Professional Documents
Culture Documents
Beza Report Summary Final
Beza Report Summary Final
መግቢያ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተጣለበትን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው የተለያዩ የስራ
ክፍሎችን በማዋቀር ወደ ስራ የገባ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የስራ ክፍሎቹ የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ መሰረት
በማድረግ በዜጎች መካከል የተሳለጠ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ የሀገርን መልካም ገጽታ ግንባታ
አዎንታዊ በሆነ መልኩ መገንባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን በማድረግ ረገድ የማህበራዊ ሚዲያ ዳሰሳ፣ክትትልና ድጋፍ
ዴስክ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም አበረታች ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን
በባለፉት ሁለት ወራት ማለትም ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ያከናወናቸውን አበይት ተግባራት
እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ክፍል አንድ
በስራ ክፍሉ ዝግጅት ምዕራፍ ወቅት የተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት ተከነውነዋል ለአብነት ያህል የአምስት
ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ (2014-2018) ረቂቅ የሰነድ ዝግጅትን መገምገም፣ ማረምና ማሻሻያ ሀሳቦችን
መስጠት፤ የ 2015 በጀት ዓመት የዘርፉ ረቂቅ እቅድ እንዲዘጋጅ ተደርጎ የማሻሻያ ሃሳብ እንዲሰጥበት
ለሚመለከተው ሃላፊ መላክ፣ በእቅድ ዝግጅት ሂደቱም ላይ የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እና
ባለሙያዎች እንዲሳተፉና ሀሳባቸውን እንዲሰጡ ማድረግ፤ የዴስክ እቅድ ለፈጻሚዎች በማውረድ (ካስኬድ
በማድረግ) የግል እቅዶቻቸውን እንዲያዘጋጁ የክትትልና ድጋፍ ስራ ተከናውኗል፡፡
ክፍል ሁለት
ለሚነሱ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ መስጠትን አስመልክቶ በተለያዩ ጊዜያት ከህብረተሰቡ የተነሱ ቅሬታዎችን
መሰረት በማድረግ የማህበራዊ ሚዲያ ዳሰሳ ቅኝት በማድረግ እና ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የማህበራዊ
ሚዲያ ዳሰሳ አዝማማያ ትንተና በመስራት ለሚመለከተው የተቋሙ አመራር በጥራትና በወቅቱ መረጃዎች
እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡
ለዘርፉ የተመደበውን ሀብትና በጀት ውጤታማ በሆነ መንገድ ስራ ላይ ማዋል፣ ለዘርፉ የሚያፈልጉትን
ግብዓቶች መጠየቅና ማስፈጸም እንዲሁም ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ተጨማሪ የሀብትና የፋይናንስ ምንጭ
ማፈላለግ በሚል ታቅዶ ለስራ የሚያስፈልጉንን አጠቃላይ ግብአቶች ከማሟላት አኳያ ለግዢ ክፍል የግብአት
አቅርቦት እንዲሟላል ተጠይቋል ፡፡
ማከናወን በሚል ታቅዶ የጀግኖች አትሌቶችን ድል፣የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሃይል ማስጀመርና የውሃ
ሙስሊሞች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ያካሄዱትን የምክክር መድረክ ወዘተ በተሰኙ የመንግስት ኮሙኒኬሽን
በየጊዜው በሚወጡ አጀንዳዎች/ ሁነቶቹን አስመልክቶ አንዲሁም አገልግሎቱ በሚያወጣቸው
መግለጫዎችን መሰረት በማድረግ የተሰሩ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ቅኝቶችና የአዝማሚያ ትንተናዎች
ተጠቃሽ ናቸው ፡፡
በሌላም በኩል ህዝቡ የሚያነሳቸዉን ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዩች በማሰባሰብ፣ በማደረጀትና ተንትኖ ለመንግስት
በማቅረብ የሁለትዮሽ ተግባቦትን ማጠናከር በሚል ታቆዶ ከህዝብ መረጃ በመሰብሰብ፣ በመተንተንና
የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር የማህበራዊ ሚዲያ ዳሰሳ በማድረግ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ
በተጨማሪም የማህበራዊ ሚዲያው ሚዛናዊና ተገቢ መረጃ በመስጠት ለሠላምና ለሀገር እድገት የበኩሉን
ሚና አንዲጫወት በሚል ርዕስ የሠላም ሚ/ር በተዘጋጀ የጋራ ምክክር መድረክ ላይ ሀለት የዴስካችን
ባለሙያዎች አንዲሳተፉ አድርገናል፡፡ በዚህም በተቋማችንና በሠላም ሚ/ር መካከል መልካም ጅማሮን
እንዲፈጠር ማድረግ ላይም በየሳምንቱ ተቀርጸው በሚሰጡ ወቅታዊ ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ የማህበራዊ
መረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀምና ስርጭትን በዘመናዊ መንገድ ተደራሽ ማድረግ በሚል ታቅዶ በየጊዜው ከስራ
ክፍላችን የሚወጡ መረጃዎችን በአግባቡ አደራጅተን የመያዝ እና ለሚፈለገው ዓላማም ለማዋል
ኢቲቪ ዳጉ በተሰኝ ፕሮግራም የመንግስት ኮሙንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደ/ር ለገሰ ቱሉ በውቅታዊ
አገራዊ ጉዳዮች ዙርያ በቀጥታ ቆይታ ያደረጉበትን ዝግጅት ፣ ክብርት ሠላማዊት ካሳ ከ TALK TO OBN
ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ እንዲሁም ኢትዮጵያ ታመስግን በሚል ርዕሰ ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ
ባስተላለፉት መልዕክት ዙርያ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሰጡትን ማብራሪያ አሰመልክቶ
ሪፓርት ቀርቧል፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚዲያ ሞኒተሪነግ ስራዎችከሜይንስትሪሙ ሚዲያ በተደረገ ክትትል
የተወሰዱ መረጃዎቹ ናቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ስራዎች አስመልክቶ ምንም እንኳን የስራ ክፍላችን
አጠቃላይ ትኩረቱን የሚያደርገው ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቢሆንም ጉዳዩ ለዘርፉ እጅግ አንገብጋቢ
በመሆኑ እና በቶሎ ለዘርፉ ኃላፊዎች መቅረብ ስለነበረበት ቅዳሜ ፣እሁድ፣ ሌሊት ሳይባል ተሰርተው የቀረቡ
ስራዎች ናቸው ፡፡
ክፍል ሦስት
8. ማጠቃለያ
የማህበራዊ ሚዲያ ዳሰሳ ክትትልና ድጋፍ ዴስክ ባላፉት ሁለት ወራት ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በዚህ በጣት
በሚቆጠሩ ጥቂት ወራት የማይናቁ ስራዎችን መስራቱን ሪፓርቱ ያሳያል፡፡በ 2015 በጀት ዓመት ባለፈው
የነበሩንን ጥንካሬዎች በማጎልበት እና ድክመቶታችንን በማረም በሙሉ ተነሳሽነት እና በቁርጠኝነት እጅ
ለእጅ በመያያዝ ስራዎችን በጥራት ለመከወን እንጥራለን፡፡