You are on page 1of 7

Abrham Yohanes https://t.

me/ethiopianlegalbrief

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሀያ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፸፭ 26th Year No.75


አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺ፲፪ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ th
ADDIS ABABA August 18 , 2020
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ

ማውጫ Content
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፳፬/፪ሺ፲፪ Proclamation No. 1224/2020
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን Ethiopian Human Rights Commission Establishment

(l¥ššL)..………………………………………………ገፅ ፲፪ሺ፯፻፳፮ (Amendment) Proclamation Page ....…………………12726

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፳፬/፪ሺ፲፪ PROCLAMATION NO 1224/2020

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS COMMISSION
ESTABLISHMENT PROCLAMATION (AMENDMENT)
ለማሻሻል የወጣ አዋጅ
WHEREAS, it is necessary to strengthen the Ethiopian
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተቋቋመበትን
Human Rights Commission’s institutional and execution capacity
የሰብዓዊ መብቶችን ግንዛቤ የማስፋፋት፣ የማስጠበቅ እና የማስከበር
to enable the Commission to fulfill its mandates of promoting,
ሥራ በተገቢው መንገድ እንዲያከናውን ማስቻል እና የማስፈጸም
ensuring the respect of and protection of Human Rights in
አቅሙን ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
Ethiopia;
WHEREAS, it is also found necessary to make nomination
ለዚህም ይረዳ ዘንድ የኮሚሽነሮች አመራረጥ እና አሿሿም
and appointment process of Commissioners participatory and
አሳታፊና ግልጽ ማድረግና የኮሚሽኑን የመዋቅር፣ የሠራተኛ
transparent in addition to making improvements to provisions
ቅጥርና አስተዳደር እንዲሁም የበጀት ነፃነት ማረጋገጥን
related to the structure of the Commission, hiring and
የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ማሻሻልና የተቋሙን ተዓማኒነት፣
management of staff and the budgetary independence of the
ተቀባይነት እና ውጤታማነት ማጐልበት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
Commission in order to enhance public trust, acceptance and
effectiveness of the Commission ;
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- NOW, THEREFORE; in accordance with Article 55(1) and
መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) እና ፶፭(፲፬) መሠረት የሚከተለው 55(14) of the Constitution of the Federal Democratic Republic of
ማሻሻያ ታውጇል፡፡ Ethiopia it is hereby proclaimed as follows.
ÃNÇ êU
Unit Price nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1
Negarit G. P.O.Box 80001
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፯፻፳፯ https://t.me/ethiopianlegalbrief12727
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፸፭ ነሐሴ ፲፪ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M
th
Federal Negarit Gazette No.75, August 18 2020 … page
፩. አጭር ርዕስ 1. Short Title
ይህ አዋጅ “የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ This Proclamation may be cited as the “Ethiopian Human
(ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፳፬/፪ሺ፲፪” ተብሎ ሊጠቀስ
Rights Commission Establishment (Amendment)
ይችላል፡፡
Proclamation No.1224/2020.
፪. ማሻሻያ 2. Amendment
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር The Ethiopian Human Rights Commission Establishment
፪፻፲/፲፱፺፪ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፦
Proclamation No. 210/2000 is hereby amended as follows:

፩/ የአዋጁ አንቀጽ ፪(፩) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፪(፩)


1/ Article 2(1) is repealed and replaced as follows:
ተተክቷል፡፡
“(፩) ተሿሚ ማለት በአዋጁ መሠረት በምክር ቤቱ የሚሾም “ (1) Appointee means the Chief Commissioner for Human
የሰብዓዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነር Rights, the Deputy Chief Commissioner, Deputy
እና የሴቶችን እና ህፃናትን ጉዳይ የሚከታተል ምክትል Commissioners for Women and Children Affairs and
ኮሚሽነር እንዲሁም ሌሎች የልዩ ልዩ ሰብዓዊ መብቶች other Commissioner heading different thematic Human
ዘርፍ ኮሚሽነሮች ማለት ሲሆን የዘርፍ ኮሚሸነሮች፣ Rights areas appointed by the House in accordance with
የአካል ጉዳተኞች፣የሲቪልና ፖለቲካ ማህበራዊ፣ ባህላዊና the Proclamation. Thematic areas include disability
ኢኮኖሚ መብቶች ጉዳይን ይጨምራል፡፡” rights, civil and political rights and socio economic and
cultural rights.”
፪. የአዋጁ አንቀጽ ፮ ስር የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ 2. The following new Sub Articles 6(11) – 6(13) are added
፮(፲፩) – ፮(፲፫) ተጨምረው፤ የቀድሞው ንዑስ አንቀጽ under Article 6 of the Proclamation and the former
፮(፲፩) ንዑስ አንቀጽ ፮(፲፬) ሆኖ ተስተካክሏል፤ Article 6(11) is accordingly amended as Article 6(14);

“፮(፲፩) በምርጫ ወቅት የሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅን ክትትል “6(11) Monitor the Human Rights situation during
ማድረግ፤ election periods;

፮(፲፪) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 6(12) Without prejudice to the power vested on the
መርማሪ ቦርድ ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ State of Emergency Inquiry Board, monitor the
ስለሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታ ክትትል Human Rights situation during state of
ማድረግ፤ emergency;

፮(፲፫)በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ማናቸውንም ማረሚያ 6(13) Visit and monitor, without prior notice, any
ቤቶች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች ወይም በቁጥጥር ወይም correction centers or prisons, police detention
በእገታ ስር የሚገኙ ሰዎች ያሉበትን ስፍራ እንዲሁም centers or any place where people are held in
እንደ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣መጠለያ ጣቢያ፣ የገበያ custody or otherwise detained anywhere in the
ማዕከል የመሳሰሉ እና የሕዝባዊ አገልግሎት መስጫ country as well as any public service institution
ተቋማትን ያለ ቅድመ ማስታወቂያ መጐብኘት፡፡” such as schools, hospitals, shelter camps and
market centers.”
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፯፻፳፰ https://t.me/ethiopianlegalbrief12728
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፸፭ ነሐሴ ፲፪ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M
th
Federal Negarit Gazette No.75, August 18 2020 … page
፫. የአዋጁ አንቀጽ ፰(፪)(መ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ 3. Article 8(2) (d) is repealed and replaced as follows:
፰(፪) (መ) ተተክቷል፡፡

“፰(፪) (መ)ሌሎች ከአራት ያላነሱ የልዩ ልዩ ሰብዓዊ መብቶች “8(2) (d) Not less than four Commissioners heading human
ዘርፍ ጉዳዮችን የሚመሩ ኮሚሽነሮች” rights thematic areas”
፬.የአዋጁ አንቀጽ ፱ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፱ 4. Article 9 is repealed and replaced as follows:
ተተክቷል፡፡

“የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ሆኖ “The Commission shall have its Head Office in Addis Ababa
በኮሚሽነሮች ጉባዔ ውሳኔ አሁን ካሉት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች and it may have additional branch offices or centers at any
በተጨማሪ በማናቸውም ስፍራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም place as determined by the Council of Commissioners”.
እንደሁኔታው መለስተኛ የኮሚሽኑ ማዕከሎች ሊኖሩት ይችላል፡፡”

፭. የአዋጁ አንቀጽ ፲፩ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፲፩ 5. Article 11 is repealed and replaced as follows:
ተተክቷል፡፡ “11(1).The Nomination Committee shall have the
“፲፩(፩) የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡- following members:

ሀ) የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ…………………………….....ሰብሳቢ፤
a. The Speaker of the House …………….Chairperson;

ለ)የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት……………..ም/ሰብሳቢ፤


b. The President of the Federal Supreme Court….Deputy
Chairperson;
ሐ)በምክር ቤቱ መቀመጫ ካላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች c. One member of the House to be elected by the joint
መካከል በጋራ ስምምነት የሚመረጥ አንድ ሰው………አባል፤ agreement of opposition parties having seats in the
House………………………………………Member;
መ)ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት አንድ ሰው………አባል፤ d. One member of the National Electoral Board of
Ethiopia……………………………………...Member;
ሠ) ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋሟት ጉባዔ አንድ ሰው……አባል ፤ e. One member from the Ethiopian Inter-Religious
Council; ……………………………………Member;
ረ) ከፌደሬሽን ምክር ቤት አንድ ሰው…..…………………አባል፤
f. One member from House of Federation , and

ሰ).ከሲቪል ማህበራት አንድ ሰው………………………….አባል፤ g. One member from Civil Society Organizations.

፲፩(፪) የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ አባላት ገለልተኛነታቸውና 11(2) Nominating Committee shall have independent and

ብቃታቸው የተረጋገጠ፣ እንደ አግባብነቱ በአዋጁ አንቀጽ competent members who shall also fulfill the criteria,

፲፪ ስር የተዘረዘሩትን ለኮሚሽነርነት የሚያበቁ as appropriate, for appointment of Commissioner under


መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡ Article 12 of the Proclamation.

፲፩(፫) ኮሚቴው የራሱን መንገድ በመጠቀም እንዲሁም ግልጽና 11(3) The Nominating Committee shall follow a transparent
አሳታፊ አሰራር በመዘርጋት በሕዝብ ጥቆማ ከቀረቡ ሰዎች and participatory public nomination process as well as
ውስጥ፤ መስፈርቱን የሚያሟሉ በአብላጫ ድምፅ የተደገፉ use its own means to identify suitable candidates and
ዕጩዎችን ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡ የዕጩዎች ዝርዝር submit to parliament nominees it has selected by a
በተቻለ መጠን የልዩ ልዩ ሕብረተሰብ ክፍሎች እና የጾታ majority vote. To the extent possible, the list of
ስብጥርን ከግምት ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡” nominees should take into consideration gender diversity
and representation from different parts of the society.''
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፯፻፳፱ https://t.me/ethiopianlegalbrief12729
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፸፭ ነሐሴ ፲፪ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M
th
Federal Negarit Gazette No.75, August 18 2020 … page

፮. የአዋጁ አንቀጽ ፲፪(፯) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ 6. Article 12(7) of the Proclamation is repealed and replaced

፲፪(፯) ተተክቷል፡፡ as follows:

“፲፪(፯) የማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ”፡፡ “12(7) Is not a member of a political organization.”

፯. አንቀጽ ፲፰ ስለ ኮሚሽነሮች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅሞች እና


7. Article 18 Salary and other Benefits of Commissioners

ተጨማሪ የሙያ ሥራ መስራት የተከለከለ ስለመሆኑ and Other Professional Work shall be prohibited

“፲፰(፩) የዋና ኮሚሽነር፤ ምክትል ዋና ኮሚሽነር እና ሌሎች “18(1) The Chief Commissioner, Deputy Chief

ኮሚሽነሮች ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅሞችን Commissioner and other Commissioners shall be

በተመለከተ በመንግስት የከፍተኛ የመንግስት entitled to the benefits and privileges determined

ተሿሚዎች ደሞዝና ጥቅማጥቅም መሰረት in accordance with the law provide for the
ይፈፀማል፡፡ benefits of Government Higher officials.

፲፰(፪) ተሿሚው በስራ ዘመኑ በማናቸውም ክፍያን 18(2) An appointee shall not be allowed to engage in
በሚያስገኝ በሌላ የመንግስትም ሆነ የግል ቅጥር other gainful, public or private employment during
ስራ ላይ መሰማራት አይፈቀድለትም፡፡” his term of office. ”

8. Article 19(2) is amended to include the following new Sub


፰. የአዋጁ አንቀጽ ፲፱(፪) ስር የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጾች
Articles (k), (l), (m) and (n):
(ተ) ፣ (ቸ) ፣ (ነ) እና (ኘ) ተጨምረዋል፡፡

“(ተ) የኮሚሽኑን የውስጥ አደረጃጀት እና መዋቅር፣ በዘርፍ “ k) Determine the internal organizational structure of the

ኮሚሽነሮች መካከል ያለውን የሥራ ክፍፍልና Commission, assign the specific post of thematic
የዘርፍ ኮሚሽነሮችን የሥራ መደብ ይወስናል፤ Commissioner’s and decide on the division of roles and
responsibilities among them;
ቸ) የኮሚሽነሮች ጉባዔን ስብሰባ ይጠራል፣ ይመራል፡፡ l) Call and preside over the meetings of the Council of
Commissioners;

ነ) ዳይሬክተሮችንና ሌሎች የሥራ ክፍል ኃላፊዎችን m) Appoint department Directors and other Senior Officers
ይመድባል፣ ተግባርና ኃላፊነታቸውን የኮሚሽነሮች and determine their roles and responsibilities in
ጉባዔ በሚያወጣው ዝርዝር የሥራ መመሪያ accordance with the work Directives adopted by the
መሠረት ይወስናል፤ Council of Commissioners;

ኘ) የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ኃላፊዎችን እንዲሁም n) Appoint heads of branch offices and Human Rights

ከኮሚሽነሮች ጉባዔ ጋር በመመካከር ለኮሚሽኑ Special Rapporteurs accountable to the Commission in


ተጠሪ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ዘጋቢዎች consultation with the Council of Commissioners. The
ይመድባል፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በኮሚሽነሮች ጉባዔ particulars shall be determined by Directives to be
በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል፡፡” issued by the Council of Commissioners. ”
Abrham Yohanes https://t.me/ethiopianlegalbrief12730
gA ፲፪ሺ፯፻፴ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፸፭ ነሐሴ ፲፪ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M
th
Federal Negarit Gazette No.75, August 18 2020 … page

፱. የአዋጁ አንቀጽ ፳፩ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ርዕስ እና 9. Article 21 is repealed and replaced as follows with a

አንቀጽ ፳፩ ተተክቷል፡ new title:

“፳፩. የልዩ ልዩ ሰብዓዊ መብቶች ዘርፍ ኮሚሽነሮች ሥልጣን “21. Powers and Duties of Thematic Commissioners

እና ተግባር In addition to heading the thematic area of human rights


የዘርፍ ጉዳይ ኮሚሽነሮች በዋናው ኮሚሽነር አማካኝነት work they have been assigned to by the Chief
የሚመደቡበትን የስራ ዘርፍ በኃላፊነት ከመምራት Commissioner, the thematic Commissioner have the
በተጨማሪ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለባቸው፡፡ following duties and responsibilities:

ሀ) ከዋናው ኮሚሽነር ጋር በመመካከር የሥራ ዘርፉን a. Organize, oversee, and administer the activities in

ማደራጀትና ማስተዳደር፤ their respective thematic areas in consultation with


the Chief Commissioner;

ለ) የሥራ ዘርፉን ሠራተኞች መከታተልና መምራት፤ b. To lead and manage staff assigned to the thematic
area;
ሐ) የሚመሩትን ዘርፍ ወቅታዊና ዓመታዊ ክንዋኔ ሪፖርት c. Submit periodic and yearly activity and performance
ለዋና ኮሚሽነሩ ማቅረብ ፤ reports to the Chief Commissioner on their respective
መ) በዋና ኮሚሽነሩ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት thematic areas;
ማከናወን፡፡'' d. Carry out other activities as may be assigned by the
Chief Commissioner. ''
፲. የአዋጁ አንቀጽ ፳፭ ስር የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ፳፭(፬) 10. Article 25 is amended including a new sub Article 25(4)
ተጨምሯል፡፡ as follows:
“፳፭(፬) ማንኛውም ለኮሚሽኑ ጥቆማ ያቀረበ ወይም ምስክር “25(4) Any witness appearing before the Commission or a
ሆኖ የሚቀርብ ሰው እንደአግባብነቱ ስለወንጀል whistleblower is afforded the same rights and
ምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ በወጣው አዋጅ protection as provided under the ‘Protection of
ቁጥር ፮፻፺፱/፪ሺ፫ የተመለከተው አይነት ጥበቃ Witnesses and Whistleblowers of Criminal Offences
ወይም በፍርድ ቤት ለሚቀርብ ምስክር ያለው ዓይነት Proclamation No. 699/2010’ or as witnesses
መብት እና ጥበቃ ይደረግለታል፡፡” appearing before a court of law, as appropriate.”

፲፩. አዋጁ አንቀጽ ፴፩(፫) እስከ (፯) ያሉት ተሰርዘው በሚከተሉት 11. Articles 31(3) to (7) are repealed and replaced with new
አዲስ ንዑስ አንቀጽ ፴፩(፫) እስከ ፴፩(፰) ተተክተዋል፡፡ Sub Articles 31(3) to (8) as follows:

“፴፩(፫) የኮሚሽኑን የሰው ሀብት፣ የንብረትና የፋይናንስ “31(3) To issue Directives and adopt Rules of Procedures

አስተዳደር መመሪያዎች እንዲሁም የፌደራል ሲቪል and manuals on management of human resources,

ሰርቪስ መርሆዎችን መሰረት በማድረግ የሠራተኞች property and finance, as well as on administration

አስተዳደር መመሪያን ያፀድቃል፤ of staff of the Commission based on Federal Civil


Service principles ;

፴፩(፬) የኮሚሽኑን የሰብዓዊ መብቶች ሥራ ፖሊሲዎችና 31(4) To adopt policies and strategies relating to its
ስትራቴጂዎች ያፀድቃል፤ activities and the human rights mandates of the
Commission;
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፯፻፴፩ https://t.me/ethiopianlegalbrief12731
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፸፭ ነሐሴ ፲፪ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M
th
Federal Negarit Gazette No.75, August 18 2020 … page

፴፩(፭) የሠራተኞች የአስተዳደር ቅሬታዎች የሚጣራበትና 31(5) To adopt rules of procedures and Directives for

የሚወሰንበት ሥርዓትና መመሪያ ያፀድቃል፤ consideration and determination of staff administrative

በሠራተኞች የአስተዳደር ቅሬታዎች ላይ በይግባኝ ሰሚ complaints including appeal procedures and the
ደረጃ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ Council of Commissioners serving as the final
appellate tribunal for administrative complaints;
፴፩(፮) በዋና ኮሚሽነሩ አቅራቢነት የኮሚሽኑን የውስጥ ኦዲተር 31(6) To appoint an internal Auditor upon the
ይመድባል፤ recommendation of the Chief Commissioner;
፴፩(፯) የሠራተኞችን የሥነ ምግባር መመሪያ እና ጥቅማ 31(7) To adopt code of ethics for staff and approve their
ጥቅም ያፀድቃል፣ benefit packages;
፴፩(፰) የጉባዔው ውሳኔዎች በአባላት ድምፅ ብልጫ ይወሰናሉ፤ 31(8) The decision of the Council shall be made by majority
ሆኖም ድምፅ እኩል በእኩል የሚከፈል ከሆነ ዋና vote. On instances of a tie, however, the Chief
ኮሚሽነሩ የደገፈው ሀሳብ የጉባዔው ውሳኔ ይሆናል፡፡'' Commissioner shall have a casting vote. ''

፲፪. የአዋጁ አንቀጽ ፴፪ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፴፪ 12. Article 32 is repealed and replaced as follows:
ተተክቷል፡፡
“፴፪. በሠራተኞች አስተዳደር ጉዳይ ላይ የኮሚሽነሮች ጉባዔ “32 A staff member dissatisfied by the final decision of the

የሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠ በ፴ ቀናት ውስጥ Council of Commissioners on administrative


በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ሊታይ ይችላል፡፡” complaints may appeal to the Federal High Court
within 30 days from receipt of the decision.”

፲፫. የአዋጁ አንቀጽ ፴፮(፪) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ 13 Article 36(2) is repealed and replaced as follows and the
፴፮(፪) ተተክቷል፡፡ እንዲሁም የሚከተለው አዲስ ንዑስ following sub-Article 36(3) is added:
አንቀጽ ፴፮(፫) ተጨምሯል:-
“36(2) As per the annual budget of the Commission
“ ፴፮(፪) ገንዘብ ሚኒስቴር ምክር ቤቱ ለኮሚሽኑ ያፀደቀለትን
approved by the House and based on request from
ዓመታዊ በጀት ኮሚሸኑ የፋይናንስ አሰራርን
the Commission in accordance with the finance
ተከትሎ በሚያቀርበው ጥያቄ መሰረት በየሶስት ወሩ
Regulations, the Ministry of Finance shall deposit
የሚያስፈልጋቸውን በጀት በቅድሚያ ወደ ኮሚሽኑ
the 3 month quarterly budget in advance to the
የባንክ ሂሳብ ማስገባት አለበት፡፡
bank account of the Commission.
፴፮(፫) የመንግስት የፋይናንስ መርሆዎችን መሰረት 36(3) In accordance with internal financial rules and
በማድረግ በኮሚሽነሮች ጉባኤ በሚፀድቅ የውስጥ Directives to be adopted by the Council of
ደንብ ኮሚሽኑ በጀቱን የማስተዳደር ሙሉ ነፃነት Commissioners, the Commission has full
አለው፡፡” financial autonomy to administer its budget.”
Abrham Yohanes
፲፪ሺ፯፻፴፪ https://t.me/ethiopianlegalbrief12732
gA Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፸፭ ነሐሴ ፲፪ ቀN ፪ሺ፲፪ ›.M
th
Federal Negarit Gazette No.75, August 18 2020 … page
፫. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ 3. Effective Date
ይህ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ቀን This Proclamation shall enter into force on the day of its
አንስቶ የጸና ይሆናል፡፡ approval by the House of People’s Representatives.

አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺ፲፪ ዓ.ም. Done at Addis Ababa On this 18th day of August, 2020.

ሳህለወርቅ ዘውዴ SAHLEWORK ZEWDE

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ PRESIDENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC

REPUBLIC OF ETHIOPIA
ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት

You might also like