You are on page 1of 4

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ ለየትኞቹ የፋይናንስ ተቋማት

ደንበኞች ዋስትና ይሰጣል?


dw.com/am/የኢትዮጵያ-የተቀማጭ-ገንዘብ-ፈንድ-ለየትኞቹ-የፋይናንስ-ተቋማት-ደንበኞች-ዋስትና-ይሰጣል/a-65294636

ኤኮኖሚ

የፋይናንስ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ለሚሰበስቡት ተቀማጭ ዋስትና የሚሰጠው የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ
መድን ፈንድ ባለፈው ሣምንት ሥራ ጀምሯል። ከአባል ተቋማት በሚሰበሰብ መነሻ የአረቦን ክፍያ እና መንግሥት
በመደበው 200 ሚሊዮን ብር የተቋቋመውን ፈንድ አቶ መርጋ ዋቅወያ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተሾመዋል።

0:00 / 9:38

9:38 min

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ በይፋ
ሥራ ማስጀመሩን ባለፈው ሣምንት አስታውቋል። የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ ለማቋቋም በሚያዝያ
2013 በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው አዋጅ መሠረት በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው "የትኛውም
የፋይናንስ ተቋም" የዚህ ፈንድ አባል ይሆናል። የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ ባለፈው ወር ሲልቨርጌት
ባንክ፤ ሲሊኮን ቫሊ ባንክ እና ሲግኔቸር ባንክ ከስረው ሲዘጉ በባንኮቹ የተቀመጠ ገንዘብ ለነበራቸው ደንበኞች
ዋስትና ከሰጠው የአሜሪካ ፌዴራል ተቀማጭ ገንዘብ ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽን የሚመሳሰል ነው።

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድን አቶ መርጋ ዋቅወያ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ በጠቅላይ
ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደተሾሙ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። አቶ መርጋ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ የቆዩ ናቸው። የኢትዮጵያ የገንዘብ
ሚኒስትር፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እና ምክትል ገዥን ጨምሮ ሰባት የቦርድ አባላት ይኖሩታል።

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ አባል የሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ለሚሰበስቡት ተቀማጭ
ገንዘብ ዋስትና የሚሰጥ ነው። በቻይናው ሻናይ የፋይናንስ እና ኤኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የፒኤችዲ ተማሪ
የሆኑት የህግ ባለሙያው አቶ ተስፋዬ ቦሬሳ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ ዓላማ "ዜጎችን መሠረት"
ያደረገ እንደሆነ ይናገራሉ።

1/4
Protecting depositors and promoting economic growth: The Ethiopian Deposit Insurance has
been established in accordance with Council of Ministers Regulation No. 482/2021.
#FinancialSafety #Ethiopia #NationalBankofEthiopia pic.twitter.com/by2KNTKIdF

— National Bank of Ethiopia (@NBEthiopia) April 7, 2023

"ዓላማው ለዜጎች፤ ለገንዘብ ቆጣቢዎች ጥበቃ ማድረግ እና አንድም ችግሩ እንዳይፈጠር ለማድረግ፤ ሁለተኛ
ደግሞ ሕብረተሰቡ በባንኮች ዙሪያ ያለው አመኔታ እንዲያድግ እና ጠንካራ እንዲሆን ማድረግ ነው" የሚሉት አቶ
ተስፋዬ "ችግር ካጋጠመ እና ባንኩ ወይም ያ ማይክሮ ፋይናንስ ያን ገንዘብ መልሶ መክፈል የማይችልበት ደረጃ
ከደረሰ ይኸ ፈንድ በየዓመቱ ከእነሱ ይኸን አረቦን እየተቀበለ ችግር ሲያጋጥም ለአንዱ እንዲከፍል ተብሎ የታሰበ
ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

ይኸ ፈንድ በሌሎች አገሮች እንዳለው አሰራር ሁሉ በባንክ ገንዘብ ለሚያስቀምጡ ግለሰቦች እና ተቋማት ሁሉ
ዋስትና የሚሰጥ አይደለም። የመድን ሰጪ፣ የካፒታል ዕቃ አከራይ ኩባንያ ወይም የሌላ ፋይናንስ ተቋም
ተቀማጭ ገንዘብ በዚህ ፈንድ ዋስትና አይሰጣቸውም። የመንግሥት ወይም የመንግሥታዊ ድርጅት ተቀማጭ
ገንዘብ ዋስትና ከተሰጣቸው ውስጥ አልተካተቱም። የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ አባል የሆኑ የፋይናንስ
ተቋማት ተደማጭነት ያላቸው ባለ አክሲዮኖች፤ ዳይሬክተሮች፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ተቀማጭ ገንዘብም
ዋስትና አያገኝም።

የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ "ብዙ ጊዜ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ ሲቋቋም
ትልልቅ ተቋማዊ [ገንዘብ] አስቀማጮችን ለመጠበቅ አይደለም። እነሱ የትኛው ባንክ ጤነኛ ነው? የትኛው ባንክ
ጤነኛ አይደለም የሚለውን የመገምገም ችሎታ ስላላቸው፤ ዋና ዓላማው ዝቅተኛ ገንዘብ የሚያስቀምጡ
ደንበኞችን መጠበቅ ነው" ሲሉ ዋና ዓላማውን አስረድተዋል። "የትኛው ተቀማጭ ዋስትና ይሰጠው የሚለው
ባንኮቹ የሚወስኑት ነው። አንድ የግል ባንክ ይኸ ይኸ ተቀማጭ ዋስትና እንሲጠው እፈልጋለሁ ካለ በየዓመቱ
በአማካይ 0.3 በመቶ ይከፍላል" ሲሉ ዶክተር አብዱልመናን አክለዋል።

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ ለማቋቋም በሚያዝያ 2013 በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው አዋጅ
መሠረት በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው "የትኛውም የፋይናንስ ተቋም" የዚህ ፈንድ አባል ይሆናል።

2/4
ይኸ ተቋም ዋስትና የሚሰጠውን የተቀማጭ ገንዘብ መድን ሽፋን ጣሪያ የመወሰን ሥልጣን አለው። ይሁንና
ጣሪያው ከ100 ሺሕ ብር ማነስ እንደማይኖርበት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው አዋጅ ይደነግጋል።
የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ የመነሻ ካፒታል በቀዳሚነት ከፈንዱ ጋር የአባልነት ውል ከተፈራረሙ
የፋይናንስ ተቋማት የሚሰበሰብ መነሻ የአረቦን ክፍያ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በአባል የፋይናንስ ተቋማት መነሻ
የአረቦን ክፍያ ላይ የሚታከል መንግሥት 200 ሚሊዮን ብር ይመድባል።  ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ የተቀማጭ
ገንዘብ ፈንድ አባል የሆኑ የፋይናንስ ተቋማት የአማካይ ተቀማጭ ገንዘባቸውን 0.3 በመቶ ዓመታዊ የዓረቦን
ክፍያ ይፈጽማሉ።

የህግ ባለሙያው አቶ ተስፋዬ "በሌሎች አገሮች የምናየው ጠንካራ የህግ ሥርዓት ያላቸው ባንኮች እና ጀማሪ
ባንኮች ወይም ሥርዓታቸው የላሉ ባንኮች ዕኩል ግዴታ አይጣልባቸውም። ይኸ ማለት ምንድነው በጣም ጠንቃቃ
የሆነ ባንክ እና ሥርዓቱ ያን ያህል ያልዳበረን ባንክ በየዓመቱ ዕኩል ክፍያ እንዲከፍል ማድረግ ተገቢ ነወይ የሚል
ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል።

በባንክ ገንዘባቸውን ለሚያስቀምጡ ደንበኞች ዋስትና የሚሰጡ መሰል ተቋማት መመሥረት በተቀረው የዓለም
ክፍል የተለመደ አሰራር ነው። ኢትዮጵያ ከባንክ አገልግሎት ከተዋወቀች ከ100 ዓመታት በላይ ቢያልፏትም
መሰል ተቋም ለመመስረት የዘገየች ሆናለች። የኢትዮጵያ ጎረቤት ኬንያ እንኳ መሰል ተቋም ካቋቋመች በርከት
ያሉ ዓመታት አልፈዋል።

ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ "የነበሩት የባንኮች ቁጥር ትንሽ ነው። እስካሁንም የኢትዮጵያ ባንኮች
በአትራፊነታቸው የሚታወቁ ናቸው። ያን ያህል የከፋ ችግር ገጥሞን ስለማያውቅ የተቀማጭ ገንዘብ መድን
ማቋቋም አላስፈለገም" ሲሉ ለምን ኢትዮጵያ እንደዘገየች ያብራራሉ። የባንኮች ቁጥር ከማደጉ በተጨማሪ
በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የፋይናንስ ዘርፍ ማሻሻያ "የባንክ ዘርፉ ክፍት እየሆነ ስለመጣ የባንክ
መውደቅ ቢመጣ፤ ወይም ችግር ቢፈጠር እሱን ለመከላከል" የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ
መቋቋሙን ገልጸዋል።

በእርግጥም ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት በከፍተኛ ለውጥ ውስጥ እያለፈ ይገኛል። በኢትዮጵያ
ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጣቸው ባንኮች ቁጥር 31 ባንኮች ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪ 18 የኢንሹራንስ
ኩባንያዎች እና 44 አነስተኛ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ይገኛሉ። ለረዥም ዓመታት ለውጭ ባንኮች ተዘግቶ
የቆየው ገበያ ሊከፈት በዝግጅት ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ ያደረጋቸውም ማሻሻያዎች
ከዚህ ቀደም በዘርፉ የነበሩ ክልከላዎችን ቀስ በቀስ በሒደት እያላሉት ናቸው። እነዚህ አዎንታዊ መሻሻሎች ግን
የዚያኑ ያክል ተቋማቱን ለኪሳራ ገፋ ሲልም ለውድቀት ሊዳርጉ ለሚችሉ ሥጋቶች የማጋለጥ ዕድል አላቸው።

የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን "የኢትዮጵያ ባንኮች ችግር በዋናነት ሊመጣ የሚችለው
ከብድር በኩል ነው" የሚል አቋም አላቸው። ባንኮቹ "የሚያበድሩት ብድር የተበላሸ እንደሆነ እና መሰብሰብ
ያልቻሉ እንደሆነ ባንኮቹ ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ባንኮቹ የሚሰጡት ብድር በጣም
ከፍ ያለ እንደሆነ የጥሬ ገንዘብ ችግር ሊኖርባቸው ይችላል። በዚህ የተነሳ አስቀማጮች ገንዘባቸው በሚፈልጉበት
ጊዜ ላያገኙ ይችላሉ" ሲሉ ዶክተር አብዱልመናን አብራርተዋል።

እንዲህ አይነት ተቋማት ለባንኮችም ሆነ ለደንበኞቻቸው ዋስትና የመስጠታቸውን ያክል ቸልተኛ ሊያደርጓቸው
ይችላሉ የሚል ክርክርም አለ። "ባንኮች ዋስትና አለን ብለው የሚያስቡ ከሆነ እንደፈለጉ የማይሆን የብድር
አሰጣጥ ውስጥ እንዲገቡ፤ ገንዘብ አስቀማጮችም ግዴለሽ እንዲሆኑ እና ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ ማንኛውም
ባንክ ጋ ሊያስቀምጡ ይችላሉ" የሚሉት ዶክተር አብዱልመናን ደንበኞች የትኛው ባንክ ጤነኛ ነው? የትኛው
ባንክ ጤነኛ አይደለም?" ብሎ የማጣራት ኃላፊነት እንዳለባቸው ይመክራሉ።

እሸቴ በቀለ

ታምራት ዲንሳ

3/4
Audios and videos on the topic

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ


ቀን
12.04.2023
ቁልፍ ቃላት
የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ,
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ,
አቶ መርጋ ዋቅወያ,
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ይገልብጡ
«ኤም ፒ 3«
አስተያየትዎ: ምላሽ
ያትሙ
ገፁን ያትሙ
Permalink
https://p.dw.com/p/4Py7I

ቀን
12.04.2023
አውዲዮዎች በጠቅላላ
ከኤኮኖሚው ዓለም
በመገናኛ ብዙኃን ማዕከል ያሉ አውዲዮዎች በጠቅላላ
ቁልፍ ቃላት
የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ,
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ,
አቶ መርጋ ዋቅወያ,
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ይገልብጡ
«ኤም ፒ 3«
ምላሽ
ያትሙ
ገፁን ያትሙ
Permalink
https://p.dw.com/p/4Py7I

4/4

You might also like