You are on page 1of 6

በአዲስ አበባ ከተማ ከመገናኛ አስከ የካ አባዶ ድረስ

የታክሲ አገልግሎት ለመጀመር መነሻ የሚሆን የንግድ


አዋጭነት ጥናት

ስራዉን ያከናወኑ የግሩፕ አባላት ዝርዝር

1. ----------------------------
2. ----------------------------
3. ----------------------------
4. ----------------------------
5. ----------------------------
6. ----------------------------
7. ----------------------------

ጥቅምት፣2016
Table of Contents

የስራዉ ባለቤት........................................................................................................................3

ስራዉ የተከናወነዉ፡-.................................................................................................................3

ይዘት....................................................................................................................................3

ሀ. ስራዉን ለማከናወን የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች፡..........................................................................3

ለ. የተሰበሰቡ መረጃዎች.........................................................................................................3

ተሳፋሪ የሚበዛበትን ሰዓት.....................................................................................................3

ዕቃ የሌላቸው ካላቸው አንጻር በመቶኛ ስሌት (7 %)...................................................................3

አገልግሎት የሰጠ መኪና የሚገዛበት ዋጋ.....................................................................................3

አዲስ መኪና የሚገዛበት ዋጋ..................................................................................................4

ለታክሲዋ ጥገና በአመት ሊወጣ የሚችል ወጪ.............................................................................4

ለስምሪት እና ለምዝገባ የሚያስከፍል ወጭ..................................................................................4

ያገለገለ መኪና ወደ ታክሲነት ለመቀየር ፣ ለግጭት መከላከያ ፣ ለመስታወት ፣ወዘተ አስፈላጊ ወጪ.................4

ሐ. የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች........................................................................................................4

አማራጭ መንገድ አንድ............................................................................................................4

የፋይናንስ ብድርና ድጋፍ ማግኛ አማራጮች.......................................................................................5

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ............................................................................................................5

ሌሎች የግል ባንኮች................................................................................................................6

ከግል ባለሀብቶች ጋር ሽርክና በመግባት.........................................................................................6

ለኢንሹራንስ አገልግሎት..........................................................................................................6

አማራጭ ሁለት (የኛ ግሩፕ በጣም የምናበረታታው).............................................................................6


በአዲስ አበባ ከተማ ከመገናኛ አስከ የካ አባዶ ድረስ የታክሲ አገልግሎት ለመጀመር መነሻ የሚሆን የንግድ
አዋጭነት ጥናት

የስራዉ ባለቤት

‘’ገሩፕ ሶስት (Group 3) የንግድና ኢንቨስትመንት አማካሪዎች ድርጅት’’

ስራዉ የተከናወነዉ፡-
ደንበኛችን ሳባ ብሩክ ባቀረቡልን ከመገናኛ እስከ የካ አባዶ ባለው መስመር የደንቦኞችን ምቾት በጠበቀ መልኩ
የታክሲ አገልግሎት ለመስጠት የአዋጭነት ጥናት ይጠናልኝ ብለው በጠየቁን መሰረት ነው።

ይዘት
ሀ. ስራዉን ለማከናወን የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች

ለ. የተሰበሰቡ መረጃዎች

ሐ. የተሰጠ ምክረሀሳብ

ሀ. ስራዉን ለማከናወን የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች፡


 ስራዉን ሊመራ የሚችል የቡድን መሪ መምረጥ (አንዋር ቃዲ)
 ሠራተኞችን ሶስት ቡድን መመደብ
 እያንዳንዱ ምድብ የራሱን ሃላፊነት እንዲወስድ ማድረግ
 መረጃ መሰበሰብን፣በተገኙት ሃሳቦች ላይ ውይይት ማድረግና የውሳኔ ሀሳቦችን ማስቀመጥ
 በመጨረሻም ለደንበኛቻችን ያገኘነዉን መረጃ ማስረከብ

ለ. የተሰበሰቡ መረጃዎች
 ተሳፋሪ የሚበዛበትን ሰዓት
o ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 12፡30-3፡00፣ እንዲሁም ምሽት

 ከ 10፡00-2፡00 ሰዓት

 ዕቃ የሌላቸው ካላቸው አንጻር በመቶኛ ስሌት (7 %)


o በቀን ውስጥ 65-80 ሰው በአንድ ታክሲ ላይ ይሳፈራል
o ይህም 100 ሰው 7 ሰው እቃ ይየዛል ማለት ነው እንዲሁም በመቶኛ ፐርሰንታይል
ከ 100% 93%ቱ ሰው ዕቃ አይዝም ማለት ነው።

 አገልግሎት የሰጠ መኪና የሚገዛበት ዋጋ


o 1.8 ሚሊየን ብር

 አዲስ መኪና የሚገዛበት ዋጋ


o 2.4 ሚሊየን ብር

 ለታክሲዋ ጥገና በአመት ሊወጣ የሚችል ወጪ


o 30,000 ብር (አጠቃላይ ሰርቪስ)
 ለስምሪት እና ለምዝገባ የሚያስከፍል ወጭ
o ላም በረት ታክሲ መነሐሪያ (ሰሜን ጀንበር) የታክሲ ስምሪት ማህበር
o ምዝገባ፦2000ETB/ ለስምሪት፦5000ETB ,ጠቅላላ 7,000ETB

 ያገለገለ መኪና ወደ ታክሲነት ለመቀየር ፣ ለግጭት መከላከያ ፣ ለመስታወት ፣ወዘተ አስፈላጊ ወጪ

ተ.ቁ ተግባራት ዋጋ (ብር)


1 መስታወት 30,000
3 ቀለም 50,000
4 ታፒሴሪ 27,000
5 ታርጋ ለመቀየር 10,000
6 3 ኛ ወገን 8,000
7 ንግድ ፍቃድ በዓመት 2,500
ግብር በዓመት 4,500
8 Over all srvice 30,000
162,000 birr

ሐ. የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች

በእነዚህ የስራ ሰዓት ውስጥ ሳባ በታክሲው የቢዝነስ ዘርፍ ብትሰራ ውጤታማ ልትሆንባቸው የምትችልባቸው ሁለት
አማራጭ መንገዶችን አስቀምጠናል ።

አማራጭ መንገድ አንድ

ከሳባ ፍላጎት አንጻር ብዙ የታክሲ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ መኪኖችን ጥናት ካደረግን በኋላ 5L መኪና
በዋጋ በጥንካሬ የተሻለ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም

 አገልግሎት የሰጠ መኪና የሚገዛበት ዋጋ 1.8 ሚሊየን ብር መይገኛል።

አንድ 5L የሚይዘዉ የሰዉ ቁጥር 13 ሲሆን ከመገናኛ የካ አባዶ ለአንድ ጉዞ በደንበኛች ፍላጎት መሰረት 30 ደቂቃ
የሚያስፈልግ ስለሆነና ከላይ በተሰበሰበው መረጃ መሰረት ደግሞ በአማካይ በቀን 180 ደቂቃ የስራ ሰዓት ስለሆነ በቀን
በአማካኝ 6 ጊዜ ይመላለሳል።

• በአማካይ 13 ሰው በአንድ ጉዞ በ 50 ብር ቢጭን ዕለታዊ ገቢው በ 6 ዙር ጉዞው 13*2*50*6=7,800


ብር ታገኛለች።
• የሚሳፈሩ ተሳፋሪዎች 7% ዕቃ ያላቸዉ ናቸው።

 ከዕቃ የሚገኘው ገቢ ለሹፌር እና ለረዳት ገቢ ይሆናል።

• ለመኪና ጥገና በዓመት ለሙሉ ጥገና 30,000 ብር ያስፈልጋል።

• ለስምሪት ፤ምዝገባ እና ለተለያዩ ጉዳይ የሚያስፈልጉ ወጭዎች

 ንግድ ፍቃድ 2,500 ብር በዓመት


 3 ኛ ወገን 8,000
 ለታክሲ ማህበራት ምዝገባ፦2000 ብር እና ለስምሪት፦5000 ብር ባጠቃላይ 7,000 ብር በዓመት
 ታርጋ ለማስቀየር 10,000 ብር
 ግብር 4,500 ብር በዓመት
• ድርጅቱ እንደሌሎች ታክሲዎች ሰልፍ ስለማይዝ ከመንግስት ጋር የራሱ የሆነ ስምምነት ይኖረዋል።

• በአጠቃላይ ድርጅቱ በቀን 7,800 ብር በአመት 300 ቀን ቢሰራ 300x7800 = 2,340,000 ብር ገቢ


የሚያገኝ ሲሆን ከዚህም ላይ የግብር፣ ለንግድ ፍቃድ ማሳደሻ፣ ለታክሲ ማህበር አባልነት እና
ለታርጋ ማስቀረጫ 162,000 ብር ወጪ ታደርጋልች። ለጥገና ደግሞ በአማካይ 30,000 ብር
ቢያወጣ የድርጅቱ ዓመታዊ የተጣራ ገቢው 2,148,000 ብር ይሆናል። በአጠቃላይ ድርጅቱ በ 1
ታክሲ ስራ ስለሚጀምር ጠቅላላ ትርፉ 2148000 ብር ይሆናል።

የፋይናንስ ብድርና ድጋፍ ማግኛ አማራጮች

ከላይ የተጠቀሰውን ቢዝነስ ለመጀመር ለሚያስፈልግ ማንኛውም የገንዘብ ድጋፍ የሚከተሉት አማራጮች
የተሻሉ ሆነው አግኝተናቸዋል።

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ


 ከዚህ በፊት ለሶስት ዓመት የሰራ የንግድ ድርጅት መኖር አለበት

 በታወቀ የሂሳብ አዋቂ ኦዲት የተደረገ የሂሳብ ሰነድና የመሳሰሉት ማቅረብ ከቻለ የብድር አገልግገሎት
ይመቻችለታል፡፡

 ሌሎች የግል ባንኮች

 በደንብ የተጠና የንግድ እቅድና ማስያዣ ካቀረበች እስከ 17 ፐርሰንት ወለድ ያበድራሉ።

 ከግል ባለሀብቶች ጋር ሽርክና በመግባት

 ለኢንሹራንስ አገልግሎት

 የኢትዮጲያ መድን ድርጅት፡

 ሌሎች የኢንሹራንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት

አማራጭ ሁለት (የኛ ግሩፕ በጣም የምናበረታታው)

ድርጅቱ ሳባ ታክሲ የሚል ብራንድ ስም እና ሞባይል አፕሊኬሽን ይኖረዋል።

 ተሳፋሪዎች ከቦታው ከመድረሳቸው በፊት በእጃቸው ሞባይል ስልክ አፕሊኬሽኑ ከሚዘረዝርላቸው የሰዓት
አማራጮች ውስጥ መርጠው በሚፈልጉት ሰዓት ይመዘገቡና በቴሌብር CBE birr ወይም ሌሎች አማራጮች
ቀድመው ክፍያ ይፈጽማሉ። ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝም ይይዛሉ።
 ተሳፋሪዎች በሰዓቱ ካልተገኙ 30% ተመላሽ ይደረግላቸዋል ወይም ደግሞ የጉዞ ታሪካቸው (Travel
history) ላይ ተመዝግቦ ለቀጣይ ጉዞ እንዲያገለግላቸው ይደረጋል።
ስለሆነም ይህን የሞባይል አፕሊኬሽን በመጠቀም ለአንድ ጉዞ የሚፈጀውን 30 ደቂቃ ወደ 25 ደቂቃ ዝቅ ማድረግ
ይቻላል።
ምክንያቱም፡
ለ 7፡00 ታክሲ አገልግሎት ታክሲው 6፡55 ላይ በቦታው ይገኛል ልክ 7፡00 ላይ ይወጣል። ታክሲው ከመገናኛ
የካአባዶ 30 ደቂቃ ይፈጅበታል። በአጠቃላይ ለአንድ ዙር ጉዞ 25 ደቂቃ ብቻ ይፈጅበታል ማለት ነው።

ስለዚህ ታክሲው በቀን 8 ዙር ይሰራል ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ለ 6 ዙር 7,800 ብር ለድርጅቱ ገቢ
ይደረግ የነበረውን ሌላ ተጨማር 2 ዙር ሲጨምር 13*2*50*8=10,400 ይሆናል ማለት ነው፡፡ይህም ማለት
2,600 ብር ተጨማር ገቢ ያስገኛል፡፡በአንድ በቀን ለባለቤቱ 7,800+2600=10,400 ብር ከፍ ያደርገዋል ማለት
ነው፡፡

አመታው ገቢ 10,400x330 = 3,432,000 ብር ይሆናል።

ከላይ የጠቀስናቸው ወጪወች ሲቀነሱ የተጣራ ትርፍ 3,240,000 ብር ይሆናል ማለት ነው።

እዚህኛው አማራጭ ላይ የሞባይል አፕሊኬሽን ለማሰራት በትንሹ 200,000 ብር ያስፈልጋል። ስለሆነም


በመጀመርያው ዓመት የድርጅቱ ትርፍ 3,040,000 ብር ይሆናል ማለት ነው።

You might also like