You are on page 1of 24

Abrham Yohanes https://t.

me/ethiopianlegalbrief

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሀያ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፪ 26th Year No. 32


አዲስ አበባ መጋቢት ፳፱ ቀን ፪ሺ፲፩ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ th
ADDIS ABABA April 7 , 2020
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ Content
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፹፫/፪ሺ፲፪ ዓ.ም Proclamation No. 1183 /2020
የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር Federal Administrative Procedure Proclamation
…….………….………………….…………...ገጽ ፲፪ሺ፬፻፸ Page…………………………………………12470

PROCLAMATION NO. 1183/2020


አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፹፫/፪ሺ፲፪

የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓትን A PROCLAMATION TO PROVIDE FOR FEDERAL

ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ADMINISTRATIVE PROCEDURE

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ WHEREAS, the Federal Democratic Republic of

መንግስት መንግስታዊ አሰራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ Ethiopia Constitution provides that the working procedure

መከናወን እንዳለበትና ማናቸውም የመንግስት ባለሥልጣን of the Government is to be transparent, and that any Public

ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን የተመለከተ Official is held accountable for failure in his duties;

በመሆኑ፤

የአስተዳደር ተቋማት በሰዎች መብቶችና ጥቅሞች ላይ WHEREAS, it is necessary to regulate Administrative


የሚያስከትሉትን ጣልቃ ገብነት በሕግ የሚመራና ለሕግ Agencies to refrain there intervention against people
የሚገዛ መሆኑን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤ Rights and Interests;

ÃNÇ êU nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1


Unit Price Negarit G. P.O.Box 80001
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፸፩ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12471
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page

የአስተዳደር ተቋማት የውሳኔ አሰጣጥና የመመሪያ WHEREAS it is necessary to guarantee administrative


አወጣጥ መርሆዎችና ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም በአስተዳደራዊ justice by promoting culture of transparency and

ውሳኔዎችና መመሪያዎች ቅር የተሰኘ ሰዉ የውሳኔዎቹንና accountability through legally establishing a system of

የመመሪያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት judicial review for persons who might be aggrieved by

ሥርዓት በመደንገግ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን አስፈላጊ acts of administrative agencies,in their rule-making and

በመሆኑ፤ decision-making capacities,

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- NOW THEREFORE, in accordance with Article 55
መንግስት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ (1) of the Constitution of the Federal Democratic Republic
of Ethiopia, it is hereby proclaimed as follows .

ክፍል አንድ SECTION ONE


GENERAL PROVISIONS
ጠቅላላ ድንጋጌዎች

 ፩ አጭር ርዕስ 1. Short Title


ይህ አዋጅ "የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ This Proclamation may be cited as “Federal
ቁጥር ፩ሺ፩፻፹፫/፪ሺ፲፪" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ Administrative Procedure Proclamation No.

፪. ትርጓሜ 1183/2020.”
2. Definition
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር
In this Proclamation, unless the context requires
በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-
otherwise:
፩/ “የአስተዳደር ተቋም” ማለት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ 1/ “Administrative Agency” means an Executive
ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አስፈጻሚ አካል Organ of the Federal Democratic Republic of
ሆኖ በሕግ የተደራጀ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሲሆን Ethiopia duly established by law and includes the
ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ የከተማ አስተዳደር Executive Organs of City Administrations
አስፈፃሚ አካላትን ይጨምራል፤ accountable to the Federal Government;

፪/ “መመሪያ” ማለት ሕግ አውጪው አካል በሚሰጠው 2/ “Directive” means a legislative document that is
የውክልና ስልጣን መሰረት በአስተዳደር ተቋም issued by an administrative agency based on
የሚወጣና በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ውጤት delegation of Power bestowed up on it by the
የሚያስከትል የሕግ ሰነድ ሲሆን በስራ ላይ ያለ Legislator which affects people’s Rights and
መመሪያን የሚያሻሻል ወይም የሚሽር የሕግ ሰነድንም Interests. The term also includes the amendment,
ይጨምራል፤ or repeal of an already existing directive;
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፸፪ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12472
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፫/ “የአስተዳደር ውሳኔ” ማለት መመሪያ ማውጣትን ሳይጨምር 3/ “Administrative Decision” means decision issued by
የአስተዳደር ተቋም በዕለት ተዕለት ተግባሩ በሰዎች መብት an administrative agency on relating to persons rights
ወይም ጥቅም ላይ የሚሰጠው የአስተዳደር ውሳኔ ነው፤ or interest in its day-to-day function, excluding
issuance of Directives;
፬/ "ሰው" ማለት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ 4/ “Person” means any Natural or Juridical Person;
የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤
5/ Any expression in the masculine gender includes the
፭/ በዚህ አዋጅ በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትን ጾታ
feminine.
ይጨምራል፡፡

 ፫.የተፈጻሚነት ወሰን
3. Scope of Application
፩/ ይህ አዋጅ በሁሉም የአስተዳደር ተቋማት ላይ ተፈፃሚ
1/ This Proclamation is applicable in all Administrative
ሲሆን በወንጀል ሥነ ሥርዓት ህጉ በሚመሩ የዐቃቤ ህግ
Agencies except Prosecutor and Police when they
እና የፖሊስ ተግባራት እንዲሁም በመከላከያና፣ የደህንነት
perform duties administered by the Criminal Procedure
ተቋማት ላይ ተፈጻሚ አይሆንም።
Law and Military and Security Institutions.

፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ድንጋጌ ቢኖርም ፣ እነዚህ 2/ Notwithstanding what is provided under Sub-article (1)
ተቋማት፣ ከዋና ኃላፊነታቸው በተጓዳኝ ፣ አገልግሎት of this Article, issuance of directives and decisions
የመስጠትና የቁጥጥር ሰራዎችን በተመለከተ፣ መመሪያ making relating to regulatory and service provision
ሲያወጡ እና አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ሲወስኑ በዚህ functions of these Institutions shall be subject to the
አዋጅ መሰረት ይገዛሉ ። requirements of this Proclamation.

፫/ የዚህ አዋጅ አንቀፅ ፲፩ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ብሄራዊ 3/ Without prejudice to Article 11 of this Proclamation,
ባንክ የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሬ ተመንና የወለድ ተመንን National Bank is not duty bound to implement

እና ሌሎች ተመሳሳይ ሚስጥራዊ ጉዳየችን በተመለከተ obligations provided under Article 7-10 of this

መመሪያ ሲያወጣ በዚህ አዋጅ አንቀፅ ከ፯-፲ Proclamation when it enacts directives concerning

የተመለከቱትን ግዴታዎች ለመተግበር አይገደድም፡፡ exchange rate, interest rate of the country and other
similar secret issues.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፸፫ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12473
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
ክፍል ሁለት SECTION TWO
ADMINISTRATIVE DIRECTIVES
የአስተዳደር መመሪያዎች
SUB SECTION ONE
ንዑስ ክፍል አንድ
ISSUANCE OF DIRECTIVE
የመመሪያ መውጣት

 ፬. መመሪያ ስለማውጣት 4. Issuance of Directives


፩/ ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም በሕግ በተሰጠው 1/ Any administrative agency can adopt directive on the
የውክልና ሥልጣን መሠረት መመሪያ ማውጣት basis of Power Delegated to it by Law.
ይችላል፡፡
፪/ የአስተዳደር ተቋም መመሪያ የሚያወጣው በዚህ አዋጅ 2/ An adminstrative agency may issue directives only
በተደነገገው ሥነ-ሥርዓት መሠረት ብቻ ነው፡፡ through the procedures provided by this
Proclamation.
፫/ ማንኛውም ሰዉ መብቱን ወይም ጥቅሙን በሚመለከት 3/ Regarding matters affecting his right or interest, any
የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ያላወጣ ቢሆንም person has the right to request an administrative
የአስተዳደር ውሳኔ እንዲሰጠው የመጠየቅ መብት aecision even though an administrative agency has
አለው፡፡ not adopted a directive,

፬/ ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣ የሚገባውን 4/ Failure on the part of an adminstarative agency to
መመሪያ አለማውጣቱ በሕግ በተሰጠው ኃላፊነት ሊሰጥ issue Directives legally empowered to adopt shall
የሚገባዉን አገልግሎት ወይም አስተዳደራዊ ዉሳኔ not be a reason to deny services or rendering an
ላለመስጠት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ Administrative Decision.

 ፭. መመሪያ ስለሚወጣበት ጊዜ 5. Timely Adoption of Directives

ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣ የሚገባውን Any administrative agency shall issues a directive

መመሪያ አስመልክቶ በእናት ህጉ መመሪያ እንዲወጣ which is on the basis of mother law , If a directive is

በአስገዳጅ ሁኔታ በተደነገገ ጊዜ በሦስት ወራት ውስጥ mandatory it shall be ratify within three month, If it is

አስገዳጅ ባልሆነ ሁኔታ በተደገገ ጊዜ ደግሞ በተገቢው ጊዜ


not mandatory it shall ratify with in a reasonable
period of time.
ውስጥ መመሪያውን ማውጣት አለበት፡፡
.

 ፮. መመሪያ እንዲወጣ ጥያቄ ስለማቅረብ 6. Petition for Adoption of Directives

፩/ ማንኛውም ሰው አንድ የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣው 1/ Any person may ask the agency through written

የሚገባዉን መመሪያ በተገቢው ጊዜ ሳያወጣ ቢቀር application to adopt a direcives, when an

መመሪያውን እንዲያወጣ በጽሁፍ ሊጠይቀው ይችላል፤ admistrative agency failed to adopt a directive it
was mandated with in a reasonable period of time. .

፪/ ጥያቄው የቀረበለት የአስተዳደር ተቋም በሠላሳ የሥራ 2/ An agency which receives a petition for adoption of a
ቀናት ውስጥ መመሪያውን የማውጣት ሂደት መጀመር Directive shall commence the process of adopting a
ወይም ምክንያቱን በመግለጽ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ rule within 30 Days or deny the petition, stating its
አለበት፡፡ reasons.
፲፪ሺ፬፻፸፬
Abrham Yohanes https://t.me/ethiopianlegalbrief 12474
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
ንዑስ ክፍል ሁለት SECTION TWO
PROCEDURES BEFORE ADOPTION OF A
የቅድመ መመሪያ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት
DIRECTIVE
 ፮.የመመሪያ አወጣጥን የሚመለከት መዝገብ ስለማደራጀት 7. Keeping an Agency Record about Directives

፩/ ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም የሚያወጣውን መመሪያ 1/ At the time of adopting a directive, an administrative
በተመለከተ የሚከተሉትን የያዘ መዝገብ ማደራጀት agency shall keep a record/file containing the
አለበት፦ following:
ሀ) በተቋሙ በመታየት ላይ ያለ ረቂቅ መመሪያ ርዕሰ a) The subject matter of the directive being
ጉዳይ እና የመመሪያውን አወጣጥ መርሃ ግብር፤ considered and time line of major steps;
ለ) የረቂቅ መመሪያው ዝግጅት በምን ደረጃ ላይ
b) An information regarding the status of the draft
እንደሚገኝ የሚያመለክት መረጃ፤ directive in the process of adoption;
ሐ) ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ የታተሙ c) Notices published in relation to the adoption of
ማስታወቂያዎች፤ the draft directive ;

መ) በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ስለሚቀርብበት d) A period of time with in which the public may
ጊዜ፤ comment on the draft ;

ሠ) ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ በዚህ አዋጅ አንቀጽ e) Comments received in accordance with Articles 8
፷ እና ፱ መሠረት የተሰበሰቡ አስተያየቶችንና and 9 of this Proclamation and positions taken
በአስተዳደር ተቋሙ በአስተያየቶቹ ላይ የተወሰዱ regarding the comments.
አቋሞችን፡፡
፪/ ማንኛውም ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሰረት 2/ Any person may inspect or get a copy of the records
የሚደራጀውን መዝገብ መመልከት ወይም አስፈላጊውን organized in accordance with Sub Article (1) of this
ወጪ ሸፍኖ ቅጂውን መውሰድ ይችላል፡፡ Article, against payment of expenses.

 ፰ ∙ማስታወቂያ ስለማዉጣት 8. Noticing


የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ከማውጣቱ በፊት An agency shall publish a notice containing the
ስለሚያወጣው ረቂቅ መመሪያ ሰፊ ስርጭት ባለው ጋዜጣ following information on a newspaper with wide
እና የተቋሙን ድረ ገጽ ጨምሮ በሌሎች የመገናኛ ብዙሃን circulation, its website and other media, prior to the
የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ ማስታወቂያ ማውጣት adoption of a directive:
አለበት፦
፩/ የመመሪያውን ረቂቅ ለማዘጋጀት መሰረት የሆነውን
1/ The legal basis for to draft the law and the subject
ሕጋዊ ሥልጣን እና በመመሪያው ስለሚካተቱት ርዕሰ
matters to be covered by the draft;
ጉዳዮች፤

፪/ የረቂቅ መመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚቻል 2/ Indicating that persons may get a copy of the draft
ስለመሆኑና የሚገኝበትን ሁኔታ፤ and where they may access it;
፲፪ሺ፬፻፸፭
Abrham Yohanes https://t.me/ethiopianlegalbrief 12475
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፫/ በረቂቅ መመሪያው ላይ ሰዎች አስተያየታቸውን መቼ 3/ Where, when and how persons may give comments
እና እንዴት ሊያቀርቡ እንደሚችሉ፤ on the draft;
፬/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ በተመለከተው መዝገብ ላይ
4/ Where, when and how persons may get access to the
የሰፈሩ መረጃዎችን የትና መቼ ማግኘት እንደሚቻል
records kept in accordance with Article 7 of this
የሚገልፅ መረጃ፡፡
Proclamation.
 ፱. ረቂቅ መመሪያን ለአስተያየት ስለመላክ 9. Soliciting Comments on the Draft

፩/ የአስተዳደር ተቋም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ በተደነገገው 1/ An administrative agency shall solicit comments from
መሰረት ለሕዝብ ያሳወቀውን ረቂቅ መመሪያ relevant administrative agencies and other
ለሚመለከታቸው የአስተዳደር ተቋማትና ለሌሎች Stakeholders by sending the draft it publicized in
ባለድርሻ አካላት ለአስተያየት መላክ አለበት፡፡ accordance with Article 8 of this Proclamation.

፪/ የሚመለከታቸው የአስተዳደር ተቋማትና ሌሎች 2/ Agencies and stakeholders who may have comments
ባለድርሻ አካላት በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት on the draft should submit such comments in writing
ካላቸው አስተያየታቸውን ተቋሙ በሚወስነው የጊዜ within a time prescribed by the agency. The period for
ገደብ ውስጥ በጽሁፍ መላክ አለባቸው፡፡ ተቋሙ comments to be prescribed by the agency shall not be
የሚወስነው የጊዜ ገደብ በማናቸውም ሁኔታ ከ፲፭ less than 15 working days.
የሥራ ቀናት ማነስ የለበትም።

 ፲. የውይይት መድረክ ስለማዘጋጀት


10. Oral Hearing
፩/ የአስተዳደር ተቋሙ በመመሪያው ረቂቅ ላይ የጽሑፍ
1/ After the expiry of the date for receiving written
አስተያየት መቀበያ ጊዜ ካበቃ በኋላ መመሪያው comments, the agency shall organize a public forum
ከመፅደቁ በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት open for all interested persons and gather inputs.
የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ
አለበት፡፡
፪/ ማንኛውም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ መሠረት 2/ Persons who have not had the chance to given
ያልተስተናገደ በመድረኩ የሚሳተፍ ሰው አስተያየቱን comments in accordance with Article 9, may submit
በጽሑፍ ጭምር ሊያቀርብ ይችላል፡፡ written comments at the hearing.

፫/ የአስተዳደር ተቋሙ በሚያዘጋጀው የውይይት መድረክ


3/ The agency shall ensure enough time is allotted for
ላይ አስተያየቶችን ማስተናገድ የሚያስችል በቂ ጊዜ
different views to be aired.
መመደብ አለበት፡፡
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፸፮ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12476
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፲፩. ከሥነ-ሥርዓት ነጻ ስለመሆን 11. Exemption from Procedures
1/ An Agency may be exempted from the requirement
፩/ ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ሲያወጣ በዚህ
provided under Articles 7 to 10 of this Proclamation
አዋጅ ከአንቀጽ ፯ እስከ ፲ ባሉት ድንጋጌዎች
where conditions listed hereunder are fulfilled :
ከተመለከቱት ግዴታዎች በሚከተሉት ሁኔታዎች ነጻ
ሊሆን ይችላል፦
a) Where there are emergencies and time does not
ሀ) የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ በመኖሩ በግዴታዎቹ ሥርዓት allow to go through the requirements;
ውስጥ ለማለፍ ጊዜ የማይፈቅድ ሲሆን፤

ለ) ቅድመ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሕዝብን ጥቅም b) Where the issuance of advance notice may be

የሚጎዳ ሆኖ ሲገኝ፤ ወይም contrary to Public Interest;

ሐ) ቅድመ ማስታወቂያ ማውጣቱ የመመሪያውን c) Where the issuance of notice may undermine the
ተፈጻሚነት ፋይዳ ቢስ የሚያደርግ ሲሆን፡፡ implementation of the directive;

፪/ የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ሲያወጣ በዚህ አንቀጽ 2/ An agency issuing directives relying on Sub Article
ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ከግዴታ ነጻ እንዲሆን (1)of this Article shall prepare a record explaining the
ያደረገውን ምክንያት የያዘ ዝርዝር መግለጫ ማዘጋጀት reasons justifying the exemption.
አለበት፡፡

ንዑስ ክፍል ሦስት SUB-SECTION THREE


RATIFICATION AND EFFECTIVENESS OF
መመሪያ ስለማጽደቅና ስለተፈፃሚነቱ
DIRECTIVES
፲፪. መመሪያ ስለሚጸድቅበት ጊዜና ሁኔታ
12. Time and Manner of Ratifying Directive
፩/ የአስተዳደር ተቋሙ በተዘጋጀው መመሪያ ረቂቅ ላይ
1/ An Agency may not ratify a Directive before the
በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ እና ፲ መሠረት የተወሰነው
period for oral hearings and written submissions
የጽሑፍ አስተያየት ማቅረቢያና የውይይት መድረክ
prescribed under Articles 9 and 10 expires.
ማካሄጃ ጊዜ እስኪያልፍ ድረስ መመሪያውን ማጽደቅ
አይችልም፡፡

፪/ የአስተዳደር ተቋሙ መመሪያውን ከማጽደቁ በፊት 2/ An agency shall consider comments submitted on
በረቂቁ ላይ የቀረበ አስተያየት ከግምት ወስጥ the draft before ratifying a Directive.
ማስገባት አለበት።

፫/ የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪)


3/ In fulfilling the obligation to consider indicated
የተመለከተውን ግዴታ ለመወጣት በአስተያየቱ under Sub Article (2) of this Article, the agency
መሠረት ማስተካከያ ማድረግ አለበት ወይም may amend the draft in line with the comments or
አስተያየቱን የማይቀበል ከሆነ፣ የማይቀበልበትን prepare a written justification for rejecting the
ምክንያት የሚያብራራ ጽሑፍ ማዘጋጀት አለበት። comments.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፸፯ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12477
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፬/ የአስተዳደር ተቋሙ ረቂቅ መመሪያውን ከማጽደቁ 4/ Prior to ratificaion of a Directive, the Agency shall
በፊት ለአስተያየት ለፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ send the draft to the Federal Attorney General for
መላክ አለበት፤ its opinion.

፭/ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በረቂቅ መመሪያው ላይ ያለውን 5/ The Attorney General shall submit its opinion
አስተያየት በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ ለአስተዳደር within 15 working days. Where the Attorney
ተቋሙ መላክ አለበት፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ General fails to submit its opinion within the time
የጊዜ ገደብ ውስጥ አስተያየቱን ካልላከ አስተያየት prescribed here, it shall be considered as though it
እንደሌለው ተቆጥሮ መመሪያውን የማጽደቁ ሂደት does not have opinion on the draft and the agency
ይቀጥላል፡፡ may proceed to ratification.

፲፫. በመመሪያው ረቂቅና በሚወጣው መመሪያ መካከል ልዩነት 13. Variance Between the Draft and Adopted Directive
ስለመኖር
፩/ የአስተዳደር ተቋሙ በማስታወቂያ ከተመለከተው ረቂቅ 1/ An Agency may not ratify a directive that is
መመሪያ ጋር መሠረታዊ ልዩነት ያለው መመሪያ substantially different form the draft publicized
ማዉጣት አይችልም፤ ሆኖም መሠረታዊ ልዩነት ያለው through notice. However the Agency may not be
መመሪያ ለማውጣት ከፈለገ የተጀመረውን የመመሪያ barred from terminating the process at hand and
አወጣጥ ሂደት በማቋረጥና አዲስ የመመሪያ አወጣጥ commence a new one, where an agency intends to
ሂደት ከመጀመር አይከለከልም፡፡ adopt a directive with substantial difference.
፪/ በመጨረሻ መልክ የተዘጋጀ መመሪያ በማስታወቂያ 2/ A final draft directive shall be considered to be
ከተመለከተው የመመሪያው ረቂቅ መሠረታዊ ልዩነት substantially different from the one publicized
አለው ሊባል የሚችለው በሚከተሉት ሁኔታዎች ነው፦ where:

ሀ) የረቂቅ መመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን በጉልህ


a) The scope of application of the draft directive
የተለወጠ ከሆነ፤ ወይም
has markedly changed ;or
ለ) ረቂቅ መመሪያው አዳዲስ ግዴታዎችን አካትቶ c) The draft directive introduces new obligations .
የተገኘ ከሆነ፡፡
፲፬. የማብራሪያ ጽሑፍ 14. Explanatory Statement

ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ በሚያወጣበት ጊዜ At the time of adopting a directive, an agency shall

የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ የመመሪያው ማብራሪያ prepare a directive explanatory note containing the

ማዘጋጀት አለበት፦ following :

፩/ መመሪያው የወጣበት የሕግ መሠረትና ዓላማ፤ 1/ The objective and legal basis for adoption of the
directive;
፪/ በማስታወቂያው የተሰራጨው ረቂቅና የመጨረሻ ሆኖ
2/ Where there are differences of content from the
በወጣው መመሪያ መካከል የይዘት ልዩነት ካለ
draft circulated through notice and the directive
የተደረጉትን ለውጦች ከነምክንያቶቹ የሚገልጽ
adopted, a note explaining the changes and the
ማስታወሻ፤
rationale thereof;
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፸፰ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12478
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፫/ በረቂቅ መመሪያው ላይ የቀረቡ አስተያየቶችና 3/ A summary of comments on the draft and measures
የተወሰዱ እርምጃዎች ማጠቃለያ፡፡ taken in accordance .

 ፲፭. የመመሪያ ይዘትና ቅርፅ 15. Content and Form of Directives


፩/ በአስተዳደር ተቋም የሚወጣ ማንኛዉም መመሪያ 1/ In addition to the substantive body, a Directive
የሚዘጋጀው በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲሆን adopted by an Agency shall be prepared in English and
ከመመሪያው ዋና ይዘት በተጨማሪ የሚከተሉትን Amharic language and contain:
መያዝ አለበት፦

ሀ) የመመሪያው ተራ ቁጥር፤ a) Serial Number of the Directive ;

ለ) መመሪያው እንዲወጣ የሥልጣን ምንጭ የሆነውን b) A reference to a specific law on the basis of which

ሕግ፤ the Directive is adopted ;


ሐ) የመመሪያውን አጭር ርእስ፤
c) A short title of the Directive ;
መ)ትርጓሜ፣ የተፈፃሚነት ወሰን፣ ዋና ዋና
d) Definition, scope of application, main Provisions;
ድንጋጌዎች፤
e) A rule referring to directives amended
ሠ) የማሻሻያ ፣ መሻሪያ፣ መሸጋገሪያ፣ ማቆያ ድንጋጌ
repealed,transitory provisions or suspended if any;
ካለ ይህንኑ የሚመለከት ድንጋጌ፤
f) Notwithstanding the date specified in Article 18 of
ረ) የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፰ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ
this Proclamation the effective date of the Directive.
መመሪያው የወጣበትንና ተፈጻሚ የሚሆንበትን
ቀን፡፡
፪/ ማንኛውም መመሪያ በአጭርና በግልጽ ቋንቋ መጻፍ 2/ Directives must be written in a precise and clear
አለበት፡፡ language .

፫/ የአስተዳደር ተቋም ሌላ አካል ያወጣቸውን በሥልጣኑ 3/ An agency may incorporate, by reference in its rules,
ክልል የሚወድቁ መመሪያዎች ወይም የሥነ-ምግባር all or part of directives or Code of conduct that has
ደንቦች በሙሉ ወይም በከፊል በማጣቀስ የራሱ መመሪያ been adopted by another agency/body where these
አካል ማድረግ ይችላል፡፡ matters fall within its scope of power.
4/ The agency shall publicize rules it has incorporated
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) መሰረት የመመሪያው
pursuant to sub Article (3) of this Article and submit
አካል ያደረጋቸውን ሰነዶች ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግና
copies to the Federal Attorney General to be
በአንቀጽ ፲፮ መሰረት እንዲመዘገብ ለፌደራል ጠቅላይ
registered in accordance with Article 16 of this
አቃቤ ሕግ መላክ አለበት፡፡
Proclamation.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፸፱ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12479
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፲፮. የመመሪያ ምዝገባ 16. Filing of Directive
፩/ ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም መመሪያ እንዳወጣ 1/ Up on adoption, an agency shall before put on the
ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት መመሪያውን ከነማብራሪያው directives it has sending the copies and
ለፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመላክ እንዲመዘገብ accompanying explanatory statement to the
ማድረግ አለበት፡፡ Attorney General.

፪/ ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ አንቀጽ ንዑስ 2/ The Federal Attorney General shall provide a serial
አንቀፅ (፩) መሰረት የተላከለትን መመሪያ ቁጥር ሰጥቶ identification number and record Directives
ይመዘግባል። መመሪያው ስለመመዝገቡም ለአስተዳደር submitted to it in accordance with sub-Article (1) of
ተቋሙ ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት፡፡ this Article. It shall also immediately notify the
agency about the status of registration.

፫/ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመዘገበውን መመሪያ


3/ The Attorney General shall publicize to the pubic a
ከነማብራሪያው መዝግቦ ለአስተዳደር ተቋሙ ካሳወቀበት
filled directives with its explanatory
እለት ጀምሮ ለሕዝብ ክፍት ማድረግ አለበት፡፡
statement.Since the date of notifying its
registration.

፬/ ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ይህ አዋጅ ከመውጣቱ 4/ All Agencies shall file directives they have adopted
በፊት በሥራ ላይ የነበረ መመሪያን ይህ አዋጅ በወጣ prior to the coming in to force of this Proclamation
ከ፺ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለፌደራል ጠቅላይ within 90 Days after the coming in to force of this
ዓቃቤ ሕግ በመላክ እንዲመዘገብ ማድረግ አለበት፡፡ Proclamation by sending copies to the Federal
Attorney General .
 ፲፯ የመመሪያ ተደራሽነት 17. Accessibility of Directives
፩/ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ አዋጅ አንቀጽ
1/ The Federal Attorney General shall post directives on
፲፮ መሠረት የመዘገበውን መመሪያ በድህረ ገጹ ላይ its own website that has filed in accordance with
መጫን አለበት፡፡ Article 16 of this Proclamation.

፪/ ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ያወጣውን መመሪያ፦


2/ Any agency shall issued a directive :
ሀ) አሳትሞ ለሚመለከታቸው መንግስታዊና ሌሎች a) Print and disseminate to Governmental and other
ባለድርሻ አካላት ማሠራጨት፣ እና Stakeholders ; and

ለ) በተቋሙ ድህረ ገጽ ላይ መጫን፣አለበት፡፡ b) Post it on its website .

፫/ ማንኛውም የመመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚፈልግ 3/ Any person who is interested can observe on the place
ሰው መመሪያውን ባለበት ሁኔታ የመመልከት ወይም situated or may get a copy of the directive subject to
ወጪውን ሸፍኖ ከአስተዳደር ተቋሙ የማግኘት payment of expenses.
መብት አለው፡፡
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፹ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12480
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፲፰ የመመሪያ ተፈጻሚነት 18. Conditions of Enforcement

፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፮ መሠረት ያልተመዘገበ እና 1/ A directive that has not been filed pursuant Article
በአንቀጽ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ (፪) ፊደል ተራ (ለ) 16 or posted on the website of the agency pursuant
መሠረት በአስተዳደር ተቋሙ ድህረ ገጽ ላይ to Article 17 (2) (b) of this Proclamation may not be
ያልተጫነ መመሪያ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ enforced

፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ተፈጻሚነቱን 2/ A directive that has lost its validity in accordance
ያጣ መመሪያ ተፈፃሚነት እንዲኖረው በዚህ ክፍል with sub Article (1) of this Article may be adopted
ንዑስ ክፍል ሁለት የተደነገገውን የቅድመ መመሪያ following the Procedures provided under this Sub
አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተከትሎ እንደ አዲስ እንዲወጣ Section of Two of this Section of Proclamation.

ሊደረግ ይችላል፡፡
፲፱. ስለመመሪያ ተፈጻሚነት ግምገማ 19. Periodic Review of Directives

ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ያወጣውን መመሪያ An Agency shall from time to time review the

አፈጻጸም በተመለከተ በየጊዜው እየገመገመ አስፈላጊውን implementation of directives it has adopted and take

እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡


necessary measures.

ክፍል ሦስት
SECTION THREE
የአስተዳደር ውሳኔዎች ADMINISTRATIVE DECISIONS
SUB SECTION ONE
ንዑስ ክፍል አንድ
INITIATION OF ADMINISTRATIVE DECISIONS
የአስተዳደር ውሳኔ አጀማመር
20. Initiation of Administrative Decision
፳. የአስተዳደር ውሳኔ መጀመር
1/ An application for an administrative decision be
፩/ የአስተዳደር ውሳኔ እንዲሰጥ የሚቀርብ ጥያቄ ጉዳዩ made by an interested person or his agent.
በሚመለከተዉ ሰዉ ወይም በወኪሉ ሊቀርብ ይችላል፡፡

፪/ የአስተዳደር ውሳኔ በሚመለከተዉ የአስተዳደር ተቋም 2/ An administrative decision process may be initiated

አነሳሽነት ሊጀመር ይችላል፡፡ by the relevant administrative agency.

 ፳፩. የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ የሚቀርብበት ሁኔታ 21. Manner of Administrative Decision Application
1/ An application for administrative decision shall be
፩/ የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ በጽሑፍ ሆኖ እንደሁኔታዉ
made in writing and may be submitted in person, a
በአካል፣ በተመዘገበ ፖስታ ወይም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ
registered postal address or electronic means.
ሊቀርብ ይችላል፡፡
፪/ የአስተዳደር ውሳኔ ይሰጥልኝ ጥያቄ አቤቱታ በፅሑፍ 2/ A written application of administrative decision
ሲቀርብ የሚከተሉትን መያዝ ይኖርበታል፡- shall include:
Abrham
፲፪ሺ፬፻፹፩ Yohanes https://t.me/ethiopianlegalbrief 12481
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
ሀ) ቀን፣ የአቤቱታ አቅራቢው ወይም ወኪሉ ስም፣
a) Date, name of the applicant or his agent,
ፊርማ እና አድራሻ፤
signature and address;
ለ) አስተዳደራዊ ተግባሩን የሚፈፅመው ተቋም
b) Name of the administrative agency to whom the
ስም፤
petition is made;
ሐ) የአቤቱታ አቅራቢው መብት ወይም ጥቅም፤
c) The right and interest of the applicant being
መ) ተቋሙ ሊፈፅመው የሚገባ አስተዳደራዊ ተግባር፤
sought;
ሠ) ተቋሙ ለሚተገብረው አስተዳደራዊ ተግባር
d) Act that the administrative authority has to do.
መሰረት የሆኑ ምክንያቶች እና ተያያዥ
e) Facts and evidence relevant for the decision.
ማስረጃዎች፤
፫/ የአስተዳደር ተቋም የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ
3/ An agency may prepare forms through which an
የሚቀርብበትን ቅጽ ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡
application may be made.
 ፳፪. ጥያቄን የመቀበል ማስረጃ 22. Record of Applications
፩/ አቤቱታ የቀረበለት ተቋም አቤቱታውን በተረከበበት 1/ Upon receiving an application for administrative
ጊዜ አቤቱታውን የተቀበለ መሆኑን መዝግቦ decision, the agency shall immediately furnish.
የማረጋገጫ ጽሑፍ መስጠት አለበት፡፡ 2/ A written confirmation of application, shall contain
፪/ የማረጋገጫ ጽሑፉ አቤቱታውን የተቀበለ መሆኑንና details of receiving relevant documents attached
ከአቤቱታው ተያይዘው የቀረቡ ሰነዶችን ዝርዝር there.
የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡
SUB SECTION TWO
ንዑስ ክፍል ሁለት
PRINCIPLES OF ADMINISTRATIVE DECISION
የአስተዳደር ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች
MAKING
 ፳፫.የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠው ሰው
23. An Administrative Decision Maker
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰው የአስተዳደር ተቋሙ
የበላይ ኃላፊ ወይም ሥልጣን የተሰጠዉ የተቋሙ የሥራ decision may only be rendered by the Head or

ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ብቻ መሆን አለበት፡፡


Authorized Official/Manager or Staff of an agency.

 ፳፬.በሕግ የተሰጠ ሥልጣን ወሰንን አለማለፍ 24. Respecting Scope of Authority


A person rendering an administrative decision shall
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ
respect the scope of authority of the agency
ለአስተዳደር ተቋሙ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን ወሰን
established by Law.
ማለፍ የለበትም፡፡
፳፭.የግል እና የሕዝብ ጥቅምን ማመዛዘን 25. Balancing of Public and Individual Interest
A person rendering an administrative decision shall
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ተቋሙን
balance the individual interest of the person
ተገልጋይ የግል ጥቅም እና በአስተዳደር ተቋሙ ዓላማ
regarding whom an administrative decision is being
የተመለከተውን የሕዝብ ጥቅም ማመዛዘን አለበት፡፡
considered with that of the public interest identified
in the objectives of the agency.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፹፪ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12482
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፳፮.አግባብነት በሌለዉ ጉዳይ ወይም ፍላጎት አለመመራት 26. Avoiding Irrelevant Matters and Interests
A person rendering an administrative decision
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ለጉዳዩ አግባብነት
should avoid influence from irrelevant facts or
በሌለዉ ጉዳይ ወይም ፍላጎት መመራት የለበትም፡፡
interests.
፳፯.ሙያዊ ውሳኔ መስጠት 27.Rendering of Professionalsm
A decision, shall abide by the ethical standards, show
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ሙያዉ የሚጠይቀዉን
due diligence and care that is required by the relevant
ሥነ-ምግባር፣ ትጋት እና ጥንቃቄ ማክበር አለበት፡፡
task or profession.
፳፰.ማዳመጥ 28. Hearing
በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፫ መሠረት የአስተዳደር ውሳኔ The person rendering administrative decisions in
የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ውሳኔ ከመሥጠቱ በፊት accordance with articles 23 of this Proclamation shall
የሚመለከተዉን ሰው ፍሬ ነገር እና ማስረጃ በሚገባ provide adequate opportunity of hearing to arguments
ማዳመጥ እና መመርመር እንዲሁም እንደነገሩ ሁኔታ and evidence presented by the person regarding
የሦስተኛ ወገን ተቃዋሚን እና የሕዝብን አስተያየት whom decision is being made, and as the case may be
ማዳመጥ አለበት፡፡ to third parties as well as the public.
29. Good faith
 ፳፱.በቅን ልቦና መወሰን
A person rendering administrative decisions should
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ በቅን ልቦና መወሰን made the decision in good faith.
አለበት፡፡ 30. Reasoned Decision

 ፴.በቂ ምክንያት መስጠት The person rendering administrative decisions


should provide adequate reason for the decision he
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ለአስተዳዳር ውሳኔው
makes.
በቂ ምክንያት መስጠት አለበት፡፡

 ፴፩.የጥቅም ግጭትን ማስቀረት 31. Avoiding Conflict of Interest


Where a person rendering administrative decisions
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ከተገልጋዩ ጋር የሥጋ
has blood, affinity or any other kind of relation that
ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው ከሆነ ወይም በማናቸውም
may cause a conflict of interest, he shall recuse
ሁኔታ የጥቅም ግጭት የሚያስከትልበት ከሆነ ጉዳዩን
himself from case.
ከማየት እራሱን ማግለል አለበት፡፡

 ፴፪.የተገልጋዮችን እኩልነት ማክበር


32. Keep Customers Equality
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ ሁሉንም ተገልጋዮች A person rendering administrative decisions shall not
በዘር፣ በብሄር፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ discriminate between persons based on race, color,
በፖለቲካ አመለካከት፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት ethnicity, sex, language, religion, political view,
መጠን፣ በትውልድ ሁኔታ ወይም በሌላ ምክንያት ልዩነት social background, class, or any other ground.
ሳያደርግ መወሰን አለበት፡፡
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፹፫ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12483
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፴፫. በተገቢዉ ጊዜ መወሰን 33. Timely Decision
፩/ የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር 1/ The person rendering administrative decision shall
ውሳኔዉን ሳይዘገይ በተገቢዉ ጊዜ መስጠት እና give a decision without delay in a reasonable period
በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ጥቅሞች በውሳኔው መዘግየት of time and ensure that interests associated with the
ምክንያት ለጉዳት እንዳይጋለጡ ማድረግ አለበት፡፡ decision are not negatively affected as a result of
delay.
፪/ የአስተዳደር ውሳኔ በተገቢው ጊዜ ሳይሰጥ መቅረት 2/ Failure to render decision within an appropriate
የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ period of time shall be considered as denial of the
እንደተሰጠ ውሳኔ ይቆጠራል፡፡ petition.

 ፴፬.ተገማች መሆን 34. Predictability


In matters involving similar facts, the person
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ በፍሬ ነገር ተመሳሳይ
rendering an administrative decision shall decide in
የሆኑ ጉዳዮችን በተመሳሳይ ሁኔታ መወሰን አለበት፡፡
the same manner.
 ፴፭ .ግልጽ መሆን
35. Transparency
የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ
A person rendering administrative decisions shall
ግልጽነትን የተከተለ እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡
ensure the transparency of the decision making
process.
ንዑስ ክፍል ሦስት SUB SECTION THREE

ጉዳዩን ስለመስማት HEARING THE ISSUE


36. Hearing of the Case
 ፴፮. ጉዳዩን ስለመስማት
1/ Before rendering any administrative decisions shall
፩/ ማንኛውም አስተዳደራዊ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት
provide adequate opportunity of hearing.
ጉዳዩ በሚገባ መሰማት አለበት፡
2/ Notwithstanding to sub article 1 of this Article
፪/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) የተጠቀሰው ቢኖርም
decision may render without hearing:-
ጉዳዩን መስማት ሳያስፈልግ ውሳኔመስጠትየሚቻለው፡- a) If there is no arguments of the facts of the
case;
ሀ) የፍሬ ነገር ከርክር ከሌለ፤
b) If it is special privilege or if the
ለ) ልዩ መብት ከሆነ ወይም የአስተዳደር ተቋሙ በህግ administrative agency has alternative
በአማራጭ እንዲወስን ስልጣኑ ካለው፤ወይም decision power ;or
c) The issue is urgent.
ሐ) አስቸኳይ ድርጊት ከሆነ፤ነው፡፡
Abrham
፲፪ሺ፬፻፹፬ Yohanes https://t.me/ethiopianlegalbrief 12484
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
 ፴፯. ጉዳዩ ስለሚሰማበት አግባብ 37. Conditions of Hearing
፩/ የአስተዳደር ጉዳይ በሚሰማበት ጊዜ ባለጉዳዩ 1/ The parties to case has the right to appear in person
በክርክሮች ሂደት ሁሉ ተገኝቶ ፡- and have the right:

ሀ) ምስክርነት የመስጠት፤ a) To give testimony ;

ለ) ምስክሮችን እና ሌሎች ማስረጃዎችን የማቅረብ እና


b) To produce evidences ;
የማሰማት፤
ሐ) ለተቋሙ የቀረቡ ማስረጃዎችን የመስማትና c) To access and examine evidences presented to the
የመመርመር፤መብት አለው፡፡ Authority .
፪/ ተቋሙ ማስረጃ ለማግኝት በክርክሩ ተካፋይ ከሆነ
2/ The Agency may use all legal methods to get
ወገን፣ ከምስክሮች፣ ሙያዊ አስረጂ፣ የሰነድ ምርመራ documents of investigation and other any
እና ሌሎች ማናቸውንም አስፈላጊ ማስረጃዎችን evidences from the party participated in the
ለማግኘት ሕጋዊ ዘዴዎችን መጠቀም ይችላል፡፡ argument, witnesses and professional persons.
 ፴፰. ስለመነሳት
38. Recusal
፩/የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጥ ሰው በሚከተሉት ምክንያቶች 1/ A person may be recused from the decision making
ጉዳዩን ከማየት ሊነሳ ይችላል፦ on one of the grounds listed here under:

ሀ) ከጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅም a) He has a direct or indirect interest on the
ካለው፤ matter ;
ለ) ጉዳዩ የስጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ወይም b) The matter at hand affects a person that has a
በቅርብ የሚታወቅ ወዳጁ ሲሆን ወይም የእነዚህ relation with a decision maker in
ሰዎች የጥቅም ግጭት ያለበት ጉዳይ ከሆነ ፤ consanguinity or Affinity, close friend ;

ሐ) በመታየት ላይ ላለው ጉዳይ እንደ ባለሙያ፣ ወኪል c) If he has represented the person regarding
ወይም የግል ጠበቃ ሆኖ ተሳትፎ ከሆነ፤ whom the decision is being considered, as an
agent, attorney or in any other professional
መ) በመታየት ላይ ያለው ጉዳይ ሰራተኛው በስር ውሳኔ
capacity ;
አይቶት በይግባኝ የቀረበለት ከሆነ፤
d) He has made a decision on the matter in
another capacity ;

፪/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) የተመለከቱ ምክንያቶች 2/ In case where one of the grounds listed under sub

ካሉ ውሳኔ በሚሰጠው ሰራተኛ አነሳሽነት ወይም ጉዳዩ article (1) of this Article are present, the person

በሚመለከተው ሰው አመልካችነት ጉዳዩን ከማየት ሊነሳ may be recused from decision making process on

ይችላል፤
his own accord, or the petition of the an interested
person;
Abrham
፲፪ሺ፬፻፹፭ Yohanes https://t.me/ethiopianlegalbrief 12485
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፫/ የይነሳልኝ ጥያቄ ከቀረበና ጥያቄው የቀረበለት ኃላፊ 3/ If recusal is requested, until the head of
የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት administrative decision rendering final decision
ሰራተኛ ውሳኔ ከመስጠት ሂደቱ ታግዶ ይቆያል፤ the person raised matter of recusal shall remain
suspended from entertaining the case;
፬/ የእነሳለሁ ወይም የይነሳልኝ ጥያቄ የቀረበለት ኃላፊ 4/ The Head accepted the recusal request initiated by
በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ ሰራተኛው ከውሳኔ ሰጪነት the interested person or others shall render
እንዲነሳ ወይም እንዲቀጥል መወሰን አለበት፡፡ decision within five working days to stay or
recused .
ንዑስ ክፍል አራት SUB-SECTION FOUR
የአስተዳደር ውሳኔ ADMINISTRATIVE DECISION

፴፱. የአስተዳደር ውሳኔውን ለተገልጋዩ ስለመስጠት


39. Giving the Decision to the Client
ማንኛውም የአስተዳደር ውሳኔ ከነምክንያቱ ለተገልጋዩ
An Agency shall notify the concerned person of its
በጽሑፍ መሠጠት አለበት፡፡
decision with its reason in writing.
 ፵. የአስተዳደር ውሳኔ
40. Administrative Decision
ማንኛውም የአስተዳደራዊ ውሳኔ በጽሑፍ ሆኖ
All administrative decision shall be made in writing
የሚከተሉትን መያዝ ይኖርበታል፦
and contain:
፩/ የውሳኔ ቀንና ቁጥር ፤
1/ Date and Number of Decision;
፪/ የተቋሙን ስም ፤
2/ Name of the Authority;
፫/ በክርክሩ ተካፋይ የሆኑ ወገኖችን አድራሻ፤
3/ Parties to the case and their address;
፬/ አከራካሪ ፍሬ ነገር፤
4/ Issues of claim;
፭/ የማስረጃዎች ትንተና፤
5/ Discretion of Evidences;
፮/ የፍሬ ነገር እና የሕግ ትንታኔ፤
6/ Description of Fact and Law;
፯/ ውሳኔ 7/ Decision.
 ፵፩. ስለ እገዳ
41. Suspension
፩/ የአስተዳደራዊ ውሳኔ ወዲያውኑ መፈፀም በመብቱ
1/The party whose who may incur irreparable on his
ወይም በጥቅሙ የማይመለስ ጉዳት የሚያደርስበት ሰው
right and intrerest by immediate enforcement of
ወሳኔው እንዲታገድለት ውሳኔውን ለሰጠው ተቋም
the decision can apply for the suspension of the
አቤቱታ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
decision to the authority rendering decision.
፪/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) መሰረት አቤቱታ 2/ An administrative agency receiving a petition as
የተቀበለ የአስተዳደር ተቋም እንደየሁኔታው ጉዳዩ per Sub Article 1 of this Article may order the case
እንደገና እንዲታይ ወይም የውሳኔውን ማናቸውም ክፍል to be seen again or to suspend any part of the
ሊያግደው ይችላል፡፡ decision.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፹፮ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12486
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
 ፵፪. የአስተዳደር ውሳኔን የሚፈጽመው ሰው 42. Person to Enforce Administrative Decisions
An administrative decision shall be enforced by the
ማንኛውም የአስተዳደር ውሳኔ የሚፈጸመው ውሳኔውን
person or a concerned body who has made the decision.
በሰጠው ሰዉ ወይም በሚመለከተዉ አካል ይሆናል፡፡

ንዑስ ክፍል አምስት SUB SECTION FIVE


COMPLAINT AGAINST ADMINISTRATIVE
በአስተዳደር ውሳኔ ላይ ስለሚቀርብ ቅሬታ
DECISION

፵፫. ቅሬታ የማቅረብ መብት 43. Right to Lodge Complaint


Any person against whom and administrative decision
ማንኛውም ሰዉ በተላለፈበት የአስተዳደር ውሳኔ ላይ
is made has the right to lodge a complaint to the
ለአስተዳደር ተቋሙ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው፡፡
Agency.
፵፬. የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ማቋቋም 44. Establishment of Complaint Handling Body
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል All administrative agencies shall establish a complaint
ማቋቋም እና ይህንኑ ለተገልጋዮች ይፋ ማድረግ handling division and notify such establishment to

አለበት፡፡ clients.

፵፭. የአስተዳደር ውሳኔው አፈፃፀም መታገድ 45. Stay of Enforcement


ማንኛውም ቅሬታ የቀረበበት የአስተዳደር ውሳኔ ቅሬታው Enforcement of any decision of an administrative
ተመርምሮ እስኪወሰን ድረስ አይፈጸምም፡፡ ሆኖም agency against which a complaint is lodged will be
የውሳኔው ሳይፈጸም መቆየት በሕዝብ ላይ የማይመለስ stayed until the complaint is processed and a final
ጉዳት የሚያስከትል ከሆነ የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ decision made. However, the head of the Agency may
ኃላፊ ዉሳኔዉ እንዲፈጸም ሊያዝ ይችላል፡፡ order the enforcement of the decision where delay in
enforcement may cause an irreversible damage to public
interest.
፵፮. ቅሬታውን ስለመመርመርና ስለመወሰን
46. Considering the complaint
፩/ የአስተዳደር ተቋሙ የቅሬታ ማስተናገጃ አካል 1/ The complaint handling body shall properly
ቅሬታውን በሚገባ መመርመር እና የዉሳኔ ሀሳብ examine the complaint it has received and present
ለአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም እሱ its recommendation to the Head of the Agency or
ለወከለዉ የሥራ ኃላፊ ማቅረብ አለበት፡፡ an officer duly authorized by the Head.

፪/ የአስተዳደር ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም እሱ


2/ The decision of the Head of the Agency or an
የወከለዉ የሥራ ኃላፊ በቅሬታ ማስተናገጃ አካል officer duly authorized by the Head of the Agency,
የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ተመልክቶ የሰጠው ውሳኔ after considering the recommendation of the
የተቋሙ የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል፡፡ complaint handling body shall be considered as the
final decision of the agency.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፹፯ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12487
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፵፯. ውሳኔውን ለተገልጋዩ ስለማሳወቅ 47. Notification of Decisions
An agency shall notify the petitioner, in writing, the
የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፮ መሠረት
decision made pursuant to Article 46 of this
የተሰጠውን ውሳኔ ወዲያዉኑ ለቅሬታ አቅራቢው
Proclamation.
በጽሑፍ መስጠት አለበት፡፡

ክፍል አራት SECTION FOUR

በፍርድ ቤት የሚደረግ የአስተዳደር መመሪያዎችና ውሳኔዎች JUDICIAL REVIEW OF DIRECTIVES AND


ADMINISTRATIVE DECISIONS
ክለሳ
SUB-SECTION ONE
ንዑስ ክፍል አንድ INITIATION OF REVIEW

የክለሳ አጀማመር

፵፮. የክለሳ አቤቱታ ስለማቅረብ 48. Filing of Petition for Review


የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፵፮ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፦
Without prejudice to the Provisions under Article 46 of
this Proclamation :
፩/ ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው የአስተዳደር
1/ Any interested person may file a petition requesting
መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ ማቅረብ
a judicial review of a directive;
ይችላል፤
፪/ ማንኛውም በአስተዳደር ውሳኔ ጥቅሙ የተነካበት ሰው 2/ Anyone whose interest is affected by an
ውሳኔው በፍርድ ቤት እንዲከለስ አቤቱታ ማቅረብ administrative decision may file a petition
ይችላል፡፡ requesting judicial review.

፵፱. የክለሳ አቤቱታ ስለሚቀርብበት ፍርድ ቤት 49. Power of Review


፩/ የአስተዳደር መመሪያ ወይም ዉሳኔ እንዲከለስ 1/ A petition to review directives or administrative
አቤቱታ የሚቀርበው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት decisions shall be submitted to the Federal High
ይሆናል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔም የመጨረሻ Court and the decision of the Court will be final.

ይሆናል፡፡
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው 2/ Notwithstanding the stipulation under Sub- article

ቢኖርም፣ የአስተዳደር መመሪያን በተመለከተ (1) of this Article, a decision of High Court

ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ወሳኔ፣ ጠቅላይ ፍርድ directive may be appealed to the Federal Supreme

ቤት ይግባኝ ሊቀርብበት ይችላል።


Court.

፫/ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክለሳ አቤቱታዎችን 3/ The Federal High Court shall establish special

የሚያስተናግድ የአስተዳደር ጉዳይ ችሎት benches dedicated to handle petitions for judicial

ያደራጃል፡፡ review of administrative acts.


Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፹፰ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12488
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
ንዑስ ክፍል ሁለት SUB-SECTION TWO
PRINCIPLES OF REVIEW
የክለሳ መርሆዎች
50. Grounds of Review
፶. የክለሳ ምክንያት

፩/ የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት የሚከለሰው:- 1/ A Directive will be revoked by the Court where

ሀ) በዚህ አዋጅ ክፍል ሁለት የተመለከቱትን የሥነ- a) It is proved to have failed to comply with the
ሥርዓት ድንጋጌዎች ሳይከተል የወጣ መሆኑ procedural rules provided in Chapter Two of this
ሲረጋገጥ፣ Proclamation;
b) It is ultravires; or
ለ) ከአስተዳደር ተቋሙ የሥልጣን ገደብ ውጪ የወጣ
ሲሆን፣ ወይም
c) It is contrary to other laws placed higher in the
ሐ) በእርከን ከመመሪያ በላይ ከሆኑ ሌሎች ህጎች Hierarchy of Laws.
የሚቃረን ሲሆን ነው፡፡

፪/ የአስተዳደር ውሳኔ በፍርድ ቤት የሚከለሰው በዚህ አዋጅ 2/ An administrative decision may be revoked if it is
ክፍል ሦስት የተደነገጉትን መርሆዎች የጣሰ ሲሆን ነው፡፡ made in violation of the Principles provided under
Chapter Three of this Proclamation.

፶፩. የክለሳ አቤቱታ የሚቀርበው በመጨረሻ ውሳኔ ላይ


51. Petition of Review of Decisions
ስለመሆኑ

ማንኛውም የፍርድ ቤት ክለሳ አቤቱታ የሚቀርበው A Judicial Review may only be sought against a final
የመጨረሻ በሆነ የአስተዳደር ውሳኔ ላይ ብቻ ነው፡፡ decision of an agency.

፶፪. አስተዳደራዊ መፍትሄዎችን አሟጦ ስለመጨረስ 52. Exhaustion of Remedies

፩/ በሕግ በሌላ ሁኔታ ካልተደነገገ በቀር ማንኛውም ለፍርድ 1/ Unless otherwise provided by law, a petitioner for

ቤት የክለሳ አቤቱታ የሚያቀርብ ባለጉዳይ አቤቱታውን Judicial Review is required to exhaust all remedies

ከማቅረቡ በፊት በአስተዳደር ተቋሙ ውስጥ ያሉትን available within the Agency before petitioning the

አስተዳደራዊ መፍትሄዎች አሟጦ መጨረስ አለበት፡፡ court for judicial review.

፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ድንጋጌ (፩) ቢኖርም 2/ Notwithstanding the rule under Sub Article (1) of
የአስተዳደር ተቋሙ አስተዳደራዊ መፍትሄ የመስጠቱን this Article, where there is an undue delay on the
ሂደት ከሚገባው ጊዜ በላይ ያራዘመ እንደሆነ አስተዳደራዊ part of the agency to provide remedies, the
መፍትሄ አሟጦ መጨረስ ግዴታ አይሆንም፡፡ obligation to exhaust remedies will not apply.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፹፱ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12489
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
ንዑስ ክፍል ሦስት SUB-SECTION THREE
PROCEDURE OF JUDICIAL REVIEW
የክለሳ ሥርዓት

፶፫. የክለሳ አቤቱታ የሚቀርብበት ጊዜ 53. Period of Limitation on Petition for Judicial Review
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶ ንዑስ አንቀጽ (፩) ፊደል ተራ
1/ A petition under Article 50 Sub Article 1 (a) to
(ሀ) መሠረት የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ ቤት
review a directive shall be submitted within 90 days
እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ መመሪያው ከጸደቀበት after the adoption of the directive.
ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የ፺ ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ
አለበት፡፡
፪/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፶ ንዑስ አንቀጽ ፩ ፊደል ተራ(ለ)
2/ A petition under Article 50 Sub Article 1 (b) or (c) to
ወይም (ሐ) መሠረት የአስተዳደር መመሪያ በፍርድ review a directive can be submitted any time.
ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ አቤቱታ በማናቸውም ጊዜ
ሊቀርብ ይችላል፡፡
፫/ የአስተዳደር ውሳኔ በፍርድ ቤት እንዲከለስ የሚቀርብ 3/ A petition to review an administrative decision shall
አቤቱታ ባለጉዳዩ ውሳኔውን እንዲያውቀው ከተደረገበት be made within 30 days after the petitioner was
ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የ፴ ቀናት ጊዜ ውስጥ መቅረብ notified of the decision .
አለበት፡፡
፶፬. የጽሑፍ መልስ ስለማቅረብ 54. Written Response
Where the court finds that the petition for review has
የክለሳ አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት አቤቱታው
the merit, court shall give to the agency against
ሊመረመር ይገባል ብሎ ሲያምን ቅሬታው የቀረበበት
whom a petition of review had been filed an
የአስተዳደር ተቋም በ፲፭ የሥራ ቀናት ዉስጥ የጽሑፍ
opportunity to submit a written response with 15
መልስ እንዲሰጥ ያዛል።
days.
፶፭. ሰነዶችን ስለማቅረብ

የክለሳ አቤቱታ የቀረበበት የአስተዳደር ተቋም አቤቱታ 55. Submission of Records,


The court may order the agency against whom a
የቀረበበትን መመሪያ ወይም ዉሳኔ በተመለከተ አስፈላጊ
review petition is being considered to submit records
ሰነዶች እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ሊያዝ ይችላል፡፡
relating to the directive or administrative decision
under consideration.
Abrham
፲፪ሺ፬፻፺ Yohanes https://t.me/ethiopianlegalbrief 12490
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
ንዑስ ክፍል አራት SUB-SECTION FOUR
DECISION OF JUDICIAL REVIEW AND
የክለሳ ዉሳኔ አሰጣጥ እና አፈፃፀም
EXECUTION

፶፮. የክለሳ ዉሳኔ አሰጣጥ 56. Judgment of Judicial Review


1/ The Court shall investigate the petition of review
፩/ ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታውን በተቻለ መጠን በአጭር
and render its decision within the shortest possible
ጊዜ ውስጥ መርምሮ ዉሳኔ መስጠት አለበት፡፡
period of time.

፪/ ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን የአስተዳደር 2/ The Court may confirm; or partially or fully reverse
መመሪያ ወይም ዉሳኔ ሊያፀና ወይም በሙሉ ወይም the administrative decision or directive submitted
በከፊል ሊሽር ይችላል፡፡ for review .

፫/ ፍርድ ቤቱ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን የአስተዳደር 3/ Where the court renders a decision which partially or
መመሪያ ወይም ውሳኔ በሙሉ ወይም በከፊል ሲሽር fully invalidate the administrative decision or
የአስተዳደር ተቋሙ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተጠቆሙ directive, it may also order the administrative agency
ግድፈቶችን አስተካክሎ መመሪያውን እንደገና እንዲያወጣ to revise or reenact the directive or reconsider its
ወይም እንዲያሻሽል፣ ወይም ውሳኔ ሰጥቶበት የነበረውን administrative decision by rectifying the
ጉዳይ እንደገና መርምሮ እንዲወስን ሊያዘው ይችላል፡፡ shortcomings identified through the court’s decision.

፶፯. የክለሳ ዉሳኔ አፈፃፀም 57. Execution of the Decision


1/ The decision of the Court to uphold or invalidate a
፩/ በፍርድ ቤት የተሰጠ የአስተዳደር መመሪያን ወይም
directive or and administrative decision shall be
ዉሳኔን የማፅናት ወይም የመሻር ውሳኔ ወዲያዉኑ ተፈፃሚ
executed immediately.
ይሆናል፡፡

፪/ ፍርድ ቤቱ የአስተዳደር መመሪያው ወይም ውሳኔው 2/ Where the Court renders a decision for the revision
እንዲሻሻል ካዘዘ የአስተዳደር ተቋሙ በዚህ አዋጅ ክፍል of an administrative decision or directive, the
ሁለት እና ሦስት የተመለከቱትን የሥነ-ሥርዓት administrative institution shall do the same in an

ድንጋጌዎች እና መርሆዎች አክብሮ መመሪያውን ወይም appropriate time, by giving due consideration to

የአስተዳደር ውሳኔውን በተገቢዉ ጊዜ ማሻሻል አለበት፡፡ the Provisions provided under Chapters Two and
Three of this Proclamation.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፺፩ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12491
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፫/ በፍርድ ቤቱ የተሰጠ የአስተዳደር መመሪያን ወይም 3/ The judgment of the Court fully or partially
ዉሳኔን በሙሉ ወይም በከፊል የመሻር ዉሳኔ ወይም invalidating a directive or administrative
የማሻሻል ትዕዛዝ የክለሳ አቤቱታ የቀረበበትን መመሪያ decision, or an order of amendment shall, either
ወይም ውሳኔ ሕጋዊ ኃይል በሙሉ ወይም በከፊል fully or partially, revoke the legality of such
ያስቀራል፡፡ directive or decision.

፬/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) የተገለጸው ቢኖርም፣


4/ Notwithstanding the rule under Sub Article (3) of
ፍርድ ቤቱ አንድን የአስተዳደር መመሪያ በከፊልም ሆነ
this Article, decisions of an administrative agency
በሙሉ የሚሸር ወሳኔ ሲሰጥ፣ የአስተዳደር ተቋሙ made on the basis of a revoked directive prior to
መመሪያው ከመሻሩ በፊት በተሻረው መመሪያ መሰረት the ruling of the court shall stay valid.
የሰጣቸው አስተዳደራዊ ውሳኔዎቸ እንደጸኑ ይቆያሉ።

ክፍል አምስት
SECTION FIVE
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች MISCELLANEOUS PROVISIONS

፶፰. የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ተፈፃሚ ስለመሆኑ 58. Applicability of the Civil Procedure Code
በዚህ አዋጅ ክፍል አራት ባልተመለከቱ የክለሳ ሥነ- On procedural matters not covered by Chapter Four
ሥርዓት ጉዳዮች ላይ አግባብነት ያላቸዉ የፍትሐብሔር of this Proclamation, the relevant Provisions of the
ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ Civil procedure Code shall apply.

፶፱. የጉዳት ካሣ ስለመጠየቅ 59. Compensation


ከአስተዳደር መመሪያ ወይም ውሳኔ ጋር በተያያዘ ጥፋት A person who has incurred damage as a result of a fault
ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ሰው መመሪያውን committed through issuance of directives or an
ያወጣው ወይም ውሳኔውን የሰጠው የአስተዳደር ተቋም administrative decision is entitled to seek
አግባብ ባለዉ ሕግ መሠረት ካሳ እንዲከፍለው የመጠየቅ compensation from the administrative authority that is
መብት አለው፡፡ responsible, in accordance with the relevant laws.

፷. መረጃ የመስጠት ግዴታ


60. Duty to Provide Information
ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም ከመመሪያ ማውጣት ወይም
Where any administrative agency is requested to
ከአስተዳደር ውሳኔ መስጠት እና እነዚህን ከመፈጸም ጋር
provide information relevant in the issuance of
በተያያዘ በሌላ ህጋዊ አካል ሲጠየቅ መረጃ የመስጠት
directives or rendering of administrative decisions by
ግዴታ አለበት፡፡
legal organ, such agency shall provide the
information.
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፬፻፺፪ https://t.me/ethiopianlegalbrief 12492
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page
፷፩. ደንብ የማውጣት ሥልጣን 61. Power to Issue Regulation
The Council of Ministers may issue Regulations that
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም
might be necessary for the proper implementation of
የሚያስፈልግ ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡
this Proclamation.
፷፪. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
62. Effective Date
ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን
This Proclamation shall enter into force on the date of
ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡ publication in the Federal Negarit Gazettee.

አዲስ አበባ መጋቢት ፳፱ ቀን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም Done at Addis Ababa, On the 7th Day of April 2020.

SHALEWORK ZEWDE
ሣህለወርቅ ዘውዴ

PRESIDENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC


የኢትዮጽያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ
REPUBLIC OF ETHIOPIA
ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት
Abrham Yohanes https://t.me/ethiopianlegalbrief 12493
th
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፴፪ መጋቢት ፳፱ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M Negarit Gazette No. 32 , April 7 2020 …..page

You might also like