You are on page 1of 4

ግርማ ካሳ - ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ አትጠራጠሩ #ግርማካሳ “ኢትዮጵያ

የመፍረስ አደጋ ተደቅኖባታል”...


facebook.com/ggkd60/posts/pfbid02hWQ85v9o7cLVH6dPoUGGQTiAXr6rxDRtvMerfhimJsYiKf8kpuFVLU1NMoJeRncXl

ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ አትጠራጠሩ #ግርማካሳ


“ኢትዮጵያ የመፍረስ አደጋ ተደቅኖባታል” የሚሉ አሉ፡፡ “ኧረ እንደው ፈርሳለች፣ ኢትዮጵያ እኮ የለችም” የሚሉም
አሉ፡፡ “ኢትዮጵያ ፈርሳለች”፣ “ልትፈርስ ነው” የሚለውን ለማየት መጀመሪያ “ኢትዮጵያ ማን ናት ?” ለሚለው
ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የስም ዝርዝር አለ፡፡ አገር ተብለው የተሰየሙ፣ የአገርነት እውቅና የተሰጣቸው አገሮችን
የያዘ፡፡ እዚህ የስም ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ አለች፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የሚባል አለ፡፡ በተባበሩት መንግስታት
ስም ዝርዝር ውስጥ እንደነበረችውና አሁን እንደሌለችው፣ እንደ ዩጎዝላቪያ ኢትዮጵያ አልሆነችም፡፡ በመሆኑም
ኢትዮጵያ አለች፣ አልፈረሰችም፡፡ ታማም፣ ቆስላም ቢሆን አሁንም አለች፡፡

“ወደፊት እንደ ዩጎዝላቪያ ልትፈርስ፣ ልትጠፋ ትችላለች ወይ ?” የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ መልሱ አትጠፋም
ነው፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንደተለየችው፣ የተወሰነ አካባቢዎች "ኢትዮጵያን አንፈልግም" በሚል ሊለዩ ይችላሉ፡፡
በሌላ በኩል እነ ኤርትራ፣ እነ ሶማሌላንድ ኢትዮጵያን ሊቀላቀሉ ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ድንበር አሁን ካለበት
ሊያንስ፣ ወይንም ሊሰፋ ይችላል፡፡ ድንበሩ ይቀያየራል እንጂ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ግን ትኖራለች፡፡ አትጠፋም፡፡

ለምሳሌ ከኢትዮጵያ የመገንጠል አጀንዳ የያዙ ኃይሎች የሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎችን እንመልከት፡፡ ህወሃት፣
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፣ ኦነግ የሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ነው ብዙ
“ኢትዮጵያን አንፈልግም፣ መለየት እንፈልጋለን” የሚሉ ድምጾች የሚሰሙት፡፡

ህወሃት የሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች


ህወሃቶች፣ ቀደም ሲል “ታላቋ ትግራይ” ከሚል ቅዠታቸው የተነሳ፣ ትግራይን ለመገነጠል ሃሳብ የነበራቸው
ቢሆንም፣ ከህዝቡ ተቃውሞ ስለገጠማቸው፣ ያንን ሃሳባቸው ወደ ጎን ያደረጉበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡ አዲስ አበባን
ከመቆጣጠራቸው ከሁለት አመታት በፊት፣ ሙሉ ትግራይን ተቆጣጥረው የነበረ ቢሆንም፣ ነጻ አገር የሆነች
ትግራይን አላወጁም፡፡ በአንጻሩ የማረኳቸውን በማሰባሰብ፣ ራሳቸውን ኢሕአዴግ የሚል ስያሜ በመስጠት ነው፣
በኢትዮጵያ ደረጃ ስልጣንን የጨበጡት፡፡ በትግራይ ህዝብ ውስጥ ስር የሰደደው የኢትዮጵያዊነት ስሜት የህወሃቶች
የመገንጠል አጀንዳ ወደፊት እንዳይሄድ አድርጎታል፡፡

ህወሃቶች ከአራት ኪሎ ተገፍተው ሲወጡና ከጥቅምት 24 2013 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 23 2015 ዓ/ም የተደረገው
ጅምላ ጭራሽ ጦርነት ተከትሎ፣ በርካታ የትግራይ ወገኖች፣ በትግራይ ላይ ለደረሰው ሰቆቃ ዋና ምክንያቱ ህወሃቶች
መሆናቸውን ዘንግተው፣ “ከሌሎች ማህበረሰባት ጋር እንዴት መኖር እንችላለን ?መለየት አለብን" የሚል አመለካከት
ሲያንጸባርቁ ታዝበናል፡፡ የኢትዮጵያን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ትተው የቬትናም የሚመስለውን ቢጫና ቀይ
አርማ እያውለበለቡ፡፡

ሆኖም እነዚህ ወገኖች ፣ አንደኛ፣ ከስሜታዊነት የተነሳ፣ በትግራይ ያለውን ነባራዊ የኢኮኖሚና የመልካምድር ሁኔታ
ሳያገናዝቡ፣ አንድ ሶስተኛ የሚሆኑ የትግራይ ወገኖች የሚኖሩት በተቀረው ኢትዮጵያ መሆኑን ያላሰቡና ትግራይ
የኢትዮጵያ የታሪክ መሰረት መሆኗን የዘነጉ ናቸው፡፡ ሁለተኛ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡

1/4
አሁን ሜዳ ላይ ባለው ሁኔታ፣ ትግራይ ከውጭ አገር ጋር ወሰን የላትም፡፡ ትግራይ ነጻ አገር መሆን አለባት ብለው
የሚያስቡት እነዚህ ጥቂት መላው የትግራይ ህዝብን የማይወክሉ ወገኖች፣ ወልቃይት ጠገዴና ካፍታ ሁመራ
የትግራይ አካል ነው በሚል ስሌት ነው፡፡ ያለነወልቃይት እነርሱም ራሳቸው የትግራይ ነጻ አገር መሆን ተግባራዊ
ሊሆን እንደማይችል ያውቃሉ፡፡

“እነ ወልቃይት ወደ ትግራይ የመግባት እድላቸው ምን ያህል ነው ?” ብለን ብንጠይቅ ደግሞ፣ መልሱ "የማይቻል
ወይንም በጣም የጠበበ ነው" የሚል ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ በጦርነት ደቋል፡፡ የትግራይ ወገኖች ጦርነት
ሰልችቷቸዋል፡፡ ባለፈው ጦርነት አንድ አምስተኛ ተጋሩ እንደ ቀላል ነገር አልቋል፡፡

ከዚህ በኋላ እነ ወልቃይትን መልሰን ወደ ትግራይ በኃይል እንወስዳለን ብለው ህወሃቶች ከተነሱ፣

# አንደኛ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ድጋፍ ያገኛሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡

# ሁለተኛ የተወሰነ ድጋፍ አግኝተው ወታደራዊ አቅማቸውን ቢያፈረጥሙም፣ እነ ወልቃይት የጎንደር አካል ናቸው
የሚሉ የአማራ ኃይሎችም የታጠቁ፣ የተደራጁና የሰለጠኑ እንደመሆናቸው በውጊያ አሸንፎ መልሶ እነ ወልቃይትን
መቆጣጠር አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ እንደገና መቶ ሺሆችን ከማስጨረስ ውጭ ምንም አይነት ፋያዳ አያመጣም፡፡

# ሶስተኛ እድል ቀንቷቸው ህወሃቶች አሸንፈው እነ ወልቃይትን ቢይዙ ደግሞ በሰላም መኖር አይችልም፡፡ ሁልጊዜ
ከአማራው ኃይሎች ጋር በጦርነት ውስጥ ነው የሚዘፈቁት፡፡

በመሆኑም የትግራይ መገንጠል ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ነው፡፡ የኢትዮጵያ መሰረት የሆነችው ትግራይ መቼም
ከኢትዮጵያ አትለይም፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የሚንቀሳቀስንባቸው ቦታዎች


የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የሚሏቸው ላለፉት አምሳ ምናምን አመታት ኦሮሚያ የሚሉትን ነጻ አገር ለማድረግ
ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው፡፡ ኦነጎችና ኦነጋዊ አስተሳሰብ ያላቸው እንደ ኦህዴድ/ኦሮሞ ብልጽግና ያሉ፣ በራሳቸው
ትግል አሸንፈው ወደ ስልጣን መምጣት ያልቻሉ ናቸው፡፡ ኦነጎች ከሰላሳ አመታት በፊት ወደ ፊት እንዲመጡ
ያደረጓቸው፣ ህወሃቶች ነበሩ፡፡ ከስድስት አመታት በፊት ኦህዴዶች እነ እነ ዶር አብይ አህመድ ወደ አራት ኪሎ
እንዲገቡ ያደረጋቸው፣ በዋናነት ብአዴኖች እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ነበሩ፡፡ ኦህዴዶች “ኢትዮጵያ” እያሉ
በማታለላቸው፡፡

እነዚህ የኦሮሞ ብሄረተኛ ድርጅቶችና ብሄረተኞች ታላቋ ኦሮሚያ የሚሏትን ለመመስረት፣ ኢትዮጵያ መበታተን
አለባት ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊነትን የሚያንጸባርቁና የሚያሳዩትን ጉዳዮች ማጥፋትና መቀየር
ትልቁ ስትራቲጂያቸውም ነው፡፡

አዲስ አበባ የኢትዮጵያዉያን ትስስርና አንድነት ምልክት የሆነች ታላቅ ከተማ ናት፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
የሚንቀሳቀሰው በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ነው፡፡ የኦሮሞ ብሄረተኞች አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት ብለው ነው
የሚያምኑት፡፡ አዲስ አበባን፣ ሊመሰርቷት ያሰቧት፣ “ታላቋ ኦሮሚያ” ዋና ከተማና እምብርት አድርገው ነው
የሚያሰቧት፡፡ አንድ ወቅት ጃዋር መሐመድ ፊንፊኔ የሚላት አዲስ አበባ የኦሮሚያ ልብ እንደሆነች ነበር የገለጸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን የኦሮሞ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞንን እንደ ምሳሌ ብንወስድ ፣ አብዛኛው ነዋሪ ኦሮሞ ያልሆነ ነው፡፡
በዚያ የሚኖሩ ኦሮሞዎችም፣ አጤ ሚኒሊክን የሚወዱ የቱለማ ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ በሚሲዮናዉያን በነ ሲያድ ባሬ
አይምሯቸው በኢትዮጵያ ጥላቻ የተመረዙ ፣ መሰረታቸው ምእራብ ወለጋና ሃረርጌ የሆኑ ኦነጎች ያመጡትን ዘረኛ
የጥላቻና የመገንጠል ፖለቲካ የማይደግፉና የሚቃወሙ፡፡

2/4
ታላቋ ኦሮሚያ እውን እንድትሆን አዲስ አበባና አዲስ አበባ ዙሪያ ያለው ማህበረሰብ በዲሞግራፊ፣ በቋንቋ፣ በባህል
ኦሮሞን መመሰል አለበት ብለው ያምናሉ፡፡ የዚህን አካባቢ ዴሞግራፉ ለመቀየር፣ ኦነጋዊና ጸንፈኛ አመለካከት
ያላቸው እንዲበዙ ለማድረግ፣ ከሌሎች አካባቢዎች የኦነግ አስተሳሰብ ያላቸውን ኦሮሞዎች በማስፈር፣ በዚያ ያሉ
ወጣት የቱለማ ኦሮሞዎችንም ኦነጋዊ አስተሳሰብ እንዲይዙ የፕሮፖጋንዳ ስራ በመስራት ዘረኛ አላማቸውን
ለማሳካት ሞክረዋል፡፡

ሆኖም ከሌሎች አካባቢዎች ፣ ከአማራ ፣ ከደቡብ፣ ከትግራይና ከመሳሰሉት ክልልች ወደ አዲስ አበባና አዲስ አበባ
ዙሪያ የሚመጣው ህዝብ ቁጥር በጣም ትልቅ ስለሆነ፣ ዴሞግራፊውን የመቀየር ሁኔታ እንዳሰቡት አልሄደላቸውም፡፡

ያ ብቻ አይደለም፣ በኦሮሞ ክልል ዘረኛና አፓርታይዳዊ የሆነ አሰራር ስለሆነ ያለው፣ ኦሮሞ ባልሆኑት ማሀብረሰባት
ላይ በነ ባሌ፣ አርሲ፣ ወለጋ፣ ሃረርጌ ወዘተ የሚፈጸመው ግፍና ናዚዛዉ አሰራር፣ ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ብዙዎች ከነ
አርሲ፣ ባሌ፣ ወለጋ፣ ሃረርጌ ከመሳሰሉት ጥለው መኖሪያቸውን አዲስ አበባና እንደ ናዝሬት ባሉ አካባቢዎች ነው
ያደረጉት፡፡ ሃረር ይኖሩ የነበሩ አማራዎች፣ ጉራጌዎች ቀላል የማይባሉ ሃረርን ለዘረኞች ጥለው፣ ወደ አዲስ አበባና
አዲስ አበባ ዙሪያ መጥተዋል፡፡

የኦሮሞ ብሄረተኛ ፖለቲከኞች በአዲስ አበባ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖረውን ማህበረሰብ ዴሞግራፊ መቀየር
ስላልቻሉ፣ ተስፋ ቆርጠው፣ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ቤቶችን እያፈረሱ ለማፈናቀል እስከመሞከር፣
ከሌሎች አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ ዜጎች እንዳይገቡ እስከማድረግ የደረሱበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖረው ማህበረሰብ የኦሮሚያ አካል መሆን አይፈልግም፡፡ ምናልባት ወለጋና
አርሲ የመሳሰሉ አካባቢዎች የሚኖሩ “ኦሮሚያ ወይም ሞት” ቢሉም፣ የአዲስ አበባና የአዲስ አበባ ዙሪያ ህዝብ ዞር
በሉ ነው የሚላቸው፡፡ በመሆኑም ኦሮሚያ የምትባለው ክልል ለሁለት ትከፈላለች ማለት ነው፡፡

በአጭሩ አነጋገር የኦሮሞ ብሄረተኞች ከአስራ አምስት ሚሊዮን በላይ በሚሆነው የአዲስ አበባና አዲስ አበባ ዙሪያ
ህዝብ ተቀባይነት የለቸውም፡፡ ይህ ህዝብ በልቡ ፋኖ የሆነ፣ ዘረኝነትን የሚፀየፍ፣ ኢትዮጵያዊነት ያነገበ ነው፡፡ ይህ
ህዝብ፣ ለሕወሃት ከነበረው ተቃውሞና ምሬት፣ አሁን በኦሮሞ ብልጽግናና በአስተሳሰብ የኦሮሞ ብልጽግ]ና ታላቅ
ወንድም በሆነው ኦነግ ላይ በመቶ እጥፍ ነው ጥላቻና ምሬቱ የጨመረው፡፡ በዚህ ሕዝብ ከኦህዴድና ኦነግ ጋር
በማስተያየት ህወሃት እንደ መልዓክ መታየት የጀመረችበት ሁኔታ ያለው፡፡

አዲስ አበባና አዲስ አበባ መቼም የኦሮሞ ክልል አካል አትሆንም፡፡ በአዲስ አበባ ዚሪያ ያሉ እንደ ናዝሬት፣ ደብረ ዘይት
ያሉ የኦሮሞ ክልል አካል መሆናቸው ይቀራል፡፡ ያለ አዲስ አበባ፣ ያለነ ናዝሬት፣ ታላቋ ኦሮሚያ የምትባል ነገር
አትኖርም፡፡ የኦሮሞ ክልል ይፈርሳል፡፡ የሌለ ። የፈረሰ ነገር ደግሞ አገር ሊሆን አይችልም፡፡

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር የሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች


“ታላቋ ሶማሊያ” በሚል የመስፋፋት ፖሊሲ፣ በሲያድ ባሬ ጊዜ፣ ኦጋዴንን ወደ ሶማሊያ ለመጠቅለል ያሰበ ተስፋፊ
የሶማሌ ብሄረተኝነት የወለደው ጦርነት ተደርጎ ነበር፡፡ የሲያድ ባሬን ሞት ተከትሎ፣ እንኳን ሶማሊያ ልትሰፋ
እንደው የተበታተነችበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው፡፡ ሚሊዮኖች ሶማሌዎች በርስ በርስ ጦርነቱ ተሰደዋል፡፡
ብዙዎችም አልቀዋል፡፡ በስንት መከራ ነው፣ እንደውም በኢትዮጵያውያን ጣልቃ ገብነት ሞጋዲሾ ልትረጋጋ
የቻለችው፡፡ ዋና ከተማዋን ሃርጌሳ አድርጋ ሶማሌላንድ ነጻነቷን አወጀች፡፡ ዋና ከተማዋን ገራዌ አድርጋ ፑትላንድ፣
እንዲሁም ዋና ከተማዋን ባድዋ አድርጋ ጁባ ላንድ ራስ ገዝ ሆኑ፡፡ ፑትላንድና ጁባላንድ፣ በአሁኑ ወቅት ነጻ አገር
ባይሆኑም የምጋዲሾ እጅ እንዲበረታባቸው አይፈልጉም፡፡ በአጭሩ አነጋገር ሞቃዲሾ ያለው የሶማሊያ መንግስት
እጅግ በጣም የተዳከመ በማንኛውም ጊዜ ሊፈርስ የሚችል ነው፡፡

3/4
ከዚህም የተነሳ በሞቃዲሾ ይደገፍ የነበረው ኦብነግ፣ ሶማሊያ የምትባለው አገር ራሷ ችግር ላይ ስላለች፣ አንደኛ
ድጋፍ የሚሰጠው የለም፡፡ ሁለተኛ ኦግዴንን ገንጥሎ ከሶማሊያ ጋር ሊቀላቅል አይችልም፡፡ ከዚህም የተነሳ የኦብነግ
ወታደራዊ እንቅስቃሴ ብዙ ርቀት ሊሄድ አልቻለም፡፡

ሌላው የኦብነግን ሕልም መቃብር ውስጥ የከተተው ደግሞ ከኦጋዴን ጎሳ ውጭ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሶማሌዎች
ናቸው፡፡ ኦብነግ በዋናነት ከኦጋዴን ጎሳዎች የተወጣጣ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አሁን የሶማሌ መስተዳደር ሙስጠፌ
ኦማር ከኦጋዴን ጎሳ ሲሆን የሶማሌ ብልጽግና ሊቀመንበር አህመድ ሺዴ ደግሞ ቦረና አካባቢ ከሚኖሩ የጋሪ
ማህብረሰብ የመጣ ነው፡፡

ጅጅጋ ከተማን ጨምሮ፣ ከጅጅጋ በስተስሜንና በስተምስራቅ የሚኖሩ የሶማሌ ጎሳዎች በዋናነት የድሬና የኢሳቅ
ጎሳዎች ናቸው፡፡ ኢሳዎች፣ ገደቡርሲዎች፣ ኦሮሞኛ ተናጋሪ የሆኑ ጉርጉራዎች የድሬ ጎሳ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ወደ
ሶማሌላንድ ድንበር አካባቢ ያሉ ደግሞ ኢሳቆች ናቸው፡፡

በሶማሌላንድና በኢትዮጵያ መካከል ላለፉት አስርተ አመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚና የንግድ እንቅስቃሴዎች ነው
ያሉት፡፡ የበርበራ ወደብ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ትልቅ ጥቅም እየሰጠች ነው፡፡ ከጂጂጋ፣ በቶጎ ጫሌ፣ ሃረጌሳ
አድርጎ በርበራ ትልቅ አስፋልት መንገድ ተዘርግቶ፣ በዚያ ትላልቅ የጭነት መኪናዎች በስፋት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ያንን
ተከትሎ በዚያ መንገድ መስመር ባሉ ከተሞች፣ ያሉ ምግብ ቤቶች፣ አልቤርጎዎች ወዘተ የገቢ ምንጭ እያገኙ ነው፡፡
በአጭሩ በዚያ መስመር ያሉ ሶማሌዎች በሃረጌሳና በአዲስ አበባ መካከል ባለው ግንኙነት የኢኮኖሚ፣ የንግድ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡፡ በመሆኑም ወደ ኋላ የሚመልሳቸውን የኦብነግ የመገንጠል ጥያቄም
አይቀብሉም፡፡

ኦብነግ ኦጋዴንን ልገንጥል ቢል እንኳን፣ ከፊቅ ከተማ በስተሰሜን ያሉ፣ ኢሳዎች፣ ገደቡርሲዎች፣ ኢሳቆችና
ጉርጉራዎች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች፣ ጂጂጋ ከተማን ጨምሮ ፣ ሶማሌላንድ ከሶማሊያ እንደተለየችው፣
ከተቀረው የሶማሌ ክልል ይለያሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በብዛት በአንድ በኩል ኦሮሞነትም የሚያጸባርቁ ጋሪዎችና
ገብራዎች የሚኖሩባቸው፣ በደቡብ ምእራብ ሶማሌ ክልል የሚኖሩ እንደ ሊበንና ዳዋ ያሉ ዞኖችም፣ የኦብነግን አጀንዳ
አይቀበሉም፡፡

ስለዚህ ኦብነግ ልገንጥል ብሎ ከተነሳ አሁን የሶማሌ ክልል በሚባለው፣ ብዙ በኢኮኖሚ ደካማ የሆነውን አንድ ሶስተኛ
ክፍል ብቻ ነው ይዞ ሊገነጠል የሚችለው፡፡ ይህ ደግሞ አዋጭ ስላልሆነ፣ የኦጋዴን ጎሳ አባላትም በኢትዮጵያ ስር
መቀጠል ነው የምንፈልገው በሚል የኦብነግን አጀንዳ ውድቅ እያደረጉት ነው፡፡ የኦጋዴን ህዝብ ድጋፍ
ስላልሰጣቸውም ነው፣ ኦብነጎች የትም መድረስ ያልቻሉት፡፡ ህዝብ ያልደገፈው የትም መሄድ ምንም ማድረግ
ስለማይችል፡፡

ስለዚህ የሶማሌ ክልል ወይንም የተወሰነው ፣ የኦጋዴን ጎሳዎች የሚኖሩበት ኦጋዴን የሚባለው የሶማሌ ክልል
ከኢትዮጵያ የመለየት እድሊ እጅግ በጣም የጠበበ ነው፡፡

በመጨረሻ አይሆንም እንጂ፣ እንደው የትግራይ ጽንፈኛ ፖለቲከኞች፣ ኦነጎችና ኦብነጎች የፈለጉት ቢሆንና ፣ ከሸዋ
ውጭ ያሉ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች፣ ትግራይና የሶማሌ ክልል ነጻ ወጥተናል ቢሉ፣ ሌሎች ክልሎች፣ ኩታ ገጠም
ስለሚሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ይቀጥላሉ፡፡

4/4

You might also like