You are on page 1of 9

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ


FEDERAL NEGARIT GAZETTE
OF THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

ሃያ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯


አዲስ አበባ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 25th Year No. 27
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ADDIS ABABA 5th, February 2019

¥WÅ CONTENT
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፪ /፪ሺ፲፩ ዓ.ም Proclamation No.1102 /2018

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ….ገፅ ፲ሺ፱፻፹፪ Reconciliation Commission Establishment


Proclamation..........................................page 10982

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፪/፪ሺ፲፩ PROCLAMATION No. 1102 /2018

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ A PROCLAMATION TO ESTABLISH RECONCILATION


COMMISSION

በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በተለያዪ ማህበረሰባዊ እና WHEREAS, it is necessary to reconcile based on


ፖለቲካዊ ግጭቶች ምክንያት በህዝቦች መካከል truth and justice the disagreement that developed among
የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም እውነትና ፍትህ peoples of Ethiopia for years because of different societal
ላይ መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈላጊ በመሆኑ፤ and political conflict;

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ WHEREAS, it is necessary to identify and ascertain


መንግሥት እንዲሁም ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም the nature, Cause and dimension of the repeated gross
አቀፍና አሕጉራዊ ስምምነቶች የተረጋገጡትን መሰረታዊ violation of human rights so as to fully respect and
የሰብዓዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ እና ተግባራዊ Implement basic human rights recognized under the
ለማድረግ በተደጋጋሚ የተከሰቱ ጉልህ የመብት ጥሰቶችን Constitution of the Federal Democratic Republic of
ምንነት በግልጽ መለየት አስፈላጊ ስለሆነ እና ለእርቀ Ethiopia and international and continental agreements
ሰላሙም አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ፤ which Ethiopian ratified and since it is important for the
reconciliation;

በተለያዩ ጊዜዎቸ እና የታሪክ አጋጣሚዎች የሰብዓዊ WHEREAS, it is believed that providing victims of
መብት ጥሰት እና ሌላ በደል ተጠቂዎች የሆኑ ወይም gross human rights abuses in different time and historical
ተጠቂዎች ነን ብለው የሚያምኑ ዜጎች በደላቸውን event with a forum to be heard and perpetrators to
የሚናገሩበትና በደል ያደረሱ ዜጎች ላደረሱት በደል disclose and confess their actions as a way of
በግልፅ በማዉጣት የሚፀፀቱበት እና ይቅርታ reconciliation and to achieve lasting peace;

ÃNÇ êU
Unit Price nU¶T Uz¤È ±.œ.q.Ü *¹þ1
Negarit G. P.O.Box 80001
፲ሺ፱፻፹፫ 10983
gA Ød‰L ነU¶TUz¤È qÜ_R ፳፯ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No 27, 5th, February 2019…….page

የሚጠይቁበት መንገድ በማበጀት እና እርቀ ሰላም


በማዉረድ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አስፈላጊ መሆኑ
ስለታመነበት ፤
ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ እየፈረሰ የሚሰራ ሳይሆን እየተገነባ WHEREAS, it is necessary to establish free and
የሚሄድ ስርዓት ለመፍጠር፣ ዲሞክራሲያዊ ሀገርና independent institution that inquire and disclose the truth of
ማህበረሰብ ለመገንባት ሰፊና ተቀባይነት ያለው የእውነትና the sources, causes and extent of conflicts and that takes

የእርቅ እና የሰላም ዓላማ ያነገበ፣ለግጭትና ቁርሾ ምክንያት appropriate measures and initiate recommendation that

የሆኑትን ዝንፈቶች ምክንያቶችና የስፋት መጠን አጣርቶ enable for the lasting peace and to prevent the future

እውነታውን በማዉጣት ተመልሰው እንዳይመጡ በዘላቂነት occurrence of such conflict.

ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራዊ እርምጃዎችን የሚወስድና


እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመነጭ ገለልተኛ እና ነጻ
ኮሚሽን ማቋቋም በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ሕገ NOW, THEREFORE, in accordance with Article 55

መንግስት አንቀፅ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው ታዉጇል፡፡ (1) of the Constitution of the Federal Democratic Republic
of Ethiopia, it is hereby proclaimed as follows:

፩. አጭር ርዕስ 1. Short Title


ይህ አዋጅ “የእርቀ-ሰላም ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ This Proclamation may be cited as the
ቁጥር ፩ሺ፩፻፪/፪ሺ፲፩” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ “Reconciliation commission establishment

፪. ትርጓሜ Proclamation No.1102 /2018.”

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ 2. Definition

በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡- Unless the Context requires otherwise, in this
Proclamation:
፩/ ክልል ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ 1/ "Region" means any of those recognized as a
ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ ፵፯(፩) መሰረት Region under Article 47 (1) of the Constitution
በክልልነት የታወቁት ሲሆኑ አዲስ አበባ እና of the Federal Democratic Republic of Ethiopia
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ይጨምራል፡፡ and include the Addis Ababa City
Administration and the Dire Dawa city
፪/ “መንግስት” ማለት እንደአግባቡ የፌደራል ወይም
Administration.
የክልል መንግስት ነው፡፡
2/ "Government" mean the Federal or a Regional
Government.
፫/ “እርቀ ሰላም ” ማለት በተለየ ምክንያት በተፈጠረ
ግጭት፣ያለመግባባት፣ቁርሾ እና ጥላቻ አዘል ብቀላ
3/ “Reconciliation" means establishing values of
በመያዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ የግጭት፣የጥላቻ መነሻ
forgiveness for the past, lasting love, solidarity
የሆኑትን በመለየት ላለፈው ይቅርታ፣ለቀጣይ and mutual understanding by identifying reasons
ደግሞ ዘላቂ ፍቅር፣አብሮ የመኖርን እና of conflict, animosity that are occurred due to
የመቻቻልን እሴት የሚሰፍንበትን ሁኔታ መፍጠር conflicts, misapprehension, developed
ማለት ነው፡፡ disagreement and revenge.
፲ሺ፱፻፹፬
gA Ød‰L ነU¶TUz¤È qÜ_R ፳፯ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No 27, 5th, February 2019…….page
10984

፬/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት 4/ Person” shall mean any physical or juridical person.
መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡
3. Establishment
፫. መቋቋም
1/ The Reconciliation Commission (hereinafter
፩/ የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽን (ከዚህ በኋላ ኮሚሽን referred to as” The Commission“) is hereby
እየተባለ የሚጠራ) በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል። established by this Proclamation.
2/ The Commission shall have its own office,
፪/ ኮሚሽኑ የራሱ ጽሕፈት ቤት፣ በጀት እና አስፈላጊ
budget and necessary staff.
የሆኑ ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡
3/ Office of the Commission shall have legal
፫/ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ሕጋዊ ሰዉነት አለው፡፡
personality.
4/ The Commission shall be accountable to the
፬/ የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል፡፡
Prime Minister.

፬. የኮሚሽኑ አባላትና አሰያየም 4. Appointment of members of the Commission


1/ Number of members of the commission shall
፩/ የኮሚሽኑ አባላት ቁጥር በመንግስት የሚወሰን
be determined by the government
ይሆናል፡፡
2/ Chairperson, Deputy Chairperson and other
፪/ የኮሚሸኑ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ሌሎች
Members of the Commission shall, up on
አባላት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ አቅራቢነት በሕዝብ
recommendation by the Prime Minister
ተወካዮች ምክር ቤቱ ይሰየማሉ:: appointed by the House Of People’s
Representative
፫/ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ የኮሚሽኑ ፀሐፊ ሆኖ
3/ The Head Of The Office serve as the
ያገለግላል::
Commission’s Secretariat.

፭. የኮሚሽኑ ዓላማ 5. Objectives of the Commission


የኮሚሽኑ ዓላማ በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ሰላም፣ Objective of the Commission is to maintain peace
ፍትህ፣ ብሄራዊ አንድነትና መግባባት፣ እንዲሁም እርቅ justice, national unity and consensus and also
እንዲሰፍን መስራት ነው፡፡ Reconciliation among Ethiopian Peoples.

፮. የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባራት


[[[[[[

6. Powers and Duties of the Commission


ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፦ The Commission shall have the following Powers and
Duties:
፩/ ስራዉን በሚመለከት ማንኛዉም ያገባኛል የሚል 1/ Concerning its work announce and make every
ሰው ወይም አካል ሃሳቡን እንዲያቀርብ ጥሪ concerned person or body to present his idea and
ማቅረብ እና አስፈላጊውን ምዝገባ ማካሄድ፤ the necessary registration.
2/ Make its work accessible, participatory by using
፪/ ስራዉን በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ ተደራሽ፣
technology; organize Reconciliation work shop in
አሳታፊ፣ ሁሉም አካል እኩል ተደማጭ የሚሆንበት
which all parties to be hear of;
የዕርቀ-ሰላም ውይይት መድረክ ማዘጋጀት፤
፲ሺ፱፻፹፭
gA Ød‰L ነU¶TUz¤È qÜ_R ፳፯ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No 27, 5th, February 2019…….page 10985

፫/ የተለያየ አቋም የያዙ የህብረተሰብ ክፍሎችን 3/ Identify principles and values which will be base
በማወያየትና ለሃገራዊ እርቅ መሰረት የሚሆኑ for national Reconciliation by making discussion

የጋራ መርህዎችንና እሴቶችን መለየት፤ with groups of society which have different view;

፬/ የግጭቶችንና የመብት ጥሰቶቹን መነሻ ምክንያት 4/ Make examination to identify the basic reasons of
ለመለየት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ disputes and violations of human rights by taking
አውዶችን፣ የተጎጂዎችንና ጥፋተኞቸን አስተያየት into consideration of political, social and economic

በመወሰድ ማጣራት ማካሄድ፤ circumstances and the view of victims and


offenders;
፭/ ለሰራው አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን 5/ To take or order presence of any document or

ማንኛዉንም የሰነድ ወይም ሌላ መረጃ ለአገር information from government or anybody which

ደህንነት ሲባል በሚስጥር እንዲጠበቁ በህግ ጥበቃ the commission deemed necessary for its work
except those that are given legal protection as
ከተደረገላቸው ውጪ ከመንግስትም ይሁን
confidential for the sake of national security ;
ከማናቸውም ሌላ አካላት የመቀበልና በፈለገው ጊዜ
እንዲያቀርቡ የማዘዝ፤

፮/ ሀላፊነቱን ለመወጣት የማናቸውንም ተቋም ይዞታ 6/ To visit premise of any institutions and to take

የመጎብኘት፣ በጉብኝቱም ጊዜ የሚያገኛቸውን copy of any information and document found by its

ማናቸውንም መረጃዎችና፣ ሰነዶችን ቅጂ visit;

የመውስድ፤

፯/ መረጃ ለመሰብሰብ በተናጠልም ሆነ በቡድን፣ 7/ To collect information make interview either

በምስጢርም ሆነ ለሀዝብ ክፍት በሆነ ሁኔታ ቃለ individually or in a group in secret or in an open

መጠይቅ ማድረግ፣ መጥሪያ በመላክ ማንኛዉም way to the public; order the presence of anyone
through summon and require to give his statement
ሰው እንዲቅርብ የማዘዝ እና ቃሉን በቃለ መሃላ
through oath;
እንዲሰጥ የማድረግ፤

፰/ ሃላፊነቱን ለመወጣት እንድሁኔታው የፌደራልም 8/ Depending on the situations to get support from
ሆነ የክልል ፖሊስ እገዛ የማግኘት፤ federal or regional state police to execute its duties;

፱/ በማጣራት የሚደርስባቸውን መደምደሚያዎች 9/ Notify to the public and concerned government

እንደሁኔታው በየጊዜው ለህዘብና ለሚመለክታቸው organs the conclusions reached through the

የመንግስት አካላት ማሳወቅ፤እና examination as appropriate; and

፲/ በህዝቦች መካከል የተፈጠረ ልዩነት እንዲረግብ እና 10/ Make Reconciliation among peoples to narrow
መግባባት እንዲፈጠር እርቀ ሰላም እንዲወርድ the difference created and to create consensus.

የማድረግ።
፲ሺ፱፻፹፮ 10986
gA Ød‰L ነU¶TUz¤È qÜ_R ፳፯ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No 27, 5th, February 2019…….page

፯. የኮሚሽኑ ስብሰባ 7. Meetings of the Commission

፩/ የኮሚሽኑ መደበኛ ስብሰባ በየአስራ አምስት ቀኑ 1/ The Commission shall hold its regular meetings

ይካሄዳል፣ ሆኖም እንደአስፈላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ every fifteen days; provided, however that it may

አስቸኳይ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡ hold extraordinary meetings at any time where
necessary.
፪/ ከኮሚሽኑ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከተገኙ 2/ There shall be quorum where more than half of the
ምልዓተ-ጉባኤ ይሆናል፡፡ members of the commission are present at a
meeting.

፫/ የኮሚሽኑ ምክረ ሃሳቦች በስምምነት ያልፋሉ፡፡ 3/ The Council shall pass its recommendation by
consensus.
፬/ በምክረ ሀሳቦቹ ላይ የጋራ ስምምነት የማይደረስ 4/ In case of failure to reach consensus on
ከሆነ በአብላጫ ድምፅ ያልፋሉ፡፡ recommendations, decisions shall be made by
majority vote.
፭. የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ኮሚሽኑ 5/ without prejudice to the provisions of this Article,
የራሱን የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ the Commission may adopt its own rules of

ይችላል፡፡ procedure.

፰. የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር 8. Powers and duties of the chair person of the
commission

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፡- Chairperson of the commission shall:

1/ Direct the general activities of the commission;


፩/ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዉን በበላይነት ይመራል፡፡
2/ Assign the necessary supportive staff to the
፪/ ለኮሚሽኑ አስፈላጊ የሆኑ የድጋፍ ሰጭ commission; and
ሠራተኞች የመድባል፡፡
3/ Make relation with third parties representing the
፫/ ኮሚሽኑን በመወከል ከሌሎች አካላት ጋር ግንኙነት Commission.
ያደርጋል፡፡
9. Powers And Duties of the Deputy Chair Person Of
፱. የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ ሥልጣንና ተግባር
The Commission
The Deputy Chairperson Of The Commission shall:
የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ፡-

፩/ ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ ሰብሳቢዉን ተክቶ 1/ Perform the activity of the chairperson in his
ይሰራል፤ absence.

፪/ ሰብሳቢው የሚሰጡት ተግባራት የፈጽማል:: 2/ Perform other activity given to him by the
Chairperson.

፲. የጽህፈት ቤቱ አቋም 10. Organization Of The Office

የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት:- Office of the Commission shall have:

፩/ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሾም ሃላፊና ፤እና 1/ Head appointed by the Chairperson Of The
Commission; and
፪/ አስፈላጊ ሰራተኞች ይኖሩታል፡፡ 2/ The necessary staff.
፲ሺ፱፻፹፯
gA Ød‰L ነU¶TUz¤È qÜ_R ፳፯ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No 27, 5th, February 2019…….page
10987

፫/ የኮሚሽኑ ዋና ፅ/ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ 3/ The head office of Commission shall be in Addis
እንደአስፈላጊነቱ በሌሎች ክልሎች ቅርንጫፍ Ababa and may have branch offices at regions, as
ሊኖረው ይችላል:: may be necessary.

፲፩. የጽህፈት ቤቱ ስልጣንና ተግባር 11. Powers And Duties Of Office


ጽህፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት The Office shall have the following Powers and
Duties:
ይኖሩታል:-

፩/ ለኮሚሽኑ አጠቃላይ የአስተዳደርና ፋይናንስ 1/ Render general financial and administrative


አገልግሎት ይሰጣል፤ service to the Commission;

፪/ ለኮሚሽኑ የህዝብ ተሳትፎና ምክክር መድረኮችን 2/ Provide logistics support to the Commission on
የሎጅስቲክስ ድጋፍ ይሰጣል፤ public participation and discussion forum;

፫/ የኮሚሽኑን ቃለ ጉባኤዎች፣ ውሳኔዎችንና ሌሎች


3/ Register and keep minutes, decisions and other
ሰነዶችን በሚገባ ተመዝግበው እንዲጠበቁ documents;
ያደርጋል፤

፬/ የኮሚሽኑን ስራ ለማሳለጥ አስፈላጊውን ድጋፍና 4/ To give necessary support and assistance to


facilitate activities of the commission.
እገዛ ያደርጋል።

፲፪. የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ስልጣንና ተግባር 12. Powers And Duties Of The Office
The Head of the Office shall:
የጽ/ቤቱ ኃላፊ :-
1/ Direct and administer the activities of the Office;
፩/ የጽሕፈት ቤቱ ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል፤
2/ Prepare the work programs and budgets of the
፪/ የኮሚሽኑ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል ሲፀድቅም ተግባራዊ
Commission and implement same upon approval;
ያደርጋል፤
3/ Represent the Office in all dealings with third
፫/ ጽሕፈት ቤቱ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው
parties.
ግንኙነቶች ጽሕፈት ቤቱን ይወክላል::
13. Independency Of The Commission
፲፫. የኮሚሽኑ ገለልተኝነት

ኮሚሽኑ ስራውን በነፃነትና በገለልተኝነት ያከናውናል። The Commission shall perform its activities freely and
independently.

፲፬. የስራ ዘመን 14. Terms Of The Commission


1/ Terms of the Commission shall be up to three
፩/ የኮሚሽኑ የስራ ዘመን አስከ ፫ ዓመት ነው።
years.

2/ Without prejudice to Sub-Article 1 of this article,


፪/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ ፩ የተጠቀሰው ቢኖርም
term of the Commission may be prolonged as may
የኮሚሽኑን የስራ ዘመን እንድሁኔታው ሊራዘም
be necessary.
ይችላል።
፲ሺ፱፻፹፰
gA Ød‰L ነU¶TUz¤È qÜ_R ፳፯ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No 27, 5th, February 2019…….page 10988

፲፭. የመተባበር ግዴታ 15. Duty to Cooperate

ማን ማንኛውም ሰው ኮሚሽኑ በዚህ አዋጅ የተሰጠውን Any person shall have an obligation to cooperate with
ሃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ the Commission for any legal questions requested by
ለሚያቀርበው ማንኛውንም ህጋዊ ጥያቄ ትብብር the Commission to enable to Commission undertake

የማድረግ ግዴታ አለበት። its responsibility provided under this Proclamation.

፲፮. በጀት 16. Budget


የኮሚሽኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል። The budget of the Commission shall be allocated by
Government.

፲፯. የሂሳብ መዛግብት 17. Books of Accounts


፩/ ኮሚሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ
1/ The Commission shall keep complete and accurate
መዛግብት ይይዛል፡፡ books of accounts.
፪/ የኮሚሽኑ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች 2/ The books of accounts and financial documents of
በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው the Commission shall be Audited annually by the
ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ፡፡ Auditor General or by auditors designated by him.

፲፰. ጠቋሚዎችንና ምስክሮችን ስለመጠበቅ 18. Protection Of Witnesses And whistle-blower


፩/ ማንኛዉም ሰው በኮሚሽኑ ፊት ቀርቦ በሚሰጠው
1/ No one may be accused by the testimony given to
ቃል መሰረት ክስ ሊመሰረትበት እንደዚሁም
the Commission as well as the testimony given
የሰጠው ቃል በእርሱ ላይ ማስረጃ ሆኖ before the Commission could not serve as and
ሊቀርብበት አይችልም፡፡ evidence up on him.

፪/ ለጠቋሚዎችና ለምስክርች ጥበቃ ለማድረግ የወጣ 2/ The provisions of the laws for the protection of the
ሕግ ለኮሚሽኑ ቃላቸው እና መረጃ ለሚሰጡ witnesses and whistle blowers shall apply to those
ሰዎችም ተግባራዊ ይሆናል:: who have provided testimonies and evidences to
the Commission.

፲፱. ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን 19. Power To Issue Regulation and Directive

፩/ የሚንስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ 1/ Council of Ministers may issue Regulations


necessary for the effective implementation of this
ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ
Proclamation.
ይችላል፡፡

፪/ ኮሚሽኑ ይህንን አዋጅና በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2/ The Commission may issue Directives necessary for

(፩) መሰረት የወጡ ደንቦችን ለማስፈፀም the effective implementation of This Proclamation
and Regulations issued under Sub Article 1 of this
የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
Article.
፲ሺ፱፻፹፱
gA Ød‰L ነU¶TUz¤È qÜ_R ፳፯ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No 27, 5th, February 2019…….page 10989

፳. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ 20. Effective Date


ይህ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት This Proclamation shall come in to force as of the 25th

ከታህሳስ ፲፮ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል። day of December 2018 of its ratification by the House
Of Peoples Representatives.

አዲስ አበባ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Done at Addis Ababa, 5th, Day Of February 2019,

ሳህለወርቅ ዘውዴ SAHLEWORK ZEWEDIE

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ


PRESIDENT OF THE FEDERAL DEMOCRATIC
ፕሬዝዳንት
REPUBLIC OF ETHIOPIA
gA Ød‰L ነU¶TUz¤È qÜ_R ፳፯ ጥር ፳፰ ቀን ፪ሺ፲፩ ዓ.ም Federal Negarit Gazette No 27, 5th, February 2019…….page
1

You might also like