You are on page 1of 1

ጉዳዩ፡- በአገር አቀፍ የህብረት ሥራ ኢግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም-2013 ላይ ወጪ እንዲጋሩ ስለመጠየቅ፡፡

ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ አዘጋጅነት እና አስተባባሪነት ከመጋቢት 9-13
ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ፤ “የኅብረት ሥራ ማህበራት ግብይት ለዘላቂ ሰላም!” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ
በኦሮሞ የባህል ማዕከል የ 8 ኛውን አገር አቀፍ የኅብረት ሥራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም ለማካሄድ በመንቀሳቀስ
ላይ እንገኛለን፡፡ ይህን የህብረት ሥራ ማህበራት ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም ማዘጋጀት ያስፈለገበት ዋናው ዓላማ
አምራችና ሸማቹን ሕብረተሰብ በቀጥታ በማገናኘት በአገሪቱ ዘላቂ ልማት፣ ለሰላም ግንባታና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን
ለማረጋገጥ የሚያስችል የተረጋጋ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ነው፡፡

ስለሆነም ይህን ታላቅ ዓላማ ለማሳካት በቀጥታ የኅብረት ሥራ ማህበራት በዋናነት የተግባሩ ባለቤቶች በመሆናቸዉ
ወጪ እንደሚጋሩ ይታመናል፡፡ በዚሁ ጉዳይም ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኅብረት ሥራ ማስፋፊያ አካላት
ጋር በመነጋገር በደረስነዉ ስምምነት መሰረት የ የሚሳተፉ በመሆኑ ክልሉ
የወሰነዉን እና ስምምነት ላይ የደረሳችሁበትን የኢትዮጵያ ብር ወጪ
በመጋራት ባለቤትነትዎን እንዲያረጋግጡ በታላቅ አክብሮት እየጠየቅን የወጪ መጋራት ገንዘብ ገቢ የሚሆንበትን የባንክ
ሂሳብ ቁጥር የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000151987226
መሆኑን እየገለፅን ባንክ ገቢ የሚሆንበት የባንክ ደረሰኝ ለአሰራር ያመች ዘንድ የአስገቢው የኅብረት ሥራ ማህበሩ ስም
እንዲሆን እየጠየቅን ለኤግዚብሽኑና ባዛሩ ስኬት ለምታደርጉት ትብብር ሁሉ ከወዲሁ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ከሰላምታ ጋር!!!፡፡
ግልባጭ
ለ 8 ኛዉ ሀገር አቀፍ ኤግዚብሽን እና ባዛር አብይ ኮሚቴ
ፌ.ኅ.ኤ

You might also like