You are on page 1of 8

ምዕራፍ ሁለት

የተዛማጅ ጽሑፎች ክለሳ

መመመመ

በዚሕ ምዕራፍ ይሕ ጥናት የሚያጠነጥንበትን የሪከርድ ስራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር

ስልጠናና ትምሕርት አስመልክቶ የተሰሩ የምርምር ስራዎች ክለሳ ቀርቧል፡፡ በዚሕ ክፍል ያየናቸዉ

ጽሑፎች በአለም ዙሪያና በአፍሪካ በዘርፉ የስልጠናና ትምሕርት ልማት እድገት፣ የተገኙ ልምዶችና

ዋና ዋና ችግሮችን በተመለከተ የተሰሩ ጥናቶች ናቸዉ፡፡

መመመመመ መመ መመመመመ መመመመመ መመመመመመ መመመመ

ሪከርድ ሥራ አመራር ሪከርዶችን ከተፈጠሩበት ወይም ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ እስከሚወገዱበት

ጊዜ ድረስ አመዘጋገባቸዉን፣ አበታተናቸዉን፣ አደረጃጀታቸዉን፣ አቀማመጣቸዉንና፣

አወጣጣቸዉን፣ ሁሉ የምንቆጣጠርበት ስርዓት ማለት ነዉ(Read & Ginn, 2011)፡፡ የመዛግብት

አስተዳደር ተመሳሳይ ሲሆን ልዩነቱ መዛግብት ቀጣይና የረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸዉ ሆነዉ

ለፈጠራቸዉ መስሪያ ቤት ቀጣይ ጥቅም ስለሚሰጡ ወይም ለጥናትና ምርምር ለ ሦስተኛ ወገኖች

የሚያስፈልጉ በመሆኑ እንዲቀመጡ የተደረጉ ሪከርዶች ናቸዉ (Williams, 2006)፡፡

መመመመመ መመ መመመመመ መመመመመ መመመመመመ መመመመ መመመመ መመመ

የሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር የሰለጠነ የሰዉ ኃይል የሚፈልግ ትልቅ ሙያ እየሆነ

የመጣ ዘርፍ ነዉ፡፡ የሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር ስልጠናና ትምሕርት ዕድገት

ታሪክ እንደሚያሳየዉ ሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር እንደሙያ ታዉቆ ስራዉ

የሚከናወንበትን ቴክኒክ ብቻ ሳይሆን ዲሲፕሊኑን የሚመለከቱ ጽንሰ ሀሳባዊና መላምታዊ

ማዕቀፎችን የመቀመርና ማስተማር እንዲሁም የሪከርድና መዛግብትን ክዋኔ የሚያበለጽግ

ምርምር የማካሄድ አስፈላጊነት እየታመነበት የመጣዉ በጣም በቅርቡ ነዉ፡፡


የሪከርድ ሥራ አመራርና የመዛግብት አስተዳደር ትምሕርትና ስልጠና የተጀመረዉ ሁለት መሰረታዊ

አስተሳሰቦችን መሰረት አድርጎ ነዉ፡፡እነዚሕ አስተሳሰቦች መዛግብት አስተዳደር ራሱን የቻለ ልዩ

ሙያ ነዉ እንዲሁም እንደማንኛዉም ሙያ በዩንቨርሲቲ ዉስጥ በሚሰጥ ስልጠናና ትምሕርት

አማካይነት የሚገኝ ነዉ የሚሉ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም የመዛግብት አስተዳደር በኋላ ደግሞ የሪከርድ

ስራ አመራር ሥልጠናዎችና ትምሕርቶች አላማ ይሕንን የመዛግብት ሪከርድ ሥራ አመራር ከማንም

ሙያ ጋር የማይደባለቅ ልዩ ሆኖ እንዲመሰረት እንዲሁም እንደ ሌሎች ስራዎች ሁሉ ይህም ስራ

የሚጠይቀዉን የእዉቀትና የክህሎት ደረጃ እንዲታወቅ ለማድረግ ያለመ ነበር(Schaeffer, 1994)፡፡

የመዛግብት አስተዳደር በኋላ ደግሞ የሪከርድ ሥራ አመራር ሥልጠና ሲጀመር በስልጠናዉ አላማ

ላይ ግልጽ የሆኑ ልዩነቶች ነበሩ(Katuu, 2009)፡፡ የመጀመሪያዉ አስተሳሰብ የአርካይቭ ስልጠና

ባለሙያዎች በመዛግብት ተቋማት ዉስጥ የሚሰሩ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ስራዎችን

በማለማመድ ላይ ያተኮረ ተግባራዊ ትምሕርት መሆን አለበት የሚል ሲሆን ከዚያ ያለፈ ልዩ ልዩ

መላምቶችንና ጽንሰ ሀሳቦችን ማስተማር አለበት የሚለዉን ሀሳብ አይቀበሉም ነበር፡፡ ሁለተኛዉ

አስተሳሰብ ደግሞ የመዛግብት አስተዳደርና ሪከርድ ስራ አመራር ትምሕርት መሰረት ማድረግ

ያለበት በመዛግብት አስተዳደር ዉሥጥ ምን ስራ እንዴት መስራት አለባቸዉ የሚለዉን ሳይሆን

ከፍ ብሎ ሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደርን በሚመለከት በደንብ ማሰብ

የሚያስችላቸዉን የጽንሰ ሀሳብና መላምቶች ትምሕርት መሆን አለበት የሚለዉን ነዉ፡፡

ምክንያቱም “የመዛግብት አስተዳደር ሥራዎችን አከናዋኞች ከዚህ ሥራ ጀርባ ያሉ መላምቶችን

ወይም ዉስብስብ የኢንፎርሜሽን ሳይንስና ከአርካይቭ ሥራ ጋር ተዛማጅ የሆነዉን የታሪክ

ትምሕርት ዕዉቀቱም ሆነ መረጃዉ የሌላቸዉ በመሆኑ …የሚያጋጥሟቸዉን ችግሮች መላምቶች

መተንተን አይችሉም”(Stielow, 1990)፡፡ የመጀመሪየዉ አስተሳብ እስክ 1970ዎቹ በአዉሮፓና

በሰሜን አሜሪካ የበላይነት አግኝቶ የቆየ ሲሆን ቀስ በቀስ ከላይ በተጠቀሰዉ ምክንያት የመዛግብት

አስተዳደርና ሪከርድ ስራ አመራር ሳይንሱ ላይ ያተኮረ ትምሕርት መሰጠት አለበት የሚለዉ

ትኩረት እያገኘ ሊመጣ ችሏል፡፡ አሁን ያለዉ የሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር

ሥልጠና የሙያዉን ተግባርና መላምት ተመጣጥኖ እንዲሄድ ማድረግን አስፈላጊነት ላይ ትኩረት

ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል(Katuu, 2009; Stielow, 1990)፡፡


መመመ መመመመመ መመ

በአሜሪካና ካናዳ በመዛግብት አስተዳደርና ሪከርድ ሥራ አመራር ባለሙ ያዎች ማሕበራት

የአሜሪካ ሪከርድ ሥራ አመራር ማሕበር /ARMA/ እና የአሜሪካ መዛግብት ባለሙያዎች ማሕበር

/SAA/ የመዛግብትና ሪከርድ ሥራ አመራር ትምሕርቶችን በተመለከተ ከፍተኛ ሚና

ተጫዉተዋል፡፡ እንደ ሸፐርድ (1998) አባባል የሙያ ማሕበራትና ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት

አንደኛቸዉ የሌላኛዉን ሥራ በማገዝ ረገድ የሚጫወተዉን ከፍተኛ ሚና በማየት በትብብር ላይ

የተመሰረተ ግንኙነት ገና በጠዋቱ ሊመሰርቱ ችለዋል፡፡ ይኸዉም ትብብር ትምሕርት ቤቶቹ

በየመስሪያቤቱ በሪከርድ ሥራ አመራርና በመዛግብት ሙያ ላይ ተሰማርተዉ የሚገኙ

ባለሙያዎችን ተከታታይ ትምሕርት የመሥጠትና በሙያዉ ላይ ያላቸዉን እዉቀት መገንባት

ሲሆን የሙያ ማሕበራቱ በበኩላቸዉ ትምሕርቱ ዉሥጥ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደመሆናቸዉ

በትምሕርት ተቋማቱ ዉሥጥ የሚሰጡ ትምሕርቶች ላይ የመወሰን መብት አለን በሚል

በትምሕርቱ ዉሥት ስለሚካተቱ ኮርሶች የሚያቀርቡት ሀሳብ ነዉ፡፡ እነዚሕ ተቋማት የሥርዓተ

ትምሕርት መመሪያዎችን በማዘጋጀትና የስልጠናና ትምሕርት አጀንዳዎችን በማራመድ ለሙያዉ

ዕድገት አስተዋጽዖ አድርገዋል (Katuu, 2009)፡፡

መመመመመ መመ መመመመመ መመመመመ መመመመመመ መመ መመመመ መመመመመ

የሪከርድና መዛግብት ሙያ ስልጠናና ትምሕርት እድገት በአፍሪካ ደረጃ ሲነገር አስቀድሞ ሁለት

ነገር ማስታወስ እንደሚያስፈልግ ካቱ (Katuu, 2015) ያስገነዝባል፡፡ እነዚሕም አፍሪካ 54 አገሮችን

የያዘ ትልቅ አሕጉር መሆኑን እና እያንዳንዱ የራሱ ልዩ ታሪክ እና የእድገት ሂደት ያለዉ መሆኑ ነዉ፡፡

በመሆኑም በየአገሩ የተለያዩ ልምዶችና በዚህ ምክንያት ደግሞ ልዩነቶች መኖራቸዉን ማስታወስ

ያስፈልጋል፡፡

አፍሪካ በቅኝ ግዛት ዘመን የጽሑፍ ሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር ሥራ

የሚከናወነዉ በቅኝ ገዥዎች የነበረ ሲሆን የሪከርድ ሥራዉ የቅኝ ግዛት አስተዳደሩን ለማከናወን

የሚያስፈልግ አንድ ሥራ ብቻ ነበር እንጂ የቅኝ ግዛቱን ሕዝብ ታሪክ ለማቆየት በሚያስፈልግ ደረጃ

ትኩረት ተሰጥቶት የተሰራ አልነበረም፡፡ ይልቁንም የቅኝ አገሩ ሰዉ በሙያዉ ሥልጠናና ትምሕርት

እንዲያገኝ አልተደረገም፡፡ይሕም በመሆኑ እንደ አዉሮፓዉያን አቆጣጠር በ1960ዎቹ ብዙዎቹ


አፍሪካ ሀገራት ነጻነታቸዉን ሲቀዳጁ የሪከርድ ሥራ አመራር ሥራዉን ለማከናወን በልምድና

ክሕሎት ዝግጁነት ያለዉ ባለሙያ አልነበረም(Katuu, 2015)፡፡ ይህም ሁኔታ በሪከርድ ሥራ

አመራርና መዛግብት አስተዳደር ሙያዎች ትምህርትና ስልጠና እንዲኖር የሚያስገድድ ነበር፡፡

ይህንን የዕዉቀትና ክህሎት ክፍተት ለመሙላት የሚያስፈልገዉ ትምሕርትና ስልጠና ለመስጠት

የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች የሪከርድ ባለሙያዎችን ወደነዚሕ አዲስ ነፃ የወጡ አገራት በመላክ ሥልጠናና

ድጋፍ ማድረግ፣ ወይም ወይም የተወሰኑ ባለሙያዎችን ሥኮላርሺፕና ፌሎሺፕ በመስጠት

እንዲሰለጥኑ ድጋፍ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ለሥልጠናዉ የሚሆነዉንም ገንዘግ ከራሳቸዉ ከቀድሞ ቅኝ

ገዢ ሀገራት ወይም ከዩኔስኮ ይሸፈን ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ ወጥነትና ተከታታይነት ሳይኖረዉ እስከ

70ዎቹ ዘለቀ፡፡ ከሳሓራ በታች ባሉት አገሮች የሪከርድ ሥራ አመራር ትኩረት አግኝቶ ተከታታይነት

ባለዉ መንገድ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ የተጀመረዉ በ1970ዎቹ ኢንተርናሽናል

ካዉንስል ኦቭ አረካይቭስ (ICA) እና ዩኔስኮ UNESCO በመተባበር የመጀመሪያዎቹን አካባቢያዊ


የማሰልጠኛ ተቋማት ሲከፍቱ ነዉ፡፡ በዚሕ ጊዜ የተከፈቱት ሁለት ተቋማት ለ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ አፍሪካ

አገራት ሴኔጋል ዉስጥ (1971) እና ለእንግሊዝኛ ተናጋሪ አገራት ደግሞ ጋና ዉስጥ (1975) ነዉ፡፡ የተቋማቱ

መከፈት ወደዉጭ አገር ልኮ ለማስተማርና ለማሰልጠን የሚወጣዉን ወጪ ለመቀነሥ እንደሚቀንስ

ታምኖበት ነበር፡፡ በነዚሕ ተቋማት የሚሰጠዉ ሥልጠና የአሕጉሩን ፍላጎት 30 ፐርሰንት የሸፍን ነበር

(Katuu, 2015)፡፡ ይሁን እንጂ ለተቋማቱ ሥራ ማስኬጃ ይሰጥ የነበረዉ ገንዘብ ድጋፍ በመቋረጡ ተቋማቱ

የሚሰጡት ሥልጠና መቀጠል አልቻለም፡፡

በመሆኑም እያንዳንዳቸዉ አገሮች ያለባቸዉን የተማረና የሰለጠነ የሪከርድ ሥራ አመራር ባለሙያ ችግር

ለመቅረፍ የባለሙያዎች ሥልጠና ፕሮግራሞች በየራሳቸዉ አገር እንዲጀመር ማድረግ ነበረባቸዉ፡፡ ኬንያ

ከፊል ሙያተኞች ማሰልጠኛ በናሽናል ፖሊቴክኒክ በ 1979 እ.ዩ.አ ጀመረች፡፡ እሷን በመከተል እነ ታንዛኒያ፣

ቦትስዋናና ኬንያ የስልጠና ፕሮግራሞችን ከፍተዉ ማስተማርና መሰልጠን ጀመሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛዎቹ

የአፍሪካ አገሮች፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ፣ የሪከርድ ሥራ አመራር ትምሕርት ከአጫጭር የስራ ላይ ስልጠና

ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲተ ድሕረ ምረቃ ትምሕርት ይሰጣል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዘርፉ የሚሰጡ ስልጠናዎች ሥራዉን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ክሕሎቶችን የሚያዳብሩ

ተግባር ተኮር መሆን አለባቸዉ ወይስ በዘርፉ ያሉ አእምሯዊ እዉቀቶችን የሚያስጨብጡ ትምሕርቶች

መሆን አለባቸዉ የሚለዉ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነዉ፡፡ እንደ ካቱ ((Katuu,

2009) በአፍሪካ በአብዛኛዉ ያለዉ አስተሳሰብ ሪከርድ ሥራ አመራር ባለሙያዎች ሥልጠና ሙያ ተኮር
መሆን አለበት የሚል ነዉ፡፡ ከዚሁ ጋረ ተያይዞ በዘርፉ የሚታይ ተግዳሮት ስልጠናዉና ገበያዉ ያላቸዉ

ግንኙነት ነዉ፡፡ ዩንቨርሲቲዎች በሪከርድ ሥራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር የሚሰጡትን ስልጠና

ለመቀጠል ሰልጣኞች ከተመረቁ በኋላ እዉቀታቸዉን የሚፈልግና የሚገዛ መኖሩን ማረጋገጥ

አለባቸዉ(Khayundi, 2011) ምክንያቱም “ስልጠናዉ ሥራ አጥ ለማድረግ ስላይደለ”፡፡

ካዩንዲ በደቡብ አፍሪካ ዩንቨርሲቲዎች አሰልጥነዉ በሚያወጡት የሰዉ ኃይልና በገበያዉ መካካል ያለዉን

ተዛምዶ አጥንቶ ገበያዉ ሰልጥኖ የወጣዉን የሰዉ ኃይል የሚፈልግ አለመሆኑን አግኝቷል፡፡ ይህ የሆነበት

ምክንያት ከ 90ዎቹ ወዲሕ እያደገ የመጣዉ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በብዙ መስሪያቤቶች

ዉስጥ ከዚሕ በፊት ይሰራበት የነበረዉን የመረጃ ሥርዓት እየቀየረዉ በመምጣቱና አሁን ያለዉ ስልጠና

ይሕንን አዲስ ፍላጎት ያገናዘበ አለመሆኑ አንዱና ዋናዉ ነዉ፡፡ የዩንቨርሲቲ ኮርሶች አንድ ጊዜ ከጸደቁ በኋላ

ለማሻሻል ጊዜ የሚፈጁ በመሆኑ ዩንቨርሲቲዎች ራሳቸዉን ከገበያዉ ፍላጎት ጋር አጣጥመዉ በመሄድ በኩል

ዘገምተኛ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

መመመመ መመ መመመመ መመመመ መመመመ

የሪከርድ ስራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር ሙያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየዳበረ የመጣ ሙያ

ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሥራዉ የሚጠይቃቸዉ ተግባራት የታወቁ ከመሆናቸዉም በላይ ማንኛዉም

የሪከርድ ሥራ አመራርን ተግባራዊ የሚያደርግ አገር ወይም ተቋም እንዲሰራባቸዉ የአገሮችን

መልካም ተሞክሮ መሰረት ያደረገ ደረጃ ወጥቷል (ISO 15489-2, 2001)፡፡ በመሆኑም ማንም

የሪከርድ ሥራ አመራር ፕሮግራም ያለዉ ተቋም የሪከርድ ሥራ አመራር ፕሮግራሞቹን ይዘትና

እነዚህን ለመስራት የሚያስፈልገዉ ክህሎትና እዉቀት ደረጃዎች አዉቆ እንዲሰራ ከፍተኛ

አስተዋጽኦ ያደርግለታል (Crockett & Foster, 2004)፡፡

በዚሁ የ አይ ኤስ ኦ ስታንዳርድ (2004) መሰረት ዋና ዋና የሪከርድ ሥራ አመራር ይዘቶች የሪከርድ

ሥራ አመራር ፖሊሲና ደረጃ ማዘጋጀት፣ በሪከርድነት መያዝ ያለባቸዉን የሥራ እንቅስቃሴዎችን

መለየትና በዚሁ መሰረት ሰንዶ መያዝ፣ ሪከርዶችን መመዝገብ፣ ሪከርዶችን በክፍል በክፍለ

መመደብ፣ የሪከርድ ሥርጭትን ማስተዳደር፣የሪከርዶችን እንደቅስቃሴ መቆጣጠርና መቆጣጠሪያ

ቴክኒኮችን ተግባራዊ ማድረግ፣ ሪከርዶችን ተደራሽነትና የማየት መመብትና ገደብ ማስተዳደር፣

የሪከርዶች አስተዳደር ሥርዓት/ሪከርድ ሲስተምስ/ መንደፍና መተግበር፣ የሪከርዶችን ቆይታ ጊዜ

ማስተዳደር፣ እንዲሁም የሪከርዶችን ምዘና መረጣና አወጋገድ ሥራዎች ሁሉ በአግባቡ መምራት


ዋና ዋናዎቹ የሪከርድ ሥራ አመራር ተግባራት ናቸዉ፡፡ በመሆኑም ማንኛዉም የሪከርድ ሥራ

አመራር ሥልጠና ተግባር እነዚሕን ተግባራት ለማከናወን የሚያስፈልገዉን እዉቀትና ክሕሎት

ማሥጨበጥ መሆን አለበት፡፡ በዚሕ አይነት ሥልጠና የሚገኘዉ ሙያ ሶስት ደረጃዎች አሉት

እነዚሕም ፓራ ፕሮፌሽናል (በፕሮፌሽናሎች ስር ሆነዉ) ማደራጀት፣ መግለጫ መስራት እና

የመሳሰሉ ሌሎች ስራዎችን የሚሠሩ ፣ ፕሮፌሽናሎች (የሪከርድ ሥራ አመራሩንና መዛግብት

አስተዳደሩን እለታዊ ሥራዎች የሚያቅዱ፣ የሚፈጽሙና የሚቆጣጠሩ)፣ እና ኃላፊነታቸዉ

ማስተዳደር፣ ማቀድና፣ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ግንኙነት ማድረግ የሆኑ ማናጀሮች ናቸዉ (Susan E.

Davis, 1989)፡፡

በመሆኑም እነዚሕን ባለሙያዎች ለማዘጋጀት የሚሰጡት የትምሕርትና ስልጠና ፕሮግራሞች

የተለያዩ ደረጃዎች አሏቸዉ፡፡ በአፍሪካ ዉሥጥ ብቻ እንኳን ባለሙያዎች የሚሰለጥኑባቸዉ

ሙያዎች ሰርተፊኬት፣ ዲፕሎማ፣ ድህረ ዲፕሎማ ሰርተፊኬት፣ የባችለር ዲግሪ፣ የድህረ ምረቃ

ዲፕሎማ፣ የማስተርስና የፒኤች ዲ ዲግሪ ፕሮግራሞች ይሰጣሉ (Katuu, 2009)፡፡


ዋቢ ጽሑፎች ዝርዝር

Crockett, M., & Foster, J. (2004). Using ISO 15489 as an Audit Tool. The Information

Management Journal, 7.

ISO 15489-1. INFORMATION AND DOCUMENTATION — RECORDS MANAGEMENT —

PART 1 (2004).

ISO 15489-2. Standard for Information and documentatio- Records management.

(2001).

Katuu, S. (2009). Archives and Records Management Education and Trainning: What

Africa Can Learn from Europe and North America. Information Development, 25(2),

133–146.

Katuu, S. (2015). The development of archives and records management education and

training in Africa – challenges and opportunities. Archives and Manuscripts, 43(2),

96–119.

Khayundi, F. (2011). Existing records and archival programmes to the job market. Journal

of the South African Society of Archivists, Vol. 44, 62–73.

Read, J., & Ginn, M. L. (2011). Records Management (9th editio). Mason,Ohaio.

Schaeffer, R. (1994). From Craft to Profession: The Evolution of Archival Education and

Theory in North America. Archiviera 37, 30–34.

SHEPHERD, E. (1998). Partnerships in professional education: a study in archives and

records management. Records Management Journal, 8(3), 19.


Stielow, F. J. (1990). The Practicum and the Changing Face of Archival Education:

Observations and Recommendations. Journal of the Society of Georgia Archivists,

8(1), 1–13.

Susan E. Davis. (1989). Archival Education: The next steps. The Midwestern Archivist,

XIV(1), 10.

Williams, C. (2006). Managing Archives: Foundations principles and practice. Oxford:

Chandos Publishing.

You might also like