You are on page 1of 76

ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.

ማውጫ
ዕንቅፋትን ጥሶ ወደ ራእይ ጉዞ

- ከተግዳሮት ባሻገር ወደ ራእይ መስፈንጠር ................................................................. 3


• መግቢያ ..................................................................................................................... 3
ክፍል አንድ
• ችግሮችን የመርታት ርእይን የመጥረግ የኢኮኖሚ ጉዞ ............................................... 8
ክፍል ሁለት
• የፖለቲካው አዲሱ ተለምዶ (The New Normal) እና የብልጽግና ጉዟችን ................. 25

ክፍል ሦስት
• የውጭ ጉዳይና ዲፕሎማሲ ....................................................................................... 51

ክፍል አራት
• ማኅበራዊ ትሥሥርንና የሞራል ልዕልናን ማሳደግ........................................................ 61

ልሳነ-ብልፅግና
በየስድስት ወሩ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በአፋርኛ፣ በሶማልኛና በትግርኛ
እየተዘጋጀች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮችን
በመዳሰስ ትንታኔ ይዛ የምትቀርብ የብልፅግና ፓርቲ መጽሔት
2ኛ ዓመት ቅፅ1 ቁጥር 3 ሰኔ 2014 ዓ.ም
አዘጋጅ፡- በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ
አሳታሚ፡- የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት
አድራሻ፡- ፖ.ሳ.ቁጥር 80002/80012
ኢሜይል፡ ppinfo@prosperity.org.et
ዌብሳይት፡ https://prosperity.org.et
ፌስቡክ፡ https://wwwfacebook,com/ prosperity parttypage
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 1
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ዕንቅፋትን ጥሶ ወደ ራዕይ ጉዞ
ቅፅ 1 ቁጥር 3 ዕትም ልሳነ-ብልፅግና መጽሄት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በመዳሰስ ለንባብ በቅታለች፡፡ መጽሄቷ በውስጥ
ገፆቿ መጀመሪያው ክፍል “ችግሮችን የመርታት ራዕይን የመጥረግ
የኢኮኖሚ ጉዞ” በሚል ርዕስ ኢኮኖሚያዊ ነባራዊ ጉዳዮች ተዳሰዋል፣
“በሁለተኛው ክፍልም “የፖለቲካው አዲሱ ተለምዶ (The New Normal)
እና የብልጽግና ጉዟችን” በሚል ርዕስ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተቃኝተዋል፣
በሶስተኛው ክፍል የውጪ ጉዳይ ዲፕሎማሲ ከሀገራችንና ከዓለም
ተጨባጭ ወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር በስፋት ተዳሶ ቀርቧል፡፡ በአራተኛው
ክፍል ማህበራዊ ጉዳዮች ተካተዋል። በመጀመርያው የፓርቲያችን ጉባኤ
ከተቀመጡት አቅጣጫዎች መካከልም ትኩረት የተሰጣቸው ነጥቦች
ተለይተው በማጠቃለያው ጽሁፍ ተመላክተዋል፡፡

በመጽሄቷ የቀረቡት በርካታ ወቅታዊ ሁኔታዎችና መረጃዎች


የአመራሩንና አባሉን ግንዛቤ በማሳደግ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውስጥም
ሆነ ከውጪ ከገጠሟት ተግዳሮቶች ተላቃ የተቀመጠውን ርእይ ማሳካት
ለሚያስችሉ የለውጥ መሪዎች ስንቅ የሚሆኑ ቁምነገሮች የተካተቱባት
በመሆኑ እንዲያነቧትና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በተግባር ላይ
እንዲያውሉ ተጋብዘዋል፡፡

መልካም ንባብ!
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 2
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ከተግዳሮት ባሻገር ወደ ራዕይ መስፈንጠር

መግቢያ
ከምድር ወደ ሰማይ ከማየት ከሰማይ ወደ ምድር መመልከት
የተለየ ስሜትን ይፈጥራል። ለዚህ ነው ምድርን ከራሷ ከፍታ ጫፍ
ላይ ሆኖ መመልከት እጅግ አስደናቂ የሚሆነው። ይህን ድንቅ ውበት
ለመመልከት ብዙዎች ኤቨርስት ተራራንና ሌሎች በዓለም ላይ ያሉ
ከፍታዎችን በመውጣት ከጫፍ ለመድረስ ወደ እነዚህ አካባቢዎች
ይጓዛሉ። በሀገራችንም ብዙዎች የራስ ዳሸን ጫፍ ላይ በመውጣት
ዙሪያ ገባውን ለመቃኘት ከቅርብም ከሩቅም ይሰባሰባሉ። ነገር ግን
የተራራውን ጫፍ ለመውጣት የሚጓጉት፣ ያቀዱትና መውጣት
የጀመሩት ሁሉ ከራስ ዳሸን ወይም ከኤቨርስት ጫፍ መድረስ
አይችሉም። ከተራራው የከፍታ ማማ መድረስ የሚችሉት ፈተናን
በብርታት ማሸነፍ የሚችሉ ጽኑዎች ብቻ ናቸው። እነዚህ ጽኑዎች
ከተራራው ጫፍ ለመድረስ ሦስት ታላላቅ የፈተና እርከኖችን ማለፍ
ይጠበቅባቸዋል።

የመጀመሪያው ደረጃ “የጉጉት ሩጫ” ሊባል ይችላል። በዚህ ደረጃ


ኤቨረስትን መውጣት የሚያስገኘው ዓለም አቀፍ ዝና፣ ብዙዎች
ሞክረውት ያልተሳካላቸው እኔ ብቻ ነኝ እውን የማደርገው የሚል
ታላቅ የመሆን መንፈስ አለው። የተራራው ጫፍ በመውጣት ወደ
ታች በማየት ከተራራው ሥር የሚገኘው መልክዐ ምድር ውበት
የማየት ጉጉት፣ የማይሞከረውን በማሳካት የሚገኝ ስኬት ወዘተ.
የሚፈጥረው ተስፋና ያልተነካ ጉልበት የሚፈጥረው የማድረግ
ጉጉትና ታላቅ ተነሳሽነት ወደ ተራራው በተስፋ ተሞልተን
እንድንሮጥ ያደርገናል። ነገር ግን በመሮጥ የጀመርነው ጉዞ ትንሽ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 3
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ከፍ እያልን ስንመጣ፣ ከተግዳሮቱ ብዛትና ከልምድ እጦት የተነሣ፣


ራስን መጠራጠርና “ምን ሆኜ ነው?” ብለን መጠየቅ እንድንጀምር
ያደርገናል። ተራራውን መውጣት ይቻላል ወይ? ብሎ መጠራጠር
ይፈጠራል። ጽናት አልባ ሰው ከዚህ ደረጃ ተሻግሮ ወደ ሁለተኛው
መሄድ አቅቶት ይመለሳል።

ሁለተኛው ደረጃ “የመማርና ተስፋ ሰጭ ስኬት” ደረጃ ልንለው


እንችላለን። ይህ ደረጃ የሚመጣው የተራራውን ጫፍ ማግኘትና
ድላችንን ቁልቁል መመልከት የሚፈጥረው ታላቅ ጉጉትና ተነሣሽነት
ከመነሻው ከጠበቅነው መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የሚላተምበት
ነው። ተግዳሮቶች እየተፈራረቁ የሚፈጥሩት ፈተና እግራችንን
የሚያዝሉበት፣ ልባችን የሚደክምበት፣ በተራራው ከፍታ ኦክስጅን
አጥሮት በላይ በላዩ የሚተነፍሰው ሳንባችን ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ
የሚሆንበት ደረጃ ነው። ወደ ተራራው ያስወጣናል ያልነው መንገድ
መልሶ ወደ ታች የሚመልስበት፤ ዳገት ያስወጣናል ብለን የያዝነው
ቅርንጫፍ እየተገነጠለ ወደ ገደል የሚወረውርበት። የወንዙ ሙላት
አላሻግር የሚልበት፣ ደፍረን ስንሻገር ጎርፉ ሊወስደን የሚከጅልበት።
የተራራው ቤተኛ አውሬ እንዳይሰለቅጠን የምንሸሸግብት፣ እባብና
ጊንጡ ሊነድፈን እያሳደደ ዕረፍት የምናጣበት። ዝናብና ብርዱ
አጥንት እየሰረሰረ የሚዘልቅበት። በውኃ ጥማቱ ብርታት ጉልበት
የሚሰልልበት። ወደ ተራራው ጉዞ ስንጀምር አብሮ የነበረን
የሚርቅበት፣ ጽናት ያጣውም የሚመለስበት፣ ሰውነት መሄድ
አቅቶት የውስጥ እግር ውኃ የሚቋጥርበት፣ ድካሙና ረሃቡ
ከውስጥ፣ አውሬውና ተፈጥሮው ከውጭ ልክ ተራራው ላይ
የመውጣቱን ራእይ ለማደናቀፍ የተመካከሩ እስኪመስል ፈተናው
መከራው የሚበራከትበት ደረጃ ነው።

ሁለተኛው ደረጃ የነበረውን የተስፋ ጉጉት የሚያጨፈግግ ፈተና


የበዛበት ቢሆንም በጽናት ወደ ተራራው ጫፍ ጉዞውን የቀጠለ
አበረታች ድሎችንም የሚያገኝበት ነው። ሲጀምር የቆሳሰለው
እግር ጠግጎ፣ አዲሱን የተራራ መውጣት ጉዞ የሚለማመድበት፣
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 4
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

የደከመው ልባችን የሚለማመድበት፣ የተራራ ከፍታ የሚፈጥረውን


የኦክስጅን እጥረት ተቋቁሞ መተንፈስ የሚችል ሳንባ የሚፈጠርበት፣
በትንሽ ውኃና በአነስተኛ ምግብ ብዙ መጓዝና አቀበት መውጣት
የሚችል ሰውነት የሚፈጠርበት፣ ትግሉን የተለማመደ ፈተናዎች
የማይበግሩት አካላዊ ብቃት እየተገነባ የሚሄድበት ይህ የመማር
ደረጃ ነው። የወንዝ ሙላት ቢኖርም መዋኘት የምንለማማድበት፣
ሊበላን የሚቋምጠውን አውሬ አድነን ቆዳውን ልብስ የምናደርግበት።
ወደ ተራራው የሚወስደው ትክክለኛው መንገድ የትኛው እንደሆነ
በትክክል የምንለይበት፣ ከፈተናዎች ተምረን ወደ ተራራው ጫፍ
ለምናደርገው ግሥጋሤ በተግባር የተፈተነ ዐቅም የምንገነባበት ነው።

በሁለተኛው ደረጃ ትልቁ ጉዳይ በፈተናዎች ሳይሰላቹ፣


በማያባራው እንቅፋት ተስፋ ሳይቆርጡ መራመድን ነው።
ባስመዘገብናቸው ጅምር ድሎች የተራራውን ጫፍና የራዕያችንን
መዳረሻ ከሩቁ እያስተዋሉ ተስፋ የሚሰነቅበት ነው ሁለተኛው
ደረጃ። ተጨባጭ ፈተናን ያለፈ፣ ልምድ የቀሰመ እውቀት፣ ከራዕይ
ተስፋ ጋር የሚገናኙበት ነው።

ሦስተኛው ደረጃ “የድል ደረጃ” ነው። በቀደመው ጉዞ


በተማርናቸው ትምህርቶች ባገኘናቸው ልምዶች የመጨረሻውን
የተራራውን ጫፍ በመውጣት የሚገኝ የድል ደረጃ ነው። በሁለተኛው
የተራራ መውጣት ደረጃ የገጠሙንን ፈተናዎች አሸንፈን ወደ
ተራራው ጫፍ ደርሰን ስንወጣ የምናገኘው ነው። እዚህ ታላቅ
ደስታ አለ። ሐሴትና ፍሥሐ አለ። ከተራራው ጫፍ ላይ ሆኖ ወደ
ታች ተአምራዊ ውበት የተጎናጸፈውን መልክአ ምድር በማየት
ሐሴት ማድረግ አለ። የተወጣውንና የተወረደውን መከራና ችግር፣
መልካሙንና ክፉውን እያስታወሱ የተራራው አናት ላይ ሆኖ፣
ማድረግና ማሳካት የተቻለውን እያዩ መደሰት በታላቅ የድል ስሜት
መጀገን አለ። ከተራራው ጫፍ በመውጣት የተከፈለው ይህ ቀረሽ
የማይባል መሥዋዕትነትና ፈተናዎቹ ተረስተው የተገኘው ድል
ታላቅ የሐሴት ስሜት ይፈጥራል።
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 5
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

የተራራ መውጣት ሂደት ያለፍንበትንና መድረስ የምንሻበትን


የለውጥና የብልጽግና ጉዟችንን ይገልጻል። በለውጡ ዋዜማና
መጀመሪያ የነበረንን ታላቅ የለውጥ ስሜትና ተነሣሽነት
የመጀመሪያውን ደረጃ ይገልጸዋል። የነበረውን ፓራዳይም ማፍረስ
ከባድ ፈተና ነበር። እሥረኞችን መፍታት፣ ሚድያዎችን መክፈት፣
የፖለቲካ ምኅዳሩን ማስፋት...ወዘተ በፖለቲካ ውሳኔ በፍጥነት
የተከወኑ ናቸው። ኢኮኖሚ ውስጥ የነበሩ ከፍተኛ ችግሮች
እንዳይባባሱ ለማድረግ የተወሰዱ ርምጃዎች ነበሩ። ብድርን
የማሻሻል፣ የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት እና መሰል ርምጃዎች
ችግሮች እጅግ ሊባባሱ የሚችሉበትን ሁኔታ ያስቆሙ ነበሩ። ነገር
ግን የኢትዮጵያ ችግሮች በፖለቲካ ውሳኔዎች ወይም የነበረውን
ፓራዳይም በማፍረስ ብቻ የሚለወጡ አይደሉም። ዲሞክራሲያዊት
ኢትዮጵያን የመፍጠር ሂደት እሥረኞችን በመፍታት፣ ሚዲያዎችን
እንዲንቀሳቀሱ በማድረግና የፖለቲካ ምኅዳርን በማስፋት አንዳንድ
ርምጃዎች የሚጠናቀቅ አይደለም። እነዚህን የመጀመሪያ ደረጃ
ለውጦች አስፍቶ በጠንካራ መሠረት ላይ ማቆም አስፈላጊ ነበር።
የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ብልጽግና ለማረጋገጥ ነባር ችግሮች
እንዳይባባሱ ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም። ሰፋፊ የኢኮኖሚ
ማሻሻያዎችንና ጠንካራ የልማት እንቅስቃሴዎችን ማድረግን
ይጠይቃል። በአጠቃላይ ከተራራው ጫፍ ወይም ከችግሮቻችን
በላይ ከሆነው ከፍታ ላይ ለመድረስ ውሳኔዎችን ተቋማዊ የማድረግ
አዲስ የመደመርና የወንድም/እኅታማችነት ፓራዳይምን መፍጠር
ይሻል። ይህም የነባሩን ፖለቲካ መዛነፎች ነቅሎ አዲሱን ፓራደይም
ለመትከል ቁርጠኝነት እና ጽናትን የሚጠይቅ ሂደት ነው።

አዲሱን ፓራዳይም የመትከል ሂደት ተራራውን ከመውጣት


ሁለተኛ ሂደት ጋር ይመሳሰላል። በለውጥ ኃይሉ ዘንድ የገጠመው
መከፋፈል፣ የጁንታው የፀረ-ለውጥ ጥቃቶች ያስከተሉት ቀውስ፣
የተፈጥሮ አደጋዎች በዚህ ምእራፍ የሚገኙ ናቸው። እነዚህን
ሁሉ ፈተናዎች ተቋቁመን ማሳካት የቻልናቸው ጉዳዮች፣ ድሎቹና
ተግዳሮቶቹ ሁሉ የሁለተኛውን ደረጃ ይገልጻሉ። የተቋማት ግንባታ፣
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 6
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ዲሞክራሲን የመትከል እና የማጽናት ሥራዎች፣ ኢኮኖሚያዊ


ችግሮችን በማረም ዕድገቱን ለማስቀጠል የሚወሰዱ እርምጃዎች፣
በራሳቸው አድካሚና ጽናትን የሚጠይቁ ናቸው። በእነዚህ
እርምጃዎች ውስጥ እያንዳንዱን ችግር ደረጃ በደረጃ ለመውጣት
የሚደረገው ጥረት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈ ሲሆን፣ በፈተና
ውስጥ በጽናት ወደ ተራራው በመውጣት ድልን ማስመዝገባችን
ለቀጣይ ጉዟችን ስንቅ ነው።

አሁን የምንገኝበት ሀገራዊ ፈተናና ድሎቹ ከተራራው ጫፍ


ባንደርስም እያንዳንዱን ፈተና በማለፍ የሰነቅነው ድል የተደቀኑ
ችግሮችን ለመሻገር በሚያስችል ዐቅምና ጥንካሬ ላይ እንድንገኝ
ያደረገን ነው። ልምድ አካብተናል፣ ተቋማትን ገንብተናል፣
ፈተናዎቹም በዛው ልክ በዝተውብናል። መሻገር የምንችለው ልክ
ተራራውን ጫፍ እያየ በተስፋ እንደሚጓዘው ተራራ ወጪ ነው። እኛም
ያለፍነውን ዳገት እያደነቅን፣ ባስመዘገብናቸው ድሎች እየበረታን፣
ተስፋ በሚሰጠው ኃይል ፈተናን እየተቋቋምን፣ በከፍታችን ልክ
የብልጽግናን ጫፍ እያየን፣ በታላቅ ተስፋ፣ በፕራግማቲዝም ወደ
ላይ ወደ ማማው መውጣት አለብን። የርእያችንን ጫፍ እያየን
መጓዝ ስንችል የችግሮቻችንን ገመድ መፍታት የሚያስችል ዐቅማችን
እየጠነከረ ይመጣል። ከጫፍ ስንደርስ ለትውልዱ የምናስተላልፈው
የበለጸገች ሀገርን ነውና። ለዚያም ጽናቱ፣ ተነሣሽነቱና ዐቅሙ አለን።
በፈተናዎች መደራረብ በፍጹም መሰላቸት የለብንም፣ ምክንያቱም
እኛ ባለርእይ ትውልዶች፣ ታሪክ ሠሪ ኃይል እንጂ ታሪክ ተራኪ
ቆዛሚዎች አይደለንም።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 7
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ክፍል አንድ

ችግሮችን የመርታት ርእይን የመጥረግ የኢኮኖሚ ጉዞ

1.1. ፈተና ያልበገረው የኢኮኖሚ ስኬት

ጉዟችን የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ ነው። በሠላሳ


ዓመት ውስጥ ከዓለም ሃያ ኢኮኖሚዎች ተርታ መሰለፍ። በዐሥር
ዓመት ውስጥ ከአፍሪካ አምስት ጠንካራ ኢኮኖሚዎች መካከል
መሆን። በ2018 ዝቅተኛ የመካከለኛ ገቢ ዐቅም ላይ መድረስ ነው።
ይህንንም ለማድረግ የሚያስችል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምግብ ጥያቄ
ያከተመባት፣ ከቁስ የተሻገሩ የሕዝብ ፍላጎቶች የማይገደቡባት፣
ኢትዮጵያውያን ሕልማቸውን መኖር የሚችሉባት ምድር እንድትሆን
ሰፊ ሥራዎችን ሠርተናል። ግን ገና ረዥም ጉዞዎች ይቀሩናል።
ኢኮኖሚ ውስጥ የነበረውን ችግር መቅረፍ በሚያስችል መልኩ
መሠረታዊ የፓራዳይም ለውጥ በማድረግ ችግሮችን መቅረፍ፣
ዕድገትን ማስቀጠልና ከፍ ወዳለው የብልጽግና ደረጃ ለመድረስ
መልካም ውጤቶች የፈጠሩና ነገን በተስፋ እንድንራመድ የሚያደረጉ
ናቸው።

ለውጥ ሲመጣ የሀገራችን ኢኮኖሚ በማክሮ ኢኮኖሚ መዛበት


ችግሮች የሚፈተን ከፍተኛ የቁልቁለት ጉዞ ውስጥ ነበር። ለመሠረታዊ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 8
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሀገራዊ ጉዳዮች ወጪ ለማድረግ ኢኮኖሚው ዐቅሙ ጥያቄ ውስጥ


ገብቶ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ለሀገር ኢኮኖሚ ዋስትና ተደረገው
የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በምዝበራና በደካማ አፈጻጸም
የቆሙበት ጊዜ ነበር። “በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ የሀገር
ኢኮኖሚ ሀብት ማመንጨት ላይችል በመቆመበት ሁኔታ የብድሮች
የመከፈያ ጊዜ ደርሶ ችግሩን አባባሰው። ሀገራችንም በከፍተኛ
የብድር ጫና ውስጥ ከሚገኙ ሀገራት ተርታ ተሰለፈች። በዚህም
ሀገር ተጨማሪ ብድር መበደር ከማትችለበት ሁኔታ ላይ ደረሰች።
የሥራ አጥነት በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ፤ የዋጋ ግሽበት የዜጋውን
ትከሻ ተፈታተነ።

የኢኮኖሚ ችግሩ በለውጡ ማግሥት የደቀነው ፈተና በተከታታይ


ቀውስ የተፈተነችውን ሀገራችንን የማያራምድ ነበረ። ስለዚህም
በለውጡ አፋጣኝ ርምጃዎችን በመውሰድ፣ ተሟጥጠው የነበሩት እጀግ
መሠረታዊ ጉዳዮችን ለማሟላት እንኳን የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ
ሀብት ለማግኘት ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል። እነዚህ በአጭር ጊዜ
የተወሰዱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እና ኢኮኖሚያዊ ርምጃዎች
ኢኮኖሚውን በማስተንፈስ ውጤት ለማስመዝገብ ችለዋል። ከዚህም
ጋር ተያይዞ የብድር ጫና ማስተካከያ ማድረግ ያስቻለ ድርድር
ከለጋሽ ሀገሮች ጋር በማድረግ፣ ለሀገራችን ኢኮኖሚ እስትንፋስን
የሚሰጥ ትልቅ ውጤት መጥቷል።

ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዳይባባሱ ሲወሰዱ የነበሩ ፈጣን የለውጥ


ርምጃዎች፣ የመጀመሪያ ደረጃ ማስታገሻ ነበሩ። ይህንንም ተከትሎ
በለውጡ ዓመታት ኢኮኖሚውን ሲፈትኑ የነበሩትን ችግሮችን
ለማረም እና ዕድገቱን ለማስቀጠል የሚያስችሉ የኢኮኖሚ ሪፎርም
ሥራዎች ሲከወኑ ቆይተዋል። እነዚህ የሪፎርም ሥራዎች ሥር
የሰደዱ ችግሮችን ለማረም እና ቀጣይነት ያለውና የተረጋጋ ዕድገት
ለማስመዝገብ በሦስት ዋና ዋና ምሦሦዎች የተከፈሉ ናቸው።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 9
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሦስቱ ዋና ዋና ምሰሶዎች
1) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ
(የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ችግርን መቅረፍ፣ የዋጋ ንረትን
መቆጣጠር፣ የተረጋጋ የዕዳ ጫና ሁኔታ ማስፈን እና
የፋይናንስ አቅርቦትን ማሻሻል)፣

2) መዋቅራዊ ማሻሻያ
(የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፎች ማሻሻያ፣ የኃይል ዘርፍ
ማሻሻያ፣ የንግድ ማሳለጥና የሎጂስቲክስ ማሻሻያ፣
የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አመራርን ማስተካከልና
የፕራይቬታይዜሽን ሂደትን ማስጀመር)፣

3) የዘርፎች ማሻሻያዎች
(የግብርና፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የቱሪዝም፣ የማዕድን እና
ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች) ናቸው።

የሀገር ውስጥ ገቢንና የሸማቹን ዐቅም በማሳደግ የምግብ ዋስትናን


ለማሻሻል፣ የሥራ ፈጠራ ዐቅምንና የሥራ ዕድልን በማሳደግ ሥራ
አጥነትን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ፣ የማምረት ዐቅም
አጠቃቀምንና የግብአት አቅርቦትን በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን
ለማሻሻል፣ የሸቀጦች ዋጋን ለማረጋጋት፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ
ዐቅም ግንባታና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ፣ የግሉን ዘርፍ ሚናን
ለማጎልበት፣ የውጪ ንግድን ለማሳደግ፣ የገቢ ምርቶችን በሀገር
ውስጥ ምርቶች ለመተካትና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ
መሥራት፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ዋና ዋና ዓላማዎች
ነበሩ።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 10
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ማሻሻያዎቹ በአዲስ ፓራዳይም ኢትዮጵያ ያልተሟጠጠ


ከፍተኛ የመልማት ዕምቅ ዐቅም ያላት ሀገር መሆኗን በመገንዘብ፣
ኢኮኖሚው እያጋጠሙት ያሉትን ማነቆዎች በዘላቂነት ለመቅረፍና
የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማስቀጠል፣ የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የዘርፎች እና
የመዋቅራዊ ማሻሻያዎች ላይ የሚያተኩሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች
ተነድፈው የተተገበሩ ናቸው። ይህም በመሆኑ ማሻሻያዎቹ የተረጋጋ
ማክሮ ኢኮኖሚ በመፍጠር፣ የዘርፎችን ምርታማነትና ቅልጥፍናን
በማሳደግ፣ እንዲሁም ለመዋቅራዊ ችግሮች መፍትሔ በማመቻቸት
ውጤት አስመዝግበዋል።

ከተፈጠሩት ፈተናዎች አንጻር የሀገር በቀል የኢኮኖሚ


ማሻሻያው ሚና በተለይም የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን ከማስቀረት
አኳያ ከፍተኛ ነበር ማለት ያስችላል። ለማሳያነት በመንግሥት ገቢ
አሰባሰብ፣ በውጭ የዕዳ ጫና ቅነሳ፣ በተረጋጋ የገንዘብ ፖሊሲ፣
በማዕድን ዘርፍ፣ በውጤታማ እና ፍትሐዊ የብድር አቅርቦትና
ድልድል እንዲሁም በሌሎችም ጉዳዮች ዙርያ የተወሰዱ ርምጃዎች
ከፍተኛ ውጤት አስገኝተዋል። የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር
በሚደረገው ጥረት ለግሉ ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ተስፋ የሚጣልበት
ነው። ተያይዞም ባንኮች ከሚያቀረቡት ብድር ጀምሮ የግሉን ዘርፍ
የሚያነቃቁ ሥራዎች ተሠርተው ወጤት እያመጡ ናቸው።

በኢኮኖሚያዊ ለውጥና ማሻሻያ ውስጥ የተደረገው የብር ኖት


ለውጥ መፍጠር ለምንፈልገው ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት አስተዋጽዖ
ያደረገ ነው። የብር ኖት ለውጡ ከተለያዩ የሞኒተሪ ርምጃዎች
ጋር ተዳምሮ በባንክ ሥርዓት የሚዘዋወረው ገንዘብ እንዲጨምር
አስችሏል። ከዚያም በዘለለ ሕገ-ወጥነትን ለመቆጣጠር ትልቁ መሣሪያ
በመሆን አገልግሏል። ከባንኮች ውጪ ሲንቀሳቀስ ከነበረው በመቶ
ቢልዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ግማሽና ከዚያ በላይ የሚሆነውን
ወደ ባንክ ሥርዓት ለማምጣት ተችሏል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም
ለፋይናንስ ሥርዓቱ ማሻሻያ በተሰጠው ትኩረት፣ የባንኮች ዐቅም
በከፍተኛ ሁኔታ ያደገ ሲሆን፣ ይታይ የነበረውን የጥሬ ገንዘብ
እጥረት ለመቅረፍ ተችሏል።
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 11
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

በኢኮኖሚ ማሻሻያው ሂደት ትልቅ ለውጥ ከመጣባቸው ጉዳዮች


መካከል የመንግሥትን የሀገር ውስጥ ገቢ በማሳደግ የበጀት ጉድለትን
የማጥበብ ጥረት አንዱ ነው። በፊሲካል አፈጻጻም ረገድ በየበጀት
ዓመቶቹ የሚታየው የመንግሥት አጠቃላይ ገቢ በተለይም በታክስ
ገቢ ዕድገት፣ በመንግሥት ወጪ አጠቃቀም መሻሻል (በጦርነት
እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከታየበት መጨመር ውጭ)
እና በበጀት ጉድለት አሸፋፈን ጥሩ ውጤት ተመዝግቧል። በጥብቅ
የበጀት አፈጻጸምና በፊሲካል ጥብቅ ክትትል የተነሣ፣ የበጀት
ጉድለቱ እየጠበበ እንዲመጣና እና የተረጋጋ እንዲሆን አድርጓል።

ከወጪ ጋር ተያይዞ መንግሥትን ለከፍተኛ ብክነትና ወጪ


እየደረጉ የነበሩ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችና የመንግሥት የልማት
ደርጅቶች ወደ ውጤታማነት ተቀይረዋል። ታላላቅ ሀገራዊ
ፕሮጀክቶች ብልሽታቸው ተገምግሞ እንዲስተካከል በማድረግ፣
እንዲሁም በፕሮጀክቶቹ መዘግየት ምክንያት የተፈጠረውን ከፍተኛ
ፋይናንስ ኪሣራ በመሸፈን ፕሮጀክቶቹ ነፍስ ዘርተው ሊቆሙ
ችለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ ያደገው የፕሮጀክት
አፈጻጸም ዐቅም አዳዲስ ፕሮጀክቶች በአጭርና ቃል በተገባላቸው
ጊዜ ተጠናቀው ለኢኮኖሚው ተጨማሪ ዐቅም እንዲሆኑ ያስቻለ
ነው። በተጨማሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በተደረገው
ማሻሻያ ትርፋማና ከፍተኛ የፋይናንስ ዐቅም ያላቸው ሆነዋል።

ሌሎች የለውጥ ሂደቱን ውጤቶች ስንመለከት የውጪ ንግድ


ገቢ የቁልቁለት ጉዞው ተቀልብሶ በዘርፉ የተገኘው የተከታታይ
ዓመታት ከፍተኛ ዕድገት የሪፎርም ሂደቱ ሌላኛው ትልቁ ስኬት
ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሀገራችን የነበረባትን የብድር ጫና
በማቃለል፣ ኢኮኖሚው መጠነኛ መሻሻል ወዳለበት የብድር ደረጃ
እንዲገባ ለማድረግ ተችሏል። የውጭ ዕዳ ጫናን ከመቀነስ አንጻር
የእፎይታ ጊዜ የሌላቸውና በገበያ መር የወለድ መጠን የሚወሰዱ
ብድሮችን በመቀነስ፣ የዕዳ ስረዛና የመክፈያ ጊዜ ማራዘሚያ ድርድር
በማካሄድ እንዲሁም ከፍተኛ የዕዳ ክፍያን በመፈጸም ሀገራችን

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 12
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ከፍተኛ የብድር ጫና ካለባቸው ሀገሮች ተርታ እንዳትሰለፍ ሆኗል።

በግብርና፣ በማንፋክቸሪንግ፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፍ


ማነቆዎችን በማቃለል በሁሉም ዘርፎ መሻሻል ታይቷል። በተጨማሪ
በዲጂታል ኢኮኖሚ ረገድ ሰፊ መሠረት ተጥሏል። ለግብርና ዘርፍ
ተዋናዮች የሚሰጠው ድጋፍ በጥናት ላይ ተመሥርቶ እንዲሻሻል
በማድረግ የግብርና ምርታችን በአስተማማኝ ሁኔታ በተከታታይ
የሚያድግበት መንገድ እየተመቻቸ ነው። የማዕድን ሀብታችንን
መረጃ በማጠናቀርና ተደራሽ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት፣
የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ለሌሎች ዘርፎች ግብአት ለማቅረብ
አቅጣጫ ተይዞ በመሠራት ላይ ይገኛል። የቱሪዝም ዘርፍ ለውጭ
ምንዛሪ ምንጭ የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ ቱሪስቶችን
በተለያየ መልኩ ለመሳብ የሚያስችሉ ተግባራት በሰፊው በመከናወን
ላይ ይገኛሉ። እንዲሁም የምግብ ዘይት፣ ስንዴና የግብርና አግሮ
ፕሮሰሲንግ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት የመተካት
ስትራቴጅን በመከተል ሰፋፊ ሥራዎች በመሠራት ላይ ይገኛሉ።
በተጨማሪም የሀገር ውስጥ የሥራ ፈጠራንም ሆነ የውጭ ቀጥተኛ
ኢንቨስትመንትን በማበረታታት እስካሁን የተሠሩ የኢንዱስትሪ
ፓርኮች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ እንቅስቃሴዎች በመከናወን
ላይ ይገኛሉ።

በኢዲስ የፓራዳይም ለውጥ የተጀመረው ኢኮኖሚያዊ የብልጽግና


ጉዞ፣ በዘላቂነትና በጥራት መርሖ ላይ የቆመ ነው። ይህን በሚያሳካ
መልኩ ከልጆቻችን የተዋስናትን ኢትዮጵያ ጠብቀን ለማቆየት
በየዓመቱ በሚካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያን
አረንጓዴ ማልበስ የሚያስችሉ የችግኝ ተከላዎች ተከናውነዋል።

በአጠቃላይ እስከ አሁን ሲወሰዱ የቆዩት ጠንካራ የኢኮኖሚ


ማሻሻያ ርምጃዎች ኢኮኖሚውን ከነበረበት የቁልቁለት ጉዞ በመታደግ
እና በማነቃቃት መልካም የሚባል ውጤት አስገኝተዋል። በተለይም
የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራው ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ ካጋጠሙ
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 13
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ተግዳሮቶች አንፃር ሲታይ፣ ሲወሰዱ


የቆዩት ርምጃዎች እንዲሁም በዚህ ደረጃ ታቅዶ ርምጃዎቹ
ባይወሰዱ ኖሮ ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት አደጋ ይደርስ
ነበረ። ይሄን አደጋ ከመቋቋም ታልፎ መልካም የሚባሉ ውጤቶችም
ተመዝግበዋል።

በዘንድሮ በጀት ዓመት በለውጡ ማሻሻያዎች ተመርኩዘን


በሠራናቸው ጠንካራ ሥራዎች ኢኮኖሚው በጦርነት፣ ከማዕቀብና
ከዓለም አቀፍ ሁኔታው በሚነሡ ጫናዎች ውስጥ ቢያልፍም፣
ዕድገትን ከማሳየት አልቆመም። የመጀመሪያና የሁለተኛ ሩብ
ዓመት የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገትን መሠረት ተደርጎ የተሠራው
ትንበያ እንደሚያሳየው፣ ኢኮኖሚው ከአምናው በተሻለ በ6.6 በመቶ
እንደሚያድግ ይጠበቃል። ለዚህም በዋናነት በግብርናው ዘርፍ
የተገኘው የምርት ዕድገት ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል።

በዘርፉ በአንድ በኩል የመሬት አጠቃቀምን በማሻሻልና


በማስፋት፤ በሌላ በኩል የሜካናይዜሽን እና ግብርናን ማዘመን
ሥራዎችን በማጠናከር ከፍተኛ የግብርና ዕድገት ተመዝግቧል።
በቆላ አካባቢ እርሻና የበጋ እርሻን ጨምሮ በዓመት ሦስቴ ለማምረት
በሚደረጉ ሥራዎች የግብርና ዘርፉ መሻሻል አሳይቷል። የኩታ
ገጠም አስተራረስ ዘዴ በሰፊው እየተለመደ እንዲሄድ ሲሠራ የቆየ
ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከተገኘው ምርት ሰፊ ድርሻ የሚይዝ ነው።
ለማሳያ ያህል የበጋ ስንዴ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ
ልዩነት በማስመዝገብ በ2014 ዓ.ም በመጀመሪያው ዙር 405 ሺህ
62 ሄክታር በመሸፈን 16 ሚልዮን ኩንታል መሰብሰብ የተቻለ
ሲሆን፣ በሁለተኛው ዙር 208 ሺህ ሄክታር መሬት ለመሸፈን ታቅዶ
8.3 ሚልዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል። በአጠቃላይም በግብርና
ዘርፍ የታየው ውጤታማነት በዚሁ መጠናከር ከቻለ፣ ምርትና
ምርታማነትን በማሳደግ ከውጭ የሚገባን ምርት በሀገር ውስጥ
ምርት ለመተካትና የምግብ ዋስትና ችግርን በተገቢው ለመቅረፍ
የሚያስችል ነው።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 14
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

የማዕድን ምርትን መጠንና ጥራት በማሳደግ በዘርፉ የሚፈጠሩ


የሥራ ዕድሎችና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ የተለያዩ የዘርፉ
ማነቆዎችን የማሻሻል ሥራ ተሠርቷል። በመሆኑም በተደረጉ
ማሻሻያዎች የማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገትን በማስመዝገብ ለወጪ
ንግድ ዕድገት የላቀ አስተዋጽዖ አድርጓል። በተጨማሪም ለተለያዩ
የምርት ጥሬ ዕቃነት በሚፈለጉ ማዕድናት ዙሪያ የውጭ ጥገኝነትን
ለመቀነስ በርካታ ሥራዎች የተሠሩ ሲሆን፣ በዚህም ለሲሚንቶ
ፋብሪካዎች የሚውለውን የድንጋይ ከሰል በከፊል በሀገር ውስጥ
ለማሟላት ተችሏል።

የቱሪዝም ዘርፉን ስንመለከት የቱሪዝም መዳረሻዎች ሥራን


ከማሳደግ በተጨማሪ ዲያስፖራው ማኅበረሰብ ለገና እና ለዒድ
ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ መርሐ-ግብሮችን በማዘጋጀት፣ ተፋዝዞ
የነበረው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ሊነቃቃ ችሏል።

በየዘርፉ የተፈጠረውን የምርታማነት ዐቅም መጎልበት


ተከትሎ፣ የውጪ ንግድ አፈጻጸም 3.24 ቢልዮን ዶላር ደርሷል።
በዚህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ዘጠኝ ወራት መሻሻል
አሳይቷል። የመንግሥት ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምም ከዓመት ዓመት
መጨመር ታይቶበታል። ሌላው ትልቁ ስኬት የተለያዩ ተጽዕኖዎች
በተደራረቡበት በዚህ ወቅት እንኳን ፕሮጀክቶች ከተባለላቸው ጊዜ
ምንም ዓይነት መዛነፍ ሳያጋጥማቸው በመጠናቀቅ ላይ መገኘታቸው
ነው። ይህም ከለውጡ በፊት የነበረንን የሀብት ብክነት ማረም
ያስቻለ ነው።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 15
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

1.2. የገጠሙን ተግዳሮቶች


የኢትዮጵያ ብልጽግና ተራራ መውጣት ስንጀምር ከፊት የነበሩ
ችግሮችን በማንሣት መልካም ውጤት አስመዝግበናል። ነገር ግን
ተራራውን በመውጣት ሂደት የጠበቅነውና ያልጠበቅነው ችግሮች
አጋጥመውናል። ዳገቶቹ፣ ከፍ እያሉ ሲሄዱ አየሩ እና ሌሎች
ተመሳሳይ ጉዳዮች እንደሚያጋጥሙ ቢጠበቅም ከዚህም ውጪ
ድንገተኛ ክሥተቶች ጉዞውን ከባድ አድርገውታል። ያልተጠበቀ
ዝናብ እና አውሎ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳይታወቅ ከታቀደው
ውጭ ኢኮኖሚው ላይ ድንገቴና ተጨማሪ ፈተናዎችን ደቅኗል።

በጠንካራ ስኬቶቻችን ውስጥም እንደ ከፍተኛ ችግር ተደንቅሮ


የቆየው ኢኮኖሚያዊ ፈተና በዋናነት የዋጋ መናር እና ግሽበት
ነው። እነዚህ የኢኮኖሚ ፈተናዎች የሌሎች ኢኮኖሚያዊ ችግሮች
መገለጫዎች ሲሆኑ ፈተናዎችን ለመሻገር ችግሩን በሁለት መልክ
መመልከት ይገባል። የመጀመሪያው የችግሩን መሠረታዊ መነሻ
መመልከት ሲሆን በመሠረታዊ መነሻዎች ላይ ተደምረው የሚያባብሱ
ምክንያቶች ሁለተኞቹ ናቸው። በመሠረታዊነት የኢኮኖሚው ችግር
ከምርታማነት ጋር ተያያዥ የሆኑ በምግብ ራስን አለመቻል፣
አነስተኛ የቴክኖሎጂ ደረጃ፣ ደካማ ኢንቨስትመንትና መሰል ጉዳዮች
ናቸው። እነዚህ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ችግሮች ቀዳሚ ኢኮኖሚውን
ጎታች ሁኔታዎች ሲሆኑ ለዘመናት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጋር
ተያይዘው የቆዩ ናቸው።

ተጠባቂ የምንላቸው ችግሮ የኢኮኖሚ ሥርዓቱ መሠረታዊ


ችግሮች ናቸው። እነዚህ ችግሮች በመሠረታዊነት ኢኮኖሚውን
ሲፈትነው የቆየው የምርታማነት ችግር ነው። ይህ የምርታማነት
ችግር ከሥርዓት ስብራት የሚነሣ ሲሆን መንግሥት፣ የግሉ ክፍል፣
ሲቪክ ማኅበራትና መካነ ትምህርት ለኢኮኖሚው የሚኖራቸውን

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 16
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

አስተዋጽዖ እንደ ሥርዓት አጣምሮ መምራት ባለመቻሉ የሀገራችን


ኢኮኖሚ ከፍተኛ የምርታማነት ችግር የሚታይበት እንዲሆን
አድርጓል። ከለውጡ ቀደሞ በነበሩ ዓመታትም ኢኮኖሚው
በሥርዓት ስብራቱን መጠገን ባለመቻሉ በተከታታይ ዓመታት
የተመዘገበ የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት የሌለው እና ዘርፈ ብዙ
ችግሮች የሚስተዋልበት ነበር።

በመሆኑም በለውጡ በማክሮ ኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊና በዘርፍ


የተደረጁ ማሻሻያዎችን በመተግበር፣ ኢኮኖሚው የተጣቡትን
መዛነፎች በማረም፣ ለብልጽግና መንገድ ጥርጊያ መፍጠር ተችሏል።
ነገር ግን ወደ ብልጽግና ተራራ በመውጣት ሂደት ውስጥ መሠረታዊ
ችግሮችን በማረም ሂደት ድንገቴ የተባሉ ችግር አባባሽ ምክንያቶች
ኢኮኖሚው ላይ ተጨማሪ ጫናን ፈጥረዋል። የተፈጥሮ አደጋዎች
ጎርፍና ድርቅ፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችና ጦርነት፣ ኮቪድና
የዩክሬኑን ጦርነት ተክትሎ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት፣
በሀገራችን ኢኮኖሚ የብልጽግና ጉዞ ላይ ትልቅ ደንቃራን የፈጠሩ
ናቸው።

ምርት ደካማ በሆነበት እና በምግብ ራሳችንን ባልቻልነበት ሁኔታ


የዋጋ ንረት መኖሩ አይቀሬ ነው። ኢኮኖሚው በመሠረታዊነት
ያለበት የምርታማነት ችግር ለሌሎች ችግሮችና ሁኔታዎች ተጋላጭ
ያደርገዋል። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉና
የተፈጠሩ ኢኮኖሚ መነሻ ያላቸውና የሌላቸው ችግሮች ኢኮኖሚው
ባለበት መሠረታዊ ክፍተት ላይ ችግሮችን ያባብሳል፤ የኢኮኖሚውን
ጤናማነት ያውካል። ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታው፣ ፖለቲካዊ
አለመረጋጋትና ጦርነት፣ ኢኮኖሚያዊ አሻጥርና ሕገ-ወጥነት
እንዲሁም የተፈጥሮ አደጋ በኢኮኖሚው ላይ ጫና እያሳረፉ ያሉ
ጉዳዮች ናቸው።

በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ የተፈጠሩ ከፍተኛ የዋጋ ንረት እና


የሸቀጦች እጥረት በገቢ ምርቶች ላይ ጥገኛ በሆነው የሀገራችን
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 17
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ኢኮኖሚ ላይ የምርት እጥረት እንዲፈጠር እና የዋጋ ንረት


እንዲባባስ አድርገዋል። ኮቪድን ተከትሎ የጤና ቀውሱን ለመቀነስ
በተወሰደው በቤት የመቀመጥ ርምጃ ፋብሪካዎች ተዘግተው
የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴዎች ታግደው በምርት እና
በአቅርቦት ሠንሰለት መስተጓጎልን ፈጥረው ነበር። ማምረቻዎች
ተዘግተው ምርት ሳይመረት በመቅረቱ ወይም የሚመረትበት ዐቅም
በመቀነሱ፣ እንዲሁም ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ባለመዘዋወሩ
በዓለም ላይ ከፍተኛ የምርት እጥረት ተከሥቷል። ይህ የምርት
እጥረት ባለበት ሁኔታ፣ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት የተረጨው
ገንዘብ የሰዎች የመግዛት ዐቅምን ጨምሮ በአነስተኛ ምርት ላይ
ሰፊ የመግዛት ፍላጎት እንዲፈጠር አድርጓል። ይህም ዓለም ላይ
ለተፈጠረው የዋጋ ግሽበት መንሥኤ ነው።

የኮቪድ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሳያባራ የተፈጠረው የሩስያ-ዩክሬን


ጦርነት በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጠንካራ በትሩን ያሳረፈ ነው። ሀገራቱ
ከፍተኛ የሰብል ምርት አምራች፣ የጋዝና የነዳጅ ከፍተኛ አቅራቢ
ከመሆናቸው፣ በአጠቃላይም በዓለም ኢኮኖሚ ካላቸው ቦታ የተነሣ፣
ጦርነቱ በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ያሳደረው ጫና ቀላል የሚባል
አይደለም። የጦርነቱ ባህሪም ቅይጥና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊ
ግንባሮችን ያዘለ እንደመሆኑ፣ የኃያላኑ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ጦርነት
በዓለም ኢኮኖሚም ሆነ በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ እየፈጠረ ያለው
ተጽዕኖ ቀላል አይደለም።

የምግብ ሸቀጦች፣ ነዳጅ፣ ማዳበሪያን የመሳሰሉ ሀገራችን በውጭ


ገበያ ላይ ጥገኛ የሆነችባቸው ምርቶች በቅርብ ዓመታት ታይቶ
በማይታወቅ ሁኔታ ጨምሯል። ነገሩን ይበልጥ ከባድ የሚያደርገው
ደግሞ ጦርነቱ ተባብሶ በዚሁ ከቀጠለ የምርት ዘመኑ ስለሚያልፍ
በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሰብል በተለይም የስንዴ ምርት እጥረት
ይበልጥ መባባሱ አይቀርም።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 18
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

1.3. ውጤትን ማጠናከር፤ ተግዳሮትን ማረም


ኢኮኖሚ በአንድ ሥርዓት ውስጥ ተናጠላዊ ደሴት አይደለም።
በሥርዓት ውስጥ ባሉ ሌሎች ንዑስ ሥርዓቶች እንዲሁም ዓለም
አቀፍ ሁኔታ ተጽዕኖ ይደረግበታል፤ ተጽዕኖም ያደርጋል። የፖለቲካ
ሥርዓት ለውጥ፣ መረጋጋት አለመረጋጋት፤ የጤና እና ሌሎች
ሀገራዊ ሁኔታዎች ክሥተቶች፣ ዓለም አቀፍ ክሥተቶችና ለውጦች
እና ሌሎች ሁኔታዎች በኢኮኖሚው ላይ ተጽዕኗቸው የላቀ ነው።
በእነዚህ ኢኮኖሚያዊ ከሆኑ ሁነቶች ውጪ የሚከሠቱ ክሥተቶች
ኢኮኖሚውን ድንገቴ እና ኢ-ተገማች በሆነ ለውጥና ጫና ውስጥ
እንዲያልፍ ያስገድዱታል።

የአንድ ኢኮኖሚ ጥንካሬ የሚለካው እነዚህ ድንገቴ ክሥተቶች


በሚያሳድሩበት ጫና ውስጥ በሚያልፍበት ጊዜ ነው። ይህ ዓይነቱ
የኢኮኖሚ ጥንካሬም በመሠረታዊነት በሦስት ጉዳዮች የሚለካ ነው።
የመጀመሪያውና ቀዳሚው መቋቋም ነው። በተጽዕኖዎቹ ሊደርሱ
የሚችሉ ጉዳቶች የተገደቡ እና አነስተኛ መሆን ነው። ተጽዕኖዎቹ
ከኢኮኖሚው ጥንካሬ በልጠው ሊሰብሩት የሚችሉ አለመሆናቸው
መቋቋምን የሚያመለክት ነው።

ሌላው ማገገም ነው። ኢኮኖሚው ከደረሰበት ተጽዕኖ


ተነቃቅቶ ወደ ነበረበት ቁመና የመመለስ ዐቅሙን የሚያመለክት
ነው። በጫናዎቹ ምክንያት የተፈጠሩ ሥራ-አጥነቶች፣ የዕድገት
መቀዛቀዞች፣ የኑሮ ውድነቶች ወደ ቦታቸው የሚመለሱበት ፍጥነት
ማገገምን ያመለክታል። ሦስተኛው ይበልጥ መጠናከር ነው።
ኢኮኖሚው ከደረሰበት የኢኮኖሚ ተጽዕኖ በማገገም ወደ ቀድሞ
ቦታው ከተመለሰ በኋላ ተጨማሪ ዕድገቶችን እና ከቀውስ በኋላ
የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም፣ ወደ ከፍተኛ ዕድገት
መጠናከሩን የሚያመለክት ነው።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 19
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

የሀገራችን ኢኮኖሚ በተከታታይ ተጽዕኖዎች ውስጥ


ቢያልፍም፣ አስቀድመን በለውጡ በተደረጉ ማሻሻያዎች ላይ
በሠራናቸው ኢኮኖሚውን የሚያጠናክሩ ሥራዎች ጫናዎችን
መቋቋም፣ ከጫናዎቹ ማገገም እና ኢኮኖሚው ይበልጥ መጠናከር
የሚችልበትን መልካም ውጤቶችን አስመዝግበናል። ምንም ያህል
ችግሮች ቢጠምዱንም ዓይናችንን ከመዳረሻችን ሳንነቅል የሕዳሴ
ግድብ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ከሚችለበት ደረጃ ደረስናል።
የስንዴ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድገናል። ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን
አጠናቅቀናል። በአጠቃላይ በጫናዎች ሳንበገር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ
ውጤቶችን አስመዝግበናል።

ይህ ጠንካራ የኢኮኖሚ ጉዟችን ከብልጽግና ጫፍ ለመድረስ


አመልካች እና ልምድ የቀሰምንበት ነው። በመሆኑም መልካም
ውጤቶችን በማጠናከር እና ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ በዓለም
አቀፍ ሁኔታው መዛባት ምክንያት ሊመጣ የሚችልን ተጽዕኖ ከአሁኑ
ተገንዝቦ መሥራት ያስፈልጋል። የብልጽግና ጉዞ መሠረታዊ የሆኑ
የኢኮኖሚ ችግሮችን በመቅረፍ የሕዝብን ፍላጎትና ጥያቄ መመለስ
ነው። የኢኮኖሚውን መሠረታዊ ችግሮች በመቅረፍ ኢትዮጵያን
ከዓለም ቀዳሚ ኢኮኖሚዎች ተርታ ማሰለፍ ነው። በዚህም አካሄዳችን
በመሠረታዊነት የኢኮኖሚውን ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ
አቅጣጫዎች ላይ ቢሆንም፣ በተጓዳኝ ሕዝብን ለምሬት እየዳረጉ ያሉ
አባባሽ ምክንያቶችን በመቅረፍና የሚያደርሱትን ተጽዕኖ በመቀነስ
ላይ የሚያተኩር ነው።

በመሆኑም፡-
• የግብርናን ምርታማነት በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል
የምናደርገውን ጥረት ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ
በትኩረት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል። የግብርናውን ዘርፍ
ለማሳደግ በበጋ ስንዴ ልማት ዙሪያ የታየውን የፖለቲካ
ቁርጠኝነት በመኸር ወቅት በመድገም ከፍተኛ ለውጥ
እንዲመጣ መትጋት ያስፈልጋል። የበልግ ወቅት ምርትና
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 20
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ምርታማነትን ለመጨመር ትኩረት ተሰጥቶት መሠራት


አለበት። አመራሩ እታች ድረስ በመውረድ የኩታ ገጠም
እርሻ እንዲስፋፋ እንዲሁም የገበሬው የውኃና የመስኖ
አጠቃቀም እንዲሻሽል ማድረግ ያስፈልጋል። በኩታ
ገጠም ማሳዎች ላይ የሚስተዋለውን የግብአት አጠቃቀም
ልዩነቶች፣ የዘር ወቅት ያለመመሳሰል፣ እንዲሁም አርሶ
አደሩ ለኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ ያለውን አመለካከት
በአግባቡ ፈትሾ ከወዲሁ ተገቢውን የእርምት ርምጃ መውሰድ
ይገባል። በተጨማሪ ከማዳበሪያ ዋጋ መወደድ ጋር ተያይዞ
ሊኖሩ የሚችሉ ክፍተቶችን በሚሞላ መልኩ፣ አርሶ አደሩ
የተፈጥሮ ማዳበሪያን በስፋት እንዲያዘጋጅና ጥቅም ላይ
እንዲያውል በቂ ክትትልና ድጋፍ ማደረግ ወሳኝ ነው።

• ለአምራች ኢንዱስትሪዎች አቅም መጎልበት የምንሰጠው


ትኩረት የመጀመሪያ ግቡ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ
እየወጣባቸው ያሉ ነገር ግን በትንሽ ጥረት ንጽጽራዊ አቅም
ሊፈጠርባቸው የሚችሉ እንደ ምግብ ዘይት፣ አልባሳት፣ ቆዳና
የቆዳ ውጤቶችን፣ የተቀነባበሩ ምግቦችና የአግሮ ፕሮሰሲንግ
ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት አላማ ያለው መሆን
አለበት። የግሉ ዘርፍ በተለይም የግብርናና ግብርና-ነክ
ምርቶችን በጥሬ እቃነት የሚጠቀሙ መካከለኛ አምራች
ኢንተርፕራይዞች ላይ አተኩሮ መስራት የሚጠቅመው
የገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ የመተካት ግባችንን ለማሳካት
የሚያግዙን ቁልፍ ዘርፎች በመሆናቸው ነው። ለእነሱ
የቢዝነስ ከባቢያዊ ሁኔታን ከማሻሻል እና አላስፈላጊ
ቢሮክራሲን ከማስወገድ ባለፈ የብድር አቅርቦት ማሻሻያዎችን
ማድረግ ይገባል። የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት
በሚደረገው ጥረት የተማሪዎችን ዩኒፎርም እና ቦርሳ በሀገር
ውስጥ የማምረት ሀገራዊ ተነሣሽነት (ኢንሼቲቭ) ሆኖ ወደ
ክልሎች እና ወደ ከተማ አስተዳደሮች እንዲወርድ የማድረግ
ሥራ መከወን አለበት።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 21
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

• የማዕድን ዘርፉ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት አንዱ ቀላል መንገድ


ከመሆኑ ባለፈ የኢኮኖሚ እድገታችንን ለማፋጠንና መዋቅራዊ
ሽግግር ለማምጣት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ትኩረት
ሰጥተን ልንሰራበት ይገባል። ለአምራች ኢንደስትሪዎቻች
እና ለግንባታ ዘርፉ በጥሬ እቃነት የሚያገለግሉ ወሳኝ የሆኑ
ግብዓቶችን የሚያመርት ዘርፍ ነው። ከዚህም በተጨማሪ
በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምናስገባቸውን የግብርና
ማዳበሪዎች በሀገር ውስጥ ለመተካት በምናደርገው ጥረትም
የማዕድን ዘርፉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም።

• አረንጓዴ ዐሻራ ቀጣይ መርሐ ግብርን በማስፋት የዘላቂ


ብልጽግና ሂደታችንን ማጠናከር። ከሀገራችን ተሻግሮ ጎረቤት
ሀገራትን ጭምር ባሳተፈ መልኩ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ
ኢትዮጵያን አረንጓዴ ለማልበስ በስኬት መሥራት አለብን።

• የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሦስተኛውን ሙሌት የሚያከናውንበትና


ሁለተኛውን ተርባይን የሚተከልበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ
ይገኛል። በመሆኑም በዚህ የሁሉንም ትኩረት በሚሻ ወቅት
ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን ተከላክሎ፣ የጸጥታ ችግሮችን
መክቶ፣ አስፈላጊውን ሀብት በማፍሰስ፣ ወሳኙ ምእራፍ
በድል እንዲጠናቀቅ ማድረግ ዓይናችንን የማንነቅልበት
ጉዳይ ነው።

• በቱሪዝም የተጀመሩ መልካም ተሞክሮዎችን ማለትም


በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ወደ
ሀገር እንዲገቡ በቀጣይ ማበረታታት ውጤታማ ያደርጋል።
የቱሪስት መዳረሻዎችን የመሠረተ ልማት አውታሮችን
በማስፋትና በማዘመን በኩልም የተጀመሩ የገበታ ለሀገር
ሥራዎች በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ
አመራሩ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ አለበት።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 22
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

• የመንግሥት ገቢን ለማጠናከር ከታክስና ታክስ ነክ ካልሆኑ


ምንጮች የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ መልካም አፈጻጸሞችን
ማስቀጠልና፣ የታክስ ማጭበርበር፣ የታክስ ሥወራና ሌሎች
ብልሹ አሠራሮችን መፍትሔ ለማበጀት በትጋት መሥራት
ያስፈልጋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም በመጪው የግብር
መሰብሰቢያ ወቅት በቀልጣፋ አሠራር እና ከማጭበርብርና
ከብልሹ አሠራሮች ለመሰብሰብ በሚያስችል መልኩ
መንቀሳቀስ ትኩረት ይሻል። ኮንትሮባንድ የሚካሄድባቸውን
ቦታዎች መለየት እና አስፈላጊውን ርምጃ መውሰድ ከዚሁ
ጋር ተያይዞ ከፌዴራል እስከ ክልል ድረስ በጋራ ሊሠራበት
የሚገባ ጉዳይ ነው።

• በተቀረው በጀት ዓመት የመንግሥትን ወጪዎች በተቻለ


መጠን ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ጉዳዮች ብቻ ማዋል
ያስፈልጋል። በተጨማሪም በዓመቱ መጨረሻ የሚታዩ
አላግባብ እና የይድረስ ይድረስ የወጪ አጠቃቀሞችን
ማስተካከል ይገባል።

• የዋጋ ንረትና ግሽበትን በተመለከተ የምርት አቅርቦቶችን


በተቻለ መጠን ማስፋት እንዲሁም የግብርናውን ምርትና
ምርታማነትን በማሳደግ በከፍተኛ መጠን እያደገ የመጣውን
የዋጋ ግሽበት /በተለይም በምግብ አቅርቦት ላይ/ ለመቀነስ
አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ማስቻል ዋነኛው ትኩረት ነው።
የገንዘብ ፖሊሲው ላይ ተጨባጭ ሥራዎችን መሥራት
ማለትም ወደ ገበያው የሚለቀቀውን የገንዘብ መጠን
መቆጣጠርና የወለድ መጠንን የማሻሻያ አማራጮቸን
ማየት፤ የተንዛዛውን የገበያ ሠንሰለት በመቀነስ ቀጥታ
ከአምራች ወደ ተጠቃሚ የሚደርስበትን መንገድ ማስፋት
አብሮ ሊታይ ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ ላልተገባ የዋጋ
ጭምሪ የሚዳርጉ ሕገ ወጥነቶችን ለመከላከል አመራሩ
ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል።
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 23
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

• ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መናሩን ተከትሎ ከፍተኛ የበጀት


ጫና ማስከተሉ የማይቀር ነው። በመሆኑም የኮንትሮባንድ
ንግዱ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ እና ኅብረተሰቡ በነዳጅ
አጠቃቀም ቁጠባ እንዲያደርግ ከወዲሁ አስፈላጊው ዝግጅት
መደረግ አለበት።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 24
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ክፍል ሁለት

2. የፖለቲካው አዲሱ ተለምዶ (The New Normal)


እና የብልጽግና ጉዟችን
በአዲስ ራእይ ጉጉትና ተስፋ ተሞልቶ የሚጀመረው ብልጽግናን
የማረጋገጥ የአቀበት ጉዞ፣ ከውስጥና ከውጭ ከሚደቀኑበት
ተግዳሮቶችና አደናቃፊ ፈተናዎች እየተሻገረ፣ ድሎቹ የሚሰጡትን
ተስፋ እየጠበቀ፣ የሚሄድበት ተስፋና ሥጋት መሳ ለመሳ ሆነው
የሚገኙበት፣ ደረጃ ላይ እንገኛለን። በዚህ የለውጡ የብልጽግና ዕድገት
ደረጃ የሚጋረጡብንን ፈተናዎች ተጋፍጦ አሸንፎ መውጣት፣
ከስሕተቶቻችን መማር ብቻ ሳይሆን ልንቀይራቸው የማንችላቸው
የዓለም ተፈጥሯዊ ነባሪዎችን አዝማሚያዎችንንና ለውጦችን
በአግባቡ ተረድቶ፣ ከተለወጠው ሁኔታ ጋር የሚላመድ ገቢር ነበብ
አካሄድን መከተል ይጠይቃል። ከዚህ አኳያ ልንመለከተውና የጋራ
መረዳት ፈጥረን ልንቀሳቀስበት የሚገባው ጉዳይ የመረጃ ቴክኖሎጂን
ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጋር አጣምሮ ለማስኬድ የሚደረገው
ጥረት የሚፈጥራቸውን አዳዲስ የፖለቲካ ተለምዶዎች ወይንም
የፖለቲካው አዲሱ ተለምዶ (The New Normal) የምንለውን
ነው።

አዲሱ ተለምዶ (The New Normal) የሚለው ጽንሰ ሐሳብ


ቀደም ብሎ በተለያዩ ተቀራራቢ አገላለጾች ሲቀርብ የነበረ ሐሳብ
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 25
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ቢሆንም አሁን ባለው ትርጓሜ መገለጽ የጀመረውና በተለያዩ


ጉዳዮች ጥቅም ላይ የዋለው የኮሮና ቫይረስን ተከትሎ በመጣው
አዲስ ዓይነት የሰዎች አኗኗር ምክንያት ነው። በኮሮና ምክንያት
የተከሠቱ የአኗኗር ለውጦች ጊዜያዊ ሳይሆኑ ተላምደናቸው ልንኖር
ግድ የሚሉን አዳዲስ የሕይወት እውነታዎች ናቸው በሚል የቀረበ
ሐሳብ ነው። ይህም ማለት ኮሮና ሄዶ ወደ ቀደመ ሕይወታቸው
ለመመለስ ሲመኙ የነበሩ የሰው ልጆችን ከዚህ በኋላ ወደ ቀደመው
ሕይወት መመለስ አይቻልም፤ ከአዲሱ እውነታ ጋር እንዴት
ተላምደን መኖር እንችላለን? የሚለውን ማሰብ ይበጃል የሚል
ዕይታ ነበር። ይህ ሐሳብ ቀደም ብሎ በፖለቲካው ዓለም አዲሱ
ሥርዓት (The New Order) በሚል ከሚቀርበው ጽንሰ ሐሳብ ጋር
ተቀራራቢነት ያለው ነው። ጽንሰ ሐሳቡ የሚነግረን ትልቅ ቁም ነገር፣
በሕይወታችን ቶሎ መጥተው ቶሎ የሚሄዱ ሰሞንኛ ክሥተቶችን
እና በአንጻራዊነት አብረውን ሊቆዩ የሚችሉ ሁኔታዎችን በአግባቡ
መለየት፣ ከአዲሱ እውነታ ጋር ራስን አግባብቶ ለመኖርና በአዲሱ
እውነታ ውስጥ አሸንፎ ለመውጣት እንደሚጠቅም ነው።

አዲስ ተለምዶዎች በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ በየዘመናቱ


ሲከሠቱ ኖረዋል። በአንድ በኩል ለውጦቹ የአንድ ሰሞን ጉዳይ
መስለዋቸው ወደ ቀደመው ሕይወታቸው ለመመለስ ሲጠብቁ የነበሩ፣
በሌላ በኩል ደግሞ ከአዲሱ ነባራዊ እውነታ ጋር ተላምደው ለመኖርና
በአዲሱ እውነታ ውስጥ ሕልማቸውን ለማሳካት ሲጥሩ የነበሩ ሰዎች
በታሪክ ውስጥ አልፈዋል። ወረርሽኞች፣ አብዮቶች፣ ጦርነቶች፣
ወዘተ. በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ አዲስ ተለምዶዎችን የመፍጠር
ዐቅም አላቸው። ሆኖም በክሥተቶቹ ምክንያት የሚመጡት የአኗኗር
ለውጦች በጥቃቅንና በመለስተኛ ጉዳዮች ላይ ከሆነ፣ አጠቃላይ
ሕይወታችንን የተመለከተ ለውጥ ስለማይኖር አዲስ ሥርዓታዊ
ተለምዶ አይኖርም። ሆኖም ክሥተቶቹ የሚፈጥሩት ለውጥ ሰፊና
መሠረታዊ የዓይነት ለውጥ ከሆነ የሰው ልጆች አጠቃላይ አኗኗር
ስለሚለወጥ፣ አዲስ ሥርዓታዊ ተለምዶዎች ይፈጠራሉ።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 26
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ከፊውዳሊዝም ወደ ካፒታሊዝም የተደረጉ ለውጦች፣


ከአምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲ የተደረጉ ሽግግሮች፣ የኢንፎርሜሽን
ቴክኖሎጂ መምጣት... ወዘተ አዲስ ተለምዶዎችን ፈጥረዋል።
ለምሳሌ:- በፊውዳሊዝምና በካፒታሊዝም ሥርዓቶች ውስጥ
ያለው የሰው ልጆች አኗኗር በእጅጉ የተለያየ ነው። በአምባገነን
እና በዴሞክራሲ ሥርዓቶች ውስጥ ያለው የሰው ልጆች አኗኗርም
በእጅጉ የተለያየ ነው። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምጣትን
ተከትሎ የመጣው የሰው ልጆች አኗኗርም ከቀደመው ተለምዶ
ፈጽሞ ይለያል።

በኢትዮጵያ አሁን ያለው አኗኗርና እውነታ ከቀደሙት ጊዜያት


በእጅጉ የተለየ በመሆኑ፣ በአዲስ ተለምዶ ውስጥ ነው ያለነው ማለት
ይቻላል። ይህንን አዲስ ተለምዶ የፈጠሩት ሁለት ጉዳዮች ናቸው።
እነርሱም፡- ሀገራዊ ለውጡ የፈጠረው የዴሞክራሲ ሥርዓት እና
ዓለም አቀፍ ለውጥ የፈጠረው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ናቸው።

2.1. ዴሞክራሲ እና የውጥረት ፖለቲካ


የዴሞክራሲ ሥርዓት በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ አዲስ
ልምምድንና የአኗኗር ዘይቤን የሚፈጥር በመሆኑ አዲስ ተለምዶ
ነው ማለት ይቻላል። የዴሞክራሲ ሥርዓት በተፈጥሮው ኃይል
(power) ያልተማከለበት በመሆኑ በውጥረት የተሞላ ሥርዓት
ነው። ይህም ማለት የሰው ልጆች ከቀደሙት ሥርዓቶች ወደ
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሲሸጋገሩ የሚጋፈጡት አንድ እውነታ አለ።
እርሱም ውጥረት አዲሱ ተለምዶ መሆኑ ነው። ዴሞክራሲያዊ
ባልሆኑ ሥርዓቶች ኃይል በአንድ ቦታ የተከማቸ በመሆኑ
በአመዛኙ ኮሽታ የማይሰማባቸው፣ ሁሌም ተመሳሳይ ሐሳብ
የሚናፈስባቸው፣ አብዛኛው ሰው ተቀራራቢ ሐሳብ የሚይዝባቸው፣
ዝምታ የነገሠባቸውና በእጅጉ የረጉ ሥርዓቶች ናቸው። በአንጻሩ
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የዜጎችን መብት የሚያከብርና ሥልጣን

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 27
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

በብዙዎች እጅ የሚወድቅበት ሥርዓት በመሆኑ ፍትጊያ፣ ውጣ


ውረድ እና ውጥረት የሥርዓቱ መለያዎች ናቸው። ፓርቲዎች፣
ሚዲያዎች፣ የመብት አቀንቃኞች፣ አክቲቪስቶች...ወዘተ
እያንዳንዳቸው ያላቸውን መብትና ኃይል ተጠቅመው የተለያዩ
ሐሳቦችን ስለሚያራምዱ፣ አለመግባባትና ውጥረት የዕለት ከዕለት
እውነታዎች ናቸው። በመንግሥት በኩል ደግሞ ሥልጣን ወደ
ሦስቱ የመንግሥት አካላት (ሕግ አውጭ፣ አስፈጻሚና ተርጓሚ)
ስለሚሠራጭና በፖለቲካ ሥርዓቱ ውስጥ የኃይል ፍሰቱ አንድ
አቅጣጫን ብቻ የሚከተል ባለመሆኑ፣ ፍትጊያና ውጥረት የተለመደ
ነው። የዴሞክራሲ ተቋማት ከአስፈጻሚዎች ጋር፣ አስፈጻሚዎች
ከሕግ ተርጓሚዎች ጋር መፋጠጣቸው የተለመደ ነው። አስፈጻሚ
አካላት እርስ በርሳቸው፣ ሕግ አውጪ አካላት እርስ በርሳቸው፣
ሌሎች ተቋማትም እንዲሁ መታገላቸውና መፋተጋቸው ጤናማና
የዘወትር ጉዳይ ነው።

በሀገራችን በአስፈጻሚዎችና በዴሞክራሲ ተቋማት (ሰብዓዊ


መብት፣ ምርጫ ቦርድ) መካከል፣ በአስፈጻሚውና በፍርድ ቤት
መካከል፣ በተለያዩ አስፈጻሚዎች መካከል... ወዘተ ፍትጊያዎችና
ውጥረቶች ታይተዋል። በሚዲያዎች፣ በፖለቲከኞች፣ በአክቲቪስቶች...
ወዘተ. መካከል የሚፈጠሩ ውጥረቶች፣ የሕዝቡንና የፖለቲከኞችን
ልብ ሲሰቅሉ ታይተዋል። ሐሳብ መወራወር፣ በቶሎ አለመግባባት፣
ክርክር... ወዘተ የአዲሱ ተለምዶ መለያዎች ናቸው። ኃይል በተለያዩ
አካላት እጅ የተሠራጨ ጉዳይ ስለሆነ፣ በእነዚህ አካላት መካከል
የሚኖር ትግልና ፍትጊያ የፖለቲካ ዐውዱን በውጥረትና በመናጥ
ይሞላዋል። ሆኖም ይህ መናጥ እንስራው እስካልተሰበረ ድረስ ቅቤ
ይወጣዋል። የረጋው ወተት በእንስራ ውስጥ ሲወዛወዝና ሲናጥ
ነው ቅቤ የሚፈጠረው። የዴሞክራሲ ሥርዓት ዋነኛ ሥነ-አመክንዮ
(ሎጅክ) ይህ ነው።

ይህን የዴሞክራሲ ጠባይ ያልተረዳ ሰው በሚነሡ ጩኸቶች፣


አለመግባባቶችና ፍትጊያዎች ሊደነግጥና ጉዳዩን የመታወክ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 28
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

(abnormality) ጉዳይ አድርጎ ሊወስደው ይችላል። ስለዚህም ከዚህ


የመታወክ ስሜት ለመውጣትና ወደ አሮጌው ተለምዶ ለመመለስ
ፍላጎቶች መታየታቸው የማይቀር ነው። ነገር ግን ይህ የውጥረትና
የመናጥ ሁኔታ አዲሱ ተለምዶ (The New Normal) በመሆኑ ከዚህ
አዲስ እውነታ ጋር ራሳችንን እንዴት አላምደን ሕልማችንን እናሳካለን
የሚለውን ማሰብ ተገቢ ነው። ውጥረቱንና ፍትጊያውን ለማስቀረት
መፈለግ ማለት የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለመቀልበስ መፈለግ ማለት
እንደሆነ በአግባቡ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ብዙ የዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት ጅማሮዎች የተቀለበሱት ይህንን የዴሞክራሲ አዲስ ጠባይ
አስቀድመው ባለመገንዘባቸውና ዴሞክራሲ በሚፈጥረው የውጥረት
አየር በመረበሻቸው ነው። ስለዚህም ውጥረቱን ለማርገብ በአሮጌ
ዘዴዎች ማለትም ያልተመጣጠኑ የኃይል ርምጃዎች (እሥር፣
እንግልት፣ ግድያ፣ ፍርሐት) መጠቀም ያስፈልጋል የሚሉ ድምፆች
ከአዲሱ ተለምዶ ጋር በሚገባ አልተዋወቁም ማለት ነው።

ሆኖም በአግባቡ መገንዘብ ያለብን ነገር፣ ጉዳዩ ከውጥረት


አልፎ በዜጎች ላይ ብርቱ ጥቃትና ጉዳት ካስከተለ የመታወክ (ab-
normality) ችግር ነውና እንደ ተፈጥሯዊ ሁኔታ ወይም እንደ
አዲስ ተለምዶ ሊቆጠር ፈጽሞ አይችልም። ሀገራችን አሁን
ያለችበትን ፈተና ስንመለከት በእጅጉ መለየት ያለብን ዋና ጉዳይም
ከዴሞክራሲ ተፈጥሮ የሚመነጨውን ውጥረት እና በጽንፈኝነት
ምክንያት የሚፈጠሩ ጉዳቶችና አደጋዎችን ነው። የፖለቲካ አየሩ
በፍትጊያ፣ በትግል፣ በውጥረት፣ በመናጥ አንዳንዴም በመለስተኛ
ጥፋት የተሞላ መሆኑ እንደ አዲስ ተለምዶ ተቀብለነው ልንኖር
የሚገባ ጉዳይ ነው። በጽንፈኝነት ዝንባሌ ምክንያት በሰውና በንብረት
ላይ የሚደርሱ ጥፋቶችን ግን ጥርሳችንን ነክሰን ልንታገላቸው
የሚገባቸው የህልውናችን አደጋዎች ናቸው።

የአዲሱ ተለምዶ ዋና ዕንቅፋትና አዲሱን ተለምዶ እንዳይጸና


የሚያደርገው ዋና ጉዳይም ጽንፈኝነት በመሆኑ ጽንፈኝነትን
መታገል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጽናት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 29
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ነው። ዋናው ጉዳይ ግን ጽንፈኝነትን ስንታገል በአሮጌው ስልታችን


ከሆነ ማለትም ሰዎች ያለአግባብ የሚታሠሩበት፣ የሚገደሉበት፣
የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት ሁኔታን ከፈጠርን፣ የዴሞክራሲ
ሥርዓትን ልናጸና አንችልም። ዴሞክራሲ የሚፈልገውን ሆደ ሰፊነት
ዘንግተን የምንወስዳቸው ርምጃዎች ከሐዲዳችን እንዳያወጡን
ሁሌም ጥንቃቄ ሊለየን አይገባም።

ሌላው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታችን በፈጠረው አዲሱ


ተለምዶ ውስጥ ልናስተውለው የሚገባን ጉዳይ የእኛ ተለምዶና
የምዕራቡ ዓለም ተለምዶ የሚለያይ መሆኑን ነው። እየገነባን ያለነው
ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ነው። ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ደግሞ
በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታና በኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ላይ የሚመሠረት
ነው። ስለዚህም አዲሱን ተለምዶ ለመረዳት በቀጥታ የምዕራቡን
ዓለም ማነጻጸሪያ ማድረግ ስሕተት ላይ ይጥላል። ለምሳሌ እኛ
የምንገነባው እንደ ምዕራባውያኑ ሂደትን ብቻ ያማከለ ዴሞክራሲ
(procedural democracy) ብቻ ሳይሆን ውጤትንም ዓላማ ያደረገ
ዴሞክራሲ ነው። ሂደትን ያማከለ ዴሞክራሲን ብንከተል እስካሁን
በርካታ ዜጎች መታሠራቸው አይቀርም ነበር። ብዙ ሕጎችን ሲጥሱ
የምናልፈው እኛ ያለንበት የዴሞክራሲ ልምምድና ምዕራባውያኑ
ያላቸው ልምድ ስለሚለያይ ነው። በሂደቱ መሠረት ከሄድን በየቀኑ
በርካታ ለወንጀል ክስ የሚበቁ ድርጊቶች በዜጎች ይፈጸማሉ። በእነዚህ
ሁሉ ላይ ርምጃ ብንወስድ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል በቀላሉ
መገመት እንችላለን። ስለሆነም ሀገርንና ሕዝብን ይጠቅማሉ ብለን
ያሰብናቸው ነገሮች እስካሉ ድረስ የሥርዓታዊ ሂደት (procedure)
እሥረኛ ሆነን፣ ሀገርን ለጉዳት አንዳርግም። ይህም ሲባል ግን
ዴሞክራሲ ያለ ሂደት ፈጽሞ ሊቆም የማይችል ነገር በመሆኑ፣
ሂደትን ዋነኛ ማጠንጠኛ ማድረጋችን የግድ ነው። በሥርዓታዊ
ሂደት ላይ ቆመን ውጤትን እያገናዘብን መሄድ ደግሞ የገቢር ነበብ
(ፕራግማቲክ) ዕይታን የሚፈልግ ፈታኝ ጉዞ ነው።

በአጠቃላይ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለዜጎች ነጻነት የሚሰጥ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 30
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሥርዓት በመሆኑ፣ ዜጎች ነጻነታቸውን ተጠቅመው ሲናገሩ፣


ሲጽፉና በተግባር ሲንቀሳቀሱ የውጥረት አየር መፍጠራቸው
የሚጠበቅ ነው። ዋናው ጉዳይ የውጥረት አየሩ ወደ ጥቃትና ጥፋት
እንዳያመራ ተመጣጣኝ ርምጃ መውሰድና አዳዲስ ዘዴዎችን መፍጠር
ነው። በነጻነት ልምምዱ እና በዜጎች ደኅንነት መካከል ሚዛናችንን
ጠብቀን ለመራመድ የሚያስችለንን መንገድ መከተል ነው። ይህ
ደግሞ አዲሱን ተለምዶና አብሮት ሊቀጥል የሚችለውን የውጥረት
ተፈጥሮውን ተቀብለን፣ ነገር ግን ውጥረቱን ተከትለው የሚከሠቱ
ጥፋቶችን እየለየን ማረም ይጠይቃል። ቅቤውንና እርጎውን በአንዴ
ማግኘት አይቻልም። ቅቤን የፈለገ የእርጎን መናጥ አምኖ መቀበል
ግድ ይለዋል። ዋናው ጉዳይ፣ እርጎው ሲናጥ እንስራዋ (ኢትዮጵያ)
እንዳትሠበር መጠንቀቅ ነው። የእርጎው መናጥ ግን የግድ ነው።
የመደመር ዕይታ ይህንን ከአዲስ ኩነቶች ጋር በቶሎ የመላመድ
(adaptive) ዕሳቤ መሠረት የሚያደርግ በመሆኑ፣ ለዴሞክራሲ
ሥርዓት ግንባታችን ስኬት መሠረት ነው።

2.2. የመረጃ ዘመን አመጣሽ ድኅረ እውነት ፖለቲካ


ሌላው አዲሱን ተለምዶ የፈጠረው ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ
የመጣው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለውጥና እሱን ተከትሎ
የተፈጠረው የድኅረ እውነት ዓለም ነው። ድኅረ እውነት ሰዎች
ከሐቅ ይልቅ በስሜት የሚመሩበት፣ ከእውነትና ከማስረጃ ይልቅ
ወሬን ማናፈስና ስሜትን መያዝ የበላይነት የያዘበት ጊዜ ነው። ይህን
የፈጠረው ደግሞ ብዙ የመረጃ ምንጮች በመኖራቸው ምክንያት
ሰዎች የትኛውን መረጃ ማመን እንዳለባቸው ስለሚቸገሩ ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ የሰዎች ግንኙነትና የመረጃ ልውውጥ በአካል
አብሮ በመገኘት የሚፈጠር ነበር። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን
ተከትሎ ስልክ፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ኢንተርኔት... ወዘተ ይህን
የግንኙነትና የመረጃ መለዋወጫ መንገድ ቀየሩት።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 31
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

በሀገራችን የሞባይል ስልክ የተስፋፋበት፣ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ


ጣቢያዎችና ተጠቃሚዎች የበዙበት፣ ኢንተርኔትና ማኅበራዊ
ሚዲያ ተጠቃሚነት ደግሞ በተለይም በከተሞች አካባቢ በሰፊው
የተለመደበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ከዓመታት በፊት ቅርብ ቦታ
ሆነው ለሰላምታ በዓመት አንዴ እንኳን የማይገናኙ ቤተሰቦችና
ጓደኛሞች አሁን በየደቂቃው በስልክና በኢንተርኔት ይገናኛሉ፤ መረጃ
ይለዋወጣሉ። ከጥቂት ዓመታት በፊት ውጭ ሀገር ያለን ወዳጅ ዘመድ
ደውሎ ማግኘት የጥቂቶች ቅንጦት ነበር። አሁን ዜጎች በማንኛውም
ሀገር ከሚኖር ወዳጅ ዘመዳቸው ጋር በኢንተርኔት አብረው ውለው
አብረው ያድራሉ፤ መረጃ ይቀያየራሉ። ትናንት ከኢትዮጵያ ራዲዮና
ቴሌቪዥን ውጭ መረጃ ለማግኘት ከሞገድ ያመለጠ የጀርመንና
የአሜሪካ ራዲዮ የሚያዳምጡ እጅግ ጥቂት ሰዎች ነበሩ። ዛሬ
በየሰከንዱ መረጃን ከዩቲዩብና ከቲክቶክ የሚከታተሉ ዜጎች ከልጅ
እስከ ዐዋቂ ሚልዮኖች ናቸው። የሚፈልጉትን ጣቢያና መረጃ፣
ቢፈልጉ በቴሌቪዥናቸው ቢፈልጉ በዩቲዩብ ሲጎነጩ ይውላሉ።
ትናንት ሳምንትን ጠብቀው ጋዜጣ፣ ወርን ጠብቀው መጽሔት
በማንበብ መረጃና ትንተናን የሚያነብቡ ጥቂት ሰዎች ነበሩ። ዛሬ
በየሰከንዱ ከፌስቡክ እስከ ትዊትር የመረጃና የትንተና መዓት
በስልካቸው ላይ ሲያገላብጡ የሚውሉ ዜጎች የትየለሌ ናቸው።

ዛሬ ሁሉ ነገር ብዙ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ኢንትርኔት እየገባ


ያለበት ጊዜ ነው። የመሬት ላይ ሕይወትና የቨርቹአል ሕይወት መሳ
ለመሳ የቆሙበትና የቨርቹአል ሕይወት ሁሉን ነገር ለመቆጣጠር
እየሞከረ ያለበት ጊዜ ነው። የዕለት ከዕለት ክንውኖቻችን ሁሉ
ወደ ኢንተርኔት ዓለም እየተጓዙ ነው። ሚዲያው፣ ኪነ ጥበቡ፣
ጨዋታው፣ ምግብ ቤቱ፣ ሱቁ፣ በጎ አድራጎቱ፣ ስብሰባው፣ ንግዱ፣
ቢሮው፣ ዘመቻው... ወዘተ ወደ ቨርቹአል ዓለም ግማሽ ጓዛቸውን
ጠቅልለው ገብተዋል። ይህ የቨርቹአል ዓለም ደግሞ ጊዜና ቦታ
የሚባሉ ሁለት ዋና ዋና የህላዌ ዓምዶችን ዋጋ አሳጥቷቸዋል። ዛሬ
ምንም ነገር ለማድረግ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ፣ ከአንድ ከተማ
ወደ ሌላ ከተማ፣ ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር መሄድ አያስፈልግም።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 32
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ጥቂት ፊደላትን በመጻፍ ብቻ የትም ቦታ መገብየት፣ ሲኒማ


ማየት፣ ስብሰባ መካፈል፣ ዘመቻ መሳተፍ... ወዘተ ይቻላል። ዛሬ
ምንም ነገር ለማድረግ ቀናትንና ወራትን መጠበቅ አያስፈልግም።
ስልካችንን በመነካካት በአንድ ሌሊት አነጋጋሪና ዝነኛ ፖለቲከኛ፣
ጋዜጠኛ፣ አርቲስት፣ አክቲቪስት... ወዘተ መሆን እንችላለን። መረጃ
ማግኘትና ማሠራጨት የቅጽበታት ጉዳይ ሆኗል።

የአንድ ለአንድ የመረጃ ልውውጥን (በአካል፣ በስልክ) እና የአንድ


ለብዙ የመረጃ ልውውጥን (በጋዜጣ፣ በሬዲዮ) እየተካ የመጣው የብዙ
ለብዙ የመረጃ ልውውጥ (ማኅበራዊ ሚዲያ)፤ ሰዎች መረጃዎችን
እንዴት አጣርተው መጠቀም እንዳለባቸው ግራ እንዲጋቡ ያደረገ
ነው። አሁን ያለው ዋና ችግር መረጃ የማግኘት ጉዳይ አይደለም።
የመረጃ መብዛትን ተከትሎ መረጃን አጥርቶ የመጠቀም ፈተና
ነው። በዚህም ምክንያት በፊት ከጥቂት ምንጮች ሞያዊነትን
ተከትለውና ተፈትሸው ለብዙኃኑ የሚሠራጩ መረጃዎች፣ ዛሬ
በአሉባልታዎችና ሁሉም ዜጋ እንደፈለገ በሚያናፍሳቸው መረጃዎች
ተተክተዋል። የመሬት ላይ ሕይወታችን ወደ ቨርቹአል ሕይወታችን
ሲቀየር፣ የተሰጥኦና የሞያ ፍለጋችንም ወደዚሁ ዓለም ተቀላቅሏል።
አሁን የሙዚቃ ተሰጥኦን ለማግኘት ለመንደር ልጆች እየዘፈነ፣
በትምህርት ቤት እያንጎራጎረ የሚያድግ ሕጻን የለም። በደቂቃዎች
እንጉርጉሮውን በማኅበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ ተሰጥኦውን
ይፈልጋል። ከተጨበጨበለት ይቀጥላል፤ ከተነወረ ያቋርጣል። ይህ
ሁኔታ የጋዜጠኝነት፣ የፖለቲከኝነት... ወዘተ ተሰጥኦ ፍለጋዎችም
አድራሻቸውን በቨርቹአል ዓለም እንዲሆን አድርጓል። ይህም
በልምምድ ደረጃ የሚቀርቡና መረጃዎችና ትንተናዎች የብዙኃኑን
አስተሳሰብ እንዲያበላሹና እውነትን እንዲያዛቡ ዕድል ይሰጣል።
ዕውቀት፣ ትምህርት፣ ልምድ፣ ሥነ-ምግባር... ወዘተ የሚባሉ
ጉዳዮች ትርጉም አጥተው፣ ፍላጎትና ስሜት ብቻ የጨዋታው ገዥ
ሕጎች ይሆናሉ።

ይህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስፋፋትና በተለይም


2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 33
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

የኢንተርኔትና ማኅበራዊ ሚዲያ መምጣት የፈጠረው አዲስ ተለምዶ፣


እውነትንና ምክንያታዊነትን በመያዝ ብቻ የሰውን ሐሳብና ዕይታ
መቅረጽ የማይቻልበት፣ ከሐሳብ ጥራት ይልቅ የሥርጭት ዐቅሙና
ስሜት ኮርኳሪነቱ የበለጠ ተጽዕኖ የሚፈጥርበትን ዓለም ነው። ቦታና
ጊዜ የሚባሉ ጉዳዮችን ማጥበቡና ማሳጠሩ ደግሞ የመረጃ ሥርጭቱና
የተጽዕኖ አድማሱ እንዲሰፋና ሰዎች የዘወትር ጥቃቅን ክሥተቶችን
የሚያዩበት (microscopic view) እንዲኖራቸው አድርጓል። በፊት
በመንደሩ ከሚከሠት ነገር ውጭ መረጃ የማይደርሰው ሰው፣
አሁን በአራቱም አቅጣጫ በየትኛውም ጠባብ መንደር ውስጥ
የሚከሠት ክሥተት በደቂቃዎች ውስጥ እንዲደርሰው ሆኗል።
ለምሳሌ:- የተለያዩ ጀርሞች በሰውነታችን ውስጥ፣ በሰውነታችን
ላይና ዙሪያችንን ሲርመሰመሱበት የሚውሉበት ዓለም ቢሆንም፣
ጀርሞቹን ስለማናያቸው ግን የዘወትር አጀንዳችንና የጭንቀትና
ረብሻችን ምክንያት አይደሉም። በማይክሮስኮፕ መመልከት ብንጀምር
ግን ምን ያክል በጀርሞችና በሽታዎች እንደተወረርን ስለምንመለከት
በየቀኑ እነሱን በማጽዳት ሥራ እንደምንጠመድና በሥርጭታቸው
ብዛት እንደምንረበሽ ጥርጥር የለውም። ኢንተርኔትና ማኅበራዊ
ሚዲያ ይህንን የማይክሮስኮፕ ዕይታ ነው በፖለቲካ ሕይወታችን
ውስጥ ያመጡት።

ይህ የማይክሮስኮፕ ዕይታ ጥቃቅን ችግሮቻችንን ሳይቀር


እየተከታተልን እንድንፈታና እንድናጸዳ የሚያስችል መሆኑ ትልቅ
ዕድል ቢሆንም፣ በምናየው ጥቃቅን ነገር ከተረበሽንና ከአዲሱ እውነታ
ጋር ካልተላመድን ግን ውጤቱ ሌላ መዘዝ ይዞ ይመጣል። ስለሆነም
ፖለቲካችንን ስንመለከትና ስንፈትሽ፣ ራሳችንን ስንመለከትና
ስንፈትሽ፣ ተግባራችንን ስንመዝንና ስንፈትሽ በዚህ አዲስ ተለምዶ
ውስጥ እንዳለን መዘንጋት የለብንም። ጥቃቅን ስሕተቶችን ንቆ
የሚያልፍና ጥንቃቄን መርሑ የማያደርግ መሪ የአዲሱ ተለምዶ
መሪ አይደለም። በሌላ በኩል በጥቃቅን ችግሮች የሚረበሽና ጥቅል
ሁኔታውን አሠናስሎ መመልከት የማይችል መሪም የአዲሱ ተለምዶ
መሪ አይደለም።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 34
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ከሁሉ በላይ እውነትን ስለያዘ ብቻ የፖለቲካ ምኅዳሩን መቆጣጠር


እችላለሁ ብሎ የሚያምንና እውነቱን እንዴት ለሌሎች አደርሳለሁ
ብሎ የማያስብ መሪ የአዲሱ ተለምዶ መሪ አይደለም። በዚህ የድኅረ
እውነታ ዓለም ውስጥ እንዴት ታግለን እውነታችንን ሕዝባችን
ጋር እናደርሳለን የሚለው ጥያቄ ትልቁ አጀንዳችን ሊሆን ይገባል።
ፖለቲካ የመረጃ ልውውጥ ውጤት ነው። የመረጃ ዐቅም የሌለው
አካል የፖለቲካ ዐቅም ሊኖረው አይችልም። መሪውና ተመሪው፣
መንግሥትና ዜጎች፣ ፓርቲዎችና ደጋፊዎች... ወዘተ. የሚገናኙት
በመረጃ ነው። ለዚህም ነው በዓለም የፖለቲካ ታሪክ ሚዲያ
ዋነኛው የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ጉልበት ሆኖ የቆየው። በሀገራችን
ታሪክ ጥቂት የመንግሥት ሚዲያዎች በነበሩበት ጊዜ መንግሥት
ሐሳቡን ወደ ሕዝብ ያለተቀናቃኝ በቀላሉ ያደርስ ነበር። መንግሥት
በአብዛኛው የመረጃ ሞኖፖሊ ነበረው።

የሚዲያዎች መበራከትና የማኅበራዊ ሚዲያ መምጣት


መንግሥታት ይህንን የሚዲያና የመረጃ የበላይነት እንዲያጡ
ስላደረጋቸው፣ መንግሥታት ከሚዲያዎችና ከማኅበራዊ ሚዲያዎች
ጋር ትንቅንቅ ውስጥ መግባታቸው የተለመደ ክሥተት ሆኗል።
እኛም ይህን የመረጃ የበላይነት በማኅበራዊ ሚዲያ በመነጠቃችን
ምክንያት፣ ፖለቲካችን በአክቲቪስቶችና በፖለቲካ ነጋዴዎች
የመጠለፍ ወይም የመማረክ አዝማሚያ አሳይቷል። በሌላ አነጋገር
በመንግሥታዊ ሙስና የሚከሠተው የሀገረ መንግሥት መጠለፍ
ወይም መማረክ (state capture)፣ ዛሬ አድራሻውን በቨርቹአል
ዓለም አድርጓል። የሀገረ መንግሥት መጠለፍ ማለት ጥቂት ጥቅመኛ
ስብስቦች የሀገርን የፖለቲካ ሥርዓት ጠልፈው ለግለሰቦች ጥቅም
የሚያገለግል የንግድ ሥርዓት ሲያደርጉት ነው። ሕጉ፣ ፖሊሲው፣
ልማቱ፣ ውሳኔው ሁሉ ለሕዝብ እንዴት ይጠቅማል? ሳይሆን
የተዘረጋውን የጥቅመኞች የንግድ ሥርዓት እንዴት ይጠቅማል?
ከሚል አንጻር መቃኘት ሲጀምር ነው የሀገረ መንግሥት መጠለፍ
የምንለው። በአሁኑ ጊዜ ይህ ዓይነት ሀገረ መንግሥትን የመጥለፍ
አዝማሚያ ቅርጹን ቀይሮ በቨርቹአል ዓለም በመምጣቱ ምክንያት፣
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 35
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

መንግሥት ዕቅዱንና ውሳኔውን በአግባቡ ሕዝብ ጋር ለማድረስና


መግባባትን ፈጥሮ ለመጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል።

ለሀገር ጥቅም የሚደረገው ጥረትና የፖለቲካ ሥራ፣ በቨርቹአል


ዓለም ላይ በሚካሄደው የፖለቲካ ንግድ ምክንያት አቅጣጫውን
እንዲስት እየተነቀነቀ ነው። ዕቅዳችንን በእነሱ ዕቅድ፣ ትኩረታችንን
በእነሱ ትኩረት ላይ እንድናደርግ የሚፈልጉ የማኅበራዊ ሚዲያ
ዘዋሪዎች፣ የሕዝቡን ዓይንና ጆሮ ከእኛ ላይ ነጥቀው ወደ እነሱ
አሉባልታ ለመውሰድ የሚያደርጉት ጥረት ፖለቲካችንን ፈተና
ውስጥ ጥሎታል። የመረጃ ዐቅምንና የበላይነትን ተነጥቀን ዓላማችንን
ማሳካት አስቸጋሪ መሆኑን መረዳትና አዲሱን ተለምዶ ተረድተንና
ተላምደን አሸናፊ አድርጎ የሚያወጣንን መንገድ በጊዜ መፈለግ
ይገባናል። የፌስቡክና የዩቲዩብ ጫጫታ ጊዜያዊና የሚያልፍ
አይደለም። የአዲሱ ተለምዶ እውነታ ነው። ድኅረ እውነትና
የመረጃ የበላይነትን መነጠቅ የአንድ ሰሞን ክሥተት አይደለም፤
የአዲሱ ተለምዶ ባሕርይ ነው። ይህንን ተገንዝበን ከዚህ እውነታ
ጋር ተጋፍጠን አሸናፊ የምንሆንበትን አዲስ ልምምድ መቀየር
ያስፈልገናል። አንጻራዊ የመረጃ የበላይነትን የምናረጋግጥበትንና
ከአጀንዳ ተቀባይነት የምንወጣበትን መንገድ ካልቀየስን ፖለቲካችንና
ሀገረ መንግሥቱ በቨርቹአል ዓለም ነጋዴዎች የመጠለፍ አዝማሚያው
(virtual state capture) እየጠነከረ መምጣቱ አይቀሬ ይሆናል።

2.3. ጽንፈኝነት ያባባሰው አዲሱ ተለምዶ


ከላይ እንደተመለከትነው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እና
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስፋፋት በቅንጅት የፈጠሩት አዲስ
ተለምዶ ያለንበትን ጊዜ ፈታኝና ውስብስብ ያደርገዋል። በአንድ
በኩል የዴሞክራሲ ሥርዓት ያልተማከለ ኃይል (power) የሚጠይቅ
መሆኑ ወይም ኃይል በተለያዩ አካላት እጅ የሚሠራጭ መሆኑ፣
በሌላ በኩል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂው ለእነዚህ የተለያዩ አካላት

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 36
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

የሚዲያ ዐቅምን ስለሚፈጥርላቸው፤ ኃይል እጅጉን ያልተማከለበት


ሁኔታ ውስጥ መንግሥትን ይጥለዋል። ያደጉት ሀገራት ጠንካራ
ኢኮኖሚ ገንብተውና ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዘርግተው
እንኳን እየገጠማቸው ያለውን የአይ.ሲ.ቲና የድኅረ እውነት ፈተና
የሚያሳዩ ሁነቶች ቀላል አይደሉም። ነገር ግን አስቀድመው
በዘረጉት ምቹ ሥርዓት ምክንያት ፈተናውን ለመቋቋም የተሻለ
ዕድል አላቸው። ያም ሆኖ ግን ጉዳዩ እጅግ እያሳሰባቸው መምጣቱን
በመግለጽ በቅርቡ ማኅበራዊ ሚዲያን የተመለከቱ ሕጎችን የማውጣት
እንቅስቃሴዎች ተበራክተዋል።

እኛ ያለንበት ሁኔታ ግን ከእነሱ በእጅጉ የተለየ ነው። የኢኮኖሚ


ግንባታ ፈተናን፣ የዴሞክራሲ ግንባታ ፈተናን፣ እና የአይ.ሲ.ቲ
ፈተናን በአንድ ጊዜ እየተጋፈጥን በመሆኑ ፈተናችን ድርብርብ
ነው። ኢኮኖሚያችንን ማሳደግ በራሱ ብዙ ጉልበትና ጥረት
ይፈልጋል። ዴሞክራሲን መገንባት በራሱ ብዙ ውስብስብ ጥረትና
ትዕግሥት ይፈልጋል። በዚህ ላይ ነው እንግዲህ አይሲቲ የወለደው
የድኅረ እውነት ፈተና የተጋረጠብን። ዋናው ጉዳይ እንግዲህ፣
ነባሩ የጽንፈኝነት ፈተናችን በዚህ አዲስ ተለምዶ ላይ ሲያርፍ
ነው ፍግ እንዳገኘ ሰብል በፍጥነት እያደገ ያለው። አዲሱ ተለምዶ
ኃይልን ከመንግሥት ቆርሶ በመውሰድ በተለያዩ አካላት እጅ ላይ
ስለሚያስቀምጥና ይህን ኃይል ደግሞ አክራሪዎች የመጠቀም ዕድል
ስለሚያገኙ፣ ጽንፈኝነት ምቹ ሁኔታ እያገኘ ይመጣል ማለት ነው።

ነባር የኢትዮጵያ ችግር የሆነው ጽንፈኝነት፣ ከአዲሱ ተለምዶ


ጋር ሲገናኝ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፈጥሯል። አዲሱ
ተለምዶ ለጽንፈኝነት ጠፍ መሬት ማለት ነው። በቀደመው ጊዜ
በመሣሪያ አገዛዝ ድምፁን አጥፍቶ የቆየው ጽንፈኝነት፣ ዴሞክራሲ
የፈጠረለትን ምቹ ሁኔታና ማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰጠውን የመረጃ
ጉልበት በመጠቀም የመፈርጠም ዕድል ያገኛል።

ዴሞክራሲና አይሲቲ በፈጠሩት አዲስ ተለምዶ ላይ በፍጥነት

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 37
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

እያደገ ያለውን ጽንፈኝነት፣ ሌላ ሦስተኛ ምቹ ሁኔታ አግኝቷል።


እርሱም የኢኮኖሚ ኋላቀርነታችን ነው። የፖለቲካ ሥርዓት ከኢኮኖሚ
ሥርዓት ጋር በእጅጉ የተገናኘ ጉዳይ በመሆኑና የኢኮኖሚ ፈተናዎች
ፖለቲካዊ ችግሮችን የሚፈጥሩና የሚያባብሱ በመሆናቸው፣
ደካማ ኢኮኖሚ ለጽንፈኝነት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ከእነዚህ
ፈተናዎች ሁሉ ጀርባ ደግሞ በውኃ ፖለቲካውና በጅኦፖለቲካው
ለውጥ ምክንያት እየጠነከረ የመጣው የውጭ ጠላቶቻችን እጅ ዋነኛ
የአክራሪዎች ቀለብ ሰፋሪ፣ ዕቅድ ነዳፊ እና ነዳጅ አቀባይ ናቸው።

አሁን ዋናው ጥያቄ በአዲሱ ተለምዶ ምክንያት የገጠሙንን


ፈተናዎች እና በፖለቲካ ሽግግሩ ምክንያት የተፈጠሩ ፈተናዎችን
ለይተን መመልከቱ ላይ ነው። በአንድ በኩል፣ አዲሶቹ የዴሞክራሲና
የአይሲቲ ሁኔታዎች ከነባሩ ደካማ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር ተደምረው
የፈጠሩት “አዲስ ተለምዶ” የደቀነው የፖለቲካ ፈተና አለ። ይህ ዘላቂ
ፈተናችን ነው። በሌላ በኩል የፖለቲካ ሽግግሮች በአዲሱ ተቋማዊ
መዋቅር በአግባቡ ሥራ እስኪጀምሩና በደንብ እስኪጠናከሩ ድረስ
የደቀኑት ፈተና አለ። ይህ ጊዜያዊ ፈተናችን ነው። ጊዜያዊ የሽግግር
ፈተናውን፣ ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት በሠራናቸው ሥራዎች
ደረጃ በደረጃ እየፈታነው መጥተናል። በሀገራችንም ሆነ በሌሎች
ሀገራት በሚደረጉ የፖለቲካ ሽግግሮች፣ አዲሱ መዋቅር በደንብ
እየጸና እስኪሄድ ድረስ፣ ለተወሰኑ ዓመታት ሽግግሩ የሚፈጥራቸው
ፈተናዎች ቀላል የሚባሉ አይደሉም። እኛም እነዚህ ፈተናዎች
ከአዲሱ ተለምዶ ጋር ተዳብለው የፈጠሩብንን ፈተና ለመፍታት
የወሰድናቸው ርምጃዎች ሀገራችን የገጠሟትን የህልውና ፈተናዎች
እንድትሻገር በማድረግ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን።

ባለፉት ሦስት ዓመታት የገጠሙንና በድል የተሻገርናቸውን


ፈተናዎችና ታሪካዊ ኃላፊነቶች በአጭሩ ለማስታወስ ያክል
የሚከተሉትን መጥቀሱ በቂ ነው፡-
• በድኅረ ለውጥ የነበርንበት ሀገራዊ አደጋና ያደረግነው እልህ
አስጨራሽና ስኬታማ ሽግግር፣

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 38
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

• ለውጡን ተከትሎ በፓርቲያችን ውስጥ ለውጡን የማይቀበሉ


እና ለውጡን ሊጠመዝዙና ሊቀለብሱ የሞከሩ ኃይሎች
የፈጠሩትን ፈተና በሚገባ በመወጣት ለውጡ የይስሙላ
ሳይሆን እውነተኛ ለውጥ መሆኑን ማረጋገጣችን፣

• የፖለቲካ ምኅዳሩን የሚያሰፉ የተለያዩ ሕጋዊ ርምጃዎችን


መውሰዳችን፣

• ለውጡን የማይፈልጉ ኃይሎች በሶማሌ ክልል የፈጠሩትን


አደጋ መቀልበሳችን፣

• በአማራ ክልል የተፈጠረውን የመሪዎች ግድያና የመንግሥት


ግልበጣ ሙከራ መቀልበሳችን፣

• በደቡብ ክልል የክልልነት ጥያቄዎችን ሥርዓት ባለው


መንገድና በሕግ ማሕቀፍ መመለሳችን፣

• በኦሮሚያ ክልል የተነሡና ወደ አዲስ አበባ የተስፋፉ የሕዝብን


ደኅንነት አደጋ ላይ የጣሉ አለመረጋጋቶችን መቀልበሳችን፣

• በትግራይ ክልል የሕወሐት ኃይሎች በመከላከያ ሠራዊት


ላይ ያደረሱትን ጥቃት በአጭር ጊዜ ውስጥ መቀልበሳችን፤
በኋላም ለሁለተኛ ጊዜ የከፈቱትን ጥቃት በከፍተኛ
ቁርጠኝነት ማክሸፋችን፣

• በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን አካባቢ የተፈጠሩ በጸጥታና


በሕዝብ ደኅንነት ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን መቀልበሳችን፣

• ውጤታማና ታሪካዊ የሆነ ኅብረ-ብሔራዊ ፓርቲ


መመሥረታችን፣

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 39
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

• ለፓርቲ ሳይሆን ለሀገር የሚቆሙ የጸጥታና የዴሞክራሲ


ተቋማትን መገንባታችን፣

• በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ምርጫ


ማድረጋችን፣

በድል የተሻገርናቸው እነዚህ ፈተናዎችና ታሪካዊ ኃላፊነቶች


አሁንም ሙሉ በሙሉ ፈተናነታቸው አልቋል ማለት ግን አይደለም።
መልካቸውን እየቀየሩና መጠናቸውን እየለዋወጡ የሚፈትኑን
ጉዳዮች መኖራቸውንና የፈተናዎቹን ጠባይና ሁኔታ መረዳት
ለቀጣይ ጉዟችን እጅግ አስፈላጊ ነው። በጥቅል ዕይታና በደፈናው
ስንመለከታቸው ፈተናዎቹ ከሀገራዊና ክልላዊ አድማሳቸው ጠበው
አካባቢያዊና የተበጣጠሰ መልክ እየያዙ መሄዳቸውን መመልከት
ይቻላል። ይህም ፈተናዎቹ የሽግግር ፈተናነታቸው አብቅቶ
በተበጣጠሰ አኳኋን ዘላቂ ፈተና የመሆን አዝማሚያ እንዳላቸው
ያመለክታል። ይህም የሚሆንበት ምክንያት ፈተናዎቹ በሽግግር ጊዜ
ርምጃዎችና በስኬታማ የሽግግር ሂደት ብቻ የሚመለሱ ሳይሆኑ፣
በአዲሱ ተለምዶ ላይ እየለመለሙ ያሉ ነባር የጽንፈኝነት በሽታ
ምልክቶች ስለሆኑ ነው። ስለሆነም ምልክቶቹን በማጥፋት ብቻ
በሽታውን በአስተማማኝ ሁኔታ ማዳን ስለማይቻል፣ የፈተናዎቹን
ዘላቂነት ተረድተን ዘላቂ የትግል አቅጣጫን መከተል አስፈላጊ ነው።
ይህም ማለት ችግሮቹ የሽግግር ጊዜ ችግሮች ብቻ ሳይሆኑ፣ በአዲሱ
ተለምዶ ምክንያት ዘላቂ ፈተና ሆነው የሚቀጥሉ የጽንፈኝነት በሽታ
ምልክቶች ናቸው። ስለሆነም ዛሬ ተከሥተው ነገ እንደሚጠፉ ብቻ
ከማሰብ ይልቅ፣ ጊዜያዊ ችግሮችንና ሊዘልቁ የሚችሉ የአዲሱ
ተለምዶ ፈተናዎችን በአግባቡ በመለየት፣ ለዘላቂው የጽንፈኝነት
ፈተና ራሳችንን ማዘጋጀት ይገባናል። ጽንፈኝነትን ለመታገል አዲስ
አቅጣጫና አዲስ ጉልበት ይዘን መነሣት ይኖርብናል።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 40
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

2.4. የጉባኤያችንን ስኬቶች በማጠናከር ጽንፈኝነት ማሸነፍ


እስካሁን በተጓዝንባቸው የለውጥ ዓመታት በሀገራችን
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባትና ሀገረ-መንግሥቱን በጽኑ
መሠረት ላይ ለማቆም የሚያስፈልጉ በርካታ የሽግግርና የሪፎርም
ሥራዎችን ሠርተናል። እነዚህ የለውጥ ሥራዎች ሀገራችንን
ከነበረችበት አጣብቂኝ አውጥቶ ጠንካራና ብርቱ ሀገር ለመመሥረት
የሚያስችሉ ስኬታማ የመትከል ዓመታት ነበሩ። ፖለቲካችንም
የሽግግሩን መነሻ፣ ሂደትና መዳረሻ በሚመለከቱ ጉዳዮችና
አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነበር። የሽግግር ፖለቲካችንን ስኬታማ
ሂደት በአጭሩ ለማስቀመጥ ያክል አራት ታሪካዊ የለውጡን ስኬት
መገለጫዎችን ማስቀመጥ ይቻላል፡-

1. የፓራዳይም ለውጥ፡- መደመር


2. የአካታች ፓርቲ ምሥረታ፡- ብልጽግና
3. የተቋማት ሪፎርም፡- ለሀገር የወገኑ ተቋማት ግንባታ
4. ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፡- ቅቡልነት ያለው መንግሥት

አዲስ ፓራዳይም ነድፈን፣ አዲስ ፓርቲ መሥርተን፣ አዲስ


ተቋማትን ገንብተን፣ አዲስ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት አቋቁመናል።
ይህ የሽግግር ጊዜ በሽግግር ጊዜ የሚገጥሙ ፈተናዎችን ተቋቁመን
ድል ያስመዘገብንበትና ጠንካራና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር
ስኬታማ የለውጥ ሂደትን ያሳለፍንበት ነበር።

ሆኖም አስካሁን ሲፈትኑን የነበሩ ፈተናዎች ከፊሎቹ በለውጥ


ተፈጥሮ ምክንያት የመጡ ስለሆኑ በራሳቸው ጊዜ እየጠፉ
መምጣታቸው የሚጠበቅ ነው። ከፊሎቹ ፈተናዎች ግን ከሽግግር
ሂደቱ ጋር አብረው የሚያበቁ ሳይሆኑ ዘላቂ የጽንፈኝነት ፖለቲካዊ
በሽታ ችግሮች ናቸው። ስለሆነም እነዚህን ዘላቂ ችግሮች ለመፍታት
ለውጡን የሚያጸና የዐሻራ ፖለቲካ ያስፈልገናል። የዐሻራ ፖለቲካ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 41
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ስንል ስኬቶቻችን ተቀልብሰው እንዳይጠፉ ይልቁንም በጠንካራ ዐለት


ላይ ታትመው ትውልድ የሚያስታውሳቸውና የሚያመሰግናቸው
እንዲሆኑ፣ የጀመርናቸውን የምናጠብቅበትና በተሰጠን የአመራር
ዘመን ለትውልድ የሚተርፍ ዐሻራ የምናኖርበት ነው።

ቀጣይ ጉዟችንን የተሳለጠ ለማድረግና የፓርቲያችን አባላት


በጸናና ግልጽ ዓላማ እንዲታገሉ ለማድረግ ተከታታይ የውይይት
መድረኮችን ስናደርግ የቆየን ቢሆንም፣ ዘመኑ ኃይል በሰጠው
የጽንፈኝነት ነፋስ የተወሰዱ ወንድሞቻችንን ለማረምና ለመገሠጽ፣
በማይታረሙት ላይ ደግሞ እንደ የሁኔታው አስፈላጊውን የማጥራት
ርምጃ ለመውሰድ ባስቀመጥነው አቅጣጫ መሠረት፣ ፓርቲያችንን
የማጥራቱ ሥራ በአግባቡ ተከናውኗል። የመጀመሪያውን የብልጽግና
ጉባዔም ያለፈውን ጉዟችንን ገምግመን በቃላችን ልክ እንድንቆም
የሚያደርግ፣ የሐሳብ ጥራትና የዓላማ ጽናት እንዲፈጠር ትልቅ
መሠረት የጣለ ሆኖ ተጠናቋል። ፓርቲያችን ከጽንፈኝነት
ዝንባሌዎች ሳይጸዳና አባላት የዓላማ ጥራትና ጽናት ሳይኖራቸው
የምንፈልጋትን የበለጸገች ኢትዮጵያ መፍጠር ስለማይቻል፣ ይህ
ፓርቲያችንን በዓላማና በዲሲፕሊን የማነጽ ሥራ ለወደፊቱም
ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

ፓርቲያችንን ካጠራን በኋላ ቀጣዩ ጉዟችን፣ ከሽግግር ፖለቲካ


ወደ ዐሻራ ፖለቲካ መለወጥ ነው። በአክራሪዎች አጀንዳ እየተጠለፍን
ጊዜያችንን በሽግግር ጊዜ እንዳንጨርሰው፣ በቀጣይ የፖለቲካችን
ትኩረት ለትውልድ የሚተርፍ ዐሻራ በማስቀመጥ ላይ ይሆናል።
ይህ ደግሞ ሁነቶች ላይ ከሚያተኩር ፖለቲካ ይልቅ፣ ከሁነቶች ጀርባ
ያደፈጠውን የጽንፈኝነት በሽታ በመፈወስ ለትውልድ የብልጽግና
ውርስ የምናወርስበት ይሆናል።

ስለሆነም ቀጣይ የፖለቲካ ርምጃዎቻችን ሁለት ዋና ዋና


ጥያቄዎችን ከግምት ውስጥ ያስገቡና እነርሱን እየመለሱ የሚሄዱ
ይሆናሉ። ትውልድን ምን እናስተምረው? እና ትውልድን ምን

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 42
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

እናውርሰው? የሚሉትን። እነዚህን ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ


ያስገቡት ቀጣይ የፖለቲካ አቅጣጫዎቻችንም የሚከተሉት ይሆናሉ::

2.4.1. የሕግ የበላይነት:-


የመንግሥትን የኃይል ምንጮች ማጠናከር

በአዲሱ ተለምዶ ውስጥ መንግሥት ሁለት ዋና ዋና ኃይሎቹ


ፈተና ውስጥ ስለገቡበት፣ እነዚህን ኃይሎች በማጠናከር የለውጡን
ዘላቂነት ማረጋገጥ ይኖርብናል። መንግሥት የጉልበተኝነት ብቸኛ
ባለቤትነቱን እና የመረጃ የበላይነቱን መያዝ አለበት። ሁለቱን የኃይል
ምንጮች ማለትም የመሣሪያ እና የመረጃ ኃይልን በተገቢው መጠን
ማስጠበቅ ለአንድ መንግሥት ፖለቲካዊ ስኬት የግድ አስፈላጊ
ጉዳዮች ናቸው።

ጽንፈኝነትን ለማረም በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ ከሽግግር ጊዜው


ባሻገር ሊዘልቅ የሚችለውን አዝማሚያ ማረም የሚቻለው በመጀመሪያ
ፈተናዎቹ የአዲሱ ተለምዶ ዘላቂ ፈተናዎች መሆናቸውን ስንቀበል
ነው። የአዲሱን ተለምዶ ፈተናዎች ደግሞ በሽግግር ጊዜ ርምጃዎች
ብቻ የምናልፋቸው አይደሉም። በየቦታው የምንወስዳቸው የጸጥታ
ማስከበርና የሰላም ጥረቶች ዘላቂ ውጤት እንዲያመጡ ከፈለግን
ከሁነቶቹ ይልቅ የሁነቶቹ መፈልፈያ የሆነውን የጽንፈኝነትን ዋሻ
መድፈን አለብን። ለዚህ ደግሞ ችግሮቹ ያልፋሉ ከሚለው የሽግግር
ጊዜ አስተሳሰባችን ወጥተን ጽንፈኝነትን የሚያርሙ አዳዲስ
ልምምዶች ያስፈልጉናል። ይህም ማለት ትውልድ ከመብቱ ባሻገር
ግዴታንና ተጠያቂነትን እያወቀና ከጽንፈኝነት ዝንባሌ እየታረመ
እንዲሄድ፣ የሕግ የበላይነትን ማለማመድ ያስፈልጋል። አክራሪዎች
ለሚፈጽሟቸው የሕግ ጥሰቶች አስፈላጊውን ተመጣጣኝ የሕግ
እርምት መስጠት ካልተቻለ፣ የዛሬን አደጋ ብናከሽፈው ነገ ሌላ
እልፍ አደጋ ተፈልፍሎ ማደሩ አይቀርም። ስለዚህም ችግሩን
በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉና የሕግ የበላይነትን ትውልድ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 43
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

እየተማረ እንዲሄድ የሚያደርጉ ሕጋዊ ርምጃዎችን መውሰድ ቀጣይ


አቅጣጫችን ሊሆን ይገባል። ይህም ሦስት ነገሮችን አጣምሮ መጓዝን
ይጠይቃል። ተገቢውን ሕጋዊ ርምጃ በተገቢው ጊዜ፣ ቦታና አካል
ላይ መውሰድ፤ በባህላዊ፣ በሃይማኖታዊና በማኅበራዊ መንገዶች
ጽንፈኝነት እጅግ የተወገዘና የተነወረ እንዲሆን መሥራት እና
ትውልዱ የሕግ የበላይነትን የተማረና የተቀበለ ትውልድ እንዲሆን
ማድረግ ናቸው።

ሆኖም በዘመቻ፣ በግርግርና የዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት


መርሖችን በሚጣረስ መልኩ የሚወሰዱ ማናቸውም ዓይነት
ርምጃዎች እንዳይኖሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
የሕግ እርምቶቹም ሕጉና ተቋማቱ በሚፈቅዱት ሂደት ብቻ
ያለጣልቃ ገብነት የሚፈጸም መሆን ይኖርበታል። በእርምት ሂደቱ
ውስጥ የሚኖሩ አላስፈላጊ ፖለቲካዊና ግለሰባዊ ጣልቃ ገብነቶች
ከጥቅማቸው ይልቅ አደጋቸው ስለሚያመዝን፣ ዜጎችም የሕግ
የበላይነትን ከመማር ይልቅ ከሂደቱ አላስፈላጊ ትምህርትና ግንዛቤ
እንዳይወስዱ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

በዚህ ሂደታችን ላይ በአንድ በኩል ጽንፈኝነትን በሕግ አግባብ


በመከላከልና በመታገል፣ በሌላ በኩል ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብቶችን
በማክበር መካከል ያለውን ሚዛን መጠበቅ ይገባል። በዴሞክራሲያዊና
በሰብአዊ መብቶች መከበር ሽፋን ጽንፈኝነት እንዳይስፋፋ፣ በሌላ
በኩል ጽንፈኝነትን ለመከላከልና ለማጥፋት ሲባል ዴሞክራሲያዊና
ሰብአዊ መብቶች እንዳይጣሱ ሚዛን መጠበቅ ተገቢ ነው።

ሀ. የመንግሥትን በብቸኝነት ኃይል የመጠቀም ሥልጣንን


(monopoly of violence) ማረጋገጥ፡- ዴሞክራሲው
የፈጠረላቸውን ክፍተት ተጠቅመው በየቦታው በጉልበተኝት
(በመሣሪያ) ፍልጎቶቻቸውን የሚያስፈጽሙ ታጣቂዎችና
ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች በጊዜ ወደ ሕግ መሥመር እንዲገቡ
ማድረግ አስፈላጊ ነው። አንድ ሀገር እንደ ሀገር እንዲቀጥል

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 44
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ከሚያደርጉት መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ መንግሥት ብቸኛ


የጉልበት ባለቤት መሆኑ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት
ዜጎች በማንኛውም ምክንያት በጉልበታቸው መጠቀም
ከጀመሩ የሕግ የበላይነትና የመንግሥት ሚና ትርጉም
ስለሚያጣ ነው። የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ
ኃላፊነት በማናቸውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ለመንግሥት
የተተወ ብቸኛ ድርሻ በመሆኑ ይህንን ማረጋገጥ ለነገ
የማንተወው ወሳኝ የቤት ሥራ መሆን ይኖርበታል።

ለ. የመንግሥትን የሚዲያ የበላይነትን የማረጋገጥ ትግል፡-


በአዲሱ የድኅረ እውነት ዓለም ውስጥ የሚዲያ የበላይነትን
የማረጋገጥ ጉዳይ በእጅጉ አደጋ ውስጥ የወደቀ ነው።
ምክንያቱም ማኅበራዊ ሚዲያ በሁሉም አካላት እጅ
የሚገኝ በመሆኑ መንግሥት ከዜጎች ጋር የሚያደርገው
ግንኙነት በእጅጉ የተመናመነ ሆኗል። የመረጃ ፍሰትንና
የሀገርን ትርክት በበላይነት መምራት ባልተቻለበት ሁኔታ
ደግሞ ሕዝብና መንግሥት ስለማይናበብ፣ ሀገር በፖለቲካ
ነጋዴዎች የሐሰት መረጃ ትናጣለች። ማኅበራዊ ሚዲያው
የሀገራችንን ፖለቲካ እየናጠው ያለውም ይህ የመረጃ
ጉልበት ከመንግሥት እጅ ቀስ በቀስ እየወጣ በአክራሪዎች
እጅ እየወደቀ ስለሆነ ነው።

የፓርቲያችንን አባላት ጨምሮ በርካታ ዜጎችን ወደ


አልተፈለገ አቅጣጫ እየመራ ያለው ይህ የድኅረ እውነት
ጊዜ የፈጠረብን የመረጃ የበላይነት መነጠቅ ነው። ስለዚህም
በአዲሱ ተለምዶ ውስጥ የተግባቦት፣ የመረጃ ልውውጥና፣
የትርክት ግንባታችንን እንዴት ማካሄድ ይኖርብናል?
የሚለውን ጉዳይ በአዲስ ዕይታ መመልከት ይገባናል።
ነባሮቹን መደበኛ ሚዲያዎች በመጠቀም ብቻ የመረጃ
የበላይነታችንን ማስጠበቅ አንችልም። ስለሆነም ሁለት
አቅጣጫዎችን መከተል ይኖርብናል፡-

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 45
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

1ኛ:- የሀገራችንን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ የጥላቻና የብጥብጥ


መልእክቶችን በሚያሠራጩ አክራሪዎች ላይ አስፈላጊውን
የሕግ እርምት ማድረግና ለሌሎች ትምህርት መስጠት
አስፈላጊ ነው። የዜጎች የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በሕግ
አግባብ እስካልተመራ ድረስ የሀገራችን ፖለቲካ በአክራሪዎች
አጥፊ መልእክት መታመሱ የማይቀር ነው። ጉዳዩ ከሽግግሩ
በኋላ የሚያቆም ሳይሆን፣ ማኅበራዊ ሚዲያ እስካለ ድረስ
አብሮን የሚቀጥል ፈተና መሆኑን ተረድተን ከወዲሁ ዘላቂ
የትግል ስልት መቀየስ ያስፈልጋል።

2ኛ:- በአዲሱ የድኅረ እውነት ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ የመረጃ


የበላይነታችንን ለማረጋገጥ የመረጃ ልውውጥና የተግባቦት
ስልታችንን ከአዲሱ እውነታ ጋር ማጣጣም አለብን።
የተቋማት ድረ-ገጾችና የሕዝብ ግንኙነቶች፣ የኮሙኒኬሽን
ተቋሞቻችንና ሚዲያዎቻችን፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮቻችን
መለወጥ አለባቸው። ማኅበራዊ ሚዲያን እንደተጨማሪ
ጉዳይ ሳይሆን የዘመኑ መደበኛ ሚዲያ መሆኑን ተገንዝበን
በግልጽ መርሕና ጥንቃቄ በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል።
አጠቃላይ የኮሙኒኬሽን ሥራዎቻችንን በተመለከተ ጥልቅ
ፍተሻ በማድረግ አዳዲስ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ
ያስፈልጋል።

2.4.2. አርአያ የሚሆን ፓርቲ መገንባትና የፓርቲውን ወጥነት


(entitativity) ማጠናከር

በዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አዲስ ተለምዶ ጊዜ፣ እያንዳንዱ


ንግግራችንና ድርጊታችን ወደ ትውልድ ይደርሳል። የማናያቸው
ዓይኖች በየቦታው ያዩናል፤ ሥራችንን፣ ፍላጎታችንን፣
ንግግራችንን ይመዝናሉ። ስለዚህ በንግግሮቻችንና በድርጊቶቻችን

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 46
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ለትውልድ አርአያ ሆነን መቅረብ የመጀመሪያው ትውልድን


የምናስተምርበትና ጽንፈኝነትን የምናርምበት መንገድ ነው።
እኛ በዘፈቀደ የምንናገራቸውና የምናደርጋቸው ድርጊቶች ናቸው
የፖለቲካ ባሕላችንን የሚቀርጹት፤ በትውልድ ልቡና ውስጥ
የሚያድሩት። ስለሆነም የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት የየዕለት
እንቅስቃሴያቸውን “ትውልድ ከዚህ ምን ይማራል?” በሚል
መንፈስ እንዲቃኙት ይጠበቃል። ፓርቲው፣ አመራሮቹ እና አባላቱ
የምንገነባውን ትውልድ በቅድሚያ በራሳቸው ባሕርይና ባሕል
ውስጥ ገንብተው ማሳየት ይኖርባቸዋል። የምንነግረውን እንዲሰማን
በተግባር ሆነን እናሳየው። የፓርቲያችን አባላት በዐርበኝነት መንፈስ
የቆሙና ከጽንፈኝነት የጸዱ፣ በሀገራቸው የሚኮሩና ለኅሊናቸው
የሚኖሩ፣ በንግግሮቻቸውና ተግባሮቻቸው ውስጥ አስተዋይና
ዲሲፕሊን የተላበሱ ከሆኑ፣ ገሚሱን የትውልድ ግንባታ ሥራ
እንደሠራነው ይቆጠራል።

ትውልድ በእኛ አዲስ ዘይቤ እንዲሳብ እኛ ያንን ዘይቤ መከተልና


ያንን ሕይወት እየኖርን ማሳየት ይጠበቅብናል። ይህ ደግሞ
በፓርቲያችን ውስጥ ከመግባባትና ከመከባበር፣ በዴሞክራሲያዊ
አስተሳሰብ ከመመራት፣ እንዲሁም ለዓላማ በጽናት ከመቆም
የሚመነጭ ነው። በአጠቃላይ ፓርቲያችን ዴሞክራሲያዊ የውስጠ
ፓርቲ ባሕልና በሕዝብ ዘንድ የሚታወቅበት መልካምና ወጥ ማንነት
ማዳበር ይኖርበታል። ፓርቲያችን ኅብረ-ብሔራዊ ፓርቲ ስለሆነ
ወጥ የሆነ ማንነት (entitativity) የሚፈጥረው በዓላማ ጽናትና
እርስ በርስ በመናበብ ነው። ለጽንፈኞችን ድንጋይ የምናቀብለውና
የፓርቲያችንን ኅብረ-ብሔራዊነትና አንድነት ለሚክዱ አካላት
ከፋፋይና መሠረተ ቢስ ትንተና የምንጋለጠው፣ የፓርቲ ወጥነትን
ስላልገነባን ነው። ጠንካራ የሆነ ወጥ ማንነት የለውም ተብሎ
የታሰበ ፓርቲ ደግሞ፣ ከውስጥም ከውጭም ለሠርጎ ገብነትና
ለከፋፋይ አጀንዳዎች የመጋለጥ ዕድሉ ሰፊ ነው። ስለሆነም ፓርቲ
የማጥራት ሥራችን ስኬት የሚገለጸው፣ የፓርቲው የውስጥ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 47
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

መናበብ ሲፈጠርና ፓርቲው ጠንካራ ወጥነት እንዲኖረው ማድረግ


ሲቻል ነው። ፓርቲያችን በአዲሱ ተለምዶ ውስጥ የራሱን ማንነት
ይዞ በጽኑ መለያ የቆመ ፓርቲ መሆን ይኖርበታል። አክራሪዎች
ከሚያስነሡት ወጀብና አቧራ ሁሌም ራሱን መጠበቅ አለበት።

2.4.3. የትውልድ ግንባታ መርሐ-ግብር (National Action


Plan) ቀርጾ መንቀሳቀስ

የትውልድ ግንባታውን ለመምራት ሀገራዊ የድርጊት መርሐ-


ግብር (National Action Plan) ቀርጾ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው።
የትውልድ ግንባታ ስትራቴጅዎቻችንን ወደ ድርጊት መርሐ-
ግብር ቀይረን ትውልዱ መቻቻልን፣ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን፣
ወንድማማችነትን፣ እኅትማማችነትንና ዐርበኝነትን እየተማረ
እንዲያድግ የሚያደርጉ ሥራዎችን ለመሥራት ጊዜያችንን በአግባቡ
መጠቀም አስፈላጊ ነው።

2.4.4. ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት


ማድረግ
ለመጪው ትውልድ ከምናወርሳቸው ጉዳዮች አንዱ ብሔራዊ
መግባባት የተፈጠረባትን ኢትዮጵያ ነው። ለዚህ ደግሞ ለረጅም
ዓመታት ስንነታረክባቸው የቆዩ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በምክክር
ሂደትና በመደማመጥ መፍታትና ስምምነት ያልተደረሰባቸውን
ጉዳዮች ደግሞ በሕዝበ ውሳኔ እልባት እየሰጡ ማለፍ ተመራጩ
መንገድ ነው። ይህ ሂደት ከጅምሩ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ
ውጤታማ እንዲሆን ለሂደቱ ብቻ ሳይሆን ለውጤቱም ትኩረት
ሰጥተን የሀገራችን የፖለቲካ ኃይሎች በበቂ ሁኔታ እንዲሳተፉበት
ጥረት ማድረግ አለብን። በሂደቱም የእኛ ተሳትፎና አስተዋጽዖ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 48
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

በጠንካራ የዓላማ ጥራትና ጽናት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።


እንደ ገዥ ፓርቲ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ማድረግ ያለብን
አስፈላጊ ድጋፍ ሁሉ በተከታታይ ማድረግ ይኖርብናል። አንድ
ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ በውጭ ጠላቶቻችን ተዘዋዋሪ
የሐሳብና የገንዘብ ጫና ሥር እንዳይወድቅ ነው። በተጨማሪም
ሂደቱ የፖለቲካ ግለቱን እንዳይጨምረውና ያልተፈለገ ሂደት ውስጥ
እንዳንገባ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።

2.5 ፖለቲካችን ብልጽግና ከማምጣት ላይ እንዲያተኩር


ማድረግ
ፖለቲካና ኢኮኖሚ በአዙሪት የሚገናኙ ጉዳዮች ናቸው።
መንግሥታት ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እንፈታለን ሲሉ ኢኮኖሚ
ለመገንባትና ብልጽግናን ለማምጣት የሚያስፈልገውን ጊዜ ሀገር
በማረጋጋት ያባክኑታል። በአንድ በኩል ኢኮኖሚው ካላደገ በዘላቂነት
የተረጋጋ ፖለቲካ መፍጠር አይቻልም። በሌላ በኩል ፖለቲካው
ካልተሻሻለ ሰላም ስለማይኖር ኢኮኖሚውን መገንባት አስቸጋሪ ነው።
ይህንን አዙሪት በጥሰን ለመውጣት እስካሁን የሠራናቸውን የለውጥ
ሥራዎች በማጽናት ላይ ትኩረት አድርገን፣ የፖለቲካው ማጠንጠኛ
ብልጽግናን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ መሆን ይኖርበታል። ለዚህ
ደግሞ የመንግሥት ተቋማት ሌብነትን የሚያጸዱበት፣ ብልሹ
አሠራርን የሚቀርፉበትና ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት የሚሰጡበት
ሥርዓት በመዘርጋት ላይ ትኩረት አድርገን መንቀሳቀስ አለብን።

የመንግሥት የልማት ሥራዎች፣ ኢንቨስትመንትና የግሉ


ዘርፍ እንቅስቃሴ፣ መሠረታዊ ማኅበራዊ አገልግሎቶች፣ የፍትሕና
የጸጥታ ሥራዎች...ወዘተ. ሁሉ ከዚህ የተቋማት አሠራር
ግልጽነትና ተጠያቂነት ጋር የተገናኘ ነው። ይህን ለመለወጥ
በርካታ ዘዴዎችንና አሠራሮችን ማስፈን፣ አንገብጋቢ ጉዳዮች
ላይ አስቸኳይ እርምቶች ማድረግ፣ ግልጽ የተጠያቂነት አሠራርና

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 49
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሕጎችን መተግበር፣ ተቋማትን ለመፈተሽና አሠራራቸውን


ለመገምገም የሚያስችሉ የተለያዩ አሠራሮችን (ለምሳሌ የተቋማትን
አሠራር ማዕከል ያደረገ የኢንተለጀንስ ሥራዎች) ተግባራዊ
በማድረግ የሕዝብ ዋና ችግሮችን ለይቶ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ
ነው። የሚዲያ ሥራዎችም በፕሮጀክቶች አካሄድና ውጤታማነት፣
በተቋማትና በአመራሮች አሠራርና ውጤታማነት ላይ መሠረት
አድርገው የፖለቲካ አጀንዳውን መቅረጽ አለባቸው። ሚዲያዎች
ብልሹ አሠራሮችን በማጋለጥ እንዲታረሙ ማድረግ፣ ሙስናን
ለመዋጋት ምርመራ ጋዜጠኝነትን መጠቀም፣ እንዲሁም ሕዝብ
የሚንገላታባቸውን አሠራሮች በመንቀስ እንዲስተካከሉ ማድረግ
አለባቸው።

በሌላ በኩል የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የጀመርናቸውን


የተለያዩ ጅምር ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ከግብ ለማድረስ
ከፍተኛ የፖለቲካ ሥራ መሥራት አለብን። ለዚህም በየደረጃው
ያለው አመራር ያለን ጊዜ በልኬት (ተርም) የተቀመጠልን መሆኑን
ተገንዝቦ ዐሻራውን ለማሳረፍ እንዲረባረብ ትልቅ የፖለቲካ ሥራ
መሠራት አለበት። በሽግግር ሂደት ውስጥ ጊዜያችንን እንዳንፈጀው፣
የአዲሱን ተለምዶ ዘላቂነት ተረድተን ዐሻራችንን ማኖር ላይ ትኩረት
የሚያደርግና ብልጽግናችንን የሚያረጋግጥ፣ ዕቅዶቻችንን በአጭር
ጊዜ እውን እንድናደርግ የሚያግዝ የፖለቲካ ለውጥ ማድረግ
ይኖርብናል።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 50
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ክፍል ሦስት

የውጭ ጉዳይና ዲፕሎማሲ


የውጭ ግንኙነት አንዲት ሀገር በዓለም አቀፍ መድረክ
የሚኖራትን ግንኙነት አቅጣጫ የሚያሳይ እና ከሌሎች ሀገራት
ጋር በሚኖራት ግንኙነት የምትከተለውን መርሕ የሚያመላክት
ነው። ዓለም አቀፍ ትሥሥር በጠነከረበት የሉላዊነት ዘመን ማንም
ሀገር ራሱን አግልሎ መበልጸግ የማይችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
የሀገራት ዕድገትም ሆነ ውድቀት የሚወሰነው ዓለም አቀፍ ትሥሥሩ
በሚፈጥራቸው መልካም ዕድሎችና አሉታዊ ተጽዕኖዎች ጭምር
እንዲሆን አድርጓል።

የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ሀገራችን ብዙ ወረት ያካበተችበት


ዘርፍ ቢሆንም የውጭ ግንኙነት ጉዳያችን ከችግሮችና ከስሕተቶች
የጸዳ አይደለም። በመሆኑም ከለውጡ አንሥቶ የውጭ ግንኙነት
ፖሊሲያዊ፣ ተቋማዊ እና የአተገባበር ግድፍቶቹን እና ጉድለቶቹን
በመለየት፣ ለማስተካከል እና ለመሙላት እንዲሁም የነበሩ
ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል ፖሊሲያዊ፣ ተቋማዊ እና የአተገባበር
ሪፎርሞችን በማድረግ ከፍተኛ ስኬት ተመዝግቧል።

ከስኬቶቹ የመጀመሪያው ውጤታማ የውጭ ግንኙነት


ለማከናወን የሚያስችለው የውጭ ግንኙነት ሕጋዊ እና ፖሊሲያዊ
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 51
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ማሕቀፍ ዝግጅት ነው። የውጭ ግንኙነታችን ከፖሊሲ ረቂቅ ጀምሮ


የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ሆኖ፤ ዓላማውንም ለዜጎች
ክብር መቆም አድርጓል። ፖሊሲ በማውጣት ረገድ ተለዋዋጩን
የዓለም ሁኔታ ያገናዘብ ሀገራዊ ለውጥንም የተረዳ የውጭ ግንኙነት
ፖሊሲ የተለያዩ ምሁራንን እና የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ
የኢትዮጵያን ታሪክ እና አንድነት እንዲሁም የዜጎቿን ክብር
እና ተስፋዋን የሚያንፀባርቅ የጋራ ስምምነት ያለው፣ ብሔራዊ
ክብራችንን እና ብሔራዊ ጥቅማችንን የሚያስጠብቅ፣ የውጭ
ግንኙነት ፖሊሲ እውን አድርገናል።

በውጭ ግንኙነት ጉዳይ ውስጥ ፖሊሲ የመጀመሪያው ቁልፍ


ደረጃ ቢሆንም ብቻውን ለውጥ አያመጣም። የማስፈጸም ዐቅማቸው
ከፍተኛ የሆኑ በዕውቀትና በመረጃ ላይ ተመሥርተው የሚሠሩ
የውጭ ግንኙነት ተቋማት መኖር ለይደር የሚተው ባለመሆኑ
የውጭ ግንኙነቱ ተቋማዊ መሠረት ይዞ የውጭ ግንኙነት ውሳኔ
አሰጣጥ የሚፈልገውን ወጥ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ የመረጃ
መቀናበርና የባለድርሻ አካላት (ተዋንያን) መሳለጥ ላይ የተመሠረተ
ፈጣን ውሳኔን መስጠት የሚችል፣ የተማከለ የውሳኔ ሰጪ አካል
እንዲፈጠር ከፍተኛ ሪፎርም ተደርጓል።

ተቋማትን ወቅቱን ባገናዘበ ሀገራዊ ሁኔታዎች እና ዓለም አቀፍ


ዕድገቶች በተቃኘ መልኩ በመገንባት እንዲሁም በተቋማት መካከል
የሚኖር ግንኙነትና ትብብርን በማሳለጥ የተማከለ የውጭ ግንኙነት
ትግበራን እውን ማድረግ ረዥም ጊዜን የሚጠይቅ ሥራ ነው። ቢሆንም
ግን ብዙውን ነገር በመለወጥ የውጭ ግንኙነት ተቋሞቻችን የውጭ
ግንኙነትን የማስፈጸም ብቃታቸው የላቀ እንዲሆን፣ የመምራት
ዐቅም ባላቸው አመራሮችና የመፈጸም ብቃት ባላቸው ባለሞያዎች
እንዲዋቀሩ ተደርጓል። በዚህም ተቋማቱ ከፓርቲ ጥገኝነት በመላቀቅ
የብሔራዊ ጥቅሞቻችን ማስከበሪያ ሆነዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ
የአምባሳደሮች ሹመት ጡረታ መውጫ ከመሆን ተሻግሮ ሁሉንም
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ያማከለ፣ ሀገራቸውን ሊያገለግሉ የሚችሉ
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 52
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሰዎችን ከየትኛውም ቦታ፣ ፓርቲና የሥራ መስክ ያካተተ እንዲሆን


ተደርጓል።

የውጭ ግንኙነታችንን ለማስፈጸምና ብሔራዊ ጥቅማችንን


ለማስከበር የዲፕሎማሲ ዐቅማችንን በሰፊው ተጠቅመን
ሠርተንበታል። ጎን ለጎን ሀገራዊ ክብራችንን ሳይደፈር የመግታት
ዐቅም ያለው ጠንካራ፣ ዘመናዊና ሁሉን አቀፍ ወታደራዊ ኃይል
እንዲኖረን ለማስቻል የመከላከያ ዐቅማችን የዘመኑን ዐውደ ውጊያ
የዋጀ፣ በዋናነት ጥቃትን ከወዲሁ የማስቀረት ዐቅምን መሠረት
የሚያደርግ፣ በማንኛውም መስክ (በምድር፣ በአየር፣ በሳይበር እና
በባሕር) የሚቃጡትን ትንኮሳዎችን መመከት የሚችል፣ ለዜጎቻችን
ኩራት የሚሆንና ብሔራዊ ጥቅማችንን የሚያስጠብቅ ሆኖ
እንዲደራጅ ለማድረግ በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል።

መከላከያችን ባሕር ኃይል ለመገንባት የመጨረሻው ደረጃ


ላይ ደርሷል። ለጎረቤት ሀገሮች ቅድሚያ በሚሰጠው የብልጽግና
የዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መሰረት ከጎረቤት ሀገራት
ጋር በምናደርገው ትብብርና የጋራ የመልማት ዕቅድ በመነሳት
በምንደርስበት ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት መሰረት ወደቦችን
በምንጠቀምበት እና ዋነኛ የንግድ መተላለፊያችን በሆነው ቀይ
ባሕር፤ የባሕር ላይ ውንብድና፣ ሽብርተኝነትና የታጠቁ ኃይሎች
እንቅስቃሴ ባለበት ቀይ ባሕር፤ የኃያላን ሀገራት ፉክክር በበዛበት
ቀይ ባሕር፣ የንግድ መርከቦቻችን በሰላም እንዲንቀሳቀሱ እና ሀገራዊ
እና ክፍለ አህጉራዊ ሰላማችን በተሟላ ሁኔታ እንዲጠበቅ፣ የባሕር
ኃይል አስፈላጊ ነው። ይሄንን በመረዳት የባሕር ኃይልን ለማቋቋም
የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀዋል። ባሕር ኃይላችን የብሔራዊ
ኩራት ምንጫችንም ይሆናል።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 53
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

3.1. ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ


ከውጭ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የነበረው አንዱ ክፍተት ለዜጎች
ተገቢውን ከለላ አለመስጠት ነበር። በዚህም ምክንያት በተለያዩ
ሀገራት ዜጎቻችን ለእንግልትና ለሰብአዊ መብት ጥሰት ብሎም
ለሕይወት ማጣት ይዳረጉ ነበር። ይህን ችግር መሠረታዊ በሆነ
መልኩ ለመፍታት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በመከተላችን በተለያዩ
ሀገራት በእሥር እና በእንግልት ላይ የነበሩ ከመቶ ሺህ በላይ ዜጎችን
ወደ ሀገራቸው ለማስመለስ ተችሏል። ዜጎቿን የማታከብር ሀገር
ሌሎች ሀገራት እንዲያከብሩላት መጠየቅ አትችልም። በመሆኑም
በየትኛውም ሀገር ያሉ አምባሳደሮቻችን ከዋነኛ ሥራዎቻቸው አንዱ
እንግልትና እሥር ላይ ያሉ ዜጎችን መታደግ እንደሆነ በተገቢው
ሁኔታ በመረዳት እየሠሩ ይገኛሉ። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም
ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሥራ ሥምሪት ስምምነቶችን መደራደርና
ከተወሰኑት ጋር ስምምነት ተጠናቋል።

በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በእሥር ቤት የነበሩ በርካታ


ዜጐቻችን ተፈተዉ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። በሕገ-ወጥ ደላሎች
አማካኝነት እና በተለያዩ ምክንያቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር
ከወጡ ዜጐቻችን መካከል፣ ለብዙዎቹ የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ
ሀገራቸዉ እንዲመለሱ ተደርጓል። የሕክምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸዉ
ዜጐቻችን ሕክምና እንዲያገኙ፣ እንዲሁም በሕክምና ላይ ያሉትን
በመጐብኘት ድጋፍ ለመስጠት ተችሏል።

የዜጎችን ክብር ለማስከበር የምንቀሳቀስበት ዜጋ ተኮር


ዲፕሎማሲያችን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያን እና ትውልደ
ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲጨምር
አድርጓል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን
ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ችግሮቻቸውን በመካፈል እንዲሁም
በሀገራቸው ጉዳይ ተሳተፊና ቅርብ እንዲሆኑ በማድረግ የአለኝታነት

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 54
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ስሜትን በመፍጠር፣ በሀገራቸውና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያን እና


ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል ድልድይ እንዲፈጠር ተሠርቷል።
ኢምባሲዎች እና ሚሲዮኖች ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ
በየሀገራቱ ላሉ ዜጎች ክፍት እና ከምንም ጊዜ በላይ ቅርብ ሆነው
እየሠሩ ይገኛሉ።

ዜጎቿ በየትኛውም የዓለም ክፍል ክብራቸው የተጠበቀባት


ኢትዮጵያን መፍጠር ግብ አድርገን እየሠራን ነው። በዚህ መሠረት
ወደ ተለያዩ ሀገሮች ለሥራ የሚሄዱ ዜጐች መብታቸዉ ተጠብቆ፣
የሚሠሩበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርና በሕጋዊ ሁኔታ እንዲሠማሩ
ለማድረግ፣ ከበርካታ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ሀገሮች ጋር የሥራ
ሥምሪት ስምምነቶችን በመፈረም፣ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
ከተቀሩት ሀገሮች ጋር ለመፈራረም በሂደት ላይ ይገኛል። ለበርካታ
ዜጐቻችን የሥራ መዳረሻ ከሆኑትም ሀገሮች መካከል ከተባበሩት
ዓረብ ኤምሬትስ፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከኳታር እና ከዮርዳኖስ ጋር
ስምምነት ተፈርሞ ወደ ሥራ ተገብቷል። በጎረቤት ሀገሮች በኩል
በሕገ-ወጥ መንገድ የሚፈልሱ ዜጎቻችንን ሁኔታ ለመከላከል
ከጅቡቲ፣ ከኬንያና ከሱዳን እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ ጋር በየጊዜው
መፍትሔ ለመሻት ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

3.2. ሀገራዊ ሉዓላዊነትን የጠበቀ ዲፕሎማሲ

ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር በምንሄድበት ርቀት


የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር እንዲሁም የራሳችንንም
ሉዓላዊነት ባለማስደፈር መልካም ውጤቶችን አስመዝግበናል።
ባለፉት አራት ዓመታት ኢትዮጵያ ከቅርብም ከሩቅም ባሉ ኃይሎች
የደረሰባት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ጫና የሀገራችንን
ውጭ ጉዳይ በእጅጉ የፈተነ ጉዳይ ነው። ከእነዚህ የቅርብና የሩቅ
ኃይሎች መካከል ግብጽ፣ ሱዳን፣ አሜሪካና አውሮፓ፣ እንዲሁም
አንዳንድ የዓረብ ሀገራት ይገኙበታል። በተጨማሪም በአሜሪካና

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 55
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

በምዕራባውያኑ ተጽዕኖ ሥር ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ


ላይ ጫና ለማሳደር ሰፊ ጥረት አድርገዋል።

በተለይ አሜሪካና ምዕራባውያን በዋናነት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ


ጫናዎችን ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት አድርገዋል። ፖለቲካዊ
ጫናዎቹ በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ እንደሽፋን በመጠቀም
በሰብአዊ ርዳታ ስም በሀገራችን ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግ
ሙከራ ነበር። ፖለቲካዊ ጫናው በሦስት አካላት የተቀናጀ ዘመቻ
የሚካሄድ ነው፡- በመንግሥታቱ፣ በ”ሰብአዊ መብት ተቋማት” እና
በሚዲያው።

በመጀመሪያ የሰብአዊ መብት ተቋማት የኢትዮጵያን ምስል


የሚያጠለሽ መግለጫና ሪፖርት ያወጣሉ፤ የወጣውን ሪፖርት
ሚዲያዎቻው “ተንታኝ” እየጋበዙ ያስተጋባሉ፤ በመጨረሻም የሆነ
ሀገር መንግሥት ፊት ለፊት መጥቶ ኢትዮጵያን የሚያወግዝና
የሚጠመዝዝ የዲፕሎማሲ ጫና ያሳድራል። በሰብአዊ መብት
ተቋማትና በሚዲያ ስማችንን አጠልሽተው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ
ዘንድ ጥፋተኞች አስመስለው ካቀረቡን በኋላ፣ የሚወስዱትን
ርምጃና ጫና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቀላሉ እንዲቀበላቸው
አስልተው ተንቀሳቅሰዋል። በኢራቅ፣ በሶርያ፣ በየመን፣ በሊቢያ፣
ወዘተ. ሲፈጽሙት የነበረውን አጥፊ ጋዜጠኝነት በሀገራችን ላይ
ደግመዋል።

ኢኮኖሚያዊ ጫናው ደግሞ በዋናነት በሁለት አካላት የተቀናጀ


ዘመቻ የሚካሄድ ነው። በመንግሥታቱና እነርሱ በሚመሯቸው
የዲፕሎማሲና የገንዘብ ተቋማት። ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማሳደር
የመሠረቷቸው እንደ ዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት
የመሳሰሉ ተቋሞቻቸው በብድርና በድጋፍ ስም እጃችንን ለመጠምዘዝ
ከፍተኛ ጥረቶችን አድርገዋል። በሌላ በኩል መንግሥታቱ በቀጥታ
ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ በማቋረጥ ለእነርሱ ፍላጎት
ተገዥ እንድንሆን ብዙ ሙከራዎችን አድርገዋል። እነዚህ ሁሉ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 56
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ጫናዎች በተቀናጀ ዘመቻ


ሲካሄዱብን ባላሰለሰ ዲፕሎማሲና የሀገራችንን ክብርና ዘላቂ ጥቅም
በሚያስጠብቅ አካሄድ ተከትለናል። መልካቸውን እየቀያየሩ የሚመጡ
የውጭ ግንኙነት ፈተናዎችን ለመቋቋም፣ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን
እያነበቡ የበሰለ የፖሊሲ አማራጮችን ማማተር ለውጤታማ የውጭ
ግንኙነት ቁልፍ የሆነበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

3.3. የዲፕሎማሲ ብስለት፣ ለተለወጠ የዓለም መልክአ ፖለቲካ


እየተለወጠ የመጣው ዓለም አቀፋዊ የኃይሎች አሰላለፍ
ያስከተለው ፉክክርና ሽግሽግ፣ የፈጠረው አዲስ ግንኙነትና
የዲፕሎማሲ አካሄድ፣ የውጭ ግንኙነታችንን ልዩ ጥንቃቄ
የሚያስፈልገው አድርጎታል። ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ
ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የሥልጣን ማዕከል የነበረው
የምዕራቡ ዓለም የነበረውን ብቸኛ የበላይነት ሥልጣን ከምሥራቅ
ሀገራት የሚጋራበት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ተፈጥሯል።
ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ የተፈጠረውን ዓለም አቀፋዊ
ሰላምና መረጋጋት፣ እንዲሁም የነጻ ገበያ ሥርዓት መስፋት አስቻይ
የኢኮኖሚ አጋጣሚዎችን በአግባቡ በመጠቀም፣ ኢኮኖሚያቸውን
በአጭር ጊዜ በማሳደግ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚና በወታደራዊ
ዘርፍ እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ሕንድና ቱርክ ያሉ ሀገራትን ኃያል
ወደ መሆን እያሸጋገራቸው ነው። ይህም በአሜሪካ መሪነት
የተደራጀውን የምዕራቡን ዓለም የሥልጣን ማዕከልነት በሁሉም
ዘርፍ በመገዳደር፣ ባለ አንድ ልዕለ ኃያል የነበረውን ዓለም አቀፍ
ሥርዓት ወደ ብዝኃ ኃያላን ሥርዓት ቀይሮታል። ዓለማችን ከአንድ
ዋልታ ወደ ብዙ ዋልታዎች በመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን ተከትሎ
የመሪነት ቦታውን ለመቆጣጠር ሲሉ ኃያላኑ የተካረረ መልክአ-
ፖለቲካዊ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 57
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ነባሩን ዓለም ዓቀፍ ሥርዓት ለመጠበቅ በሚሹ ምዕራባውያንና


ነባሩን የመቀየር አጀንዳ ባላቸው ሀገራት መካከል የሚደረገው
ፉክክርና መሽቀዳደም፣ በምዕራባውያኑ ፍጹም የበላይነት የቆየው
የዓለማችን ሥርዓት ወደ አዲስ የኃያላን ፉክክርና የአለመረጋጋት
ምእራፍ እያስገባው ይገኛል። ዓለም አቀፍ ፉክክሩ ወደ ተረጋጋ
ሚዛን የሚያደርገው ተፈጥሯዊ ዑደት፣ የቀዝቃዛው ጦርነት
መልክ ያለው የእጅ አዙር ፍትጊያና በየቀጣናው ወዳጅ ለማፍራት
የሚደረገው ሩጫ የሚፈጥረው የአጋር ሀገራት መቀያየር፣ የዓለም
አቀፉ ፖለቲካ መለያ ባህሪ እንዲሆን እያደረገ ይገኛል። የኃያላኑ
ፉክክር ተገማችና ሰላማዊ መሥመርን የማይከተል ከሆነ ዓለም
አቀፍ ጥፋትን ሊያስከትል የሚችል ሥጋትን ያጭራል። ወዳጅ
ለማብዛት የሚደረገው ፉክክር እንደ ሀገራችን ላሉ አዳጊ ሀገሮች
የልማት አጋር አማራጭን ሊያሰፋ ይችላል።

የአፍሪካ ቀንድ ክልል የኃያላኑ የፉክክር መድረክ ከሆነ


ሰንብቷል። በቀደመው የትራምፕ አስተዳደር ተዳክሞ የነበረውን
የምዕራቡን ዓለም መሪነት ዳግም ማደስ የውጭ ጉዳይ ቀዳሚ
አጀንዳ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የባይደን አስተዳደር፣ የሚከተላቸው
ተጋፊ የዲፕሎማሲ ስልቶች የፉክክሩን ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ
ሙቀት ከፍ አድርጎታል። ፉክክሩን የህልውና ያደረገው የምዕራቡ
ዓለም፣ ከተለመደው ሕጋዊነት መርሕ ይልቅ፣ መልክአ-ፖለቲካዊ
ግብ ማዕከል አድርጎ መንቀሳቀስን ወደ ማስቀደም አምርቷል።

በአሁኑ ወቅት በሩሲያና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው


ጦርነት በዓለም ላይ በልዕለ ኃያላን ሀገሮች መካከል እያደገ
የመጣውን የመልክአ-ፖለቲካዊ ፉክክርና የኃይል ሚዛን የበላይነትም
የመቆጣጠር እሽቅድምድም የሚያሳይ ዓይነተኛ መገለጫ ነው።
ከምዕራባውያኑ ጎራ በመሰለፍ፣ ራሷንም የፉክክሩ ዐውድማ
በማድረግ፣ ከሩስያ ጋር ወደ ጦርነት ገብታ ለከፍተኛ ሰብአዊና
ቁሳዊ ኪሣራ የተዳረገችው የዩክሬን ሁኔታ ብዙ ያስተምረናል።
የኃያላን ፉክክር በጦዘበት የዓለም ሥርዓት ውስጥ የሀገርን ጥቅምና

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 58
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሉዓላዊነት አስከብሮ ለመሄድ፣ በኃያላኑ ፉክክር ተወስዶ በወላፈኑ


ላለመጠበስ፣ ሚዛንን የጠበቀ ጠንቃቃ የውጭ ግንኙነት ቁልፍ
የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂ እየሆነ የመጣበት ጊዜ ላይ እንደምንገኝ
ያመላክታል።

በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት መነሻ


ምክንያት ከኔቶ ወደ ምሥራቅ አውሮፓ መስፋፋት ጋር የተገናኘ
ነው። ጦርነቱ በዩክሬንና በሩሲያ መካከል የሚደረግ ቢሆንም፣
ጦርነቱ የተለያዩ አካላት የሚሳተፉበትና ከአካላዊ ውጊያ ባሻገር
ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ገጽታ የተላበሰ ነው። በመሆኑም በመላው
ዓለም ላይ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና እያሳረፈ
ይገኛል። ጦርነቱ ያስከተለው የኢኮኖሚ አሉታዊ ተጽዕኖ፣ ነዳጅን
ጨምሮ በሌሎች መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ ላይ ከፍተኛ
ጭማሪ እንዲከሠት በማድረግ፣ በኮቪድ ወረርሽኝ የተጎዳውን
የዓለም ኢኮኖሚ ወደ ተባባሰ ሁኔታ አስገብቶታል። ጦርነቱ
ያስከተለው የምርት እጥረት የምርቶች ዓለም አቀፋዊ ዋጋ መናር፣
የኑሮ ውድነትን እያባባሰው ይገኛል። ዓለማችንም ከዚህ ቀደም
በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ወቅት እንዳየችው የፖለቲካ ጎራ
መከፋፋል ሥጋት አንዣቦባታል። በእንደዚህ ዓይነት ጦርነቶች
ውስጥ በብዛት የሚጎዱት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ
ሁኔታቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አዳጊ
ሀገሮች መሆናቸው እርግጥ ነው።

ዓለም አቀፉ የፖለቲካ ሥርዓት ከአሐዳዊ ወደ ብዝኃ ኃይልነት


የሚያደረገው ሽግግር እየፈጠራቸው ያሉ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች፣
የሀገራችንን ጥቅምና ሉዓላዊነት ሳይጎዱ ለማስተናገድ ማሰላሰል፣
አርቆ ማስተዋልና ስክነት ያለው የውጭ ዕይታ ያስፈልገናል።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት አንዱ መገለጫው ቢሆንም ከዓለም
አቀፉ የኃይል ሽግግር ጋር ተያይዞና በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ
ደረጃ እየታዩ ካሉ ለውጦች አኳያ፣ በሁለትዮሽም ይሁን በባለ
ብዙ ወገን ግንኙነት መድረኮች ላይ በሚፈጠሩ የኃያላን ሀገሮች
2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 59
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሽኩቻ ላይ ወገንተኝነትን የማያንፀባርቅ፣ ሚዛናዊነትን የጠበቀ፣


ብልህነትን የተላበሰና ወጥነት ያለው አካሄድ (geopolitical bal-
ancing) በመከተል፣ የሀገራችንን ዘላቂ ጥቅም የሚያስከብር ዐቋም
ማራመድ ይገባናል።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 60
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ክፍል አራት

ማኅበራዊ ትሥሥርንና የሞራል ልዕልናን ማሳደግ


ለረጅም ክፍለ ዘመናት በዘለቀው አብሮነታችንና በተጋራናቸው
ታሪካዊ ሂደቶች ውስጥ ከፍተኛ የሆኑ ማኅበራዊ ረቂቅ ሀብቶችንና
ትሥሥሮችን ማፍራታችን ይታወቃል። ይህ የተከማቸ ረቂቅ
ማኅበራዊ ሀብት (Social Capital) የተፈጠረውም ሆነ ተጠብቆ
ሊቆይ የቻለው ደግሞ በወታደራዊ ወይንም በሌላ መንግሥታዊ
ኃይል አይደለም። በእምነቶቻችንና በባህሎቻችን ውስጥ ሠርጸውና
ገዝፈው በተቀመጡ የሥነ-ምግባርና የግብረገባዊነት ዕሴቶችና
ማኅበራዊ ተቋማት አማካኝነት ነው። የኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ
ጉዞ ጅማሬ እስከሆነው የተማሪዎች እንቃስቃሴ ድረስ ሃይማኖታዊና
ባህላዊ የሆኑ አሠራሮችና ዕሴቶች የማኅበራዊ ትሥሥሩም ሆነ
የሞራል ሥልጣን ምንጭ ሆነው ቆይተዋል ለማለት ይቻላል።
ከዚያ በፊት የነበሩት መግሥታትም ቢሆኑ አብዛኛውን ሀገር
የማስተዳደርና ማኅበረሰብን አስተሣሥሮ የማቆየት ጉልበታቸውን
የሚያገኙት ከነዚህ የእምነትና የሞራል ተቋማት ከሚያገኙት
ቅቡልነት ነው ሊባል ይችላል።

ከአብዮቱ ፍንዳታና ዘውዳዊ አገዛዙ ካከተመ በኋላ ተያይዞ


በሰፈነው የኮሙኒስት ርእዮትም ሆነ ከደርግ በኋላ የመንግሥት
መንበሩን በተቆጣጠረው ኢሕአዲግ አገዛዝ ውስጥ እነዚህ የግብረግባዊ
የሥነ-ምግርባር ዕሴቶችና በማኅበረሰቡ ውስጥ ሠርጸው የኖሩ
ሌሎች አስተሣሣሪ ገመዶች ብዙም ዋጋ ሳይሰጣቸው ቆይቷል።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 61
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ይህም የትምህርት ሥርዓቱን ጨምሮ ሌሎች ትውልድ ቀራጭና


ማኅበረሰብ አስተሣሣሪ ተቋማት ደካማ እንዲሆኑ አድርጓል።
ቀስ በቀስም የነበሩን ማኅበራዊ ዕሴቶችና ግብረገባዊ ባህርያት
እየተሸረሸሩ መጡ። የብዙ ወጣቶችን ሕይወት ከቀጠፉት የቀይና
ነጭ ሽብር እልቂትና፣ የእርስ በርስ ጦርነቶች በኋላ የተፈጠሩ
የስደት፣ የረሃብ፣ የወረርሽኝና የመብት ረገጣ ተደጋጋሚ ጫናዎች
በማኅበረሰባችን ኅሊናና ሥነ-ልቦና ላይ ጥለው ያለፉት ቁስልና
ተከድኖ የኖረው ጠባሳ ተጽዕኖው ዛሬም ይታያል። በደርግ ዘመን
ተጨፍልቆ አንድነቱን ብቻ እንዲቀበል ሲገደድ የኖረው ሕዝብ፣
በኢሕአዲግ ዘመን ደግሞ ወደ ሌላኛው የብሔር ጫፍ ላይ ተጎትቶ
ማኅበራዊ ትሥሥሩንና ሀገራዊ አንድነቱን በሚፈታተን መንገድ
ብሔርተኝነትን እንዲያራምድ ተደረገ።

ለግማሽ ክፍለ ዘመን አካባቢ ግበረገባዊነትና የሞራል ሥነ


ምግባር ችላ ተብሎ ቆየ። በዚህም የተነሣ የሙስናና የስንፍና
አስተሳሰብ በባህላችን ውስጥ ሠርጾ ገባ። ለቃልና ለሀገር ታማኝ
ሆኖ በትጋት ለመሥራት ያለን ቁርጠኝነት፣ የሌሎችን መብትና
ንብረት ለማክበር ያለን ፈቃደኝነት፣ እንዲሁም ከስርቆት፣
ከስንፍናና ከአቋራጭ ጥቅም ማግበስበስ የጸዳ ሕይወት ለመኖር
ያለን ዐቋም በእጅጉ ተሸረሸረ። እንደ ሀገር ለምናደርገው የብልጽግና
ጉዞና ለመረጥነው አዲስ የመደመር ፓራዳይም የሞራል ልዕልናና
ጠንካራ ማኅበራዊ ትሥሥራችን መተኪያ የሌላቸው ግብአቶች
ናቸው። ብልጽግናችንን ዕውን ለማድረግም ሆነ በመደመር መንገድ
ላይ ፍሬያማ ሆነን ለመጓዝ፣ የተበጣጠሰውን ማኅበራዊ ድር ዳግም
መጠገንና በራስ ወዳድነትና በግለኝነት የተጠመደውን ሕዝባችንን፣
የሞራል ስብእናውን ገንብተን በሀገራዊ ዐርበኝነትና በወገናዊ ፍቅር
ልናድሰው ያስፈልጋል።

ለሰላማችንና ተረጋግተን በመኖር ሀገራችንን ወደምናስበው


ብልጽግና ለማሸጋገር ሰንቀን ለተነሣነው ራእይ፣ ከፊታችን
ከተጋረጡብን ተግዳሮቶች ውስጥ የሥነ ምግባር መሸርሸርና

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 62
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

የማኅበራዊ ትሥሥራችን ላልቶ መገኘት ዋነኛ ናቸው ሊባል ይችላል።


ብዝኃነታችን ውበታችን የሚሆነውን ያህል ማኅበራዊ ካፒታላችንን
በማደርጀት በመካከላችን ያለውን ግንኙነትና ትሥሥር ይበልጥ
ካልገነባን፣ አሁን በየስፍራው የሚታዩ ብሔርንና ሃይማኖትን
መሠረት አድርገው የሚፈጠሩ ግጭቶች የሀገርን ህልውና ሊገዳደሩ
የሚችሉ ፈተናዎች መሆናቸው አይቀርም። ሙስሊም ከክርስቲያን፣
ሲዳማ ከወላይታ፣ ትግራዋይ ከአማራ፣ አፋር ከሱማሌ፣ ጉራጌ
ከስልጤ፣ ኦሮሞ ከአማራ ያለው ትሥሥርና የጋራ ዕሴት፣
ከልዩነቱና ከሚያጋጨው ሰበብ የላቀ ነው። አንድ ሀገር፣ አንድ
ራእይና አንድ ማኅበራዊ ዕሴት ከያዝን፣ ልዩነታችን ውበታችን
እንጂ ችግራችን ሊሆን አይችልም።

በሰው ሰውነት ውስጥ ያሉ አካላት ሁሉ መልካቸውም ሆነ


ግብራቸው አይመሳሰልም። ሆኖም ግን አንዱ የሌላውን ተግባር
ሊፈጽም አይችልም፤ አንዱም ሌላኛውን አታስፈልገኝም ሊለው
አይችልም። ሁሉም የሚሠሩት ለአንድ ሰው ሙሉና ደስተኛ መሆን
ነው። አንዱ አካል ቢታመም ስቃዩ የሁሉም ነው፤አንዱ ቢደላውና
ቢመቸው ደስታው የጋራ ነው። እንዱ የሰውነት ክፍል በተውሳክ
ቢወረር ሁሉም የሰውነት ክፍል ያንን የሰውነት ብልት ለማዳን
ይረባረባል። ሰውነትን ከሕመም ለመከላከል የተቋቋመው የሕመም
መከላከያ ኃይልም ሙሉ ኃይሉን ያንን ደዌ ለመዋጋት አስተባብሮ
ያውላል። በሽታን የመከላከል ኃይላችን የሁሉም አካላት እንጂ የማንም
የግል መጠቀሚያ አይደለም። ታዲያ እነዚህ በመቶ የሚቆጠሩ
አካላትና በቢልዮን የሚቆጠሩ ሴሎች እንዴት ተግባብተው ነው አንዱ
ሌላውን በማገዝና በመተጋገዝ አብረው የሚኖሩትና የሚናበቡት?
እንዴትስ ነው ሁሉም ተናብበው ሳይለግሙ፣ ሳይሰርቁና በአቋራጭ
ለራሳቸው ጥቅም ሳይፈልጉ በአንድነት በጋራ ተባብረው ለፈጠሩት
ሰው የሚሠሩት? ይህ በመካከላቸው በዳበረው የአካላት መናበብ
ማኅበራዊ ትሥሥርና ግብረገባዊ ጉድኝት የሚፈጠር እንከን የለሽ
ሥርዓት ነው... ሀገርም እንደዚሁ ናት።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 63
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሁሉም ዜጎች እንደ አንዲት ሴል/ሕዋስ ቢሆኑ፣ ብሔረሰቦች፣


ሃይማኖቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ራሳቸውን እንደ እያንዳንዱ
ብልት/organs ማየት ይችላሉ። ክልሎችና ዘርፎች፣ የመንግሥት
ቅርንጫፎች ደግሞ ራሳቸውን እንደ ተለያዩ አሠራሮች/systems
ሊቆጥሩ ይችላሉ። ለምሳሌ:- በሰውነታችን ውስጥ ብዙ ብልቶችን
አስተባብረው የሚሠሩ አሠራሮች (systems) አሉ። የአተነፋፈስ
ሥርዓት /Respiratory System/፣ የደም ዝውውር ሥርዓት
/blood Circulation System/፣ የነርቭ ሥርዓት /Nervous sys-
tem/፣ በሽታን የመከላከል ሥርዓት /immune system/፣ የሰውነት
እንቅስቃሴ ሥርዓት /Mesculo Skeletal System/... ወዘተ እነዚህ
ሁሉ ሥርዓቶች በሥራቸው ያሉ ብልቶችንና ሴሎችን አቀናብረው
የተሰጣቸውን ሥራ ሳያስተጓጉሉ በትጋት ቀን ከሌት ይፈጽማሉ።
አንዱ በሌላው አይቀናም፣ አንዱ የሌላውን ሥራ ያግዛል እንጂ
አያደናቅፍም። ማንም ሌላውን ሊተካ አይችልም። ይሄ ሁሉ
በዓመታት መካከል በመካከላቸው በተፈጠረ መተዋወቅና ተናብቦ
የመሥራት ልምድ መሠረት ይተገበራል... ይህም ሰውነት ይባላል፤
በሀገር ደግሞ ማኅበረሰብ እንደሚባለው። ማኅበራዊ ትሥሥርና
የሞራል ልዕልና ደግሞ የዚህ መሠረት ነው።

የሰውነታችን ክፍሎች ከውጭ ደዌ ሲገባ ባላቸው ትሥሥርና


መናበብ በጋራ ይዋጉታል። የራስ ሴሎች ባህርያቸውን ለውጠው
ሲገኙና የጋራ ሰውነቱን እየበዘበዙ ራሳቸውን ሲያፈሩና ከሥፍራ
ሥፍራ እየተሠራጩ ሌላውን በማጥፋት ሥራ ላይ ሲሠማሩ ካንሰር
ይባላል። ካንሰር ደግሞ በጊዜ ካልታከመና ካልተወገደ በመጀመሪያ
የተነሣበት አካል (የሳንባ ካንሰር ከሆነ መጀመሪያ ሳምባን ከዚያ
ደግሞ ጉበትን፣ ጭንቅላትን፣ የጀርባ አጥንትን... ወዘተ በመውረር)
ከዚያም ሰውነትን ሙሉ አክስቶና አድቅቆ በመጨረሻም ባለቤቱን
ለስቃይ ሞት ይዳርጋል። በዚህም በሰውነት መካከል ያለውን ጤናማ
ትሥሥር ያበላሻል። በራስ ወዳድነትና በሞራል ዝቅጠትም ከራሱ
ብልት ጀምሮ ሙሉ ሰውነትን ለስቃይና ለሞት ይዳርጋል።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 64
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

በሀገርም እንደዚሁ ነው። ማኅበራዊ ትሥሥርንና ካፒታልን


የሚሸረሽሩ ነገሮች መነሻቸው ከአንድ ቡድን ወይንም አካባቢ
ሊሆን ይችላል። የአንድ ዘመን ዕሳቤና አሠራርም ሊሆኑ ይችላሉ።
ከውጪ የተፈጸመ ወረራ ወይንም ተፈጥሯዊ አደጋ ከሆነ
ኅብረተሰብን የማስተባበርና አንድነትን የማጠንከር ባህርይ አለው።
ነገሩ ከዐቅም በላይ የሆነ ቀውስ እስካልሆነ ድረስ የማኅበራዊ
ትሥሥርን የሚያዳብርና የሚያሳድግ ነው። በጣልያን ወረራ ጊዜ
ያየነው ይሄንን ነው። በቅርቡም በሀገራችን ላይ ከውጪ በተፈጠሩ
ፍትሕ አልባ ጫናዎች ጊዜ በ’#NOMORE’ እንቅስቃሴ የታየው
ይሄው ነው። ነገር ግን በራሳችን ውስጥ በሃይማኖትና በብሔር፣
በፖለቲካ ዕይታና በአካባቢ መሠረትና ሰበብ አድርገው የሚፈጸሙ
ሀገር ገዝጋዥና ነቀርሳ ሆነው ማኅበራዊ ትሥሥራችንን የሚበሉና
የሞራል ዝቅጠት የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎችን ተጋፍጠን ትውልድን
ማዳን ይጠበቅብናል።

አሁን ማኅበራዊ ትሥሥራችንና ካፒታላችን በብዙ ምክንያቶች


ተሸርሽሮ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በተጓዳኝ የሚታየው የሞራል
ዝቅጠትና የግብረገባዊነት መላላት ሀገራዊ ወረርሽኝ በሚባል ደረጃ
እየተሠራጨ ይገኛል። የስንፍናና የልመና ባህል፣ የዝርፊያና
በአቋራጭ የመክበር አባዜ የተጠናወተው ሰው ቁጥር ቀላል የሚባል
አይደለም። ግብረገባዊነትና ሥነ-ምግባራዊ ንጽሕና አደጋ ላይ
የወደቀና ለአደጋ የሚዳርግ እንደ ዋልያና ቀይ ቀበሮ እየተመናመነ
ያለ ብርቅዬ ባህርይ ሆኗል። ለዚህም ከጀመርነው የኢኮኖሚ፣
የፖለቲካና የውጭ ግንኙነት ተሐድሶና እመርታዊ ለውጥ እኩል
የማኅበራዊ ትሥሥር /ካፒታል ግንባታችንንና የግብረገባዊ ሥነ-
ምግባር ግንባታ ሥራችንን በትኩረትና በስፋት ልንሠራ ይገባናል።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 65
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ማኅበራዊ ትሥሥርንና ግብረገባዊ ሥነ-ምግባርን


የመገንባት ስልትና ሂደት
የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበረሰባዊ ተቋማት፣
የሚዲያ ተቋማት፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎችና የትምህርት ሥርዓቱ
በተለይ የሀገራችንን የማኅበራዊ ትሥሥር ካፒታልና የግብረገባዊ
ሥነ-ምግባር ግንባታ ላይ ልዩ ኃላፊነትን በመውሰድ ሊረባረቡ
ይገባል። በተለይም ደግሞ ተተኪ ትውልዱን ቀርጾ በማውጣትና
ባለው ትውልድ ላይ ደግሞ አዎንታዊ ተጽዕኖዎችን በማሳደር፣
ያሉ ጉድለቶችን በመሙላትም ሆነ የጠፉብንን ዕሴቶች መልሶ
በመፍጠር ያለባቸው ኃላፊነት ትልቅ ነው። ለዚህ አስፈላጊውን
ፖሊሲና የአሠራር ሂደት መፍጠርና በአርአያነት ያስፈልጋል።
ይሄንንም ለመምራት ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበት በመደመር ዕሳቤ
የሚመራው፣ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ግቡ ያደርገው፣ የፓርቲያችን
አመራር ነው።

በትምህርት ፖሊሲያችንና ትግበራችን ውስጥ ግብረገባዊ ሥነ-


ምግባርን የሚያሠርጹና በተተኪው ትውልድ ውስጥ የማኅበራዊ
ትሥሥር ካፒታልን የሚያሳድጉ እንደ ስፖርት፣ ሙዚቃ፣ ሀገራዊ
አገልግሎት፣ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች፣ አካባቢን የማልማትና
የማጽዳት ባህልን የሚፈጥሩ ተግባራዊ ትምህርቶች ተቀርጸው
ሊሰጡ ይገባል። ለዚህም ሚዲያው፣ የኪነ-ጥበብ ኃይላትና ሲቪክ
ማኅበራት በመላ ሀገራችን ውስጥ ተግተው ሊሠሩ ያስፈልጋል።

በተለይ ግን የሃይማኖት ተቋማት በአሁኑ ጊዜ የሚታይባቸውን


ልዩነትና ቁስ ተኮር አካሄዳቸውን ቀይረው ትውልድና ሞራል ተኮር
ሥራቸውን እንዲሠሩ ሊደፋፈሩና ሊታገዙ ይገባል። ቤተሰብንና
ማኅበረሰብን በግብረገባዊ ሥነ-ምግባር በመገንባት፣ የጎደለውን
የማኅበራዊ ትሥሥር ለመሙላት፣ የመተማመንን፣ የይቅርታንና

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 66
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

የዕርቅን ድር በመፍተልና ሸምኖ ሕዝቡን በማልበስ ከፍተኛ


አስተዋጽዖ ሊያደርጉ ይችላሉ።

ሁሉም ሰውና ሁሉም ተቋም በሚባል ደረጃ ፖለቲከኛነትን


እንደ ፋሽን በተያያዘበት የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን፣ የፖለቲካ ሥራ
ሞያንና ጊዜን የሚጠይቅ፣ በከፍተኛ ሞራልና ጥበብ የሚከወን የላቀ
ጥሪ መሆኑን ለማሳየት የፖለቲካ አመራሩ በብቃት፣ በባህርይና
በሚያሳየው የሥራ ትጋት በልጦ መገኘት ይገባዋል። ቃል የገባውን
ሠርቶ ማስረከብ፣ ሕገ-ወጥነትንና ሥርዓተ አልበኝነትን ፊት
ለፊት መጋፈጥ፣ የማኅበራዊ ትሥሥር ካፒታላችንን የሚሸረሽሩ
ተግባራትን ማስወገድ ይገባዋል። በተጨማሪም ግብረገባዊ ሥነ-
ምግባርን በአርአያነት በማሳየት ተንሠራፍቶ ያለውን ሌብነት፣
ስንፍናና ግዴለሽነት አጥብቆ ሊዋጋ ይገባል። ነገር ግን ግብረገባዊ
ሥነ-ምግባር የሚሰፍነውና ባህል የሚሆነው አመራሩ በቃልና
በተግባር ትጋትን፣ ሠራተኝነትን፣ ታማኝነትን፣ ያገባኛልነትን
ማስተማርና ማሳየት ሲችል ነው።

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 67
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ማጠቃለያ
የለውጥ ችቦ ከተለኮሰበት ወርሃ መጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ
ኢትዮጵያ እንደሃገር፣ እኛም ታሪካዊ ኃላፊነት እንደተረከቡ የለውጥ
መሪዎች በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፈናል። አራቱ ዓመታት
በብዙ ጋሬጣዎች የተሞሉ ነበሩ። ፈተናዎቹ የሚመነጩት ከአንድ
አቅጣጫ ብቻ አይደለም። እንደ ፖለቲካው ሁሉ በኢኮኖሚውም፣
በማህበራዊና በዲፕሎማሲ ዘርፎችም ልዩ ልዩ እንቅፋቶች
እየተጋረጡብን በፈለግነው ልክ ወደፊት እንዳንስፈነጠር ሲያደርጉን
ነበር። ዋልታ ረገጥ የሆኑ የፖለቲከኞች እንቅስቃሴ በዚህ ስንላቸው
በዚያ እየሾለኩ አልጨበጥ ብለው ስንትና ስንት ሀገራዊ ችግሮችን
መቅረፍ የሚያስችለንን ውድ ጊዜ፣ ጉልበትና ሐብት በከንቱ ለማባከን
ተገድደናል። እዚህም እዚያም ሴራና የጦር መሳሪያ ያነገቡ አማጺያን
የሚፈጥሩት ትንኮሳ ሥራችንን በሰላም እንዳንሠራ አድርጎናል።
የሐሳብ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ማስተናገድ በተሳናቸው
ኃይሎች በሚቀሰቀሱ ጦርነትና የአመጻ እንቅስቃሴዎች የምስራቁን
ቋጨን ስንል በምዕራብ እያፈተለከ፣ የደቡቡን መስመር አስያዝን
ስንል ሰሜንና መሐሉ ከመስመር እያፈነገጠ፣ አራቱን ዓመት ልክ
ሀያና ሦላሳ ዓመታት የተቆጠሩበት አስመስሎታል። ከሕዳሴ ግድብ
ሙሌት ጋር ተያይዞ እንዲሁም የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ከውጭ
የተቃጣብን የዲፕሎማሲ አጣብቂኝ በከፍተኛ ፅናት ተቋቁመነው
እስካሁን በመዝለቃችን ነገሩ ቀላል ይመስል ይሆናል እንጂ ሀገርና
መንግሥት የሚያሳጣ ከባድ አደጋ በፈጠረ ነበር። ይኽም ሳይበቃ
ያልታሰቡት የኮቪድ ወረርሽኝና የአንበጣ መንጋ እንዲሁም ሰው
ሰራሽ የሕዝብ መፈናቀሎች የፈጠሩት ጫና በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን
ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሶችን አስከትለውብን አልፈዋል።

በእነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ውስጥ አልፈን ዛሬም አንድ ነገር


እርግጠኛ ሆነን እንናገራለን። የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ ነው።
የከፍታው ጫፍ ሆነን ችግሮቻችንን ከሥር የምንመለከትበት ጊዜ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 68
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

አድካሚ የሆነውን ከፍታ ለመውጣት በምናፈሰው ላብ ልክ እየቀረበ


ይመጣል። ለዚህም ማሳያ የሆኑት መነሻዎቻችን ከገጠሙን
ተግዳሮት በላይ ሆነው ቁልጭ ብለው ይታያሉ። በጩኸት እንዲሸፈኑ
የተደረጉ ድሎች ነገን ለማጠልሸት ከሚደረገው ርብርብ ይልቅ
ጎልተው ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሆነው ይቀርባሉ። ነገር
ግን ድል የትናንት ሥራ ውጤት እና የነገ አመልካች እንጂ የነገ
ዋስትና አይደለም። ዛሬ እየገጠሙን ያሉትንና ነገ ሊገጥሙን የሚሉ
ችግሮችን በመገንዘብ መዘጋጀት አለብን።

ይህ ወቅት የብልጽግና ወቅት ነው። በዚህ ወቅታችን መጠቀምና


ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና መምራት እንዳንችል ዙሪያ ገባ ፈተናዎች
ተደቅነውብናል። እነዚህም ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ወደ ጸጥታ
ችግር፤ የጸጥታ ችግር ወደ ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት በመሻገር
በዴሞክራሲ ምርጫ ያገኘነውን ወቅት... የባከነ ወቅት ለማድረግ
የሚደረጉ ጥረቶች ናቸው። ይህም ሀገራችንን ያለመረጋጋት አዙሪት
ውስጥ ለመክትት የሚደረግ ጥረት ነው። ስለዚህ ይህንን ተገንዝበን፣
የገጠመንን ፈተና ዐውቀን፣ ችግሮችን እየመከትን፣ ወደ ራእያችን
የሚያስኬዱን ግቦቻችንን ለማሳካት ጥረት እናደርጋለን።

በመሆኑም ከመጀመርያው የፓርቲያችን ጉባኤ አቅጣጫዎች


በመነሳት በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንሠራለን።

• የመጀመሪያዊ የአክራሪነትና የጸጥታ ችግሮችን


መከላከል ነው

ኢትዮጵያ ባለብዙ መልክ ሀገር ናት፡፡ አንድና ተመሳሳይ መልክ


ያላት ሀገር አይደለችም፡፡ የብዝሀነት አድማስ ከጫፍ እስከጫፍ
የሚያንጸባርቅባት ሀገር በመሆኗ ይህንን ጸጋዋን ወደ ዕድል
መቀየርና የዜጎቿ መለያ ፈርጥ አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል፡
፡ ከእምነት አኳያ ባለብዙ ቀለም መሆኗን አምኖ በመቀበል
አክራሪነትን መቃወምና ማረም ያስፈልጋል፡፡ የአክራሪነት ምንጩ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 69
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

እኔ ብቻ የሚል ስግብግብና ዋልታ ረገጥ ፍላጎት ነው፡፡ ሁሉም


ዕምነቶች እንደወትሮው ሁሉ ተከባብረውና ተቻችለው የሚኖሩባት
ሀገር እንድትሆን በኃይማኖት ሽፋን የሚፈጸሙ አጥፊ ዝንባሌዎችን
ያለምህረት መታገልና መስመር ማስያዝ ያስፈልጋል፡፡

አክራሪነትን ማዕከል አድርገው ከውስጥም ከውጭም እርስ


በእርስ የሚመጋገቡ ኃይሎች የዘላቂ ሰላማችን ጸር ከመሆናቸውም
በላይ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ዕንቅፋቶች ናቸው፡፡
የአክራሪነት አዝማሚያ እና የታጠቁ ኃይሎች በውስጥና በውጭ
ካሉ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ ከሚፈልጉ ኃይላት
የሚፈጠረውን የጸጥታ ችግር በመከላከልና በመቅረፍ መረጋጋትን
ማስፈን ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ የሁሉም ሀገር መሆኗንና በኢትዮጵያ
ውስጥ ያሉ ሁሉም እምነቶችና የእምነቶቹ ተከታዮች ለሀገራቸው
ዕኩል የባለቤትነትና የኃላፊነት ስሜት ይዘው በሀገራቸው የብልጽግና
ጉዞ ላይ አዎንታዊ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ
በውስጥና በውጭ ከሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች ጋር በግልጽም ሆነ
በህቡዕ ተደራጅተው የሚያደርጉት ያልተገባና ከየእምነቱ ጋር
የሚቃረን አሉታዊ እንቅስቃሴ በየትኛውም መንገድ የማይፈቀድ
ቀይ መስመር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የአክራሪነት ዝንባሌ
ለኢትዮጵያ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ሁነኛ እንቅፋት ስለሆነ
በጋራ መታገልና ማረም ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡

• ሁለተኛው ኢኮኖሚው የደረሰበትን ተጽዕኖ በመቋቋም፣


ከችግሮች በማገገም ይበልጥ እንዲጠናከር ለማድረግ
እየወሰድናቸው ያሉ ርምጃዎችን ማጠናከር ነው።

ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፍ ሁኔታው ተደምሮ የውስጥ


ተግዳሮታችንን ማወሳሰቡ የሚካድ አይደለም፡፡ ውስጣዊ ሁኔታችን
እነዚህ ውጫዊ ሁኔታዎችን መቋቋም ተስኖት የሚያርፍበትን
ተጽዕኖ ብቻ እየተመገበ የሚቀጥል ከሆነ ሁለንተናዊ ጉዟችን
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል፡፡ ቁምነገሩ የአለምአቀፍ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 70
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ተጽዕኖው መብዛትና መወሳሰብ ሳይሆን ይህንን ዘርፈ ብዙ ተጽዕኖ


በውስጥ አቅምና ጥንካሬ መቋቋም የምንችልበት ዘዴና ብልሀት ላይ
ነው ያለው፡፡ ስለሆነም ሁለንተናዊ አቅማችንን በማረባረብ ሙሉ
አቅማችንን ደምረን ወቅታዊና ምንአልባትም በተወሰነ መልኩ ሊቆይ
የሚችለውን አለምአቀፍ ተጽዕኖ መቋቋም የሚችል የማይበገር
ኢኮኖሚ (resilient economy) መገንባት ያስልጋል፡፡

ያጋጠመንና ሊያጋጥመን የሚችለውን መጻኢና ውስብስብ


ተጽዕኖ ተቋቁመን መሻገር የምንችለው በብዝሀ ዘርፍ የልማት
አቅጣጫ ሁሉንም አቅሞቻችንን ደምረን ምርትና ምርታማነትን
ማስፋት ስንችል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የግብርና ምርታችንን
አስፍተንና የግብርና ልማት ሀብትን አሟጦ መጠቀም የሚችል
የአሰራር ዲሲፕሊን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመኸርም
ሆነ በበጋ ወራት የክረምትና የመስኖ እርሻ ልማትን፣ የአትክልትና
የፍራፍሬ ልማትን፣ ከእንስሳት ሀብት ልማት አኳያ በሙሉ
ጉልበት ወደስራ መግባት፣ ከቦታ ቦታ የሚታየውን የአፈጻጸምና
የምርታማነት ክፍተት መሙላትና ማቀራረብ፣ በምግብ ራስን
ከመቻል ባለፈ ለአገር ውስጥ ገበያና ለውጭ ገበያ የሚሆኑ ምርቶች
ላይ የተለየ ትኩረትና ርብርብ ማድረግ ይገባል፡፡

በማዕድን የልማት ዘርፍም ሆነ የኢንዱስትሪ መስኩን በማዘመን


የገቢ ምርትን ሊተኩ የሚችሉ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በማምረት
ራስን የመቻል አቅጣጫ መከተል ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት
የሌለበት የብልጽግና አቅጣጫ ነው፡፡ የአገልግሎት ዘርፉን በተለይም
የቱሪዝም መስክ እንዲዘምንና አውራ የገቢ ምንጭነት ሚናውን
እንዲጫወት የተጀመረውን ሰላም የማስፈን ተልዕኮ ለስኬት ማብቃት
ያስፈልጋል፡፡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር ሙሌት፣ ሁለተኛ
ተርባይን ተከላ፣ ለአፍታም ሳይንገራገጭ በተያዘለት ዕቅድ መሰረት
እዲከናወን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ አጋዥ የሆኑ ሰላምና ጸጥታ
ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው በልዩ ትኩረት መመራት
ይኖርባቸዋል፡፡

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 71
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሌላው የቁጠባና የኢንቨስትመንትን ሚዛን የጠበቀ አመራር


የማረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡ ዜጎች ያላቸውን ጥሪት በቁጠባ የመጠቀም
ባህል የመገንባት ሂደት የሁልጊዜ ስራ መሆን አለበት፡፡ የአለም
ሁኔታ በየጊዜው እየተቀያየረ በሄደ ቁጥር የሚተራመስና ለከፍተኛ
የኢኮኖሚ ጉድለት የሚጋለጥ አገር ባለቤት እንዳንሆን ቀጣይነት
ያለው ተደማሪ አቅም የሚፈጥር በዜጎች አኗኗር ላይ መሰረታዊ
ለውጥ ሊያመጣ የሚችል መሰረታዊ የማምረት አቅም መገንባት፣
በቁጠባ የመጠቀም ባህል፣ ከዕለት ፍጆታ አስተርፎ በቁጠባ ጥሪት
የመያዝ ልምድ እንዲያጎለብቱ ማድረግ ጎን ለጎን የኢንቨስትመንትን
ሚዛን መጠበቅ ይገባል፡፡ ሌላው በሁሉም መስክ የገቢ መሰብሰብ
ዐቅም በትኩረት ልንሠራባቸው የሚያስፈልጉ ጉዳዮች ናቸው።

• ሦስተኛው ደግሞ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን እያሰከኑ በመሄድ


እንዲሁም በኢኮኖሚ የተገኙ መልካም ውጤቶችን
በማጠናከር፣ ችግሮችን ለማረም በነባራዊ ዓለም አቀፍ
ሁኔታ ውስጥ እንዴት እንደምንጫወት በአግባቡ ማሰብ
ነው።

አለም ከአንድ ዋልታ ወደ ብዙ ዋልታ እየተቀየረች ትገኛለች፡፡


በአለም ላይ የተለያዩ ሀገራት ደረጃቸውን ለማሻሻልና ከያዙት ደረጃ
ፈቀቅ ላለማለት ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረጉ በሚገኙበት ወቅታዊ
ሁኔታ ሉአላዊ ክብርንም ሆነ ጥቅምን ጠብቆ ማቆየት በእጅጉ
ፈታኝ መሆኑ አይቀርም፡፡ ጂኦ-ፖለቲካዊም ሆነ ጅኦ-ኢኮኖሚያዊ
አለምአቀፍ ሰጣገባዎች በጣም የተወሳሰቡ ናቸው፡፡ በዚህ ውስብስብ
ሁኔታ ውስጥ ሁልጊዜም ተጎጂ የሚሆኑት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ
በማደግ ላይ ያሉ ድሀ ሀገራት ናቸው፡፡ ሚዛኑን ያልጠበቀ፣
የተወሳሰበና ተገማች ያልሆነ ውድድርና ፉክክር በበዛበት አለምአቀፍ
ሁኔታ የኢትዮጵያ አቋም ወጥና ብሄራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ
መሆን አለበት፡፡

በበለጸጉ ሀገራት መካከል የሚካሄደው ጅኦ-ፖለቲካዊና ጂኦ-

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 72
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ኢኮኖሚያዊ ውድድርና ፉክክር ሚዛኑን በለቀቀ ቁጥር ግጭትና


ጦርነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መከሰቱ አይቀርም፡፡ የሩስያና
የዩክሬን ጦርነት ወደ ተሟላ አለም አቀፍ ጦርነት ላለመግባቱ
ዋስትና የለም፡፡ የቻይናና የታይዋን ጉዳይ ምንአልባትም በቅርብ
ርቀት ሊከሰት የሚችል የታመቀ የግጭት ምክንያት ነው።
ወቅያኖሶችንና አለም አቀፍ መተላለፊያ ካናሎችን እንዲሁም ለጂኦ-
ፖለቲካውና ለጂኦ-ኢኮኖሚው አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥሩ ደሴቶችንና
ጥምረቶችን መነሻ ያደረጉ ፍጥጫዎች መከሰታቸው አይቀሬ ሊሆን
ይችላል፡፡ ዋልታ ለዋልታ በተወጠረው ዓለም አቀፍ ሁኔታ ውስጥ
ሚዛንን በመጠበቅ በነባራዊ ዓለም አቀፍ ሁኔታ ሊደርሱ የሚችሉ
ጫናዎችን መከላከልና ጥቅማችንን በተገቢው መንገድ ማስጠበቅ
እንዴት እንችላለን የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል። ይህ
እንደተጠበቀ ሆኖ ቅድሚያ የሚሰጠውና ሊሰጠው የሚገባው የውስጥ
ጠላትን በማሸነፍ ከውጭ ጠላት ጋር ያላቸውን ትስስር መበጣጠስ፣
ልዩነትን በማጥበብ ውስጣዊ ሁኔታን የመጠበቅ ጉዳይ ነው፡፡

እንደሀገር ፖለቲካውን ማርጋትና ማስከን ቀዳሚ ተግባራችን


መሆን አለበት፡፡ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በማስከበር ውስጣዊ
አንድነታችንን መጠበቅ ህብረ-ብሄራዊ ወንድማችነትንና
እህትማማችነትን የሚያጎለብት ስራ መስራት ለዚህም መትጋት
ያስፈልጋል፡፡ እንደሀገር በበርካታ አውድ ሊታይ የሚችል መዋቅራዊና
ስርአታዊ ችግሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ሁሉም ውዝፍና ጊዜ ወለድ
ችግሮች በአንድ ለሊት ሊቀረፉ አይችሉም፡፡ ዛሬ ማከም ያለብንን
ወቅታዊ ችግር በትግል ማረም ያስፈልጋል፡፡ የግለሰብ፣ የቡድንም
ሆነ የመዋቅር ሚዛናችን ተጨባጭ ውጤትን ማዕከል ያደረገ መሆን
ይገባዋል፡፡ ወቅታዊ ተግዳሮቶቻችንን ማሸነፍ የሚያስችል የተግባር
ስምሪት በማድረግ ተስፋ ሰጭ ለውጥ ያረጋገጠው ማን ነው ከሚል
ውጤት ተኮር ሚዛን ወይም መለኪያ መነሳት ይገባል፡፡

ከለውጥ ወዲህም ሆነ ከለውጥ በፊት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን


ለመፍታት ሁሉም ዜጋና በየደረጃው የሚገኝ አመራር፣ አባልም

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 73
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ሆነ መዋቅር ኃላፊነት አለበት፡፡ ከዚህ አኳያ ስብሰባዎቻችን፣


ስልጠናዎቻን፣ አጠቃላይ ስምሪታችን ውጤት ተኮር ሚዛን ውስጥ
መግባት ይኖርበታል፡፡ ወቅታዊ ችግርን ውጫዊ ከማድረግ ተቆጥበን
የየአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ በተጨባጭ ማረጋገጥ፣ ከአሁን ቀደም
ያረጋገጥናቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድሎችን ጠብቆ የበለጠ
ማስፋትና ከፍ ያለ ደረጃ ማድረስ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና አለማቀፋዊ
ተጽዕኖን በሁሉም መስክ ሊገዳደር የሚችል ሁለንተናዊ ብቃት
መገንባት ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ቢሆንም በተለይም
ከአመራሩና ከብልጽግና ፓርቲ አባላት በእጅጉ የሚጠበቅ ህዝባዊ
አደራ ነው፡፡

• የመጨረሻውና አራተኛው የመሪዎችን፣ የተቋማትንና


የሀገርን ህልውና እየተፈታተነ ያለውን የማኅበረሰባዊ
ትሥሥር ካፒታል ግንባታና የግብረገባዊ ሥነ-ምግባር
ተሐድሶ ማምጣት ነው።

ይሄኛው ጉዳይ ከላይ ከተዘረዘሩት ሦስት ጉዳዮች ጋር


የሚተሣሠር ነው። ባለፉት ዐሥርተ ዓመታት የተሸረሸረውን
የማኅበራዊ ትሥሥር ካፒታላችንን ከኢኮኖሚውና ከፖለቲካው
ሳይነጠል መሳ ለመሳ ልንሠራበት ይገባል። ለዚህ ደግሞ የዜጎች፣
የመሪዎችና የተቋማት ግብረ-ገባዊ ሥነ-ምግባር ላይ ሊሠራ
ይገባል። ዕንቅፋቶቻችን የሆኑ ድንጋዮችን ተጠቅመን ወደ ራእያችን
የምንገሠግሥበትን መንገድና ድልድዮች እንሠራለን። በመንገዶቹ
ላይ ሄደን እንደርሳለን፣ ዕንቅፋቶቻችንን ትግሎቻችን ብቻ ሳይሆን
ዕድሎቻችን አድርገን በማየት ድልን እንቀዳጃለን።

ያሳለፍናቸውና ያለፍንባቸው ጊዚያት በእጅጉ የተወሳሰቡ ቢሆንም


ቅሉ ውስብስብ ችግሮችንን እንደመሸጋገርያ ድልድይ ተጠቅመን
በድል ላይ ድል የምናስመዘግብ ብርቱ ተጨዋች ሆነን መገኘት
አለብን፡፡ በእንቅፋቶች የምንሰላችና የምንደክም መሆን የለብንም፡፡
ከፊት ለፊታችን አዘውትረው የሚያጋጥሙንን እቅፋቶች ተላምደን

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 74
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

በመዘናጋት የምንኖር ዝንጉዎች መሆንም የለብንም። ሁል ጊዜም


ቢሆን ለሀገራዊ ርዕይ ስኬት መትጋት አለብን። ከርእያችን
የሚያስቆመን ለአፍታም ቢሆን ከጉዟችን የሚገታን እንቅፋት
መኖር የለበትም፡፡ ይልቁንም እንቅፋቶቻችንን ሁሉ ወደ ዕድል
በመቀየር የመዋቅራችንን ታማኝነትና አቅዶ የመፈጸም ወሳኝ ብቃት
ማጎልበት ይኖርብናል፡፡

መሪ ሁልጊዜም ቢሆን ምሳሌ መሆን አለበት፡፡ ስለሆነም በአሉታ


የሚነሱብንን የግብረ-ገብነት ችግሮች በግልጽ ታግለን ማሸነፍ
ይኖርብናል፡፡ ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ በሚል ከትላንትና
ዕንቅፋቶቻችን ጋር ስንነጻጸር አንድና ያው ሆነን መገኘት በፍጹም
የለብንም፡፡ ትላንት በትግል ያሸነፍናቸውን ችግሮችና ለለውጥ ገፊ
ምክንያት አድርገን የተጠቀምንባቸውን ዘርፈብዙ ተግዳሮቶች ዛሬ
ላይ የምናሽሞነሙናቸውና ተለማምደናቸው የምንቀጥል ከሆነ
በምናውቃቸው ችግሮች ተጠልፈን በገዛ ፈቃዳችን ለመውደቅ
የተዘጋጀን ከንቱዎች እንሆናለን፡፡ ስለሆነም ዕንቅፋቶቻችንን ሁሉ
ጥሰን ወደፊት መስፈንጠር የምንችልና ተግዳሮቶቻችንን ሁሉ
ተገዳድረን አገርና ህዝብ የምናሻግር ከፊት ለፊታችን ያለውን
ግዙፍ ተራራ ወጥተን በድል ከፍታው ጫፍ ላይ የምንደርስ መሆን
ይኖርብናል፡፡

ሲጠቃለል የፓርቲያችን የመጀመርያው ጉባኤ በውል ለይቶ


ያስቀመጣቸውን ወሳኝ አቅጣጫዎች ልቅም አድርጎ መፈጸምና
በተጨባጭ የለውጥ ዕምርታ ማረጋገጥ ከላይ እስከታች ያለው
የመዋቅራችን አሁናዊ ግዴታና ኃላፊነት ነው፡፡ ከለውጥ ወዲህ
የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራትና የተሳኩ ውጤቶች የመኖራቸውን
ያህል አክራሪነትና ጽንፈኝነት የወለዳቸው ህዝብ ያስመረሩና ለዜጎች
አንጻራዊ ሰላምና የመልማት አቅም እንቅፋት የሆኑ ተግዳሮቶችም
ዕልፍ ናቸው፡፡ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘም ህዝብን ተስፋ
ያስቆረጡ የተለያዩ ዕንቅፋቶች በየመዋቅሩ ደጃፍ ላይ ተኮልኩለውና
ተሰድረው ይገኛሉ፡፡ ወጣቶችና ሴቶች በተለይም ከተለያዩ ከፍተኛ

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 75
ልሳነ-ብልፅግና ሰኔ 2014 ዓ.ም

ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በስራ


አጥነት ችግር ተተብትበው መድረሻ በማጣት ህሊናዊ ሁኔታ ውስጥ
የሚገኙ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ የተደራጀ ስርቆትና ዘረፋ፣
በዘመድ አዝማድ መስራት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ተነሳሽነት ዝቅተኛ
መሆን፣ መሰረታዊ የሆነ የኑሮ ውድነትና የገበያ አለመረጋጋት
እንገነባዋለን ብለን ለምናልመው ሁለንተናዊ ብልጽግና ሁነኛ
ተግዳሮት ነው፡፡

ስለሆነም መፍጠን አለብን፡፡ በተለመደው ቀርፋፋ አካሄድ


የሚፈታ ችግር የለም፡፡ የችግሮቻችንን ፍጥነት የእንቅፋቶቻችንን
ስፋት ሊገዳደር የሚችል በጣም ፈጣንና ተደራሽ የሆነ አመራር
ማረጋገጥ ካልቻልን ከፊት ለፊታችን የሚታይ አደገኛ የቁልቁለት
ጉዞ አለ፡፡ ወደ ተራራው የመጨረሻ ጫፍ ለመድረስ የጀመርነውን
ጉዞ ድንገት ከለቀቅነው ወደየትኛው ገደል እንደምንፈጠፈጥ መገመት
እንኳን ያስቸግራል፡፡ ይህንን አደገኛ የመንሸራተትና የተራራውን
ከፍታ ለቅቆ ወደ ቁልቁል የመሽቀንጠር ዕጣ ፋንታ መፍቀድ ቀርቶ
ማሰብ በፍጹም የለብንም፡፡ የጀመርነውን ጉዞ ወደ ከፍታ ማምጣት
የሚያስችል ጎላ ያለ ተስፋና ዘርፈ ብዙ አማራጭ ያለን መንገደኞች
ነን፡፡

ለፈተናዎቻችን ሳንበገር የጀመርነውን የከፍታ ጉዞ አጠናክሮ


ማስቀጠልና የሀገራችንን ህልውና በሁለንተናዊ ብልጽግና ቀይረን
የዜጎቻችንን ተስፋ ማለምለም አለብን፡፡ ያለን ብቸኛ አማራጭም
ይኸው ብቻ ነው፡፡ በስድስተኛው ምርጫም ሆነ በአጠቃላይ
የብልጽግና ጉዟችን እናሳካዋለን ብለን የገባነውን ቃል ማረጋገጥ
አለብን እንችላለንም፡፡ ከችግሮቻችን ፍጥነት በላይ እንፍጠን፤
ከእንቅፋቶቻችን ስፋት በላይ ስምሪታችንን፣ ርብርባችንንና
ስኬታችንን እናስፋ፤ በመጨረሻ የምናሸንፍና ወደ ከፍታው
በመብረር የተራራውን ጫፍ የምንጨብጥ በእርግጥም ርዕያችንን
የምናሳካ መሆን አለብን፡፡

2ኛ ዓመት ቅፅ 1 ቁጥር 3 76

You might also like