You are on page 1of 12

የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን

የ 2012 ዓ.ም አመታዊ እቅድ

| የ 2012 ዓ.ም የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ዓመታዊ ዕቅድ 1


ሐምሌ 2012 ዓ.ም

ማውጫ ገፅ

1. መግቢያ..........................................................................................................................................3

2. አላማ…………………………………………………………………………………………..3

3. ተልዕኮ............................................................................................................................................3

የተቋሙ ራዕይ...................................................................................................................................3

የተቋሙ ተልዕኮ.................................................................................................................................3

የቡድኑ ተልዕኮ...................................................................................................................................4

4. እሳቤዎች የግፊት ሃይሎች...................................................................................................................4

5. የሁኔታ ትንተና (SWOT) Analysis...................................................................................................5

6. የ 2011 ዓ.ም የቬቲንግ እና ስክሪኒግ ቡድን ዕቅድ......................................................................................6

6.1. በዓመቱ የሚተኮርባቸው ግቦችና የግብ መግለጫዎች...........................................................................7

6.2. መለኪያ ……………………………………………………………………………………8

6.2. ስኮር ካርድ……….............................................................................................................…….9

7. ማጠቃለያ……………………………………………………………………………………….10

| የ 2012 ዓ.ም የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ዓመታዊ ዕቅድ 2


1. መግቢያ

በተቋማዊ ደህንነት ዳይሬክቶሬት የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ተልዕኮ የሆነውን የተቋሙን የሰው ሀይል

ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እንዲችል ከዚህ በፊት የነበሩትን የስራ እንቅስቃሴዎች

ስኬቶችና ውስንነቶችን በመገምገም ለቀጣይ የስራ ዕቅድ እንደ ግብዓት መጠቀም በሚያስችል አኳኋን

አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ለ 2012 ዓ.ም በጀት አመት ለኤጀንሲያችን ተልዕኮ መሳካት የበኩላችንን ድርሻ

ለመወጣት አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት የምንሰራ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት አጠቃላይ የተቋሙን የሰው

ሀይል የተጋላጭነት ስጋቶች ለመቀነስ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ የተቋሙን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማረጋገጥ

የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በዋናነት ትኩረት በማድረግ የቡድኑን የመፈጸም አቅም የማሳደግ፣ ተቋማዊ

ትስስሮችን የማጠናከር፣ የሰው ሀይል የማወቅ ደረጃ የማሳደግ እና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን በመስራት

የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ የምንሰራ ሲሆን የባለድርሻና የሌሎች አጋር አካላትን ድጋፍ በመደመርና

በመጠቀም ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በትጋት መስራት በዚህ ዓመት በስራ ክፍሉ ትኩረት የሚሰጠው

ጉዳይ ነው::

2. አላማ

የሰው ሀይል ደህንነትን ለማረጋገጥ ያለፉ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ ውስጣዊና ውጫዊ ከባቢዎችን

በመፈተሸ ክፍሉ በ 2012 ዓ.ም የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመለየትና የአፈጻፀም ስልት በመንደፍ

ተልዕኮውን ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት እና ተጣጣሚነት በዚህ ሪፖርት ማቅረብ ነው፡፡

3. ተልዕኮ

 የተቋሙ ራዕይ

 በ 2017 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ብቃት ያለው እና በሃገሪቱ ህዳሴ ቁልፍ ሚና የሚጫወት

ብሄራዊ የሳይበር ሴኪውሪቲ ተቋም ዕውን ማድረግ ፡፡

| የ 2012 ዓ.ም የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ዓመታዊ ዕቅድ 3


 የተቋሙ ተልዕኮ

 የአገሪቱን የኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማትን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል

አቅም በመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅ

 የቡድኑ ተልዕኮ

 ማንነቱ የታወቀ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ንቁ ተቋማዊ ማህበረሰብ ለመገንባት በሚያስችሉ የመረጃ

አሰባሰብ፣ የኋላ ታሪክ ጥናት፣ የምልመላ እና መረጣ ስራዎች አቅም በመገንባት ቀጣይነት ያለው

የሰው ሀይል ማንነት ፕሮፋይል መገንባት፤

4. እሳቤዎች (የግፊት ሃይሎች)

 ከሰው ሀይል የሚመነጭ የደህንነት ስጋቶች መበራከት

 የውስጥና የዉጪ የጠላት ሃይሎች ትስስር እያደገ መምጣትና ተቋማችን የነዚህ ኃይሎች ዋነኛ ኢላማ

መሆን

 ሀገራዊና ተቋማዊ ለውጦችን ለመቀልበስ የሚሰሩ አካላት መበራከት

 ሌሎች የመንግስት ቁልፍ ተቋማት ለዘርፉ ያላቸው ከፍተኛ ፍላጐት

 በሀገር ደረጃ በዘርፉ የተፈጠረ አቅም አለመኖር

5. የሁኔታ ትንተና (SWOT) Analysis

 የቬቲንግ እና ስክሪኒግ ቡድን ተልዕኮውን ሲፈፅም ሊያጋጥሙት የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን

አቅዶ ለመከላከል እንዲችል ውስጣዊና ውጫዊ ከባቢዎችን በመፈተሽ እና ይህንኑም መነሻ

በማድረግ የዘርፉን ጥንካሬ፣ ድክመት፣ መልካም እድሎችን እና ስጋቶችን መለየት አስፈላጊ

በመሆኑ በሚከተለው መንገድ ተቀምጧል፡፡

ጥንካሬ መልካም አጋጣሚ

| የ 2012 ዓ.ም የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ዓመታዊ ዕቅድ 4


 የሰው ሀይልን ደህንነት በማረጋገጥ ተግባራት  በሰው ኃይል ደህንነት ጉዳዮች የተፈጠረ

ባለፉት አመታት በተግባር ተፈትነን ያገኘናቸው መልካም ግንኙነትና ትስስር ከጊዜ ወደ ጊዜ

ልምዶች እየጠነከረ መምጣቱ

 ስራዎቻችን ዝርዝር የአሰራር ስርዓት ያላቸው እና  ለክፍሉ ስራዎች መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ
በመመሪያዎች የተደገፉ መሆናቸው የአሰራር ስርዓቶችና አቅሞች መኖራቸው

 ተቋሙ ለክፍሉ የሚሰጠው ትኩረት እያደገ  ተቋማዊ እና ሀገራዊ ለውጦችን በቀላሉ

መምጣቱ እና ከዘርፉ ከፍተኛ ውጤት መፈለጉ የሚላመድ እና በብቃት መፈጸም የሚችል

ወጣት ሀይል ያለን መሆኑ


 ስራዎችን በራስ ተነሳሽነት የሚሰራ እና ተደምሮ
 ስራዎችን በሚፈለገው ጥራት እና
በመስራት ውጤት ለማስመዝገብ ፍላጎት ያለው
ጥልቀት ለመከወን ሚያስችል አደረጃጀት
የሰው ኃይል ያለን መሆኑ
መፈጠሩ
 ከተቋሙ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በትስስር

ለመስራት ያለን ዝግጁነት እያደገ መምጣቱ  ከሚፈለገው የተቋሙ ተልዕኮ አንፃር ሰውን

ማወቅ መቻሉ
 በክፍሉ የሰው ሀይልን ደህንነት የማረጋገጥ

ተግባራት የጠላትን እንቅስቃሴ እና የስለላ ተልዕኮ  ዘርፉ በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት

በተወሰነ ደረጃ መግታት (ዲተር ማድረግ) መቻሉ የሚሰጠው መሆኑ


ውስንነት ወይም ክፍተት ስጋት
 ፕሮፌሽናሊዝም ለመፍጠር የሚያስችል የአቅም  የሰው ልጅ ባህሪ ተለዋዋጭ እና ውስብስብ

ግንባታ ስራ በተፈለገው መጠን ያለመሰራቱ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሰው የማወቅ

አቅማችንን የሚፈታተን መሆኑ


 የተልዕኮ ግልፅነት በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑ
 ተቋማችን ለተለየያዩ የውስጥና የውጭ ጠላት
 የተቋሙ ሰራተኞች የተቋሙን ደህንነት የማስፈፀሚያ
ኃይሎች ግንባር ቀደም ዒላማ መሆን
ቁልፍ መሳሪያ ያደረገ አካሄድ ያለመፈጠሩ
 ሰውን በሳይንሳዊ ዘዴ ለማወቅ የሚያስችሉ
 ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር ሊፈጠር የሚገባው
የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ውድ መሆን
ትስስር በሚፈለገው ደረጃ አለመሰራቱ
 በሀገር ደረጃ ዘርፉ ብዙ ያልተሰራበት መሆኑ
 የስራዎች ጥራት ላይ ትኩረት ያለማድረግ
እና በዘርፉ አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ወጪ
 በማንነት ማጣራት (ቬቲንግ) ስራዎች የሶስተኛ ወገን

| የ 2012 ዓ.ም የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ዓመታዊ ዕቅድ 5


ጥገኝነት ያለብን መሆኑ የሚጠይቅ መሆኑ

 የአሰራር ስርዓቶቻችን በቴክኖሎጂ የተደገፉ አለመሆኑ  የጠላቶች እና የይሆናል ጠላቶች አይነት ባህሪ

 የተቋሙ ማህበረሰብ የደህንነት ግንዛቤ አናሳ መሆኑ እና የማጥቂያ ስልቶች በየጊዜው ተለዋዋጭ

ቀድሞ ለመገመት አዳጋች መሆኑ


 ስራው ከሚያስፈልገው ፕሮፌሽናል የሰው ሀይል

ብዛት አንፃር ያለው ሀይል አነስተኛ መሆኑ  ዘርፉ ከግለሰቦች ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ

መብቶች ጋር በተየያዘ ጥያቄ የሚያስነሱ


 የፈፃሚ አካላት የአቅም ውስንነት መኖር
ጉዳዮች መኖራቸው

| የ 2012 ዓ.ም የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ዓመታዊ ዕቅድ 6


6. የ 2012 ዓ.ም የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ዕቅድ

5.1. በዓመቱ የሚተኮርባቸው ግቦችና የግብ መግለጫዎች

ግብ 1፡- የተቋሙን የሰው ሀይል ደህንነት ማረጋገጥ (የሰው ኃይል የማወቅ ደረጃ ማሳደግ) የቀደምትነት
ዋና ዋና ተግባራት ደረጃ
 ለተቋሙ ተልዕኮ የሚመጥን፣ ማንነቱ የታወቀ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የሰው ሀይል መለየት (የሰው ኃይል የማወቅ
1
ደረጃ ማሳደግ)
 የቅድመ ቅጥር ምልመላ እና መረጣ ስራዎችን ማከናወን
 የቅድመ ቅጥር ኢንተርቪው ማድረግ

 በውስጥ ቅጥር፣ዝውውር እና እድገት የሚቀጠሩ አባላትን ኢንተርቪው ማድረግ

 በማስታወቂያ ቅጥር የሚገቡ አዲስ አባላትን ኢንተርቪው ማድረግ


 አዲስ የመረጃ(ቋንቋ) ባለሙያዎችን ምልመላና መረጣ ስራ ማከናወን

 መረጃ መሰብሰብ፣ ክትትል ማድረግና መቀመር


 ኘሮፋይል ዝግጅት
 የማንነት ማጣራት (ቬትንግ) ስራዎች ማከናወን
1
 በተቋሙ የተለያዩ የቅጥር አይነቶች ቅጥር የሚፈፅሙና የሚመደቡ አባላት
 በልዩ ሁኔታ የተመረጡ በተቋሙ የስራ ክፍሎች ውስጥ የሚሰሩ አባላት
 ከተቋሙ ውጭ ባሉ ቁልፍ የመንግስት ተቋማት የሚመጡ የቬቲንግ ጥያቄዎች
 ዋና ዋና ተግባራት
 ኢንተርቪው እና ኢንትሮጌሽን ማድረግ
 ትንተና ማከናወን
 የጥናት ውጤት ሪፖርት ማዘጋጀት
 ፕሮፋይል ማዘጋጀት
ግብ 2፡- ከአጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት በመፍጠር ለተልዕኳችን ኃይል ማብዛት፤
 በማንነት ማጣራት ስራ (ቬቲንግ) ከተቋሙ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር ትስስር መፍጠር፤ በቀጣይነት አጠናክሮ መቀጠል
 ባለድርሻ አካላት
 ከተቋሙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር፤
1
 በዳይሬክቶሬቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች ቡድኖች ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር፤
 አጋር አካላት
 ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት
 በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስተዳደር መዋቅሮች (ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣ቀበሌ)
 ሌሎች የደህንነት መዋቅሮች (እንዳስፈላጊነቱ)
 በቅድመ ቅጥር ምልመላ እና መረጣ ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት መፍጠር
 ከሰው ሀይል ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
 ከቀጣሪ ክፍሎች
 ምልመላው ከሚከናወንበት ተቋም (የት/ተቋም፣ ማሰልጠኛ ተቋማት፣በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስተዳደር
መዋቅሮች)
 የክፍሉን ስራዎች ትራንስፎርም ሊያደርጉ በሚችሉ እና አጠቃላይ ተቋማዊ ጥናቶችን ማከናወን በሚያስችሉ ስራዎች
ላይ ተሳትፎ ማድረግ

ግብ 3፡- የክፍሉን የመፈፀም አቅም ማሳደግ


ዋና ዋና ተግባራት
 የክፍሉን የአሰራር ስርዓቶች ማሻሻል (የማንነት ማጣራት እና የቅድመ ቅጥር ምልመላና መረጣ)

 የክፍሉን እስትራቴጂክ እቅዶች እና የአፈፃፀም መመሪያዎች ማዘጋጀት፣ ማፀደቅ፣ ተግባራዊ ማድረግ

 የአባላትና የአመራር ፕሮፋይል በቀጣይነት ማደራጀት (እቅድ፣ ሪፖርቶች እና ግምገማዎች) 1


 የተልዕኮ ግልፅነት የሚፈጥሩ ውይይቶችን ማድረግ (ሀገራዊ እና ተቋማዊ መመሪያዎች፣ ደንቦች፣ የአሰራር ስርዓቶች)

 የተቋሙን የሰው ሀይል ልማት እስትራቴጂዎች መሰረት ያደረገ የአባላትን የስልጠና እና ትምህርት እድሎች ማመቻቸት

 የአሰራር ስርዓቶችን ማዘመን (ሰው ለማወቅ የሚያግዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ሳይንሳዊ የአሰራር ስርዓቶችን

ማጥናት)

መለኪያ
ግቦች
ቀዳማይ ዳህራይ

የማንነት ማጣራት (ቬቲንግ) ስራዎችን መፈፀም (100%)  ትንተና የተሰጠበት የአባላት ፕሮፋይል
የቅድመ ቅጥር ምልመላና መረጣ ስራዎችን መፈፀም  ትንተና የተሰጠበት የአባላት ፕሮፋይል
1
(100%)

የአባላትን ፕሮፋይል ማደራጀት (100%)  ካታሎግ ስርዓት ውስጥ የገባ የአባላት ፕሮፋይል
ከባለድርሻ አካላት ጋር የተፈጠረ ትስስር 
2  የደንበኛ እርካታ
ከአጋር አካላት ጋር የተፈጠረ ትስስር 
 የደንበኛ እርካታ
የተዘጋጁ የውይይት መድረኮች ብዛት  የተፈጠረ የተልዕኮ ግልፀኝነት

 የቀረቡ ግብዓቶች
3 የተሻሻሉ የአሰራር ስርዓቶችና ስትራቴጂዎች  ፀድቀው የተተገበሩ የአሰራር ስርዓቶች
የተዘጋጁ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች  የተፈጠረ አቅም
የፀደቀ መመሪያ  የተተገበረ መመሪያ
6.2. መለኪያ
6.3. ስኮር ካርድ
የግብ
መስፈሪያ የመለኪያ ዒላማ 1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ
ክብደት መነሻ
ግቦች መለኪያ ክብደት ሩብ ሩብ ሩብ ሩብ

የማንነት ማጣራት (ቬቲንግ) በ% 50 0% 100% 100% 100% 100% 100%


50
የተደረገባቸው አባላት ብዛት
በ% 30 0% 100% 100% 100% 100% 100%
1 የቅድመ ቅጥር ኢንተርቪው የተደረጉ

አባላት ብዛት
የተደራጀ የአባላት ፕሮፋይል በ% 20 0% 100% 100% 100% 100% 100%

በ% 40 50% 90% 60% 70% 80% 90%


ከባለድርሻ አካላት ጋር የተፈጠረ
2 20

ትስስር
30% 60% 30% 40% 50% 60%
ከአጋር አካላት ጋር የተፈጠረ ትስስር በ%
30
በ% 30 50% 90% 60% 70% 80% 90%
የደንበኛ እርካታ መጠን
የተዘጋጁ የውይይት መድረኮች ብዛት በቁጥር 20 0 16 4 4 4 4
የተሻሻሉ የአሰራር ስርዓቶች እና በ% 20 50% 90% 60% 70% 80% 90%

3 30 ስትራቴጂዎች
በቁጥር 30 0% 4 1 1 1 1
የተዘጋጁ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች
በቁጥር 30 0 1 ዝግጅ ማፀደቅ 1 ትግበራ
የፀደቀ መመሪያ

7. ማጠቃለያ

የቬቲንግና ስክሪኒንግ ቡድን የ 2012 ዓ.ም አመታዊ እቅድ የክፍሉ ተልዕኮ የሆነውን ከሰው ሀይል ሊመነጭ የሚችልን

የደህንነት ስጋት በመቀነስ ማንነቱ የታወቀ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሰው ሀይል የመለየት ተግባራት ላይ ትኩረት በማድረግ

የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከመቸውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ርብርብ የሚደረግ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ጊዜያት

የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ከኦፕሬሽናል ስራዎች በተጨማሪ ተቋማዊ ትስስሮችን የማጠናከር፣

ስራዎቻችንን የማስተዋወቅ እና የአሰራር ስርዓቶችና የማሻሻል፣ የማዘመንና ሳይንሳዊ የማድረግ ስራዎች

በስፋት የሚሰሩ ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የጠላት እንቅስቃሴ

እና ተለዋዋጭ የማጥቂያ ስልቶች ማወቅ የሚያስችል አቅም መፍጠርን የሚጠይቅ እና ከቅርብ ጊዜ ወደህ

በአገራችን እየተፈጠሩ ካሉ ክስተቶች ጋር በተየያዘ የዘርፉ አስፈላጊነት ከተቋማችንም ባለፈ የሌሎች ተቋማትን

ትኩረት የሚስብ በመሆኑ በዘርፉ ሀገራዊ አቅም ለመፍጠር ለአቅም ግንባታ ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰጦ

የሚሰራ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ክፍሉ በ 2012 በጀት አመት በሁሉም የክፍሉ አባላት ዘንድ የተልዕኮ ግልፀኝነት

በመፍጠር በከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት እና የአመራር ቁርጠኝነት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የምንሰራ

ይሆናል፡፡

You might also like