You are on page 1of 50

የታክስ አስተዳደር ህግ

መጋቢት 2014 ዓ.ም


ይዘት

o የህጉ አላማ

o በህጉ የሚመሩት የታክስ ህጐች፡

o በህጉ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች፣

o ግንኙነት ያላቸው ሰዎች

o ታክስ ከፋዮች

o ደረሰኞች

o የታክስ ማስታወቂያዎች

o የታክስ ስሌት/ውሳኔ

o ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል

o መረጃን ስለመሰብሰብና ስለማስፈፀም

o የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም


1. የህጉ አላማ
o የታክስ አስተዳደሩ ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተገማችነት ያለው እንዲሆን

ማድረግ፤
o የአገር ውስጥ ታክሶች ሁሉ የሚመሩበት ራሱን የቻለ አንድ የታክስ አስተዳደር ህግ

እንዲኖር ማድረግ፤
o በታክስ ሕጐች አተረጓጐም ረገድ በታክስ አስተዳደሩ ውስጥ በሚፈጠረው ልዩነት

ምክንያት ታክስ ከፋዩ ሲያጋጥመው የነበረውን እንግልት ለማስቀረት የሚያስችል


ወጥነት ያለው የአተረጓጐም ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ፤
o ተደራሽነት ያለው፣ በሚገባ የተደራጀ እና የተቀላጠፈ ውሳኔ መስጠት የሚያስችል

የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት ለመዘርጋት


2. በህጉ የሚመሩት የታክስ ህጐች
o የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ፣

o የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ፣

o የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ፣

o የቴምብር ቀረጥ አዋጅ፣

o የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣

o የጉምሩክን ሕግ ሳይጨምር ባለሥልጣኑ ታክሱን፣ ቀረጡን ወይም ክፍያውን

የማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠው እስከሆነ ድረስ ማንኛውም ይህንን ታክስ፣ ቀረጥ፣

ወይም ክፍያ የሚጥል ሌላ ሕግ፣

o ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት አዋጆች መሠረት የሚወጣ ማንኛውም ደንብ ወይም

መመሪያ ናቸው፡፡
3. በህጉ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች፣

o ጠቅላላ (አንቀጽ 2 - 4)

 ትርጓሜ

 ትክክለኛ የገበያ ዋጋ

 ግንኙነት ያላቸው ሰዎች

o የታክስ ህጐችን ስለማስተዳደር (አንቀጽ 5 - 8)

 የባለሥልጣኑ ኃላፊነት

 የገቢዎች ሚኒስቴር፣
 የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣
 የድሬዳዋ ገቢዎች ቢሮ፤
 የታክስ ሠራተኞች ግዴታዎችና ኃላፊነቶች
በህጉ የተካተቱ …የቀጠለ
 የመተባበር ግዴታ

 የታክስ መረጃ በምስጢር የሚያዝ ስለመሆኑ

o ታክስ ከፋዮች (አንቀጽ 9 - 16)

 ስለምዝገባና ስረዛ (አንቀጽ 9 - 11)

 ስለታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (አንቀጽ 12 - 15)

 የታክስ እንደራሴዎች (አንቀጽ 16)

o ስለሠነዶች (አንቀጽ 17 - 20)

o የታክስ ማስታወቂያዎች (አንቀጽ 21 - 24)


በህጉ የተካተቱ …የቀጠለ

o የታክስ ስሌቶች/ውሳኔዎች (አንቀጽ 25 - 29)

o ታክስና ሌሎች ክፍያዎችን ስለመሰብሰብና ማስከፈል (አንቀጽ 30 - 48)

 ታክስንና ሌሎች ክፍያዎችን ስለመክፈል (አንቀጽ 30 - 36)

 ለዘገየ ክፍያ ስለሚከፈል ወለድ (አንቀጽ 37)

 ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል(አንቀጽ 38 - 48)

o ማካካሻ፣ተመላሽ እና ከታክስ ዕዳ ነጻ ስለመሆን (አንቀጽ 49 - 51)

o ከታክስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር አለመግባባት (አንቀጽ 52 - 60)

o መረጃን ስለመሰብሰብና ስለማስፈፀም (አንቀጽ 61 - 67)


በህጉ የተካተቱ …የቀጠለ

o የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም (አንቀጽ 68 - 76)

 በሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም (አንቀጽ 68 - 70)

 በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም (አንቀጽ 71 - 75)

 የሚኒስቴሩ ሌሎች አስተያየቶች (አንቀጽ 76)

o ስለግንኙነቶች፣ ቅጾችና ማስታወቂያዎች (አንቀጽ 77 - 85)

o ስለይግባኝ ኮሚሽን (አንቀጽ 86 - 94)

o ለታክስ ወኪሎች ፈቃድ ስለመስጠት (አንቀጽ 95 - 99)


በህጉ የተካተቱ …የቀጠለ

o ስለ አስተዳደራዊ ጉዳዮች፣የወንጀል ቅጣቶች እና ሽልማቶች (አንቀጽ 100 - 135)

 አስተዳደራዊ ቅጣቶች (አንቀጽ 101 - 115)


 የታክስ ወንጀሎች (አንቀጽ 116 - 133)
 ሽልማቶች (አንቀጽ 134 - 135)
o ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች (አንቀጽ 136 - 139)
4. ግንኙነት ያላቸው ሰዎች

o ለታክስ ሕጐች አፈፃፀም ሁለት ሰዎች ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ናቸው

የሚባለው ከሁለቱ አንዱ ሰው በሌላኛው ሰው ትዕዛዝ፣ጥያቄ፣ አስተያየት


ወይም ፍላጎት መሠረት ይንቀሳቀሳል ተብሎ ሲገመት፤
o ሁለቱም ሰዎች በሌላ ሦስተኛ ወገን ትዕዛዝ፣ ጥያቄ፣ሃሣብ ወይም ፍላጎት

መሠረት ይንቀሳቀሳሉ ተብሎ ሲታመን ፤


o በተጨማሪም የሚከተሉት ሰዎች ግንኙነት ያላቸው ሰዎች እንደሆኑ

ይቆጠራል፡
 ባለሥልጣኑ ከሁለቱ አንዱ በሌላኛው ትዕዛዝ፣ ጥያቄ፣ አስተያየት ወይም
ፍላጎት መሠረት አይንቀሳቀስም ብሎ ካላመነ በስተቀር፣ አንድ ግለሰብና
የዚህ ግለሰብ ዘመድ፤
ግንኙነት ያላቸው ሰዎች …የቀጠለ

 አንድ ድርጅት ወይም የዚህ ድርጅት አባል በራሱ ወይም ግንኙነት ካላቸው ሰዎች
ጋር በመሆን በቀጥታ ወይም በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑና በተሳሰሩ
ድርጅቶች አማካይነት የድርጅቱን ሃያ አምስት በመቶ (25%) ወይም ከዚያ በላይ
የመምረጥ፣ የትርፍ ድርሻ ወይም የካፒታል ድርሻ መብት የሚቆጣጠር ሲሆን
ድርጅቱና የድርጅቱ አባል፤
 ሁለት ድርጅቶች ግንኙነት ያላቸው ናቸው የሚባሉት አንድ ሰው ብቻውን ወይም
ግንኙነት ካለው ሰው ጋር በመሆን የሁለቱን ድርጅቶች የትርፍ ድርሻ ወይም
ካፒታል በቀጥታ ወይም በሌሎች በተሳሰሩ ድርጅቶች አማካይነት 25 %( ሃያ
አምስት በመቶ) ወይም ከዚያ በላይ የሆነ የመምረጥ መብት፣ የተቆጣጠረ እንደሆነ

ግንኙነት ያላቸው ሰዎች …የቀጠለ

o የአንድ ግለሰብ ዘመዶች ናቸው የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፤

 የትዳር ጓደኛ፤

 የአንድ ግለሰብ የትዳር ጓደኛ የሚባሉት፤

 ግለሰቡ/ሰቧ በህጋዊ መንገድ ያገባው/ችው፣

 ጋብቻ ሳይኖር ከግለሰቡ/ቧ ጋር እንደባልና ሚስት አብሮ/ራ የሚኖር/ የምትኖር፤

 ቅድመ አያት፣ አያት፣ ወደታች የሚቆጠር ዘመድ፣ ወንድም፣ እህት፣ አጎት፣ አክስት፣

የወንድም ልጅ፣ የእህት ልጅ፣ የእንጀራ እናት፣ የእንጀራ አባት፣ የጉዲፈቻ ልጅ እና

የእነዚህ ግለሰቦች ባል ወይም ሚስት፤

 የጉዲፈቻ ልጅ ወላጅ፣ ወይም የእርሱ/ሷ ባል ወይም ሚስት፤ አንድ የጉዲፈቻ ልጅ

ከጉዲፈቻ አድራጊዎች የአንደኛ ደረጃ ዘመዶች ጋር ዝምድና እንዳለው ይቆጠራል፤


5. ታክስ ከፋዮች (አንቀጽ 9 - 16)
o ታክስ ከፋዮችን ስለመመዝገብ

 በታክስ ሕግ መሠረት ታክስ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ሰው በባለሥልጣኑ ዘንድ


ለመመዝገብ ማመልከት አለበት፤
 ይህ ድንጋጌ፡-

 በገቢ ግብር በኢትዬጲያ ነዋሪ ያልሆነ ሰው የትርፍ ድርሻ፣ ሮያሊቲ፣ ወለድ፣

የስራ አመራር ክፍያ ፣ የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ ወይም የመድን አረቦን


ከኢትዬጲያ ውስጥ ያገኘን ሰው እና በኢትዬጲያ ነዋሪ ያልሆኑ የመዝናኛ
አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፤
 በሠንጠረዠ “መ” መሰረት የሚጣለው የመጨረሻ ግብር የሚከፈልበት ገቢ

ብቻ ያለው ግለሰብ ላይም ተፈጻሚ አይሆንም፡፡


ታክስ ከፋዮች …የቀጠለ
o ለውጦችን ስለማሳወቅ

 ማንኛውም የተመዘገበ ሰው የሚከተሉትን በተመለከተ ለውጥ ሲከሰት ለውጡ

በተከሰተ በ21 ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት፤

 ስሙ፣ ቋሚ አድራሻው ወይም የፖስታ አድራሻው፣ የተቋቋመበት

መተዳደሪያ ደንብ ወይም ዋንኛ የሥራ እንቅስቃሴው ወይም

እንቅስቃሴዎቹ ከተለወጡ፤

 ከባለሥልጣኑ ጋር ግንኙነት የሚያደርግበት የባንክ አድራሻ፣ የኤሌክትሮኒክ

አድራሻ ከተለወጠ፤

 ባለሥልጣኑ በመመሪያ የሚወስናቸው ሌሎች ዝርዝሮች፣


ታክስ ከፋዮች …የቀጠለ
o የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር

 ታክስ ከፋዮችን ለመለየት እንዲቻል ባለሥልጣኑ ለታክስ ሕጐች ዓላማ ሲባል


ለተመዘገበ ሰው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር በሚል የሚታወቅ ቁጥር ይሰጣል፤
 ታክስ ከፋዩም የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን የታክስ ሕጎች በሚያዙት መሠረት
መጠቀም አለበት፤
 ለሁሉም የታክስ ሕጐች አንድ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የሚሰጥ ሲሆን
አንድ ታክስ ከፋይ በማንኛውም ጊዜ አንድ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ብቻ
ይኖረዋል፤
ታክስ ከፋዮች …የቀጠለ
 የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ የሚሰጥ የመንግሥት አካል ወይም ተቋም ታክስ
ከፋዩ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን ሳያቀርብ ፈቃድ መስጠት አይችልም፡፡
ታክስ ከፋዮች …የቀጠለ
o የታክስ እንደራሴ

 ታክስ ከፋዩን በመወከል በኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውንም ገንዘብ ለመቀበል ወይም ለመክፈል

ኃላፊነት ያለበት ግለሰብ ሲሆን የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

 የሽርክናን ማህበር በተመለከተ የሽርክና ማህበሩ ሸሪክ ወይም ሥራ አስኪያጅ፣

 ኩባንያን በተመለከተ የኩባንያው ዳይሬክተር፤

 ችሎታ የሌለውን ግለሰብ በተመለከተ ችሎታ የሌለውን ግለሰብ በመወከል ወይም ለዚህ
ግለሰብ ጥቅም ገቢ የሚቀበል ህጋዊ ወኪል፣

 የአንድ ታክስ ከፋይ ሀብት ተረካቢ በተመለከተ የታክስ ከፋዩ ባለአደራ፣

 አንድ የታክስ እንደራሴ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብንና ታክስ መክፈልንም ጨምሮ የታክስ

ሕግ በታክስ ከፋዩ ላይ የሚጥለውን ማንኛውም ግዴታ የመወጣት ኃላፊነት አለበት፡፡


ታክስ ከፋዮች …የቀጠለ
o በታክስ ሕግ በሌላ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር በታክስ እንደራሴ መከፈል የሚኖርበት

ታክስ በታክስ እንደራሴው ይዞታ ወይም ቁጥጥር ሥር ባለው ገንዘብ ወይም ሀብት
መጠን ከታክስ እንደራሴው መሰብሰብ አለበት፤
o ነገር ግን በታክስ እንደራሴው መከፈል የነበረበት ታክስ ሳይከፈል ሲቀር የታክስ

እንደራሴው ታክሱን ለመክፈል የግል ኃላፊነት የሚኖርበት፡-


 የተቀበለውን ወይም ሊቀበለው የሚችለውንና ታክስ የሚከፈልበትን ገንዘብ
ያጠፋ፣ ለሌላ ዓላማ ያዋለ ወይም ያስተላለፈ እንደሆነ፣
 የታክስ ከፋዩ ሀብት የሆኑ እና በታክስ እንደራሴው ይዞታ ሥር የነበሩ ወይም
ታክስ መከፈል ከነበረበት ጊዜ በኋላ በይዞታው ሥር የሆኑ እና ለታክሱ ክፍያ
ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ወይም ገንዘብ ያስተላለፈ ወይም በከፊል ለሌላ
የሰጠ እንደሆነ ነው፡፡
ታክስ ከፋዮች …የቀጠለ
o የታክስ እንደራሴው በታክስ ከፋዩ ላይ በታክስ ሕግ የተጣለውን ማንኛውንም ግዴታ

ሳይወጣ ቢቀር ታክስ ከፋዩ ካለበት ማንኛውም ግዴታ ነፃ ሊያደርገው አይችልም፡፡


6. ደረሰኞች
o የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ደረሰኞች ከማሳተሙ

በፊት የእነዚህን ደረሰኞች ዓይነትና ብዛት በባለሥልጣኑ ማስመዝገብ አለበት፤


o ማንኛውም የህትመት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው ደረሰኞችን ለማሳተም

ከታክስ ከፋዩ ጥያቄ ሲቀርብለት ደረሰኞቹን ከማተሙ በፊት የእነዚህ


ደረሰኞች ዓይነትና መጠን በባለሥልጣኑ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጥ
አለበት፤
o ማንኛውም የሂሣብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ
ለሚያከናውነው ግብይት ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
7. የታክስ ማስታወቂያዎች
o የታክስ ማስታወቂያዎችን ስለማቅረብ

 በታክስ ሕግ የታክስ ማስታወቂያ የማቅረብ ግዴታ የተጣለበት ሰው


ማስታወቂያውን በፀደቀው ቅጽ እና በዚህ አዋጅ መሰረት በወጣ ደንብ
በተመለከተው አካሃን ማቅረብ አለበት፤
 ባለሥልጣኑ በታክስ ከፋዩ በቀረበ የታክስ ማስታወቂያ አይገደድም፤ ባገኘው
ማንኛውም አስተማማኝ እና ሊረጋገጥ የሚችል መረጃ ላይ በመመሥረት ታክስ
ከፋዩ መክፈል ያለበትን የታክስ መጠን ሊወስን ይችላል፤
የታክስ ማስታወቂያዎች …የቀጠለ
o የታክስ ማስታወቂያዎች አስቀድሞ ስለማቅረብ
 ታክስ ከፋይ ሥራውን ያቋረጠ እንደሆነ

 ማንኛውም ታክስ ከፋይ ከኢትዮጵያ ሊወጣ ከሆነና የታክስ ከፋዩ


ከኢትዮጵያ መውጣት በጊዜያዊነት አለመሆኑ የሚገመት ከሆነ፣
 ባለስልጣኑ በማንኛውም የታክስ ጊዜ ታክስ ከፋዩ የታክስ ጊዜውን የታክስ
ማስታወቂያ ማቅረብ በሚገባው ጊዜ አያቀርብም ብሎ ማመን
የሚያስችል ምክንያት ሲኖረው
8. የታክስ ስሌት/ውሳኔ
o የራስ ታክስ ስሌት

 የራሱን ታክስ ስሌት የሚያዘጋጅ ታክስ ከፋይ ባቀረበው የታክስ ስሌት


ማስታወቂያው የገለፀው መጠን ዜሮን ጨምሮ ሊከፈል የሚገባውን የታክስ
መጠን ስሌት እንዳቀረበ ተደርጎ ይቆጠራል፤

 የታክስ ባለስልጣኑ ግብር ከፋዩ ባቀረበው የራስ ታክስ ስሌት ያልረካ እንደሆነ፣

የታክስ ስሌቱን ሊያሻሽል የሚችለው በአዋጁ አንቀጽ 28 የተቀመጡለት

ገደቦችን ጠብቆ ነው ፤

 የጊዜ ገደብ ተቀምጦዋል

 ባለስልጣኑ የራስ ታክስ ስሌት ቀርቦለት ሳለ በአንቀጽ 26 መሰረት የግምት

ታክስ ስሌት ሊያወጣ አይችልም


የታክስ ስሌት/ውሳኔ
o በግምት የሚከናወን የታክስ ስሌት

በግምት ላይ የተመሰረተ የታከስ ስሌት ታክስ ከፋይ የታክስ ማስታወቂያ በማቅረቢያ

ጊዜው ሳያቀርብ ሲቀር በታክስ ባለስልጣኑ የሚዘጋጅ የታክስ ስሌት ነው


 በግምት ላይ የተመሰረተ የታከስ ስሌት በማናቸውም ጊዜ ሊከናወን ይችላል

 የጊዜ ገደብ ተፈጻሚ የሚሆነው የታክስ ስሌትን ለማሻሻል ነው

o የስጋት ታክስ ስሌት

ባለሥልጣኑ የታክስ ማስታወቂያ አስቀድሞ የሚቀርብበት ወይም በፋይናንስ ተቋማት

የተቀመጠ ገንዘብ እና ንብረት ይዞ ማቆየት የሚጠበቅበት ሁኔታዎች ሲኖሩ የስጋት

ታክስ ስሌት ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡


የታክስ ስሌት/ውሳኔ …የቀጠለ
o የተሻሻለ የታክስ ስሌት
 የታክስ ስሌትን ሊያሻሻል የሚችለው የታክስ ባለስልጣኑ ብቻ ነው፡፡
 ታክስ ከፋይ የራስ ታክስ ስሌት አዘጋጅቶ ካቀረበ በኃላ፣ በታክስ ስሌቱ ላይ
ማሻሻያ ማድረግ አይችልም፡፡
 ታክስ ከፋዩ በታክስ ስሌቱ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ከፈለገ ለታክስ ባለስልጣኑ
በአንቀጽ 29 መሰረት ጥያቄ ማቅረብ አለበት
 በአንቀጽ 28 ላይ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ የራስ ታክስ ስሌትን ለማሻሻል
ለሚቀርብ ማመልከቻም ተፈጻሚ ይሆናል
የታክስ ስሌት/ውሳኔ …የቀጠለ

 የማጭበርበር ድርጊት ወይም በከፍተኛ ሁኔታ ወይም በማወቅ የተፈፀመ

የቸልተኝነት ድርጊት ሲኖር የታከስ ስሌቱን ለማሻሻል የተቀመጠ የጊዜ ገደብ

የለም፣

 ከዚህ ውጪ ባለ ሁኔታ ግን ቀጥሎ ከተመለከቱት ጊዜያት ጀምሮ ባለ 5 ዓመት ጊዜ

ውስጥ ሊያሻሻል ይችላል


 የራስ ታክስ ስሌት – የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ
 ሌሎች ስሌቶች – የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋይ ከደረሰበት ቀን
ጀምሮ
የታክስ ስሌት/ውሳኔ …የቀጠለ

 ባለሥልጣኑ ለታክስ ከፋዩ የሰጠውን የታክስ ስሌት ማሻሻያ ማስታወቂያ ከሚከተሉት

ሁኔታዎች ዘግይቶ በተፈጸመው ጊዜ እንደገና ሊያሻሽል ይችላል፡፡

 የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ከቀረበበት ቀን / በሌላ ሁኔታ የታክስ ስሌት

ማስታወቂያ ለታክስ ከፋይ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ 5 ዓመት

 የተሻሻለ የታክስ ማስታወቂያ ለታክስ ከፋይ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ 1 ዓመት


9. ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል
o የታክስ ስሌቶችን/ውሳኔዎችን ስለማስፈጸም

 ታክስ ከፋዩ በታክስ አስተዳደር አዋጅ አግባብነት ባላቸው አንቀጾች

በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ቅሬታ ወይም ይግባኝ ካላቀረበ ባለሥልጣኑ ለታክስ

ከፋዩ የሚሰጠው የታክስ ስሌት የቅሬታ/የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ካበቃበት

ቀን ጀምሮ የመጨረሻ እና ተፈጻሚነት ያለው ይሆናል፡፡

 የመጨረሻ በሆነ የታክስ ስሌት የሚፈለግበትን ታክስ ያልከፈለ ታክስ ከፋይ

ግዴታውን ያልተወጣ የታክስ ባለዕዳ ይሆናል፡፡


ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል …የቀጠለ

o በሀብት ላይ የሚቀርብ የቀደምትነት መብት

 ባንኮች ዋስትና የተቀበሉባቸው የገንዘብ ጥያቄዎችና የተቀጣሪዎች የደመወዝ ክፍያ

የቅድሚያ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ላልተከፈለ ታክስ ባለሥልጣኑ በታክስ ከፋዩ ሀብት

ላይ የቀደምትነት መብት ይኖረዋል፡፡

 ባንኮች የቀደምትነት መብት የሚኖራቸው ብድሩ ከመሰጠቱ በፊት ታክስ ከፋዩ የታክስ ዕዳ

የሌለበት መሆኑ በባለሥልጣኑ የተረጋገጠ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

 ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ በሚከፈል ታክስ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ፣ በተርን ኦቨር

ታክስ፣ በኤክሳይዝ ታክስ፣ እና ለሦስተኛ ወገን በሚሰጥ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ መሠረት

ሊከፈል በሚገባው ገንዘብ ላይ በማንኛውም ሁኔታ የቅድሚያ መብቱ የታክስ ባለስልጣኑ

ነው፡፡
ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል …የቀጠለ
o ሀብትን ስለመያዝ

የታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 40 የሚፈለግበትን ታክስ በመክፈያ ጊዜው ያልከፈለን


ታክስ ከፋይ ሀብት ይዞ ለታክስ ዕዳው እንዲያውል ለታክስ ባለስልጣኑ ስልጣን ይሰጣል፡፡

o በፋይናንስ ተቋማት የተቀመጠ ሀብት ይዞ ስለማቆየት

 ተፈፃሚ የሚሆነው ባለሥልጣኑ በበቂ ምክንያት ከታክስ ከፋዩ ላይ የሚፈለገው


ታክስ የሚሰበሰብ ስለመሆኑ ስጋት ሲኖረውና ታክሱ በአስቸኳይ መሰብሰብ ያለበት
ሲሆን ነው፡፡

 ባለሥልጣኑ አንድ የፋይናንስ ተቋም የሚከተሉትን እንዲፈጽም ትዕዛዝ ሊሰጥ


ይችላል፡፡

  የታክስ ከፋዩ ሂሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ እንዲያደርግ፣


ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል …የቀጠለ
 በፋይናንስ ተቋሙ ውስጥ ባለ በጥንቃቄ የሚያዙ ዕቃዎች ማስቀመጫ ሣጥን ውስጥ
የተቀመጠ ማንኛውም የታክስ ከፋዩ ጥሬ ገንዘብ፣ ውድ እቃ፣ የከበረ ጌጣጌጥ፣ ወይም ሌላ
ንብረት እንዳይንቀሳቀስ፣

 በጥንቃቄ በሚያዙ ዕቃዎች ማስቀመጫ ሣጥን ውስጥ ስለሚገኙ ሀብቶች ተገቢውን መረጃ
ወይም በሣጥኑ ውስጥ ያሉትን ሀብቶች ዝርዝር ለባለሥልጣኑ እንዲሰጥ፣

 ባለሥልጣኑ ለፋይናንስ ተቋሙ የዕግድ ትዕዛዝ በደረሰው በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ትዕዛዙ እንዲቀጥል
ለማድረግ የሚያስችል የፍርድ ቤት ፈቃድ ካላገኘ በስተቀር የሰጠው ትዕዛዝ ተፈጻሚነት ያቆማል ፡፡

 አንድ የገንዘብ ተቋም ያለምንም በቂ ምክንያት የተሰጠውን ትዕዛዝ ሣይፈፅም የቀረ እንደሆነ
በትዕዛዙ ለተመለከተው የገንዘብ መጠን በግሉ ኃላፊ ይሆናል፡፡
ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል …የቀጠለ
o የታክስ ዕዳን ከሦስተኛ ወገኖች ስለማስከፈል

የታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 43 ባለሥልጣኑ ለታክስ ከፋዩ ገንዘብ ለሚከፍል ሦስተኛ

ወገን በጽሑፍ በሚሰጠው ትዕዛዝ በትዕዛዙ የተመለከተውን ገንዘብ ለባለሥልጣኑ እንዲከፍል

ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚችልበትን ስርዓት ይደነግጋል


o ከሀገር መውጣትን ለመከልከል የሚሰጥ ትዕዛዝ

 ባለሥልጣኑ ታክስ ከፋዩ ወይም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም በአንድ ኩባንያ ወሳኝ ድምጽ

ያለው አባል ታክስ ሳይከፍል ከሀገር ሊወጣ ይችላል የሚል በቂ ምክንያት ሲኖረው ከአገር እንዳይወጣ

የሚከለክል ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡

 ከሀገር መውጣትን የሚከለክል ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚችለው በዋና ዳይሬክተሩ ወይም ዋና

ዳይሬክተሩ ሥልጣን በሰጠው የታክስ ኦፊሰር ብቻ ነው፡፡


ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል …የቀጠለ

 ባለሥልጣኑ በሚያቀርበው ማመልከቻ ፍርድ ቤት ካላራዘመው በስተቀር

የሚተላለፈው ከሀገር መውጣትን የሚከለክለው ትዕዛዝ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ

ከአስር ቀናት በኋላ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

o የንግድ ድርጅትን ለጊዜው ስለማሸግ

ታክስ ከፋይ በተደጋጋሚ በታክስ ሕግ መሠረት የሚፈለግበትን ሰነድ ሳይዝ ሲቀር ፣

ወይም ታክሱን በመክፍያ ጊዜው ሳይከፍል ሲቀር የንግድ ድርጅቱ የሚታሸግበትን

ስርዓት ያስቀምጣል
ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል …የቀጠለ
o ሀብት የተላለፈለት ግንኙነት ያለው ሰው

 አንድ ታክስ ከፋይ ከሚያካሂደው የንግድ ሥራ ጋር በተገናኘ ያልተከፈለ የታክስ ዕዳ

ያለበት እንደሆነ እና የንግዱን ሀብቶች በሙሉ ወይም በከፊል ግንኙነት ላለው ሰው

ያስተላለፈ እንደሆነ ያልተከፈለውን ዕዳ ሀብቱ የተላለፈለት ሰው የመክፈል ግዴታ

ይኖርበታል፡፡

 ባለሥልጣኑ የተላለፈውን የታክስ ዕዳ በሙሉ ወይም በከፊል ከሀብት አስተላላፊው

ላይ እንዳይጠይቅ አያግደውም፡፡
ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል …የቀጠለ
o በድርጅት ስለሚከፈል ታክስ

 ታክሱ ባልተከፈለበት ጊዜ ወይም ታክሱ ከመከፈሉ በፊት ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ


ውስጥ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የነበረ ማንኛውም ሰው ላልተከፈለው ታክስ ከድርጅቱ
ጋር የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡

 ይህ ድንጋጌ በስራ አስኪያጁ ላይ ተፈጻሚ የማይሆነው ፡-

 ድርጅቱ ታክሱን ሳይከፍል የቀረው ከሥራ አስኪያጁ ፈቃድ ወይም ዕውቀት ውጭ


የሆነ እንደሆነ፣ እና

 ሥራ አስኪያጁ ድርጅቱ ታክስ ላለመክፈል የሚያደርገውን ጥረት ለመከላከል


ተገቢውን ትጋት አሳይቶ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
ያልተከፈለን ታክስ ስለማስከፈል …የቀጠለ
o ከታክስ ማጭበርበር ወይም ስወራ ጋር የተያያዘ የታክስ ኃላፊነት

 ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው ታክስ ከፋይ ታክስን ማሳነስ ወይም መሰወር


የሚያስከትል የማጭበርበር ድርጊት ፈጽሞ ሲገኝ እና ኦዲተሩ ወይም የሂሳብ
ባለሙያው ፡ -

 ታክስ ከፋዩን የረዳ፣ ያበረታታ፣ የመከረ እንደሆነ፣

 በማንኛውም መንገድ እያወቀ ከታክስ ከፋዩ ጋር ከተባበረ ወይም የድርጊቱ አጋር ከሆነ

 ኦዲተሩ ወይም የሂሳብ ባለሙያው በታክስ ማጭበርበሩ ወይም በታክስ ስወራው


ምክንያት ለሚከሰተው የታክስ መቀነስ ከታክስ ከፋዩ ጋር በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት
ይኖርበታል፡፡
10. መረጃን ስለመሰብሰብና ስለማስፈፀም

o የታክስ ክሊራንስ

o ኦዲተሮች የደንበኞቻቸውን የኦዲት ሪፖርት ለደንበኞቻቸው ካቀረቡበት ቀን

ጀምሮ በሚቆጠር የ3 ወራት ጊዜ ውስጥ የኦዲት ሪፖርቶቹን ለባለሥልጣኑ

ማቅረብ አለባቸው፡፡

o ምንጩ ኢትዮጵያ የሆነ የአገልግሎት ውል (የቅጥር ውልን ሳይጨምር) በኢትዮጵያ

ነዋሪ ካልሆነ ሰው ጋር የሚገባ ማንኛውም ሰው ውሉን ከፈረመበት ወይም

መፈጸም ከጀመረበት ቀድሞ ከመጣው ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 30 ቀናት ውስጥ

መሠረት ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ አለበት፡፡


መረጃን ስለመሰብሰብና ስለማስፈፀም …የቀጠለ

o መረጃ ወይም ማስረጃ ለማግኘት ማስታወቂያ ስለመስጠት

 ማንኛውንም የታክስ ሕግ ለማስተዳደር ሲባል ባለሥልጣኑ ታክስ ከፋይ ቢሆንም ባይሆንም

ለማንኛውም ሰው የጽሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት፡-

 የራሱን ወይም የሌላ ማንኛውንም ሰው የታክስ ጉዳይ የሚመለከት በማስታወቂያው

የተገለፀውን መረጃና ማስረጃ እንዲሰጠው፣ ሰነዶችን እንዲያቀርብ፣ ሊጠይቅ ይችላል፡፡

 ይህ ጥያቄ፡-

 በኢሌክትሮኒክ መልክ የሚገኙትን ጨምሮ ማንኛውንም መረጃ መስጠትን ወይም

ሰነድ ማቅረብን በተመለከተ ልዩ መብት የሚሰጥ ወይም የህዝብ ጥቅምን

የሚመለከት ሌላ ሕግ፣ ወይም

 ሚስጥር የመጠበቅ ግዴታን የሚጥል ውል፣ ቢኖርም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡


መረጃን ስለመሰብሰብና ስለማስፈፀም …የቀጠለ

o የመግባትና የመበርበር ሥልጣን


 ማንኛውንም የታክስ ሕግ ለማስተዳደር ሲባል ባለሥልጣኑ በማንኛውም ጊዜና
ያለምንም ማስታወቂያ በሚከተሉት ቦታዎች ላይ የመገኘት ወይም
የሚከተሉትን የማግኘት ሙሉ እና ያለተገደበ መብት አለው፤
 በማንኛውም ግቢ ወይም ቦታ፣ ማንኛውንም ዕቃ ወይም ንብረት፤

 ማንኛውንም ሰነድ፤

 ማንኛውንም የመረጃ ማከማቻ፤


መረጃን ስለመሰብሰብና ስለማስፈፀም …የቀጠለ

 በኤሌክትሮኒክ መልክ የተያዘን ጨምሮ የማንኛውንም ሰነድ የተወሰነ ክፍል ወይም

ቅጂ ሊወስድ ይችላል፡፡

 የታክስ ከፋዩን የታክስ ግዴታ ለመወሰን ጠቃሚ ማስረጃ ይሆናል ብሎ የሚያምንበትን

ማንኛውንም ሰነድ ሊይዝና በማንኛውም የታክስ ሕግ መሠረት የታክስ ከፋዩን የታክስ


ግዴታ ለመወሰን ወይም ለማንኛውም የታክስ ክርክር እስካስፈለገ ጊዜ ድረስ ይዞ
ማቆየት ይችላል፡፡

 የታተመ መረጃ ወይም በመረጃ ማጠራቀሚያ መሳሪያ የተከማቸ መረጃ ካልተሰጠው

የመረጃውን ቅጅ ለመውሰድ አስፈላጊ ለሆነ ጊዜ መሳሪያውን ይዞ ማቆየት ይችላል፡፡


መረጃን ስለመሰብሰብና ስለማስፈፀም …የቀጠለ

 የመግባትና የመበርበር ሥልጣን ሊሰራበት የሚችለው ሚኒስትሩ ወይም በዚህ

ሥልጣን እንዲሠራ በሚኒስትሩ ግልጽ ውክልና የተሰጠው የታክስ ሠራተኛ ብቻ ነው፡፡

 ለተወሰደና ለተያዘ ማንኛውም ሰነድ ወይም የዳታ ማከመቻ መሳሪያ ሚኒስትሩ

ወይም በሚኒስትሩ የተወከለ የታክስ ሠራተኛ በፊርማው ማረጋገጫ መስጠት

አለበት፡፡
11. የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም
o የገንዘብ ሚኒስቴር በታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን የህግ ትርጉም ሊሰጥ

ይችላል፡፡
o የሚሰጡ ትርጉሞች በታክስ ባለስልጣኑና በሚኒስቴሩ ላይ አስገዳጅ ሲሆኑ

በታክስ ከፋዮች ላይ ግን አስገዳጅነት የላቸውም (አንቀፅ 68 እና 71) ፡፡


o የሚሰጡ ትርጉሞች በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ እና በሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ

ተፈፃሚ የሚሆኑ ትርጉሞች በሚል በሁለት ይከፈላሉ፡፡


o ለዚህ አዋጅ ወይም ለሌላ ሕግ አፈጻፀም ሲባል የሚኒስቴሩ ውሳኔ ተደርገው

አይወሰዱም፡፡
የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም …የቀጠለ
o ትርጉሞቹ ሚኒስቴሩ የሰጠውን አስተያየት የሚገልፁ ስለሆነ በትርጉሙ
ያልተስማማ ግብር ከፋይ ቅሬታ ሊያቀርብ ወይም ትርጉሙን አስመልክቶ በህግ
ሊከራከርበት ወይም ክስ ሊያቀርብ አይችልም፡፡
o በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም በግብር ከፋዩ ጥያቄ መሰረት
የሚሰጥ ነው፡፡
o በሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም ያለ ግብር ከፋይ ጥያቄ
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚሰጥ ትርጉም ነው፡፡
የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም …የቀጠለ
 በሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም፡-

 በሚኒስቴሩ ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ላይ የሚገለጽ ሲሆን የሚሰጠው ትርጉም ይዘት


በሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ መሆኑን የሚገልጽ ርዕስና መለያ ቁጥር
ሊኖረው ይገባል፤
 የሚሰጠው ትርጉም ተፈጻሚነት የሚጀምረው ትርጉሙ ላይ ከተመለከተው
ቀን ጀምሮ ሲሆን በትርጉሙ ላይ ምንም ቀን ካልተመለከተ በሚኒስቴሩ
ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡
 ሚኒስቴሩ የሰጠውን ትርጉም በሙሉ ወይም በከፊል ሊያነሳ ይችላል፡፡
የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም …የቀጠለ

 የትርጉሙ ተፈጻሚነት መቋረጥ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ወይም


በሚኒስቴሩ ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ላይ ከወጣበት ቀን ከሁለቱ በዘገየው ቀን
ይጀምራል፡፡
 የተነሳ ትርጉም ከመነሳቱ በፊት ለተጀመሩ ግብይቶች ተፈጻሚነቱ ሲቀጥል
ትርጉሙ ከተነሳ በኋላ ለተጀመሩ ግብይቶች ግን ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

 በሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ ከሚሆን ትርጉም ጋር የሚቃረን ሕግ

ከወጣ ወይም ሚኒስቴሩ የተለየ ትርጉም ከሰጠ ነባሩ ትርጉም እንደተነሳ


ይቆጠራል፤
የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም …የቀጠለ
o በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም

 ታክስ ከፋይ በፈጸመው ወይም ሊፈጽም ባሰበው ግብይት ላይ የአንድን ታክስ

ሕግ ተፈጻሚነት በተመለከተ የሚኒስቴሩ አቋም ምን እንደሆነ የሚገልጽ


ትርጉም እንዲሰጠው ለሚኒስቴሩ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል፡፡

 ሚኒስቴሩ ማመልከቻ በደረሰው በ፷ (በስልሳ) ቀናት ውስጥ ለቀረበለት ጥያቄ

ጉዳዩን የሚመለከት ትርጉም መስጠት አለበት፡፡

 በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም ትርጉሙ በተሰጠበት ጊዜ

ጸንቶ ካለ በሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ ከሚሆን ትርጉም ጋር የሚቃረን


ከሆነ በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ እንዲሆን የተሰጠ ትርጉም ተፈጻሚነት
ይኖረዋል፡፡
የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም …የቀጠለ
 ሚኒስቴሩ በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም እንዲሰጥ

በታክስ ከፋዩ የቀረበን ማመልከቻ ላይቀበለው ይችላል

 ሚኒስቴሩ ማመልከቻውን የማይቀበልባቸው ምክንያቶች በአዋጁ አንቀጽ

72 ተዘርዝረዋል፡፡

 ሚኒስቴሩ በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም እንዲሰጥ

የቀረበን ማመልከቻ ውድቅ ለማድረግ መወሰኑን ለታክስ ከፋዩ በጽሑፍ


ማሳወቅ አለበት፡
የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም …የቀጠለ

 ሚኒስቴሩ በቂ ምክንያት ሲኖር በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን

ትርጉም ለሚመለከተው ታክስ ከፋይ የጽሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት በሙሉ

ወይም በከፊል ሊያነሳ ይችላል፡፡

 ትርጉሙ በማስታወ ቂያው ላይ ከተገለጸው ቀን ጀምሮ እንደተነሳ ይቆጠራል፡፡

 በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ ከሚሆን ትርጉም ጋር የሚቃረን ሕግ ከወጣ

ወይም ሚኒስቴሩ በሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን አዲስ ትርጉም

ከሰጠ ነባሩ በአንድ ታክስ ከፋይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ትርጉም እንደተነሳ

ይቆጠራል፡
የታክስ ሕጎችን አስቀድሞ መተርጎም …የቀጠለ
o ሚኒስቴሩ የሚሰጣቸው ሌሎች አስተያየቶች

 በሚኒስቴሩ የሚቀርቡ የሕትመት ውጤቶች ወይም በሌላ መልኩ


በቃልም ሆነ በጽሑፍ የሚሰጡ አስተያየቶች በሚኒስቴሩ ወይም
በባለሥልጣኑ ላይ አስገዳጅነት አይኖራ ቸውም፡፡
አመሠግናለሁ

You might also like