You are on page 1of 8

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሃያ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፯ 26th Year No. 7


አዲስ አበባ ታህሣሥ ፴ ቀን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ADDIS ABABA 9th Junuary, 2020
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ Content
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፷፬/፪ሺ፲፪ ዓ.ም Proclamation No. 1164/2019
የአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ /ማሻሻያ/ አዋጅ…..ገጽ ፲፪ሺ፸፰ Microfinance Business (Amendment) Proclamation
Page ……………………………..…………………12078
ማረሚያ ቁጥር ፲፭/፪ሺ፲፪…………………ገጽ፲፪ሺ፹፭ Corrigendum No.15/2020………………….page 12085

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፷፬/፪ሺ፲፪ Proclamation No. 1164/2019


የአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ A PROCLAMATION TO AMMEND MICROFINANCE
BUSINESS PROCLAMATION

የአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ አዋጅ ቁጥር ፮፻፳፮/፪ሺ፩ን WHEREAS, it has become necessary to amend
ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ the Microfinance Business Proclamation
No. 626/2009;
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ NOW, THEEFORE, in accordance with
መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) መሰረት የሚከተለው Article 55(1) of the Constitution of the Federal
ታውጇል:- Democratic Republic of Ethiopia, it is hereby
proclaimed as follows:
፩. አጭር ርዕስ
1. Short Title
ይህ አዋጅ “የአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ /ማሻሻያ/ “This Proclamation may by cited as Microfinance
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፷፬/፪ሺ፲፪” ተብሎ ሊጠቀስ Business (Amendment) ProclamationNo.1164/ 2019.”
ይችላል፡፡
፪. ማሻሻያ 2. Amendment
የአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ አዋጅ ቁጥር The Microfinance Business Proclamation
፮፻፳፮/፪ሺ፩ እንደሚከተለው ተሻሽሏል:- No.626/2009 is hereby amended as follows:
፩/ የአዋጁ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ (፫)፣ (፬) እና 1/ Sub Article (3), (4) and (6) of Article 2 of the
(፮)፣ ተሰርዘው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ Proclamation are deleted and replaced by the
አንቀጽ (፫)፣ (፬) እና (፮) ተተክተዋል፡፡ following new Sub-Articles (3), (4) and (6):

፫/ ‹‹ኩባንያ›› ማለት በንግድ ሕግ የተሰጠውን 3/ “company” means a share company as


ትርጉም የያዘ ሆኖ አክሲዮኖቹ:- defined under the Commercial Code, the
capital of which is:
ሀ) በሙሉ በኢትዮጵያውያን ወይም የውጭ
a) owned fully by Ethiopian nationals or
ሀገር ዜግነት ባላቸው ትውልደ foreign nationals of Ethiopian origin
ኢትዮጵያውያን ወይም በኢትዮጵያውያን or jointly owned by Ethiopian
እና የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው ትውልደ nationals and foreign nationals of
ኢትዮጵያውያን በጋራ የተያዘ፣ ወይም Ethiopian origin, or

ÃNÇ êU nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1


Unit Price Negarit G. P.O.Box 80001

www.chilot.me
gA ፲፪ሺ፸፱ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፯ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No.7, 9th Junuary,2020…..page 12079

ለ) ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ወይም b) organizations owned fully by


የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው ትውልደ Ethiopian nationals or foreign
ኢትዮጵያውያን ወይም በኢትዮጵያውያን nationals of Ethiopian origin or jointly
እና የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው owned by Ethiopian nationals and
ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጋራ ባለቤትነት foreign nationals of Ethiopian origin;
በተቋቋሙ ድርጅቶች የተያዘ፤
በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የተመዘገበና ዋና registered under the laws of, and
having its head office, in Ethiopia;
መሥሪያ ቤቱ በኢትዮጵያ የሆነ አክሲዮን
ማኅበር ነው፣
፬/ ‹‹የግዴታ ቁጠባ›› ማለት ገንዘቡን የሚቆጥቡት 4/ “compulsory savings” means mandatory
deposits made for the purpose of enabling the
ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ወይም የንግድ
individuals, groups or businesses making the
ድርጅቶች ፈቃድ ከተሰጠው ተቋም ብድር
savings to qualify to receive loans from an
ለመውሰድ ብቁ ለመሆንና ለሚያገኙት ብድር authorized institution and to serve as
በመያዣነት እንዲያገለግል በግዴታ collateral against the loans so obtained;
የሚያስቀምጡት የቁጠባ ገንዘብ ነው፤
፮/ ‹‹የፋይናንስ ተቋም›› ማለት መድን ሰጪ 6/ “financial institution” means insurance
company, bank, capital goods finance
ኩባንያ፣ ባንክ፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም፣
company, micro-financing institution, a
የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ኩባንያ፣ የጠለፋ reinsurer, a micro insurance provider, postal
መድን ሰጪ፣ አነስተኛ መድን ሰጪ፣ የፖስታ savings, money transfer institution, an
ቁጠባ ድርጅት፣ የሐዋላ ድርጅት፣ በዲጅታል institution providing financial service through
ዘዴዎች የፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጥ digital channels or such other similar
institution as determined by the National
ድርጅት ወይም በብሔራዊ ባንክ የሚወሰን
Bank;
ሌላ ተመሳሳይ ድርጅት ነው፣
፪/ ከአዋጁ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ (፲፯) ቀጥሎ 2/ The following new Sub-Articles (18), (19)
and (20) are added after Sub Article (17)
የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጾች (፲፰)፣ (፲፱)
of Article 2 of the Proclamation, and the
እና (፳) ተጨምረው ንዑስ አንቀጽ (፲፰) ንዑስ
existing Sub-Articles(18) is renumbered as
አንቀጽ (፳፩) ሆኖ ተሸጋሽጓል፡፡
Sub-Article (21);
፲፰/ “በዲጅታል ዘዴዎች የሚሰጥ የፋይናንስ 18/ “digital financial service” means financial
አገልግሎት” ማለት በዲጅታል ዘዴዎች services including payments, remittances and
የሚሰጡ የክፍያ፣ የሐዋላ እና የመድን insurance accessed and delivered through
digital channels.
አገልግሎቶችን ያጠቃልላል፡፡"
‹‹ 19/ “Foreign National of Ethiopian Origin” means
፲፱/ የውጭ ዜግነት ያለው ትውልደ
a foreign national of Ethiopian origin as
ኢትዮጵያዊ›› ማለት የኢትዮጵያ ተወላጅ
defined under Proclamation No. 270/2002
የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ ሀገራቸው providing Foreign Nationals of Ethiopian
የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ origin with certain rights to be exercised in
የወጣው አዋጅ ቁጥር ፪፻፸/፲፱፻፺፬ ላይ their country of origin.
የተሰጠውን ትርጓሜ ይይዛል፡፡"
20/ “Liquid assets” shall include:
፳/ ‹‹ገንዘብ አከል ንብረት›› ማለት የሚከተሉትን
ያጠቃልላል፣
ሀ) ጥሬ ገንዘብ፣ a) cash;
ለ) በሀገር ውስጥ ባንኮች እና በአነስተኛ b) deposits with local banks and micro
ፋይናንስ ተቋማት ያለ ተቀማጭ ገንዘብ፣ finance institutions;
ሐ) በቀላሉ ወደ ጥሬ ገንዘብ ተቀይረው c) other assets readily convertible into
ወዲያውኑ ተከፋይ ሊሆኑ የሚችሉ cash; and
ንብረቶች፤ እና

www.chilot.me
gA ፲፪ሺ፹ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፯ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No.7, 9th Junuary,2020…..page 12080

መ) በብሔራዊ ባንክ በየጊዜው ተቀባይነት d) Such other assets as the National Bank
አላቸው ተብለው የሚወሰኑ ሌሎች ገንዘብ may from time to time declare to be
አከል ንብረቶች፡፡" liquid assets.
፫/ የአዋጁ አንቀጽ ፫ ንዑስ አንቀጽ (፪) ፊደል ተራ 3/ Paragraph (g), (i) and (k) of Sub Article (2) of
(ሰ)፣ (ቀ) እና (ተ) ተሰርዘው በሚከተሉት ፊደል Article 3 of the Proclamation are deleted
ተራ (ሰ)፣ (ቀ) እና (ተ) ተተክተዋል:- and replaced by the following new paragraph
(g), (i) and (k):
ሰ) “በከተማና በገጠር በጥቃቅንና አነስተኛ
የሥራ መስኮች ወይንም በሌሎች ምርታማ g) “Supporting income generating projects of
urban and rural micro and small scale
ተግባራት ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሚያካሂ
operators or others engaged in productive
ዷቸውን ገቢ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶች activities;”
ማገዝ፤”
i) “Managing funds for micro and small
ቀ)“ለጥቃቅንና ለአነስተኛ የንግድ ሥራዎች
scale businesses or other related
ወይም መሰል ምርታማ ተግባራት ዓላማ
productive activities;”
የሚውል ገንዘብ ማስተዳደር፤”
ተ) “የፋይናንስ ኪራይ አገልግሎት በካፒታል k) “Providing financial leasing service to
ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር lessees in accordance with Capital Goods
፩፻፫/፲፱፻፺ እና የካፒታል ዕቃ ኪራይ Leasing Business Proclamation No
.103/1998 and Capital Goods Leasing
ንግድ ሥራ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር
Business (Amendment) Proclamation
፰፻፯/፪ሺ፭ መሠረት ለተከራዮች No. 807/2013;”
መስጠት፤
፬/ ከአዋጁ አንቀጽ ፫ ንዑስ አንቀጽ (፪) ፊደል ተራ 4/ The following new paragraphs (l), (m) and
(ተ) ቀጥሎ የሚከተሉት አዲስ ፊደል ተራ (n) are added after paragraph (k) of Sub-
(ቸ)፣ (ኀ) እና (ነ) ተጨምረው ነባሩ ፊደል ተራ Article 2 of Article 3 of the Proclamation,
(ቸ) ፊደል ተራ (ኘ) ሆኖ ተሸጋሽጓል፡፡ and the existing paragraph (l) is renumbered
as paragraph (o):
ቸ) "በዲጅታል ዘዴዎች የዲጅታል l) Provide digital finance services;
ፋይናንስ አገልግሎት፣
ኀ) የወኪል ባንኪንግ አገልግሎት መስጠት፤ m) Agent banking service; and
እና
n) Provide interest-free microfinance
ነ) ከወለድ ነፃ አነስተኛ የፋይናንስ ሥራ
service;
አገልግሎት መስጠት፣"
፭/ ከአዋጁ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ (፩) 5/ The following new paragraph (c), (d) and (e)
ፊደል ተራ (ለ) ቀጥሎ አዲስ ፊደል ተራ are added after paragraph (b) Sub Article (1)
(ሐ)፣ (መ) እና (ሠ) ተጨምረዋል፡፡ of Article 8 of the Proclamation:

ሐ) “ተቋሙ የገንዘብ አከል ንብረት


እጥረት ሲያጋጥመው፣ c) “The institution has become illiquid;
መ) ተቋሙ ዕዳ መክፈል ወደማይችልበት
ወሰን ሲደርስ፣ ወይም d) The institution has become insolvent ; or
ሠ) ተቋሙ ህግንና መመሪያን ተቀብሎ
e) The institution has failed to obey and
ለመስራት ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር፤”
operate in line with the law and
፮/ የአዋጁ አንቀጽ ፲፫ ንዑስ አንቀጽ (፩) directive or is unwilling to do so;”
ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ 6/ Sub Article (1) of Article 13 of the Proclamation is
deleted and replaced by the following new sub-
(፩) ተተክቷል፡፡
article (1):

www.chilot.me
gA ፲፪ሺ፹፩ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፯ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No.7, 9th Junuary,2020…..page 12081

፩/ “የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም የውጭ 1/ “The auditor of any microfinance institution


ኦዲተር የኦዲት ግኝቶችን፣ ድምዳሜዎችን shall submit to the National Bank a
እና አስተያየቶችን ያካተተ የተሟላ የኦዲት complete audit report, including audit
ሪፖርት እና የውጭ ኦዲተር ዝርዝር findings and recommendations and a
ግኝቶችን በብሔራዊ ባንክ መመሪያ management letter, within the time limit set in
በሚወሰን የጊዜ ገደብ ውስጥ ለብሔራዊ the National Bank Directive. In addition, the
external auditor of a microfinance institution
ባንክ ማቅረብ አለበት፡፡ በተጨማሪም
shall report its audit findings and conclusions to
የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም የውጭ ኦዲተር
the shareholders of the institution. ”
የተቋሙን ሂሳብ መርምሮ ያገኛቸውን
ውጤቶች እና የደረሰባቸውን ድምዳሜዎች
ለተቋሙ ባለአክሲዮኖች ሪፖርት ማቅረብ
አለበት፡፡
፯/ የአዋጁ አንቀጽ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ (፬) 7/ Sub Article (4) of Article 17 of the
ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ Proclamation is deleted and replaced by the
(፬) ተተክቷል፡፡ following new Sub-Article (4);
፬/ "የተሻሻለውን የመመሥረቻ ጽሁፍ ወይም 4/ “register its amended memorandum of
መተዳደሪያ ደንብ ማስመዝገብ ወይም association and articles of association or
ፈቃድ ያገኘበትን ስም መለወጥ፤" alter the name under which it is licensed;”
፰/ ከአዋጁ አንቀጽ ፳፭ ቀጥሎ የሚከተሉት 8/ The following new articles 26, 27, 28, 29, 30,
አዲስ አንቀጾች ፳፮፣ ፳፯፣ ፳፰፣ ፳፱፣ ፴፣ 31 and 32 are added after Article 25 of the
፴፩ እና ፴፪ ተጨምረው ከአንቀጽ ፳፮ Proclamation, and the existing articles 26 to
እስከ ፴ ያሉት አንቀጾች እንደቅደም 30 are renumbered as Article 33 to 37,
ተከተላቸው ከአንቀጽ ፴፫ አስከ ፴፯ ሆነው respectively:
ተሸጋሽገዋል፡፡
፳፮/ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች 26. Financial Consumer Protection
መብት ጥበቃ “The National Bank may issue directive for
“የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን protecting the right and interest of financial
መብት እና ጥቅም ለማስከበር consumers.”
የሚያስችል መመሪያ ብሔራዊ ባንክ
ሊያወጣ ይችላል፡፡”
፳፯/ የብድር መረጃ ልውውጥ ሥርዓት 27. Credit-Information-Sharing System
“ብሔራዊ ባንክ አነስተኛ የፋይናንስ The National Bank may issue directive for
ተቋማትን ጨምሮ በፋይናንስ ተቋማት the establishment, operation, and cost
መካከል የሚደረግ የብድር መረጃ ልውውጥ apportionment of credit-information-sharing
ሥርዓት ስለሚደራጅበት፣ ስለአሰራሩና system among financial institutions including
microfinance institutions.
የወጪ መጋራትን በተመለከተ መመሪያ
ሊያወጣ ይችላል፡፡”
፳፰/ የማስታወቂያ ይዘትን ስለመቆጣጠር 28. Regulation of Advertisement
"ማንኛውም አነስተኛ የፋይናንስ “The National Bank may at any time direct
ተቋም በማንኛውም ጊዜ በብሔራዊ a microfinance institution to withdraw,
ባንክ እምነት ሀሰተኛ፣ አሳሳች፣ amend, or refrain from issuing a paid radio
or television announcement, a poster,
አደናጋሪ ወይም የሌላውን ጥቅም
billboard, brochure, circular or other
የሚጎዳ የተከፈለበት የሬድዮ ወይም
document, and a paid advertisement in
የቴሌቪዥን ማስታወቂያ፣ ፖስተር፣ regularly published newspaper or
ቢልቦርድ፣ በራሪ ወረቀት ወይም ሌላ magazine that it considers to be false,
ሰነድ እና የተከፈለበት የጋዜጣና misleading, deceptive, or offensive.”
የመጽሄት ማስታወቂያ አውጥቶ ቢገኝ

www.chilot.me
gA ፲፪ሺ፹፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፯ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No.7, 9th Junuary,2020…..page 12082

ተቋሙ ማስታወቂያውን እንዲያቋርጥ፣


እንዲያሻሽል ወይም ከማስተዋወቅ
እንዲቆጠብ ብሔራዊ ባንክ ሊያዘው
ይችላል፡፡"
፳፱/ ዋናና ወሳኝ ሥራን በውጭ አካላት 29. Outsourcing of Critical and Important
ስለማሰራት Functions
"አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ወሳኝ “Minimum conditions for outsourcing of
ሥራቸውን በውጭ አካላት ስለሚያሰሩ critical and important functions shall be
በት ሁኔታ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው determined by the directive to be issued
መመሪያ ሊወሰን ይችላል፡፡ ለዚህ by the National Bank. For the purpose of
አንቀጽ አፈጻጸም ‹‹ዋናና ወሳኝ ሥራ›› this Article, “critical and important
functions” of a microfinance institution
ማለት ቁጠባ መሰብሰብን፣ ብድር
include: functions related to deposits,
መስጠትን፣ የሀገር ውስጥ ሀዋላን፣
loans, local money transfer, micro
የአነስተኛ የመድን ሥራ እና ብሔራዊ
insurance and any other function as may
ባንክ የሚወስነውን ሌሎች ሥራዎችን be determined by the National Bank. ”
ያጠቃልላል፡፡"
፴/ በዲጅታል ዘዴዎች የፋይናንስ 30. Digital Financial Services
አገልግሎት መስጠት
"በዲጅታል ዘዴዎች የፋይናንስ አገልግሎት “Minimum conditions to provide digital
financial services shall be determined by the
ስለሚሰጥበት ሁኔታ ብሔራዊ ባንክ
National Bank directive.”
በመመሪያ ይወስናል፡፡"
፴፩/ ከወለድ ነፃ አነስተኛ የፋይናንስ ሥራ 31. Interest free microfinance service
አገልግሎት ስለመስጠት
፩) በአዋጁ የተጠቀሱ አነስተኛ 1) “Without prejudice to the
የፋይናንስ ሥራዎችን ለመሥራት requirements specified under the
የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች provisions of the Proclamation, the
እንደተጠበቁ ሆነው፣ ብሔራዊ ባንክ National Bank shall issue directive
ከወለድ ነፃ አነስተኛ የፋይናንስ to prescribe additional conditions
አገልግሎት ለመስጠት ለሚቋቋሙ
of licensing, supervision and
አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ፈቃድ
requirements to establish Interest
ስለሚሰጥበትና ቁጥጥር ስለሚያካሄድ
Free Microfinance Institution. For
በት ሁኔታ ተጨማሪ ግዴታዎች
ለመደንገግ መመሪያ ያወጣል፡፡ ለዚህ the purpose of this Sub-Article,
ንዑስ አንቀጽ "ከወለድ ነፃ አነስተኛ “Interest Free Microfinance
የፋይናንስ ሥራ የሚሠራ ተቋም" institution” means a microfinance
ማለት ከወለድ ነፃ አነስተኛ institution licensed by the National
የፋይናንስ ሥራ ብቻ እንዲሠራ Bank to undertake only interest
በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው free microfinance business.
ተቋም ነው፡፡
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) 2) Without prejudice to Sub Article (1)
የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ of this Article, the National Bank
ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛው may issue directive to regulate
የአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ጋር microfinance businesses related to
የወለድ ነፃ ተቀማጭ ገንዘብ interest-free deposit mobilization and
አሰባሰብና አጠቃቀም ጋር የተያያዙ fund utilization within a conventional
የአነስተኛ ፋይናንስ ሥራዎችን microfinance service.”
ለመቆጣጠር መመሪያ ያወጣል፡፡

www.chilot.me
gA ፲፪ሺ፹፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፯ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No.7, 9th Junuary,2020…..page 12083

፴፪/ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ 32. Manner of Participation of Foreign Nationals of
ኢትዮጵያዊ በአነስተኛ የፋይናንስ Ethiopian Origin in a Microfinance Business:
ዘርፍ ስለሚሳተፉበት ሁኔታ
፩/ "በአዋጁ አንቀጽ ፳፭ የተደነገገው 1/ “Without Prejudice to Article 25 of thi
ክልከላ እንደተጠበቀ ሆኖ የውጭ Proclamation foreign nationals of Ethiopian
ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ origin or organizations owned fully by
ኢትዮጵያዊ ወይም ሙሉ በሙሉ
foreign nationals of Ethiopian origin, or
የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው
jointly by foreign nationals of Ethiopian
ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለቤትነት
origin and Ethiopian nationals may be
ወይም የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው
ትውልደ ኢትዮጵያውያንና በኢትዮ allowed to acquire the shares of an
ጵያውያን የጋራ ባለቤትነት የተቋቋ Ethiopian micro-financing institution or
ሙ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ establish a micro-financing institution.
በተቋቋመ አነስተኛ የፋይናንስ
ተቋም የአክስዮን ባለቤት መሆን
ወይም አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም
ማቋቋም ይችላሉ፡፡
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) 2/ If a foreign national of Ethiopian origin
በተደነገገው አግባብ የውጭ ሀገር holds a share directly in a microfinance
ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ institution or indirectly by holding a share
ቀጥታ የአንድ የአነስተኛ ፋይናንስ in another organization that holds a share
ተቋም ባለአክስዮን ሲሆን ወይም in a microfinance institution, in accordance
በተዘዋዋሪ መንገድ የአክስዮን with the provisions of Sub Article (1) of
ባለቤት የሆነበት ሌላ ድርጅት this article, a foreign national of Ethiopian
የአንድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም origin or the organization in which he is
ባለአክስዮን ሲሆን የውጭ ሀገር shareholder, shall pay the values of the
ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ shares in a microfinance institution only in
ወይም እሱ ባለአክስዮን የሆነበት
an acceptable foreign currency.
እና በአነስተኛ ፋይናንስ ተቋሙ
ባለአክሲዮን የሆነ ድርጅት
በአነስተኛ ፋይናንስ ተቋሙ
የሚኖረው የአክስዮን ድርሻ ዋጋ
በሙሉ ተቀባይነት ባለው የውጭ
ምንዛሪ ብቻ የሚከፈል ይሆናል፡፡
፫ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) 3/ Notwithstanding the provisions of sub-
የተደነገገው ግዴታ ቢኖርም:- article (2) of this article, all types of
payments due to a foreign national of
Ethiopian origin resulting from:
ሀ) ከአክስዮን ባለቤትነት የሚያገኘው a) dividends earned from a share in a
የትርፍ ድርሻ፣ microfinance institution;
ለ) የአክስዮን ድርሻውን ለሌላ ሰው b) transfer of shares in a microfinance
ሲያዛውር፣ institution;
ሐ) ባለአክስዮን የሆነበት አነስተኛ c) sales or liquidation of a microfinance
የፋይናንስ ተቋም ሲሸጥ ወይም institution; or
ፈርሶ ሂሳቡ ሲሰራ፣ ወይም
መ) ሌሎች ከአክሲዮን ባለቤትነት ጋር d) any other matters related to shareholding
በተያያዘ፤ in a microfinance institution;
የውጭ ሀገር ዜግነት ላለው ትውልደ shall be paid in local currency, i.e., Birr,
ኢትዮጵያዊ ወይም እሱ ባለአክሲዮን meanwhile, he shall not be allowed to repatriate
ለሆነበት ድርጅት እና በአነስተኛ any asset or interest obtained in this manner.
የፋይናንስ ተቋም ውስጥ አክሲዮን ላለው

www.chilot.me
gA ፲፪ሺ፹፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፯ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No.7, 9th Junuary,2020…..page 12084

የሚከፈሉ ማናቸውም ዓይነት ክፍያዎች


በሙሉ በብር የሚከፈለው ይሆናል፣
እንዲሁም በዚህ አግባብ የሚያገኘውን
ሀብት ወይም ጥቅም ወደ ውጭ ሀገር
ማዛወር አይፈቀድለትም፡፡
፬/ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው 4/ The National Bank may issue directive related to
ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአነስተኛ additional conditions for investment in a
የፋይናንስ ዘርፍ መዋዕለ ንዋያቸውን microfinance institution by foreign nationals of
በሥራ ላይ ስለሚያውሉበት ተጨማሪ Ethiopian origin. ”

ሁኔታዎች ብሔራዊ ባንክ መመሪያ


ሊያወጣ ይችላል፡፡"
፱/ የአዋጁ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ (፫) 9/ Paragraph (a) of Sub Article (3) of Article
ፊድል ተራ (ሀ) እና አንቀጽ ፲፫ ንዑስ 12 and Sub Article (1) of Article 13 as well
አንቀጽ (፩) እንዲሁም አንቀጽ ፲፬ ንዑስ as paragraph (c) of Sub Article( 2) of Article
አንቀጽ (፪) ፊደል ተራ (ሐ) ተሰርዘዋል፡፡ 14 of the proclamation are deleted.
፲/ በአዋጁ በተለያዩ ቦታዎች ‹‹ተቆጣጣሪ›› ወይም
‹‹ 10/ “Inspector” or “Inspection” mentioned in
የቁጥጥር ሥራ›› የሚለው እንደ ቅደም
different parts of the proclamation is replaced by
ተከተላቸው ‹‹መርማሪ›› ወይም ‹‹የምርመራ “Examiner” or “Examination” , respectively.
ሥራ›› በሚል ተተክቷል፡፡

፫. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
3. Effective Date
ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት
This Proclamation shall come into force on the date
ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል:: of publication in the Federal Negarit Gazette.

Done at Addis Ababa, this 9th day of Junuary 2020.


አዲስ አበባ ታህሣሥ ፴ ቀን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም
SAHLEWORK ZEWDIE
ሳህለወርቅ ዘውዴ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ PRESIDENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC


ፕሬዚዳንት REPUBLIC OF ETHIOPIA

www.chilot.me
gA ፲፪ሺ፹፭ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፯ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No.7, 9th Junuary,2020…..page 12085

ማረሚያ ቁጥር ፲፭/፪ሺ፲፪ Corrigendum No.15/2020


የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፶፮/፪ሺ፲፩ Article 88(4) of Labour Proclamation No.
አንቀጽ ፹፰ (፬)“ሠራተኛዋ ከመውለዷ በፊት የወሰደችው 1156/2019 which read as “Where a pregnant
የ፴ የሥራ ቀናት የቅድመ፣ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ worker does not deliver within the 30 working days
of her pre-natal leave, she is entitled to an
ካልወለደች እስከምትወልድበት ቀን ድረስ
additional leave until her confinement in
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት እረፍት
accordance with Sub-Article (2) of this Article.
ልታገኝ ትችላለች፡፡ የ፴ የሥራ ቀናት የቅድመ-ወሊድ
However, if birth takes place before the expiry of
ፈቃዷ ሳያልቅ ከወለደች ፺ የሥራ ቀናት የድህረ
the pre-natal leave, the 90 working days of post-
ወሊድ ፈቃዷ ይጀምራል፡፡ የተባለው “ሠራተኛዋ natal leave shall commence.” is hereby corrected
ከመውለዷ በፊት የወሰደችው የ፴ ተካታታይ ቀናት and shall be read as “Where a pregnant worker
የቅድመ፣ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ካልወለደች እስከ does not deliver within the 30 consecutive days of
ምትወልድበት ቀን ድረስ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀ her pre-natal leave, she is entitled to an
(፪) መሠረት እረፍት ልታገኝ ትችላለች፡፡ የ፴ additional leave until her confinement in
ተከታታይ ቀናት የቅድመ-ወሊድ ፈቃዷ ሳያልቅ accordance with Sub-Article (2) of this Article.
ከወለደች ፺ ተከታታይ ቀናት የድህረ-ወሊድ ፈቃዷ However, if birth takes place before the expiry of
ይጀምራል፡፡”ተብሎ ይነበብ። the pre-natal leave, the 90 consecutive days of post-
natal leave shall commence.”

www.chilot.me

You might also like