You are on page 1of 7

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

26th Year No.6


ሃያ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፮ ADDIS ABABA 9th Junuary, 2020
አዲስ አበባ ታህሣሥ ፴ ቀን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ
Content
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፷፫/፪ሺ፲፪ ዓ.ም Proclamation No. 1163/2019
Insurance Business (Amendment) Proclamation …Page 12071
የመድን ሥራ /ማሻሻያ/ አዋጅ…………ገጽ ፲፪ሺ፸፩
ማረሚያ ቁጥር ፲፬/፪ሺ፲፪......................ገጽ ፲፪ሺ፸፯ Corrigendum No.14/2020…………………………Page 12077

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፷፫/፪ሺ፲፪ PROCLAMATION No. 1163/2019

የመድን ሥራ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ A PROCLAMATION TO AMEND INSURANCE


BUSINESS PROCLAMATION
የመድን ሥራ አዋጅ ቁጥር ፯፻፵፮/፪ሺ፬ን ማሻሻል WHEREAS, it has become necessary to amend
አስገፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ the Insurance Business Proclamation No.746/2012;

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ NOW, THEEFORE, in accordance with Article


መንግሥት አንቀጽ ፶፭ (፩) መሠረት የሚከተለው 55 (1) of the Constitution of the Federal Democratic
ታውጇል:- Republic of Ethiopia, it is hereby proclaimed as
follows:
፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የመድን ሥራ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር 1. Short Title
This Proclamation may by cited as “Insurance
፩ሺ፩፻፷፫/ ፪ሺ፲፪” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
Business (Amendment) Proclamation No.
፪. ማሻሻያ 1163/2019.”
የመድን ሥራ አዋጅ ቁጥር ፯፻፵፮/፪ሺ፬ 2. Amendment
እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡፡ The Insurance Business Proclamation
፩/ የአዋጁ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ (፰) እና (፲፪) No.746/2012 is hereby amended as follows.
ተሰርዘው በሚከተሉት ንዑስ አንቀጾች ተተክተዋል:- 1/ Sub Article (8) and (12) of Article 2 of the
Proclamation are deleted and replaced by the
፰/ “ኩባንያ” ማለት በንግድ ሕግ የተሰጠውን following new Sub Articles (8) and (12):
ትርጉም የያዘ ሆኖ አክሲዮኖቹ በሙሉ 8/ “company” means a share company as
በኢትዮጵያውያን ወይም የኢትዮጵያ ተወላጅ defined under the Commercial Code, the
በሆኑ የውጭ ዜጎች ወይም በኢትዮጵያውያንና capital of which is owned fully by
የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆኑ የውጭ ዜጎች በጋራ Ethiopian nationals or foreign nationals of
የተያዘ ወይም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን Ethiopian origin or jointly owned by
ወይም የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆኑ የውጭ ዜጎች Ethiopian nationals and foreign nationals
of Ethiopian origin, or organizations
የተያዘ ወይም በኢትየጵያውያን እና
owned fully by Ethiopian nationals or
የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆኑ የውጭ ዜጎች በጋራ
foreign nationals of Ethiopian origin or
ባለቤትነት በተቋቋሙ ድርጅቶች የተያዘ፣

ÃNÇ êU nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1


Unit Price Negarit G. P.O.Box 80001
gA ፲፪ሺ፸፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፮ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.6, 9th Junuary,2020….page 12072

በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የተመዘገበና ዋና jointly owned by Ethiopian nationals and


መሥሪያ ቤቱ በኢትዮጵያ የሆነ አክሲዮን foreign nationals of Ethiopian origin,
ማኅበር ነው፣
፲፪/ ‘‘የፋይናንስ ድርጅት” ማለት መድን ሰጪ 12/ ‘‘financial institution” means an
ኩባንያ፣ ባንክ፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም፣ insurance company, a bank, a micro
የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ኩባንያ፣ የጠለፋ finance institution, a capital goods
መድን ሰጪ፣ አነስተኛ መድን ሰጪ፣ finance company, a reinsurer, a micro
የፖስታ ቁጠባ ድርጅት፣ የሐዋላ ድርጅት፣ insurance provider, postal savings,
በዲጅታል ዘዴዎች የፋይናንስ አገልግሎት money transfer institution, digital
የሚሰጥ ድርጅት ወይም ብሔራዊ ባንክ financial service provider or such other
institution as determined by the
በሚወስነው መሠረት በዚህ ዘርፍ ሥር
National Bank;”
የሚመደብ ሌላ ድርጅት ነው፤
፪/ ከአዋጁ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ (፴፯) ቀጥሎ 2/ The following new Sub-Articles (38, 39, 40,
የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጾች (፴፰፣ ፴፱፣ 41, 42, 43, 44, 45, and 46) are added after
፵፣ ፵፩፣ ፵፪፣ ፵፫፣ ፵፬፣ ፵፭፣ እና ፵፮) Sub Article (37) of Article 2 of the
ተጨምረው ከንዑስ አንቀጽ ፴፰ እስከ ፵ ያሉት Proclamation, and the subsequent Sub-
እንደቅደም ተከተላቸው ከ፵፯ እስከ ፵፱ ሆነው Articles (38) to (40) are renumbered as Sub
ተሸጋሽገዋል:- Articles (47) to (49), respectively:

፴፰/ “በዲጅታል ዘዴዎች የሚሰጥ የፋይናንስ 38/ “digital financial service” means financial
አገልግሎት” ማለት በዲጅታል ዘዴዎች services including payments, remittances
የሚሰጡ የክፍያ፣ የሐዋላ እና የመድን and insurance accessed and delivered
አገልግሎቶችን ያጠቃልላል፤ through digital channels;”
፴፱/ “ታካፉል” ማለት ሰዎች የተወሰነ የገንዘብ 39/ “takaful” means a cooperation between
መዋጮ ከማህበራቸው አባሎች በመሰብሰብ members of a community whereby each
በአባሎቻቸው ላይ ለሚደርስ ጥፋት (loss) member undertakes to contribute a
ወይም ጉዳት(damage) ቀደም ብሎ በተወሰነ certain sum of money to a fund which
የገንዘብ ልክ ለመርዳት የሚያቋቁሙት will be used mutually to assist the
members against a defined loss or
ኅብረት ነው፤
damage;
፵/ “የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ 40/ “foreign national of Ethiopian origin”
ኢትዮጵያዊ” ማለት የኢትዮጵያ ተወላጅ means a foreign national of Ethiopian
የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራቸው origin as defined under Proclamation No.
የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ 270/2002 Providing Foreign Nationals of
በወጣው አዋጅ ቁጥር ፪፻፸/፲፱፻፺፬ ላይ Ethiopian Origin with Certain Rights to
የተሰጠውን ትርጓሜ ይይዛል፣ be Exercised in their Country of Origin;”
፵፩/ “መድን ሰጪ ኩባንያ” ማለት የመድን ሥራ 41/ “insurance company” means a company
እንዲሰራ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው licensed by the National Bank to
undertake insurance business or an
ኩባንያ ወይም በመንግሥት ባለቤትነት
insurance company owned by the
የተያዘ መድን ሰጪ ነው፤
Government;”
፵፪/ “አነስተኛ መድን” ማለት መሰረታዊ የመድን 42/ “micro insurance” means any form of
መርሆዎችን የሚከተል፣ በአረቦን ክፍያ ላይ protection against risks that is designed
የተመሰረተ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች for and accessed by low-income people,
ሊጠቀሙበት የሚያስችል፣ እነዚህን የኅብረተሰብ provided by different categories of
ክፍሎች ከማንኛውም ስጋት ለመከላከል carriers but operating on basic principles
እንዲያስችል የተቀረጸ እና በተለያዩ አነስተኛ of insurance and funded by premiums;”
መድን ሰጪዎች የሚቀርብ የመድን ሽፋን ነው፤
gA ፲፪ሺ፸፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፮ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.6, 9th Junuary,2020….page 12073

፵፫/ “አነስተኛ መድን ወኪል” ማለት በኢትዮጵያ 43/ “micro insurance agent” means a person
ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው እና አንድ licensed by the National Bank as a micro
ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ አነስተኛ መድን insurance agent who, acts for and on
ሰጪዎች ስም የሚሰራ እና አነስተኛ መድን behalf of one or more micro insurance
ገቢዎችን እና አነስተኛ መድን ሰጪዎችን providers, and engages in intermediary
services;”
የማገናኘት ስራ የሚሰራ ሰው ነው፤
፵፬/ “አነስተኛ መድን ሰጪዎች” ማለት 44/ “micro insurance providers” means
የአነስተኛ መድን ሥራን ለመስራት ብቻ insurers, including those dedicated to
የተቋቋሙትን ጨምሮ መድን ሰጪ deal in micro insurance business and
ኩባንያዎች እና አነስተኛ የፋይናንስ microfinance institutions;”
ተቋማት ናቸው፤
፵፭/ “የኢንሹራንስ መግቢያ ዋጋ (ፕሪሚየም)” 45/ “premium” means the amount of money
ማለት በመድን ፖሊሲ ውስጥ የተገለጸውን an insurer charges to provide the
ሽፋን ለመስጠት መድን ሰጪ coverage described in an insurance
የሚያስከፍለው ገንዘብ ነው፤ policy;”
፵፮/ "ዕዳን መክፈል የሚያስችል ወሰን" ማለት 46/ ‘‘margin of solvency” means the excess
በእያንዳንዱ አብይ የመድን ሥራ ዓይነት of admitted assets over admitted
ተቀባይነት ያለው ሀብት ተቀባይነት ካለው liabilities to be maintained for each main
ዕዳ ሊበልጥበት የሚገባው ወሰን ነው፤ class of insurance business;”
፫/ ከአዋጁ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ (፱) ቀጥሎ 3/ The following new Sub Article (10) is added
የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፲) after Sub Article (9) of Article 5 of the
ተጨምሯል፡፡ Proclamation;
፲/ ብሔራዊ ባንክ ለአነስተኛ መድን ሰጪና 10/ “The National Bank may issue a
ለአነስተኛ መድን ወኪል ስለሚሰጥበትና directive prescribing the manner of
ቁጥጥር ስለሚካሄድበት ሁኔታ መመሪያ licensing and supervising micro
ሊያወጣ ይችላል፡፡ insurance provider and micro insurance
agent.”
፬/ የአዋጁ አንቀጽ ፲ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ 4 / Article 10 of the Proclamation is deleted
አንቀጽ ፲ ተተክቷል፡፡ and replaced by the following new article 10:
፲/ የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ 10/ Manner of participation of a Foreign
ኢትዮጵያዊ በመድን ሥራ ስለሚሳተፍበት National of Ethiopian Origin in an
ሁኔታ:- Insurance Business
በአንቀጽ ፲፮ ንዑስ አንቀጽ (፭) ላይ የተጣለው
Without Prejudice to the prohibition laid
ክልከላ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፣
down under Sub Article (5) of Atricle 16 of
the proclamation,
፩/ የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ 1) “A foreign national of Ethiopian origin or
ኢትዮጵያዊ ወይም ሙሉ በሙሉ የውጭ ሀገር an organization owned fully by foreign
ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን nationals of Ethiopian origin or jointly by
ባለቤትነት ወይም የውጭ ሀገር ዜግነት foreign nationals of Ethiopian origin and
ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵ Ethiopian nationals are allowed to acquire
ያውያን የጋራ ባለቤትነት የተቋቋመ ድርጅት the shares of Ethiopian insurer or to open
በኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋመ መድን ሰጪ an insurance company;
ኩባንያ የአክሰዮን ባለቤት ወይም መድን ሰጪ
ኩባንያ ማቋቋም ይችላል፡፡
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) በተደነገገው 2) If a foreign national of Ethiopian origin
አግባብ የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ holds a share directly in an insurance
company or indirectly by holding a share
gA ፲፪ሺ፸፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፮ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.6, 9th Junuary,2020….page 12074

ኢትዮጵያዊ በቀጥታ በመድን ሰጪ ኩባንያ in another organization that holds a share


የአክስዮን ባለቤት ሲሆን ወይም በተዘዋዋሪ in an insurance company, in accordance
መንገድ የአክስዮን ባለቤት የሆነበት ሌላ with the provisions of Sub-Article (1) of
ድርጅት የመድን ሰጪ ኩባንያ ባለአክስዮን this Article, a foreign national of
ሲሆን የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ Ethiopian origin or the organization to
which he is a shareholder, shall pay the
ኢትዮጵያዊ በድርጅቱ የሚኖረው የአክስዮን
values of the shares in an insurance
ድርሻ ዋጋ በሙሉ ተቀባይነት ባለው
company only in an acceptable foreign
የውጭ ምንዛሪ ብቻ የሚከፈል ይሆናል፡፡
currency;
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተደነገገው 3) Notwithstanding the provisions of Sub-
ግዴታ ቢኖርም:- Article (2) of this Article, all types of
payments due to a foreign national of
Ethiopian origin resulting from;
ሀ) ከአክስዮን ባለቤትነት የሚገኝ የትርፍ a) dividends earned from a share in an
ድርሻ፤ insurance company;
ለ) የአክስዮን ድርሻውን ለሌላ ሰው b) transfer of shares in an insurance
ሲያዛውር፤ company;
ሐ) ባለአክስዮን የሆነበት መድን ሰጪ c) sales or liquidation of an insurance
ኩባንያ ሲሸጥ ወይም ፈርሶ ሲጣራ፤ company; or
ወይም
d) any other matters related to
መ) ሌሎች ከአክስዮን ባለቤትነት ጋር
shareholding in an insurance
በተያያዘ፤ company;
የውጭ ሀገር ዜግነት ላለው ትውልደ shall be paid to him in a local currency, i.e.
ኢትዮጵያዊ የሚከፈሉ ማናቸውም ዓይነት Birr; meanwhile, he may not be allowed to
ክፍያዎች በሙሉ በብር የሚከፈለው ይሆናል፤ repatriate any asset or interest obtained in
እንዲሁም በዚህ አግባብ የሚያገኘውን ሀብት this manner.
ወይም ጥቅም ወደ ውጭ ማዛወር
አይፈቀድለትም፡፡
፬/ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች
4) The National Bank may issue directive
related to additional conditions for
በመድን ሰጪ ኩባንያ ውስጥ መዋዕለ
investment in an insurance company by
ንዋያቸውን በሥራ ላይ ስለሚያውሉበት
foreign nationals of Ethiopian origin.”
ተጨማሪ ሁኔታዎች ብሔራዊ ባንክ መመሪያ
ሊያወጣ ይችላል፡፡"
፭/ የአዋጁ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ (፭) 5/ Sub Article (5) of Article 12 of the
ተሰርዟል፡፡ Proclamation is repealed.
፮/ የአዋጁ አንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ (፬) ፊደል 6/ Paragraph (c) of Sub Article (4) of Article
ተራ (ሐ) ተሰርዞ በሚከተለው ፊደል ተራ 15 of the Proclamation is deleted and
(ሐ) ተተክቷል፡፡ replaced by new paragraph (c);
ሐ) “የመድን ሰጪ ዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊ c) “the duties and responsibilities of
ነትና ግዴታዎችን እና የመድን ሰጪ board of directors and manner of
ኩባንያን መልካም የኩባንያ ሥራ corporate governance of an
አመራርን፤” insurance company;”
፯/ የአዋጁ አንቀጽ ፲፮ ንዑስ አንቀጽ (፫) ተሰርዞ 7/ Sub Article (3) of Article 16 of the
በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፫) የተተካ Proclamation is deleted and replaced by
ሲሆን ከንዑስ አንቀጽ (፬) ቀጥሎ the following new Sub Article (3) and
የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፭) new Sub Article (5) is added after sub
ተጨምሯል:- Article (4):
gA ፲፪ሺ፸፭ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፮ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.6, 9th Junuary,2020….page 12075

፫) “ማናቸውም መድን ሰጪ ዳይሬክተር 3) “A director of an insurer may not, at the


በተመሳሳይ ጊዜ የሌላ ፋይናንስ ተቋም same time, serve as a director of another
ዳይሬክተር ሆኖ ሊያገለግል አይችልም፡፡ financial institution. Moreover, a business
entity or a company in which such
በተጨማሪም ዳይሬክተሩ አሥር በመቶና
director has ten percent and more equity
ከዚያ በላይ የባለቤትነት ድርሻ የያዘበት
interest may not serve as a director of an
የንግድ ድርጅት የመድን ሰጪ ዳይሬክተር
insurer.”
ሆኖ ሊያገለግል አይችልም፡፡

፭) ”የውጭ ሀገር ዜጎች ወይም በከፊልም ሆነ 5) “Foreign nationals or organizations


በሙሉ በውጭ ሀገር ዜጎች ባለቤትነት fully or partially owned by foreign
የተያዙ ድርጅቶች ወይም የውጭ መድን nationals may not be allowed to
ሰጪ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ open an insurance company or carry
የመድን ሥራ ማካሄድ ወይም የመድን on insurance business or operate
branch offices or subsidiaries of
ሥራ የሚያካሂዱ ቅርንጫፎች ማቋቋም
foreign insurers in Ethiopia or
እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋሙ acquire the shares of Ethiopian
መድን ሰጪዎች የአክስዮን ባለቤት መሆን insurers.”
አይችሉም፡፡”
፰/ የአዋጁ አንቀጽ ፳፮ ንዑስ አንቀጽ (፩) 8/ Sub Article (1) of Article 26 of the
ተሰርዟል፡፡ Proclamation is repealed.
9/ Sub Article of (1) Article 30 of the
፱/ የአዋጁ አንቀጽ ፴ ንዑስ አንቀጽ (፩) Proclamation is repealed.
ተሰርዟል፡፡
10 Sub Article (1) of Article 46 of the
፲/ የአዋጁ አንቀጽ ፵፮ ንዑስ አንቀጽ (፩)
Proclamation is deleted and replaced by
ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፩) the following new Sub-Article (1):
ተተክቷል፡፡
1/ “Unless otherwise provided by
፩/ "በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጡ ደንቦች
regulations or directives issued
ወይም መመሪያዎች በሌላ አኳኋን
pursuant to this Proclamation, no
ካልተደነገገ በስተቀር መድን ሰጪው
insurer may grant any loan or
ለማንኛውም ዳይሬክተር፣ ባለአክስዮን፣ ዋና
financial guarantee, except
ሥራ አስፈፃሚ፣ ኦዲተር፣ አስሊ ወይም employment benefits allowed to all
ለማንኛውም የመድን ረዳት ወይም ከነዚህ employees of an insurer or loans on
ሰዎች ጋር ግንኙነት ላለው ማንኛውም ሰው life policies issued by him within
ለመድን ሰጪው ኩባንያ ሰራተኞች ሁሉ their surrender value, to any director,
ከተፈቀደ የሰራተኞች ጥቅማጥቅም በስተቀር shareholder, chief executive officer,
ማናቸውንም ዓይነት ብድር ወይም የገንዘብ auditor, actuary or to any insurance
ዋስትና ሊሰጥ አይችልም፡፡ ሆኖም ይህ auxiliary or to any other person
ገደብ መድን ሰጪው የገባውን የሕይወት connected with such persons.”
መድን ውል ዋጋ መጠን ሳያልፍ
ለሕይወት መድን ገቢዎች የሚሰጠውን ብድር
አይጨምርም፡፡"
፲፩/ ከአዋጁ አንቀጽ ፶፬ ቀጥሎ አዲስ አንቀጽ 11/ The following new Articles (55, 56, 57,
፶፭፣ ፶፮፣ ፶፯፣ ፶፰፣ ፶፱፣ ፷ ተጨምረው 58, 59, 60) are added after Article 54 of
ከአንቀጽ ፶፭ እስከ ፷ ያሉት እንደቅደም the Proclamation and the subsequent
ተከተላቸው ከአንቀጽ ፷፩ እስከ ፷፮ ሆነው Articles 55 to 60 are renumbered as
ተሸጋሽገዋል፡፡ Articles 61 to 66, respectively .

፶፭. የጠለፋ መድን ሰጪን ስለመቆጣጠር 55. Supervision of A Reinsurer


፩/ ብሔራዊ ባንክ የጠለፋ መድን ሰጪን 1/ The National Bank shall supervise a
ይቆጣጠራል፡፡ reinsurer.
gA ፲፪ሺ፸፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፮ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.6, 9th Junuary,2020….page 12076

፪/ ብሔራዊ ባንክ የጠለፋ መድን ሰጪን 2/ The National Bank shall issue
directive necessary to supervise a
ለመቆጣጠር አስፈላጊ የሆነ መመሪያ
reinsurer.
ያወጣል፡፡
፫/ ከአንቀጽ ፮(፪-፭)፣ ፳፯(፫)፣ ፴፬ (፪)፣ ፴፱- 3/ All Articles of this Proclamation
are applicable to a reinsurer licensed
፵፭፣ ፵፰-፶፣ ፶፰ እና ፶፱ (እንደተሸጋሸገው)
under the Proclamation except
በስተቀር ሁሉም የአዋጁ ድንጋጌዎች Articles 6 (2-5), 27 (3), 34 (2), 39-
በጠለፋ መድን ሰጪ ላይ ተፈጻሚ 45, 48-50, 58 and 59 (as amended).
ይሆናሉ፡፡
፶፮. በዲጅታል ዘዴዎች የመድን አገልግሎት 56. Digital Insurance Services
ስለመስጠት Minimum conditions to provide
በዲጅታል ዘዴዎች የመድን አገልግሎት digital insurance services shall be
ስለሚሰጥበት ሁኔታ ብሔራዊ ባንክ determined by a National Bank
በመመሪያ ይወስናል፡፡ directive.
፶፯/ የማስታወቂያ ይዘትን ስለመቆጣጠር 57. Regulation of Advertisement
ማናቸውም መድን ሰጪ በማናቸውም ጊዜ The National Bank may at any time
በብሔራዊ ባንክ እምነት ሐሰተኛ፣ አሳሳች፣ direct an insurer to withdraw, amend or
አደናገሪ ወይም የሌላውን ጥቅም የሚጎዳ refrain from issuing a paid radio or
የተከፈለበትን የሬዲዮ ወይም የቴሌቪዥን television announcement, a poster ,
ማስታወቂያ፣ ፖስተር፣ ቢልቦርድ፣ በራሪ billboard, brochure, circular, or other
ወረቀት፣ ሰርኩላር ወይም ሌላ ሰነድ እና document, and a paid advertisement in
የተከፈለበትን የጋዜጣ እና የመጽሄት a regularly published newspaper or
ማስታወቂያ አውጥቶ ቢገኝ መድን ሰጪው magazine that it considers to be false,
ማስታወቂያውን እንዲያቋርጥ፣ እንዲያሻሽል misleading, deceptive, or offensive.
ወይም ከማስተዋወቅ እንዲቆጠብ ብሔራዊ
ባንክ ሊያዘው ይችላል፡፡
፶፰/ የኢንሹራንስ መግቢያ ዋጋ (ፕሪሚየም) ስለመወሰን 58. Determining Insurance Premium
ብሔራዊ ባንከ ዝቅተኛ የኢንሹራንስ መግቢያ
The National Bank may determine an
ዋጋ ለመወሰን ይችላል፡፡ ዝቅተኛ የኢንሹራንስ economic (minimum) premium rate in a
መግቢያ ዋጋ ስለሚወሰንበት ሁኔታ በመመሪያ manner to be specified by a directive.
ሊያወጣ ይችላል፡፡
፶፱/ የመድን አገልግሎት ተጠቃሚዎች መብት ጥበቃ 59. Insurance Services Consumer Protection
የመድን አገልግሎት ተጠቃሚዎችን መብት እና The National Bank may issue directive for
ጥቅም ለማስከበር የሚያስችል መመሪያ ብሔራዊ protecting the right and interest of
ባንክ ሊያወጣ ይችላል፡፡ insurance service consumers.

፷/ ለታካፉል መድን ሰጪ ኩባንያ ፈቃድ ስለመስጠት 60. Licensing and Supervision of A Takaful
እና ሰለመቆጣጠር Insurance Company
፩/ በአዋጁ የመድን ሥራን ለመሥራት እና 1/ Without prejudice to the requirements
ለመቆጣጠር የተደነገጉ ድንጋጌዎች እና specified under the provisions of the
መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ብሔራዊ Proclamation and directive the National
ባንክ የታካፉል መድን ሥራ ለሚሰራ መድን Bank shall issue directive to prescribe
additional conditions for the licensing and
ሰጪ ፈቃድ ስለሚሰጥበት እና ቁጥጥር
supervision of a takaful insurance
ስለሚያካሄድበት ሁኔታ ተጨማሪ ግዴታዎችን
company.
ለመደንገግ መመሪያዎችን ያወጣል፡፡
gA ፲፪ሺ፸፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፮ ታህሣሥ ፴ qN ፪ሺ፲፪ ›.M Federal Negarit Gazette No.6, 9th Junuary,2020….page 12077

፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው 2/ without prejudice to Sub-Article (1) of this
እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛው Article, the National Bank may issue
የመድን ሥራ ጋር የታካፉል አገልግሎት directive to regulate takaful insurance
የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመቆጣጠር መመሪያ carried on alongside a conventional
ሊያወጣ ይችላል፡፡ insurance business.
፫. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ 3. Effective Date
ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ This Proclamation shall come into force on the date
ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡ of publication in the Federal Negarit Gazette.

አዲስ አበባ ታህሣሥ ፴ ቀን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም Done at Addis Ababa, this 9th day of Junuary 2020

ሳህለወርቅ ዘውዴ SAHLEWORK ZEWDIE

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ PRESIDENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC


ፕሬዚዳንት REPUBLIC OF ETHIOPIA

ማረሚያ ቁጥር ፲፬/፪ሺ፲፪ Corrigendum No.14/2020

የኢትዮጵያ ምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና Article 65 (1) (a) of the Ethiopian Electoral,
የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፷፪/፪ሺ፲፩ Political Parties Registration and Election’s Code of
አንቀጽ ፷፭ (፩) (ሀ) “ ፬ መቶ ሺ መስራች አባላት Conduct Proclamation No. 1162/2019 Amharic
version which read as “it has 400,000 founding
ሲኖሩት፤” የተባለው “፬ ሺ መስራች አባላት ሲኖሩት፤”
members;” is hereby corrected and shall be read as
ተብሎ ይነበብ።
“it has 4000 founding members;”

You might also like