You are on page 1of 6

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሃያ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ 25th Year No. 2


አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፱ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ADDIS ABABA 29th October 2018
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ
ማውጫ Content
ደንብ ቁጥር ፬፻፴፪/፪ሺ፲፩ ዓ.ም Regulation No. 432/2018
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች Ethiopian Diaspora Agency Establishment
ምክር ቤት ደንብ…………………..……..ገጽ ፲ሺ፭፻፷፪ Council of Ministers Regulation……Page
10562
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬፻፴፪/፪ሺ፲፩ Council of Ministers Regulation No. 432/2018

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲን ለማቋቋም Council of Ministers Regulation to Provide for the
Establishment of the Ethiopian DIASPora Agency
የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ This Regulation is issued by the Council of

ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና Ministers pursuant to Article 5 of the Definition of

ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፱፻፲፮/፪ሺ፰ Powers and Duties of the Executive Organs of the
Federal Democratic Republic of Ethiopia
(እንደተሻሻለ) አንቀጽ ፭ እንዲሁም በውጭ ግንኙነት
Proclamation No.916/2015(as amended) and Article
አገልግሎት አዋጅ ቁጥር ፯፻፺/፪ሺ፭ አንቀጽ ፶፮(፩)
56 (1) of the Foreign Relation Service Proclamation
መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል።
No. 790/2013.

፩/ አጭር ርዕስ 1. Short Title


This regulation may be cited as the “Ethiopian
ይህ ደንብ “የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ
Diaspora Agency Establishment Council of
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬፻፴፪/፪ሺ፲፩”
Ministers Regulation No. 432/2018”.
ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

፪. ትርጓሜ 2. Definition
In this Regulation, unless the context
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ
otherwise requires:
በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፦
1. “Ministry” or “Minister” means the
፩/ “ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር” ማለት እንደቅደም
Ministry or Minister of Foreign Affairs of
ተከተሉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ
the Federal Democratic Republic of
ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም
Ethiopia, respectively;
ሚኒስትር ነው፤
2. “Proclamation” means the Foreign Relation
፪/ “አዋጅ” ማለት የውጭ ግንኙነት አገልግሎት
Service Proclamation No. 790/2013;
አዋጅ ቁጥር ፯፻፺/፪ሺ፭ ነው፤

ÃNÇ êU nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1


Unit Price Negarit G. P.O.Box 80001
gA ፲ሺ፭፻፷፫ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፪ ጥቅምት ፲፱ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No. 2 29th October , 2018 …...page 10563

፫/ “የኢትዮጵያ ዳያስፖራ” ማለት ከኢትዮጵያ 3. Ethiopian Diaspora” means an Ethiopian


ውጭ በቋሚነት የሚኖር የኢትዮጵያ ዜግነት National or a foreign national of

ያለው ወይም የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ Ethiopian origin that permanently resides
abroad;
ዜጋ ነው፤
፬/ “ምክር ቤት” ማለት በዳያስፖራ እና ተያያዥ 4. “Council” means an entity established to
undertake Diaspora and related activities
ጉዳዮች ላይ በዚህ ደንብ የተሰጡትን ተግባራት
pursuant to this Regulation;
ለማከናወን የተቋቋመ አካል ነው፤
5. "Mission" means Ethiopia's diplomatic
፭/ “ሚሲዮን” ማለት በውጭ አገር የሚገኝ
mission, permanent mission, consular
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
office or trade office abroad;
ኤምባሲ፣ ቋሚ መልክተኛ ጽ/ቤት፣ ቆንስላ
ጄኔራል ጽ/ቤት ወይም የንግድ ጽ/ቤት ነው፤
፮/ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊ 6. “Regional State" means any State referred

ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯(፩) to in Article 47(1) of the Constitution of

የተመለከተው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ the Federal Democratic Republic of

ሪፐብሊክ አባል የሆነ ክልል ሲሆን፣ የአዲስ አበባ Ethiopia and includes the administrations

እና የድሬዳዋ የከተማ አስተዳደሮችን ያካትታል፡፡


of Addis Ababa and Dire Dawa ;

፯/ በአዋጁ አንቀጽ (፪) የተሰጡ ትርጓሜዎች ለዚህ 7. The definitions provided under article (2)

ደንብም ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፤ of the Proclamation shall also apply to


this regulation;
፰/ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም 8. Any expression in the masculine gender
ፆታ ያካትታል፡፡ includes the feminine.

፫. መቋቋም 3. Establishment
፩/ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ (ከዚህ በኋላ 1. The Ethiopian Diaspora Affairs Agency
“ኤጀንሲ” ተብሎ የሚጠራ) የሕግ ሰውነት ያለው (hereinafter referred to as “Agency”) is
የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤት ሆኖ በዚህ hereby established as an Autonomous

ደንብ ተቋቁሟል። Federal Government organ having its own


legal personality.
፪/ ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል፡፡ 2. The Agency shall be accountable to the
Ministry.
፬. ዋና መሥሪያ ቤት
4. Head Office
የኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ The Agency shall have its head office in Addis
እንደአስፈላጊነቱ በሌሎች የአገሪቱ ስፍራዎች Ababa and may have other branches elsewhere

ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል፡፡ in Ethiopia as may be necessary.

፭. ዓላማ
5. Objectives
የኤጀንሲው ዓላማ፡-
The objectives of the Agency include:
፩/ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ፖሊሲን ማስፈጸም፤እና
1. Implementing the Ethiopian Diaspora
Policy; and
gA ፲ሺ፭፻፷፬ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፪ ጥቅምት ፲፱ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No. 2 29th October , 2018 …...page 10564

፪/ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር 2. Protecting the rights and interests of


የኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች መብትና ጥቅም Ethiopians Diaspora in collaboration with
እንዲከበር ማድረግ ነው። relevant bodies.

፮. የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባራት 6. Powers and Duties of the Agency


ኤጀንሲው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት The Agency shall have powers and duties to;
ይኖሩታል፤
1. facilitate Diaspora affairs;
፩/ የዳያስፖራ ጉዳዮችን ያስተባብራል፣
፪/ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የምዝገባ እና የመረጃ 2. establish a system of registration and
አያያዝ ስርዓት ይዘረጋል፤ documentation of Ethiopian Diaspora;
፫/ በውጭ አገራት የተቋቋሙ እና አዲስ ለሚቋቋሙ 3. support the existing and future Ethiopian
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች Diaspora media outlets abroad.
ድጋፍ ያደርጋል፤
፬/ ከዳያስፖራው የሚገኙ የእውቀት እና የቴክኖሎጂ 4. establish a system to facilitate knowledge
ሽግግር እድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም and technology transfer opportunities to be
የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፤ accrued from the Ethiopian Diaspora;
፭/ የዳያስፖራ የገንዘብ እና የሃብት አስተዋጽኦ 5. establish and administer financial and other
አሰባሰብ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስተዳድራል፤ contribution collection systems;
፮/ በአገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በኢትዮጵያ 6. support events organized by the Ethiopian
ዳያስፖራ ለሚዘጋጁ መድረኮች እና ዝግጅቶች Diaspora at home and abroad;
ድጋፍ ያደርጋል፤
፯/ በውጭ አገራት የተመሰረቱ የኢትዮጵያ 7. support and facilitate institutional capacity
ዳያስፖራ ማኅበራት ወይም ድርጅቶች ሕጋዊ of Ethiopian Diaspora societies and

እውቅና የሚያገኙበትን እና ተቋማዊ አቅም organizations on their effort to acquire

የሚያጎለብቱበትን እንዲሁም በአገር ውስጥ ያሉ legal personality and support locally


organized Diaspora organizations to be
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበራት ሥራቸውን
fully functional ;
በአግባቡ እንዲያከናውኑ ድጋፍ ይሰጣል፤

፰/ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በአገር ውስጥ የበጐ 8. Coordinate and facilitates conditions for

ፈቃድ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ያስተባብራል፣ the Ethiopian Diaspora to engage in


voluntary activities in Ethiopia;
ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
9. provide the necessary support to entities
፱/ የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማስተባበር በፌደራል
working in Diaspora engagement at the
እና በክልሎች ለሚገኙ የዳያስፖራ ማስተባበሪያ
Federal and Regional level;
አደረጃጀቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
10. encourage and support Ethiopian Diaspora
፲/ የዳያስፖራ አባላት በአገራችን የኢንቨስትመንትና
to actively get involved in investment and
የእውቀት ሽግግር መስክ እንዲሰማሩ ያበረታታል፣
knowledge transfer , and follow up on its
ድጋፍ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
implementation;
፲፩/ በዳያስፖራ ጉዳዮች እና ሌሎች ተያያዥነት 11. prepare studies and policy
ባላቸው ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን ያከናውናል፣ recommendations on Diaspora and other
የፖሊሲ ሃሳቦችን ያቀርባል፤ related issues;
gA ፲ሺ፭፻፷፭ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፪ ጥቅምት ፲፱ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No. 2 29th October , 2018 …...page 10565

፲፪/ ተገቢነት ካላቸው የአገር ውስጥና የውጭ 12. create working mechanism with relevant
ተቋማት ጋር የስራ ግንኙነት ይፈጥራል፣ domestic and foreign institutions;

፲፫/ ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች 13. Undertake other activities necessary for the
accomplishment of its objectives.
ተግባራትን ያከናውናል።
፯. የኤጀንሲው አወቃቀር 7. Organization of the Agency
ኤጀንሲው፦ The Agency shall have:
፩/ አማካሪ ምክር ቤት፣ 1. Advisory Council;

፪/ በመንግሥት የሚሾሙ ዋና ዳይሬክተር እና 2. A Director General and Deputy Director

እንደአስፈላጊነቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፤ Generals to be appointed by the


Government;
፫/ አስፈላጊ ሰራተኞች ይኖሩታል። 3. The necessary staff.
፰. የአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት 8. Members of the Advisory Council
፩/ አማካሪ ምክር ቤቱ ሰብሳቢውን ጨምሮ 1. The members of the Council, including the

በመንግሥት ይሰየማሉ፣ ቁጥራቸውም እንደ chairperson, shall be appointed by the


Government, and their number shall be
አስፈላጊነቱ ይወሰናል።
determined as necessary.

፪/ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የአማካሪ ምክር 2. The Director General of the Agency shall
act as member and the secretary of the
ቤቱ ፀሐፊ እና አባል ይሆናል። Advisory council .
፱. የአማካሪ ምክር ቤቱ ሥልጣንና ተግባራት 9. Powers and Duties of the Advisory Council
The Advisory Council shall have powers and
አማካሪ ምክር ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣን እና
duties to:
ተግባራት ይኖሩታል፤
1. Provide strategic direction to implement
፩/ የኤጀንሲውን ዓላማ ለማስፈጸም የሚረዱ
the objectives of the Agency ;
ስትራተጂያዊ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፤
፪/ የኤጀንሲውን የሥራ ዕቅድ እና አፈጻጸም 2. Evaluate the Agency’s wok plans and

ይገመግማል፤ implementations;
3. Hold consultations and provide
፫/ ከዋና ዳይሬክተሩ በሚቀርቡለት ሌሎች ጉዳዮች
recommendations on matters presented by
ላይ በመምከር የውሳኔ ሀሳቦችን ያቀርባል። the Director General.
፲. የአማካሪ ምክር ቤት ስብሰባዎች 10. Meetings of the Advisory Council
1. The regular meetings of the Council shall
፩/ የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በየሦስት ወሩ
be held every three months; provided,
ይካሄዳል፣ ሆኖም እንደአስፈላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ
however, that an urgent meeting may be
አስቸኳይ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡
held whenever necessary.
፪/ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአማካሪ ምክር ቤቱ 2. There shall be quorum where more than
አባላት በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልዐተ ጉባኤ half of the members of the Advisory
ይሆናል፡፡ Council are present at a meeting.
gA ፲ሺ፭፻፷፮ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፪ ጥቅምት ፲፱ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No. 2 29th October , 2018 …...page 10566

፫/ የምክር ቤቱ ውሳኔዎች በስምምነት ይወሰናሉ። 3. The decisions of the Advisory Council


ሆኖም ውሳኔዎችን በስምምነት መወሰን ካልተቻለ shall be by consensus. In the absence of
በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ፤ ድምጽ እኩል በእኩል consensus; decisions shall be made by

የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን የምክር majority vote and in case of a tie, the
Chairperson shall have a casting vote;
ቤቱ ውሳኔ ሆኖ ያልፋል፡፡
፬/ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው 4. Without prejudice to the provisions of this
አማካሪ ምክር ቤቱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት Article, the council may adopt its own

ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡ rules of procedure.

፲፩. የዋና ዳይሬክተር ሥልጣን እና ተግባር 11. Powers and Duties of the Director General
፩/ ዋና ዳይሬክተሩ የኤጀንሲው ዋና ሥራ 1. The Director General shall be the chief

አስፈጻሚ በመሆን ኤጀንሲውን ይመራል፤ executive officer of the Agency and shall

ያስተዳድራል፡፡ direct and administer the activities of the


Agency.
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተመለከተው 2. Without prejudice to sub-article (1) of this
ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ዳይሬክተሩ:-
Article, the Director General shall:
ሀ) በዚህ ደንብ አንቀጽ (፮) የተመለከቱትን a) implement the powers and duties of the
የኤጀንሲውን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ Agency specified under Article (6) of
ላይ ያውላል፤ this Regulation;
ለ) የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ሰራተኞችን b) employ and administer Foreign
በአዋጅ ቁጥር ፯፻፺/፪ሺ፭ እንዲሁም በውጭ Relation Service Officers in accordance
ግንኙነት አገልግሎት ሰራተኞች አስተዳደር with the Proclamation No. 790/2013
ደንብ ቁጥር ፫፻፺፱/፪ሺ፰ መሠረት እና and the Foreign Relation Service

ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በፌደራል ሰርቪስ Officers Administration Regulation no

ህግ መሠረት ይቀጥራል፣ ያሰተዳድራል፡፡ 399/2017 and support staff in


accordance with federal civil service
laws;
ሐ) የኤጀንሲውን የሥራ ፕሮግራምና በጀት c) prepare and submit to the Ministry the
አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል፣ በመንግሥት work program and budget of the

ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ agency, and implement same up on


approval by the Government;
መ) ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ የሥራ
d) represent the Agency on its dealings
ግንኙነቶች ኤጀንሲውን ይወክላል፤
with third parties;
ሠ) የኤጀንሲውን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች e) prepare and submit the work
ለሚኒስቴሩ ያቀርባል፤ performance report to the Ministry;
ረ) የኤጀንሲውን የሂሳብ ሪፖርቶች በማዘጋጀት f) prepare and submit financial reports of
ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር the Agency to the Ministry of Finance
ያቀርባል፤ and Economic Cooperation ;
gA ፲ሺ፭፻፷፯ Ød‰L ነU¶T Uz¤È qÜ_R ፪ ጥቅምት ፲፱ qN ፪ሺ፲፩ ›.M Federal Negarit Gazette No. 2 29th October , 2018 …...page 10567

፫/ ዋና ዳይሬክተሩ ለኤጀንሲው ሥራ ቅልጥፍና 3. The Director General may delegate part of


በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን his powers and duties to other officers and

በከፊል ለኤጀንሲው ሌሎች ኃላፊዎችና staff of the Agency to the extent necessary
for the efficient performance of the
ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡
activities of the Agency.
፲፪. በጀት 12. Budget
የኤጀንሲው በጀት በመንግሥት ይመደባል፡፡ The Agency’s budget shall be allocated by
the Government.
፲፫. የሂሳብ መዛግብት 13. Books of Accounts
፩/ ኤጀንሲው የተሟሉ እና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ 1. The Agency shall keep complete and

መዛግብት ይኖሩታል፤ accurate books of account.

፪/ የኤጀንሲውን የሂሳብ መዛግብት እና ገንዘብ 2. The books of account and financial

ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው documents of the Agency shall be audited
annually by the Auditor General or by an
ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ
auditor assigned by him.
ይመረመራል፡፡

፲፬. መመሪያ የማውጣት ስልጣን 14. Power to Issue Directives


ሚኒስቴሩ ይህን ደንብ ለማስፈጸም የሚያስችል The Ministry may issue directives necessary
መመሪያ ሊያወጣ ይችላል። for the implementation of this regulation.

፲፭. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ 15. Effective Date

ይህ ደንብ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ This Regulation shall enter into force on the date
of publication in the Federal Negarit Gazette.
ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል።

አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፱ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Done at Addis Ababa, this 29thday of October 2018.

ዶ/ር አብይ አህመድ ABIY AHMED (D/R)

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ PRIME MINISTER OF THE FEDERAL


DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትር

You might also like