You are on page 1of 2

 

ዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሳ/ Abduljelil Ali


Favorites · 28m ·

ሸገርና እስላም __ቅንጭብጭ ሃሳቦች


★★★// //★★★
(በዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ)
[ ] ሸገር ሲቲ የምትገኘው በሽዋ ውስጥ ብቻ ነው
[ ] ለሽዋዋ ሸገር ሲቲ አርሲ፣ ባሌ፣ ሀረርጌ፣ ጅማ፣ መቱ ወዘተ ተወላጆች አይደሉም።
[ ] በሽዋዋ ሸገር ሲቲ ቤታቸው የማይፈርስባቸው የሽዋዎቹ የሸገር ሲቲ ቀጠና ተወላጆች እና ህጋዊ ካርታ ያላቸው ብቻ ናቸው።
[ ] ሽዋ የቀድሞ የሽዋ ሙስሊም ሱልጧኔት ግዛት የነበረ የወርጅዎች አገር የነበረ ቢሆንም በንጉስ ሳህለ ስላሴ ሽዋ እና በሸነን ቤት ሽዋ ኦሮሞዎች
የዘመናት መስፋፋት ሳቢያ የኦርቶዶክስ አማራዎችና የኦርቶዶክስ ኦሮሞዎች ግዛት ሆኗል። ምን ለማለት ሽዋ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በዝ ቀጠና ነው
ለማለት ነው።

[ ] የዲሞግራፊ ለውጥ በተለየ የፖለቲካ ተልእኮና ስልጣን ካልቀየርከው በስተቀር በተፈጥሯዊ ሂደት የረጅም ጊዜ ጉዞ በመሆኑ የኢትዮጵያውያን
ሙስሊሞች በአዲስአበባማ በዛሬዋ ሸገር ሲቲ አካባቢ በመስፈር 2015 ላይ ላለው የዲሞግራፊ መጠን የደረሱት በዝግመተኛው የተፈጥሮ አሰፋፈር
ሂደት ነው።
[ ] አዲስአበባ የተመሰረተችው በአፄ ምኒሊክ ስርአት በመሆኑ ቀዳማይ መስራች ህዝቦቿ ኦርቶዶክስ አማራዎች፣ ኦሮሞዎችና ትግሬዎች አመዛኞቹ
ናቸው።
[ ] እነዚህ ቀዳማይ መስራቾች የአዲስአበባን መሬት ባላባቶች ወይም ባለ ርስቶች ነበሩ።
[ ] በሂደት የነዚህ አካላት የስጋ፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካ፣ የአስተሳሰብ ተጋሪዎች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።
[ ] ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአዲስአበባ ውስጥ በመሬት ባለይዞታነትና በነዋሪነት ያላቸው የዴሞግራፊ አሀዝ እጅግ አነስተኛ ሆኖ ምእተ አመቱ
ተጋምሷል። የመሬት ከበርቴው መደብ አካል አልነበሩም። ሐረሪዎችና ስልጤ ጉራጌዎች በከፊል ወደ ከተማዋ ቀድመው ከገቡት ውስጥ ናቸው።
ወርጂዎች ነባር ባለ ይዞታዎች በመሆናቸው በሸገር ሲቲ ቀጠና ነበሩ።
[ ] የ1967ቱ የመሬት ላራሹ ህግ ሲወጣ በአዲስአበባ ከመሬት ከበርቴው መሬት ተነጥቆ ሲደለደል የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አዲስአበባ ቀጠና
ላይ በብዛት ስላልነበሩ የመሬት ድልድሉ ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም።
[ ] ድህረ ደርግ የአድስ አበባ መሬት ዋጋ እጅግ ውድ በመሆኑ አዲስ መጤ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መሬት ከቀድሞ ባለይዞታዎች ገዥዎች እንጅ
ሻጪዎች መሆን አልተቻላቸውምና የቻሉት በከፍተኛ ገንዘብ ሲገዙ ያልቻሉት ከከተማ ወጣ ብለው በዛሬው የሸገር ሲቲ ከገበሬ መሬት እየገዙ
ንብረት አፍርተዋል።
[ ] በአዲስ አበባ በቢሮክራትነት አሊያም የመጀመሪያው መሬት ከበርቴ ትውልድ ሆኖ መሬት ማግኘት ያልቻለው የኢትዮጵያ ሙስሊም አብዛኛው
በንግድና በመለስተኛ የግል ቢዝነሶች ላይ ተሰማርቶ ወደ አዲስአበባ ዘግይቶ የገባ በመሆኑ በስሞል ስኬል ሪተርን ከሚገኝ ገቢ/ትርፍ፣ ወይም አረብ
አገር በቅጥር ከሚገኝ ደመወዝ አዲስ አበባ ውስጥ መሬት ገዝቶ ንብረት ለማፍራት የከበደው ህዝበ ሙስሊም በአዲስ አበባ ዙሪያ ከገበሬ መሬት
እየገዛ ቤት እየገነባ ተስፋፍቷል።
[ ] በተያዘና በሞላ ከተማ ላይ ዘግይቶ የመጣው የኢትዮጵያ ሙስሊም በአዲስአበባ ዙሪያ መስፈሩ አማረጭ አልነበረውም።
[ ] በሂደትም በኦትዮጵያ ማእከል ላይ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ዴሞግራፊ ፕረዘንስ በትንሹም ቢሆኑ ሊወክሉ የሚችሉ ሙስሊሞች
በዘገምተኛው የአሰፋፈር ሂደት በአዲስአበባ አዳድስ መንደሮች (ምዕራብ አዲስአበባ) እና በአዲስአበባ ዙሪያ ተገኝተው ነበር።
[ ] እነዚህ የኢትዮጵያ ማእከላዊ እና ካፒታል ቀጠና ሙስሊሞች የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ማህበረ ፖለቲካና፣ ኢኮኖሚያዊ መብትና ግዴታ
ወሳኞችና አስፈፃሚዎች፣ አስረጋጮችና አስከባሪዎች ናቸው።

[ ] የሸገር ሲቲ ፕሮጀከት የጨረቃ /ህገወጥ ይዞታዎች ምንጠራ ተቀዳሚ ገፈት ቀማሾች ዘግይተው ወደ አዲስአበባ የመጡ እና አንድም ከተማዋ
ከሞላች በኋላ ሁለትም የከተማዋን የመሬት ዋጋ afford ማድረግ ያልቻሉ ወገኖች ናቸው።
[ ] በሌላ አባባል ዘግይተው ወደ አዲስአበባ ያቀኑና ለባለፉት 30 አመታት የተሰባሰቡልን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ወካይ ዲሞግራፊ ነው
የተመነጠረው ማለት ነው።
[ ] በቀጣይ ከማእከላዊው ኢትዮጵያ የተባረረው ሙስሊም ከሴንትራል ፓወሩ ተገፍቶ ወደ የዳርቻ ህዝብነት (peripherals) ይሆናል ማለት
ነው።
 

131 15 27

Like Comment Share

Most relevant

Write a comment…

John Robert James

Like Reply 25m

Suley man · Follow

Like Reply 11m

Sami Edi
ለቅሶ ብቻ ሆነን እንቅር!
ካልተደራጀን አንድነታችንን ካልያዝን የት ይቀርልናል
Like Reply 21m

ሱልጣን አህመድ · Follow


ክበርልኝ ወንድም!!
Like Reply 18m

Abu Adilah
እሺ የመፍትሄ ሀሳብ ስጥ !
Like Reply 16m

John Robert James


እጅህ ይባረክ!
Like Reply 27m

Hamidu Muhamed
ወይ ጉድ ዘንድሮ
Like Reply 23m

Alewi Bedru Gunchire


አብዱ ገልፀሕልኛልኮ!
Like Reply 19m

Hundachala Tolera
እቺ ጠጋ ጠጋ ሌላ እስከንድር ለመከተል ነው መሰለኝ፣ ለማንኛውም እኛ ሸዋ ተወላጆች የሙስሊሙ ጉዳት ጉዳታችን ብለን ነው
የሚናስበው እንጂ እንደ አንተ እና ህገወጥ ድርጊት ፈጻሚዎች ከፋፋይ አጀንዳ የለንም።
Like Reply 20m

1 Reply

Muna Muna

Like Reply 23m

Kassahun R. Gared
ቢሆንም እንደ ሞጣ አይሆንምi
Like Reply 20m

የደራው ረመጥ
ሸለመጥማጥ ዝም በል እባክህ
Like Reply 22m
Most Relevant is selected, so some comments may have been filtered out.

You might also like