You are on page 1of 23

https://chilot.

me

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሀያ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፷ 26th Year No. 60


አዲስ አበባ ሐምሌ ፫ ቀን ፪ሺ፲፪ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ th
ADDIS ABABA July 10 , 2020
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ Content
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፮/፪ሺ፲፪ Proclamation No. 1206/2020

የመንግሥት የልማት ድርጀቶችን ወደ ግል ስለማዛወር


Public Enterprises Privatization Proclamation
Page……………………………………………...12619
የወጣ አዋጅ ………………………….………………ገጽ፲፪ሺ፮፻፲፱

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፮/፪ሺ፲፪ PROCLAMATION NO. 1206 /2020

የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደግል A PROCLAMATION TO PROVIDE FOR THE


PRIVATIZATION OF PUBLIC ENTERPRISES
ስለማዛወር የወጣ አዋጅ

የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገትና ትራንስፎርሜሽን WHEREAS, it has become necessary to


ዘላቂነት እንዲኖረው ለማድረግ እና ለግል introduce reforms to sustain the country’s economic
ኢንቨስትመንት አመቺ የሆነ የፖሊሲ ከባቢዎችን growth and transformation and to create an enabling
ለመፍጠር የሕግ ማሻሻያዎች ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ policy environment for private sector investment;
በመገኘቱ፤
WHEREAS, it has become necessary to
ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ አፈጻጸም
improve the provision of finance for development to
አስተዋጽዎ እንዲኖረው ለማድረግ ለልማት የሚውልን
contribute to implementation of the country’s
የፋይናስ አቅርቦት ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
economic growth strategy;

ÃNÇ êU
Unit Price nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1
Negarit G. P.O.Box 80001
፲፪ሺ፮፻፳
https://chilot.me 12620

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

የግል ዘርፉ በኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖረውን ሚናና WHEREAS, it has become necessary to
ተሳትፎ ማስፋፋትና ማዳበር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ broaden the role and participation of the private
sector in the economy;
የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ቅልጥፍና
WHEREAS, it has become necessary to
ማሻሻል፣ ተወዳዳሪነታቸውን ማጎልበት፣ ለካፒታል
improve the efficiency of public enterprises, enhance
ያላቸውን ተደራሽነት እና የአገልግሎታቸውን ጥራትና
their competitiveness, improve their access to capital
ተደራሽነት ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
and improve the quality and accessibility of their
services;
ይህንኑ ዓላማ ከግብ ለማድረስ በሰፊ መሠረት
WHEREAS, to achieve this objective it is
ላይ የተጣለ ይፋና ግልጽ የሆነ የፕራይቬታይዜሽን
found necessary to implement of a privatization
ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
program in an open and transparent manner;

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ NOW, THEREFORE, in accordance with

ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው Article 55(1) of the Constitution of the Federal
ታውጇል። Democratic Republic of Ethiopia, it is hereby
proclaimed as follows.

ክፍል አንድ PART ONE


ጠቅላላ GENERAL
፩. አጭር ርዕስ 1. Short Title
ይህ አዋጅ “የመንግሥት የልማት ድርጀቶችን ወደ This Proclamation may be cited as the “Public
ግል ስለማዛወር የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፮/፪ሺ፲፪” Enterprises Privatization Proclamation No.
ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ 1206/2020”.
፪. ትርጓሜ 2. Definition
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ
In this Proclamation, unless the context
በስተቀር፣ በዚህ አዋጅ ውስጥ፦
otherwise requires:
፩/ “ፕራይቬታይዜሽን” ማለት የልማት ድርጅትን 1/ "Privatization" means a transaction or
ንብረት ወይም አክሲዮኖችን በሙሉ ወይም transactions resulting in either a sale of
በከፊል ለግል ዘርፉ በሽያጭ የማስተላፍ ውጤት assets or share capital of a Public
የሚያስከትል ግብይት ነው፤ Enterprise, in full or in part, to private
ownership;
፲፪ሺ፮፻፳፩
https://chilot.me 12621

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፪/ “የመንግሥት የልማት ድርጅት” ማለት 2/ "Public Enterprise" means an Enterprise


በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር governed by the Public Enterprises
፳፭/፲፱፻፹፬ የሚተዳደር የመንግሥት የልማት Proclamation No. 25/1992;
ድርጅት ነው፤

፫/ “ቅድመ ፕራይቬታይዤሽን ሥራዎች” ማለት 3/ “Pre-Privatization Activities” means any

በሚኒስቴሩ የሚከናወን የልማት ድርጅትን activity or process performed by the


ንብረት ወይም አክሲዮኖችን በሙሉ ወይም Ministry intended to prepare a Public
በከፊል ወደ ግል ለማዛወር የታቀደ Enterprise for privatization;
ማናቸውም ዝግጅት ወይም ሂደት ነው፤
፬/ “ወርቃማ አክሲዮን“ ማለት በዚህ አዋጅ 4/ “Golden Share” means a share in the
መሠረት የመንግሥት የልማት ድርጅትን capital of a company, formed by
በመለወጥ የካፒታሉ አካል የሆነና conversion of a Public Enterprise pursuant
በማናቸውም የቦርድ ውሳኔ ላይ ድምፅ to this Proclamation, carrying such special
የመስጠትና ድምፅን በድምፅ የመሻር rights as are set out in the Articles of
መብቶችን ለመንግሥት የሚያጎናጽፍ association of the company to enable the
በአክሲዮን መመስረቻ ፁሁፍ ውስጥ የተደነገጉ Government to protect the national
ልዩ መብቶችን የያዘ አክሲዮን ነው፤ interest with voting and veto rights over
any board resolution;
፭/ “ኤጀንሲ” ማለት የመንግሥት የልማት 5/ “Agency” means the Public Enterprise
ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ነው፤
Holding and Administration Agency;

፮/ “ሚኒስቴር” እና “ሚኒስትር” ማለት 6/ “Ministry” or “Minister” means the


እንደቅደምተከተሉ የገንዘብ ሚኒስቴር ወይም Ministry of Finance or the Minister of
ሚኒስትር ነው፤ Finance, respectively;
፯/ “ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን” ማለት ኤጀንሲውን 7/ "Supervising Authority" means an
ጨምሮ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች authority, including the Agency,
አዋጅ ቁጥር ፳፭/፲፱፻፹፬ መሠረት designated by the Council of Ministers
የመንግሥት የባለቤትነት መብቶችን with a view to monitoring, protecting and
ለመከታተል፣ ለመጠበቅ፣ ለመተግበር exercising the ownership rights of the
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተሰየመ Government in accordance with Public
ባለሥልጣን ነው፤ Enterprise Proclamation No. 25/1992;
፲፪ሺ፮፻፳፪ https://chilot.me 12622

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፰/ “ባለአደራ” ማለት በሚኒስቴሩ ሥር የተደራጀ 8/ "Trustee" means the Trustee Directorate


የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ General organized within the Ministry.
ዳይሬክቶሬት ጄነራል ነው፡፡
፱/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ 9/ "Person" means a natural person or a
የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤ juridical person;

፲/ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለፀው የሴትንም 10/ Any expression in the masculine gender

ፆታ ይጨምራል፡፡ includes the feminine.

፫. የፕራይቬታይዜሽን ዓላማዎች 3. Objectives of Privatization

የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም የሀገሪቱን የኢኮኖሚ The privatization program shall support the
ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የሚደግፍ በግልፅነት፣ country’s economic growth and
በአሳታፊነትና በተአማኒነት መርሆዎች ላይ transformation, be conducted based on the
ተመሥርቶ የሚከናወን ሲሆን የሚከተሉት principles of transparency, openness and
ዓላማዎች ይኖሩታል፦ integrity, and shall have the following
objectives:
፩/ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን 1/ To improve the efficiency of Public
ውጤታማነትን ማሻሻል፣ ተወዳዳሪነታቸውን Enterprises, enhance their
ማጎልበት፣ የቴክኒክ ሙያንና ክህሎትን መጋበዝ competitiveness, attract technical
እና የካፒታል አቅርቦትን ማሻሻል፤ expertise and skill sets, and improve
access to capital;
፪/ መንግሥት የሚያካሂዳቸውን የፋይናንስ 2/ To generate revenue and enhance the
እንቅስቃሴዎች ለማጎልበት ገቢዎችን provision of development finance in
ማሰባሰብና የልማት ፋይናንስ አቅርቦትን order to promote financing activities
ማጎልበት፤ undertaken by the Government;
፫/ ለግል ኢንቨስትመንት የፖሊሲ ከባቢዎችን 3/ To promote the Country's economic
በማጎልበትና የግል ዘርፉን መስፋፋት development by enhancing the policy
በማበረታት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ልማት environment for private investment and
ማሳደግ፡፡ encouraging the expansion of the private
sector.
፲፪ሺ፮፻፳፫ https://chilot.me 12623

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

ክፍል ሁለት PART TWO


ስለቅድመ ፕራይቬታይዚሽን ሥራዎች PRE-PRIVATIZATION ACTIVITIES

፬. ለቅድመ ፕራይቬታይዜሽን ሥራዎች የተለያዩ አካላት 4.Responsibilities of Different Institutions for


ኃላፊነት
Pre-Privatization Activities
፩/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚኒስቴሩን እና 1/ The Council of Ministers shall determine the
የተቆጣጣሪውን ባለሥልጣን የውሳኔ ሃሣብ Public Enterprise to be fully or partially
ከግምት ውስጥ በማስገባት ሙሉ በሙሉ privatized, taking into consideration the
ወይም በከፊል ወደ ግል መዞር ያለበትን recommendations of the Ministry and the
የልማት ድርጅት ይወሰናል፡፡ Supervising Authority of the Public
Enterprise.
፪/ ሚኒስቴሩ፡- 2/ The Ministry : -

ሀ) ማናቸውንም የቅድመ ፕራይቬታይዜሽን a/ Shall determine any necessary Pre-

ሥራዎች የሚያከናውን ሲሆን privatization activities including when to


የሚመለከተውን የመንግሥት የልማት begin the Pre-privatization process and
ድርጅት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በማማከር which activities shall be included in
የቅድመ ፕራይቬታይዜሽን ሂደት መቼ coordination with the Supervising
መጀመር እንዳለበትና የትኞቹ ሥራዎችም Authority of the Public Enterprise;
መካተት እንዳለባቸው፣
ለ) ከመንግሥት የልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ b/ In consultation with the Supervising

ባለሥልጣን ጋር በመመካከር የእያንዳንዱን Authority of the Public Enterprise, shall

ሽያጭ አመላካች የሽያጭ ዋጋ (ወይም determine the modality of each sale along

መነሻና መድረሻ ዋጋ) እና ወደ ግል with an indicative price (or price range)

የሚዛወረውን የአክሲዮን መጠንን and number of shares (or proportion of the

(የድርጅቱን መጠን)፣ company) to be privatized;

ሐ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ዋጋ ግምትን፣ c/ Shall determine the readiness of each

እንደገና የማዋቀር ጥረቶች ውጤቶችን፣ Public Enterprise for privatization, taking

ወቅታዊው የገበያ ሁኔታዎችን እና ድርጅቱ into account factors including but not

ኢንቬስተሮችን መሳብ የመቻሉን ዕድል limited to the Public Enterprise’s

ከግምት ውስጥ በማስገባት እያንዳንዱ valuation, results of any restructuring

የመንግሥት የልማት ድርጅት ወደ ግል efforts, current market conditions and the

ለመዛወር ያለውን ዝግጁነት፣ ይወስናል፡፡ likelihood that the Public Enterprise will
attract investors.
፲፪ሺ፮፻፳፬ https://chilot.me 12624

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፫/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) የተመለከተው 3/ Once a Public Enterprise is deemed
እንደተጠበቀ ሆኖ የመንግሥት የልማት ready for privatization and the
ድርጅቱ ለፕራይቬታይዜሽን ዝግጁ መሆኑ privatization modality has been
ታምኖ የፕራይቬታይዜሽን ስልቱ ሲወሰን determined, upon the recommendation
ኤጀንሲው ፕራይቬታይዜሽኑን የመተግበር of Ministry, the Agency shall
እንቅስቃሴ ይጀምራል፡፡ commence implementation of the
privatization transaction.
፬/ ወደ ግል የሚዛወር የልማት ድርጅት የሥራ
4/ The Management Board of a Public
አመራር ቦርድ፦
Enterprise to be privatized shall:

ሀ) ከሚኒስቴሩ እና ከተቆጣጣሪው ባለሥልጣን a) Provide the Ministry and the

በሚቀርብለት ጥያቄ መሠረት የመንግሥት Supervising Authority all

የልማት ድርጅቱን በሚመለከት የተሟላ information regarding the Public

መረጃ ይሰጣል፤ Enterprise as requested;

b) Prepare the enterprise for pre-


ለ) ከተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ጋር
privatization and privatization in
በመመካከር በሚኒስቴሩ በተሰጡ
accordance with instructions given
መመሪያዎች መሠረት የመንግሥት
to it by the Ministry, in consultation
የልማት ድርጅቱን ለቅድመ
with the Supervising Authority;
ፕራይቬታይዜሽንና ለፕራይቬታይዜሽን
ያዘጋጃል፤

ሐ) በቅድመ ፕራይቬታይዜሽን ሂደትና c) Ensure that the assets of the Public


በፕራይቬታይዜሽን ወቅት የልማት ለብክነት Enterprise do not deteriorate or
አለመዳረጉን ያረጋግጣል፤ become dissipated during the pre-
መ) በመደበኛው የንግድ እንቅስቃሴ ምክንያት privatization or privatization phases;
ወይም በሚኒስቴሩ ስምምነት ካልሆነ በቀር፣
d) Refrain from making any new
በቅድመ ፕራይቬታይዜሽን ወቅትና
investments during the privatization
በፕራይቬታይዜሽን ደረጃ ማናቸውም አዲስ
or pre-privatization phases except in
ኢንቬስትመንት ከማድረግ መቆጠብ
the ordinary course of business or
ይኖርበታል፡፡
with the agreement of the Ministry.
፲፪ሺ፮፻፳፭ https://chilot.me 12625

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፭. በቅድመ ፕራይቬታይዜሽን የመንግሥት የልማት


5. Public Enterprise Restructuring and Other
ድርጅትን እንደገና ስለማዋቀርና ሌሎች ተግባሮች
Activities Prior to Privatization
፩/ ሚኒስቴሩ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ 1/ Pursuant to Article 4 (2) and (3) of this
(፪) እና (፫) መሠረት ከተቆጣጣሪው Proclamation, the Ministry, in
ባለሥልጣን ጋር በመቀናጀት የልማት ድርጅቱ coordination with the Supervising
ወደ ግል ከመዛወሩ በፊት ተገቢው የካፒታል Authority, shall evaluate whether the
አደረጃጀቶች፣ የንግድ ስትራቴጂ፣ የኮርፖሬት Public Enterprise has the appropriate
አስተዳዳር መዋቅሮች እና የሪፖርት capital structure, business strategy,
አቀራረብና የመረጃ አገላለጽ ልምዶች ያለው corporate governance structures and
መሆኑን ይገመግማል፤ ጉድለት በሚኖርበትም reporting and disclosure practices prior to
ጊዜ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡ privatization, and take appropriate action
in the event of deficiencies.
፪/ ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን የሚኒስቴሩን የቅድመ 2/ The Supervising Authority shall provide
ፕራይቬታይዜሽን እንቅስቃሴን ለመደገፍ to the Ministry any financial and
በመንግሥት የልማት ድርጅቱ ላይ ክትትል operational analyses, and related
ባደረገበት ወቅት ያደረጋቸውን ማናቸውንም supporting information it has already
የኦፕሬሽን ግምገማዎችንና ተዛማጅ መረጃዎችን conducted in the course of its oversight
ለሚኒስቴሩ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ efforts to support the Ministry’s pre-
privatization activities.
፫/ ሚኒስቴሩ አስፈላጊ የሆኑ ማናቸውም 3/ The Ministry shall be responsible for any
የኦፕሬሽንና የፋይናንስ ሥርዓትን እንደገና operational or financial restructuring
የማዋቀር ኃላፊነት አለበት፤ ወደ ግል ከመዛወሩ required and shall ensure that such
በፊትም እንደገና መዋቀሩ የመንግሥት restructuring is limited to bolstering the
የልማት ድርጅቱን ዋጋና ተፈላጊነቱን value of the Public Enterprise and
የሚያሳድግ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡ attractiveness prior to privatization.
፬/ ሚኒስቴሩ ከፕራይቬታይዜሽን በኋላ ተገቢ 4/ The Ministry shall take all necessary action
ያልሆነ የውድድር ባህርያት፣ የገበያ ልምዶች during the pre-privatization phase to
እና መጠኑ ያለፈ የገበያ የበላይነት እንዳይከሰት prevent anti-competitive behavior, unfair
በፕራይቬታይዜሽን ደረጃ ወይም ወቅት በሥራ market practices and excessive market
ላይ ባለው ሕግ መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ dominance following privatization, in
ሁሉ ይወስዳል፡፡ accordance with prevailing laws of the
country.
፲፪ሺ፮፻፳፮ https://chilot.me 12626

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፮. የመንግሥት የልማት ድርጅትን ወደ አክሲዮን 6. Conversion of a Public Enterprise to a


ማኅበርነት ስለመለወጥ Share Company
፩/ የንግድ ሕግ አንቀጽ ፫፻፯ (፩) ቢኖርም፣ አንድን 1/ Notwithstanding Article 307 (1) of the
የመንግሥት የልማት ድርጅትን Commercial Code, a Public Enterprise
ለፕራይቬታይዜሽን ዝግጁ ለማድረግ በአንድ may be converted into a share company
ባለአክሲዮን ባለቤትነት ወደሚያዝ የአክሲዮን with only one shareholder in preparation
ማኅበርነት ሊለወጥ ይችላል፡፡ for privatization.
፪/ የልማት ድርጅቱ ወደ አክሲዮን ማኀበርነት 2/ In the event the Public Enterprise is
በሚለወጥበት ወቅት አክሲዮኖቹ ወደ ግል converted into a share company, the
ባለቤትነት እስከሚዛወሩ ድረስ የድርጅቱ capital of the share company shall be
ካፒታል በአክሲዮኖች ተከፋፍሎ አክሲዮኖቹ divided in to shares which shall be held
በመንግሥት ይያዛሉ፡፡ as government shares until such time as
any shares are transferred to private
ownership.
፫/ በንግድ ሕጉ ለባለአክሲዮኖች ጉባዔ የተሰጡ 3/ Authorities given to shareholders meetings
ሥልጣኖች በመንግሥት የልማት ድርጅቶች under the Commercial Code shall be
አዋጅ መሠረት አግባብነት ላለው የመንግሥት deemed given to the Supervising
የልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን Authority of the Public Enterprise in
እንደተሰጡ ይቆጠራሉ፡፡ accordance with Public Enterprise
Proclamation;
፬/ ከንግድ ሕጉ አንቀጽ ፫፻፯ (፩) ፣ አንቀጽ ፫፻፲፩፣ 4/ All provisions of the Commercial Code
አንቀጽ ፫፻፵፯ (፩) እና አንቀጽ ፫፻፵፱ በስተቀር shall be applicable, with the exception of
ሌሎቹ የንግድ ሕግ ድጋጌዎች ተፈጻሚ the provisions of Articles 307(1), 311,
ይሆናሉ፡፡ 347(1) and 349.

፭/ በንግድ ሕጉ አንቀጽ ፭፻፵፮ ከንዑስ አንቀጽ (፩) 5/ Notwithstanding Article 546 Sub-Articles
እስከ (፬) እና በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር (1) - (4) of the Commercial Code and
፱፻፸፱/፪ሺ፰ አንቀጽ ፷፱ (፩) እና (፪) Article 69(1) and (2) of the Income Tax
የተደነገጉት ቢኖሩም፣ ሚኒስቴሩ የመንግሥት Proclamation No. 979/2008, the Ministry
የልማት ድርጅትን ወደ አክስዮን ማኅበርነት shall, in converting a Public Enterprise
በሚለውጥበት ጊዜ ለአክሲዮን ማኅበሩ into a share company, have the power to
የሚተላለፉትን የመንግሥት የልማት ድርጅቱን determine the assets and liabilities of the
፲፪ሺ፮፻፳፯ https://chilot.me 12627

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

ሀብትና ዕዳዎች እንዲሁም ንብረቶቹ እንደገና Public Enterprise that may be transferred
ከተገመቱ በኋላ ካፒታሉን የመወሰንና የማሳደግ to share company, fix its capital and
ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ increase its capital after reevaluating its
assets.
፮/ ወደ አክሲዮን ማኅበርነት የተለወጠ የመንግሥት 6/ A Public Enterprise converted into a share
የልማት ድርጅት እንደተመዘገበ ህልውናው company shall cease to exist upon
ያከትማል፡፡ registration of the share company.
፯. የመንግሥት የልማት ድርጅቱን ዋጋ ስለመተመን 7. Valuation of Public Enterprise

፩/ ሚኒስቴሩ የልማት ድርጅትን፣ የልማት 1/ The Ministry shall cause an independent


ድርጅትን የተወሰነ ክፍል ወይም ንብረት valuation of the Public Enterprise, its
ወይም የመንግሥት አክሲዮንን ወደ ግል assets, units or government-owned shares
ለማዛወር በቅድሚያ ዋጋው ገለልተኛ በሆነ by a qualified expert.
ብቃት ባለው ባለሙያ እንዲተመን ማስደረግ
አለበት፡፡
፪/ የዋጋ ትመናው የሚከናወነው በሚኒስቴሩ 2/ The valuation shall be carried out following
ቁጥጥር ሥር የሚደረገው የልማት ድርጅቱን the completion of any financial and/or
የፋይናንስ እና/ወይም የኦፕሬሽን እንደገና operational restructuring overseen by the
የማደራጀት ሥራ መጠናቀቅ ተከትሎ Ministry and shall be conducted in
ሚኒስቴሩ ባወጣው የዋጋ ትመና መመሪያ accordance with guidelines issued by the
መሰረት ይሆናል፡፡ Ministry.
፫/ በዋጋ ትመናው መሰረት የሚወሰነው የመሸጫ 3/ The floor or indicative price determined as
መነሻ ወይም አመልካች ዋጋ the result of the valuation shall be subject
በፕራይቬታይዚሽኑ ሂደት በኤጀንሲው ጥቅም to approval by the Ministry prior to its
ላይ ከመዋሉ በፊት በሚኒስቴሩ መጽደቅ usage by the Agency in privatization
አለበት፡፡ process.
፲፪ሺ፮፻፳፰ https://chilot.me 12628

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

ክፍል ሦስት PART THREE


የፕራይቬታይዚሽን አፈጻጸም ማዕቀፍ PRIVATIZATION IMPLEMENTATION FRAMEWORK

፰. የፕራይቬታይዜሽን አፈጻጸም 8. Privatization Implementation

፩/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፕራይቬታይዜሽን 1/ The Council of Ministers shall have the

አፈጻጸምን በተመለከተ የሚከተሉት ሥልጣንና following Powers and Duties with respect
to privatization implementation activities:
ተግባራት ይኖሩታል፦
a) For a Public Enterprise accountable to
ሀ) ከኤጀንሲው ውጭ ላለ ተቆጣጣሪ
a Supervising Authority other than the
ባለሥልጣን ተጠሪ የሆነን የመንግሥት
Agency , approve the transfer of the
የልማት ድርጅት ወይም በተቆጣጣሪ
Public Enterprise to the Agency prior
ባለሥልጣን የተያዙ አክሲዮኖች ወደ ግል
to the privatization transaction;
ማዛወሩ ከመከናወኑ በፊት ለኤጀንሲው
መተላለፋቸውን ያፀድቃል፤
b) Approve the use and structure of any
ለ) የሚኒስቴሩንና የኤጀንሲውን የውሳኔ ሀሳብ
golden share, and the exercise thereof,
ከግምት ውስጥ በማስገባት የማናቸውም
ወርቃማ አክሲዮን አጠቃቀም፣መዋቅር እና
taking into account the

አተገባበሩን ያፀድቃል፤ recommendation of the Ministry and


the Agency.
2/ The Agency shall have all the functions
፪/ ኤጀንሲው የፕራይቬታይዜሽንን አፈጻጸም
necessary for the implementation of
በተመለከተ የሚከተሉትን ተግባራት
privatization and shall in particular
ያከናውናል፦
include the following:
ሀ) የሽያጭ ማከናወኛ ሥነ ሥርዓቶችን a) Develop procedures for conducting
ያዘጋጃል፤ sales;
ለ) ለእያንዳንዱ ሽያጭ የሚያገለግል b) Determine the bid evaluation criteria
የጨረታ መመዘኛ መስፈርቶችን for each tender transaction;
ይወስናል፤
ሐ) የመሸጪያ ጊዜን ይወስናል፣እያንዳንዱን c) Determine the timing of sale,
ሽያጭ ያመቻቻል፣ ሽያጩን በበላይነት organize and oversee each
ይከታተላል፤ transaction;
መ) ሽያጭ ሲከናወን የሚያግዙ ባለሙያዎችን d) Hire experts as needed to assist in
ይቀጥራል፤ carrying out transactions;
፲፪ሺ፮፻፳፱ https://chilot.me 12629

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

ሠ) ፍላጎት ያላቸው ኢንቬስተሮች በግዢው e) Publicize the offering appropriately


እንዲሳተፉ ከበቂ ጊዜ ጋር ሽያጩን providing sufficient time for
በሕዝብ መገናኛ ያሳውቃል፤ interested investors to participate in
the transaction;
ረ) አስፈላጊውን ሰነዶችና ናሙና ውሎችን f) Prepare all necessary documentation
ያዘጋጃል፤ and sample agreements;
ሰ) በማናቸውም ድህረ ፕራይቬታይዜሽን g) Decide on any post-privatization
ኢንቬስትመንት መስፈርቶች ላይ ውሳኔ investment requirements;
ይሰጣል፤
ሸ) ማንኛውም ባለሀብት በረዥም ጊዜ h) In consultation with the Ministry,
በሚፈጸም ክፍያ የሽያጩን ዋጋ የመክፈል decide whether to grant the right to
መብት የሚሰጠው መሆን አለመሆኑን እና any investor to pay for sales on an
ክፍያ የሚፈጸምበትን ሕጋዊ ገንዘብ installment basis and the currency of
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር payment;
በመመካከከር ይወስናል፤
ቀ) የፕራይቬታይዜሽን ሂደት አተገባበሩ i) Ensure the systematic execution,
ሥርዓት ያለው፣ ሕጋዊ፣ግልጽና ቀልጣፋ legality, transparency and efficiency
መሆኑን ያረጋግጣል፤ of the privatization process;
በ) ከፕሮግራሙ አፈጻጸም ጋር በተያያዙ
j) Submit recommendations to the
የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ እንደአግባቡ
Government as may be appropriate
ለመንግሥት የውሳኔ ሃሣብ ያቀርባል፤
on policy issues relating to the
ተ) ከሕዝብ ጋር ግንኙነት ይፈጥራል፣ implementation of the program; and
የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም k) Communicate with the public and
እንቅስቃሴዎችን ወይም ክንዋኔዎችን publicize the activities of the
ያስተዋውቃል፡፡ privatization program.

፫/ የመንግሥት የልማት ድርጅት ለፕራይቬታይዜሽን 3/ Pursuant to Article 4 sub-Article (2)-(4) of this


ዝግጁ መሆኑ ከተረጋገጠ እና የፕራይቬታይዜሽን Proclamation, once a Public Enterprise is
ስልቱ በሚኒስቴሩ ሲወሰን ኤጀንሲው በዚህ አዋጅ deemed ready for privatization, and the
አንቀጽ ፬ ከንዑስ አንቀጽ (፪) እስከ (፬) በተደነገገው privatization modality has been determined by
መሠረት ለዚሁ ባቋቋመው ክፍል አማካይነት ወደ the Ministry, the Agency shall commence the
ግል የማዛወሩን ተግባር ማከናወን ይጀምራል፡፡ implementation of the privatization transaction,
through a dedicated unit at the Agency.
፲፪ሺ፮፻፴
https://chilot.me 12630

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፬/ ኤጀንሲው ከሚኒስቴሩ ጋር በመቀናጀት የመሸጪያ 4/ The Agency shall determine, in
መነሻ ዋጋ ወይም በግብይት ወይም በንግድ ላይ collaboration with the Ministry the final
የተመሠረተ ተመሳሳይ ዋጋ ወይም በውድድር ላይ offering size and share price immediately
የተመሠረተ ጨረታ ወይም በጨረታ ላይ before the commencement of an Initial
የተመሠረተ ተመሳሳይ ሽያጭ ከመጀመሩ ቀድም Public Offerings (“IPO”) or similar
ብሎ የሚቀርበውን የመጨረሻውን የሽያጭ መጠንን exchange- or trading-based share offering
እና የአክሲዮን ዋጋን ይወስናል፡፡ or based on final transaction negotiations
in the case of competitive bid or similar
tender-based sale.
፭/ ኤጀንሲው ፕራይቬታይዜሽንን፣ ለሽያጭ 5/ The Agency shall revert to the Ministry for
የሚቀርበውን የአክሲዮን ዋጋን ወይም መጠንን their agreement in the event the
ወይም የልማት ድርጅቱን ድርሻ በተመለከተ recommended modality for privatization or
የቀረበውን ሀሳብ በገበያው፣ በዘርፉ ሁኔታዎች the recommended share price or number of
ወይም በሌሎች ምክንያቶች መቀያየር ማሻሻል shares (or proportion of company) to be
የሚያስፈልግ ሆኖ ከተገኘ ለሚኒስቴሩ መልሶ offered requires modification as a result of
ያሳውቃል ፡፡ changing market or sector conditions or
other factors.
፮/ የመንግሥት የልማት ድርጅትን ወደ ግል ማዛወር 6/ Where a Public Enterprise privatization
ያልተቻለ እንደሆነ ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን transaction fails, upon request by the
አግባብ ባላቸው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች Supervising Authority to the Council of
ሕግ መሠረት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥያቄ Ministers and approval thereof and in
አቅርቦ ሲፀድቅለት የመንግሥት የልማት ድርጅቱ accordance with relevant provisions of the
ሊፈርስ ይችላል፡፡ Public Enterprises law, the Public
Enterprise may be dissolved.
፲፪ሺ፮፻፴፩
https://chilot.me 12631

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

ክፍል አራት PART FOUR
የፕራይቬታይዜሽን ስልቶች MODALITIES OF PRIVATIZATION
፱. የፕራይቬታይዜሽን ስልቶች
9. Modalities of Privatization
፩/ በሥራ ላይ የሚውል ማናቸውም
1/ The use of any transaction modality of
የፕራይቬታይዜሽን ስልት አተገባበር በግልጽነት
privatization shall be based on the
መርሆዎች ላይ የተመሠረተ እና ግቡም
principles of transparency and the goal of
ለመንግሥት ተስማሚ የሆኑ ስምምነቶች ላይ
securing the most favorable terms for the
መድረስ ነው፡፡
Government.
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ከዚህ 2/ In accordance with Sub-article (1) of this
በታች ከተመለከቱት የፕራይቬታይዜሽን ስልቶች Article, any one of the following modes of
አንዱ እንደአግባቡ ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል፤ privatization may be used as appropriate:
ሀ) በውድድር ላይ በተመሠረተ ጨረታ፤ a) Competitive tender;
ለ) ለሕዝብ ክፍት በሆነ ጨረታ፤
b) Public auction;
ሐ) የአክሲዮን ገበያ ወይም ሌሎች ተስማሚ
የግብይት መድረኮች ያሉ እንደሆነ፣ c) Initial Public Offerings (“IPO”); where
ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ለሽያጭ there is a stock exchange or other
በሚቀርብ አክሲዮን፤ suitable trading platform and
መ) በረዥም ጊዜ ተከፋፍሎ በሚሸጥ d) Sales, featuring sale tranches over
የተሰበጣጠረ ግዢ፡፡ time.

፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገው 3/ Notwithstanding Sub Articles (1) of this

እንደተጠበቀ ሆኖ ኤጀንሲው በሚኒስቴሩ ፈቃድ Article the Agency may after approval

ተስማሚና ለኢንዱስትሪው ደረጃ የሚመጥን የንግድ from the Ministry, select other privatization

ወይም የስትራቴጂክ ሽያጭን በቅድሚያ በተመረጡ modalities that are appropriate and are

አነስተኛ ቁጥር ባላቸው የኮርፖሬት ኢንቬስተሮች industry standard, such as trade or strategic
ላይ ያነጣጠረ ሽያጮችን የመሳሰሉ ሌሎች sales (targeted to a small number of pre-
የፕራይቬታይዜሽን ስልቶችን መምረጥ selected corporate investors),If they are the
ይችላል፡፡ጠቀሜታቸው በበቂ ምክንያት የተደገፈ most appropriate for the circumstance,
ከሆነ ሂደቱም በተቻለ መጠን በግልጽነት መሆን provided there is a clear justification for
ይኖርበታል፡፡ their use and the process is carried out in as
transparent manner as possible.
፲፪ሺ፮፻፴፪
https://chilot.me 12632

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፬/ የፕራይቬታይዜሽን ስልቶች በተመለከተ 4/ Notwithstanding the privatization modality,
የተደነገገው ቢኖርም፣ ሚኒስቴሩ ከኤጀንሲው ጋር the Ministry, in consultation with the
በመመካከር ከሚሸጡት አክሲዮኖች ውስጥ Agency, shall decide if a portion of a
የተወሰኑት በመንግሥት የልማት ድርጅቱ Public Enterprise shares shall be reserved
ሠራተኞች ተለይተው የሚያዙበትን ሁኔታ እና for sale to the Public Enterprise employees
የአክሲዮኖቹን ዋጋና መጠን ይወስናል፡፡ including the amount of the share reserved
for employees and the price of each share,
፭/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት 5/ Pursuant to Article 4 sub-Article (1) of this
የፕራይቬታይዜሽን ሽያጭ የመንግሥትን Proclamation, privatization sales may
አክሲዮኖች መቶ በመቶ ወይም ከፊሉን ሊያካትት include hundered percent of the
ይችላል፡፡ Government’s shares or any portion of
shares thereof.

፮/ አብላጫውን ወይም ወሳኝ የሆኑ አክሲዮኖችን 6/ The Government may choose, in the case of
ሽያጭ በሚመለከት መንግሥት ወርቃማውን the sale of a majority or controlling
አክሲዮን ማስቀረትን መምረጥ ይችላል፡፡ ወርቃማ interest, to retain a golden share. A golden
አክሲዮን መንግሥት የሕዝብ ጥቅምን አያስጠብቅም share shall provide the Government
ብሎ ባመነበትን በማናቸውንም የቦርድ ውሳኔ ላይ with voting and veto rights over any board
ድምፅ የመስጠትና ድምፅን በድምጽ የመሻር resolution which it believes is not in the
መብት ያጎናጽፈዋል፡፡ public's interest.

፯/ የፍታብሔር ሕግ አንቀጽ ፩ሺ፯፻፶ ድንጋጌ 7/ Notwithstanding the provision of Article


ቢኖርም፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቱ የሽያጭ 1750 of the civil code, the price of the
ዋጋ የሚከፈለው በውሉ በተመለከተው ሕጋዊ enterprise shall be paid in the currency
ገንዘብ ይሆናል፡፡ specified in the contract.
፲፪ሺ፮፻፴፫ https://chilot.me 12633

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

ክፍል አምስት PART FIVE

ድህረ ፕራይቬታይዜሽን ታሳቢዎችና ግምገማዎች POST PRIVATIZATION CONSIDERATIONS AND


EVALUATION
፲. ድህረ ፕራይቬታይዜሽን የኢንቬስትመንት ታሳቢዎች
10. Post Privatization Investment Considerations
እና ግምገማዎች

፩/ የድህረ ፕራይቬታይዜሽን የኢንቬስትመንት 1/ Post-privatization investment obligations

ግዴታዎች የፕራይቬታይዜሽን ውሉ አካል maybe included in a privatization

ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ agreement when warranted.

፪/ የልማት ድርጅት ገዢ በውሉ በተመለከተው 2/ A purchaser of a Public Enterprise shall be

የጊዜ ገደብ ውስጥ እና በሽያጭ ውሉ obliged to implement, within the time

በተደረሰው ስምምነት መሠረት ማናቸውንም limit specified and as agreed in the sales

ድህረ ፕራይቬታይዜሽን ኢንቬስትመንት contract, any post-privatization


የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡ investment.
3/ The Agency shall monitor the execution of
፫/ ኤጀንሲው የድህረ ፕራይቬታይዜሽን
any post-privatization obligations.
ግዴታዎች አፈጻጸምን ይከታተላል፡፡
4/ The investor shall be obliged to
፬/ ባለሀብቱ የውል ግዴታዎችን ለመከታተል
periodically submit to the Agency
የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ለኤጀንሲው
information that is necessary for
በየጊዜው የማቅረብ እና የኤጀንሲው ተወካዮች
monitoring contractual requirements and
ቅድመ ዝግጀት በማድረግ በማናቸውም ጊዜ
to allow the representatives of the Agency
ወደ ተሸጠው የልማት ድርጅት እንዲገቡና
to enter and inspect the enterprise at any
ግምገማ እንዲያካሂዱ የመፍቀድ ግዴታ
pre-arranged time to make assessments.
አለበት፡፡

፲፩. ድህረ ፕራይቬታይዜሽን ግምገማ 11. Post Privatization Evaluation

፩/ ኤጀንሲው በፕራይቬታይዜሽን ክንውኑ ላይ 1/ The Agency shall commission an


ግምገማ የሚያካሂድ ገለልተኛ ባለሙያ independent expert to conduct an
በመሾም በግኝቶቹ ላይ ዓመታዊ ሪፖርት evaluation of the privatization
ማውጣት ይኖርበታል፡፡ transactions undertaken and issue an
annual report of its findings.
፲፪ሺ፮፻፴፬
https://chilot.me 12634

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th
፳፩
፪/ የግምገማው ሪፖርት የተላለፉና ቀሪ የሆኑ 2/ The evaluation report shall assess transfer
ወይም የተከፈሉ የመንግሥት ዕዳዎችን፣ or extinguishment of government
የመንግሥት ዋስትናዎች ያሉበትን ደረጃና liabilities, status of any government
ሌሎች ተያያዥ ዕዳዎችን፣ ወደ ግል guarantees and other contingent
በተዛወረው የመንግሥት የልማት ድርጅት liabilities, effects of the absence of
የመንግሥት ገንዘብ ያለመኖር ያስከተለውን government funding on privatized
ተፅዕኖ ወይም ውጤቶች፣ በግል ዘርፉ Public Enterprises, assessment of
ውጤታማነት መገምገም ይኖርበታል፡፡ efficiency gains realized by the private
እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች የግምገማ sector, and shall include other
መለኪያዎችን ማካተት ይኖርበታል፡፡ assessment measurement parameters as
necessary.
፲፪. ስለ ልማት ድርጅቶች መብትና ግዴታ መተላለፍ 12. Transfer of Rights and Obligations of
Public Enterprises
፩/ ወደ ግል የተዛወረ የመንግሥት የልማት
1/ A privatized Public Enterprise shall cease
ድርጅት በአክሲዮን ማኅበርነት እንደተመዘገበ
to exist upon the completion of registration
ህልውናውን ያጣል፡፡ የመንግሥት የልማት
of the share company. The rights and
ድርጅቱ መብቶችና ግዴታዎች በሽያጭ ውሉ
obligation of the Public Enterprise shall be
መሠረት ለገዢው መተላለፍ ይኖርባቸዋል፡፡
transferred to the buyer pursuant to the
sales contract.
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ
2/ Notwithstanding the Provisions of Sub-
ቢኖርም፣ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሣቦች ወደ
Article (1) of this Article, rights and
ገዢው እንደማይተላለፉ በሽያጭ ውሉ ውስጥ
obligations pertaining to receivables and
ስምምነት ከተደረገ ከዚሁ ጋር የተያያዙ
payables shall be transferred to the trustee
መብትና ግዴታዎች ወደ ባለአደራ
where the sales contract provides for the
ይተላለፋሉ፡፡
non-transferability of such receivables and
payables to the buyer.
፲፪ሺ፮፻፴፭ https://chilot.me 12635

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፫/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ (፭) 3/ The residual assets and liabilities
መሠረት ከሚኒስቴሩ ውሳኔ በኋላ ወደ አክሲዮን following the decision of the Ministry,
ማኅበርነት ወደ ተለወጠው የመንግሥት የልማት in accordance with Article 6 (5) of this
ድርጅት ከተላለፉት ሀብትና ዕዳዎች ላይ proclamation, on the transfer of assets
ዕዳቸው ተከፍሎ የቀሩ ንብረትና ዕዳዎች ወደ and liabilities of public enterprise being
ባለአደራ መተላፍ ይኖርባቸዋል፡፡ converted into a share company, shall be
transferred to the Trustee.
፬/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፪) 4/ The provision of Sub Article (1) and ( 2 )
ድንጋጌዎች በአዋጅ ቁጥር ፩፻፲/፲፱፻፹፯ of this Article shall similarly be
መሠረት በኤጀንሲው በተሰጠ ውሳኔ ለቀድሞው applicable with respect to the transfer of
ባለንብረቶች ለተመለሱ የመንግሥት የልማት rights and obligation of public
ድርጅቶች የሚተላለፉ መብትና ግዴታዎችን Enterprises returned to their former
በተመለከተ በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚ owners by the decision of the Agency
ይሆናሉ፡፡ Pursuant to Proclamation No 110/1995.

፭/ የመንግሥት የልማት ድርጅት ወደ ግል 5/ Employees' pension coverage existing


ከመዛወሩ በፊት የነበረ የጡረታ ሽፋን ሳይቋረጥ before the privatization of any enterprise
ይቀጥላል፡፡ የአዲሱ ድርጅት ባለቤት shall continue without interruption. The
የሠራኞችን ጡረታ በተመለከተ አግባብ ባላቸው new owner of a Public Enterprise shall
ሕጎች በአሠሪዎች ላይ የተጣሉትን ግዴታዎች respect employers' obligations imposed
ማክበር ይኖርበታል፡፡ by the appropriate laws with regard to
employees' pension.
፲፫. አለመግባባትን ስለመፍታት 13. Settlement of Disputes

፩/ በውላቸው ውስጥ በግልጽ በተመለከተ የግልግል 1/ Disputes arising between the Agency

ዳኝነት ሂደት ወይም አካል እንዲታይ and a buyer of a Public Enterprise

የተስማሙ ካልሆነ በስተቀር፣ በኤጀንሲውና shall be referred to the appropriate


በመንግሥት የልማት ድርጅት ገዢ መካከል Federal Court unless the parties have
የሚነሳ ክርክር የሚቀርበው ሥልጣን ላለው agreed in their contract to submit such
የፌደራል ፍርድ ቤት ይሆናል፡፡ disputes to a specific arbitration
process or tribunal.
፲፪ሺ፮፻፴፮ https://chilot.me 12636

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፪/ ተዋዋይ ወገኖች ክርክራቸው በግልግል ዳኝነት 2/ Where the parties have agreed to submit
አካል እንዲታይ የተስማሙ ከሆነ፣ የግልግል their disputes to an arbitration tribunal,
ሂደቱ በውሉና አግባብ ባላቸው የፍትሐብሔር the proceedings thereof shall be
ሕግና የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ conducted in accordance with the
ድንጋጌዎች መሠረት ይመራል ። provisions of their contract and that of
the Civil Procedure Code.
፲፬. ስለታክስ
14. Taxation
፩/ ታክስ የሚያርፍባቸውን ገቢዎች መወሰንን 1/ For the purpose of determining taxable
በተመለከተ የንብረት የእርጅና ቅናሽ ስሌት income, the calculation of depreciation
በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ መሠረት በተደረገው of assets shall be based on their
የልማት ድርጅቶች ዋጋ ግምት ላይ valuation done in accordance with
የተመሠረተ ይሆናል፡፡ ሆኖም የጨረታው ዋጋ Article 7 of this Proclamation; provided,
አነስተኛ ከሆነ ገዢው በከፈለው ትክክለኛ however, that it shall be based on the
ገንዘብ ላይ የተመሠረተ ይሆናል፡፡ actual amount paid by the buyer where
the tender price is lower.
፪/ ኤጀንሲው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) 2/ The Agency shall send to the concerned
መሠረት የተወሰነውን የንብረቶቹን ዋጋ ዝርዝር Tax Authority the breakdown of asset
ለሚመለከተው የታክስ ባለሥልጣን ማቅረብ values determined in accordance with
ይኖርበታል፡፡ Sub-Article 1 of this Article.

፫/ ኤጀንሲው ከንብረት ባለቤትነት ሰነድ ጋር 3/ The Agency shall also send to the
በተያያዘ የቀረጥ ቴምብር የተከፈለባቸውን concerned Tax Authority the
ለገዢው የተላለፉ ንብረቶች ዋጋ ዝርዝርንም breakdown of values of assets
ለሚመለከተው የታክስ ባለሥልጣን ማቅረብ transferred to the buyer and which are
ይኖርበታል፡፡ subject to the payment of stamp duty in
relation to documents of title to
property.
፲፪ሺ፮፻፴፯ https://chilot.me 12637

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

ክፍል ስድስት PART SIX


MISCELLANEOUS PROVISIONS
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
፲፭. ከፕራይቬታይዜሽን የተገኘ ገንዘብን ስለመጠቀም 15. Use of Proceeds from Privatization

ከፕራይቬታይዜሽን ከተገኘ ገንዘብ ላይ ለክንውኑ Any proceeds from privatizations shall be paid

የተደረገው ወጪ ተቀንሶ ቀሪው ገንዘብ ሚኒስቴሩ net of the costs of the transaction into an
በሚያስተዳድረው የኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ Industrial Development Fund Bank account
የባንክ ሂሣብ ተቀማጭ ይደረጋል፡፡ administered by the Ministry.

፲፮. የመተባበር ግዴታ እና የኤጀንሲው ኃላፊነት 16. Duty to Cooperate and the Responsibilities
of the Authority
፩/ ማንኛውም የፌደራል ወይም የክልል
1/ Any Federal or Regional Government Organ
መንግሥት አካል ወይም የመንግሥት
or Official shall have the duty to cooperate
ባለሥልጣን የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራሙን
in furnishing any information or rendering
በማስፈጸም ሂደት የሚጠየቀውን መረጃ ወይም
any assistance requested in the course of
ድጋፍ በመስጠት የመተባበር ግዴታ
implementing privatization transaction.
አለበት፡፡
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከተው 2/ Without limiting the generality stated in
አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ Sub-Article (1) of this Article, the time limit
ለኤጀንሲው የሚተላለፉ መረጃዎችና ለገዢዎች for furnishing information to the Agency
የሚሰጡ አገልግሎቶች የሚቀርቡበት የጊዜ and providing required services to buyers
ገደብ በኤጀንሲው ይወሰናል፡፡ shall be determined by the Agency.

፫/ ከባለቤትነት ማስረጃዎች፣ ከአገልግሎት ውሎች 3/ Time spent waiting for the buyer to comply
እና ከንግድ ፈቃዶች ዝውውር ጋር በተያያዘ with formalities in relation to the transfer of
ገዥው ፎርማሊቲዎችን ለማሟላት የሚያጠፋው title deeds, utility contracts and licenses
ጊዜ የጊዜ ገደቡን ለማስላት ታሳቢ shall not be considered for the purpose of
አይሆንም፡፡ calculating the time limit.

፲፯. ሕገወጥ ባለይዞታዎችን ስለማስለቀቅ 17. Eviction of Illegal Occupants

፩/ ወደ ግል እንዲዛወር የተደረገ የልማት ድርጅት 1/ A court to which an application of suit is


ሕንፃን ወይም ቅጥር ግቢን በሕገወጥ መንገድ lodged for the eviction of a person alleged
በመያዝ ርክክብ እንዳይፈጸም ያወከ ሰውን to illegally occupy the building or premises
ለማስለቀቅ የክስ አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ of a privatized Public Enterprise and impede
ቤት የይዞታውን ሕጋዊነት የሚያሳይ መከላከያ the handover thereof, shall, unless a
፲፪ሺ፮፻፴፰ https://chilot.me 12638

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

ካልቀረበለት በስተቀር በ፴ (ሰላሣ) ቀናት statement of defense showing the legality of


ውስጥ የማስለቀቂያ ትእዛዝ በመስጠት the occupation is submitted to it, issue and
ውሳኔውን ያስፈጽማል፡፡ enforce an eviction order within thirty (30)
days.
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ ከአዋጅ 2/ The provisions of sub-Article (1) of this
ውጭ ስለተወሰዱ ንብረቶች በወጣው አዋጅ Article shall also be applicable with respect
ቁጥር ፩፻፲/፲፱፻፹፯ መሠረት በኤጀንሲው ውሳኔ to the restitution of properties by the
ለቀድሞ ባለቤቶቻቸው በሚመለሱ ንብረቶችም decision of the Agency pursuant to
ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ሆኖም የይዞታውን Proclamation No. 110/1995 provided,
ሕጋዊነት የሚመለከት መከላከያ ተቀባይነት however, that any defense regarding the
አይኖረውም። legality of the occupation shall not be
entertained.
፲፰. የተሻሩ እና ተፈጻሚ የማይሆኑ ህጎች 18. Repealed and Inapplicable Laws

፩/ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል 1/ The Privatization of Public Enterprises

ለማዛወር በወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፮/፲፱፻፺፩ Proclamation No. 146/1998 (as amended)

(እንደተሻሻለ) በዚህ አዋጅ ተሽሯል። is hereby repealed.

፪/ ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም ሕግ፣ ደንብ 2/ No Law, Regulation, Directive or


መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሰራር በዚህ አዋጅ Practice shall, in so far as it is
በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት inconsistent with this Proclamation,
አይኖረውም፡፡ have force or effect in respect of matters
provided for by this Proclamation.
የ ፲፱. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ
19. Transitional Provision
ከዚህ አዋጅ መውጣት በፊት የመንግሥት
Any Existing contract related with
የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዛወር
privatization and issues which are not
በወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፮/፲፱፻፺፩
concluded under Privatization of public
(እንደተሻሻለው) መሰረት ከፕራይቬታይዜሽን
Enterprizes Proclamation No.146/1991
ጋር ተያይዞ ለተደረጉ ውሎችና ፍጻሜ ላላገኙ
(Amneded) shall remain enforce in respect of
ጉዳዮች የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ
this Proclamation.
ይሆናሉ፡፡
፲፪ሺ፮፻፴፱ https://chilot.me 12639

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

፳. ተፈጻሚነት ያለው ሕግ 20. Applicable Laws


፩/ ነባር ድርጅትን ለማስፋፋትና ለማሻሻል 1/ Modification, Expansion of priorly
ስለሚሰጡ ማበረታቻዎች እንዲሁም የውጭ existed enterprizes and also Foreign
ዜጎችና ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት መስክ citzens and investors who are render on
ስለሚሳተፉበት ሁኔታ ስለሚጠበቁላቸው መብቶች investment sectors obtain incentives and
አግባብነት ባላቸው ኢንቨስትመንት ሕጎች rights on the basis of appropriate
የተደነገጉት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች investment laws shall to effect on those
ወደ ግል በተዛወረላቸው ላይም ተፈጻሚ public Enterprises transfered into
ይሆናል፡፡ privatization .
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ቢኖርም፣ 2/ Notwithstanding the provision of Sub-
በኢንቨስትመንት ሕጉ ለሀገር ውስጥ ባለሀብት Article (1) of this Article, the definition
የተሰጠው ትርጉም ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም given to “domestic investor “ under the
መንግሥትንና የመንግሥት የልማት investment Proclamations does not
ድርጅቶችን አይጨምርም፡፡ include Government or public enterprise
for the purpose of implementation of
this Proclamation.
፳፩. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ 21. Effective Date
ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ This Proclamation shall come into force as
ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡ of the date of its publication in the Federal
Negarit Gazette.

አዲስ አበባ ሐምሌ ፫ ቀን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም.


Done at Addis Ababa On the 10th Day of July 2020.

ሳህለወርቅ ዘውዴ SAHLEWORK ZEWDE

PRESDIENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC


የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ
REPUBLIC OF ETHIOPIA
ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት
https://chilot.me 12640

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th
https://chilot.me 12641

gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፷ ሐምሌ ፫ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.60, July 10 2020 … page
th

You might also like