You are on page 1of 23

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሃያ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፲፮ 29th Year No. 16


አዲስ አበባ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ADDIS ABABA, 27th February, 2023
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ Content
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፸፰/፪ሺ፲፭ Proclamation No. 1278/2023
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን እንደገና Ethiopian Broadcasting Corporation

ለማቋቋም የወጣ አዋጅ…………ገጽ ፲፬ሺ፮፻፹፭ Re-Establishment Proclamation……Page 14685

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፸፰/፪ሺ፲፭ PROCLAMATION NO. 1278/2023

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ETHIOPIAN BROADCASTING

እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ CORPORATION RE-ESTABLISHMENT


PROCLAMATION

ኮርፖሬሽኑ የገቢ አቅሙ የተጠናከረ ሆኖ WHEREAS, it has become necessary to

ተልዕኮውን በተሻለ ሁኔታ በመወጣት በሀገሪቱ strengthen the financial capacity of the

ሁለንተናዊ እድገት እና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት Corporation to enable it to better accomplish its

ግንባታ ሂደት የሚጠበቅበትን አዎንታዊ ሚና mission in order to be able to play a positive


role that is expected of it in the country’s
መጫወት እንዲችል ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
endeavor to ensure overall development and
build a democratic system;

የኮርፖሬሽኑ ሥልጣንና ተግባር ከተለያዩ WHEREAS, it has become necessary to


ሁለት አዋጆች መመንጨቱ የአሠራር ክፍተት include in one Proclamation the powers and

በመፍጠሩ በአንድ አዋጅ ሥር ማጠቃለሉ ተገቢ responsibilities of the Corporation which

መሆኑ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር emanate from two separate Proclamations and

ቦርድ ተቋሙን በተሻለ ሁኔታ የሚደግፍበትን has created a gap in the practice of the

ሥርዓት ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑንና Corporation, and also to create a system

የኮርፖሬሽኑን ዓላማ፣ ሥልጣን እና ተግባራት


whereby the Board of the Corporation can
support the institution in a better way, and to
በግልጽ ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
clearly stipulate the objectives, power and
responsibilities of the Corporation;

ÃNÇ êU nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1


Unit Price Negarit G. P.O.Box 80001
gA ፲፬ሺ፮፻፹፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14686

የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያን በማሻሻል WHEREAS, it has become necessary to


እና በዘመናዊ አሠራር እንዲደገፍ በማድረግ improve television service fee and modernize
ህብረተሰቡ ግዴታውን በቀላሉ እንዲወጣ its payment system to enable the society to
የሚያስችል ሥርዓት እንዲፈጠር እንዲሁም discharge its obligation easily and also to
ግዴታቸውን የማይወጡ የቴሌቪዥን ባለቤቶች stipulate legal accountability for those

ላይ የሕግ ተጠያቂነትን መደንገግ አስፈላጊ television set owners who do not discharge

በመሆኑ፤ their duties;

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ NOW, THEREFOR, in accordance with

ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ንዑስ- Article 55(1) of the Constitution of the Federal

አንቀጽ (፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ Democratic Republic of Ethiopia, it is hereby


proclaimed as follows.

ክፍል አንድ PART ONE

ጠቅላላ GENERAL

፩. አጭር ርዕስ 1. Short Title

ይህ አዋጅ “የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ This Proclamation may be cited as the


“Ethiopian Broadcasting Corporation Re-
ኮርፖሬሽንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር
Establishment Proclamation of No.
፩ሺ፪፻፸፰/፪ሺ፲፭” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
1278/2023”.

፪. ትርጓሜ 2. Definition
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ Unless the context requires otherwise, in this
በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡- Proclamation:
፩/ “ሠራተኛ” ማለት ከዋና ሥራ አስፈፃሚ እና 1/ “Employee” means any worker of the
ከምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ውጪ ያሉ Corporation other than the Chief Executive
በተለያየ ደረጃ የሚገኙ አመራሮች /የሥራ and Deputy Chief Executives and it
ኃላፊዎች/፣ ጋዜጠኞች፣ የቴክኒክ ባለሞያዎችና includes unit leaders at various levels,
ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን ያካትታል፤ journalists, technical experts and support
staff;

፪/ “ብሮድካስቲንግ” ማለት ሕዝብን ለማስተማር፣ 2/ “Broadcasting” means audio and audio-


ለማሳወቅ ወይም ለማዝናናት በሬዲዮ፣ visual transmission that is conducted to
በቴሌቪዥን፣ በዲጂታል ሚዲያ እና በተለያዩ educate, inform or entertain the public
የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች አማካኝነት through radio, television, digital media, and
የሚከናወን የድምጽ እና የምስልና የድምጽ various electronic devices;
ሥርጭት ነው፤
gA ፲፬ሺ፮፻፹፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14687

፫/ “ቦርድ” ማለት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት 3/ “Board” means the higher management
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚሾሙ body of the Corporation composed of
አባላትን የያዘ ኮርፖሬሽኑን በበላይነት members appointed by the House of
የሚመራ አካል ነው፤ Peoples’ Representatives upon
recommendation by the Prime Minister;

፬/ “የበላይ ኃላፊ” ማለት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ 4/“Higher Official” includes the Corporation’s


አስፈፃሚ እና ምክትል ዋና ሥራ Chief Executive and Deputy Chief
አስፈፃሚዎችን ያካትታል፤ Executives;

፭/ “ቴሌቪዥን” ማለት ድምፅንና ሥዕልን 5/ “Television Set” means a device that

በአንቴና፣ በሳተላይት፣ በኬብል ወይም በሌላ receives, transmits and displays audio and

ተመሳሳይ መንገድ ተቀብሎ የሚያሰማ እና pictures using antenna, satellite, cable or

የሚያሳይ መሣሪያ ሲሆን ኮምፒውተር፣ other similar means but does not include

ላፕቶፕ፣ አይፓድ፣ ታብሌትን እና ስማርት computer, laptop, ipad, tablets, and smart
phones;
ስልክን አይጨምርም፤

፮/ “ነጋዴ” ማለት የሙያ ሥራው አድርጎ ጥቅም 6/ “Trader” means a person who
ለማግኘት በቴሌቪዥን አስመጪነት፣ professionally and for gain engages in the
አከፋፋይነት ወይም ሻጭነት ተሰማርቶ importation, distribution or sale of television

የሚገኝ ሰው ማለት ነው፤ sets;

፯/ “የቴሌቪዥን ባለቤትነት እና አገልግሎት 7/ “Television Set Ownership and Service


ፍቃድ” ማለት ማንኛውም ሰው ቴሌቪዥን License” means license issued by the
ወደ ሀገር ሲያስገባ ወይም ከነጋዴ ወይም Corporation to any person who imports
ከቴሌቪዥን አምራች ሲገዛ በቴሌቪዥኑ television set into the Country or buys it
ለመጠቀም እንዲችል በኮርፖሬሽኑ የሚሰጠው from a trader or a manufacturer to enable
ፍቃድ ነው፤ him to use the television set;

፰/ “የቴሌቪዥን ባለቤትነት እና አገልግሎት ፍቃድ 8/ “Television Ownership and Service


ክፍያ” ማለት ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለቤት License Fee” means a payment made to the
የሆነ ሰው የቴሌቪዥን ባለቤት በመሆኑ እና Corporation by any owner of a television set
ቴሌቪዥኑን የመገናኛ ብዙሃን ሥርጭትን for being the owner of a television set and
ለመከታተል እንዲችል ለሚያገኘው ፍቃድ the license he has been issued to use it to
ለኮርፖሬሽኑ የሚከፍለው ክፍያ ማለት ነው፤ follow mass media transmissions;
gA ፲፬ሺ፮፻፹፰ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14688

፱/ “ዲጂታል ሚዲያ” ማለት ከመደበኛ የቴሌቪዥን 9/ “Digital Media” means any transmission
እና የሬዲዮ ስርጭት ውጪ በድህረ-ገፅ፣ service made, without using the regular
በበይነ መረብ ወይም በማናቸውም የማህበራዊ television and radio broadcasting, by using
ሚዲያ መጠቀሚያ መንገድ በመጠቀም website, internet, or any other social media
የሚደረግ የስርጭት አገልግሎት ማለት ነው፤ means;

፲/ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ 10/ “Region” means any State included under
ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት Article 47 of the Constitution of the Federal
አንቀፅ ፵፯ የተካተተ ማንኛውም ክልል ሲሆን Democratic Republic of Ethiopia and
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የድሬዳዋ includes Addis Ababa and Dire Dawa City
ከተማ አስተዳደርን ይጨምራል፤ Administrations;

፲፩/ “አጋር አካላት” ማለት ለኮርፖሬሽኑ ዓላማ 11/“Partners” means institutions that have
መሳካት ጉልህ ሚና ያላቸው ተቋማት እና significant roles in the achievement of the
ኮርፖሬሽኑ የቴሌቪዥን ፍቃድ የአገልግሎት Corporation’s objectives and bodies that
ክፍያ ለማስከፈል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ execute the Corporation’s efforts to ensure
በአጋርነት የሚያስፈፅሙ ተቋማት ማለት payment of television license fees as
ነው፤ associates;

፲፪/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ 12/ “Person” means natural or legal person;
የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤

፲፫/ ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም 13/ Any expression in the masculine gender
ያካትታል፡፡ includes the feminine gender.

ክፍል ሁለት Part Two


ስለ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን Ethiopian Broadcasting Corporation

፫. ስለመቋቋም
3. Establishment

፩/ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ከዚህ 1/ The Ethiopian Broadcasting Corporation


በኋላ “ኮርፖሬሽን” እየተባለ የሚጠራ) የሕግ (hereinafter the “Corporation”) is hereby

ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ ህዝባዊ አገልግሎት re-established by this Proclamation as an

የሚሰጥ የህዝብ የሚዲያ ተቋም ሆኖ በዚህ አዋጅ autonomous public media institution

እንደገና ተቋቁሟል፡፡ having legal personality to render public


services.
gA ፲፬ሺ፮፻፹፱ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14689

፪/ ኮርፖሬሽኑ ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር 2/ The Corporation shall be accountable to


ቤት ይሆናል፡፡ the House of Peoples’ Representatives.

፬. ዋና መሥሪያ ቤት 4. Head Office

የኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ The Corporation shall have its head office

ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በመላ ኢትዮጵያ እና


in Addis Ababa and may estabilish,
branches and agents in all parts of Ethiopia
በውጭ ሀገራት በተለያዩ ሥፍራዎች ቅርንጫፎች
and at different places in foreign countries.
እና ወኪሎች ሊኖሩት ይችላል፡፡
as may necessary.

፭. የኮርፖሬሽኑ ዓላማዎች 5. Objectives of the Corporation

የኮርፖሬሽኑ ዓላማዎች፡- The objectives of the Corporation shall be:

፩/ በመገናኛ ብዙሃንና በሌሎች አግባብ ባላቸው 1/ Making the public actively participate in

ሕጎችና ፖሊሲዎች መሠረት በሀገር ውስጥና the prosperity of the country by creating

በውጭ ሀገር ስለሚፈጸሙ አበይትና ወቅታዊ awareness about all affairs taking place

ጉዳዮች እንዲሁም ትምህርታዊና አዝናኝ in the country through presentation, in

ዝግጅቶችን በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በዲጂታል accordance with mass media and other

ሚዲያ በማቅረብ፤ ከሕዝቡም በግብረ-መልስ


relevant laws and policies, of main and
current events occurring domestically or
ሥርዓት ወይም በቀጥታ የሚገኘውን ግብዓት
in foreign country and educational and
በመጠቀም ሕዝቡ በሀገሪቱ በሚካሄዱ
entertainment programs using radio,
ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ኖሮት በሀገር
television and digital media and by using
ብልፅግና ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ፤
inputs received from the public directly
or through feedback procedures;

፪/ በህዝቦች መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረተ 2/ Supporting national effort that is made to

አንድነት እንዲጠናከርና ትስስራቸው ሥር strengthen trust-based unity among

እንዲሰድ፤ እንዲሁም ብሔራዊ መግባባት peoples and deepen their connections

በመፍጠር ወንድማማችነትና ሕብረ-ብሔራዊ and also to promote fraternity and


national unity by creating national
አንድነትን ለማጎልበት የሚደረገውን ሀገራዊ
consensus;
ጥረት ማገዝ፤

፫/ በሀገሪቱ ጠንካራ የዲሞክራሲ ሥርዓት እውን 3/ Playing key role in the efforts made to

እንዲሆን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ ሚና create a strong democratic system in the

መጫወት፡፡ country.
gA ፲፬ሺ፮፻፺ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14690

፮. የኮርፖሬሽኑ ሥልጣንና ተግባራት 6. Power and Responsibilities of the


Corporation
ኮርፖሬሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት
The Corporation shall have the following
ይኖሩታል፡- power and responsibilities:

፩/ ለሕዝብ ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ዜናዎችና 1/ To gather and prepare news and news
መዋዕለ-ዜናዎችን ማሰባሰብ፣ ማዘጋጀትና packages which are useful to and
በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በዲጂታል ሚዲያ necessary for the public and broadcast
በልዩ ልዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎች them to the users through radio,
በማሠራጨት ለተገልጋዩ የማድረስ፤ television, and digital media in various
local and foreign languages;

፪/ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ፤ ለሁለንተናዊ 2/ To present educational and informative


እድገት እና ለሀገራዊ አንድነት ህብረተሰቡን programs which motivates the society for
የሚያነሳሱ፤ በህዝቦች መካከል መቀራረብን building democratic system, overall

የሚያጎሉ እንዲሁም በመተማመን ላይ development, and national unity; promote

የተመሰረተ አንድነት ለማምጣት የሚያስችሉ proximity among peoples; and enable

ትምህርታዊና አሳዋቂ ፕሮግራሞችን bringing about trust-based unity; and,

የማቅረብ፣ የመንግሥትን ፖሊሲዎችና ሕጎች introduce government policies and laws

ለሕዝብ ማስተዋወቅ፤ to the public;

፫/ ሕዝቡ ስለ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች 3/ To present programs that help to promote


ያለው ግንዛቤ እንዲዳብር የሚረዱ public awareness about human and
ፕሮግራሞችን የማቅረብ፤ democratic rights;

፬/ ነጻ የሕዝብ አስተያየቶችንና ጥቆማዎችን 4/ To receive and transmit free public


ተቀብሎ የማስተላለፍ፤ comments and disclosures;

፭/ የሕዝቡን ዕውቀትና ፈጠራ የሚያዳብሩና 5/ To present various programs that promote


የመዝናናት ፍላጎቱን የሚያረኩ ልዩ ልዩ public knowledge and creativity and
ኘሮግራሞችን የማቅረብ፤ satisfy the entertainment needs of the
public;

፮/ በሀገር ውስጥና ከውጭ ካሉ ተመሳሳይ 6/ To create relations with similar domestic


ድርጅቶች ጋር ግንኙነት የመመሥረት፤ and foreign organizations;
gA ፲፬ሺ፮፻፺፩ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14691

፯/ ለጋዜጠኞች፣ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች 7/ To give professional training to


እና ሌሎች በዘርፉ የሚመለከታቸው journalists, mass media experts and other
ባለሙያዎች የሙያ ሥልጠና መስጠት፤ concerned experts in the sector;

፰/ ለሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ የመወሰንና 8/ To determine and collect service charges;


የመሰብሰብ፣ እንደ አስፈላጊነቱ በከፊል ወይም to exempt from payment in part or in
በሙሉ ከክፍያ ነፃ የማድረግ፤ whole, as deemed necessary;

፱/ በሀገሪቱ የሚመረቱ እና ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ 9/ To register television sets imported and


ቴሌቪዥኖችን የመመዝገብ ፍቃድ የመስጠት manufactured in the country, to issue
ለዚህም ዓመታዊ የፍቃድ ክፍያ የማስከፈል፤ license, and to receive annual license fee;

፲/ ማናቸውንም የቴሌቪዥን ነጋዴን ወይም 10/ To register any television set trader or

የቴሌቪዥን አምራችን ለመመዝገብ፣ television manufacturer and to require any

ማናቸውም ነጋዴ የሚሸጠውን ቴሌቪዥን trader to register the television set he sells;

በመዝገብ እንዲይዝ ለማድረግ፤


11/ To own property, to enter into
፲፩/ የንብረት ባለቤት መሆን፣ ውል የመዋዋል፣ agreements, to borrow and lend in its
በስሙ የመበደር እና የማበደር፤ የመክሰስና own name, to sue and be sued;
የመከሰስ፤
12/ Without prejudice to the protection
፲፪/ በቅጂ እና ተዛማጅ መብት አዋጅ የተቀመጠው
provided in the Copyrights and
የብሮድካስት አገልግሎት ጥበቃ እንደተጠበቀ
Neighbouring Rights Proclamation for
ሆኖ ኮርፖሬሽኑ ለሚሠራቸው የሬዲዮ እና
broadcasting service, to become the
የቴሌቪዥን የዶክመንተሪ እንዲሁም
owner of intellectual property right for
የዲጂታል ሚዲያ ሥራዎች የአእምሮአዊ
radio and television documentaries it
ንብረት ባለቤት መሆን፤
prepares and digital media works;

፲፫/ በሀገሪቱ ግልፅነት እና ተጠያቂነት ያለበት 13/ To work on investigative journalism with
ሥርዓት እንዲሰፍን ለማስቻል የምርመራ emphasis to facilitate the system of
ጋዜጠኝነት ላይ በትኩረት መሥራት፤ transparency and accountability to
prevail in the country;

፲፬/ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ሌሎች 14/ To carry out other related activities that
ተዛማጅ ተግባራትን የማከናወን፡፡ will enable it to achieve its objectives.
gA ፲፬ሺ፮፻፺፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14692

፯. የኮርፖሬሽኑ አቋም 7. Organizational Structure of the


Corporation
ኮርፖሬሽኑ፡- The Corporation shall have:

፩/ ቦርድ፤ 1/ The Board;

፪/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና አስፈላጊ የሆኑ 2/ Chief Executive and necessary Deputy

ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች፤ Chief Executives; and,


3/ Other necessary staff.
፫/ አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች፤

ይኖሩታል፡፡

፰. ስለ ቦርዱ 8. The Board

1/ The members of the Board, including the


፩/ የቦርዱ አባላት ሰብሳቢውን ጨምሮ በጠቅላይ
Chairperson, shall be appointed by the
ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች
House of Peoples’ Representative upon
ምክር ቤት ይሾማሉ፤ ቁጥራቸው እንደ
recommendation by the Prime Minister;
አስፈላጊነቱ የሚወሰን ሆኖ ከሰባት ማነስ
While their number may be determined
የለበትም፤
as deemed necessary; it shall not be less
than seven;

፪/ የቦርዱ አባላት ስብጥር አግባብነት ካላቸው 2/ The members of the Board shall be drawn
ተቋማትና ከልዩ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች from pertinent institutions and various
የተውጣጣ እና የፆታ ስብጥርን ያማከለ groups of the society and by considering
ይሆናል፤ gender diversity;

፫/ የቦርዱ ተጠሪነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር 3/ The Board shall be accountable to the
ቤት ይሆናል፤ House of Peoples’ Representatives;

፬/ የቦርዱ የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል፤ 4/ The term of the Board shall be five years;

፭/ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ያለድምጽ 5/ The Chief Executive of the Corporation


የሚሳተፍ አባልና ጸሐፊ ይሆናል፤ shall be a non-voting member and
Secretary of the Board;

፮/ ቦርዱ የራሱን የአሠራር መመሪያ ያወጣል፡፡ 6/ The Board shall adopt Directives to
govern its working procedure.
gA ፲፬ሺ፮፻፺፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14693

፱. የቦርዱ ሥልጣንና ተግባራት 9. Power and Responsibilities of the Board

ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት The Board shall have the following power

ይኖሩታል፡- and responsibilities:

፩/ መገናኛ ብዙሃንን በሚመለከቱ የመንግሥት 1/ To ensure that government policies and


ፖሊሲዎች እና ሕጎች በኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ laws concerning mass media are
መሆናቸውን የማረጋገጥ፤ implemented by the Corporation;

፪/ በሕዝብ መታወቅ ያለባቸው የመንግሥት 2/ To ensure that government policies and


ፖሊሲዎችና ሕጎች በወቅቱ መተላለፋቸውን laws which should be known by the

ማረጋገጥ፤ public are communicated timely;

፫/ በኮርፖሬሽኑ የሚሰራጩ ፕሮግራሞች ሀገራዊ 3/ To follow up that programs transmitted by


አንድነትን እና ብልፅግና ማረጋገጥ ላይ ግብ the Corporation aim to ensure national
ያደረጉ መሆናቸውን መከታተል፣ unity and prosperity;

፬/ በኮርፖሬሽኑ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን 4/ To follow up that programs with diverse


ሚዲየሞች የሃሳብ እና የይዘት ብዝሃነት views and contents are prepared and
ያላቸው ፕሮግራሞች ተቀርፀው ለህዝብ transmitted to the public through the
መቅረባቸውን መከታተል፤ Corporations radio and television
mediums;

፭/ ኮርፖሬሽኑ በሚሰጠው አገልግሎት ሕዝቡ 5/ To evaluate if the public is benefiting from


ተጠቃሚ መሆኑን የመገምገም፣ ህዝቡ the services rendered by the Corporation;
በሚዲያው ይበልጥ ተጠቃሚ ስለሚሆንበት to present ideas on how the public can
ሁኔታ ሃሳብ የማቅረብ፤ benefit more from the media;

፮/ የተለያየ አመለካከት ያላቸው የፖለቲካ 6/ To ensure that political parties and sections

ፓርቲዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ሚዛናዊ of the society which have different views

የሆነ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፍትሐዊ አገልግሎት obtain balanced radio and television service

ማግኘታቸውን የማረጋገጥ፤ in a fair manner;

፯/ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በዲጂታል ሚዲያ እና 7/ To evaluate the contents of the programs


በሌሎች በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች transmitted through radio, television, digital
የሚተላለፈውን ፕሮግራም ይዘት የመገምገም፣ media and other electronic devices, and to
ስለሚሻሻልበትም ሁኔታ ሐሳብ የማቅረብ፤ present ideas as to how they can be
improved;
gA ፲፬ሺ፮፻፺፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14694

፰/ ከአድማጭና ከተመልካች በኮርፖሬሽኑ ላይ 8/ To investigate and make appropriate


የሚቀርቡ ቅሬታዎችን የመመርመር፣ ተገቢውን decisions on complaints lodged against the
ውሳኔ የመስጠት፤ Corporation by listeners and viewers;

፱/ በዚህ አዋጅ እና በኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች 9/ In accordance with the power given to it by


አስተዳደር ደንብ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት this Proclamation and the Corporation’s
ቦርዱ መመሪያ ሊያወጣ በሚገባቸው ጉዳዮች Employees Regulation, to issue Directives
ላይ መመሪያ የማውጣት፣ የኮርፖሬሽኑ on matters the Board shall issue Directives,
ሠራተኞች የደመወዝ፣ አበልና ሌሎች ጥቅማ to decide on the salary, allowance, and

ጥቅሞቻቸው ላይ የመወሰን፤ other benefits of the employees of the


Corporation;

፲/ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት 10/ To create conducive environment for the

እንዲችል የዘመነ ቴክኖሎጂ ባለቤት Corporation to own latest technology to be

የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤ የኮርፖሬሽኑ able to achieve its establishment

ፕሮግራሞች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተደራሽ objectives; to follow up that the programs

መሆናቸውን መከታተል እንዲሁም ኮርፖሬሽኑ of the Corporation are accessible in all

የሚጠናከርበትንና አሠራሩ የሚሻሻልበትን


parts of the Country; and to design a
mechanism that can strengthen the
መንገድ የመቀየስ፤
Corporation and improve its practice;

፲፩/ የኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ የሥራ ዕቅድና የሥራ 11/ To evaluate and approve the annual work
እንቅስቃሴ ሪፖርት መገምገም እና ማፅደቀቅ plan and activity report of the
እንዲሁም በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የተላኩ Corporation; and also to follow-up to
የኦዲት ግኝቶች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ensure that the findings sent by the Office
ይከታተላል፤ of the General Auditor receive swift
response;

፲፪/ የኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ የገቢ እና የወጪ በጀት 12/ To approve the annual income and
ማፅደቅ፤ expenditure budget of the Corporation;

13/ To advise and decide on other policy


፲፫/ ኮርፖሬሽኑን በሚመለከቱ ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮች
issues concerning the Corporation.
ላይ የመምከር፣ የመወሰን፡፡
gA ፲፬ሺ፮፻፺፭ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14695

፲. የቦርዱ ስብሰባዎች 10. Meetings of the Board

፩/ ቦርዱ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ 1/ The Board shall hold at least one regular
ያደርጋል፤ meeting per month;

፪/ አስቸኳይ ሁኔታ ሲያጋጥም በቦርዱ ሰብሳቢ 2/ In case of emergency, meeting may be


ወይም ከቦርዱ አባላት መካከል ቢያንስ አንድ held at any time upon request by the
ሦስተኛው አባላት ከጠየቁ በማናቸውም ጊዜ Chairperson of the Board or by at least
ሊሰበሰብ ይችላል፤ one-third of the Board members;

፫/ በቦርዱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ አባላት ከተገኙ 3/ There shall be a quorum if more than half
ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል፤ of the members are present at the Board’s
meeting;

፬/ ቦርዱ ውሳኔ የሚያሳልፈው በድምጽ ብልጫ 4/ Decisions of the Board shall be passed by
ይሆናል፤ ሆኖም ድምጽ እኩል ለእኩል a majority vote. However, in case of a tie,
የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን the Chairperson has a casting vote;
ሐሳብ የቦርዱ ውሳኔ ሆኖ ያልፋል፤
5/ The Board shall adopt its own meeting
፭/ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥርዓት መመሪያ
rules of procedure.
ያወጣል፡፡
11. Chief Executive of the Corporation
፲፩. ስለ ኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
1/ The Chief Executive shall be appointed by
፩/ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በጠቅላይ ሚኒስትሩ
the House of Peoples' Representatives
አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
upon recommendation by the Prime
ይሾማል፤ Minister;

2/ The Chief Executive of the Corporation


፪/ ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ
shall spearhead and administer the tasks of
አስፈጻሚ በመሆን ከቦርዱ በሚሰጠው
the Corporation in accordance with the
አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኮርፖሬሽኑን
overall direction given by the Board;
ሥራ ይመራል፤ ያስተዳድራል፤

3/ Without prejudice to the generality of the


፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ (፪) የተደነገገው
provision of Sub-Article (2) of this Article,
አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና
the Chief Executive shall:
ሥራ አስፈጻሚው፡-
a) Implement the power and responsibilities
ሀ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ለኮርፖሬሽኑ
entrusted to the Corporation in
የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት ሥራ ላይ
accordance with Article 6 of this
ያውላል፤
Proclamation;
gA ፲፬ሺ፮፻፺፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14696

ለ) የኘሮግራሞች ይዘት አቅጣጫን ያቅዳል፣ b) Plan content direction of programs; follow


አፈጻጸማቸውንይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤ up and control their execution;

c) Hire and administer employees of the


ሐ) የኮርፖሬሽኑን ሠራተኞች ይቀጥራል፣ Corporation;
ያስተዳድራል፤
d) Prepare and submit to the Board and the
መ) የኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ የሥራ
House of Peoples’ Representatives the
ፕሮግራምና የበጀት ፍላጎት እንዲሁም Corporation’s annual work plan, budget
የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት አዘጋጅቶ needs, and activity report;
ለቦርዱ እና ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት
ያቀርባል፤
e) Prepare draft annual budget support that
ሠ) ኮርፖሬሽኑ ከመንግስት የሚያስፈልገውን
the Corporation needs from the
ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ ረቂቅ አዘጋጅቶ
government and submit it to the Ministry
ለገንዘብ ሚኒስቴር ያቀርባል፤
of Finance;

ረ) ለኮርፖሬሽኑ በተፈቀደው በጀትና የሥራ f) Effect expenditure in accordance with the


ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ budget and work plan approved for the
ያደርጋል፤ በተለያዩ የንግድ ባንኮች Corporation; open bank accounts in
ተቋሙን በመወከል የባንክ ሒሳብ different commercial banks representing
ይከፍታል፤ the Institution;

ሰ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ


g) Represent the Corporation in all dealings
ግንኙነቶች ሁሉ ኮርፖሬሽኑን ይወክላል፤
made with third parties;

ሸ) የኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ አቅም h) Prepare and follow-up implementation of


እንዲጠናከር ስትራቴጂ ይነድፋል፤ strategies that can strengthen the financial
ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤ capacity of the Corporation;

ቀ) ከቦርዱ የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን i) Discharge other responsibilities assigned


ያከናውናል፡፡ by the Board.

፬/ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለኮርፖሬሽኑ የሥራ 4/ The Chief Executive may delegate part of


ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና his power and responsibilities to the
ተግባሩን በከፊል ለኮርፖሬሽኑ የሥራ officials and employees of the Corporation
ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና to the extent necessary for the efficiency of
ሊያስተላልፍ ይችላል፤ the work of the Corporation;
gA ፲፬ሺ፮፻፺፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14697

፭/ ዋና ሥራ አስፈፃሚው በተለያየ ምክንያት 5/ The Chief Executive shall delegate one the
በሥራ ላይ በማይገኝበት ጊዜ ከምክትል ዋና Deputy Chief Executives if he is not present
ሥራ አስፈፃሚዎቹ አንዱን ይወክላል፡፡ at work for various reasons. However, if it is
ሆኖም ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሥራ ላይ known in advance that the duration of his
የማይገኘው ከሁለት ወር በላይ መሆኑን absence from work will be for more than

በቅደሚያ የሚታወቅ ከሆነ የሚወከለው two month, the delegation of the Deputy

ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ውክልና Chief Executive shall obtain a written

የቦርዱን ሰብሳቢ የጽሑፍ ፍቃድ ማግኘት permission from the Chairperson of the

ይኖርበታል፡፡ Board.

፲፪. ስለምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች 12. Deputy Chief Executives

1/ The Deputy Chief Executives of the


፩/ የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች
Corporation shall be appointed by the
በዋና ሥራ አስፈጻሚው አቅራቢነት በቦርዱ
Board upon recommendation by the
ይሾማሉ፤ ተጠሪነታቸው ለዋና ሥራ አስፈፃሚ
Chief Executive; They shall be
ይሆናል፡፡
accountable to the Chief Executive.

፪/ እያንዳንዱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ 2/ Every Deputy Chief Executive or Sector


ወይም የዘርፍ መሪ ከዋናው ሥራ አስፈጻሚ Head shall, in accordance with the
በሚሰጠው መመሪያ መሠረት በሥሩ direction given by the Chief Executive,
የተመደበለትን ዘርፍ ሥራ ይመራል፣ lead and coordinate the tasks of the sector
ያስተባብራል፣ እንዲሁም ከዋና ሥራ under his leadership and perform other
አስፈጻሚው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት activities assigned to him by the Chief
ያከናውናል፡፡ Executive.

፲፫. ሪፖርት ስለማቅረብ 13. Reporting

The Corporation shall submit, through its


ኮርፖሬሽኑ በሥልጣን ክልሉ
Chief Executive, periodic reports to the
ስለሚያከናውናቸው ተግባራት በዋና ሥራ
Board and the House of Peoples'
አስፈፃሚው በኩል በየጊዜው ለቦርዱ እና
Representatives on the activities it
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት
performs within the limits of its power.
ያቀርባል፡፡

14. Budget of the Corporation


፲፬. የኮርፖሬሽኑ በጀት
1/ The budget of the Corporation shall be
፩/ የኮርፖሬሽኑ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች
generated from the following sources:
የተውጣጣ ይሆናል፡-
gA ፲፬ሺ፮፻፺፰ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14698

ሀ) በዚህ አዋጅ መሠረት ኮርፖሬሽኑ a) Income collected by the Corporation


ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ከሚሰበሰብ from the services it renders in
ገቢ፤ accordance with this Proclamation;

ለ) ከመንግስት ከሚደረግለት ዓመታዊ b) Annual budget support made by the

የበጀት ድጋፍ፤ Government;

ሐ) በዚህ አዋጅ መሠረት ከቴሌቪዥን c) Service charges collected in

ባለቤቶች ከሚሰበሰብ የቴሌቪዥን accordance with this Proclamation

ባለቤትነት አገልግሎት ፍቃድ from television set owners for

ክፍያ፤ television service license;

መ) ከሌሎች የገቢ ምንጮች፡፡ d) Other income sources.


[[[[[

፪/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) (ለ) መሠረት 2/ In order to determine the amount of
በመንግስት ለኮርፖሬሽኑ የሚሰጠውን regular budget support the government
የመደበኛ በጀት ድጋፍ መጠን ለመወሰን gives to the Corporation in accordance
እንዲችል ኮርፖሬሽኑ በየዓመቱ with Sub-Article (1) (b) above, the
የሚያስፈልገውን የመደበኛ በጀት ድጋፍ ጥያቄ Corporation shall submit to the Ministry of
በዝርዝር እና የበጀት ድጋፉ ያስፈለገበትን Finance every year detailed request for
ምክንያት በሚያሳይ መልኩ ለገንዘብ regular budget support and the reasons
ሚኒስቴር ያቀርባል፡፡ thereof.

፫/ ከላይ በንዑስ-አንቀጽ (፩) እና (፪) የተቀመጠው 3/ Without prejudice to the provisions of


እንደተጠበቀ ሆኖ የኮርፖሬሽኑ የካፒታል Sub-Article (1) and (2) above, the capital
በጀት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል budget of the Corporation may be covered
በመንግስት ሊሸፈን ይችላል፡፡ by the Government wholly or in part.

፲፭. ስለኮርፖሬሽኑ የግዢና የፋይናንስ ሥርዓት 15. Procurement and Financial Procedures
of the Corporation
የኮርፖሬሽኑ የግዢና የፋይናንስ ሥርዓት
የመንግስት የፋይናንስ እና የንብረት አስተዳደር The procurement and financial system of

ፅንሰ ሀሳቦችን መሠረት በማድረግ ቦርዱ the Corporation shall be governed by the

በሚያወጣው የግዢ እና የፋይናንስ መመሪያዎች Procurement and Financial Directives

የሚመራ ይሆናል፡፡ issued by the Board on the basis of the


procurement and financial administration
concepts of the Government.
gA ፲፬ሺ፮፻፺፱ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14699

፲፮. የሒሳብ መዛግብት 16. Books of Account


፩/ ኮርፖሬሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሒሳብ 1/ The Corporation shall keep complete and

መዛግብትና የገንዘብ ሰነዶች ይይዛል፤ accurate books of accounts and financial


documents;
፪/ የኮርፖሬሽኑ የሒሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ 2/ The books of accounts and finance related
ሰነዶች በፌደራል ዋናው ኦዲተር በየዓመቱ documents of the Corporation shall be
ይመረመራሉ፡፡ audited annually by the Auditor General
of the Federal Government.

ክፍል ሦስት PART THREE

የቴሌቪዥን ምዝገባ እና የፍቃድ TELEVISION REGISTRATION AND


እድሳት አገልግሎት LICENSE RENEWAL SERVICE

፲፯. የቴሌቪዥን ምዝገባ እና የአገልግሎት ፍቃድ 17. Television Registration and License Fee
ክፍያ

፩/ ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለቤት የሆነ ሰው 1/ Any person who owns a television set
ቴሌቪዥኑን ማስመዝገብ እና በዚህ አዋጅ shall register his television and pay
የተመለከተውን የቴሌቪዥን ባለቤትነት ownership and service charge indicated in
እና አገልግሎት ፍቃድ ክፍያ መፈጸም this Proclamation;
አለበት፤
፪/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) በተጠቀሰው 2/ The Corporation shall establish a working
መሠረት ኮርፖሬሽኑ የቴሌቪዥን system to register television set owners
ባለቤቶችን የሚመዘግብበትን እና ፍቃድ and issue license in accordance with
የሚሰጥበትን የአሠራር ሥርዓት Sub-Article (1) of this Article. The
ይዘረጋል፡፡ የአገልግሎት ፍቃድ ክፍያ system of service charge payment shall
ሥርዓቱ በዚህ አዋጅ አንቀፅ ፲፰ be guided by the provision of Article 18
በተቀመጠው ድንጋጌ መሠረት የሚመራ of this Proclamation.
ይሆናል፡፡
፲፰. የቴሌቪዥን አገልግሎት ፍቃድ ክፍያ መጠን እና 18. Amount of Television Service License
አተገባበር Fee and Its Implementation
፩/ ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለቤት 1/ Any owner of a television set shall pay
ለሚጠቀምብት ለእያንዳንዱ ቴሌቪዥን annual television ownership and service
በዓመት ብር ፩፻፳ (አንድ መቶ ሃያ ብር) license fee of 120 Birr (One Hundred
የቴሌቪዥን ባለቤትነት እና አገልግሎት Twenty Birr) for every television set he
ፍቃድ ክፍያ መክፈል ይኖርበታል፤ uses;
gA ፲፬ሺ፯፻ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14700

፪/ የቴሌቪዥን ባለቤት የሆነ ሰው ከአንድ በላይ 2/ If a person owns more than one television
ቴሌቪዥን ባለቤት ከሆነ እያንዳንዱን set, he shall have the duty to register each
ቴሌቪዥን ማስመዝገብ እና ለእያንዳንዱ television set and make the payment
ቴሌቪዥን በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) indicated in Sub-Article (1) of this
የተቀመጠውን ክፍያ የመፈፀም ግዴታ Article;
አለበት፤
፫/ የቴሌቪዥኑ አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት 3/ If a television set is used for a residential
በሆነ ጊዜ በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) house, the payment indicated in Sub-
ያለው ክፍያ አፈፃጸም በየወሩ በማስላት Article (1) of this Article shall be collected
ወይም በዓመት አንድ ጊዜ በኢትዮጵያ through the Ethiopian Electric Utility by
የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል calculating it every month or once in a
እንዲሰበሰብ ይደረጋል፤ year;

፬/ የቴሌቪዥኑ አገልግሎት ለሆቴሎች፣ የእንግዳ 4/ If the television set is used for hotels, guest
ማረፊያዎች እና ሌሎች የመዝናኛ houses and other entertainment purposes,
አገልግሎቶች የሚውል በሆነ ጊዜ ድርጅቶቹ the concerned enterprises shall pay annual
ዓመታዊ የቴሌቪዥን ባለቤትነት እና television ownership and service license
አገልግሎት ፍቃድ ክፍያቸውን በአንድ ጊዜ fee at once and their business licenses shall
መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ዓመታዊ not be renewed unless they produce a
የቴሌቪዥን የአገልግሎት ክፍያ payment receipt to the effect that they have
ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው የሚገልጽ discharged this duty;

የከፈሉበትን የክፍያ ደረሰኝ ካላቀረቡ


የንግድ ፍቃድ እድሳት አይደረግላቸውም፤

፭/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) 5/ The amount of television ownership and


የተቀመጠውን የቴሌቪዥን ባለቤትነት እና service license fee indicated in Sub-Article
አገልግሎት ፍቃድ ክፍያ መጠን እንደ (1) of this Article may be amended by the
ኢኮኖሚው ሁኔታ እየታየ ቦርዱ Directives to be issued by the Board taking
በሚያወጣው መመሪያ ሊሻሻል ይችላል፡፡ into account prevailing economic
considerations.
gA ፲፬ሺ፯፻፩ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14701

፲፱. ምርመራ የማድረግ ሥልጣን እና የሕግ 19. Power to Conduct Inspection and Legal
ተጠያቂነት Accountability
፩/ ቴሌቪዥን እንዲመዘግብ እና የቴሌቪዥን 1/ Any employee who is authorized to
መዝገብ መያዙን እንዲመረምር register television set and examine if
በኮርፖሬሽኑ ሥልጣን የተሰጠው ሠራተኛ television set register is kept shall have

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ the right to ascertain, at any time during

ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት ስለግለሰብ ሰብዓዊ working hours by holding evidence of

መብቶች የተጠቀሱ ድንጋጌዎችን በማክበር his authorization by the Corporation, the

እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የፍርድ ቤት existence of television set with any

ፍቃድ በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት


television set trader or manufacturer and
in any house of television set owner by
ከኮርፖሬሽኑ የተሰጠውን ሥልጣን
complying with the human rights
የሚያሳይ ማስረጃ በመያዝ በማንኛውም
provisions of the Constitution of the
የቴሌቪዥን ነጋዴ ወይም አምራች
Federal Democratic Republic of Ethiopia
እንዲሁም የቴሌቪዥን ባለቤት ቤት
and, when necessary, by securing court
ቴሌቪዥን መኖሩን የማረጋገጥ መብት
warrant.
አለው፡፡

፪/ ቴሌቪዥን እንዲመዘግብ እና የቴሌቪዥን 2/ In relation to the tasks of an employee

መዝገብ መያዙን እንዲመረምር who is authorized by the Corporation to

በኮርፖሬሽኑ ሥልጣን የተሰጠው ሠራተኛ


register television set and examine if
television set register is kept in
በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) መሠረት
accordance with Sub-Article (1) of this
በሚያደርገው አንቅስቃሴ፡-
Article:

ሀ) ነጋዴው ወይም የቴሌቪዥን አምራቹ a) Television set trader or manufacturer


በዚህ አዋጅ መሰረት የሚጠበቅበትን shall have the duty to cooperate with

የቴሌቪዥን መዝገብ መያዝ the employee in his effort to ascertain

አለመያዙን ለመመርመር በሚያደርገው whether or not the expected television

እንቅስቃሴ የመተባበር ግዴታ set register is kept;

አለበት፤
ለ) ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለቤት b) Any television set owner shall have the
የሚጠቀምበትን ቴሌቪዥን duty to cooperate when the employee
ማስመዝገቡን ወይም አለማስመዝገቡን makes house to house movement to

ለማጣራት ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ examine whether or not the television

በሚያደርገው እንቅስቃሴ የመተባበር set the owner uses is registered;

ግዴታ አለበት፤
gA ፲፬ሺ፯፻፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14702

፫/ የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲፰ በመተላለፍ 3/ Any television set owner who fails to
ቴሌቪዥኑን ያላስመዘገበ ወይም register his television set or is not willing
የቴሌቪዥን ባለቤትነት እና አገልግሎት to pay television set ownership and
ፍቃድ ክፍያ ለመክፈል ፍቃደኛ ያልሆነ service license fee in violation of Article
የቴሌቪዥን ባለቤት ቴሌቪዥኑን 18 of this Proclamation shall have civil

ባለማስመዝገቡ እና የፍቃድ ክፍያ liability for failing to register his

ባለመፈጸሙ የፍትሐብሔር ተጠያቂነት television set and for not paying the fee;

ይኖርበታል፤

4/ Unless contrary evidence is produced, the


፬/ የቴሌቪዥን ባለቤቱ ሌላ ተቃራኒ ማስረጃ
minimum civil liability of a television set
ካላቀረበ በስተቀር ቴሌቪዥኑን
owner for not registering his television set
ባለማስመዝገቡ እና የቴሌቪዥን ባለቤትነት
and not paying television set ownership
እና አገልግሎት ፍቃድ ክፍያ ባለመፈጸሙ
and license fee shall be calculated
ምክንያት የሚኖርበት ዝቅተኛው የፍትሐ
retroactively by taking into account the
ብሔር ተጠያቂነት ቴሌቪዥን እንዳለው
time from which it is known that he
ከታወቀበት ጊዜ አንስቶ ወደኋላ የሚቆጠር
owned a television set and it shall be:
ሆኖ፡-
ሀ) የቴሌቪዥኑ አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት a) 600 Birr (Six Hundred Birr) per
ከሆነ በአንድ ቴሌቪዥን የአምስት television set for five years if the
ዓመት ማለትም ከብር ፮፻ (ስድስት television service is used for
መቶ ብር) እንዲከፍል ይገደዳል፤ residential house;
ለ) የቴሌቪዥኑ አገልግሎት ለሆቴል፣
b) 840 Birr (Eight Hundred Forty Birr)
ለፔኒሲዮን፣ ለእንግዳ ማረፊያዎች፣
per television set for seven years if the
ለካፌዎች፣ ለመዝናኛ ድርጅቶች
television service is used for hotels,
ወይም ተመሳሳይ አገልግሎቶች
pensions, guest houses, cafeterias,
ለሚሰጡ ድርጅቶች ከሆነ በአንድ recreational centres, or other
ቴሌቪዥን የሰባት ዓመት ማለትም enterprises rendering similar services.
ብር ፰፻፵ (ስምንት መቶ አርባ ብር)
እንዲከፍል ይገደዳል፡፡

፳. ቅጣት 20. Penalty

፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፱ ንዑስ-አንቀጽ ፪ (ሀ)


1/ Failure to give evidence requested in
written form by the employee who is
እና (ለ) የተጠቀሱትን ተግባራት ለመፈጸም
authorized by the Corporation to perform
የሚንቀሳቀስ በኮርፖሬሽኑ ሥልጣን የተሰጠው
the tasks stated under Article 19(2) (a)
ሠራተኛ የሚጠይቀውን ማስረጃ እንዲሰጥ
and (b) of this Proclamation shall be
በጽሑፍ ተጠይቆ አለመስጠት ከአንድ ወር
gA ፲፬ሺ፯፻፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14703

እስከ ስድስት ወር በሚደርስ ቀላል እስራት punishable with simple imprisonment of


ወይም ከብር ፭፻ /አምስት መቶ ብር/ እስከ one month up to six months or with fine
ብር ፭ሺ /አምስት ሺህ ብር/ በሚደርስ from Five Hundred Birr (500 Birr) to Five
የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፤ Thousand Birr (5,000 Birr);

፪/ የዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) ቅጣት 2/ The punishment stipulated in Sub-Article

ተግባራዊ የሚሆነው የድርጊቱን መፈጸም (1) of this Article shall be applicable in

በሚመለከት ኮርፖሬሽኑ በሚያቀርበው accordance with the decision given by the

የከሳሽነት አቤቱታ መነሻነት ጉዳዩ


concerned justice organ after
investigating the matter based on the
በሚመለከተው የፍትሕ አካል ተጣርቶ
complaint lodged by the Corporation
በሚወሰን ውሳኔ መሠረት ይሆናል፡፡
about the commission of the acts.

፳፩. ስለፈቃድ መታደስ 21. License Renewal

1/ Licenses granted to television set owners


፩/ በዚህ አዋጅ መሠረት ለቴሌቪዥን
in accordance with this Proclamation
ባለንብረቶች የተሰጠው ፍቃድ በየአምስት
shall be renewed every five years;
ዓመቱ የሚታደስ ይሆናል፤

፪/ ማንኛውም የቴሌቪዥን ባለንብረት 2/ Any television set owner shall report to

ቴሌቪዥኑ በመበላሸቱ ወይም በመጥፋቱ the Corporation for the cancellation of his

ወይም በሌላ በማንኛውም ምክንያት television license if his television set is

ቴሌቪዥኑ ሥራ ላይ ሊውል የማይችል


not working and cannot be used due
malfunction or loss or any other reason;
በመሆኑ ምክንያት ሥራውን ያቆመ
እንደሆነ የቴሌቪዥኑ ባለቤት የተሰጠው
የቴሌቪዥን ፍቃድ እንዲሰረዝ ለኮርፖሬሽኑ
ማመልከት ይኖርበታል፤

3/ The Corporation shall examine the report it


፫/ ኮርፖሬሽኑ በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፪)
receives in accordance with Sub-Article
መሠረት ቴሌቪዥን ስለመበላሸቱ ሪፖርት
(2) of the Article about the
በደረሰው በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ጉዳዩን
malfunctioning of a television set and
አጣርቶ ውሳኔ ይሰጣል፤
give decision in three months from the
time of the report;
gA ፲፬ሺ፯፻፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14704

፬/ የቴሌቪዥን ባለቤት ቴሌቪዥኑ ስለመበላሸቱ 4/ The owner of a television set shall be


ሪፖርት ካቀረበበት ጊዜ አንስቶ በጉዳዩ ላይ exempted from payment from the time he
ውሳኔ እስኪሰጥ ጊዜ ድረስ ከክፍያ ነፃ has reported about the malfunctioning of
ይሆናል፤ his television set and until a decision is
made on the matter;

፭/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፬) የተጠቀሰው 5/ Without prejudice to the provision of Sub-
እንደተጠበቀ ሆኖ ኮርፖሬሽኑ በዚህ አንቀፅ Article (4) of this Article, if the
ንዑስ-አንቀጽ (፫) መሠረት ባደረገው Corporation ascertains that the television
ማጣራት ቴሌቪዥኑ ስለመሥራቱ ካረጋገጠ set is operational in accordance with the
የቴሌቪዥኑ ባለቤት ሳይከፍል የቀረውን inspection it makes pursuant to Sub-Article
ውዝፍ ሒሳብ ለኮርፖሬሽኑ እንዲከፍል (3) of this Article, the television set owner
ይደረጋል፤ shall be required to pay arrears of payment
he did not pay to the Corporation;

፮/ ከላይ በንዑስ-አንቀጽ (፪) መሠረት 6/ Any owner whose television set has
ቴሌቪዥኑ ችግር ያጋጠመው የቴሌቪዥን encountered a problem shall pay annual
ባለቤት ችግሩን ለኮርፖሬሽኑ እስካላሳወቀ television service license fee as long as he
ጊዜ ድረስ ዓመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት has not reported the problem to the

ፍቃድ ክፍያውን እንዲከፍል ይገደዳል፡፡ Corporation in accordance with Sub-


Article (2) above.

፳፪. ከክፍያዎች ነፃ ስለማድረግ 22. Exemptions from Payments

1/ The employees of the Corporation and


፩/ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች እንዲሁም
employees who retired after serving the
በኮርፖሬሽኑ ሲያገለግሉ ቆይተው በጡረታ
Corporation shall be exempted from
የተገለሉ ግለሰቦች ለመኖሪያ ቤት
television ownership and service license
ለሚጠቀሙበት ቴሌቪዥን በዚህ አዋጅ
fee stipulated in this Proclamation for
መሠረት ከሚከፈል የቴሌቪዥን ባለቤትነት
television sets they use in residential
እና አገልግሎት ፍቃድ ክፍያ ነፃ
houses;
ተደርገዋል፤
gA ፲፬ሺ፯፻፭ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14705

፪/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) ከተጠቀሰው 2/ In addition to what is listed under Sub-
በተጨማሪ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ Article (1) of this Article, the Chief
አስፈፃሚ በኢንተርናሽናል ልምድ ወይም Executive of the Corporation may
ስምምነት መሠረት ወይም ለሕዝብ ጥቅም decide, based on International Custom or
ሲባል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ Agreement or for public interest, to

የቴሌቪዥን ባለቤቶች በዚህ አዋጅ exempt lower class people from

መሠርት ከሚከፈል የቴሌቪዥን television ownership and service license

ባለቤትነት እና አገልግሎት ፍቃድ ክፍያ fee stipulated in this Proclamation.

ነፃ እንዲሆኑ ሊወስን ይችላል፤ ዝርዝሩ Particulars shall be determined by

ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው መመሪያ Directive.

ይወሰናል፡፡ ‹

ክፍል አራት PART FOUR


ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች MISCELLANEOUS PROVISIONS

23. Conclusion of Cooperative Agreements


፳፫. ከሌሎች ተቋማት ጋር የትብብር ስምምነት
with Other Institutions
ስለመፈራረም

In order to make the implementation of Part


ለዚህ አዋጅ ክፍል ሦስት አፈፃፀም እንዲረዳ
Three of this Proclamation possible, the
ኮርፖሬሽኑ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣
Corporation shall sign cooperative
ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከፌደራል እና ከክልል
agreements with Ethiopian Electric Utility,
የንግድ ቢሮዎች እና ከሌሎች ከሚመለከታቸው
Ministry of Revenue, Federal and Regional
መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ አጋር
Trade Bureaus, and other pertinent
አካላት ጋር በጋራ ለመሥራት የትብብር
Governmental and Non-Governmental
ስምምነት ይፈራረማል፡፡
partners.

24. Power to Issue Regulations and


፳፬. ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን
Directives

፩/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ 1. The House of Peoples’ Representatives


may issue Regulations necessary to
ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ
implement this Proclamation;
ይችላል፤

፪/ ቦርዱ ይህን አዋጅ ወይም አዋጁን ተከትሎ 2. The Board may issue Directives
የሚወጣውን ደንብ ለማስፈፀም መመሪያዎችን necessary to implement this
ያወጣል፡፡ Proclamation or Regulation issued
thereunder.
gA ፲፬ሺ፯፻፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14706

፳፭. የተሻሩና ተፈፃሚነት የሌላቸው ሕጎች 25. Repealed and Inapplicable Laws

የሚከተሉት ሕጎች በዚህ አዋጅ ተሽረዋል፡- The following laws are hereby repealed by
this Proclamation:

፩/ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 1. Ethiopian Broadcasting Corporation


ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፰፻፶፰/፪ሺ፮ እና Establishment Proclamation No.858/2014
እሱን ለማስፈፀም የወጣው የኮርፖሬሽኑ and the Corporation’s Employees
ሠራተኞች አስተዳደር ደንብ ቁጥር ፭/፪ሺ፯ Administration Regulation No.5/2015,
እና እነሱን ተከትለው የወጡ and also Directives issued pursuant to
መመሪያዎች፤ እንዲሁም these laws; and

፪/ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎት 2. Ethiopian Radio and Television Service


ድርጅት አዋጅ ቁጥር ፲፭/፩ሺ፱፻፷፯ ዓ.ም Agency Proclamation No.15/1975 and
እና የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን Ethiopian Radio and Television Service
አገልግሎት ድርጅት ደንብ ቁጥር Agency Regulation No.20/1975.
፳/፩ሺ፱፻፷፯፤ በዚህ አዋጅ ተሸረዋል፡፡

፫/ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም አዋጅ 3. Any Proclamation or Regulation or


ወይም ደንብ ወይም መመሪያ Directives which is inconsistent with this
የኮርፖሬሽኑን ሥራ በሚመለከት Proclamation shall be inapplicable.
ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፡፡

፳፮. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ 26. Transitory Provisions


፩/ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፳፭ ንዑስ-አንቀጽ (፩) 1. Notwithstanding the provision of Sub-
የተደነገገው ቢኖርም የኢትዮጵያ Article (1) of Article 25 of this

ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሠራተኞች Proclamation, the application of

አስተዳደር ደንብ ቁጥር ፭/፪ሺ፯ በሕዝብ Ethiopian Broadcasting Corporation

ተወካዮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ እስኪተካ Employees’ Administration Regulation

ጊዜ ድረስ ተፈፃሚነቱ ይቀጥላል፡፡ No. 5/2015 shall continue until it is


replaced by a Regulation to be issued by
the House of Peoples’ Representatives.
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ (፩) የተጠቀሰው 2. Notwithstanding the provisions of Sub-
ቢኖርም የኮርፖሬሽኑ የሠራተኞች አስተዳደር Article (1) of this Article, the provision of
ደንብ ቁጥር ፭/፪ሺ፯ አንቀጽ ፷፮ ንዑስ Sub-Article (1) (C) of Article 66 of the
አንቀጽ (፩) (ሐ) ድንጋጌ በዚህ አዋጅ Ethiopian Broadcasting Corporation
ተሸሯል፡፡ Employees Regulation No.5/2015 is
repealed by this Proclamation.
gA ፲፬ሺ፯፻፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፲፮ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No. 16, 27th February, 2023 ….page 14707

፳፮. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ 27. Effective Date

ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ This Proclamation shall be effective from
ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡ the date of its publication in the Federal
Negarit Gazzette.

አዲስ አበባ የካቲት ፳ ቀን ፪ሺ፲፭ ዓ.ም Done at Addis Ababa, On this 27th Day of
February, 2023.

ሣህለ ወርቅ ዘውዴ SAHLE-WORK ZEWDE

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ PRESIDENT OF THE FEDERAL


ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

You might also like