You are on page 1of 5

የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን

የ 2012 ዓ.ም የቡድኑ


አመታዊ
የልማት ቡድን እቅድ
ሀምሌ 2011

ገንዳ ውሃ

መግቢያ

የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን ያለበትን ደረጃ በየሳምንቱ በመገምገምና በማስተካከል የቡድኑ
አባላት ለዜጎች ቀልጣፋ ፣ ዉጤታማና ተጠያቂነት ያለው አገልግሎት መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ ስለሆነም
የሲቪል ሰርቪስ የለውጥ ፕሮግራም እውን ለማድረግ ሁሉም የልማት ቡድኑ አባላቶች ለታቀደዉ እቅድ
መሳካት ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ አሰፈላጊ ነዉ፡፡

የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የ 2012 የልማት ቡድን ዕቅድ Page 0
በአጠቃላይ ይህ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የ 2012 በጀት ዓመት የልማት ቡድኑ እቅድ ውስጥ
የእቅዱ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች፣ መርሆች፣ ዓላማ፣ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ስጋቶች፣ መፍትሔዎችና
የልማት ቡድኑ አባላትን ስም ዝርዝር አካቶ የታቀደ ነው፡፡

ተልዕኮ፡- በቡድኑ ቀልጣፋና ዉጤታማ አደረጃጀት አሰራርና የሰዉ ሀይል በመገንባት ተጨባጭ
ለውጥ

ማምጣትና መልካም አስተዳደር ማስፈን የሚያስቸል አቅም መገንባት ፡፡

ራዕይ፡- ተግባራት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መፈፀማቸውና አለመፈፀማቸውን በልማት


ቡድን የሚወያይ ባለሙያ

ተፈጥሮ ማየት ፡፡

የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የ 2012 የልማት ቡድን ዕቅድ Page 1
እሴቶች

 ለዉጥ ናፋቂና አራማጅ እንሆናለን ፡፡


 የስራ ፍቅር ከበሬታና ስነ-ምግባር መለያችን ይሆናል
 ለተገልጋዮች /ለዜጋዉ/ ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት መለያችን ባህላችን እናደርጋለን
 ግልጽነትና ተጠያቂነት እናሰፍናለን
 ፍትሃዊነትን ማስፈን የመልካም አስተዳደር ገጽታችን ዋነኛ አካል መሆኑን
እንገነዘባለን
 ሁሌም ተማሪና አስተማሪ መሆን እንደሚገባን እንገነዘባለን
 ቀልጣፋና ዉጤታማነትን እናረጋግጣለን

መርሆች

 12 ቱን የስነ-ምግባር መርሆች ማክበርና መከተል

 ከኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን


 ታማኝነትና ሚስጥር ጠባቂ መሆን
 ንብረትና በጀትን በአግባቡ መጠቀም
 የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻልና ተገልጋዮች እርካታ እንዲያገኙ የሚያስችል
ስርአት መፍጠር
 ሀቀኛ፣ገለልተኛና ሚዛናዊ የሆነ አገልግሎት መስጠት
 የቅሬታ አቀራረብ ስርአቱን ዉጤታማ ማድረግ
 የተለያዩ መረጃወችን ግልፅ በሆነ መንገድና ቦታ ማስቀመጥ መቻል
 በመልካም የስራ ዲሲፒሊን የታነፀ ሃይል መፍጠር

ዓላማ
 የቡድኑ አባላትን ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት ማሳደግ
 የቡድኑ አባላትን የሳምነቱን ተግባር መገምገምና ማረም
 የልማት ቡድኑ አደረጃጀቱን በማጠናከር ተከታታይነት ያለው ግምገማ ፣ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ
የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማረጋገጥ

በልማት ቡድን የመደራጀት አስፈላጊነት

የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የ 2012 የልማት ቡድን ዕቅድ Page 2
የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ስኬት በተሻለ ፣በተፋጠነ፣ ተደራሽ በሆነና ዘላቂነት
ባለዉ መንገድ ለማስቀጠል በቡድን መሪውና በባለሙያዉ በኩል እየታየ ያለዉን የአፈፃፀም
ክፍተት በማስወገድ የሚፈለገዉን ለዉጥ ለማምጣት በተደራጀና ወጥነት ባለዉ መንገድ
መንቀሳቀስ አስፈላጊ በመሆኑ ነዉ ፡፡ ዉጤት የሚመዘግቡት ባላዉ የስራ ህብረት እንጂ
በተናጠል እንዳልሆነ ሁሉም የቡድኑ አባላት በመተማመን ነው፡፡ በቡድናችን የምናከናዉናቸዉ
ተግባራት ዉጤታማ የሚሆኑት በቡድኑ ዉስጥ ያለነዉ ሰራተኞች በምናደርገዉ የሥራ
እንቅስቃሴ በመሆኑ የልማት ቡድን አደረጃጀት አስፈላጊ ነዉ ፡፡

የሂደቱ ሰራተኞች በልማት ቡድን የተደራጁበት አግባብ

በቡድኑ ዉስጥ የቡድን መሪዉን ጨምሮ አራት /4/ ሰራተኞች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ
ሰራተኞች በአንድ የስራ ቡድን ተደራጅተዋል ፡፡ ስለሆነም ይህ የስራ ቡድን በቡድን
መሪዉ የሚመራ ሆኖ በአንድ የልማት ቡድን የተደራጀ ነዉ ፡፡

በልማት ቡድኑ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት


 አንድን ተግባር የባለሙያው ሳይሆን የቡድኑ ተግባር አድርጎ በመረዳት በልማት ቡድን መፈፀም
 በወረዳችን የትምህርት ተቋማቶች ውስጥ እየታዩ ያሉ ጥንካሬዎችንና እጥረቶችን እየለዩ የጋራ
በማድረግ ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ስርዓት በማምጣት ትግል ማድረግ
 የልማት ቡድን ውይይት ዓርብ ከ 11፡30 ስዓት ጀምሮ በሁለት ሳምንቱ የተሰሩና ያልተሰሩ ስራዎችን
ግምገማ ማድረግ የቀጣይ 2 ሳምንታት ተግባራትን ለይቶ ማስቀመጥ
 እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ርዕሶችን በመምረጥ መወያየት ፡፡
 የልማት ቡድን ውይይት በዓመት ውስጥ 24 ጊዜ ውይይት ማድረግ

እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና ስጋቶች


ምቹ ሁኔታዎች
 በቡድኑ ያሉ ሰራተኞች ወጣትና በቀላሉ መግባባት የሚችሉ መሆኑ
 አብዛኛዎቹ የቡድኑ ሰራተኞች በቡድን የመስራት ልምድ የተሻለ መሆኑ
 አደረጃጀቱን ዉጤታማ ለማድረግ የሂደቱ ሰራተኞች በየሳምንቱ የሚያደርጉት
የስራ ግምገማ እየተጠናከረ መምጣቱ

የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የ 2012 የልማት ቡድን ዕቅድ Page 3
 ሁሉም ባለሙያዎች ለስራ አመች በሆኑ የ BSC /ዉጤት ተኮር ሰርዓት/
መታቀድና ባለሙያዉ በዉጤት ለመለካት ግቦችን ቆጥሮ በመረከብ ተግባራት
ሳይንጠባጠቡ መፈፀም የሚችሉበትን ሰርዓት መዘርጋት መቻሉ
ስጋቶች
 የልማት ቡድኑ ውይይት የአባላቱ ቁጥር አንድ ሲሆን፣ በመስክ ስራ፣ በህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት፣
በደራሽ ስራ፣ በስልጠና እና በሰብስባ ምክንያት ተከታታይነትና ወጥነት ላይሆን ይችላል ፡፡
መፍትሄ
 የልማት ቡድኑ ዉይይት ተከታታይነት ያልሆነበትን ቀን ተጨባጭ ምክንያት በቃለጉባኤ እንዲሰፍር
ማድረግ ፡፡

የልማት ቡድኑ አባላት ስም ዝርዝር


1. አታላይ ሹሜ…….. የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ ------------------- ስብሳቢ
2. አትንኩት አዛናው……. የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ባለሙያ ------------------ ፀሐፊ
3. ግርማ ከበደ ……..የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ባለሙያ ---------------------------አባል
4. ወ/ሮ እስከዳር ደሳለኝ…….. የጽህፈትና ቢሮ አስተዳደር ባለሙያ ------------------------አባል

የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የ 2012 የልማት ቡድን ዕቅድ Page 4

You might also like