You are on page 1of 26

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሃያ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፵፬ 28th Year No. 44


አዲስ አበባ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ADDIS ABABA 15th July, 2022
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ Content
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፸፬/፪ሺ፲፬ Proclamation No. 1274/2022
የመንገድ ትራንስፖርት አዋጅ……….ገጽ ፲፬ሺ፫፻፸፩ Road Transport Proclamation…...Page 14371

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፸፬/፪ሺ፲፬ PROCLAMATION NO.1274/2022

የመንገድ ትራንስፖርት አዋጅ ROAD TRANSPORT PROCLAMATION

ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት WHEREAS, the economic and social


የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያበረክተውን development of the country requires that road
አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጎልበት ዘርፉ አስተማማኝ፤ transport service be regulated to make it more
የተቀናጀ፤ ዘመናዊና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ሆኖ reliable, integrated, modern and safe;
እንዲራመድ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣

የመንገድ ትራንስፖርት አስተዳደር የመንግሥትን WHEREAS, it is necessary to ensure that


የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ፖሊሲ በአግባቡ the administration of road transport properly
ለመተግበር፤ የመንገድ ትራስፖርት እስከታችኛው implements the government’s economic and

የሀገራችን መዋቅር ድረስ ጠንካራ አፈጻጸምና የቁጥጥር social affairs policies; ensure that there is a

ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግና የመንገድ ትራስፖርት strong enforcement and monitoring system in

ዘርፉን በቴክኖሎጂ ተደግፎ ተደራሽና አስተማማኝ the road transport up to the lower

እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ሥልጣንና ተግባር administrative level; and ensure that the road

ማበጀት በማስፈለጉ፣ transport sector is equipped with technologies


essential for its reliability and accessibility;

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ NOW, THERFORE, in accordance with


ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው Article 55(1) of the Constitution of the Federal
ታውጇል፡፡ Democratic Republic of Ethiopia, it is hereby
proclaimed as follows:

ÃNÇ êU nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1


Unit Price Negarit G. P.O.Box 80001
gA ፲፬ሺ፫፻፸፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14372

ክፍል አንድ PART ONE

ጠቅላላ ድንጋጌዎች GENERAL PROVISIONS

፩. አጭር ርዕስ 1. Short Title

ይህ አዋጅ “የመንገድ ትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር This Proclamation may be cited as the "Road
፩ሺ፪፻፸፬/፪ሺ፲፬” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ Transport Proclamation No. 1274/2022".

፪. ትርጓሜ 2. Definition

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ In this Proclamation, unless the context

በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡- requires otherwise:

፩/ “ሚኒስቴር” ወይም “ሚኒስትር” ማለት እንደ 1/ "Minster" or "Ministry" means the

ቅደም ተከተሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ


Minister or Ministry of Transport and
Logistics, respectively;
ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው፤

2/ "Enterprise" means a legal person


፪/ “ድርጅት” ማለት በንግድ የመንገድ
engaged in commercial road transport
ትራንስፖርት አገልግሎት ሥራ ላይ
service as established in accordance with
ለመሰማራት በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ
the Ethiopian Commercial Code and
መሠረት የተቋቋመ እና በዚህ አዋጅ መሠረት
registered in accordance with this
የተመዘገበ የሕግ ሰውነት ያለው አካል ነው፤
Proclamation.

፫/ “ተቋም“ ማለት በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማራ 3/ "Institution" means any governmental or

እና በዚህ አዋጅ፣ በአሽከርካሪ ብቃት non-governmental institution engaged in

ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ፤ በተሽከርካሪ መለያ፣


the transport sector; and regulated and
administered by this Proclamation, the
መመርመሪያና መመዝገቢያ አዋጅ እና
Driver’s Qualification Certification
በጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ዲመሬጅ
License Proclamation and the Vehicles
ክፍያ አዋጅ መሠረት ቁጥጥር እና ክትትል
Identification, Inspection and
የሚደረግበት መንግሥታዊ የሆነ ወይም
Registration Proclamation and Trucks
መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ነው፤
Demurrage Proclamtion.
‹‹‹‹‹‹

፬/ “የመንገድ ትራንስፖርት” ማለት ለዚህ አዋጅ 4/ “Road Transport” means for the

አፈጻጸም በተለያየ የትራንስፖርት ዘዴ purpose of this Proclamation the service

በመንገድ ላይ ሰዎችን ወይም ዕቃን ወይም of transporting persons or goods or

ሰዎችን እና ዕቃን ከአንድ ስፍራ ወደሌላ


persons and goods from point of
gA ፲፬ሺ፫፻፸፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14373

ስፍራ የማጓጓዝ አገልግሎት ሲሆን የባቡር departure to point of destination using


ትራንስፖርትን አይጨምርም፤ different modes of road transport in
exclusion of railway transport;

፭/ “የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት” ማለት 5/ "Road Transport Service" means the


በግለሰብ ወይም በድርጅት የሚከናወንና service of transporting of passengers or
መንገደኞችን ወይም ዕቃዎችን በክፍያ goods with remuneration by natural or
የማጓጓዝ የንግድ ሥራ ሆኖ እንደሚከተለው juridical persons; and is classified as

የግል ወይም የንግድ የመንገድ ትራንስፖርት either private or commercial road

ተብሎ ተለይቷል፡- transport as follows:

ሀ) “የግል ንግድ የመንገድ ትራንስፖርት” a) "Private Commercial Road

ማለት መንገደኞችን ወይም ዕቃዎችን Transport" means if the vehicle used

የሚያመላልሰው ተሽከርካሪ ንብረትነቱ


for carrying passengers or goods is
owned by the enterprise, and
የድርጅት ሆኖ፤

(1) የሚመላለሱት ዕቃዎች የዚያው (i) in the case of goods being


ድርጅት ንብረት የሆኑ ወይም transported, the goods are owned by
ለጥገና ወይም ለማደስ በአደራ the enterprise or have been

የተሰጡ የሆኑ እንደሆነና entrusted to it for the purpose of


maintenance or repair and the
ዕቃዎችን ማመላለስ ለድርጅቱ
transportation of said goods is
ዓይነተኛ የንግድ ሥራ አስፈላጊና
necessary and complementary to the
ማሟያ የሆነ እንደሆነ፤
principal commercial activity
carried out by the enterprise;

(2) የሚመላለሱት መንገደኞች የዚያው (ii) in the case of passengers being


ድርጅት ሠራተኞች ሆነው transported, the passengers are
የሚመላለሱትም ወደ ሥራ employees of the enterprise and
ቦታቸውና ከሥራ ቦታቸው የሆነ are being transported to or from
ወይም የድርጅቱን ሥራ their place of work or are
ለማከናወን የሆነ እንደሆነ ነው፤ engaged in the business of the
enterprise;
gA ፲፬ሺ፫፻፸፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14374

ለ) “የንግድ የመንገድ ትራንስፖርት” ማለት b) "General Commercial Road


ከከተማ ታክሲ በስተቀር የግል ተብሎ Transport" means except the city taxi all
ያልተመደበ ማንኛውም የንግድ commercial road transport not classified
የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት as private;
ነው፤ [[

6/ “Business Entity” means for the purpose


፮/ “የንግድ ማህበር” ማለት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም
of this Proclamation any person or
አግባብነት ባላቸው የኢትዮጵያ የንግድ ሕጎች
enterprise registered as trader in
መሠረት የንግድ ሥራ ለማከናወን ሥልጣን
accordance with the applicable
ባለው አካል የተመዘገበና የትራንስፖርት
commercials laws of Ethiopia and is
ንግድ ሥራ እንዲያከናውን የሚያስችለው
issued with a transport trade license from
የንግድ ፈቃድ የተሰጠው ግለሰብ ወይም
the competent authority;
ድርጅት ነው፤

7/ "Disciplinary Manual" means a


፯/ “የዲስፕሊን መመሪያ” ማለት በሚኒስቴሩ የወጣ
Directive issued by the Ministry
የዲስፕሊን እርምጃ አወሳሰንና አፈፃፀም
governing disciplinary action and its
መመሪያ ነው፤
execution;

፰/ “አውራ ጎዳና” ማለት የኢትዮጵያ መንገዶች


8/ "Highway" means a road administered
አስተዳደር የሚያስተዳድረውና አውራ ጎዳና
and designated as such by the Ethiopian
ብሎ የሚሰይመው መንገድ ነው፤
Roads Administration;

፱/ “የስምሪት ፕሮግራም” ማለት የሕዝብ


9/ "Trip Schedule" means yearly, monthly,
ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን የዓመት፤ የወር፤
weekly or daily program scheduled for
የሳምንት ወይም የቀን አገልግሎትና
the operation of public commercial road
እንቅስቃሴ የሚወስን የስምሪት መርሃ-ግብር transport vehicles;
ነው፤

፲/ “የመንገድ ተጠቃሚ” ማለት አሽከርካሪ፣ 10/“Road User” means a driver, bicycle


የብስክሌት አሽከርካሪ ወይም የመንገድ rider and a person using a road transport
ትራንስፖርት ተገልጋይ ሲሆን እግረኛን service; and includes pedestrian;
ይጨምራል፤
11/“Driver” means a natural person issued
፲፩/ “አሽከርካሪ” ማለት አግባብነት ባለው የመንገድ with a valid driving permit from a

ትራንስፖርት ሕግ መሠረት ተሸከርካሪን competent authority for operating a

እንዲያሽከረክር በሕግ ሥልጣን ከተሰጠው vehicle in accordance with the

አካል የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ appropriate road transport law;

የተሰጠው የተፈጥሮ ሰው ነው፤


፲፬ሺ፫፻፸፭
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14375

፲፪/ “የስምሪት መስመር“ ማለት በሚኒስቴሩ 12/ "Assigned Route" means the specific
የሚወሰን የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ departure and destination point to be
የስምሪት መነሻና መድረሻ ነው፤ determined by the Ministry where public
commercial road transport vehicles are
assigned to operate;

፲፫/ “መንገደኛ” ማለት በተሽከርካሪ ተሳፍሮ 13/"Passenger" means any person boarding
የሚሄድ ማንኛውም ሰው ሲሆን for travel in a vehicle, other than the
አሽከርካሪውን፤ ገንዘብ ተቀባዩንና driver, cashier or any other person
በተሽከርካሪው ላይ የተመደበ ማንኛውንም assigned to work on a vehicle;
ሌላ ሠራተኛን አይጨምርም፤

14/"Supervision" means ascertaining of the


፲፬/ “ቁጥጥር” ማለት በዚህ አዋጅ፤ በአዋጁ
proper implementation of Road
መሠረት የሚወጡ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣
Transport Proclamation; Regulations,
ደረጃዎች እና ውሳኔዎች በትክክል በሥራ
Directives, Standards and decisions
ላይ መዋላቸውን የማረጋገጥ ተግባር ነው፤
issued in accordance with this
Proclamation;

፲፭/ “ተቆጣጣሪ” ማለት የቁጥጥር ተግባሮችን 15/"Supervisor" means an employee


እንዲያከናውን በማናቸውም የኢትዮጵያ assigned by the Ministry to execute
ክፍል በሚኒስቴሩ የሚመደብ ሠራተኛ ነው፤ supervisory activities in any part of
Ethiopia.

፲፮/ “መንገድ“ ማለት በተለምዶ ተሸከርካሪዎች 16/"Road" means any road, street, highway
የሚጠቀሙበት ማንኛውም መንገድ፤ የከተማ or other travel route customarily used by
መንገድ፤ አውራ ጎዳና ወይም መተላለፊያ vehicles including bridges;
ሲሆን ድልድይንም ይጨምራል፤

፲፯/ “ተሽከርካሪ” ማለት ልዩ ወታደራዊ 17/"Vehicle" means any type of wheeled

ተሽከርካሪዎችን ሳይጨምር በመንገድ ላይ vehicle other than specialized military

በመንኮራኩር የሚሄድ ማንኛውም ዓይነት


vehicle; and includes wagons, cycles,
motorized vehicles, semi-trailers and
ተሽከርካሪ ሆኖ ሠረገላን፣ ሳይክልን፣
trailers;
ባለሞተር ተሽከርካሪን፣ ግማሽ ተሳቢን እና
ተሳቢን ያጠቃልላል፤
gA ፲፬ሺ፫፻፸፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14376

፲፰/ “ሠረገላ” ማለት ከብስክሌት፣ ከባለሞተር 18/"Wagon" means any vehicle other than a
ተሽከርካሪ፣ ከግማሽ ተሳቢ እና ከተሳቢ bicycle, a motorized vehicle, a semi-
በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪ ነው፤ trailer or a trailer;

፲፱/ “ብስክሌት” ማለት በሚያሽከረክረው ሰው 19/"Cycle" means a pedaled vehicle with


የጡንቻ ኃይል አማካኝነት እየተነዳ የሚሄድ two wheels in tandem as propelled by the
ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሲሆን muscular force of the person riding it;
ለመንቀሳቀስ ተጨማሪ ወይም አማራጭ and includes bicycles using electricity as
የኤሌክትሪክ ኃይልን የሚጠቀም ባለሁለት power source;
እግር ተሸከርካሪን ይጨምራል፤

፳/ “ባለሞተር ተሽከርካሪ” ማለት በመካኒካል 20/"Motor Vehicle" means a vehicle


ወይም በኤሌክትሪክ ኃይል እየተንቀሳቀሰ moving by mechanical or electrical
የሚሄድ ተሽከርካሪ ሆኖ የጭነት ማመላለሻ power; and is classified as truck,
ተሽከርካሪ፣ ባለሞተር ብስክሌት፣ የግል motorcycle, private motor car, public
አውቶሞቢል፣ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ፣ service vehicle, truck tractor and special
ጎታች መኪና እና ልዩ ተንቀሳቃሽ መሣሪያን mobile equipment;
ያጠቃልላል፤

፳፩/ “የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ” ማለት 21/"Truck" means a motor vehicle made or
ማንኛውንም ዓይነት ዕቃ እንዲያመላልስ adapted for the conveyance of goods or
ተብሎ የተሠራና ለዚሁ አገልግሎት used primarily for the conveyance of
እንዲውል የተደረገ ባለሞተር ተሽከርካሪ goods of any description; and includes a
ሲሆን ጎታች መኪናን ይጨምራል፤ truck tractor;

፳፪/ “ባለሞተር ብስክሌት” ማለት የጎን 22/"Motorcycle" means a motor vehicle


ተሽከርካሪውን ሳይጨምር ክብደቱ ከ፬፻ ኪሎ with less than 4 (four) wheels, the weight
ግራም የማይበልጥ ፬(ከአራት) መንኮራኩር of which, exclusive of any side-car
በታች ያለው ባለሞተር ተሽከርካሪ ነው፤ attached thereto, does not, when unladed,
exceed 400 kilograms;

፳፫/ “የግል ተሽከርካሪ” ማለት ከጭነት ማመላለሻ 23/"Private Vehicle" means a motor vehicle
ተሽከርካሪ፣ ከባለሞተር ብስክሌት፣ ከሕዝብ used for private service exclusive of a
ማመላለሻ ተሽከርካሪ፣ ከጎታች መኪና እና truck, a motorcycle, a public service
ከልዩ ተንቀሳቃሽ መሣሪያ የተለየ ለግል vehicle, a truck tractor and special
መጠቀሚያ የሚውል ባለሞተር ተሽከርካሪ mobile equipment;
ነው፤
gA ፲፬ሺ፫፻፸፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14377

፳፬/ “የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ” ማለት 24/"Public Transport Vehicle" means a


መንገደኞችን ለማመላለስ የሚያገለግል motor vehicle used to carry passengers;
ባለሞተር ተሽከርካሪ ሲሆን የንግድ and includes commercial motor car and
አውቶሞቢልና አውቶቡስን ያጠቃልላል፤ motor omnibus;

፳፭/ “የንግድ አውቶሞቢል” ማለት ከአስራ ሁለት 25/"Commercial Motor Car" means a
የማይበልጡ መንገደኞችን ለማመላለስ public transport service vehicle having
የሚችል የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት accommodation for not more than twelve
ማመላለሻ ተሽከርካሪ ነው፤ passengers;

፳፮/ “አውቶቡስ“ ማለት የታክሲ አገልግሎት 26/"Motor Omnibus" means a public


ከሚሰጡት በስተቀር ከአስራ ሁለት service vehicle other than vehicles

መንገደኞች በላይ ለማመላለስ የሚችል engaged in taxi service; and having a seat

የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ነው፤ accommodation for more than twelve


passengers;

፳፯/ “ጎታች መኪና” ማለት በተለይ ሌሎች 27/"Truck Tractor" means a motor vehicle
ተሽከርካሪዎችን ለመጎተት የሚያገለግል ሆኖ made or adapted for drawing other
የሌላ ጭነትን ሳይሆን የሚጎትተውን vehicles, and so constructed as to carry
ተሽከርካሪና በተጎታቹ ላይ ያለውን ጭነት no load other than part of the weight of
ክብደት ብቻ በከፊል ለመሸከም የተሠራ the vehicle and the load thereon;
ባለሞተር ተሽከርካሪ ነው፤

፳፰/ “ልዩ ተንቀሳቃሽ መሣሪያ” ማለት ሰውን 28/"Special Mobile Equipment" means any
motor vehicle designed, made, adapted or
ወይም ዕቃን በመንገድ ላይ እንዲያመላልስ
used for agricultural, horticultural,
ሆኖ የተሠራ ተሽከርካሪ ሳይሆን ለእርሻ፣
livestock, road construction, building,
ለአትክልት፣ ለከብት እርባታ፣ ለመንገድ፣
digging or any other similar purposes in
ለሕንፃ፣ ለቁፋሮ ወይም ለማንኛውም
exclusion of vehicles designed, adapted
ተመሳሳይ ሌላ ሥራ የተሠራ ወይም ለዚሁ
or used for the transportation of persons
ጉዳይ እንዲውል የተደረገ ባለሞተር
or goods;
ተሽከርካሪ ነው፤
፲፬ሺ፫፻፸፰
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14378

፳፱/ “ግማሽ ተሳቢ” ማለት ለመንገደኞች ወይም 29/"Semi-Trailer" means a vehicle


ለጭነት ማመላለሻ የሚያገለግልና በሌላ designed or adapted for carrying
ባለሞተር ተሽከርካሪ የሚሳብ ሆኖ passengers or goods; and so constructed
የተሽከርካሪውም የጭነቱም ክብደት በከፊል as to be drawn by a motor vehicle that
በባለሞተር ተሽከርካሪው ላይ እንዲያርፍ some part of its weight and the load
ወይም በሌላ ተሽከርካሪ እንዲሳብ ተደርጎ thereon rest upon or is carried by the
የተሠራ ተሽከርካሪ ነው፤ motor vehicle;

፴/ “ሙሉ ተሳቢ” ማለት ለራሱ የተለየ የሞተር 30/"Trailer" means a non-motorized vehicle
ኃይል የሌለው ሆኖ ጎታች በሆነ በሌላ designed to be pulled by and behind a
ባለሞተር ተሽከርካሪ ላይ ሊቀጠልና ሊጎተት motor vehicle; and so constructed that no

የሚችልና ክብደቱ ጎታች በሆነው ባለሞተር part of its weight rests upon the motor

ተሽከርካሪ ላይ እንደማያርፍ ሆኖ የተሠራ vehicle by which it is drawn, but shall

ተሽከርካሪ ነው፤ ሆኖም ከባለሞተር ብስክሌት not include a side car attached to a

ጋር ተያይዞ የሚሳበውን የጎን ተሽከርካሪ motorcycle;

አይጨምርም፤

፴፩/ "ሞተር አልባ የትራንስፖርት መገልገያ" 31/"Non-motorized Transport Equipment"

ማለት በመካኒካል ወይም በኤሌክትሪክ ኃይል means any non-motorized equipment


used for transport services except motor
እየተንቀሳቀሱ ከሚሄዱ ተሽከርካሪዎች
vehicles operated with mechanical or
በስተቀር ማናቸውም ሞተር አልባ የሆነ
electrical force;
የትራንስፖርት መገልገያ መሣሪያ ነው፤

፴፪/ "የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት


32/ “Public Transport Station” means
መናኸሪያ" ማለት የሕዝብ ትራንስፖርት
infrastructure developed and designated
አገልግሎት ተሽከርካሪዎች መንገደኞችን
for the boarding and disembarkation by
እንዲያሳፍሩ እና እንዲያደርሱ ወይም
public transport vehicles of passengers or
የመንገደኞች ዕቃዎችን እንዲጭኑበት/
loading/unloading of their cargos;
እንዲያራግፉበት ታስቦ የለማ መሠረተ-ልማት
ነው፤

፴፫/ “የአውቶቡስ ዴፖ” ማለት የህዝብ 33/ “Bus Depot” means a hub infrastructure
ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አውቶቡሶች designated for maintenance, car-wash,
ለጥገና፣ ለመታጠቢያ፣ ነዳጅ ለመቅዳት እና fueling and parking of Omnibuses;
ለማደር በጋራ እንዲጠቀሙበት ታስቦ የለማ
መሠረተ-ልማት ነው፤
፲፬ሺ፫፻፸፱
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14379

፴፬/ “የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት 34/ “Cargo Terminal” means a hub


መናኸሪያ” ማለት የጭነት ትራንስፖርት infrastructure developed and designated
አገልግሎት ሰጪዎች ተሽከርካሪዎች for loading, unloading by cargo trucks;
ጭነቶችን እንዲጭኑበት፣ እንዲያራግፉበት፣ packing and unpacking of cargos by
እንዲያሽጉበት እና እንዲበትኑበት ታስቦ cargo transport operators;
የለማ መሠረተ-ልማት ማለት ነው፤

፴፭/ “መጋዘን” ማለት የጭነት ትራንስፖርት 35/ “Warehouse” means an infrastructure


አገልግሎት መነሻ ወይም መድረሻ ሆኖ specifically designated for the purpose of
እንዲያገለግል ታስቦ የለማ መሠረተ-ልማት departure or destination of cargo transport
ነው፤ services;

፴፮/ "የሀገር ውስጥ የመንገድ ትራንስፖርት 36/ “National Road Transport Services”
አገልግሎት" ማለት ሁለት ወይም ከሁለት means a commercial transport service
በላይ ክልሎችን በሚያገናኝ መንገድ ላይ operated on roads connecting two or

የሚከናወን የንግድ መንገድ ትራንስፖርት more Regions;

አገልግሎት ነው፤

፴፯/ “ክልል” ማለት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ ፵፯ 37/ “Region” means any Regional States

መሠረት የተቋቋመ ማንኛውም ክልል ሲሆን established as per Article 47 of the

የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ Constitution of the Federal Democratic

አስተዳደሮችን ይጨምራል፤ Republic of Ethiopia; and includes


Addis Ababa and Dire Dawa City
Administrations;

፴፰/ “ዓለም-አቀፍ የመንገድ ትራንስፖርት 38/ "International Road Transport


አገልግሎት” ማለት የኢትዮጵያን ድንበር Service" means border crossing road
አቋርጦ የሚካሄድ ድንበር አቋራጭ የንግድ transport service conducted by crossing
መንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ነው፤ the Ethiopian border;

፴፱/ “ቢሮ” ማለት የትራንስፖርት ሕጎችን 39/ "Bureau" means a State Executive Organ
ለማስፈጸም ሥልጣን የተሰጠው የክልል in charge of enforcing road transport
አስፈፃሚ አካል ነው፤ laws;
፲፬ሺ፫፻፹
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14380

፵/ “ልዩ ሥልጠና” ማለት የጸና መደበኛ 40/ "Special Training" means training
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ላለው specially provided for holder of a valid
አሽከርካሪ ለልዩ የአሽከርካሪ ባለሙያነት regular driving permit as identified by
በሚኒስቴሩ ወይም በክልል ተለይቶ የሚሰጥ the Ministry or Region for acquiring a
ሥልጠና ነው፤ special driving license;

፵፩/ “መደበኛ ሥልጠና” ማለት የአሽከርካሪ 41/ "Regular Training" means training given
ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌለው ሰው for the first time to persons with no
ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም አስቀድሞ driving permit; or to persons intending to
የያዘውን የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ change their existing valid driving permit
ፈቃድ ምድብ ለመቀየር ወይም ለማሳደግ to a different category; or to persons

የሚሰጥ ሥልጠና ነው፤ upgrading their valid driving permit;

፵፪/ "ሰው" ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ 42/ “Person” means any natural or juridical

የሰውነት ችሎታ የተሰጠው ነው፤ person;

፵፫/ በዚህ አዋጅ ውስጥ በወንድ ጾታ የተገለጸው 43/ Any expression in the masculine gender

የሴት ጸታንም ያጠቃልላሉ፡፡


includes the feminine.

፫. የተፈፃሚነት ወሰን 3. Scope of Application

ይህ አዋጅ ሁለትና ከሁለት በላይ ክልሎችን This Proclamation shall be applicable to all
በሚያገናኙ ማናቸውም መንገዶች ላይ በሚከናወኑ transport services carried out on all roads
የመንገድ የትራንስፖርት አገልግሎቶች፤ linking two or more Regions; to any road
ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሚያገናኙ infrastructures and transport services carried
ማናቸውም መንገዶች ላይ በሚሰጡ የመንገድ out on such roads which link Ethiopia with
ትራንስፖርት አገልግሎቶችና መሠረተ-ልማቶች፤ neighboring Countries; and on all vehicles
እንዲሁም የኢትዮጵያን መንገዶች በሚገለገሉና using roads in Ethiopia, on all drivers and all
በሚንቀሳቀሱ ሁሉም ተሽከርካሪዎች፤ other road users.
አሽከርካሪዎች እና የመንገድ ተጠቃሚዎች ላይ
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
፲፬ሺ፫፻፹፩
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14381

፬. የአዋጁ ዓላማዎች
4. Objectives of the Proclamation
የአዋጁ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፤
The Proclamation has the following objectives:
፩/ አስተማማኝ፤ የተቀናጀ፤ ዘመናዊና ሁሉን አቀፍ
1/ to ensure the accessibility of an reliable,
የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት
integrated, modern and comprehensive
ተደራሽነትን ማረጋገጥ፤
road transport services;
[[[[

፪/ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ደኅንነትን 2/ to ensure the safety of the road transport

ማረጋገጥ፤
services;

3/ to ensure the road transport service is


፫/ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ከአካባቢ
free from environmental pollution and
ብክለት የጸዳና ለአካባቢ ተስማሚ መሆኑን
environment friendly;
ማረጋገጥ፤

4/ to ensure a strong regional transport


፬/ ቀጠናዊ የትራንስፖርት ትስስርን በማጠናከር
integration that enables an enhanced
ቀልጣፋ ዓለም ዓቀፍ የሎጂስቲክስ አፈጻጸም
logistics performance;
ውጤታማነትን ማጎልበት፤

5/ to ensure intermodal integration of the


፭/ ሀገር ዓቀፍ የትራንስፖርት አገልግሎት
national transport services.
የተሳለጠና ተመጋጋቢ እንዲሆን ማድረግ፤

PART TWO
ክፍል ሁለት

POWER AND DUTIES OF THE


ስለሚኒስቴሩ ሥልጣንና ተግባር
MINISTRY

፭. የሚኒስቴሩ ሥልጣንና ተግባር


5. Power and Duties of the Ministry

ሚኒስቴሩ በፌደራል አስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና


Without prejudice to the powers and duties
ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፷፫/፪ሺ፲፬
vested in it by The Definitions of Powers
የተሠጡት ሥልጣንና ተግባራት እንደተጠበቁ
and Duties of the Federal Executive
ሆነው በተለይ የመንገድ ትራንስፖርትን
Organs Proclamation No. 1263/2021, the
በተመለከተ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት Ministry shall, on road transports in
ይኖሩታል፡- particular, have the following powers and
duties:
gA ፲፬ሺ፫፻፹፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14382

፩/ የመንገድ ትራንስፖርትን የሚመለከቱ የፖሊሲ 1/ initiate policies and laws relating to


ሐሳቦችንና ሕጎችን ያመነጫል፣ ሲጸድቁም road transport; and implement the
ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈጻጸማቸውንም same upon approval; follow up and
ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ supervise their implementations;

፪/ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ደኅንነቱ 2/ undertake, cause to be undertaken,

የተረጋገጠ፣ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ፤ ፍትሃዊ and supervises activities that ensure

እና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ the safety, efficiency, reliability,

ተግባራትን ያከናውናል፤ እንዲከናወኑ fairness and accessibility of road


transport services;
ያደርጋል፤ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤

፫/ በአካል ጉዳተኝነት ምክንያት ልዩ ድጋፍ 3/ ensure the availability of safe and


ለሚያስፈልጋቸው የመንገድ ተጠቃሚዎች suitable road transport service for
ምቹ የሆነ የመንገድ የትራንስፖርት people with special needs due to
አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ አተገባበሩ disability; monitor and inspect its
ላይ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤ implementation;
4/ follow up the implementation at
፬/ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን የመንገድ national level of International,
ትራንስፖርትን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ፤ Continental or Regional Road
አህጉራዊና ቀጣናዊ ስምምነቶች ተግባራዊነት Transport related Agreements to which
በሀገር አቀፍ ደረጃ ይከታተላል፤ Ethiopia is a Party;
5/ administer, supervise and ensure
፭/ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ ክልሎችን
accessibility of road transport services
የሚያገናኙ አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚከናወኑ
carried out on high ways linking two
የትራንስፖርት አገልግሎቶችን
or more regions;
ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል፤ የትራንስፖርት
አገልግሎቶችን ተደራሽነት ያረጋግጣል፤
6/ issue Directive for the development of
፮/ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀናጀ የሕዝብ an integrated passenger and cargo
ማመላለሻና የዕቃ ማጓጓዣ የመንገድ transport system throughout Ethiopia;
ትራንስፖርት አገልግሎት ሥርዓት the transportation of passengers, goods
እንዲስፋፋ፤ መንገደኞች፣ ዕቃዎችና and postal services through
ፖስታዎች በንግድ የመንገድ ትራንስፖርት commercial road transport; and follow
ስለሚጓጓዙበት ሁኔታ የአሰራር መመሪያ up their implementation;
ያወጣል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
gA ፲፬ሺ፫፻፹፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14383

፯/ የንግድ የመንገድ ትራንስፖርት ሥራ ላይ 7/ enforce appropriate remedial measures


በተሰማሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የገበያ where individuals or enterprises
እጦት ሲያጋጥም ወይም ለተገልጋዩ engaged in commercial road transport
ህብረተሰብ የመንገድ የትራንስፖርት may face demand deficit or where the
አገልግሎት አቅርቦት እጥረት ሲከሰት public faces with supply side deficit of

ተገቢውን ክትትል በማድረግ የመፍትሄ road transport services; and, where

እርምጃዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፤ አስፈላጊ necessary, employ a market based

ሆኖ ሲገኝም በገበያ ሥርዓት መሠረት approach;

አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፤

፰/ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት 8/ Approve trip schedules submitted to it

ላይ የሚሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች by individuals or enterprises engaged

የሚያቀርቡለትን የስምሪት ፕሮግራም in public transport services; follow up

መርምሮ ያጸድቃል፤ የስምሪት ፕሮግራሙ and supervise the fairness and

ፍትሃዊነትና አተገባበር ላይ ክትትልና implementation of approved trip


schedules; develop schedules and
ቁጥጥር ያደርጋል፤ የስምሪት ፕሮግራም
implement where no such schedules
ካልቀረበለትም በራሱ አዘጋጅቶ ተግባራዊ
are submitted to it; implement
እንዲሆን ያደርጋል፤ ለዚሁ የወጣውን
disciplinary Directive;
የዲሲፕሊን መመሪያ ይተገብራል፤

፱/ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም ጊዜያዊ


9/ mobilize and assign commercial road
transport vehicles to operate in areas
የኢኮኖሚ ወይም የማህበራዊ ችግሮች ሲከሰቱ
and routes where their service are
ወይም ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ
demanded, where the occurrence of a
የንግድ የመንገድ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን
natural disaster or sever economic
በአስፈላጊው ቦታና መስመር በመደልደል
reasons or social crises or public
እንዲሰማሩ ያደርጋል፤ ስምሪቱን
interest so demand; follow up and
ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
supervises the implementation of
፲/ በሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የንግድ የመንገድ same;
ማመላለሻ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች 10/ issue Directives governing the

ወይም ድርጅቶች የሚያቋቁማቸውን የንግድ operation of the transport services of

ተቋሞች የትራንስፖርት አሠራር የሚመለከት individuals or enterprises engaged in

መመሪያ ያወጣል፤ ለእነዚህ ግለሰቦችና national and international commercial

ድርጅቶች የሙያ ብቃት ደረጃ እና road transport services; determine


levels and requirements for
የኦፐሬተርነት ብቃት መስፈርት ይወስናል፤
competence to be operators; issue,
የሙያ ብቃትና የኦፐሬተር ብቃት ማረጋገጫ
renew or cancel operators competence
ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ይሰርዛል፤
፲፬ሺ፫፻፹፬
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14384

ለድንበር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች ፈቃድ permit; issue cross-border permits;


ይሰጣል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ follow up and supervise its
ይቆጣጠራል፤ implementation;

፲፩/ በሀገር ውስጥ የንግድ የመንገድ ማመላለሻ 11/ undertake periodic review of tariff and
ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም may determine tariff cap on
ድርጅቶች የሚያስከፍሉትን ታሪፍ individuals or enterprises engaged in
በተመለከተ ለሚሰጡት አገልግሎት ማግኘት national commercial public transport
ስለሚገባቸው ጥቅም እና የተጠቃሚዎችን services having due considerations to
የመክፈል አቅም በሚመለከት በየጊዜው their services as well as the
ጥናት ያካሂዳል፤ የአገልግሎት ሰጪውንና overwhelming economic capability of
የአገልግሎት ፈላጊውን ጥቅም እና አቅም the consumer; and may determine

ግምት ውስጥ በማስገባት የታሪፍ መጠኑን tariff cap where the above

ሊወስን ይችላል፤ circumstances demand so;

፲፪/ በዓለም አቀፍ የንግድ የመንገድ 12/ study and implement mechanisms on
ትራንስፖርት አገልግሎት የሚስፋፋበትን the expansion of international
ሁኔታ እያጠና ተግባራዊ ያደርጋል፤ commercial road transport services;

አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ and follow up and supervise its


implementation;
፲፫/ በዓለም አቀፍ የመንገድ ትራፊክ የሚሰማሩ 13/ determine the registration system of
ተሸከርካሪዎችንና አሽከርካሪዎችን drivers and vehicles engaged in
አመዘጋገብ ሥርዓት ይወስናል፤ international road traffic; issue
የአሽከርካሪዎችንና የተሸከርካሪዎቹን registration certificate or special
የምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም ልዩ ፈቃድ permits to these drivers and vehicles;
ይሰጣል፤ ሌሎች የተሸከርካሪዎቹን decide on other vehicle identifications;
መለያዎች ይወስናል፤ ፈቃድ ይሰጣል፤ issue licenses; supervises and
ይቆጣጠራል፤ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ administers international road traffic
ዓለም አቀፍ የመንገድ ትራፊክን within the Ethiopian territory;
ያስተዳድራል፤

፲፬/ ከመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ 14/ provide arbitration services when so
ጋር በተያያዘ በማንኛውም አካል መካካል requested by adversaries engaged in

አለመግባባትና ክርክር ሲፈጠር እና commercial road transport services;

ባለጉዳዮቹ ሲጠይቁ በግልግል አይቶ and provide final administrative

ይወስናል፤ እንዲሁም በሁለት ወይም decisions on disputes involving two or

ከሁለት በላይ በሆኑ ክልሎች መካከል more regions and relating to road
፲፬ሺ፫፻፹፭
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14385

የትራንስፖርት አገልግሎትን አስመልክቶ transport services; and ensure its


አለመግባባት ቢፈጠር አለመግባባቱ ላይ implementation;
የመጨረሻ አስተዳደራዊ ውሳኔ ይሰጣል
አፈጻጸሙን ያረጋግጣል፤

15/ ensure the development of non-


፲፭/ በኢትዮጵያ ውስጥ የሞተር አልባ
motorized transport services in
ትራንስፖርት ከሀገራችን ጂኦግራፊያዊ
Ethiopia as may be suitable to the
አቀማመጥ እና አየር ንብረት ጋር
users and harmonious with the
በሚጣጣምና ለተጠቃሚው በሚያመች
geography and environment;
መልኩ እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ የማበረታቻ
implement incentive mechanisms;
የአሰራር ሥርዓቶችን ይዘረጋል፤
follow up and supervise its
አተገባበራቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ implementation;

፲፮/ መንገዶችን የሚጠቀሙ ባለሞተር 16/ determine the weight and dimension,
ተሽከርካሪዎች በሚሰጡት አገልግሎት number of passengers and payload of
ዓይነት ሊኖራቸው የሚገባውን ክብደትና motor vehicles depending on the
መጠን እንዲሁም የተሳፋሪን ብዛትና transport services they are purposed
የጭነት ክብደት ይወስናል፤ for;

፲፯/ ከውጭ ሀገር የሚመጡትን፤ በሀገር ውስጥ 17/ follow up and implement decisions
የሚሠሩትንና የሚገጣጠሙትን ወይም relating to vehicle age limit on
በከፊል የሚሠሩትን ወይም በሥራ ላይ imported, locally manufactured,
የተሰማሩ ማናቸውም ዓይነት ባለሞተር assembled or semi-assembled motor
ተሽከርካሪዎች የዕድሜ ገደብ በማስወሰን vehicles or motor vehicles already in
ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ለዚሁም use; and issue technical specifications
መመዘኛ የሚያገለግል ዝርዝር መስፈርት thereof; undertake monitoring and
ያወጣል፤ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤ supervision;

፲፰/ የመንገድ ደህንነት ደረጃዎችን ያዘጋጃል፤ 18/ issue standards relating to road safety;
በእነዚህ ደረጃዎች መሠረት issue Directives for the registration
የተሽከርካሪዎችን አመዘጋገብና የቴክኒክ and inspection of vehicles; and
ምርመራ የሚመለከት መመሪያ ያወጣል monitor its proper enforcement;
ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
gA ፲፬ሺ፫፻፹፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14386

፲፱/ ማናቸውንም የተሽከርካሪ ጋራዥ የቴክኒክ 19/ issue Directives under which
ብቃት ለማረጋገጥ፣ የሥራ ፈቃድና ዕድሳት certification of technical competence,
አሰጣጥ እና ደረጃውን ለመወሰን operational license and levels of
የሚያስችል መመሪያ ያወጣል፤ የብቃት vehicle maintenance and overhaul
ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ garages may be determined, issue,

ይሰርዛል፤ renew, cancel certificate of


competence;
፳/ ተሽከርካሪዎች እንደገና ስለሚሠሩበት፣ 20/ determine through Directives the
ስለሚፈቱበት ወይም ይዘታቸውንና manufacturing, dismantling,
አገልግሎታቸውን ስለሚቀይሩበት ሁኔታ; refurbishment or changing the original
አገልግሎት የማይሰጡና ከጥቅም ውጭ የሆኑ purpose of motor vehicles; scraping or
ተሸከርካሪዎች ወይም በዕድሜ ገደብ disposing of motor vehicles either due
ምክንያት አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚደረጉ to damage or vehicle age limit; follow
ተሸከርካሪዎች ስለሚወገዱበት ሁኔታ up and supervise its implementation
መመሪያና የአሰራር ሥርዓት በማውጣት through guidelines developed for this
ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ purpose;

፳፩/ የንግድ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት 21/ monitor the movement of commercial

እንቅስቃሴን የሚመለከቱ መረጃዎችን road transport services through

በቴክኖሎጂ በተደገፈ አሠራር ይቆጣጠራል፣ technology based platforms;

መረጃ ያጠናቅራል ጥቅም ላይ እንዲውሉ consolidate data relating thereof and

ያደርጋል፤ employ the data for appropriate


purposes;
፳፪/ የባለሞተር ተሽከርካሪዎች ማቆሚያን፣ 22/ determines standards to motor vehicle
የሕዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያዎችን፣ parking areas, public transport
የአውቶቡሶች ዴፖን፣ የጭነት ተርሚናሎችን stations, cargo terminals, depots;
ደረጃዎች ይወስናል፣ አተገባበራቸውን ensure their observance; and where
ይከታተላል፣ እንደአስፈላጊነቱም እነዚህን appropriate it shall develop and
የትራንስፖርት መሠረተ-ልማቶች administer such infrastructures;
ያስፋፋል፤ ያስተዳድራል፤

፳፫/ የባለሞተር ተሽከርካሪዎችን የቴክኒክ 23/ determines, through Directives,


standards for vehicle inspection and
ምርመራ የሚያከናውኑ፤ የልዩ ማሽነሪ
drivers training institutions including
አሽከርካሪነትን ጨምሮ ልዩ ወይም መደበኛ
special or ordinary drivers permit
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ሥልጠና
drivers training institutions; issue,
የሚሰጡ ተቋማትን ደረጃ ይወስናል፤
renew or cancel certificate of
ለእነኚህና ለአሽከርካሪ አሠልጣኞች የብቃት
፲፬ሺ፫፻፹፯
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14387

ማረጋገጫ ፈቃድ ይሠጣል፤ ያድሳል፤ competence for them; inspect,


ይሰርዛል፤ የሚመለከታቸው አካላት supervise the enforcement of same by
የሚያከናውኑትን የብቃት ማረጋገጫና other concerned organs; follow up
የሥራ ፈቃድ አሰጣጥ ይመረምራል፤ their performance;
ይቆጣጠራል፤ አሰራራቸውን ይከታተላል፤

፳፬/ የተለያዩ ዓይነት ተሸከርካሪዎችን 24/ determine through Directives the

ለማሽከርከር የሚያስችሉ የአሽከርካሪ ብቃት different classes of driving permits, the

ማረጋገጫዎችን ደረጃ፤ ዲዛይን፤ ቀለም designs, colors and detailed contents;


and requirements for getting such
ዝርዝር ይዘታቸውን ይወስናል፤ የአሽከርካሪ
driving permits; and monitor and
ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለማግኘት
supervise their implementation;
የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ይወስናል፤
አፈጻጸማቸውን ይቆጣጠራል፤
25/ set standards through Directives and
፳፭/ በፌደራል ደረጃ ወይም በክልል ቢሮዎች
cause the manufacturing of plates for
በሚመዘገቡ ማናቸውም ዓይነት
all categories of motor vehicles to be
ተሽከርካሪዎች ላይ ለሚለጠፍ ሠሌዳ
registered either at the federal or
ዝርዝር መስፈርት ያወጣል፤ እንዲመረት
regional transport bureau; cause their
ያደርጋል፣ ሥርጭቱንና አጠቃቀሙን
production; follow up the distribution
ይከታተላል፣ አገልግሎታቸውን የጨረሱ
and proper usage; determines the
ሠሌዳዎች የሚወገዱበትን እና ባለቤታቸው situation to discard and dispose worn-
ጠፍቶ ብዙ ጊዜ የቆሙ ተሽከርካሪዎች out plates and vehicles abandoned
የሚሰበሰቡበትንና የሚወገዱበትን ሁኔታ with no claims; follow up and
ይወስናል፤ አፈጻጸማቸው ላይ ክትትልና supervise their implementation; issues
ቁጥጥር ያደርጋል፤ ሠሌዳ ለሌላቸው አዲስ a single trip pass for new vehicles
ተሸከርካሪዎች ለአንድ ጊዜ ጉዞ ብቻ having no plates;
የሚያገለግል መሸኛ ይሰጣል፤

፳፮/ ተግባርና ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመፈፀም 26/ assign supervisors on permanent or

እንዲቻለው ተቆጣጣሪዎችን በቋሚነትም ሆነ temporary basis in any region in

በጊዜያዊነት በማንኛውም የኢትዮጵያ ክልል Ethiopia for the proper execution of its

ውስጥ ሊመድብ ይችላል፤ duties and responsibilities;


27/ Cause legal measures to be taken
፳፯/ የመንገድ ትራንስፖርት ዘርፉንና የተጠቃሚውን against any body engaging in illegal
ህብረተሰብ ደኅንነት በሚጎዳ ወይም አደጋ ላይ acts that may harm the safety of the
በሚጥል በማንኛውም አካል ላይ ተገቢው ሕጋዊ
road transport sector and the public
እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
using it;
gA ፲፬ሺ፫፻፹፰ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14388

፳፰/ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎቶች 28/ identify and implement, in


በአካባቢና አየር ንብረት የሚኖራቸውን coordination with concerned organs,
ተፅዕኖ ለመቀነስ የሚያስችሉ ስልቶችን measures that mitigate the impact of
በመለየትና ከሌሎች አካላት ጋር road transport service on the
በመተባበር በሥራ ላይ ያውላል፤ environment and the climate; monitor

አተገባበራቸውን ይቆጣጠራል፤ its implimentation;

፳፱/ በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎች፤


29/ establish an advisory council
comprising of members represented
ድርጅቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው
from persons, enterprises engaged in
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ተጠቃሚ
the transport sector, the concerned
ህብረተሰብ የሚወከሉበት አማካሪ ጉባዔ
government organs and the service
ያቋቁማል፤
users;
፴/ የመንገድ ትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን 30/ organize information technology data
የመንገድ ትራንስፖርትን የሚመለከቱ ሀገር center for the collection, consolidation
አቀፍ መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ለማደራጀት and dissemination of data nationwide
እና ለማሰራጨት የሚያስችል relating to the road transport services;
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል and that enable to modernize the road
ያደራጃል፤ የመረጃ ሥርጭት ሥርዓትን transport services; put in place an
በመዘርጋት የሚመለከታቸው አካላት ጥቅም information distribution system and

ላይ እንዲያውሉት ያደርጋል፤ ensure that relevant stakeholders


utilize it;
፴፩/ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎትን 31/ in collaboration with the concerned
ለማቀላጠፍና ደህንነቱን ለመጠበቅ organs, issues standards of
በተሸከርካሪዎች ላይ የሚገጠሙ ወይም technologies and communications
በአሽከርካሪዎች የሚተገበሩ ቴክኖሎጂዎችና equipment that may be fixed to
የመገናኛ ቁሳቁሶችን ደረጃ ከሚመለከተው vehicles or operated by drivers for the
አካላት ጋር በመተባበር ይወስናል፣ ይህን efficient and safe road transport
አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት የብቃት service; and issue, renew or cancel
ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ certificate of competence for
ይሰርዛል፤ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤ institutons providing such services;
ይቆጣጠራል፤ follow up and supervise their
implementation;
gA ፲፬ሺ፫፻፹፱ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14389

፴፪/ ዓለም ዓቀፍ የማኔጅመንት መስፈርቶችን 32/ identify and publicize annual
ተጠቅሞ የትራንስፖርት ቢሮዎችን እና performance ratings of transport
የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት bureaus and road transport service
ሰጪዎችን የአፈጻጸም ደረጃ በየዓመቱ ይፋ providers based on international rating
ያደርጋል፤ standards;

፴፫/ በንግድ የመንገድ ማመላለሻ ሥራ ላይ 33/ conduct or cause to be conducted by


የሚሰማሩ ወይም ንብረትነታቸው organs to which such duty is
የዲፕሎማቲክ፤ የዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች፤ delegated, the registration and annual
ከአንድ ክልል በላይ የሚንቀሳቀሱ technical inspection to motor vehicles
የተራድኦ ድርጅቶች ወይም የፌደራል engaged in commercial road transport
መንግስት የሆኑ ባለሞተር ተሽከርካሪዎችን services or which are owned by

በራሱ ወይም ውክልና በሰጠው አካል diplomatic missions, international

መመዝገባቸውንና የቴክኒክ ምርመራ organizations, aid organizations

ማድረጋቸውን ይከታተላል፤ ቁጥጥር operating in more than one region, or

ያደርጋል፤ the Federal Government; follow up


and supervise the registration and
annual technical inspection thereof;

፴፬/ ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ የንግድ


[

34/ follow up and supervise that


የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት international and national commercial
መሥመሮች ላይ ፍትሃዊ የስምሪት road transport service routes are fairly
አገልግሎት እና አቅርቦት መኖሩን distributed and available;
ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤

35/ represent Ethiopia in the Tripartite


፴፭/ ኢትዮጵያ አባል በሆነችበት የሦስትዮሽ
Transport and Transit Facilitation
የትራንስፖርትና የትራንዚት ፋሲሊቴሽን
Program in which Ethiopia is a party;
ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ
execute activities in the Program that
ይሳተፋል፤ በፕሮግራሙ ውስጥ የተካተቱና
are duties of the Ministry; follow up
ሚኒስቴሩን የሚመለከቱ ተግባራትን
and supervise their national
ያከናውናል፤ በሀገር ዓቀፍ ደረጃም
implementation at a national level;
አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
36/ support and follow up the expansion of
፴፮/ የገጠርና የከተማ መንገዶችን በሚያስተሳስሩ
commercial road transport services on
መንገዶች ላይ የንግድ የመንገድ
roads linking urban and rural areas;
ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስፋፋ
ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
gA ፲፬ሺ፫፻፺ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14390

፴፯/ ለልዩ አገልግሎት ተብለው የተሰሩ ወይም 37/ develop detail technical manual and
የተሻሻሉ ተሸከርካሪዎችን የሚመለከት register vehicles that are designed or
ዝርዝር የቴክኒክ መስፈርት ያዘጋጃል፤ repurposed for special purposes;
ይመዘግባል፤ ተሽከርካሪዎቹ ለተሰሩበት monitor and supervise that such
ወይም ለተሻሻሉበት ልዩ አገልግሎት ብቻ vehicles are employed only for the

ስለማዋላቸው ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤ purpose they are designed or


repurposed;
፴፰/ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የማበረታቻ ድጋፍ 38/ identify, where necessary, individuals,
የሚያስፈልጋቸውን በዘርፉ የተሰማሩ enterprises and institutions engaged in
ግለሰቦች ድርጅቶችና ተቋማትን በመለየት the road transport service that deserve
ለሚመለከተው የመንግሥት አካል በማቅረብ special assistance or incentive and
ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤ submit to the government; and execute
when approved;
፴፱/ ታዳሽ ኃይልን የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች
39/ study and implement mechanisms
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚስፋፉበትን መንገድ
through which vehicles using
እያጠና ተግባራዊ ያደርጋል፤ ለታዳሽ
renewable energy could be more
ኃይም ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት accessible in Ethiopia, in collaboration
የሚሰጡ የመሠረተ-ልማት አገልግሎቶችን with concerned organs, ensure the
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት development of charging
እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ infrastructures;

፵/ በማንኛውም ዓይነት ኃይል የሚንቀሳቀሱ 40/ issue, renew or cancel competency


አዲስ ተሸከርካሪዎችን ለሚያመርቱ፤ ሙሉ license to new vehicle manufacturers,
ለሙሉ ለሚገጣጥሙና በከፊል manufacturers and assemblers of
ለሚገጣጥሙ አምራቾችና ገጣጣሚዎች፤ assembled and semi-assembled
አዲስ ተሸከርካሪ ወደ ሀገር ውስጥ vehicles; importers of new vehicles
ለሚያስመጡ አስመጪዎች የብቃት using any type of energy;
ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤
ይሰርዛል፤

41/ provide support to the industry of


፵፩/ በሀገራችን ውስጥ የባለሞተርና ሞተር አልባ
manufacturing and assembling of
ተሸከርካሪዎች ማምረቻና መገጣጠሚያ
motorized and non-motorized vehicles
ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ እገዛ ያደርጋል፤
in Ethiopia; coordinate the creation of
ለዚህ ኢንዱስትሪ መስፋፋት ምቹ
suitable investment environment for
ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ የሚመለከታቸውን
such industry in collaboration with
አካላት በማቀናጀት ያስተባብራል፤
gA ፲፬ሺ፫፻፺፩ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14391

ቴክኒካዊ ብቃታቸውን በሚመለከት concerned organs; undertakes


ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ monitoring and inspections regarding
their technical worthiness.

ክፍል ሦስት PART THREE

የንግድ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት COMMERCIAL ROAD TRANSPORT


SERVICE
፮. ንግድ ፈቃድ አስፈላጊ ስለመሆኑ
6. Business License Necessary

፩/ በንግድ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት 1/ Any person intending to engage in


ሥራ ላይ ለመሠማራት የሚፈልግ ማንኛውም commercial road transport services shall
ሰው በቅድሚያ በሕግ ሥልጣን ከተሰጠው first secure a valid transport business
አካል የትራንስፖርት ንግድ ፈቃድ ማግኘት license from a legally authorized organ;
አለበት፤

፪/ በንግድ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት 2/ The requirements to obtain operator’s

ለማከናወን ማንኛውም ሰው የኦፐሬተርነት


permit by any person for undertaking a
commercial road transport service shall
የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለማግኘት ማሟላት
be determined by a Directive to be
የሚገባው መስፈርት ሚኒስቴሩ በሚያወጣው
issued by the Ministry.
መመሪያ ይወሰናል፡፡

ክፍል አራት PART FOUR

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች MISCELLANEOUS PROVISIONS

፯. የመረጃ ማዕከል ስለማቋቋም 7. Establishment of Data Center

1/ The Ministry shall establish a data


፩/ ሚኒስቴሩ በዚህ አዋጅ የተሰጡትን ሥልጣንና
center to collect and compile the
ተግባራት የሚመለከቱ መረጃዎችን
necessary information as regards its
ለመሰብሰብና ለማጠናቀር የመረጃ ማዕከል
power and duties.
ያቋቁማል፤

፪/ የክልል ቢሮዎች፣ የፌዴራልና የክልል ፖሊስ 2/ The Regional Bureau, Federal and

አደረጃጀቶች፣ የንግድ የመንገድ ማመላለሻ State Police Commissions, individuals

ግለሰቦችና ድርጅቶች ሚኒስቴሩ በሚያወጣው or enterprises engaged in commercial

መመሪያ መሠረት ከመንገድ ትራንስፖርት road transport services shall have the

ጋር የተያያዘ አስፈላጊውን መረጃ በተዘረጋው duty to provide or transfer the


gA ፲፬ሺ፫፻፺፪ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14392

የቴክኖሎጂ መሠረተ-ልማት ለሚኒስቴሩ እና necessary information relating to road


ለክልሉ ማቅረብ ወይም ማስተላለፍ ግዴታ transport through the technology
አለባቸው፤ infrastructure established for this
purpose to the Ministry;
፫/ አስፈላጊውን መረጃ ለማስተላለፍ የሚረዳ 3/ The Ministry shall develop sample
የናሙና ቅፅ እና የቴክኖሎጅ መሠረተ format and technology infrastructure
ልማት ሚኒስቴሩ ያዘጋጃል፤ መረጃ necessary to provide or transfer of
የማስተላለፍ ግዴታ ላለባቸው አካላትም such information; and disseminate
ያሰራጫል፡፡ same to organs having the obligation
to transfer the information.
፰. ስለ ሥልጣን ውክልና
8. Delegation of Powers
፩/ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሚኒስቴሩ ከሥልጣንና 1/ The Ministry may, where necessary and
ተግባሩ በከፊል እንደ አግባቡ ለክልል as may be appropriate, delegate part of
የትራንስፖርት አስፈጻሚ አካላት እና ለሌሎች its powers and duties to Regional
መንግስታዊ አካላት በውክልና ሊሰጥ transport executive organs and other
ይችላል፡፡ government organs.

፪/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ-አንቀጽ (፩) መሠረት 2/ The organs referred to in Sub-Article


ውክልና የተሰጣቸው አካላት በውክልና (1) of this Article shall, in exercising the
የተቀበሉትን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ powers and duties delegated to them, be
ሲያውሉ ስለ መንገድ ትራንስፖርት የወጡ abide by and observe laws and
ሕጎችና ደረጃዎችን መከተልና ማክበር standards relating to road transport.
አለባቸው፡፡

9. Repealed, Cancelled and Effective Laws


፱. የተሻሩ፤ የተሰረዙና ፀንተው የሚቆዩ ሕጎች

1/ The Transport Proclamation


፩/ የትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፰/፲፱፻፺፯
No.468/2005 is hereby repealed by this
በዚህ አዋጅ ተሽሯል፡፡
Proclamation.

፪/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ (፩) ድንጋጌ 2/ Without prejudice to the provisions of


ቢኖርም በአዋጅ ቁጥር ፬፻፷፰/፲፱፻፺፯ Sub-Article (1) of this Article all
መሠረት ወጥተው ወይም ፀንተው የነበሩ Regulations and Directives issued based
ደንቦች እና መመሪያዎች ሁሉ ከዚህ አዋጅ on Proclamation No. 468/2005 shall, in
ድንጋጌዎች ጋር እስካልተቃረኑ ድረስ በዚህ so far as they are not inconsistent with
አዋጅ መሠረት እንደወጡ ተቆጥረው የፀኑ the provisions of this Proclamation, be
ይሆናሉ፡፡ deemed to have been issued under this
Proclamation and shall remain in force.
gA ፲፬ሺ፫፻፺፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14393

፫/ የተሸከርካሪ መለያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 3/ Article 15 and the Annex of Vehicle
፮፻፹፩/፪ሺ፪ አንቀጽ ፲፭ እና አባሪው በዚህ Identification and Registration
አዋጅ ተሰርዘዋል፤ Proclamation No. 681/2010 is cancelled
by this Proclamation;
፬/ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ 4/ Article 7, 12 and the Annex of Drivers’
ቁጥር ፩ሺ፸፬/፪ሺ፲ አንቀጽ ፯፤ ፲፪ እና Competence Certification Proclamation
አባሪው በዚህ አዋጅ ተሰርዘዋል፤ No. 1074/2019 is cancelled;
5/ Matters covered by Article 15 and the
፭/ በተሸከርካሪ መለያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር
Annex of Vehicle Identification and
፮፻፹፩/፪ሺ፪ አንቀጽ ፲፭ እና አባሪው፤
Registration Proclamation No. 681/2010
እንዲሁም በአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ
and Article 7, 12 and the Annex of
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፸፬/፪ሺ፲ አንቀጽ ፯፤ ፲፪ እና
Drivers’ Competence Certification
አባሪው ውስጥ ተደንግገው የነበሩትን ጉዳዮች
Proclamation No. 1074/2019 shall be
በሚመለከት ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ
governed by Directives to be issued by
የተቀበለቻቸውን ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች
the Ministry in accordance with the
መሰረት አድርጎ በሚያወጣው መመሪያ
international agreements ratified by
መሠረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፤ Ethiopia.

፮/ ይህን አዋጅ የሚቃረን ሌላ ማንኛውም አዋጅ፣ 6/ Any Proclamation, Regulation and

ደንብ እና መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሰራር Directive or practice inconsistent with

በዚህ አዋጅ ውስጥ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ the provisions of this Proclamation shall

ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ have no effect on matters stated herein.

10. Transfer of Rights and Obligations


፲. ስለመብትና ግዴታዎች መተላለፍ

፩/ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት 1/ The Addis Ababa Transport Bureau and

ባለስልጣንና የድሬዳዋ ከተማ የትራንስፖርት the Dire Dawa Administration


Transport bureau shall be established as
ጽህፈት ቤት ተጠሪነታቸው ለየከተማ
independent bureaus of their respective
መስተዳድሮቻቸው ሆኖ እራሳቸውን ችለው
city administrations through the
ሥልጣን ባለው አካል ይደራጃሉ፡፡
appropriate organ;

፪/ በትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፰/፲፱፻፺፯ 2/ The rights and obligations of the Addis

መሠረት ተቋቁመው የነበሩት የአዲስ አበባ Ababa and Dire Dawa Transport

እና የድሬዳዋ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ Branch office established under

ጽሕፈት ቤቶች መብቶችና ግዴታዎች በዚህ Proclamation No. 468/2005 are hereby

አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ (፩) መሠረት transferred to the respective transport

ለሚደራጁት የትራንስፖርት ተቋማት


bureaus to be established in accordance
gA ፲፬ሺ፫፻፺፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14394

ተላልፈዋል፡፡ with Sub-Article (1) of this Article.

፲፩. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ 11. Transitional Provisions

1/ Commercial Road Transport enterprises


፩/ በትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፰/፲፱፻፺፯
and individuals established or registered
መሠረት የተቋቋሙና የብቃት ማረጋገጫ
pursuant to Proclamation 468/2005 shall
ፈቃድ የተሰጣቸው የንግድ የመንገድ
be considered as being established by
ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎችና
this Proclamation and shall continue
ድርጅቶች በዚህ አዋጅ እንደተቋቋሙና
their activities.
የብቃት ማረጋገጫው እንደተሰጣቸው
ተቆጥረው ሥራቸውን ይቀጥላሉ፡፡

፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው 2/ Notwithstanding the provisions of Sub-
ድንጋጌ ቢኖርም በትራንስፖርት አዋጅ Article (1) of this Article, individuals
ቁጥር ፬፻፷፰/፲፱፻፺፯ መሠረት የተቋቋሙ and enterprises established as per
ግለሰቦችና ድርጅቶች ይህ አዋጅ በነጋሪት Proclamation No. 468/2005 shall be re-
ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በአንድ registered within one year from the
ዓመት ጊዜ ውስጥ በዚህ አዋጅ ሥልጣን coming into force of this Proclamation;
በተሰጠው አካል እንደገና መመዝገብ
አለባቸው፡፡

፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ (፪) መሠረት 3/ Persons or enterprises not re-registered

ያልተመዘገቡ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች in accordance with the provisions of

ተሰጥቶት የነበረው የኦፐሬተርነት ብቃት Sub-Article (2) of this Article shall be

ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰረዛል፤ ዝርዝሩ revoked their operator’s certificate;

ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፤ details shall be determined in the


Directive to be issued by the Ministry;

፬/ በትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፰/፲፱፻፺፯ 4/ Commercial Road Transport

መሠረት ተመዝግበው የነበሩ የትራንስፖርት Associations established pursuant to

ማህበራት ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ


Transport Proclamation No. 468/2005
shall be re-established as a business
ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ዘጠኝ ወራት
company in accordance with the
ውስጥ ወደ ንግድ ማህበርነት የመለወጥና
appropriate laws and secure their
አስፈላጊውን የኦፐሬተርነት የብቃት
operators permit with nine months from
ማረጋገጫ ሥልጣን ካለው አካል የመውሰድ
the coming into force of this
ግዴታ አለባቸው፡፡
Proclamation;
gA ፲፬ሺ፫፻፺፭ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14395

፭/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ (፬) ከተጠቀሰው 5/ After the lapse of the period provided
ጊዜ በኋላ ማንኛውም የትራንስፖርት ማህበር under Sub-Article (4) of this Article any
ምዝገባው እንደተሰረዘ ተቆጥሮ ምንም Commercial Road Transport
ዓይነት ሕጋዊ ሰውነት አይኖረውም፡፡ Association shall have considered
dissolved and shall have no legal
personality.
፮/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ (፬) መሠረት ወደ 6/ Commercial Road Transport
ንግድ ማህበርነት የሚለወጡ የቀድሞው Associations registered in the former
የትራንስፖርት ባለሥልጣኑ ዘንድ Authority and intending to re-establish
ተመዝግበው የነበሩ ማህበራት ያፈሩትን as a commercial entity as per Sub-
ንብረት በሕግ አግባብ ወደሚለወጡበት የንግድ Article (4) of this Article may transfer
ማህበር ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ they accumulated assets to the newly
reestablished commercial entity.
፯/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ (፮) የተደነገገው 7/ Without prejudice to the provisions of
ቢኖርም በዚህ አንቀጽ መሠረት ወደ ንግድ Sub-Article (6) of this Article, the
ማህበርነት ሳይለወጥ የችሮታ ጊዜው accumulated assets of an Association
ያለፈበት የትራንስፖርት ማህበር ያፈራው which failed to be reestablished as a
ንብረት ላይ አግባብነት ያለው የኢትዮጵያ commercial entity shall be treated in
የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌ ተፈጻሚ accordance with the relevant provisions
ይደረጋል፡፡ of the Ethiopian Civil Code.

፰/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ንዑስ-አንቀጽ (፭) ስር 8/ The provisions of Article 15 and the
የተደነገገው ተፈጻሚ እስከሚሆን ድረስ Annex of Vehicle Identification and

በተሸከርካሪ መለያና መመዝገቢያ አዋጅ Registration Proclamation No. 681/2010

ቁጥር ፮፻፹፩/፪ሺ፪ አንቀጽ ፲፭ እና አባሪው፤ and Article 7, 12 and the Annex of

እንዲሁም በአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ Drivers’ Competence Certification

ፈቃድ አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፸፬/፪ሺ፲ አንቀጽ ፯፤ Proclamation No. 1074/2019 shall


continue to be applicable until such time
፲፪ እና አባሪው ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፤
that Sub-Article (5) of Article 9 of this
Proclamation becomes effective.
gA ፲፬ሺ፫፻፺፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፵፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ›.M Federal Negarit Gazette No. 44, 15th July, 2022 ….page 14396

፲፪. ደንብ እና መመሪያ የማውጣት ስልጣን 12. Power to Issue Regulation and Directive

፩/ ይህን አዋጅ በአግባቡ ሥራ ላይ ለማዋል 1/ The Council of Ministers may issue


የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ሊያወጣ Regulation for the proper
ይችላል፡፡ implementation of this Proclamation.

፪/ ይህን አዋጅ እና አዋጁን መሠረት አድርገው 2/ The Ministry may issue Directive
የሚወጡ ደንቦችን በአግባቡ ሥራ ላይ necessarily for the proper
ለማዋል ሚኒስቴሩ መመሪያ ሊያወጣ implementation of this Proclamation
ይችላል፡፡ and Regulations issued pursuant to this
Proclamation.
፲፫. የመተባበር ግዴታ
13. Duty to Cooperate

ማንኛውም አካል ለዚህ አዋጅ እና አዋጁን


Any person shall have the duty to
መሠረት አድርገው ለሚወጡ ደንቦች እና
cooperate for the implementation of this
መመሪያዎች ተፈፃሚነት የመተባበር ግዴታ
Proclamation, Regulations and Directives
አለበት፡፡
issued pursuant to this Proclamation.

፲፬. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ


14. Effective Date

ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት


This Proclamation shall enter into force from
ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡
the date of its publication in the Negarit
Gazette.

አዲስ አበባ ሐምሌ ፰ ቀን ፪ሺ፲፬ ዓ.ም Done at Addis Ababa, On this 15th Day of
July, 2022.
ሣህለ ወርቅ ዘውዴ
SAHLE-WORK ZEWDE
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት PRESIDENT OF THE FEDERAL
DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

You might also like