዊ የቋሚ ተክሉ
ምርት ወቅታዊ የገበያ ዋጋ እና በመሬቱ ላይ የቋሚ ማሻሻያ
ያደረገበትን የገንዘብና የጉልበት ዋጋ የሚተካ ካሳ ጨምሮ ይከፈለዋል፡፡
ሀ. ፍሬ መስጠት የጀመረ የቋሚ ተክል ካሳ = [የተክል ብዛት
(በእግር)/ ወይም በአንድ ሄ/ር ሊኖር የሚችል ተክል ብዛት X በሄ/ር
X ተክሉ በአንድ እግር በዓመት የሚያሰገኘው ምርት ብዛት (በኪሎ
ግራም) x የቋሚ ተክሉ ምርት የወቅቱ የገቢያ ዋጋ ብር በኪሎ
ግራም] + የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ወጪ
ለ. የዛፍ ካሣ = [የዛፉ ዓይነት ምሳሌ ዋንዛ (ከፍተኛ ዛፍ ብዛት x
የአንዱ ዋጋ) + (መካከለኛ ዛፍ ብዛት x የአንዱ ዋጋ) + (ዝቅተኛ
ዛፍ ብዛት x የአንዱ ዋጋ)] + [የዛፉ ዓይነት ግራር (ከፍተኛ ዛፍ
ብዛት x የአንዱ ዋጋ) + (መካከለኛ ዛፍ ብዛት x የአንዱ ዋጋ) +
(ዝቅተኛ ዛፍ ብዛት x የአንዱ ዋጋ)] + …...
ሐ. ለማገዶና ለግንባታ የተተከለ ባህር ዛፍ ወይም ተመሳሳይ ዛፍ =
(የወራጅ ብዛት x የአንዱ ዋጋ) + (የማገር ብዛት x የአንዱ ዋጋ) +
(ምሰሶ ብዛት x የአንዱ ዋጋ) + (የጨፈቃ ብዛት x የአንዱ ዋጋ)
/በወቅቱ የገበያ ዋጋ መሠረት/
26.1.5. የንብረት ማንሻና መልሶ መትከያ ካሣ ተመን በተመለከተ
ሀ. የንብረት ማንሻና መልሶ መትከያ ካሣ ተመን = የንብረቱ ማንሻ
ወጪ + የማዛወሪያ ወጪ + መልሶ የመትከያ ወጪ /በወቅቱ የገበያ
ዋጋ መሠረት/
26.1.6. የጥብቅ ሳር ካሳ ተመን በተመለከተ
ሀ. የጥብቅ ሳር ካሳ = ሳሩ የሸፈነው ቦታ በሄ/ር x በሄ/ር የሚሰበሰበው ሳር
በሸክም x የሚመረተው የሳር ምርት ወቅታዊ የገቢያ ዋጋ በሸክም

32
26.1.7. የመካነ መቃብር ካሣ ተመን በተመለከተ
ሀ. የመካነ መቃብር ካሣ = ለመካነ መቃብር ማንሻ ወጪ+ የተለዋጭ
ማረፊያ ቦታ ማዘጋጃ ወጪ+ አጽሙን ለማዛወሪያና ማሳረፊያ የዋለ ወጪ+
ሀይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓት ማስፈፀሚያ ወጪ
26.1.8. ለውሃ ጉድጓድ፣ የጎለበቱ ምንጮች፣ የተቆፈሩ ኩሬዎች፣ የመስኖ
ግንባታዎች፣ የውሃ ማፋሰሻ ቦዮች፣ የውሃና አፈር ጥበቃ ህዳጎች እና ሌሎች
ስትራክተሮች ተመን በተመለከተ
ሀ. ለውሃ ጉድጓድ፣ የጎለበቱ ምንጮች፣ የተቆፈሩ ኩሬዎች፣ የመስኖ
ግንባታዎች፣ የውሃ ማፋሰሻ ቦዮች፣ የውሃና አፈር ጥበቃ ህዳጎች እና
ሌሎች ስትራክተሮች = የወቅቱ የግንባታ ወጪ (የማቴርያል + የጉልበት
+ የገንዘብ ወጪ)
26.2. የመፈናቀያ ካሳ
1. የመሬት ይዞታውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲለቅ ለሚደረግ የገጠር መሬት
ባለይዞታ ወይም ለወል መሬት ባለይዞታዎች መሬቱ እንዲለቀቅ ከመደረጉ
በፊት በነበሩት አምስት ዓመታት ያገኙት አማካኝ ምርታማነት በወቅቱ
የገቢያ ዋጋ ተባዝቶ መሬቱ እሰኪመለስ ድረስ ባለው ጊዜ ታስቦ ከሚከፈለው
የግንባር ካሳ በተጨማሪ የማፈናቀያ ካሳ ይከፈላቸዋል፡፡ ሆኖም የሚከፈለው
የካሳ መጠን በቋሚነት ከሚከፈለው የማፈናቀያ ካሳ መብለጥ የለበትም፡፡
2. በጊዚያዊነት ለሚለቀቁ ይዞታዎች = (የሰብል ካሳ + ፍሬ መስጠት የጀመረ
ቋሚ ተክል ካሳ + የጥብቅ ሳር ካሳ + የተረፈ ምርት ካሳ) x በሚወሰደው
ጊዜ ብዛት
3. በቋሚነት ለሚለቀቁ ይዞታዎች = (የሰብል ካሳ + ፍሬ መስጠት የጀመረ
ቋሚ ተክል ካሳ + የጥብቅ ሳር ካሳ+ የተረፈ ምርት ካሳ) x 10
4. በማናቸውም ሁኔታ የተደረገ የመሬት ቋሚ ማሻሻያ ወጪ የሚከፈለው
ለአንድ ጊዜ ብቻ ይሆናል፤ በቋሚ ማፈናቀያ ካሳ ስሌት አብሮ
አይታሰብም፡፡

33
5. በዚህ መመሪያ መሠረት ከለቀቁት መሬት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ትክ መሬት
ያገኙ ባለይዞታዎች የመፈናቀያ ካሣ አይከፈላቸውም፡፡ ይሁን እንጂ ትክ
መሬቱ ከቀድሞው ይዞታ ጋር ተመጣጣኝ መሬት ካልሆነ ላጋጠመው ልዩነት
ብቻ የመፈናቀያ ካሣው ሊከፈለው ይገባል፡፡
26.3. ስለሌሎች የተለያዩ የካሣ ክፍያዎች ስሌት ቀመር

ከዚህ በታች የተመለከቱት የካሣ ክፍያዎች በሚከተለው አኳኋን ይሰላል፡፡


1. መሬት በመከራየት የእርሻ ስራ ለጀመረና ለአዘመረ ግለሰብ የሚከፈለው ካሣ =
በዚህ መመሪያ ውስጥ ለሰብል /ለመኸር፣ ለበልግ፣ ለቀሪ ዕርጥበት ወይም
በመስኖ ለሚለማ መሬት/ በተደነገገው ዓይነት ለአንድ ዓመት ያህል
ይሆናል፤
2. በሊዝ ለተከራዬ ባለመብት የሚከፈለው ካሣ= ባለ ሊዙ ላከናወናቸው የልማት
ተግባራት ያወጣቸው ወጪዎች በመሬቱ ላይ አንስቶ መውሰዱ
ለማይችላቸው ቋሚ ንብረቶች በማካተት + የቀሪ ዘመን የመሬት ሊዝ
ክፍያ ተመላሽ በማድረግ ይሆናል፡፡
3. ግዴታን ባለመወጣት መብታቸውን ለሚያጡ የመሬት ባለይዞታዎች
ስለሚከፈል ካሳ = በመሬቱ ላይ የለማ ቋሚ ንብረት ግምት ብቻ ይከፈላል፤
4. የይዞታ መብታቸውን በፈቃደኝነት ለሚተው ባለይዞታዎች የሚከፈለው ካሳ =
በመሬቱ ላይ ለለማው ቋሚ የንብረት ግምት ብቻ ይከፈላል፤
5. በቋሚነት ለሚለቀቅ የመተላለፊያ መሬት የሚከፈለው ካሳ = በዚህ መመሪያ
ለሰብል (ለመኸር፣ ለበልግ፣ ለቀሪ ዕርጥበት ወይም በመስኖ ለሚለማ መሬት
በተደነገገው መሰረት) በዘላቂነት ለሚለቀቅ መሬት በሚከፈለው የካሣ ግምት
አኳኋን ነው፤
6. በመስኖ ልማት የመሬት ሽግሽግ ሂደት ሳቢያ የሚከፈው ካሳ= በመሬት ላይ
የለማውን ንብረት ዋጋ ግምት ለመስራት በሚያስችለው ቀመር የተደነገገው
የካሣ ክፍያ x የመስኖው መሬት እስኪሰጥ ወይም መሬቱ ለሚለቀቅባቸው
ዓመታት ብቻ ወይም በቋሚነት የሚለቀቅ መሬት ከሆነ በቋሚ የካሳ
አከፋፈል ስርዓት መሰረት ነው።

34
ክፍል አራት

የካሳ ሰነድ ስለማጽደቅ፣ ስለ ካሳ ክፍያና ውሳኔ አሰጣጥ


27. የካሳ ሰነድ ሰለማጽደቅ
በወረዳ፣ በከተማ አስተዳደር፣ በመሪ ማዘጋጃ ቤት፣ በንዑስ ማዘጋጃ ቤትና
በታዳጊ ከተሞች ለሚለቀቅ መሬትና ቋሚ ንብረት የካሳ ሰነድ ማስጸደቅ
በተመለከተ፡-
1. እስከ 5 ሚሊዮን ብር ድረስ ለሚደርስ ካሳ ሰነድ በወረዳ ወይም በከተማ
አስተዳደር በሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም
ኃላፊ በኩል ተመርምሮ ይጸድቃል፤ ለገንዘብ ከፋዩ አካልም የክፍያ
ትዕዛዝ እንዲተላለፍ ያደርጋል፤
2. የካሳ ሰነዱ ከ5 ሚለዮን ብር በላይ ሁኖ ሲገኝ፡-

ሀ. ተዘጋጅቶ የቀረበው ካሳ ሰነድ ለከተማው ከንቲባ፤ እርሱ በማይገኝበት


ጊዜ ለምክትል ከንቲባ ወይም ሁለቱም ከዓቅም በላይ በሆነ ምክንያት
እንደማይገኙ ሲረጋገጥ ለከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊው በከተማ አስተዳደሩ
በሚገኘው የግብርና፣ መሬት አስተዳደርና መልሶ ማቋቋም መመሪያ
ወይም ጽ/ቤት በኩል ካሳ ሰነዱ ቀርቦ እንዲጸድቅ ይደረጋል፤ ለገንዘብ
ከፋዩ አካልም የክፍያ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ ያደርጋል፤
ለ. በወረዳ ደረጃ የካሳ ሰነድ መመርምርና ማጽደቅን በተመለከተ
በወረዳው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት በኩል
ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሰነድ የወረዳው አስተዳደሪ፤ እርሱ በማይገኝበት
ጊዜ ምክትል አስተዳደሪ ወይም ሁለቱም ከዓቅም በላይ በሆነ ምክንያት
እንደማይገኙ ሲረጋገጥ፣ የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ መርምሮ
ያጸድቃል፤ ለገንዘብ ከፋዩ አካልም የክፍያ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ
ያደርጋል፤
ሐ. በሚመለከተው አካል ከመጽደቁ በፊት ካሳው ለባለይዞታው ቀድሞ
አይነገርም፤ ነገር ግን በይፋ በጽ/ቤቱ ከጸደቀ በኃላ ለእያንዳንዱ

35
ባለይዞታ የተገመትለትን የካሳ መጠን በዝርዝር ተገልጾ በደብዳቤ
እንዲደረሰው ይደረጋል፡፡
28. የካሳ አከፋፈል ስርዓት

በከተማም ሆነ በገጠር መሬታቸው ለተወሰዳባቸው፣ ቋሚ ንብረታቸው


ለተነሳባቸው ባለይዞታዎች የካሳ ክፍያ ስርዓትን በተመለከተ በሚከተለው
መለኩ ተደንግጓል፡፡
1. በተዋረድ የሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም የካሳ
ክፍያ መፈጸም እንዲቻል ባለይዞታዎች የግል የቁጠባ ሂሳብ አካውንት
እንዲከፍቱ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙም በክልሉና በተዋረድ ባለው
አስተዳዳር ለሚከናወን ልማት የቁጠባ ሂሳብ የሚከፈተው በአማራ
ብድርና ቁጠባ ተቋም ሲሆን የፌደራል ፕሮጀክቶች እንደ አስፈላጊነቱ
ከፋዩ አካል በሚመርጠው ህጋዊ የፋይናንስ ተቋማት የቁጠባ ሂሳቡ
እንዲከፈት በማስደረግ ክፍያ ይፈጸማል፤
2. ካሳ ከፋዩ የክልሉ መንግስት፣ የከተማ ወይም የወረዳ አስተዳደር ሆኖ
ሲገኝ ለአርሶ አደሩ የሚከፈለው ካሳ ገንዘብ በተዋረድ በሚገኘው የአማራ
ብደርና ቁጠባ ተቋም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር በጥቅል የተጠየቀው
ገንዘብ ከነክፍያ ሰነዱ ፔሮል ተዘጋጅቶ እንደፈጸም ይደረጋል፤
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በተዋረድ
የሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም፣ ካሳ
የሚከፈላቸውን አርሶ አደሮች ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት ለከፋዩ አካል
የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደበተር፣ የተወሰደውን የመሬት ስፋት፣
ለባለይዞታው የሚከፈለው ዝርዝር ካሳ ገንዘብ መጠን፤ የቀበሌ
መታወቂያና ሌሎች ደጋፊ መረጃዎች በማሟላት በጸደቀው የካሳ ሰነድ
መሰረት ክፍያው እንዲከናወን ለአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወይም
ህጋዊ ባንኮች መረጃዎችን በማደራጃት ያስተላልፋል፤

36
4. በተዋረድ የሚገኘው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም ለካሳ
ተከፋዮች ገንዘቡ በእያንዳንዱ ተከፋይ በተከፈተው የቁጠባ ሂሳብ
በትክክል መግባቱንና ክፍያ መፈጸሙን ያረጋግጣል፤
29. በቀበሌ ማዕከላት በኩል የሚፈጸም ካሳ ክፍያን አስመለክቶ
ሀ. ከእያንዳንዱ ቦታ ፈላጊ ግለሰብ ወይም ተቋም በተገመተው ካሳ መሰረት
በተዋረድ የሚገኘው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ተቋም በአማራ ብድርና
ቁጠባ ተቋም አማካኝነት በሚከፈተው የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር የሚፈለገው
ገንዘብ ገቢ እንዲሆን ያደርጋል፤ ከፋዩ አካል ገቢ ያደረገበትን ህጋዊ የሂሳብ
ደረሰኝ ቦታውን ከመረከቡ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፤
ለ. በጥቅል ከእያንዳንዱ መሬት ተረካቢ ገቢ ከተደረገው የካሳ ገንዘብ፣ ለካሳ
ተከፋዮች ክፍያ እንዲፈጸም በእያንዳንዱ ተከፋይ ስም በአማራ ብድርና
ቁጠባ ተቋም በተከፈተው የቁጠባ ሂሳብ ገንዘቡ እንዲተላለፍላቸው የመሬት
ይዞታ ማረጋገጫ ደበተር፣ የተወሰደውን የመሬት ስፋት የሚያሳይ ካርታ፣
ለባለይዞታው የሚከፈለው ዝርዝር ካሳ ገንዘብ መጠን፤ የቀበሌ መታወቂያና
ሌሎች ደጋፊ መረጃዎችን በማያያዝ የወረዳው ገጠር መሬት አስተዳዳርና
አጠቃቀም ጽ/ቤት የክፍያ ትዕዛዝ ለወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር
ጽ/ቤት ይሰጣል፤
ሐ. የወረዳው ገጠር መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ለካሳ ተከፋዮች
ገንዘቡ በአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በእያንዳንዱ ተከፋይ ስም በተከፈተው
የቁጠባ ሂሳብ በትክክል መግባቱንና ክፍያ መፈጸሙን ያረጋግጣል፡፡
30. ስለካሳ አከፋፈልና ውሳኔ አሰጣጥ
30.1. የካሳ አከፋፈል ሂደት
1. በገጠር መሬት ይዞታዎች ላይ ይህንን መመሪያ መሠረት በማድረግ
የተሠራው ግምት ለከተማው ወይም ለወረዳው የመሬት ጠያቂ አካላት
ወይም ባለቤቶች እንደ ደረሰ በፕሮጀክቱ ወይም በወኪሎቻቸው
አማካኝነት በ30 ቀናት ውስጥ አግባብ ላላቸው ባለይዞታዎች ወይም
እነርሱ በህግ ለሚወክሏቸው ሰዎች እንዲከፈል ይደረጋል፤

37
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ማንኛውም ባለይዞታ የካሳ
ክፍያውን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ለዚሁ ዓላማ በወረዳው ወይም
በከተማ አስተዳደር ዘንድ በስሙ በተከፈተ ዝግ የባንክ ሂሣብ
እንዲቀመጥና ይህንኑ ባለይዞታው እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
3. በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ደንብ መሰረት፡-

ሀ. ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በማይኖሩበት ጊዜ እና አንደኛው


የትዳር ጓደኛ በህይወት ላለው ኑዛዜ አደረጎ የሞተ አንደሆነ
በህይዎት የቀረውና የመጠቀም መብት ያለው የትዳር ጓደኛ የራሱ
ድርሻ በሆነው ይዞታ ላይ የሚከፈለውን ካሳና በውርስ ደግሞ በሞት
ከተለየው የትዳር ጓደኛው በሚለቀቀው ይዞታ መሬት ላይ
ለተደረገው ቋሚ ማሻሻያና የለማ ንብረት ካሣ ክፍያዎችን
ይቀበላል፤
ለ. የሟች ህጋዊ ኑዛዜ በማይኖርበት ጊዜ በህግ መሰረት ወራሽ ለሆኑ
አካላት ማስረጃቸው እየተረጋገጠ የንብረት ካሳና የመፈናቀያ ካሳ
ክፍያ አንዲፈጸም ይደረጋል፤
ሐ. ሟች ለማንኛውም ህጋዊ ወራሽ ያወረሰው በመሬቱ ላይ
ያፈራውን ሃብት ብቻ በሚሆንበት ጊዜ የካሳ ክፍያው የሚፈፀመው
ይህንኑ መሰረት አድርጐ በመሬቱ ላይ ካፈራው ሃብት ጋር
እየተመዛዘነ ይሆናል፤
መ. መሬት የመለካት ስራውና በመሬቱ ላይ የለማው ንብረት ቆጠራ
ከተከናወነ በኋላ በካሣ ክፍያ ወቅት ጋብቻ የፈፀሙ ሰዎች
ያጋጠሙ እንደሆነ ክፍያው የሚፈፀመው የንብረት ቆጠራው
ሲካሄድ ተገኝቶ ለፈረመው ባለይዞታ ይሆናል፡፡
4. በግል ይዞታ የጋራ ተጠቃሚዎች ለህዝብ ጥቅም ወይም አገልግሎት
ሲባል ይዞታቸውን በሚለቁበት ጊዜ የሚከፈለው የካሳ ክፍያ ለሁሉም
የመሬቱ ተጠቃሚዎች በጋራ፣ እነርሱ በሚወክሉት አካል ወይም
ለእያንዳንዳቸው በማከፋፈል ይሆናል፤

38
5. የወል መሬት የካሳ ክፍያ ለወል መሬቱ ተጠቃሚዎች በጋራ
ለሚጠቀሙበት የማህበራዊ አገልግሎትና መሰረተ ልማት ግንባታ
ይውላል። የወል መሬት የካሳ ገንዘብ ለወል ተጠቃሚዎች በግለሰብ
ደረጃ አይከፋፈልም፡፡

30.2. በካሳ አከፋፈል ስለሚሰጥ ውሳኔ


30.2.1. በአካባቢ ባልተገኙ የመሬት ባለይዞታዎች ላይ ስለሚሰጥ ውሳኔ
ሀ. መሬት የመለካቱና የሃብት ቆጠራ ስራው ከተከናወነ በኋላ በካሳ
ክፍያ ወቅት ባለይዞታው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካሳውን
መቀበል አለመቻሉ የተረጋገጠ እንደሆነ ህጋዊ ተወካዮቹ
ሲያመለክቱ የአንድ ወር ማስታዎቂያ በማውጣት ክፍያው
እንዲፈፀም ይደረጋል፤
ለ. ባለይዞታው በሞት ከመለየቱ የተነሣ የካሣ ክፍያውን አለመቀበሉ
የታወቀ እንደሆነ ክፍያው ለህጋዊ ወራሾቹ እንዲፈፀም ይደረጋል፡፡
ሐ. ከዓቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በመንግስት በተሰጠ ጊዚያዊ
ኃላፊነት፣ በብሄራዊ አገልግሎት፣ በፓርላማ ምርጫና በመሣሰሉት
ሣቢያ በአካባቢው አለመኖራቸው ለተረጋገጠ ባለይዞታዎች
የመሬት ልኬታና የሃብት ቆጠራ ሥራው በሌሉበት ተካሂዶ
የተወሰነላቸው ካሳ በወረዳው ወይም በከተማው አስተዳደር በኩል
በስማቸው በተከፈተ ዝግ የባንክ ሂሣብ እንዲቀመጥላቸው ተደርጎ፣
ግለሰቦቹ በአካል ሲቀርቡ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን ሲልኩ
ክፍያውን እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡ ነግር ግን በግመታው ላይ
ቅሬታ ከላቸው በህጉ በተቀመጠው ስርዓት መሰረት የሚፈጸም
ይሆናል፡፡
30.2.2. በሰፈራና በመሬት ድልድል አማካኝነት የተገኘ የመሬት ይዞታ
ሲለቀቅ በሚከፈል ካሳ ላይ ስለሚሰጥ ውሳኔ
1. የክልሉ መንግስት በሚያዘጋጀው የሰፈራ ፕሮግራም በፈቃደኝነት
ተሳትፎ ምትክ መሬት ተሰጥቶት ማምረት የጀመረና ምርጫው
39
በሰፈረበት አካባቢ ለመኖር መሆኑን በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ
ከሰፈራ በፊት ይኖርበት ለነበረው ቀበሌ መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ኮሚቴ እና ለቀበሌው አስተዳደር በፅሁፍ ያሳወቀ አርሶ
አደር፣ በመሬቱ ላይ ያለማውን ቋሚ ንብረት አንስቶ የመውሰድ
እንዲሁም አንስቶ መውሰድ ለማይችለው ደግሞ በዚህ መመሪያ ስለ
ቋሚ ንብረት ካሳ አከፋፈል በተደነገገው መሰረት በቅድሚያ
ተመጣጣኝ ካሳ እና የመሬቱን ለምነት ጠብቆ ለማቆየት ያወጣውን
ወጪ አግባብ ካለው የቀበሌ አስተዳደር ወይም ይዞታውን ከሚረከበው
አዲስ ባለይዞታ እንዲያገኝ ይደረጋል፤
2. የቀበሌው አስተዳደር በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2.2.1) መሰረት
የተወሰነውን ካሳ ለመክፈል አቅም የሌለው በሚሆንበት ጊዜ መሬቱን
የተረከበው አካል ክፍያውን ይፈጽማል፤
3. ማንኛውም ባለይዞታ በዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች መሰረት በሚሰጥ
ውሳኔ ላይ ቅር የተሠኘ እንደሆነ በ60 ቀናት ውስጥ ቅሬታና
አቤቱታውን ለካሳ አጣሪ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል፡፡

30.2.3. የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ባልወሰዱ ባለይዞታዎች


ላይ ስለሚሰጥ ውሳኔ
1. በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓት ማስፈፀሚያ
ደንብ መሰረት ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት የይዞታ ማረጋገጫ
ደብተር ሳያወጣ የተገኘ ማንኛውም ባለይዞታ መሬቱን ለሕዝብ
ጥቅም እንዲለቅ የተወሰነበት እንደሆነ ያለ ካሳ እንዲለቅ ይገደዳል፡፡
30.2.4. በካሳ ግመታና አከፋፈል ወቅት በተሳሳተ ወይም በተጭበረበረ
ማስረጃ ለሚጠየቅ የካሳ ክፍያ የሚሰጥ ውሳኔ
1. በሃሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ የተካሄደ መሬት የመለካትና የሃብት
ቆጠራ ሥራ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም፤

40
2. መሬት የመለካትና የንብረት ሃብት ቆጠራ ሥራው በሚካሄድበት
ወቅት ሆነ ብሎ መረጃዎችን ማዛባትና የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም
ማድረግ በህግ ተጠያቂ ያደርጋል፤
3. ማንኛውም ባለይዞታ ነኝ ባይ በማናቸውም ሁኔታ የሰጠው መረጃ
ትክክለኛ ሆኖ ካልተገኘና ይዞታውም የእርሱ አለመሆኑ ከተረጋገጠ
የጠየቀውን የካሣ ክፍያ አያገኝም፡፡ ክፍያውን ከወሰደ በኋላም ቢሆን
በተሳሳተ ማስረጃ የተከፈለ መሆኑ ከተረጋገጠ በህግ ተገዶ እንዲመልስ
ይደረጋል፤ በፈጸመው የማጭበርበር ስራ በህግ ተጠያቂ ይሆናል፤
4. በዚህ መመሪያ መሠረት ባለይዞታዎች ድንበር መግፋታቸው
ከተረጋገጠና ችግሩ በአዋሳኝ ባለይዞታዎች ስምምነት ካልተፈታ
ይኸው እስኪስተካከልና ስሌቱ በዚያው መሠረት እስኪታረም ድረስ
በተጨማሪ ለተያዘው መሬት ወይም ለተገፋው ድንበር የተጠየቀው
የካሳ ክፍያ ሊፈፀም አይችልም፤
5. በዚህ መመሪያ መሠረት የንብረት ገማች ቡድን በፈፀመው የመሬት
መለካትና የሃብት ቆጠራ ተግባር ስህተት ምክንያት በማንኛውም ሰው
ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ፣ የጉዳቱን ካሣ በመክፈል ረገድ ሀላፊነት
ያለበት አግባብ ያለው የወረዳ ወይም የከተማ አሰተዳደር ይሆናል፡፡
ሆኖም የወረዳው ወይም የከተማ አስተዳደር ለተጐጅው የከፈለውን
የጉዳት ካሣ እንዲተካለት ጥፋቱን የፈፀመውን ሰራተኛ ወይም የገማች
ባለሙያዎች ቡድን እንደአግባብነቱ በተናጠል ወይም በቡድን በህግ
ተጠያቂ ያደርጋል፤ የከፈለውን ገንዘብ ያስመልሳል፡፡
30.2.5. በክርክር ላይ ስላሉ የመሬት ይዞታዎች የካሳ አከፋፈል ሂደት
1. ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የይዞታ መሬት እንዲለቀቅ በሚደረግበት
ወቅት የሚነሳ ማናቸውም የይገባኛል ጥያቄ መጀመሪያ በክልሉ
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የህግ ማዕቀፍ መሰረት
በሽምግልና ታይቶ በዕርቅ እንዲፈታ ይደረጋል፡፡

41
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2.5.1) ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ
ሆኖ በባለይዞታዎች መካከል በህግ ክርከር ላይ ያለ መሬት
ወይንም የይገበኛል ጥያቄ የቀረበበት ይዞታ የካሳ ግምት ክርክሩ
ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ለጊዜው በወረዳው ወይም በከተማ፣ወይም
በወረዳ አስተዳደር ስም በሚከፈት ዝግ የባንክ ሂሣብ ተቀመጦ
ውሳኔ እንዳገኘም ካሣው ለባለመብቱ ይከፈላል።

42
ክፍል አምስት

የልማት ተነሽዎችን በዘላቂነት ስለማቋቋም


31. የልማት ተነሺዎችን በጉዳት ደረጃ ስለመለየት፡
1. ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚከናወኑ የልማት ስራዎች የሚነሱ የልማት
ተነሺዎችን መልሶ የማቋቋም ተግባር የደረሰባቸውን የጉዳት መጠን
መሠረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡ በዚህም መሠረት የልማት ተነሽዎችን
መልሶ የማቋቋም ተግባር ከዚህ ቀጥሎ በተቀመጠው የጉዳት ደረጃ በጥናት
ተልይቶ ይከናወናል፡፡

ሀ. ሙሉ በሙሉ እና ከዘጠና እስከ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የይዞታ


መሬቱ፣ የለማ ቋሚ ንብረቱ ወይም ኑሮው የተመሠረተበት የገቢ
ምንጭ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም የልማት ተነሽ፣ የማጨሻ ቤቱ
በልማት ምክንያት ቢፈርስበትም ወይም ባይፍርስበትም አንደኛ
ደረጃ ተጎጂ ተብሎ ይመደባል፤
ለ. ከሰባ አስከ ሰማኒያ ዘጠኝ በመቶ የይዞታ መሬቱ፣ የለማ ቋሚ
ንብረቱ ወይም ኑሮው የተመሠረተበት የገቢ ምንጭ ጉዳት የደረሰበት
የልማት ተነሽ የማጨሻ ቤቱ በልማት ምክንያት ቢፈርስበትም ወይም
ባይፍርስበትም ሁለተኛ ደረጃ ተጎጂ ተብሎ ይመደባል፤
ሐ. ከአርባ እስከ ስልሣ ዘጠኝ በመቶ የይዞታ መሬቱ፣ የለማ ቋሚ
ንብረቱ ወይም ኑሮው የተመሠረተበት የገቢ ምንጭ የተነካበት
ማንኛውም የልማት ተነሺ ሶስተኛ ደረጃ ተጎጂ ተብሎ ይመደባል፤
መ. ከሃያ እስከ ሰላሣ ዘጠኝ በመቶ የይዞታ መሬቱና ቋሚ ንብረቱ
የተጎዳበት ማንኛውም የልማት ተነሺ አራተኛ ደረጃ ተጎጂ ተብሎ
ይመደባል፤
ሠ. ከሃያ በመቶ ያነሰ የይዞታ መሬቱ የተወሰደበትና ቋሚ ንበረት
የተነካበት የልማት ተነሺ ደረጃ አምስት ተጎጂ ተብሎ ይመደባል፤
2. በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የሚፈናቀሉ ህጋዊ ባለይዞታዎች ይኸው
መፈናቀል የሚያስከትልባቸው ጉዳት ከወዲሁ ታይቶ፡-

43
ሀ. እንደ የፍላጎታቸው በተናጠልም ሆነ በጋራ በመደራጀት በተለያዩ
የስራ ዘርፎች ተፈላጊው ፕሮጀክት ተቀርጾላቸው ወደስራ እንዲገቡ
ይደረጋል፤
ለ. በመንግሥትም ሆነ በአልሚ ባለሃብቶች አማካኝነት የስራ እድል
በቅድሚያ እንዲፈጠርላቸውና ለስራ የደረሱ የቤተሰብ አባሎቻቸውም
በአካባቢው ከሚካሄደው ልማት ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ተገቢው
ክትትልና ድጋፍ ይደረግላቸዋል፤
ሐ. እንደ አስፈላጊነቱ የብድር አገልግሎት ወይም ሌላ አይነት ልዩ
ድጋፍ ይመቻችላቸዋል፤
መ. የሚያቀርቧቸው ምርቶች በገበያ ረገድ ተወዳዳሪዎች እንዲሆኑ
በስልጠናና በግብይት እሴት ሰንሰለት ትስስር ፈጠራ ረገድ ተገቢው
ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
32. ለልማት ተነሽዎች በጉዳት መጠናቸው መሰረት የመሥሪያና የመኖሪያ
ቦታ አሰጣጥ ስርዓት

32.1. በጉዳት ደረጃ የልማት ተነሺዎች የመኖሪያና የመስሪያ ቦታ


አቅርቦትን በተመለከተ
1. ምንም ቀሪ መሬት የሌላቸው ወይም ያላቸው ቀሪ መሬት ከዝቅተኛ
የይዞታ መጠን በታች በመሆኑ ምክንያት ተጎጂ እንዳይሆኑ፣
በተከፈላቸው ካሳና በሚደረግላቸው ድጋፍ በነበሩበት አካባቢ ቀድሞ
የነበራቸውን የኑሮ ዘይቤ በተሟላ ሁኔታ ለማስቀጠል ይረዳ ዘንድ፣
ቀጥሎ የተዘረዘሩት ተግባራት ሊከናወኑ ይገባል፡-

ሀ. አንደኛ ደረጃ የልማት ተነሺዎችን በተዋረድ በሚገኘው የገጠር


መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም በሚቀርብ መረጃ
መሠረት ቀድሞ ያገኙት የነበረውን የገቢ መጠን እንደመነሻ
በመውሰድ፣ ሠርተው ገቢ የሚያገኙበት የመኖሪያና የመስሪያ
ቦታ ፍላጎታቸውን እና የመረጡትን የሥራ ዘርፍ መሠረት
44
በማድረግ በአቅራቢያ በሚገኘው ከተማ ወይም በገጠር ቀበሌ
ማዕከል በነጻ እንዲያገኙ ይደረጋል፤ ሆኖም የመኖሪያ ቤት
መስሪያ ቦታ የሚሰጣቸው ቤታቸው ለፈረሰባቸው ብቻ ይሆናል፣
ይኸኑን የቦታ አቅርቦት አስመለክቶ መሬቱን ያስለቀቀው
የአስተዳዳር አካል የማመቻቸት ግዴታ አለበት፤
ለ. ለአንደኛ ደረጃ የልማት ተነሺዎች የሚሰጠው የመሥሪያ ቦታ
ስፋት ወይም መጠን ጣሪያ ተነሺዎች የመረጡት የገቢ ማስገኛ
ኢንተርፕራይዝ ዓይነት፣ የሚያስገኘው ጠቀሜታ፤ ሊከናወን
ከታሰበው ልማት ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በሚመለከታቸው
የከተማ አስተዳደርና የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ተቋም አማካኝነት በጋራ ይወሰናል፡፡
ሐ. ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ የልማት ተነሺዎችን አስመልክቶ፣
ባሉበት አካባቢ የተወሰነ ቀሪ መሬት ያላቸው በመሆኑ
በተከፈላቸው ካሳ ቀድሞ የነበራቸውን የኑሮ ዘይቤ በከፊልም
ቢሆን ሊያስቀጥሉ ይችላሉ፤ በመሆኑም እነዚሁ የልማት
ተነሽዎች የመስሪያ ቦታ በዋናነት በገጠር ቀበሌ ማዕከላት
እየተጠና እንዲያገኙ ይደረጋል፤
መ. አራተኛ ደረጃ የልማት ተነሺዎች፣ ባሉበት አካባቢ ከነበራቸው
መሬት ከግማሽ በላይ ቀሪ መሬት ያላቸው በመሆኑ በተከፈላቸው
ካሳና በመንግሥት የልማት ድጋፍ ቀድሞ የነበራቸውን የኑሮ
ዘይቤ በአካባቢው የሚመለከተው ባለሙያ ታግዘው በተረጋጋ
ሁኔታ ኑሯቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም የኑሮ
ሁኔታቸውን በተሻለ ሁኔታ ለማስቀጠል የሌሎችን ጥቅም እና
የአካባቢዉን ዘላቂ ደህንነት ለአደጋ በማያጋልጥ አግባብ
እየተጠናና እየተረጋገጠ በዋናነት በራሳቸው ማሳ ላይ የመልሶ
ማቋቋም ሥራዎችን እንዲሠሩ ዕገዛ ይደረግላቸዋል፡፡
45
ሠ. ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ የልማት ተነሺዎች የተከፈላቸውን
የካሳ ክፍያ፣ የቁጠባ ገንዘብና የመንግሥትን ድጋፍ አቀናጅተው
በከተሞችም ሆነ በገጠር ቀበሌ ማዕከላት ገብተው የተሻለ
የመዋዕለ ንዋይ ሥራ የመሥራት ፍላጎት ያላቸው እንደሆነ፣
ያቀረቡትን የሥራ ዘርፍ ፋይዳ፣ ከመንግሥት የልማት ፍላጎት
ቅደም ተከተልና ከከተሞች የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ፍላጎት ጋር
እንዲጣጣም ተገቢው ድጋፍ እየተደረገ በሂደት ወደ ላቀ
ኢንቨስትመንት በሚሸጋገሩበት አግባብ በቅድሚያ የመሥሪያ
ቦታ በምደባ ይመቻችላቸዋል፡፡
ረ. ከደረጃ ሁለት እስከ ደረጃ አምስት በቀበሌ ማዕከላት ለሚቋቋሙ
ባለይዞታዎች የመስሪያ ቦታ አቅርቦት የካሳ ክፍያ የሚሸፈነው፣
በልማት ተነሽው ይሆናል፡፡
33. በከተማ አስተዳደር፣ በመሪ መዘጋጃ ቤት፣ በንዑስ ማዘጋጃ ቤትና በታዳጊ
ከተሞች በልማት ምክንያት ከመሬታቸው ለሚነሱ ባለይዞታዎች ትክ
የመኖሪያ ቤት እና የመስሪያ ቦታ ስለሚዘጋጅበትና ስለሚሰጥበት ሁኔታ
33.1. ትክ ቦታ ስለመለየትና ስለማዘጋጀት
1. በልማት ምክንያት ከይዞታቸው ለሚነሱና በከተማ ውስጥ ለሚገኙ የገጠር
ቀበሌ ነዋሪዎች በትክነት ሊሰጥ የሚችል ቦታ የያዘ ስፍራ
የሚመለከታቸውን ከተማ ቀጣይ ዕድገት ታሳቢ በማድረግ በጥናት ላይ
ተመስርቶ ይመረጣል፤
2. በትክነት ስለሚመረጠው ስፍራ ተገቢነት በቅድሚያ የጋራ ውይይት
ከተካሄደ በኋላ ቁጥራቸው ከአምስት የማያንሱ የልማት ተነሽ ተወካዮች
መሬቱን ከሚያሰለቅቀው ተቋም ጋር የስምምነት ሰነድ ይፈራረማሉ፤
3. ትክ ቦታ ሆኖ እንዲሰጥ በተመረጠው ስፍራ ላይ የሚገኙ ቀደምት የመሬት
ባለይዞታዎች ቢኖሩ አግባብ ባላው የካሳ አከፋፈልና ትክ ቦታ አሰጣጥ

46
መመሪያ መሰረት ተገቢው የንብረትና የመፈናቀያ ካሳ እንዲከፈላቸው
ተደርጎ ቦታው ከሶስተኛ ወገን ነጻ ይደረጋል፤
4. በትክነት የተመረጠው ቦታ በሚመለከተው ከተማ አማካኝነት አስፈላጊው
የማስፋፊያና የሽንሻኖ ፕላን ተዘጋጅቶለት የከተማው የዕድገት ፕላን አካል
ሆኖ እንዲጸድቅና በዚሁ ፕላን መሰረት በሚመለከተው አካል መሰረተ-
ልማት እንዲሟላለት ይደረጋል፤
5. በከተሞች ለማስፋፊያም ይሁን ለሌላ ልማት ተብሎ ፣ መሬት ከገጠር
መሬት ባለይዞታ በሚወሰድበት ጊዜ፤ ባለይዞታው የማጨሻ ቤት ወይም
ቤትና ቦታ በራሱ ወይም በትዳር ጓደኛው ስም በከተማው ፕላን ውስጥ
ከሌለው 500 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በቅድሚያ
እንዲያገኝ ይደረጋል፤ ሆኖም ግን ከከተማው ፕላን ውጭ ቤት ቢኖረውም
ወደ ከተማ ከሚካለለው ወይም በልማት ምክንያት ከሚወሰድበት መሬት
ላይ ማጨሻ ቤት ባይኖርም 500 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ
ለባለይዞታው በቅድሚያ እንዲያገኝ ሊደረግ ይችላል፤
6. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በከተማው
የፕላን ወሰንም ሆነ ከከተማ ፕላን ወሰን ውጭ ለልማት ሲባል የአርሶ
አደሮች የመሬት ይዞታ በሚወሰደበት ወቅት፣ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት
በላይ ለሆናቸውና በቀበሌው የሚኖሩም ይሁን በማንኛውም ደረጃ
በትምህርት ላይ የሚገኙ ልጆቻቸው እንዲሁም በተሻሻለው የገጠር መሬት
አስተዳደተርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ
(9) የቤተሰብ አባል ተብሎ ትርጉም በተሰጠው መሰረት የቤተሰብ አባል
ለሆኑም ጭምር መረጃው እየተጣራ ለመኖሪያ ቤት የሚውል የመስሪያ
ቦታ በከተማው ፕላን እስታንዳርድ መሰረት ወደ ከተማ የተካለለው
የወላጆቻቸው/ የአሳዳጊዎቻቸው መሬት በቂ ሆኖ እስከ ተገኘ ድረስ የቤት
መስሪያ ቦታ እንዲያገኙ ይደረጋል፤
7. በውርስ የባለይዞታነት መብታቸውን በህግ አግባብ አረጋግጠው የሚቀርቡ
አመልካቾች፣ በከተማው ውስጥ የመኖሪያ ቤት የሌላቸው መሆኑ ሲረጋገጥ

47
ወደ ከተማ ከተካለለው መሬት በአባወራ/በእማወራ ባለ ይዞታዎች የቦታ
መጠን ልክ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲያገኙ ይደረጋል፤
8. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (6) እና (7) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣
በጊዜያዊነት በስደት ከአካባቢያቸው የሌሉ ወደ ሀገር ውጭም ይሁን በሃገር
ውስጥ የተሰደዱ/ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ አካባቢያቸው ከተመለሱ
የቆይታ ጊዜ ከግምት ውስጥ ሳይገባ እና የወላጆቻቸው መሬት ወደ ከተማ
ክልል ከተካተተ እንደመበኛ የቀበሌው ነዋሪ ተቆጥረው በከተማው የፕላን
ስታንዳርደድ መሰረት የቤት መሰሪያ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል፤
9. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (7) እና (8) የተደነገገው ቢኖርም በውርስ
የባለይዞታነት መብታቸውን አረጋግጠው የሚቀርቡ አመልካቾች፣ ምንም
እንኳ ገጠር ላይ የመኖሪያ ቦታበ /ቤት/ ቢኖራቸውም በከተማው ውስጥ
የመኖሪያ ቦታ ከሌላቸው በአባወራ/በእማወራ ባለ ይዞታዎች የቦታ መጠን
ልክ ወደ ከተማ ከተካለለው ወይም ለልማት ከተወሰደው መሬት ውስጥ
የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲያገኙ ይደረጋል፤
10. በተሻሻለው የክልሉ ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ
ቁጥር 252/2009 ዓ.ም አንቀፅ 10 ንዑስ አንቀፅ /4/ ስር እድሜያቸው 18
ዓመት ያልሞላቸዉ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት የሚተዳደሩበት መሬት
በሞግዚቶቻቸው ወይም በወኪሎቻቸው አማካኝነት ሊያገኙ እንደሚችሉ
አስቀድሞ የተደነገገ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ፣ ተሰጥቷቸው የነበረው
ይኸው የመሬት ይዞታ በልማት ምክንያት ተወስዶ ለልማት እንዲውል
የተደረገ እንደሆነ፣ ተገቢውን ካሳ የማግኘት መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ
በአባወራ/በእማወራ ባለ ይዞታዎች የቦታ መጠን ልክ አንድ የመኖሪያ ቤት
መስሪያ ቦታ ብቻ ይሰጣቸዋል፤ ሆኖም ግን እድሜያቸው 18 ዓመት
የሞላቸው ወራሾች የውርስ መሬቱን በጋራ የሚጠቀሙበት ከሆኖነና
የመሬቱ መጠን በቂ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ በከተማው ፕላን ስታንዳርድ
መሰረት ለእያንዳንዳቸው የቤት መስሪያ ቦታ ይሰጣቸዋል፡፡ ነገር ግን

48
መሬቱ በቂ ሆኖ ካልተገኘ አንድ የአባዎራ ወይም የእማወራ የቦታ ድርሻ
ይሰጣቸዋል፤
11. በየትኛውም የከተማ ፕላን ወሰን የሚኖሩ የመሬት
ባለይዞታዎች፣የመኖሪያ ይዞታቸው በከተማው የፕላን ምደባ የንግድ
አገልግሎት ሆኖ ከተገኘና በዚሁ በግል ይዞታቸው ላይ የማልማት ፍላጎትና
አቅም ካላቸው፣ የከተማውን ስታንዳርድ የሚያሟሉ ከሆነ እና በከተማው
ፕላን መሰረት ደረጃውን የጠበቀ የፕሮጀክት ሃሳብ አቅርበው በዚሁ
መሰረት የውል ግዴታ ለመግባት እስከተስማሙ ድረስ፣ በከተማው የፕላን
ምድብ የቦታ ስታንዳርድ መጠን የመሬት ባለይዞታዎች በተናጠል
በስማቸው አንድ የንግድ ቦታ ብቻ ሊከበርላቸው እና ቅድሚያ ተሰጥቷቸው
ሊስተናገዱ ይገባል፤ ይዞታቸውም በካርታ ተደግፎና ተረጋግጦ
ይሰጣቸዋል፤
12. በማንኛውም ከተማ የፕላን ወሰን በተጠቃለለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ
በሚገኝ የግል ይዞታው ላይ የመኖሪያ ቤት ወይም የንግድ ድርጅት
ለመገንባት የተፈቀደለት ማንኛውም ባለይዞታ፣ በከተማው በኩል የይዞታ
ማረጋገጫ ካርታና የምስክር ወረቀት የተሰጠው እንደሆነ በምስክር ወረቀቱ
ላይ የተመለከተው ይኸው የቦታ መጠን በገጠር የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ
ደብተሩ ላይ ከሰፈረው ጠቅላላ ይዞታው ላይ ተቀናሽ ተደርጎ፣ ደበተሩ
ላይና ባህር መዘገብ ላይ የሰፈረው የቀድሞው መረጃ መስተካከል
ይኖርበታል፡፡
33.2. የመሬት ይዞታቸው ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚወሰድባቸውን ባለይዞታዎች
በዘላቂነት ስለማቋቋምና ስለመደገፍ
1. በቦታ አቅርቦት ረገድ ቅድሚያ ስለማግኘት፡

ሀ. ከመሬት ይዞታቸው የሚነሱ ባለይዞታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ


በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተደራጅተውና ሼድ ገንብተው
እንዲሰሩ ወይም በዘመናዊ የከተማ ግብርና ሥራ ላይ ለመሰማራት

49
እንዲችሉ ለዚሁ የሚያስፈልገው ቦታ በቅድሚያ በነጻ ምደባ
ይሰጣቸዋል፤
ለ. በተሻሻለው የክልሉ ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም
አዋጅ ቁጥር 252/2009 ዓ.ም አንቀፅ 18 ንዑስ አንቀጽ (1)
መሰረት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የመጠቀም መብቱን
እንደያዘ በከተማው የፕላን ምድብ በሚፈቅደው መሰረት በግል
ይዞታው ላይ ከግል ባለሃብቱ ጋር በጹህፍ ተዋውሎ ይዞታውን
በጋራ የማልማት መብት ይኖረዋል፤
ሐ. ከመሬቱ የተነሳ የገጠር መሬት ባለይዞታ በመሬት የመጠቀም
መብቱን በካፒታል መዋጮነት በመጠቀም ቅድሚያ የማልማት
መብት ይከበርለታል፤
መ. በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የሚነሱ ባለይዞታዎች
ተደራጅተው G+1 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የገበያ ማዕከላትን ወይም
ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ህንፃዎችን በጋራ ለመገንባትና
ለመጠቀም በሚፈልጉበት ጊዜ፣ በጥናት ላይ ተመስርተው
የሚያቀርቡትን የፕሮጀክት ሰነድ መነሻ በማድረግ የሚጠይቁት
የከተማ ቦታ በምደባ ይሰጣቸዋል፡፡
34. ከከተማ ውጭ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከመሬታቸው ለሚነሱ የገጠር
መሬት ባለይዞታዎች የሰፈራ ቦታ፣ ትክ የእርሻ እና የግጦሽ መሬት ስለ
መለየትና ስለ ማዘጋጀት
1. ከከተማ ውጭ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በልዩ የልማት ፕሮጀክት
ምክንያት ከመሬታቸው ለሚነሱ ባለይዞታዎች ትክ ሆኖ
የሚያገለግል የመልሶ ማቋቋሚያ ሰፈራ ቦታ በጥናት ተለይቶ
ተመጣጣኝነት ያለው የእርሻ፣ የግጦሽ እና የመኖሪያ ስፍራ
እንዲዘጋጅ ይደረጋል፤

50
2. የተመረጠው ትክ ወይም የሰፈራ ቦታ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ
ተዘጋጅቶለት እንዲጸድቅና ፕላኑን ተከትሎ አስፈላጊው መሰረተ
ልማት እንዲሟላለት ይደረጋል፡፡
35. ስለ ሌሎች ተጨማሪ ድጋፎች
1. በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የሚፈናቀሉ ህጋዊ ባለይዞታዎች ይኸው
መፈናቀል የሚያስከትልባቸው ጉዳት ከወዲሁ ታይቶ፡-

ሀ. እንደ የፍላጎታቸው በተናጠልም ሆነ በጋራ በመደራጀት በተለያዩ የስራ


ዘርፎች ተፈላጊው ፕሮጀክት ተቀርጾላቸው ወደ ስራ እንዲገቡ
ይደረጋል፤
ለ. በራሱ በክልሉ መንግሥትም ሆነ በአልሚ ባለሀብቶች አማካኝነት የስራ
እድል በቅድሚያ እንዲፈጠርላቸውና ለስራ የደረሱ የቤተሰብ
አባሎቻቸውም በአካባቢው በሚካሄደው ልማት ቅድሚያ ተጠቃሚዎች
እንዲሆኑ ተገቢው ክትትልና ድጋፍ ይደረግላቸዋል፤
ሐ. እንደ አስፈላጊነቱ የብድር አገልግሎት ወይም ሌላ አይነት ልዩ ድጋፍ
ይመቻችላቸዋል፤
መ.የሚያቀርቧቸው ምርቶች በገበያ ረገድ ተወዳዳሪዎች እንዲሆኑ
በስልጠናና በግብይት እሴት ሰንሰለት ትስስር ፈጠራ ረገድ ተገቢው
ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
2. በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የሚነሱ ባለይዞታዎች ከክልሉ መንግስት
የልማት ድርጅቶች ጋር በመሻረክ ወይም የየራሳቸውን የንግድ ማህበራት
በማደራጀት በእርሻ ስራ ውጤቶች ግብይት፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ
ፕሮጀክቶችና በኢንዱስትሪ ተቋማት ግንባታ እንዲሳተፉ ተገቢው ማበረታቻ
ይደረግላቸዋል።
3. በከተማ የአስተዳደርና የፕላን ወሰን ወይም በገጠር በልማት ምክንያት
በቋሚነትም ይሁን በጊዚያዊነት ለሚነሱ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች
የማጨሻ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ምትክ ቦታ እንዲያገኙ የሚደረግ ሆኖ
ግንባታውን አጠናቀው እስኪገቡ ድረስ፡-

51
ሀ. በተሰጠው የግንባታ ፈቃድ መሰረት ቤቱን አጠናቀው እስኪገቡ ድረስ
በወቅታዊ የኪራይ ግምት ተሰልቶ የአንድ ዓመት የቤት ኪራይ ክፍያ
እንዲከፈላቸው ይደረጋል፤
ለ. በጊዜያዊነት ለሚነሱ ባለይዞታዎች ቤታቸውን ለቀው ወይም ከመኖሪያ
ቦታቸው ተነስተው ለሚቆዩበት ጊዜ በወቅታዊ የኪራይ ግምት ተሰልቶ
የቤት ኪራይ ክፍያ ይፈጸመላቸዋል፤ ነገር ግን የቤት ኪራይ ክፍያው
የሚከፈለው ወደ ቀድሞ የመኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው እስከሚገቡበት
ጊዜ ድረስ ላለው ተሰልቶ ይከፈላቸዋል፡፡

52
ክፍል ስድስት

ስለቅሬታ አቀራረብና ውሳኔ አሰጣጥ፣ መረጃ ስለመጠየቅን ስለመቀበል፣


ስለገማች ቡድን ተግባርና ኃላፊነት

36. ለሕዝብ ጥቅም መሬት የሚለቁ ባለይዞታዎች ቅሬታ አቀራረብና ውሳኔ


አሰጣጥ በሚከተለው መልኩ ተደንግጓል፡-
1. ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚለቀቅን የገጠር መሬት ይዞታ ወይም በመሬት
ላይ የተደረገን ቋሚ ማሻሻያ አስመልክቶ የሚቀርብ ማናቸውም አቤቱታ
መሬቱን ላስለቀቀው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም ውሳኔው
በተሰጠ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት፤
2. የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም ጉዳዩን አግባብ ካላቸው
የህግ ማዕቀፎችና ሰነዶች ጋር በማገናዘብ በ5 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለቅሬታ
አቅራቢ ወገኖች የጽሁፍ ውሳኔ እንዲደርሳቸው ያደርጋል፤
3. በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም ምላሽ ያላገኙና ለህዝብ
ጥቅም ሲባል በሚሰጥ የመሬት ማስለቀቅ ውሳኔ፣ በንብረት ግምታ፣ የካሳ
መጠንና አከፋፈል ውሳኔ ላይ ቅር የተሰኘ የመሬት ባለይዞታ
ቅሬታ/አቤቱታ የሚቀርበው በከተማ ወይም በወረዳ አስተዳደሩ ለተቋቋመው
የካሣ ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ይሆናል፤

4. ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የይዞታ መሬቱን የለቀቀ ማናቸውም ባለይዞታ


በመሬት ማስለቀቅ ሂደቱና አስተዳደራዊ ውሳኔው ቅር ከተሰኘ ፣ እንዲለቀቅ
ትእዛዝ የተሰጠበትን መሬት ለወረዳው ወይም ከተማ አስተዳደር ማስረከቡን
የሚያረጋግጥ ሰነድና ሌሎች ይግባኙ የቀረበበትን ምክኒያት የሚገልጹ
መረጃዎች ኮፒ በማያያዝ በወረዳው ወይም በከተማ አስተዳዳሩ ለተቋቋመው
የካሳ ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ መሬቱን እንዲለቅ ትዕዛዝ ከተላለፈበት ወይም
ውሳኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ባሉ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ
ይችላል፤

53
5. ቅሬታ አቅራቢው ቅሬታ የቀረበበትን ማሳ፣ የቅሬታው መነሻ ምንጭ፣
ይዞታው የሚገኝበት ቀበሌ፣ ን/ቀበሌና ጎጥ የሚገልጹ መረጃዎች ከቅሬታ
ማመልከቻው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፤
6. ባለይዞታው የካሣ ክፍያውን ከተቀበለ በኋላ በካሳው መጠንም ይሁን
በንብረት አገማመቱ ላይ ቅሬታ ማቅረብ አይችልም፡፡
7. በንብረት ገማች ቡድን/ባለሙያዎች በኩል በተወሰነው የካሳ መጠን ወይም
በካሳው አከፋፋል ላይ ቅር በመሰኘቱ አቤቱታና ይግባኝ በማቅረቡ ለህዝብ
አገልግሎት መለቀቅ የሚገባው መሬት ርክክብ እንዲታገድ ወይም እንዲዘገይ
አያደርገውም፡፡ በመሆኑም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) መሠረት ይግባኝ
የሚያቀርብ የመሬት ይዞታ ማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ባለይዞታ ይግባኙ
ሊታይለት የሚችለው እንዲለቀቅ ትዕዛዝ የተሰጠበትን መሬት ለወረዳው
ወይም ለከተማ መሬቱን ማስረከቡን የሚያረጋግጥ ሰነድ ከይግባኝ አቤቱታው
ጋር አያይዞ ካቀረበ ብቻ ይሆናል፤
8. የካሳ ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴው የቀረበውን የአቤቱታና ቅሬታ ማመልከቻ
መሰረት በማድረግ አግባብ ያላቸውን ሰነዶች በመመርመር፣ ጉዳዩ
የሚለከታቸውን አካላት በማነጋገር እና ስራ ላይ ከዋሉ የህግ ማዕቀፎች ጋር
በማገናዘብ አቤቱታው በደረሰው በ7 ቀናት ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን ለአቤቱታ
አቅራቢዎች ወይም ለተወካዮቻቸው፣ ለወረዳው ወይም ለከተማ አስተዳደር
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም በጽሁፍ ውሳኔ መስጠት
አለበት፤
9. ቅሬታ ያቀረበው ባለይዞታ ወይም ተከራካሪ ወገን በካሳ ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ
ውሳኔ ቅር ከተሰኘ ይግባኙን ውሳኔው በተሰጠው በ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለዞን
ከፍተኛ ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡ በከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ያልረካ
አስከ ሰበር ሰሚ ማቅረብ ይችላል፤
10. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (9) የተመለከተው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ
አመልካቹ ይግባኝ ሲጠይቅ የውሳኔውን ግልባጭ አዘጋጅቶ ለመስጠት
የሚወስደውን ጊዜ አይጨምርም፤

54
37. መረጃ ስለመጠየቅና ስለመቀበል
1. በዚህ መመሪያ መሠረት የንብረት ገማች ወይም የካሳ ቅሬታ አጣሪ
ኮሚቴዎች ለሚያከናውኗቸው ተግባራት አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች
አግባብ ካላቸው የፌዴራል፣ የክልል፣ የወረዳ፣ የከተማ፣ የቀበሌ ወይም ሌሎች
አካላት የመጠየቅና የማግኘት መብት አላቸው፤
2. በዚህ አንቀጽ መሰረት ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም አካል የተጠየቁትን
መረጃዎች የመስጠት ግዴታ አለበት፤
3. የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም ለካሳ ግመታ የሚጠይቃቸው
የምርታማነትና የወቅቱ የገቢያ ዋጋ መረጃዎች አለመኖራቸው ሲረጋገጥ
ቡድኑ የግል የአሰራር ስልትና ዕውቀት በመጠቀምና ቅኝታዊ ጥናት
በማካሄድ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ያደራጃል፤ ጥቅም ላይ እንዲውል
ያደርጋል፤

38. ስለንብረት ገማች የባለሙያዎች ቡድን ተግባርና ኃላፊነት


1. የንብረት ገማች ባለሙያዎች ቡድን በዚህ መመሪያ መሠረት የሚከተሉት
ተግባራትና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-
1.1. የካሳ ግመታ ዓላማውን ለባለይዞታዎቹ በግልጽ ያስረዳሉ፣ ያብራራሉ፡
1.2. ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚለቀቀው መሬት ተወስኖ በደረሰበት በ15
ቀናት ውስጥ የመሬቱ ባለይዞታ፣ አጎራባች ባለይዞታዎች፣ የቀበሌው
መሬት አስተዳደር ተወካይ በተገኙበት ለልማት የተፈለገውን የይዞታ
መሬት፣ አጠቃቀምና ስፋት፣ የምርታማነት ደረጃ፣ የመሬት
ባለይዞታዎችን ማንነትና በመሬቱና በቋሚ ንብረቱ ላይ ያላቸውን
መብት፣ የባለይዞታዎች መሰረታዊ መረጃ፣ በመሬቱ ላይ ያፈሩትን
ንብረት ማለትም ቤት፤ አጥር፤ እርከን፤ የውሃ ጉድጓድ፤ ዛፎችና
ቋሚ ተክሎት ወ.ዘ.ተ… እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን
በአዋጅ፣ ደንቡና በዚህ መመሪያ ለማስፈፀም በሚዘጋጅ የቴክኒክ
ማስተገበሪያ ሰነድ መሰረት መረጃዎችን ለካሳ ትመና በሚያመች

55
መልኩ ይሰበስባል፣ ያጣራል፣ ይመረምራል፣ በህብረተሰቡ
ያስገመግማል፣ ያደራጃል፤
1.3. የመሬት ምዝገባና የመለካት ስራ እንዲሁም የንብረት ቆጠራ
በሚካሄድበት ጊዜ የመሬት ባለይዞታዎች፣ አጎራባች ባለይዞታዎች፣
የቀበሌ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ ተወካዮች እንዲገኙ
ጥሪ መደረጉን ወይም አስፈላጊው ጥሪ ደርሷቸው አለመገኘታቸውን
በማረጋገጥ የመሬት መለካት፣ መመዝገብና የንብረትና በመሬቱ ላይ
የተደረጉ ማሻሻያዎችን የቆጠራ ተግባር ያከናውናል፤
1.4. የመሬት ልኬታና በመሬት ላይ ያፈሩት ንብረት ቆጠራ
ባለይዞታዎችን ያሳተፈ መሆኑን ለማረጋገጥ በመሬት ምዝገባውና
በንብረት ቆጠራው ላይ ባለይዞታዎቹና የንብረት ገማች ቡድን
አባላት በመተማማኛ ቅጹ ላይ እንዲፈርሙበት ያደርጋል፤
1.5. በመሬት ልኬታና በንብረት ቆጠራ የተሰባሰቡ መረጃዎችን
ለህብረተሰቡ በማቅረብ የማስተቸትና ባለቤትነታቸውን የማረጋገጥ
ስራ ያከናውናል፤
1.6. ለንብረት ግመታ ስራ አስፈላጊ የሆኑ የቅርብ አምስት ዓመታት
የምርታማነት መረጃና ወቅታዊ የገቢያ ዋጋ እና ሌሎች ለትመና
ስራው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ከሚመለከታቸው የወረዳው ወይም
የከተማ መስሪያ ቤቶች ህጋዊ ጥያቄ በማቅረብ ተረጋግጠው ለገጠር
መሬት አስተዳርና አጠቃቀም ተቋም መሰጠት አለበት፤
እንዳስፈላጊነቱም ተጨማሪ መረጃ ሲያሰፈለግ የገማች ባለሙያዎች
ቡድን ጥናት እያካሄደ ያልተሟሉ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ያደራጃል
ይተነትናል፤
1.7. በመሬት ልኬታ፣ በንብረት ሃብት ቆጠራና ወቅታዊ የገበያ ዋጋ፣
ከሚመለከታቸው አካላት የተሰባሰቡ መረጃዎችን ጥቅም ላይ በማዋል
የካሳ ትመና ያካሄዳል፤

56
1.8. ካሳ ገማች ቡድኑ የሚያከናውናቸውን ማናቸውም ተግባራት
በሚመለከት የተሟላ ቃለጉባኤ ይይዛል፤ ቃለጉባኤዎችና ሌሎች
መረጃዎች ከካሳ ሰነዱ ጋር አብረው ተሰነደው ወይም ተደራጅተው
እንዲያዙ የደርጋል፤
1.9. በካሳ ግመታ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና አቤቱታዎችን
ተቀብሎ እንደተገቢነቱ ወቅታዊ ምላሾችንና ማብራሪያዎችን
ይሠጣል፤
1.10. አግባብነት በሌላቸው የይዞታ ማረጋገጫ ሰነዶችና ሆነ ተብሎ
በተጭበረበረ ማስረጃ ባለይዞታዎችን ለመጥቀምም ሆነ ለመጉዳት
በሚካሄድ አሰራርና ትክክለኛ ባለይዞታውን በአግባቡ ባለመለየት
ምክንያት ካሳ እንዲከፈል አድርገው የተገኙ እንደሆነ ለተጎጅው
የሚገባውን ካሳ ከመሸፈን በተጨማሪ በተናጠልም ይሁን በቡድን
በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ፤

1.11. በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በግለሰቦች መካከል በሚደረግ ክርክርም

ይሁን በግለሰብ ደረጃ የሚቀርብ የካሳ ይገመትልኝ ጥያቄ


በተዋረድ በሚገኜው የገጠር መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም
ተቋም ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
39. የወረዳ ወይም የከተማ አስተዳደር ተግባርና ኃላፊነት
1. ለህዝብ ጥቅም በሚለቀቀው መሬት ላይ በሚካሄደው የንብረት ግምት
መሠረት ተገቢው የካሣ መጠን እንዲከፈል ወይም ትክ መሬት እንዲሰጥ
የመወሰን ስልጣን የወረዳው ወይም የከተማ አስተዳደር ይሆናል፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ
የወረዳው ወይም የከተማው አስተዳደር የሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና
ኃላፊነቶችን ይወጣል፡፡
2.1. ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚለቀቀው መሬት የሚነሳውና የሚገመተው
ንብረት ከገማች ባለሙያዎች አቅም በላይ የተለዬ እውቀትና ልምድ
የሚጠይቅ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ በተዋረድ ባለው የገጠር መሬት

57
አስተዳዳርና አጠቃቀም ተቋም በኩል ጥያቄው ሲቀረብ ንብረቱን
ለመገመት የሚችሉ ልዩ ሙያና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች
እንዲካተቱ ያደርጋል፤
2.2. የመሬት ማስለቀቅ እና ግመታ ስራው የሚካሄድበትን ጊዜና ሁኔታ
ይወስናል፤
2.3. የመሬት ምዝገባና የመለካት ስራ እንዲሁም የንብረት ቆጠራ
በሚካሄድበት ወቅት የመሬት ባለይዞታዎች፣ አጎራባች ባለይዞታዎች፣
የቀበሌ አስተዳደርና የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተወካዮች
እንዲገኙ ትዕዛዝ ይሰጣል ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
2.4. ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የይዞታ መሬታቸውን ለለቀቁ ባለይዞታዎች
ፀድቆ የተላከው የካሳ ክፍያ ለትክክለኛ ባለይዞታዎች ወይም
የመሬቱ ተጠቃሚዎች መድረሱን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤
2.5. ካሳ የተከፈለበትን መሬት ለልማት መለቀቁንና መተላለፉን
ያረጋግጣል፤ መሬቱ ለመሬት ጠያቂው ካልተላለፈ የማስተካከያ
ዕርምጃ ይወስዳል፤
2.6. የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች መሬት የሚለቁ
ባለይዞታዎቹን ለዘለቄታው ማቋቋም የሚያስችሉ አማራጮች
እንዲያቀርቡ ያደርጋል፤ መፈጸማቸውንም ይከታታላል፤
ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊውን ምክርና ድጋፍ መሰጠቱን ያረጋግጣል፤
2.7. በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የተነሱ ባለይዞታዎችን በዘላቂነት
መልሶ ለማቋቋም ኃላፊነታቸውን የማይወጡትን የመንግሰት የስራ
ኃላፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
3. ከመሬት ማስለቀቅ፣ ካሳ ግመታና ክፍያ ጋር በተያያዘ ለሚቀረቡ
ቅሬታዎችና አቤቱታዎች በወረዳው ወይም በከተማ አስተዳደሩ 3 አባላት
ያሉት የካሳ ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ይቋቋማል፡፡ የካሳ አጣሪ ኮሚቴው በመሬት
ማስለቀቅና ካሳ ክፍያ የሚቀረቡ ቅሬታዎችን በህጉ መሰረት በማጣራት

58
የውሳኔ አስተያየት ሲያቀርብ መርምሮ ይወሰናል፤ ለቅሬታ አቅራቢው
በፁሁፍ ምላሽ ይሰጣል፡፡
40. ስለ መሬት አቅርቦት ጠያቂ አካላት

ማንኛውም የልማት አስፈፃሚ መስሪያ ቤት ባቀረበው የመሬት ይለቀቅልኝ ጥያቄ


መሰረት፡-
1. በሚለቀቁ የይዞታ መሬቶች ላይ ለሚከናወኑና ከንብረት ግመታም ሆነ ከካሣ
አከፋፈል ጋር የተያያዙ ተግባራት እውን የሆኑ ዘንድ አስፈላጊው
ሎጅስቲክስ እንዲሟላ ያደርጋል፤
2. እንደ ልማቱ ዓይነት፣ መሬት ጠያቂው አካል የካሣ ክፍያና የዘላቂ መልሶ
ማቋቋም የድርጊት መረሃ ግብር እንዲቀረፅና በዚሁ መሰረት ተግባራዊ
እንዲደረግ ሰነድ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤ በተዘጋጀው የድረጊት መርሃ ግብር
መሰረት የልማት ተነሽዎችን የዘላቂ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንዲያገኙ
የማድረግ ግዴታ ይኖርበታል፤
3. የሚፈለገውን የይዞታ መሬት በትክክል የሚያመላክት የፕሮጀክት ዲዛይን
በማዘጋጀት ለገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም በወቅቱ
መድረሱን የማረጋገጥ፣ ማናቸውም የፕሮጀክት ዲዛይን ለውጥ በሚደረግበት
ወቅት በተቻለ ፍጥነት ለውጡን የማሳወቅ፣ ከለውጡ ጋር በተያያዘ አስቀድሞ
የተከፈለ የካሳ ክፍያ ስለመኖሩ የማጣራት፣ የቅርብ ክትትል እንዲካሄድ
ያደርጋል፤
4. የካሣ ክፍያውን ያካሂድለት ዘንድ ለየትኛውም አካል ህጋዊ ውክልና ሊሰጥ
ይችላል፤ ስለአከፋፈሉም የራሱን ውስጣዊ የአሰራር መመሪያ ያዘጋጃል፤
5. የክፍያ ትዕዛዝ የተሰጠባቸውን የካሳ ሰነዶች በግልፅ ማስታወቂያ
ለባለይዞታዎቹ ያሳውቃል፡፡ እንደ መሬቱ አስፈላጊነትና እንደ ውሳኔዎቹ
አመጣጥ ቅደም ተከተል ለባለይዞታዎቹ አግባብ ባለው የአከፋፈል ስልት
ክፍያው እንዲፈፀም ያደርጋል፤
6. በባለይዞታዎች ስም የባንክ ሂሣብ እንዲከፈትና ክፍያው በቀጥታ ወደ
ሂሣባቸው እንዲተላለፍላቸው አበክሮ ይሰራል፤

59
7. የክፍያ አፈፃፀሙን በተመለከተ ለወረዳው ወይም ለከተማ አስተዳደርና
ለሚመለከተው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ተቋም ወቅታዊ
መረጃዎችን ይሰጣል፤

8. ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ ከባለይዞታዎች ለሚቀርቡ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች


ተገቢ ምላሾችንና ማብራሪያዎችን ይሰጣል፤ ግልጽነት የተላበሰ አሰራር
እንዲሰፍን ያደርጋል፤
9. ለልማት ተነሽዎች የዘላቂ መልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ በገንዘብ፣ በቦታ
አቅርቦት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታና ሌሎች መሰል ድጋፎች የማከናወን
ኃለፊነትና ግዴታ ይኖርበታል፡፡

41. የግምት ስራ ወጪዎችን በተመለከተ


1. ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚለቀቅ መሬት ላይ ለሰፈረ ንብረት ስለሚከፈል ካሳ፣
በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው ደንብ ደንብ ቁጥር 135/1999 መሰረት
ለሚሠየመው የንብረት ገማች ባለሙያ/ ቡድንና እንዳሰፈላጊነቱም ለካሳ
ቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ የሚከፈለውን አበል ጨምሮ በዚህ መመሪያ መሠረት
ንብረት ለመገመት አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎች እንደ አግባብነቱ በወረዳው
አማካኝነት የሚሸፈን ይሆናል፤
2. መሬቱ የሚለቀቀው በአስፈጻሚ መሥሪያ ቤት ጥያቄና በፕሮጀክቶች
አነሳሽነት ከሆነ ደግሞ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተጠቀሰው ወጪ
በሚመለከተው አስፈፃሚ መስሪያ ቤት ወይም ፕሮጀክት አማካኝነት
የሚሸፈን ይሆናል፡፡

60
ክፍል ስባት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
42. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ
በዚህ መመሪያ የተሸፈኑና ይህ መመሪያ ከመጽናቱ በፊት ተጀምረው ያልተቋጩ
ጉዳዮች በወቅቱ በነበሩት ህግጋት፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት
መስተናገዳቸውን ቀጥለው እልባት ያገኛሉ።

43. የተሻሩና ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጎች

1. ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካሣ የሚከፈልበትን


ሁኔታዎች ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 5/2003 በዚህ መመሪያ
ተሽሯል፤
2. ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬታቸውን የሚለቁ የገጠር ባለይዞታዎችን መልሶ
ለማቋቋም እና ይዞታቸውን ለማስተዳደር የወጣ ክልል መስተዳድር ምክር
ቤት መመሪያ ቁጥር 26 /2008 ዓ.ም ተሸሮ በዚህ መመሪያ ተተክቷል፤
3. ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሌላ መመሪያ ወይም ልማዳዊ
አሰራር በዚህ መመሪያ ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

44. የመተባበር ግዴታና የወንጀል ኃላፊነት


1. ማንኛውም ሰው ይህንን መመሪያ በስራ ላይ ለማዋል የመተባበር ግዴታ
አለበት፤
2. የዚህን መመሪያ ድንጋጌዎች የጣሰ ወይም አፈፃፀማቸውን ያሰናከለ ማንኛውም
ሰው አግባብ ባለው የወንጀል ህግ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
45. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ በአ.ብ.ክመ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ከፀደቀበት
ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
ባህር ዳር
ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ.ም
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ

61

You might also like