You are on page 1of 22

2012

ለ2ኛው ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የቴክኖሎጂ፣


የክህሎት እና ተግባራዊ ምርምር ውድድርና
ሲምፖዚየም የተዘጋጀ የጋራ ዕቅድ

ጥቅምት 2012ዓ.ም
ይዘት
 መግቢያ
 የጋራ ዕቅዱ አስፈላጊነት
 የዕቅዱ ዓላማ
 ዋና እና ዝርዝር ተግባራት
 የአመራርና የአፈጻጸም አደረጃጀቶች
 የክትትልና ድጋፍ አግባብ
 ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና መፍትሄ
 የድርጊት መርሃ-ግብር
መግቢያ
• የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከላት ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪ
የሚያደርግ ምርጥ ቴክኖሎጂ በማቀብና በማሽጋገር፤ ምርታማ የሆነ ዜጋ
በመፍጠር ለማህበራዊና ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ ለማበርከት እርብርብ
እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፤
• ይሁን እንጂ ከሚፈለገው የተወዳዳሪ ቴክኖሎጂ እና እንዲሁም የበቃ የሰው
ሃይል በሚፈለገው ደረጃ ከማቅረብ አንፃር ርብርብ የሚጠይቅ ሲሆን፤
• ለዚህም አሁን ያለውን አጠቃላይ የአፈጻጸም ችግር ለመፍታት መወሰድ
ካለባቸው ወሳኝ እርምጃዎች አንዱ በአገር አቀፍ ደረጃ የክህሎት እና
የቴክኖሎጂ ውድድር፣ አውደ ርዕይ እና የምርምር ኮንፍረንስ በማካሄድ
በአሠልጣኝ፣ በሠልጣኝ፣ በኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች እና በሌሎች
ምሁራን ዘንድ የውድድርና የተነሳሽነት መንፈስ በመፍጠር ሀገራዊ ተልኮን
መወጣት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን በመረዳት ለዚህም
አፈፃፀም ይረዳ ዘንድ ይህ የጋራ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
የጋራ ዕቅድ አስፈላጊነት

 1ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የዘርፉ ሲምፖዚየም ላይ ከፍተኛ የሆነ ተነሳሽነትን


የፈጠረ ከመሆኑም ባሻገር የነበሩ ድክመቶችን በማረም በቅንጅት በ2ኛው
ዙርም አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ፤
 በተቋም፣ በክላስተር፣ በክልል እና በፌደራል ደረጃ ስኬታማና ውጤታማ
ተግባራትን ለማከናወን አስፈላጊ መሆኑ፤
የዕቅዱ ዓላማ

 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እና የቴክኒክና


ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የተናበበና የተቀናጀ
አሠራርን በመዘርጋት በየደረጃው የክህሎት፣ የምርምር እና
የቴክኖሎጂ ውድድር ለማካሄድ በአሰልጣኝ፣ በሠልጣኝ፣
በኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች እና በሌሎች የዘርፉ
ምሁራን ዘንድ ለውድድር ተነሳሽነትን መፍጠር የሚያስችል
የጋራ አደረጃጀት እና ስልት እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡
ዋና እና ዝርዝር ተግባራት
 የጋራ እቅድ ማዘጋጀት
 የአሰራር ሰነዶችን ማዘጋጀት
 የጋራ ዕቅዱንና የአሰራር ሰነዶችን ለሚመለከታቸው አመራርና ፈጻሚዎች
ማስተዋወቅ
 በፌዴራል ደረጃ ስራውን የሚመሩና የሚያስፈጽሙ አደረጃጀቶችን
መፍጠር
 ለክህሎት ውድድር ሙያዎችን መምረጥ
 የክህሎት ውድድር መሳሪያዎችን ማዘጋጀትና ግብዓቶችን ማሟላት
 በየደረጃው ውድድር መካሄዱን መከታተል እና መረጃ ማሰባሰብ
 ዳኞችን መምረጥ እና ማሰማራት
 ለውድድሩ እና ለተያያዥ መድረኮች አስፈላጊ ሁኔታዎችን ማሟላት
 ውድድሩንና ተያያዥ መድረኮችን ማካሄድ
የአመራርና የአፈጻጸም አደረጃጀቶች
 የአብይ ኮሚቴ አባላት
 የቴክኒክና ሙ/ት/ስ/ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ……………………(ሰብሳቢ)
 የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ት/ስ/ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር………(ም/ሰብሳቢ)
 የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ት/ስ/ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር……...(አባል)
 የፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ የስልጠናና ተ/አ/ግ/ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር
(አባል)
 የፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ የኢ/ሞ/ሙ/ደ/ብ/ም ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር
(አባል)
 የፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ የአመራርና አ/ሰ/ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር
(አባል)
 የፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት የቴ/ሽ/ምርምር ም/ዋና ዳይሬክተር
(አባል)
 የፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት የአካዳሚክ ም/ዋና ዳይሬክተር (አባል)
 የፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት የአስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር
(አባል)
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
• የአብይ ኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት
 ተዘጋጅቶ የቀረበለትን እቅድ ያጸድቃል፤
 ኦፕሬሽናል ኮሚቴን ያቋቁማል፤
 ለስራው ማስፈጸሚያ በጀት ይመድባል፤
 ለክልሎች ድጋፍ ያደርጋል፤
 በየወሩ በኦፕሬሽናል ኮሚቴው የሚቀርብለትን፤ ሪፖርት
እየገመገመ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 ኦፕሬሽናል ኮሚቴ አባላት
 የፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ የስ/ተ/አ/ ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር (ሰብሳቢ)
 የፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ሥ/ ኢንስቲትዩት የቴ/ሽ/ምርምር ም/ዋና ዳይሬክተር (ም/ሰብሳቢ)
 በፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤ/ የሰልጠና አ/ኤ/ቴ/ሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር (አባል)
 በፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤ/ የተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር (አባል)
 በፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤ/ የኢ/ሞ/ሙ/ደ/ብ/ ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር (አባል)
 በፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ሕ/ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር (አባል)
 በፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/ኢ የቴክኖሎጂ ቅ/ክ/ሽ/ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር (አባል)
 በፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት የጥ/ም/ ዳ/ዳይሬክተር (አባል)
 በፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ የኢ/ሞ/ሙ/ደ/ብ/ም/ ዘርፍ ም/ዋ/ዳ (አባል)
 በፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ የአመራርና አ/ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር (አባል)
 በፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ የዋና ዳይሬክተር አማካሪ (አባልና ፅኃፊ)
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት
 የቴክኒክ ኮሚቴዎችን ይደግፋል፣ ወቅቱን የጠበቀ አቅጣጫ ይሰጣል፤
 ከቴክኒክ ኮሚቴዎች የቀረቡለትን የበጀት ጥያቄዎች አጠናቅሮ በአቢይ
ኮሚቴ ያጸድቃል፤
 ለክልሎችና ለክላስተሮች በእቅዱ ላይ ግንዛቤ ይፈጥራል፤
 ክላስተሮችንና ክልሎችን በአካል በመገኘት ይደግፋል፤
 በየ15 ቀኑ እየተሰባሰበ ስራዎችን ይገመግማል፤

 ቴክኒካል ኮሚቴዎችንና እንዳስፈላጊነቱ ሌሎችን ኮሚቴዎችን ያደራጃል፤

 ለአብይ ኮሚቴው በየወቅቱ ሪፖርት ያቀርባል፡፡


አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 ቴክኒካል ኮሚቴዎች አባላት (ለቴክኖሎጂ ዉድድር)
• የሰልጠና አ/ኢ/ኤ/ቴ/ሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ………………….ሰብሳቢ
• ከፌ/ቴ/ሙ/ስ/ኢንስቲትዩት ቴ/ሽግግር ቡድን ……………………….አባል
• ከቴክኒክና ሙያ ት/ስ/ኤጀንሲ 4 ባለሙያዎች ……………………...አባል
• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ኢንስቲትዩት 2 ባለሙያዎች ………………………….አባል
• የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ………………………….አባል
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ ኤ/ኤ/ቴ/ሽ/ ቡድን መሪ …………...አባልና ፅሃፊ
 የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት
• የቴክኖሎጅ ማወዳደሪያ መመሪያ ያዘጋጃል፤
• በክልል ደረጃ አሸናፊ የሆኑትን ተወዳዳሪዎችን መረጃ ያጠናቅራል
• የቴክኖሎጂ ውድድር ዳኞችን ይመለምላል፤
• ለአሸናፊዎች የሽልማት አይነት ለይቶ ለኦፐሬሽናል ኮሚቴ ያቀርባል፤
• ለክልሎችና ለክላስተሮች ድጋፍ ይሰጣል፤
• ተወዳዳሪዎች ከነቴክኖሎጂያቸው በወቅቱ ለውድድሩ እንዲገኙ ያስተባብራል፤
• በየሳምንቱ እየተገናኘ የስራ አፈጻጸሙን ይገመግማል ለኦፕሬሽናል ኮሚቴው ሪፖርት
ያቀርባል፤
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 ቴክኒካል ኮሚቴዎች አባላት (ለክህሎት ዉድድር)
• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢ የቴክኖሎጂ ቅ/ክ/ሽ/ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር …..ሰብሳቢ
• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት 2 ባለሙያዎች ………………………..አባል
• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ 3 ባለሙያዎች ………………………………አባል
• ከፌ/ቴ/ሙ/ ስልጠና አሰጣጥ ቡድን መሪ ……………….…..አባልና ፅሃፊ
 የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት
• የክህሎት ማወዳደሪያ መመሪያ ያዘጋጃል፤
• ውድድር በሚካሄድባቸው ሙያዎች መወዳደሪያ መሳሪያ (ፕሮጀክት) ዝግጅት
ያስተባብራል፤
• ለክልሎችና ለክላስተሮች ድጋፍ ያደርጋል፤
• የተወዳዳሪዎችን ፕሮፋይል ይይዛል፤
• አወዳዳሪ ዳኞችን ይመለምላል፤
• ለውድድሩ አሸናፊዎች የሚሆን ሽልማት ፕሮፖዛል አዘጋጅቶ ለኦፕሬሽናል ኮሚቴው
ያቀርባል፤
• በየሳምንቱ እየተገናኙ የስራ ግምገማ ያካሂዳል፣ ለኦፐሬሽናል ኮሚቴው ሪፖርት
ያደርጋል፤
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ኮሚቴ አባላት

• ከፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር...


…………………………………………………..……ሰብሳቢ

• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት 2 ባለሙያዎች ……………………….አባል

• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ 2 ባለሙያዎች ………………………………አባል


 የኮሚቴው ተግባርና ሃላፊነት

• ማወዳደሪያ መመሪያ ያዘጋጃል፤


• ለክልሎችና ለክላስተሮች ድጋፍ ያድርጋል፤
• የተወዳዳሪዎችን ፕሮፋይል ይይዛል፤
• አወዳዳሪ ዳኞችን ይመለምላል፤
• ለውድድሩ አሸናፊዎች የሚሆን ሽልማት ፕሮፖዛል አዘጋጅቶ ለኦፕሬሽናል ኮሚቴው ያቀርባል፤
• በየሳምንቱ እየተገናኙ የስራ ግምገማ ያካሂዳል፣ ለኦፕሬሽናል ኮሚቴው ሪፖርት ያደርጋል፤
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 የሎጅስቲክስና ሀብት አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት
• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ኤ/ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳሬክተር………..ሰብሳቢ
• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ኢ/ የፋይናንስ ግዥ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር …………….ም/ሰብሳቢ
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ የፋይናንስ ግዥ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ………….አባል
• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ኢ/ የእ/በጀ/እና ሀብት ማፈላለግ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር……...አባል
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ ሰው ሃብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር …………አባል
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ተ/አ/ ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር…………አባል
• ከቴ/ሙ/ት/ስ/ኤ/ የእ/በ/ሀብት ማፈላለግ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር …..አባልና ፅሃፊ
 የኮሚቴው ተግባርና ሃላፊነት
• ከላይ ከተጠቀሱት ኮሚቴዎች እቅድ በመነሳት የራሱን እቅድ ያዘጋጃል፤
• ለዝግጅቱ የሚሆን ስፖንሰር ያፈላልጋል፤
• ሁለቱም ተቋሞች ለዝግጅቱ በጀት እንዲይዙ አጥንቶ ያቀርባል፤
• ለዝግጅቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በወቅቱ ገዝቶ ያቀርባል፤
• ቢያንስ በየ15 ቀኑ እየተገናኘ ስራዎችን ይገመግማል ለአቢይ ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባል፤
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 ፓናል ውይይት አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤ/ የኢ/ሞ/ሙ/ደ/ም/ብ/ ምዘና ዘርፍ ም/ዋና
ዳይሬክተር…………………………………………………………..ሰብሳቢ
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት አካዳሚክስ ም/ዋና ዳይሬክተር….ም/ሰብሳቢ
• በፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት 1 ባለሙያዎች…………………..…..አባል
• በፌቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ 1 ባለሙያዎች………………………...አባል
• የፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ ተቋማት አ/ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አባል
 የኮሚቴው ተግባርና ሃላፊነት
• ኮሚቴው የራሱን እቅድ ያዘጋጃል፤
• የፓናል ውይይት ጽሁፎችን መለየትና ማዘጋጀት፤
• የፓናል ውይይት ተሳታፊዎችን ይለያል፤
• የፓናል ውይይት ላይ ሰነድ ያቀርባል፤
• የፓናል አወያዮችን ይመለምላል፤ ይመድባል፤
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባላት
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤ ሕ/ግ/ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ……………...ሰብሳቢ
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኢ የሕ/ግ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር……………ም/ሰብሳቢ
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኢንስቲትዩት 2 ባለሙያዎች ……………………አባል
• ከፌቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ 2 ባለሙያዎች ……………………..አባል
 የኮሚቴው ተግባርና ሃላፊነት
• ኮሚቴው የራሱን እቅድ ያዘጋጃል፤
• የውድድሩን እና የሲምፖዚየሙን አላማ የሚገልጽ ጹፎችን ያዘጋጃል፤
• ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ውድድሩና ሲምፖዚየሙ በህዝብ
ግንኙነት እንዲታጀብ ያደርጋል፤
• የቴክኖሎጅ ሲምፖዚየሙ በህዝብ እንዲጎበኝ ጥሪ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፤
• ዝግጅቱ ሁሉም የሚዲያ አውታሮች ሽፋን እንዲሰጡት ያስተባብራል፤
• ስራዎችን በየሳምንቱ ይገመግማል ለአብይ ኮሚቴውም ሪፖርት ያደርጋል፡፡
አደረጃጀቶች የቀጠለ………
 የእንግዳ ጥሪ እና ሽልማት ዝግጅት ኮሚቴ

• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


ዳይሬክተር …………………………………..ሰብሳቢ
• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ 3 ባለሙያዎች……………………..አባል

• ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኢንስቲትዩት 1 ባለሙያ…………………...አባል
 የኮሚቴው ተግባርና ሃላፊነት

• ተገቢ የሆኑትን የዝግጅት ተሳታፊዎችን ይለያል፤

• ለታዳሚዎች በወቅቱ ጥሪ ያደርጋል፤


• ለሁሉም የውድድር ዓይነቶች ሽልማት ያዘጋጃል፤

• ለሁሉም የውድድር አሸናፊዎችና/ተሳታፊዎች ሽልማትና ዕውቅና ይሰጣል፡፡


የክትትልና ድጋፍ አግባብ

• ዕቅዱ በአጠቃላይ በአብይ ኮሚቴው የሚመራ ሲሆን


ኦፕሬሽናል ኮሚቴ ለየተግባራቱ በሚያደራጃቸው
ቴክኒካል ኮሚቴዎች አፈጻጸም ላይ የቅርብ ክትትልና
ድጋፍ በማድረግ እያንዳንዱ ተግባር ከሚጠበቅበት
ውጤትና ከተቀመጠለት ጊዜ-ገደብ አንጻር ግምገማ
በማካሄድ ለአቢይ ኮሚቴው ሪፖርት እንዲያደርግ
ይጠበቃል፡፡
ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና መፍትሄ
 ችግሮች

• ከፍተኛ አመራር በተለያዩ ወቅታዊ እና ደራሽ ስራዎች መጠመድ፤


• የኮሚቴዎች በተያዘላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት አለመደራጀትና ተገናኝቶ
ወደ ስራ ያለመግባት አለመስራት፤
• ለሥራው የተመደቡ አመራሮችም ይሁን ባለሙያዎች ተግባሩን እንደ መደበኛ
ሥራ አይተው ትኩረት አለመስጠት፤
• የገንዘብ፣ የባለሙያና የሌሎች ግብዓቶች እጥረት፤
• የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ስራዎች በዕቅዱ መሰረት አለማከናወን፤

• የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር መጓደል እና ሌሎች


ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና መፍትሄዎች
 የመፍትሄ ሃሳቦች
• ከፍተኛ አመራሩ ለጋራ ሥራው ትኩረት በመስጠት ደራሽ ሥራዎችን የእቅዱ አካል
አድርጐ እንዲንቀሳቀስ የኦፕሬሽናል ኮሚቴ ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል
• የሚያደራጁና የሚከታታሉ አካላት ኮሚቴዎችን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት
እንዲያደራጁና ወደ ስራ እንዲያስገቡ ከገቡም በኋላ ጠንካራ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ
ማድረግ ያስፈልጋል
• ለሥራው የተመደቡ አመራሮችም ይሁን ባለሙያዎች ተግባሩን የራሳቸው
ቢ.ኤስ.ሲ. ዕቅድ አካል እንዲያደረጉትና በአፈጻጸሙም እንዲለኩበት ማድረግ
• ለጋራ ዕቅዱ መፈጸም አስፈላጊ የሆነው በጀት መመደቡን ማረጋገጥና የአስፈላጊ
ግብዓቶች ግዥ በወቅቱ መፈጸሙን እና ትክክለኛው ባለሙያ ተገኝቶ መመደቡን
መከታተል
• በጋራ ዕቅዱ በተቀመጠው የድርጊት መርሃ-ግብር መሰረት የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ
ስራዎችን ማከናወን
• በሚመለከታቸው አካላት ዘንድ የቅንጅት ስራ አስፈላጊነት ላይ ተገቢውን ግንዛቤ
በመፍጠር ከወዲሁ የዕቅዳቸው አካል እንዲያደርጉት የሚያስችል የተግባቦት ስራ
መስራት
የድርጊት መርሃ-ግብር

• የድርጊት መርሃ-ግብር
 በተቋም ደረጃ እስከ ጥር 30/2012ዓ.ም
 በክላስተር ደረጃ እስከ የካቲት 30/2012ዓ.ም
 በክልል ደረጃ እስከ መጋቢት 15/2012ዓ.ም
 በፌዴራል ደረጃ እስከ መጋቢት 30/2012ዓ.ም የሚከናወን
ይሆናል፡፡
አመሰግናለሁ!!

You might also like