Professional Documents
Culture Documents
በጎፋ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ፆሊንቶ መጽሔት በየዓመቱ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ሲሆን የዘንድሮው ቁጥር-2
መጽሔት የጎፋ ጋዜ ማስቃላን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ የመጽሔቱ ይዜት በአራት ክፍሎች የተዋቀረ በመሆኑ
ክፍል አንድ የተለያዩ አካላት ያስተላለፉት መልዕክት፤ ክፍል ሁለት የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች ታሪክ፤ ክፍል ሶስት የባህል አምድ
ሆኖ በውስጡ የተለያዩ የባህላዊ ክዋነና ስርዓት ያካተተ ነው፡፡ የመጨረሻው ክፍል ደግሞ ኢኮኖሚያዊ አምድ ሆኖ የዞኑን
ኢኮኖሚያዊ አቅሞች በተመጠነ መልኩ ያካተተ በመሆኑ ለአንባብያን መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይታመናል፡፡
በመጨረሻም በመጽሔቱ አዘገጃጀት ላይ አንባብያን የሚሰጡትን አስተያየት ለመቀበልና በቀጣይ ዝግጅታችን ለማካተት
ጠቃሚ በመሆኑ ማንኛውንም አወንታዊም ሆነ አሉታዊ ጎን አስተያየት ከአንባቢያን እንጠብቃለን፡፡
አዘጋጆች
ምስጋና
ለዚህ መጽሔት ዝግጅት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት፤ መረጃዎችን በመስጠት፤ የእርማት ሥራዎችን በመሥራትና
በጽሑፍ ሥራ ላገዙን ሁሉ የላቀ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ በተለይ ደግሞ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደርና የዞኑ ባህልና ቱርዝም
መምሪያ ከሚመለከታቸው የመንግስት ኃላፊዎች ጋር በመሆን አስፈለጊውን በጀት በመመደብና ትኩረት በመስጠት
ላደረጉልን አስተዋጽዖ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
መልካም ንባብ
ክፍል አንድ
መልዕክቶች
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ጌትነት በጋሻው መልዕክት
ውድ የዞናችን ሕዝቦች ባለፉት አራት ዓመታት በተለይም ከ 2013 ዓ.ም ጀምሮ የውስጥም ሆኔ የውጭ ታሪካዊ
ጠላቶቻችን የተጀመረውን የለውጥና ብልጽግና ጉዞ ራዕይ ለማደናቀፍና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕቅድ ይዘው
የተንቀሳቀሱበት ጊዜ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በማጠናከር የጠላቶቻችን እኩይ ሴራ በማክሸፍ
ኢትዮጵያ በአሸናፊነት እንድትቀጥል የራሳችሁን የማይተካ ሚና በሀገር ደረጃ መክፈላችሁ ሁሌም ሲታዎስ ይኖራል፡፡
የዘንድሮው የጎፋ ጋዜና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላን በዓልን ልዩ የሚያደርገው ነገር ብኖር፤ በዞናችን የወቅቱን የአየር ንብረት
ለውጥ ተከትሎ በተከሰተው ድርቅና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ያስከተሉት ከፍተኛ ተጽዕኖዎችን በመቋቋም
በሀገራችን ኢትዮጵያ በአሸባርው የህይዋት ቡድን የተደቀነውን የ 3 ኛ ጊዜ ጦርነት ለመመከት ህዝባችን የራሳቸውን
ፈታኝ ችግሮችን ወደ ጎን በመተው ሀገርን በማስቀደም ለጀግናው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት እንደከዚህ ቀደሙ
ጽኑ ደጄንነቱን እያሳዬ በሚገኝበት ወቅት ላይ ማክበር መቻላችን ነው፡፡
ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ በይፋ የተደራጀው እንዲሁም ከለውጡ ትሩፋቶች መካከል አንዱ የሆነው የጎፋ ዞን መደራጀቱን
ተከትሎ የለውጡ መንግሥት በሰጠው ዕድል ሕዝባችን ለዘመናት ሲያነሷቸው የነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር
ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል። በሀገራችን ብሎም በአካባቢያችን ሁለንተናዊ ለውጥ፣ልማትና እድገት ማምጣት
የሚቻለው ሁላችንም ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን የዞናችን አነድነት በማስጠበቅ የአከባቢውን እምቅ አቅም
በማጎልበት በ 2015 ዓ.ም በሁሉም የልማት ዘርፎች ተወዳዳርና ብቁ ሆነው እንድገኙ በዚህ አጋጣም መልዕክተን
ለማስተላለፍ እወዳለው፡፡
በድጋሚ እንኳን የጎፋ እና እና ኦይዳ ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ የሆነው ጋዜ ማስቃላ እና ዮኦ ማስቃላ በዓል በሠላም
አደረሳችሁ እያልኩኝ፣አዲሱ ዓመት የሠላም፣የፍቅር፣የስኬት፣የልማትና የብልጽግና፣የበጎነትና የመተሳሰብ ዓመት
እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልጻለው።
አቶ ድንበሩ ድርቤ ዲላ
በሁለቱ ብሔረሰቦች ዘንድ በየዓመቱ በወርሃ መስከረም የሚከበረው የጎፋ ብሔረሰብ "ጋዜ ማስቃላ" እና የኦይዳ
ብሔረሰብ "ዮኦ ማስቃላ ክብረ በዓል አንዱ ሲሆን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል። በጎፋ እና እና ኦይዳ
ብሔረሰቦች ዘንድ በየዓመቱ በደማቅ ባህላዊ ስነስርዓት የሚከበረው የመስቀል በዓል አከባበር በአለምአቀፍ ደረጃ እውቅና
እንዲያገኝና በማይዳሰሱ ቅርሶች እንዲመዘገብ መምሪያው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። በመግቢያው
እንደገለጽኩት የጎፋ እና ኦይዳ ሕዝቦች የራሳቸው የሆነ ባህላዊ እሴቶች፣ ታሪክ፣ ቋንቋና የበርካታ ተፈጥሮ መስህቦች
ባለቤቶች ቢሆኑም ብሔረሰቦች ለዘመናት ጠብቀው ያቆያቸው የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች የመስቀል በዓል
አከባበርን ጨምሮ በአግባቡ ያልተጠኑና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ሳይሰጡ መቆየታቸው ይታወቃል።
በመሆኑም ቱሪዝም ለአንድ ሀገር ምጣኔ ሀብታዊ እድገት የሚያበረክተውን ፋይዳ በመገንዘብ መምሪያው የተሰጠውን
ሥልጣንና ኃላፊነት በአግባቡ በመጠቀም በቀጣይም በዞኑ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን በማልማትና
በማስተዋወቅ የተቋሙን ራዕይ እውን ለማድረግና ተልዕኮውን ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ
ለመግለጽ እወዳለሁ። በተለይም የዞናችን መቀመጫ የሆነችው ሳውላ ከተማን ጨምሮ በሁሉም ከተማ አስተዳደሮች
የሚስተዋለውን የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እጥረት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከዞኑ መንግሥትና
ከባለሀብቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን እገልፃለሁ።
ዞናችን የበርካታ ባህላዊና ተፈጥሮአዊ መስህቦች ባለቤት መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የአካባቢው ማህበረሰብ
በየአካባቢያቸው የሚገኙ ተፈጥሮአዊና ባህላዊ ቅርሶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ከዘርፉ ልገኙ የሚችሉ ጥቅሞችን
በማሳደግ እና አከባቢውን ይበልጥ እንድያስተዋወቁ በዚህ አጋጣሚ አሳስባለሁ። በመጨረሻም የዞናችን ነዋሪዎች፣ በሀገር
ውስጥ በተለያዩ ከልሎች እንዲሁም ከሀገር ውጭ የምትኖሩ የጎፋ እና ኦይዳ ብሔረሰብ ተወላጆች እንኳን ለጎፋ
ብሔረሰብ "ጋዜ ማስቃላ" እና ኦይዳ ብሔረሰብ "ዮኦ ማስቃላ" በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን ለማለት
እወዳለሁ።
መግቢያ
በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ከሚገኙ 13 ዞኖች አንዱ የጎፋ ዞን ነው ፡፡ የጎፋ ዞን እንደ ሀገር
ለውጡ ከወለዳቸዉ የለውጡ ፍሬ ከሚባሉ እንዱ ስሆን የዞኑ አጠቃላይ ቆዳ ስፋቷም 4551 ስኩዋር ኪሎ
ሜትር ነው ፡፡ የዞኑ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ 5'54N - 6'44N ላቲትዩድ እና 36'20 E-37' 20 E ሎንግቲውድ
ነው ፡፡ በሰሜን ከዳውሮ ዞንና ኮንታ ልዩ ወረዳ በደቡብ ከደቡብ ኦሞ ዞንና ጋሞ ዞን በምስራቅ ከዳውሮ ዞንና
ከጋሞ ዞን በምዕራብ ከደቡብ ኦሞ ዞንና ከባስከቶ ልዩ ወረዳ ጋር ይዋሰናል ፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ሣውላ ሲሆን
ከአድስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በ 516 ኪሎ፤ ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ሐዋሳ 296 ኪሎ ሜተር ርቀት
ላይ ይገኛል፡፡ በዞኑ ሁለት ነባር ብሔረሰቦች ጎፋና ኦይዳን ጨምሮ ሌሎች የሀገርቱ ወንድምና እህት ከሆኑ
ህዝቦች መጥተው በጎፋ ዞን ተጋብተዉ ተዋልደው በማይነጣጠል አንድነት ተጋምደው በሠላምና በፍቅር ሰዎች
የምኖሩባት ትንሹዋ ኢትትዮጵያ ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡
የዞኑ ሕዝብ ብዛት ከ 1.5 ሚሊየን በላይ ሲሆን የአከባቢው ህዝብ ኑሮ በአብዛኛዉ በሚባል ደረጃ በግብርና ሥራ
ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የዞኑ የአየር ንብረት በሦስት ተከፍሎ 20.92% ደጋ፣ 31.12% ወይና ደጋ 47.96% ቆላማ
የአየር ፀባይ ያለው ነው፡፡ የዞኑ የመሬት አቀማመጥ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 1976 ሜትር ከፊታ ያለዉ
ሲሆን በከፍታቸው የታወቁ በመሎ ኮዛ ወረዳ 3439 ሜትር ከፍታ ያለው የዳሞታ ተራራ እና በኡባ ደብረፀሐይ
ወረዳ 3421 ሜትር ከፍታ ያለው የሀገር ማሰዲዚ ተራራ እና በደምባ ጎፋ 3400 የፃንጋ አልባ ዙማ ባለሻኛው
የጎፋ ብሔረሰብ ጋዜ ማስቃላና የኦይዳ ብሔረሰብ ዮኦ ማስቃላ 2014 ዓ.ም. 3
ተራራ ይገኙበታል፡፡ የዞኑ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን 170.5 ሚ.ሜትር ነው፡፡ የጎፋ ዞን ለአስተዳዳራዊ
አመችነት በ 7 ወረዳዎችና በ 4 የከተማ አስተዳደሮች እንድሁም በ 196 የገጠርና ከተማ ቀበሌዎች የተከፋፈሉ
ነው፡፡
የዞኑ የአየር ንብረትና የመሬት አቀማመጥ ለሰዉ ልጅ ኑሮ ተስማሚ፤ መልካዓምድር አቀማመጥ በጣም
ማራኪና መሬቱ ለእርሻ ሥራ፣ለኢንቨስቲመንት እና ለቱሪዝም ክፍለ ኢኮኖሚ ተመራጭ እና ሠላሟ በህዝቦቿ
የተረጋገጠ ከመሆኑ የተነሳ ወደ ዞኑ በመምጣት አዋጭ በሆኑ የሥራ ዘርፍ ላይ ኢንቨስት በማድረግ ዳጎስ ያለ
ትርፍ በማግኘት ለመበልፀግ ለሚፈልጉ ባለ ሀብቶችና ድያስፖራዎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት
በሩ ክፍት ሙኑን በዚሁ አጋጣሚ የጎፋ ዞን አስተዳደር ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ክፍል ሁለት
የታሪክ አምድ
2.1 የጎፋ ብሔረሰብ ታሪክ
መግቢያ
“To be ignorant of what occurred before you were born is to remain always a child”
የጎፋ ብሄረሰብ ታሪክን በአጭሩ ለመጽሄት መሙያ አድርጎ ማዘጋጀት ከግምት በላይ ነው፡፡ በመሆኑም የጎፋ
ብሄረሰብ ሙሉ ታሪክ ሳንል የታሪክ ቅንጭብጭብ (Demo) ብለን ብንመለከተው ጥሩ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም
የጎፋ ብሄረሰብ ታሪክ እናወሳለን ካልን በፖለቲካ ታሪኩ ራሱን ከማስተዳደር አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያገኘው
ዕውቅና፤በኢኮኖሚውና ማህበራዊው ዘርፍ ብንሄድ የማህበራዊ ትስስርን ለኢኮኖሚያዊው ጠቀመታ ያዋለበት
ጥበብ፤ በትምህርትና ዕውቀት ብንመለከት የጎፋ ብሄረሰብ በቋንቋ፤በሥነ-ቃል፤በሙዝቃ፤በአርት እና በተለያዩ
የጥበብ ሥራዎች፤በዘመን አቆጣጠሮች፤እጅግ ብዙ ፈርጅ ያለው የታሪክ ሰንሰለት በመሆኑ በዚህ ክፍል በትንሹ
ከየዓይነቱ ቀንጨብ ቀንጨብ ተደርጎ ለጎፋ ጋዜ ማስቃላ መጽሄት እንደመነሻ ሆኖ ቀርቧል፡፡
ታሪክን መሥራት እንደ ታሪክ መማር፤ማስተማርና መጻፍ ቀላል አይሆንም፤ሆኖም ግን ታሪክን መጻፍና
ማስተማር የራሱ የሆነ ከፍ ያለ አስተዋጥኦ አለው፡፡ ታሪክ ለሰው ልጆች ምን ያህል ጥቅም እንደሚሰጥ ወይም
ስለአስፈላግነቱ በዓለማችን ዕውቅ የሆኑ መሪዎችና ምሁራን ተጠቅመውበታል፤መልሰውም ተንትነውበታል፡፡
የዛሬዋን የጎፋ ብሄረሰብ ታሪክ የሚሰሙም ሆኑ የሚያሰሙ ለትውልዳቸው የሚሆን ትልቅ ታሪክ እየሰሩ ነው፡፡
ከዓለማችን መሪዎች የአሜርካው ፕርዝዳንት ተወዳጁ አብራሃም ሊኒኬን ስለታሪክ ተቀመታ ያሉትን
የእንግልዘኛውን ሀሳብ በቀጥታ አስቀምጠን ትርጉሙን ቀለል ባለ ማብራሪያ እንመለከተዋለን፡፡
Abraham Lincoln (in the context of The American Civil War of 1861 to 1865)
…የሰው ልጅ ተፈጥሮ አሁን ካለው ወደፊት በብዙ ትውልድን በምፈትኑ ነገሮች ብያልፉም እምብዛም
አይለወጥም፤ ግን … ደካማ እንዳለ ሁሉ ጠንካራ ፤እንድሁም ሞኝም እንዳለ ሁሉ ብልህም፤ መጥፎም እንዳለ
ሁሉ ጥሩም እየሆነ ይቀጥላል፡፡ ስለዚህ ማጥናት ያለብን በታርክ ከተፈጸሙት እንደ አንድ መሰረታዊ ነገር
(principles) ጥበብን (wisdom) እንማራለን፤ ይህን ብናደርግ እምብዛም አያስኮንንም… ይላሉ፡፡
ስለዚህ በመግቢያየ እዳስቀመጥኩ እውቁ ሲስሮ (Ceciro) ከክርስቶስ ልደት በፊት ታሪክን ያለማጥናት፤
ያለማወቅና ያለማሳወቅ ሳያድጉ ልጅ ሆኖ መቅረት ነው ካሉት ለማሚለጥ፤እንደ ፕርዝዳንት አብራሃም
ሊኒከን ምክር ከትውልዶች ታሪክ ጥበብን ለመማር እንድሁም በዚህ ዘመን ያለው የታሪክ ሺሚያውና ማጥፊያ
ዘዴው እኛ ከሚንገምተው በላይ በመሆኑ የጎፋ ብሄረሰብ ታሪክ ለማዳን ተባብሮ ጽፎ ለትውልድ ማቆዬቱ
መልካም በማለት አቅርበናል፡፡ ይህንንም ትውልድ ተሻጋር ሥራ የሚከውኑ ሁሉ አስተዋዮች ናቸው፡፡
በዚህ ላይ አንድ ጸሐፊ ደራስና ጋዜጠኛ የሆኑት ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም በቅርቡ ገበያ ላይ ባዋሉት “ሀገረ“
በምለው መጽሐፋቸው ከገትኔት እንየው እውቀትን ፍለጋ ከተሰኘው መጽሐፍ ለምክር የሚሆን አንድ ግጥም
መሣይ ስለማንነትና ማንነትን ፈልጎ ስለማግኘት ያስቀመጡትን አይተን እናበቃለን፤
የጎፋ ብሄረሰብ ምናልባትም የሰው ዘር ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በብዙ ጥናት ተዳስሶ ወጥተው ቀደምት
አከባብ፤ ብሄረሰብ፤ የሰው ዘር መገኛ ተብሎ ከሚታወቁ አከባቢዎች አንዱ ይሆናል ሚል እምነትና ግምት
አለኝ፡፡ ለዚህ በዋናነት ምክንያት የሚጠቀሰው በአንዳነድ የሚርምር ውጤቶችና የቋንቋ ጥናቶች
እንደተመለከተው የጎፋ ብሄረሰብ በጥነታዊነቱ በታወቀው በኦሞትክ ህዝቦች ውስጥ መገኘት ብቻ ሳይሆን
በጂኦግራፋዊ አቀማመጡም ማዕከላዊ በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ አንዳንድ ታሪክ ጻሀፍዎች የዖሞትክ ህዝቦች
በድሮ ከጥንት ዘመን ጀምረው ከደቡብ ሸዋ ፈልሰው የኦሞ ወንዝ ተከትለው የሰፈሩ ህዝቦች ናቸው ስለሚሉ
በተጨማርም በዓለማችን በተደረጉ የቋንቋ ጥናቶች፤የሥኔ- አጽም ምርመራ ያስገኘው ውጤት የተለያዩ
ቅርቴ አካሎችና የጥንታዊ ሰዎች መገልገያ መሳሪያዎች በተለይ በቅርቡ እየተደረገ ባለው ጥናት ከሉሲ ቀጥሎ
ከፍተኛ ዕድሜ ያለው ሰው መሰል አጽም (Homo erectus) የተገኘው በምሥራቅ አፍርካ ሲሆን የተገኘበት
የቱርካና ሐይቅ አከባብ መሆኑ እና ለቱርካና ሐይቅ ዋነኛ መጋቢው “ዑማ“ ወንዝ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ስንነሳ
በከንያና በኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ የተደረገው ጥናት የዑማን ወንዝ ተከትሎ ከፍ ቢል የበለጠ ማስረጃ ሊገኝ
ይችላል የሚል ግምት ምሁራን ያስቀምጣሉ፡፡
እንደገናም የጥንቷ ኢትዮጵያ ተብሎ በኢትዮጵያ ካርታዎች ድርጅት ተዘጋጅቶ ለታሪክ ከተረፈው ካርታ ላይ
ከተሰጡት ማብራርያዎች ታሪካዊ ሥፍራ (Historical Sites) ተብለው ከተለዩት አንዱ የኦሞ ሸለቆ
ከመሆኑም በላይ ከ 1.8 እስከ 3 ሚልዮን ዓመት እነዳስቆጠረ ጥንታዊነቱን ቁልጭ አድረግዎት አሳይቶናል፡፡
በዚህ ላይ ተጨማር መረጃዎችን ለላ ጊዜ፡፡ በመጨረሻም አንዳንድ በብሔረሰቡ ሚከናወኑ ባህላዊ ሥርዓቶችና
ክዋነዎች እንደ “ጎሜ“ ዓይነቶች በአሁኑ ሰዓት ሥልጣነ ጣራ በነካው በረቀቀው ቴክኖሎጅ ወቅት የሌሉ
መሆናቸው እውነትም ከለላ ቦታ ፈልሰው የመጡናቸው የሚለውን ለመቀበል ያስቸግራል፡፡
በሌላ በኩል የጥንቷ ኢትዮጵያ ተብሎ በኢትዮጵያ ካርታዎች ድርጅት ተዘጋጅቶ ለታሪክ የተላሌፈውን የጥንት
ኢትዮጵያ ከ 2800 ዓመተ ዓለም እስከ 1270 አመተ ምህረት ካርታ ላይ ስንመለከት ያነ እንኳን በሙላት
የኢትዮጵያ ቅርጽ ባልወጣበት ኦሞትክ ህዝቦች ተብልው የሚጠሩት ከጉራጌ በታች፤ ሀድያና ሲዳማን ወደ
ምስራቅና ደቡብ ጎን በመተው እንደሚታወቁ ተገልጿል፡፡ በዚህ ላይ የኦሞ ወንዝ ተከትለው በተሰየመው
ማህበረሰብ ውስት ወንዙን “ዑማ“ እያለ በዋናነት ከቦ በመኖር የሚታወቀው የጎፋ ብሄረሰብ መሆኑን
ጂኦግራፊካል ሎኬሽን የተለዬ ዕድል መስጠቱን ያሰያል፡፡ በዚህም ማዕከላዊ ቦታ ከመያዙ የተነሳ በሚያስገርም
ሁኔታ ከሁሉም ለሎች አጎራባቾች ጋር ከፍተኛ የሆነ የቋንቋ መወራረስ መኖሩን ደራሲው መምህር በላይነህ
“… በአስራ አራተኛው መዕተ ዓመት በኢትዮጵያ የአፄ ማዕከላዊ መንግሥትግዛት ውስጥ ከመቀላቀላቸው
አስቀድሞ የሀርላ፤ ሸዋ፤ ይፋት፤ አርጎባ፤ወርጅ፤ አዳል፤ ሀዲያ፤ ሲዳሞ፤ ደዋሮ፤ ፈጠጋር፤ አራባቢኒ፤
ሻርክ፤ ባሌ፤ ዳራ፤ ወጅ፤ ጉራጌ፤ ዳሞት፤ ገንዝና ኦሞ ልዩ ልዩ ማህበረሰቦች እስከ 1000 ዓ.ም. ድረስ
የራሳቸው አስተዳዳራዊ ሥርዓት ፈጥረው ይኖሩ እንደነበር ይገመታል…፡፡“
በዚህ ላይ ዋና ዋናዎቹ ዑማውያን ብለው ቼሩል የተሰኘው ባህር ማዶ ጸሀፍ ካስቀመጣቸው አንዱ ጎፋ
መሆኑን ገልጸውታል፡፡ (በላነህ አሰጉ እንደጻፈው፤Cerulli, 1956, p 96)፡፡ ከመሳፍንት በኋላ ጎፋ በጠቅላይ ግዛት
በመደራጀት ለመጀመሪያ ጊዜ ከማዕከላዊ መንግሥት ቀጥታ ተጠርነቱ ወደ ታች ዝቅ ያለበትና በኋላ ወደ
አውራጃ ግዛትነት ተቀይሮም በኢትዮጵያ ካሉት 12 አውራጃዎች አንዱ እንደሆነ ታሪክ ያስረደናል፡፡ በቀዳማዊ
ኀ/ሥላሴ ዘመን የነበረውን የጎፋ ብሄረሰብ ከብረት የጠነከረውን ታሪክ በዚህች አጭር ጽሁፍ ለማቅረብ
ይከብዳል፡፡ (ቀዳማዊ ኀ/ሥላሴ 2 ኛ መጽሐፍ 328)
የጎፋን ብሄረሰብ ታሪክ ሲናጠና ከምኒልክ ዘመነ መንግሥት ቀደም ብሎ ያለና የተደራጄ፤ ማእከላዊነቱን የተበቀ
አስተዳደር መዋቅር ያለበት መሆኑን ከብዙ መረጃዎች አረጋግጠናል፡፡ ለምሳሌ ፕሮፌሰር ላጵሶ ጌ. ደሌቦ
ከ 1600 ዓ.ም.እስከ 1855 ዓ.ም. የነበረውን ታሪክ ዳስሰው በኢትዮጵያ ታሪክ መነሻ መጽሐፋቸው
ያስቀመጡት ከምኒልክ ዩኒፊኬሽን በፊት የተጠናከረ መንግስት ያለበት መሆኑን በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡
“… በሌላ በኩል ከ 1696 እስከ 1855 ዓ.ም.ባለው ጊዜ በደቡብ የተጠናከረና ማዕከላዊነቱን የጠበቀ የሸዋ ንዑስ
ግዛት ተመስርቷል፡፡ በምዕራብ ክልል ጃንጀሮ፤ ሊሙ ኢናሪያ፤ ቦሻ፤ ጅማ፤ጎማ፤ጌራ፤ ከፋ፤ ኩሎ፤ ኮንታ፤ ሞቻ
የተሰኙና በደቡብ ምዕራብ ወላይታ፤ ጋሞ፤ ጎፋና ጎንሶ፤ በምስራቅ የሐረር ንዑስ ግዛት ከተማና የአውሳ
ሡልጣናዊ ንዑስ ግዛት፤ በሩቅ ሰሜን የትግሬ ቤጃዎች ወይም ቤኒአምር ግዛት፤ በሩቅ ምዕራብ ቤኒሻንጉል
ሡልጣናዊ ግዛት የነበረው የባል ጀብለዊ ንዑስ ግዛቶች የተፈጠሩ ሲሆን በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ንዑስ
አከባብ ግዛቶች በየአቅጣጫው የተፈጠሩበት ወቅት ነበር…“
አይበገረው የጎፋው ንጉሥ ካማ ዳዳ በሠራቸው የጀግንነት ገድሉ የጎፋው አፄ ቴዎደሮስ በሚል ታሪኩ
እነደሚወሳ ሁሉም የጎፋ ትውልድ ይስማማል፡፡ በተረጋጋው የንግስና ዘመናቸው በምወዱ ህዝቦች መሀል
ረጅም ጊዜ ከኖሩ በኋላ የምኒልክ ጦር አከባቢውን ተቆጣጥሮ ለመግዛት ይመጣል፡፡ በወቅቱ በቂ መረጃ
ከየአቅጣጫው ያገኘ ቢሆንም በተለዬ መልክ ከጅማው ንጉሥ አባጅፋርና ከዳውሮው ንጉሥ ሀላላ እንድህ
የሚል መልዕክት መጥቶለት ነበር፤ “አንቴ ጀግና እንደሆንክ እናውቃለን…’ጀግንነትና ጦርነት ሁሌ አይቀናም’፤
ራስህንና ህዝብህን ትጎዳለህ እባክህ እጅህን ስጥና ግብር ትከፋላለህ“ የሚል ነበር፡፡ አይበገረው ካማ ዳዳ ስለ
መልዕክቱ አመስግአቸው እንድህ የሚል መልስ ላከላቸው “ወንድ ለወንድ እንደት እጅ ይሰጣል እጄን በሰማይ
ላለው ለእግዝአብሔር እሰጣለው“ ደግሞስ “እኔም በሀገረ ንጉሥ ነኝና እንደት ለእርሱ እገብራለው?“
እንግድህ እኔ ለሱ “kana kaaca kasttole girana“ ሲለው በጣም ቅኔንና ንቀትን የተሞላ ሁለት ትረጉም የያዘ
አንድ ዐረፍተ ነገር ነበር የተናገረው፡፡ ትርጓመውም የመጀመሪያው ሰሙን “ውሻ፤ ጦር እና ቁንጫን እገብራለው“
የሚለው ጦር እገብራለው ማለቱ በጦር እዎጋዋለው ማለቱ ሲሆን፤ ወርቁ ደግሞ “የሀገረ ሰው የውሻ ራስ ጥሪ ቁንጫ
ነው የሉታልና ቁንጫን እገብራለው እንጅ እውነተኛ ግብር አልገብርም ማለቱ ነው“ እንደሆነ ይነገራል፡፡
አይቀረው የፈተናው እሳት መጣ ተዘጋጅቶ ሲጠባበቅ ነበረና የፃንጋውን አልባ ዙማ ምሽግና የውርጪውን
ምሽግ ሁለቱን ትቶ የመጀመሪያውን የፊት የወይደዎችን ምሽግ ይዞ በወይደ ዛፋ ዴሌ ዑማ/ ኦሞ ወንዝ
ወርደው በዳውሮ ተሻግሮ የመጣውን የሸዋውን ጦር ገጠመው፡፡ በቂ ዝግጅት በማድረጉ የምኒልክ ጦር
በሚመጣበት ወቅት ከፍተኛ መከላከል በማድረጉ በራስ ወልደጊዮርጊስ የተመራው በመጀመሪያ ዙር ተሸንፎ
ተመልሶ በሁለተኛ ጊዜ እንደገና ተጠናክሮ ብመጣም እንደገና ተሸንፎ ወደ ኋላ መመለሱን ታሪክ የስረዳል፡፡
በመሆኑም የምኒልክ ጦር በከፍተኛ ዝግጅት ተጠናክሮና ለሎችን ከባባዊ ሥልቶችን በመጠቀም በከባድ
መስዋዕትነት ጦሩን ለሦስተኛ ጊዜ በማምጣት ሲዋጋ የጎፋ ንጉሥ ካማ ዳዳም ከነ ጦራቸው እጅ ባለመስጠት
ስፋለሙ ቆይተው በመጨራሻም በመስዋዕትነት ደማቁን የጎፋን ታሪክ ጽፌው አልፈዋል፡፡
በውግያው ፊልሚያውም ድሎችን ብያስመዘግብም በመጨረሻውቃሉን ጠብቆ ለጎፋ ህዝብ ስምና ክብር
በማለት “ውርጪ ጭልዣ“ በሚባል በጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ የሚገኝ እጅግ በታወቀው የጦር አውድማ
ወይም ግምባር ከነአጋሮቻቸው ጋር አብረው የጎፋ ጀግኖች የምኒልክንም ጦር በአይበገርነትም ተዋግተው፤
ለራሳቸውም በዚው የጎፋን ታሪክ በደማቅ የደም ቀለማቸው በመጻፍ በመስዋዕትነት ዘግተዋል፡፡ ትውልድ ግን
ከታሪክ ማህደር ስያስታውስና ስዘክር የኖራል፡፡
ጎፋ በማዕከላዊው መንግሥት እጅግ የሚታወቅና ተጽዕኖ ፈጣርነቱን ከጎፋው ንጉሥ ካማ ዳዳ ምስትም ማየት
እንችላለን፡፡ ካማ ዳዳ በመስዋዕትነት የጎፋ ህዝብ ታሪክ በጀግንነት ህያው አድርጎ ሲያልፍ ታሪኩም ህያው ሆኖ
በዚያው እጅግ ናኝቶ ወደ አዲስ አበባ የንጉሥ በቴ- መንግስት ሰተት ብሎ ገባ፡፡ የሸዋው ጦር ጎፋና ለሎች
የኢትዮጵያ ግዛቶችን ከተቆጣጠረ በኋላ በ 1908 በምኒልክ በቴመንግሥት የዙፋኑ አማካሪዎች (ካውንስል)
ሲያቋቁም ከተሰዩሙ ሚኒስቴሮችና ዋና ዋና ከሆኑት ያነ ተስፋፊ ጦሩ በሚዘምትበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ
ከፈጸሙትና ሰፋፊ ግዛቶች በማምጣት ለሀገረ መንግሥት መረጋጋት አደራጅቶ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ የጎፋ ገኔ
(ንግሥት) አቅለሲያ በሸዋው በቴመንግሥት ቦታ ለመያዝ በቃች፡፡ በወቅቱ ጄግናና ታዋቅ ከነበረው ከነ ወላይታ
ንጉሥ ጦና ጋር በመሆን ወንበር ተጋራች፡፡ ንጉሤ ነገሥቱ ለቆራጥና በደማቸው ጀግንነት ላላቸው ሰዎችና
አከባቢዎች የተለየ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ የጎፋ ጦር አይበገረትና የጎፋ ገኔ (ንግሥት) አቅለሲያ የነበራትን
አጠቃላይ ሁነታ በማየት ከሚትርባት “ሜላ” ግዛታቸው (በአሁኑ ሰዓት በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ)
ወደ በቴመንግሥት ወክለው እንድገቡ ተደርገዋል፡፡ በኋም አፄ ምኒልክ ከበቴመንግስታቸው ወጥተው አድዋ
ሲዘምቱ በቴመንግስታቸውንና አዲስ አበባ ከተማን ለአይበገረውና ጀግናው ለወላይታ ካዎ (ንጉሥ) ጦና ሀደራ
ሰጥተው ሄደው ነበር፡፡ ታድያ በዚህ ወቅትም የጎፋ ገኔ (ንግሥት) አቅለሲያ የበቴመንግሥት ሚናዋ እንደቀጠለ
ታሪክ ያወሳል፡፡
ቀደም ብላ ኃይለኛው ንጉሥ ካማ ዳዳ (ባለበቷ) ከተሰዋ በኋላ ከካማ ዳዳ የወለደችውን አንዷን ልጅ አይካን
ይዛ ሜላ ወደ ሚባል ሥፍራ ላይ ግዛት ወስዳ ትኖር እንደነበረ ይነገራል፡፡ በዚያም ብዙ ሥራዎችን እንደሰራችና
ከፍተኛ የሆኑ የመብት ጥያቀዎችን በማንሳት ትሟገት ነበር፡፡ የመጀመሪያ ስሟ ሻሹሬ ሲሆን በኋላ ክርስቲና
ተነሳችና ስሟ አቅለሲያ (ጎፋ ጌኖ አቅለሶ) ተባለ፡፡ በዚህም በክርስትናው ዓለም በግዛቷ ሜላ ብዙ ወጣቶችን
ሰብስባ ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል መምህራንን በመቅጠርና ቅስናን በማስተማር በአከባቢው አጠራር ሜላ ቄሴ
በማለት የሚታወቁትን ዛሬ ላይ ትልቅ የሆኑትን የሃይመኖት አባቶችን (ቄሳውስትን) አፍርታም ነበር፡፡
አንድ ወቅት በዚያ “ሜላ” በራስዋ ግዛት እያለች ለምኒልክ አስተዳደር ጥያቄ አቅርባለች፡፡ ንግስት አቅለሲያ
ተሟጋችና ለመብት ቀናዕ እንደሆነች አፄ ምኒልክም ዕውቅና የሰጣት ስለመሆኑ ከታሪክ ማስረጃ መመልክት
እንችላለን፤
“አፄ ምኒልክ ለደጃዝማች ለማ መጋብት 24 ቀን 1900 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ የጎፋ ገኔ በዛላ
ውስጥ ያለኝ ረዕስት ተወሰደ በደል ደረሰብኝ ብለው ደብዳቤ መጻፋቸውን በመግለጽ
ደጃዝማች ለማን ጎፋ ገኔ አትድረስባት ብለዋቸዋል፡፡”
(በላይነህ አሰጉ 2009፤ 44)
በተጨማርም ዶናልድ ዶሃም የሚለው ጸሐፍ መምህር በላይነህ አሰጉ እንደጠቀሱ ከሹመቷ አኳያ በምኒልክ
በቴመግሥት በመደበኛነት ግብር ከሚጠሩ መኳንንት አንዷ እንደነበረች ተጽፏል፡፡ (ዶናልድ ዶሃም ገጽ 44
በመ/ር በላይነህ አሰጉ፤ 2009፤44-45 እንደተጻፈው)
በተረጋጋው የንግስና ዘመናቸው በሚወዱ ህዝቦች መሀል ረጅም ጊዜ ከኖሩ በኋላ ለጎፋ ህዝብ ስምና ክብር
“ወንድ ለወንድ እንደት እጅ ይሰጣል እጄን በሰማይ ላለው ለእግዝአብሔር እሰጣለው“ በማለት “ውርጪ
ጭልዣ“ በጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ወስጥ የሚገኝ አከባቢ ወይም የጦር ግምባር ከነአጋሮቻቸው ጋር አብረው
የጎፋ ጀግኖች የምኒልክንም ጦር በአይበገርነት ተፋልመው፤ ለራሳቸውም በዚው የጎፋን ታሪክ በደማቅ የደም
ቀለማቸው በመጻፍ በመስዋዕትነት ዘግተዋል፡፡ ትውልድ ግን ከታሪክ ማህደር ስያስታውስና ስዘክር የኖራል፡፡
ይህን ተከትሎ የአዔ ምኒልክ ሹም የነበሩት ራስ ወ/ጊዮርጊስ አከባቢውን ሲቆጣጠሩ ስለ የጎፋ ንጉሥ ካማ ዳዳ
ፈረስ ወረውን ይሰሙታል፡፡ ይህ ተዓምረኛው ፈረስ በአሁኑ ሰዓት በሰለጠኑ ሀገሮች የሰለጠኑ አነፍናፍ ውሻዎች
ከሚያገለግሉት በላይ የጎፋን ንጉሥ ካማ ዳዳን ሲያገለግል እንደነበረ ይነገራል፡፡ በወቅቱ ይህ ፈረስ
አቅጣቻዎችን ይለያል፤ ስመሽና ከባድ ዝናብ የሚጥልበትን ሁነታ ሲመጣ ምልክትን ማሳየት ይጀምራል፤
ከንጉሡ ውጭ ለሎች እንድቀመጡ ጨርሶ አይወድም ያምጻል፤ ከልክ በላይ የተገራ ፈረስ ከመሆኑም በላይ
እነደ ዘመኑ ባለሥልጣን ጠባቂ (ጋርድ) ከንጉሡ አጠገብ ለመለየት አይፈልግም ነበር ይላሉ የአከባቢው ታሪክ
አዋቅ የዕድሜ ባለጼጎች፡፡ ታሪኩ ያስደንቃል በጎፋ ምድር ሰውም ሆነ እንስሳ ሁሉም ጀግንነት በደማቸው ያለ
የሚያስመስል ነው፡፡ እንግድህ ይህን ተከትለው ራስ ወ/ጊዮርጊስ በሁነታው ተገርመው የራሳቸውን በቅሎ
በመተው የጎፋ ንጉሥ ካማ ዳዳ ፈረስን በራሳቸውን እንደገና በማላመድ በመጨረሻም ይህንን ፈረስ ይጠቀሙ
እንደነበር ይነገራል፡፡ ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚገልጹት ይህ ፈረስ በወርቅና በብር ዕቃዎችም እጅግ ያገጠ
እንደሆነ እንረዳለን፡፡
በመጨረሻም ይህ ፈረስ ሄኖክ ስዩም (ተጓዡ ጋዘጠኛ) አሌክሳንደር ቡላቶቪቺ ከአፄ ምኒልክ ሠራዊት ጋር ብሎ
የፃፋቸውን መጽሐፍ ዶክተር አምባቸው ከበደ ተርጉመውት በአዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ አሳትሞ ለንባብ
አብቅተዋል በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ይህ እጅግ ውብ የሆነውና ያገጠው ፈረስ ከራስ ወ/ጊዮርጊስ
ለአሌክሳንደር ቡላቶቪቺ በግምቦት 23 ቀን 1892 ዓ.ም. በሥጦታ ተበርክቷል ይላል፡፡ ከዚህ የተነሳ በሁሉም
በጎፋ ህዝብ ታሪክ ሲታዎሱ የሚኖሩ ዋና ዋና የኢትዮጵያ የጦር አውዴ ግምባሮችን ስናስብ የዚህ ብሄረሰብ
ትልቅነትና ሀገር ወዳድነቱ፤አስተዋይነቱ፤ስልጡንነቱ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፡፡ ምናልባትም የዚህ ሁሉ
መነሻ የጎፋ ህዝብ የማዕከላዊ መንግስት ጥሪ ተቀብለው ፈጣን ምላሽ መስጠትና የኢትዮጵያዊነት ጥግ
በማሳየት እንደ ንብ 516 ኪሎ ሜትር በእግራቸው በመትመማቸው ነው፡፡ በመሆኑም በአዲስ አበባ የጎፋና
አከባቢዋ ልጆች መጥተው እንድሰፍሩ ቦታ/ሰፈር እስከ መሰጠት የደረሰበት ሁነታን ሲንመለከት ነገሩ በምን
ያህል የአስተሳሰብ ልዕልና እንደተፈጸመ ያስገርመናል፡፡ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ለጎፋና ኦይዳ ብሔረሰብ ባህል ማዕከል ግምባታ ቦታ የሰጡትን ስንመለከት በተለይ ከጎፋ ብሔረሰብ አኳያ
ታሪክ ራሱን ለ 2 ኛ ጊዜ ጊዜውን ጠብቆ እየደገሜ ያለ እውነተኛ የታሪክ ማስታወሻ ነው ያስብላል፡፡
በአድዋ ጦርነት የጎፋ ጦር በደጃዝማች ባሻህ አቦዬ እየተመሩ ተዋግተዋል፡፡ ከአድዋ ጦርነት በኋላ የጥቁር
ህዝቦች ችቦ ሲለኮስና የአድዋ የድል ብሥራትታላቅ ሰልፍ በንጉሥ ነገሥቱ ፊት በክብር ስበሰር የጎፋ ጦር የሰልፉ
አድማቂ የክብር ባለበት ሆኖ ተሰይሟል (ሄኖክ ስዩም (ተጓዡ ጋዘጠኛ) 2013፤166) በወቅቱ ለጎፋው ጦር
የተሰጠው ዕውቅና እጅግ የሚያስገርምና የሚያስደንቅ ሆኖ አልፏል፡፡ ለሎች ጠለቅ ሉትን በሌላ ጊዜ መመለከት
ይቻላል፡፡
ከአድዋ ጦርነት ውጭም የጎፋ ህዝብ ጀግንነቱንና ሀገር ወዳድነቱን የሚገልጹ ብዙ ለሎች ኢትዮጵያ
ያሳለፈቻቸው ጦርነቶችም አሉ፡፡ ከአነሱም በተለይ ከጦርነቱ በኋላ በአከባቢው ዋና ዋና ከሚነገሩ የጦር
ግምባሮች እነ ማይጨው፤ኦጋደን፤ጎንደር፤ዶጋሌ፤ሰገሌ የሚባሉ ይጠቀሳሉ፡፡ አንዳንድ የጦር አውዴ ግምባሮች
በአከባቢው ቋንቋና ዘዬ በቀጥታ ባለመጠራት ተቀይረው ስጠሩም እንሰማለን፡፡ የእነዚህን ማብራርያ በለላ
ወቅት ተያያጅ ጥናቶችን በማድረግ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አሁን ጦሩን ወይም አጠቃላይ ከጎፋ
የዘመቱትን የዘማቾች ሁነታና የመሩት የጦር መሪዎች በአጭሩ ስንመለከት በዋናነት የጥቁር ታሪክ በደማቅ
የተጻፈበት ጦርነት የአድዋ ጦርነት በደጃዝማች ባሻህ አቦዬ፤የኦጋዴን ዘመቻ በደጃዝማች አበበ ዳምጠው
እተመሩ ተዋድቀዋል በለሎች ግምባሮች ለአብነት የማይጨው፤የጎንደር፤በዶጋሌ፤ የሳጋሌ ወዘተ በእኔ ማን
እንደሆነ፤ የብሄረሰቡን ለማዕከላዊ መንግስት ምላሽ አሰጣጣቸውና ለሀገራቸው አንድነትና ዳር ድምበር
መከበር መዋደቅ ከብረት የጠነከረ ጀግንነት ያሳዩት ሌላ ብዙ ጥናት ይጠይቃል፡፡ በነገራችን ላይ አያንዳንዱ ጦር
ግምባር በአከባቢው የቋንቋ ልዩነት፤ ዜየና የረጅም ጊዜ ታሪክ ከመሆኑ የተነሳ ዘማቾቹ እየፎከሩና እየመሰከሩ
ኖረው ሰያልፉና በሌላ ትውልድ ሲተካ ወደ እኛ ዘመን የደረሰው አጠራር በትንሹ ስንመለከት ለአብነት፤
ኦጋዴን የሚባለውን “ዑጋዴ/ ውጋዴ ዖላ” ይላሉ ይህ ጦርነት የሶማሊያ ወራርዎች የኢትዮጵያን ድምበር
ጥሰው በገቡበት የተደረገው የቅርቡ ሳይሆን የሁለተኛው ጣሊያን ወረራ ወቅት በ 1936 በጄነራል ሮዶልፎ
ጊራዚያኒ የተመራውን ጦር ለመመከት ነበር የጎፋ አባቶች የተመሙት፡፡ በሚገርም ሁነታ ያኔ አባቶች ዘመቻ
የሰጋሌ ጦርነት ደግሞ “ሳጋሌ ኦላ” እየተባለ ይጠራል፡፤ የታሪክ ፃሀፊዎች ይህ ጦርነት የእርስ በርስ ጦርንትና
ከአድዋ ጦርነት ቀጥሎ የተደራገ ትልቁ ጦርነት ይሉታል፡፡ የጎፋ ብሄረሰብ በዚህ የሳጋለ ጦርነትም ማዕከላዊውን
መንግስት ደግፈው ከጠላት ጋር ተፋልመዋል፡፡ ሳጋሌ ከአዲስ አበባ 40 ማይል ርቀት በስተ ሰሜን በኩል የሚገኝ
ሥፍራ ሲሆን በጥቅምት 27 /1916 ንግሥት ዘውድቱን በመደገፍ በዚህ ጦር ተሳትፈዋል፡፡
የማይጨው ጦርነት በራሱ ‘’ማይጮ ዖላ’’ እተባሌ ይጠራል፡፡ በዚህ ጦርነት ላይም የጎፋ ብሄረሰብ ከፍ ያለውን
መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡ በተለይ የዛላ ካዎ ወይም ንጉስ ፊኖ አማዶ ከነሙሉ ጦራቸው ጋር ዘምተው እዚያው
ማይጨው ለውድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንደተሰው መምህር በላይነህ ገ/ማሪያም በመጽሀፋቸው ጽፈዋል፡፡
የ 1936 ቱ የሁለተኛው ኢትዮ - ኢታልያ ጦርነት በንጉሥ ኃይለ ስላሴ ዘመን ነበር፡፡
በአጭሩ ሲጠቃለል በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የጎፋ ብሄረሰብ ሚና እጅግ የጎላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ለሎች ተያያዥ ጀብዶችና ታሪኮች ለሌላ ጊዜ ስንተው ጎፋ የሚለው ስም በምኒልክ በቴመንግሥት የጀግንነት
መለኪያ የሆነው ከእደዚህ ድንቅ ታሪኮች የተነሳ መሆኑን እንገነዘባለን፡
2.1.4 ማጠቃለያ
የጎፋ ብሔረሰብ ከጥንት ጀምሮ ነባር፤ ገናናና ታዋቂ በመሆኑ በራሱ ግዛት ተደላድሎና ሰፍቶ ያለ መሆኑን፤
በኋላም ከምኒልክ ዩኒፍኬሽን ጀምሮ እስከ 1934 ዓ.ም. የጠቅላይ ግዛት ዘመን ድረስ ተጠርነቱ ለማዕከላዊ
መንግሥት በቀጥታ እንደሆነ፤ ከ 1934 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ደርግ መንግሥት ውድቀት ድረስ ደግሞ በአውራጃ
ደረጃ ተደራጅቶ ከፍታውን ሳይለቅ እንደቆየ ውብ የሆነውን የታሪክ ሰንሰለቱን በአጭሩ ለማየት ችለናል፡፡
ከ 1983 ዓ.ም. ከደርግ ውድቀት ተከትሎ ቦታ በያዘውም መንግሥት አደረጃጀቱ ከአውራጃው ጋር የሚመጣጠን
ልሆን የሚችለው ዞን ነውና በዞን ደረጃ ለመደራጀት የመብት ጥያቄዎች በየጊዜው እዳቀረበና እንደታገሌ
ይሄው ረጅሙን 27 ዓመት በትግል አሳልፈዋል፡፡ በቅርቡ የሀገራዊ ለውጥ ተከትለው የመጣው መንግሥት
የቀደመውን የጎፋን ታሪክ ያውቅ ይመስል ይህን የጎፋን በዞን የመደራጀት ዕድል ፈቅዷል፡፡ በመሆኑም የጎፋና
አከባብው ህዝብ ለለውጡ መንግሥት የተለየ ክብር አለው፡፡ ወንድም የሆነውን የኦይዳ ብሔረሰብን ከራሱ ጋር
በመያዝ በዞን ደረጃ ከፍ ብሎ በመደራጀት በየወረዳዎች ተሰራጭተው ለየቅል ስፘፘጡ የነበሩትን የጎፋ
ብሔረሰብ፤ሀብትና ጉልበት እንድሁም ኦይዳን ጨምሮ ወደ አንድ አሀድ ለማሰባሰብ ዕድል በማግኘት የከፍታ
ጉዞውን ገና አሃዱ ብለው ጀምረዋል፡፡ በዚህ ላይ ብዙ ረፈደብን ብንልም አንድ ተስፋ አለን ይህም ታሪክ ሁል
ጊዜ ራሱን ይደግማል ስለምል ምናልባት በቁጭት ጠንክረን ከሠራን /ከሰሩ በአጭር ጊዜ በከፍታው ላይ
መውጣትና የቀደሙ ብዙዎችን ልንደርስ እንችላለን፡፡
‹‹አንተ ሰዉ ነህ ግን ባለህበት የሚያቃጥል ዉሃ ሆነህ ፈልተህ ቅር›› እንዳለችዉ በሄደበት የሚፍለቀለቅ ብልቦ
ፍል ዉሃ ሆኖ እንደተገኘ አፈ-ታሪክ ይናገራል፡፡ በጥንት ጊዜ ‹‹ጋሎ ፃማቶ (Gaalo Xamaato)›› ተብላ
የምትታወቅና ለነገስታት ቀረቤታ የነበራት አንድት የታወቀች ብርቱ ሴት ነበረች ዋና ተግባሯም ጎበዙን በማጀገን
እንድሁም ሰነፉን በንግግሯ ነቁራ በመተቸት ጎፋ ከጠላት ጋር በነበራት ዉጊያ ከነገስታት ጎን በመሆን ከፍተኛ
የማነሳሳት ስራዎችን ስትፈፅም እንደነበረች የታሪኩ አዋቂ አባቶች ይገልፃሉ፡- በአንድ ወቅት ንጉሱ ጠላትን
ለመዋጋት ተዋጊዎችን ለማሰባሰብ ስፈልግ ‹‹ጋሎ ፃማቶ›› እንድህ ስትል ለአዋጅ ነጋሪዉ መልዕክቷን ሰጠች
‹‹ጉፖዋ ጋንፃዳ ጉፒያ ፓራ ቶጋዳ ጉምቦ ቶራ ኦይክዳይሶ ኦላስ ጋጦ ጋጦ›› በማለት ጎበዙን ስታጀግን
ፈሪዉንና ድንጉጡን ደግሞ ‹‹ጉሳዉ ጉቱማጬያዉ ጉቶይ ቃፅን ሳጼያይሶ ሾጭ ዎጣ ኦይቃዳ ሞርናታስ ጌምቦ
ቆፃናዉ ጋጣ ጎቻ›› በዚህ ጊዜ አብዛኞች በቤተ-መንግስት (kawo gadho) ብገኙም ይታወቁ የነበሩ አንዳንዶች
አልተገኙም ነበር፡፡ ‹‹ጋሎ ፃማቶም (Gaalo xamaato)›› ቀጥ ብላ ወደ መጠጥ ቤት ስትሄድ አገኘቻቸውና
ልታናግራቸው ስትፈልግ ድምፅ ያለዉን ፈስ ፈሳችባቸው ተደናግጠውም አንደት ሴት ሆነሽ በወንድ ፊት
ወይም በእኛ ላይ እንድህ ታደርግያለሽ ስሏት
‹‹እናንተማ የምን ወንድ ናችሁ ወንዶች የሆኑማ በዚህን ሰዓት በጦር ሜዳ የጠላትን ብልት ስገፉ
ይህን ንግግሯን እንደ ሰሙም የያዙትን ጥለዉ ወደ ክተቱ ዘመቻ ተመሙ ይባላል፡፡ በተጨማሪም ይህች ሴት
ጋዜ ማስቃላ ስደርስ ወደ ንጉሱ ቀርባ ንጉስ ሆይ ገዜ ማስቃላን እንዴት የሚወሳ ገድል ሳንጨብጥ እናከብራለን
ብላ አማከረችዉ በዚህም ንጉሱ ጎበዛዝትን ድል እንድያመጡ ይገፋፋቸዉ እንደነበረና አንዳንዶችም ከባባድ
አውረዎችን (አንበሳ፤ዝሆን፤ጎሽ፤ነብር) በመግደል ትኩስ የፊት ገጽታን ስያቀርቡ አንዳንዱም ደግሞ ጠላትን
ገድሎ የተገፈፈ ብልትን በንጉሱ ፊት በማምጣት ከንጉሱ የክብር ስጦታ (yallo yoosha) በመቀበል የሚወሳ
ሁኔታዎችን በመፍጠር አዲሱን ዘመን በሙገሳ እና በደስታ እንድቀበሉ ታደርግ ነበር፡፡
ባለፉት ዘመናት ሴቶች በብዙ ሁኔታ በተመረጠ አኳኃን ለትዳር ይታጫሉ ይህም የሚሆነው በአብዛኛውን
ህዝብ ዘንድ በጋብቻ ትስስር ዝምድናን መፍጠር ዋናው ጉዳይ ሆኖ በትስስሩ ጥንካሬና ብርታትን እንድሁም
የገዘፈ ድጋፍ እንድኖር ያስችላል፡፡ በመሆኑም ጋብቻን መፈፀም በብዙ መልኩ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ በብሔረሰቡ
በዋናነት ለትዳር ትጭጭት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች አሉ፡- እነዚህም በዋናነት የሴቷ ብርታትና ታታሪነት
የተመስከረላት መሆኑ የታወቀ ይሆናል፡፡ ለአብነትም ከትዳር በፊት ታታሪነቷን ማሣያ የሆኑ አልባሣትን
ማዘጋጀት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ በመቀጠልም በማህበረሰቧ ትሁት መሆኗ ልነገርላት የተገባ በመሆኑ በብዙ መልኩ
ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን ተመራጭ ያደርጋቸዋል፡፡
ለሎችም ደግሞ ተጠቃሽ ሴቶች አሉ፤- ከእነዚህም ውስጥ ማሌ ሻራፌ ተጠቃሽ ናት፡፡ ይህች ሴት የማሎ ካዎ
ማዳ ፆና ዘር እንደሆነች ይነገርላታል፡፡ በመሆኑም ሳውላ ከተማ ኑሮዋን በማድረግ በከተማዋ የታዋቀ ቡና ቤት
በመከፈቷ ስትታወቅ በሆደ ስፈነቷና በእንግዳ ተቀባይነቷ በሁሉም ሰው ስሙዋ የታወቀ ነው፡፡ እንድሁም የባዮ
ካዎ ጉጃ አሻ ሚስት የሆነችው ማሌ/ጎዳተ/ሞርካሜ ቶጋ (የእራ ካዎ ዜማ ቶጋ ልጅ) ሲትሆን ንጉሡን
በማማከርና ከንጉሡ በታች ትዕዛዛትን በመስጠትና በማስፈፀም በጠንካራ አመራር ሰጭነት ትልቅ ሚና እንደ
ነበራት ትወሳለች፡፡
በጎፋ ሴቶች እንደተገኙበት ዘረ ሐረግና በመሰረተችዉ ትዳር የተለያየ የማዕረግ ስም አጠራር ይኖራቸዋል፡፡
በዚህም መሠረት ሴቷ የምትጠራበት አጠራር ከየትኛው ዘር ሐረግ እንደሆነችና በየትኛው ስልጣን ደረጃና
ዓይነት እንደሚትገኝ በሚገባ ይገልፃል፡፡ በዚህ መሠረት የማዕረግ ሥም ማግኘትና በሁሉም ህብረተሰብ ክፍል
በዚህ ስያሜ መጠራት ክብርን ያስገኛል፡፡
ወደ ስያሜና አጠራሩ ስንመለስ ሴቶች ከተወለዱበት ዘር ሐረግ አንፃር ብቻ የሚያገኙት የማዕረግ ስም አለ፡፡
ይህ ስም ማሌ /MaalIe/ ይባላል፡፡ በጎፋ ብሔረሰብ ይህ ሊገኝ የምችለው ''ጎሻና ወይም አይካ'' ዘር ሐረግ ስኖር
ብቻ ነው፡፡ የማዕረግ ስም አጠራሩ በየትኛውም ጋብቻና በየትኛውም የኑሮ ሁኔታ ሊታጣ የማትችለው ማዕረግ
ነው፡፡ በመሆኑም በዘላቅነት እስከ ህይወት ፍፃመዋ ድረስ በዚህ ስም ትጠራላች፡፡ ነገር ግን ሴቷ በምትፈፅመው
ጋብቻ ምክንያት ተጨማሪ የማዕረግ መጠሪያ ስም ሊኖራት ይችላል፡፡ እነዚህም እንደሚከተሉት ተዘርዝሯል፡፡
ስለሆነም ጎዝዳ ለጎፋ ሕዝብ የብሔረሰቡ መግለጫ ነው፡፡ የጎፋ ብሔረሰብ የሆነ ሁሉ ጎዚዳ እንደ ማለት ነው፡፡
ጎዝዳ ለመሆን በአጭሩ የጎፋ ብሔረሰብ መሆን አለብህ፡፡ በጎፋ ብሔረሰብ ጎዚዳ ለሁሉም የተሰጠ ነው፡፡ ወንድ፣
ሴት፣ ህፃን እና አዋቂ ሁሉም ጎዚዳ ናቸው፡፡ ጎዝዳን ግን ስጠቀሙ በተለያየ መልኩ መመልከት ይቻላል፡፡
ጎፋ የሆነ ሁሉ ጎዝዳ ነው ማን ማንን ይላል፡፡ ነገር ግን ከሌላ ብሔር ጋር ከላይ በተጠቀሰው መልኩ የሚፈጠር
ነገር ቢኖር ለምሳሌ፡- ለላው ብሔር ጋ ታ ጎፌ ና ጎዝዳይ ልል ይችላል፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው; የራሱን
ጥንካሬ አይበገሬነት ለሌላው ልገልጽ ይችላል ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ለላ ብሔር የሆነ ሁሉ የጎፋን
ብሔር ተወላጅ በእንድሁ መልክ ልጠራ ልያሞግስ ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- ጎፋ ና ጎዝዳው ፣ጎፋ ና ጎዝዳቴ፣ በማለት
ጠንካራ፣ጎበዚ አይበገሬ መሆናችንን ልገልፅ ይችላል፡፡
የጎፋ ብሔረሰብ ከጥንት ጀምሮ ጎሻ፣ጎባን እንደወለደና እስከዚህ እንደመጣ ከሆነ ጎባ (Gooba) ማለት ኃያል
ጠንካራ አይበገሬ እንደማለት ሲሆን ይህንን ጥንካሪያቸውንና አይበገሬነታቸውን ጎፋዎች በንጉሳቸው ዳዳ ካማ
በጎፋ አከባቢ ጫቆ ቆጴ በሚባል ስፍራ ያስመሰከሩ በማይጨው በሳጋሌ በአዱዋ ያሳዩ ለዚህም ማሳያ በአዲስ
አበባ ጎፋ ሰፈር አዱዋ የዘመቱ የጎፋ አባቶች ማረፍያ ስፍራ የተሰጠው እስከ ዛሬ ታሪክ ሆኖ ለእኛ ለልጅ
ልጃችንን ቆይቷል፡፡ ስጠቃልል ጎዝዳ የጎፋዎች የአበገሬነትና የጥንካሬ መግለጫ በመሆን ሁሉም እሴቱን ልጠበቅ
ይገባል ባልተገባ መንገድ መጠቀም የለበትም፡፡
ታሪካዊ ዳራ
የኦይዳ ሕዝብ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ከሚገኙ ሁለት ነባር ብሔረሰቦች አንዱና የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ባህልና
ታሪክ ያለው፤ እስከ መሳፍንት ዘመን ማቢቅያ ድረስ የኦይዳ ብሔረሰብ በራሳቸው ባህላዊ አስተዳደር ሥርዓት
ሲተዳደሩ ቆይተዋል ፡፡ የኦይዳ መልካአ-ምድራዊ አቀማመጡ ፡- በሰሜን የገዜ ጐፋ ወረዳ፣ በደቡብ የዑባ
ደብረ-ፀሐይ ወረዳ፤ በምስራቅ የደንባ ጐፋ ወረዳ፣ በምዕራብ ሰሜን አሪ ወረዳ (የደቡብ ኦሞ ዞን) ያዋስናሉ ፡፡
የኦይዳ ዋና ከተማ ሸፍቴ ከጎፋ ዞን ዋና ከተማ ሣዉላ በ 9 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የኦይዳ ብሔረሰብ
ሰፍሮ የሚገኝበት የወረዳው የቆዳ ሲፋት 20,000 ሄክታር ሲሆን የወረዳው ስነ-ምህዳር ስንመለከት፡-ደጋ፣
ወይናደጋ እናቆላ ነው፡፡ የኦይዳ መልካአ - ምድር አቀማመጥ ውብ እና ማራኪ ከመሆኑ የተነሳ የተለያዩ
ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦች መገኛ እንድትሆን ተፈጥሮ አድሏታል ብባል ግነት አይሆንም ፡፡
(የኦይዳ ወረዳ መልካአ ምድራዊና አጠቃላይ ነባራዊ ሁነታ፤ ፆሊንቶ ቁርጥር 1.ጥቅምት፤2014 ዓ/ም፤ 43)
የሕዝቡ አመጣጥና አሰፋፈረ በአከባቢዉ ጥንታዊ ሲሆን ከአንድ ከተወሰነ ቦታ መጥተዉ የሰፈሩ አይደሉም፡፡
የሕዝቡ መጠሪያ ኦይዳ ሲሆን የቃሉ ልዩ ትርጉም ለምለም (ለመለመ) ማለት ነዉ ፡፡ ይህም ማለት ኦይዳ
የሕዝቡና የመሬቱ አጠቃላይ ስያሜ ነዉ ፡፡
የኦይዳብ ሔረሰብ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ከሚገኙ ሁለት ነባር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ሲሆን
የብሔረሰቡ ቋንቋ በደቡብ ክልል በአብዛኛው አከባቢ ከምነገር የቋንቋ ቤተሰብ ዘር ግንድ ከሆነው ከኦሞቲክ
የቋንቋ ቤተሰብ እንደመጣ የዘርፉ አጥኝዎች በህትመታቸው ያሰፈሩት መረጃ ያስረዳል ፡፡ የኦይዳ ሕዝብ
የምናገረው ቋንቋ ኦይድኛ፤ ሲሆን የማህበረሰቡ ኑሮ መሠረት ያደረገው በዋናነት በእርሻ ሥራ ላይ ነው፡፡
የማህበረሰቡ አመጣጥና አሰፋፈረ ስንመለከት ኦይዳ “ዞንጋር” ተብሎ ከሚጠራው ወንድና “ጉዳሮ” ተብላ
ከምትጠራ ሴት መነሻ እንደሆነ የሀገር ሽማግሌዎች ያስረዳሉ ፡፡ የሁለቱ ሰዎች መነሻ (መፍለቅያ) ቦታ በኦይዳ
ወረዳ በባልጣ ቀበሌ ከላይኛው ባልጣ “እንዳአክ ምንጭ” አከባቢተነስቶ ወደ ታችኛው ባልጣ ቀበሌ በመውረድ
መኖረያቸውን “ዞባ” በሚባል ንዑስ መኖር ጀምረዉ እዛዉ ዞባ የበኩር ልጃቸዉን ማዳር የተባለዉን ወልደዉ
ሀብት ንብረት አፍርተዉ ተደራጅተዉ በአከባቢዉ እርሻ በማረስ ኑሩዋቸዉን አደረጉ ፡፡ የመጀመሪያ የኦይዳ
ሰዎች የኑሩበት ጥንተዊ አከባቢ ዞባ የምባልበት ስፍራ እንደሆ በስፋት ይነገራል ፡፡ በዚህ በጥንታዊ አከባቢ የዛን
ጊዜ ሰዎች ለምግብነት የምሆኑ ሰብሎችን እና ስራስር እህሎችን በማረስ እንድሁም የተለያዩ ፍራፍረዎችን
በማምረት እየተመገቡ በምቾት እንደምኖሩ የሀገር ሽማግለዎች ያስረዳሉ ፡፡ በኦይዳ በጥንት ጊዜያት ሰዎች
ለምግብነት አዘወትረዉ የምጠቀሙት የእህል ዓይነት መካከል ለአብነት፡-እንሰት፣ ገፍስ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ፣
በቆሎና ለሎች የእህል ዓይነቶች ይገኛሉ ፡፡
በዞባ እየኖሩ ማዳር የተባለዉን የበኩር ልጃቸውን ወለዱ ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዋለዱ እና የህዝብ ቁጥር
እየጨመረ ስመጣ የሰው ልጆች አሰፋፈረ በተለያዩ የኦይዳ አከባቢዎች ማድረግ እንደተጀመረና እየጨመረ
የመጣው የሰው ልጅ ውልደት ማለትም ማዳር እና ሌሎች ልጆች እየተዋለዱና እየተባዙ ቁጥራቸው
እየጨመረ መምጣቱ በጎሳ ለመከፋፈል ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳበረከተ ይነገራል ፡፡ ከየወገናቸው የተለያየ
ስያሜና መጠሪያ ተሰጥቶ እስከአሁን በብሔረሰቡ የሚገኙ 42 (አርባሁለቱ) ጎሳዎችን ስንዘረዝር ፡- ዣዥንቴ፣
ሻራ፣ ጋኮና፣ አጋር፣ አንታል፣ ወርቃ፣ ካታ፣ ዙል፣ ዞባ፣ አማን፣ አይግር፣ ሸፋል፣ አዢ፣ ጋናዝ፣ ጐሀ፣ አሳ፣ አይካ፣
ሳርካ፣ ዛግርሳ፣ ሞያ፣ ዝና፣ ጉዳርቲ፣ ሳውራር፣ ጋርፃ፣ ኦቅ፣ ማንግ፣ ጋንጅሬ፣ ዛካ፣ ጐንት፣ ሶዙም፣ ሃይቦማል፣
ጎሎማል፣ ወርዝ፣ ጋድር፣ ጋውህና፣ ማሽን፣ ጋንሳ፣ አምፋርሲ፣ ዛግን፣ ዛል፣ ማርንት፣ እና አርጋማ ሲሆኑ ደቢ
እና ኦይድ ካፋሼ ከሚት ባልሴት የተወለዱ መንታል ጆች እየተባዙ ሲመጡ ”ደቢና” እና “ኦይዲና” የሚል የጎሳ
ስያሜ ተሰጥቶአቸው የኦይዳ ብሔረሰብ ቁጥር ወደ 44 (አርባአራት) ከፍብሏል፡፡ ኦይዳዎች በሁሉም አቅጣጫ
ከምያዋስኑዋቸው አጎራባች ህዝቦች ጋር በልዩ ልዩ የሰዉ ልጅ የዕለት ተዕለት ኑሮ እና እንቅስቃሰዎች የጋራ
የሆኑ የአብሮነት እሴት የሆነውን ሠላምን በማረጋገጥ በጋብቻ፣ በንግድና በልዩ ልዩ መንገዶች የተጋመዱ ፍቅር
ህዝቦች ናቸው፡፡
1. ካቲ (Kaati) ንጉስ
2. ቢታን (Bittan)
በኦይዳ ብሔረሰብ ባሕላዊ አስተዳደር ካቲ ሆነዉ የነገሡ ግለበሶች፡- 1 ኛ ካቲዣዦ 2 ኛ.ካቲ ዣልሽ 3 ኛ.ካቲ
ጉሳ 4 ኛ.ካቲ ኦይዲ 5 ኛ.ካቲ ድጋ 6 ኛ.ካቲ ቡዴ 7 ኛ.ካቲ አይሎ 8 ኛ.ካቲ ካቺ 9 ኛ.ካቲ ወጋ 10 ኛ.ካቲ ጎድ
11 ኛ.ካቲ ሳዴ 12 ኛ.ካቲ ካማ 13 ኛ.ካቲ አፋ 14 ኛ. ካቲ ግጋናቸው፡፡
2. ቢታን /Bitan/
ቢታን፤- ከካቲ ቀጥሎ የሚገኝ ባሕላዊ የሥልጣን እርከን ሲሆን ከሁለት እስከ አምስት ቀበሌያት የሚመራ
ሆኖ፤ በኦይዳ ብሔረሰብ ቢታን በዋናነት ባሕላዊ የእምነት ሥርዓት ላይ ያተኩራል፤ በራሱ አካባቢ ያሉትን
ሕዝቦች በሚያስተዳድርበት ወቅት ድርቅ እና ወረርሽኝ ሲከሰት የ“ዉርሶ” ሥርዓትን ይፈፅማል ፡፡
አለመግባባቶችንም ያስወግዳል ፡፡ ከካቲው የሚተላለፈውን ትዕዛዝ በተዋረድ ወደ ታችኛው እርከን ያወርዳል
፡፡ ከታችኛው እርከን የሚቀርቡ ጥያቄዎችን እና ሀሳቦችን ተቀብሎ ይፈፅማል ፡፡ ከአቅም በላይ ሲሆን ወደ
ካቲው ያደርሳል ፡፡
3. ጮማች /Comachch/
ጮማች፡-በካቲ አስተዳደር እርከን ከቢታን ቀጥሎ የሚገኝ ባሕላዊ የአስተዳደር እርከን ሲሆን በዘመኑ
አደረጃጀት የቀበሌ መዋቅር ነው፡፡ ጮማች የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት በድንብር ጉዳይ የሚነሱ
ጥያቄዎችን ያስተዳድራል፡፡ የስድብ እና የማዋረድ አቤቱታዎችን ይመረምራል፣ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ የተለያዩ
ባሕላዊ ሀይማታዊ ሥርዓቶችን ያስፈፅማል፡፡ የካቲው እና የቢታን የእርሻ ማሳዎች በወቅቱ እንዲታረሱ
ያስተባብራል፡፡ ግጭቶችን ያስወግዳል፤ ከአቅሙ በላይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቢታንን በመጋበዝ ችግሮቹ እንዲፈቱ
ያደርጋል፡፡ በጦርነት እና በአደን ወቅት ታዋቂ የሆኑ ግለሰቦችን ከሕዝቡ ጋር በማዋሄድ ጠንካራ ሥራን
ይሠራል፤ ምክንያቱም በጦርነት ወይም በአደን ወቅት የተላበሰው ጭካኔ ከሆነ ለዓይኑ የገደላቸውን የአውሬ
4. ጐዲ
ጐዲ፡- ይህየባህላዊ የአስተዳደር እርከን ከጮማች ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን፤እንደ ሌሎች የባሕላዊ መሪዎች
በግልና በቡድን የሚያከናውናቸው ተግባራት አሉት፡፡ ጐዲ በሚገኝበት አከባቢ ባሕላዊ መሪዎች እና ከሕዝቡ
ጋር በመቀናጀት በአካባቢው በዋናነት የሚከሰቱትን ባሕላዊ እና ሀይማኖታዊ ነክ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፡፡
ከሚተግባራቸው ጉዳዮችም ዋና ዋናዎቹ፤ በሚኖርበት አካባቢ ከጐሳዉ ወይም ከቤተሰብ አባላት አቅም በላይ
የሆኑ፤ በአከባቢዉ ሕዝብ እና በብሔረሰቡ ባሕል ዉግዝ የሆኑ ጉዳዮች ሲከሰቱ የወግ እና የባሕል መተላለፍ
ኃጢያትን ወይም ጐሜን /Gome/ የማንፃት ሥርዓትን ያስፈፅማል፡፡ ከላይኛው እርከን በተዋረድ የሚተላለፉ
ትዕዛዛትን ያስፈፅማል፡፡ የካቲ፣ የቢታን እና የጮማች እርሻዎችን /Maddo/ ያሳርሳል፡፡ ከሕዝቡ የሚቀረቡ
ጥያቄዎችን ወደ ላይኛው እርከን ያደርሳል፡፡ በተለያዩ ጉዳዮችም ሕዝቡን ያማክራል፤ መዋጮዎችን
ያሰባስባል:: ለካቲ፣ለቢታን እና ለጮማች የሚሰጥ እህል አሰባስቦ ለሚመለከታቸው ያቀርባል፡፡ በፌሾ /Feesho/
በዋናዉ የልቅሶ ቀን፣በደቦ ዕለት ዝናብ እንዳይዘንብ፤ከሱ ከፍ ላለዉ አካል በዕለቱ ወደ አምላክ
እንዲማፀንላቸዉ መልዕክት ያስተላልፋል ፡፡
5. ቡጫ /Buca/
ቡጫ፡- /Buca/ የመጨረሻ የመዋቅር እርከን ሲሆን አወቃቀሩም ከሕዝቡ በተወጣጡ የሀገርሽማግሌዎች
ስብስብ ነው ፡፡ ይህ መዋቅር እጅግ የሚከበር፤ የሚፈራ እና ተሰሚነት ባላቸው የሀገር ሽማግሌዎች ዳኝነትን
የሚሰጡበት መዋቅር ሲሆን፤በተጨማሪም እንዲያከናውኗቸው፤ የተሠጣቸው ሥልጣንም፤የአስተዳደር
እርከኖችንም የመሾም እና የመሻር ኃላፊነት ተሰቷቸዋል፡፡ በአከባቢያቸው ለሚፈጠሩ ማናቸውም ግጭቶች
እና አለመግባባቶች የመጀመሪያ ደረጃ አጣሪ እና ዉሳኔ ሰጪ አካል ሆኖ ከታች ወደላይኛው እርከን የሚተላለፉ
ጉዳዮችን ከላይኛው እርከን ጋር እየተመካከሩ ዉሳኔ የመስጠት እና በሚሰጡ ዉሳኔዎች በማይስማሙትም ላይ
የመጨረሻ እርምጃ የመውሰድ ሥልጣንም አላቸው፡፡ የእርምጃ ዓይነቶችም ከጎረቤት እሳት እንዳይጭሩ
መከልከል ከብቶቻቸው ከሕዝቡ ከብቶች ጋር በግጦሽ እንዳይሰማሩ የመከልከል፣ ልጆቻቸው ከሕዝቡ ልጆች
ጋር በሜዳ እንዳይጫወቱ መከልከል እና ከማናቸውም የማሕበራዊ ጉዳዮች የማግለል እና ወዘተ… ናቸው፡፡
(መረጃ ሰጪ፡ የብሔረሰቡ ተወላጅ የሆኑት ፤ አቶ አየለ አሸናፊ፣ አቶ እንግዳ እንድርያስ እና አቶ ደስታ ካሰሳ)፡፡
ለመስቀል በዓል ካለው ከበሬታ የተነሳ ገና በዓመቱ እስከ ሚመጣ ታስቦ ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ ለልጆች
ልብስ በዕለቱ የሚዘጋጅ ምግብና መጠጥ በተለይ ለመስቀል ሥጋ ተብሎ ዓመቱን በሙሉ በመቆጠብ በዕድር
ዝግጅት ከመደረጉም ባለፈ ለመስቀል ተብሎ ለሚደረግ ነገር ሁሉ ሳይሰስት ማንም የሚፈጽመው ይሆናል፡፡
ለእርድ የሚሆኑ ሰንጋዎች ተገዝተው ይዘጋጃሉ፣ ለገንፎ የሚሆን በቆሎ ታምሶ ይፈጫል፣ ቡላ ና ቆጮ
እንዲሁም የሃረግ ቦዬ ይዘጋጃል፣ ለቦርዴና ለጌሾ ጠላ የሚሆን ዝግጅት ይደርጋል፣ ለጠጅና ለብርዝ ማር
ይቆረጣል ይጠመቃልም፡፡ አከባቢው አዳይ አበባ ሲደመቅ በብሔረሰቡ አጠራር ቤላ ጭሻ (Bella ciisha)
ጋራው ሸንተራሩ ሲያሽበርቅ አርሶ አደሩ በብሔረሰቡ ዘንድ በስፋት ከሚታወቀው ምርት በዋናነት ጤፍን
በጊዜው ከአረም ነፃ የሚያደርጉበት ሰብሉን አብቦ የሚደምቅበት ነው፡፡ ወረሃ መስከረም መግቢያ የመስቀል
በዓል መድረሻ ለመሆኑ መግለጫ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም መስቀል በዓል ሲቃረብ ልጆች በተሠማሩበት የሥራ
መስክ ላይ ሆነው ከብቶችን በመጠበቅ ላይ፣ ለእንጨት ለቀማ፣ ውሃ ለመቅዳት እና ሣር ለማጨ ከአንድ በላይ
ሆነው በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ያለማንም ቅስቀሳ ሲያዘሙ ይደመጣሉ፡፡
ሎያ ባይ ሎያ ባይ
ሎያ ማሰቀላ ባይ
ማስቀላ ኡፋይሳ ባይ
ሙሳ ኡሻ ባይ ሲሎ ይዳመጣሉ፡፡
ይህ ማለት መስቀል እንኳን መጣህልን!
የእኛ ደስታ! የእኛ መዝነኛ መስቀል እንኳን መጣልህን! በማለት በጉጉት ስለሚጠባበቁት መስቀል በዓል
ሲያዜሙ ይደመጣሉ፡፡
በጎፋ ብሔረሰብ ለመስቀል በዓል የምግብና መጠጥ አዘገጃጀቱም ሆነ በሌላ የሚሰጠው ትኬረት ካሉት በዓላት
ልዩ የሚያደረገው ሲሆን ለመስቀል ተብሎ የሚወጣው ወጪ የማንን በር የሚያንኳኳ እና ያለውን የሌለውም
አመቱን ሙሉ በመቆጠብ ሳይሳሳ የሚያዘጋጅበት መሆኑ ነው፡፡
በተለያ በመስቀል በዓል ከሁሉም ቅድሚያ የሚሰጠውን የቤትሰብ አባል ሆነው ተለያይተው የቆዩት
የሚገናኑበት ከአከባቢው በተለያዩ ምክንያቶች ርቀው ያሉት በዳመራ ዕለት በመገናኘት ናፍቆታቸውን
የሚወጡበት፣የተጣሉት የሚታረቁበት፣ሀዘን ውስጥ የነበሩ ሀዘኑን የሚረሱበት፣የተነፋፈቁየሚገናኙበት እና
የትዳር ጓደኛ የሚይዙበት ዓይነተኛ ቀንና ጊዜ መሆኑን ልዩ ያደረገዋል፡፡
1. የምግብ ዝግጅት
በጎፋ ብሔረሰብ ለመስቀል በዓል የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች የሚዘጋጁ ሲሆን በዋናነት በዳመራው ዕለት
የሚበላው ከበቆሎ የሚዘጋጅ ገንፎ ሲሆን ስያመውም / Masqqala dhote /በመባል ይተወቃል፡፡ አዘጋጃጀቱም
ከሣምንት በፊት ወተት በማጠራቀም ምንም ውሃ ሳይታከልበት ከበቆሎ ዱቄት በተነጠረ ቅቤ፣በአይብና
ይህም በመካከላቸው መደማመጥና መከባበር እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡ የችቦ አለኳኮስን በተመለከተ በመጀመሪያ
ቀኑ ደንገዝገዝ ወይም ለዓይን ያዝ ስል አባወራው በወንድ ቁጥር የታሰረውን ችቦ አጠቃላይ በመያዝ ምሶሶ
ካለበት ጎጆ ቤት ውስጥ ለገንፎ ከተጣደው ድስት ስር ከሚነድ እሳት የሁሉም ችቦ ከለኮሰ በኃላ በቀኝ
በመታጠፍ ምሶሶሰውን በመዞር ምሶሶሰውን የከብቶች ጋጣና በበሩ ላይ በቀኝና በግራ የቆሙትን መሪ
ግድግዳዎችን ማስቃላ ዮ! ዮ! እያሉ በተለከሰው እሳት እየነካካ ከቤት ወደ ደጅ ይወጣል፡፡ አባትም ማስቃላ ዮ!
ዮ! እያለ ችቦን በዕድሜ ደረጃቸው ካካፈለ በኃላ መሃል ላይ ሆኖ በወንዶች ታጅቦ ማስቃላ ዮ! ዮ! ዳናው ዳና
እያሉ በዱቡሻው ስር ወደ ተተከለው ደመራ ደርሰውን ዳመራውን ዞረው አባት በመጀመሪያ ችቦን ሲያስቀምጥ
ሌሎች በዕድሜያቸውመሠረት ያሰቀምጣሉ በህላዊ ጨዋታዎችን ይጫወታሉ ይጨፈራሉ፡፡
ችቦ ሲታሰርና ዳመራው ሲተከል ከወንዶቹ መካከል በዕለቱ መገኘት ያልቻለ ቢኖር የለም ተብሎ ደመራ
ሳይወጣለት አይቀርም፡፡ ለሌሎች የሚደረገው ሁሉ ለእርሱም ይደረግለታል፡፡ በሌላው ልጅ ምትክ የታሰረውን
ችቦና ዳመራ አባት ይይዛል፡፡ ዳመራው ከተለኮሰ በኃላ ማስቃላ ዮ! ዮ! እያለ ወደ ቤት ተመልሶ ከእናት
ከእነዚህም ለአብነት
የመልከአ ምድር አቀማመጥንና የመሬቱን ለምነት መግለጫ የመሆኑ፣
የብሔረሰቡ ተወላጆች የተለያዩ ሰብሎች አምራችና የሥራ ተነሳሽነታቸው ከፍተኛ መሆኑን
አመላካችነቱ፣
በግል ከመሠራት ይልቅ ተሰባስበው በጋራ የማምረት ልምድ ያካበቱ መሆናቸውን፣
የሠላም ማብሰሪያ የደስታና የፍቅር መግለጫ ዋነኛ ድልድይ የመሆኑ፣
የትዳር ጓደኞችን የመምረጫ ሁነት ስለመሆኑ በዓይነተኝነት ሊጠቀሱ የሚገቡ ናቸው፡፡
የመስቀል ዘፈኖችና አጨዋወት ሥራዓቶች ከባህሪያቸው አንጻር በ 3 የከፈላሉ፡፡
እነዚህም በመስቀል ከጅማረው ቀን እስከ መጨረሻው ወይም እስከ ሽኝት ቀን ድረስ የሚዘፈኑና የሚጫወቱት
የጫዋታ ዓይነቶች ጋዜ ወይም ኢኤ፤ ጋሼ፣ሎያ፣ጋሳሊያን ኦይካ፤ ጊሶሌ እንደ ትንፋሽ መሰብሰቢያ ዘፈኖች
ሲበሉና ሲጠጡ የሚዘፈን ወይም የሁል ጊዜ ዘፈኖች ተብሎው ሊጠቀሱ የሚችሉት ደግሞ ባራንቼ፣ላሌና ሄሎ
ሄራሳ የሚባሉው ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በዋናነት የመስቀል በዓል የመጨረሻው ቀን ለሽኝት (ሞይዞስ) የሚዘፈን በብሔረሰቡ አጠራር
"ሆሴ" (Hosse) ይባላል፡፡ በመሆኑም ከሌሎች በብሄሩ ከሚከበሩ በዓላት ይህ ጋዜ ማስቃላ ይጅግ የተለዬና በብዙ
የጨዋታ ዓይነቶች የታጀበ ነው፡፡ ጋዜ ማስቃላ (መስቀል) በጎፋ ብሔረሰብ ከዳመራው ዕለት ጀምሮ በቀጣዮች
7/ሰባት ቀናት ማለትም እስከ መስቀል ሽኝት ቀን ደረስ ባለው በከፍተኛ ድምቀት የሚከበር ሲሆን በዚህ ጊዜ
አዳዲስ ክስተት ስፈፀም ወይም የሚከናወን ሥራዓት አላቸው፡፡
እንደ አጋጣሚ ሆኖ በሚያከብሩበት አከባቢ በደመራው ዕለት ሰው ቢሞት ቀብርና ሌሎች ሥራዓቶችን
በሟቹ ደጅ ላይ ነዋሪዎች ተሰብስበው ይፈፅሙና የማይለቀስበት በመስቀል እሳት ተበልቷል
8 ኛ. ላሌ የላሌ ትርጉሙም
ሀገርን ከሀገር ጋር በማወዳደር ጀግንነት ምርታማነትን ለማሳየትና ለማወዳደር ህብረተሰቡም ሆነ
ግለሰቡ ይሞግሳል፣ ይወደሳል፡፡ የብሔረሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ይዘትን ለመግለጽም
ያገለግላል፡፡ ጨዋታውን ድምፃዊያን (አውጪዎች) ተራ በተራ ሆኖ ሲያቀነቅኑ ታዳሚዎች ይቀበላሉ፡፡
ወንዶችና ሴቶች ከድምፁ ጋር ዜማንና ምቱን አዋህደው ይጨፍራሉ፡፡
9 ኛ. ሄላሎ (Heelalo)
ሄላሎ ይህ ጨዋታ መስቀልን በደስታ ከተቀበሉ በኃላ ከሦስትና ከአራት ቀን በኃላ የሚጫወቱት ጨዋታ
ነው፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት በጉጉት ሲጠባበቁ የቆዩትን የመስቀል በዓልን በደማቅ ሁኔታ
ሲቀበሉ በደስታ እየጨፈሩ እየዘለሉ በሁለት እና በሦስት ቀን ናፍቆታቸውን ሲወጡ ይደክማቸዋል፡፡
የሄላሎ ጨዋታ ግን እርስ በርስ በመተቃቀፍ ክብ ሠርተው በእንድነት በተረጋጋ መንፈስ የሚጨፈሩት
በመሆኑ ይመረጣል፡፡
10 ኛ. ወሎ ቦላዶ (Wollo Bolado)
ይህ ጨዋታ ከላይ በተራ ቁጥር ዘጠኝ ላይ ከተጠቀሰው ሄላሎ ከሚባለው ጨዋታ ጋር ተመሳሳይነት
ያለው ሲሆን ዜማውም ሆነ አጨፋፈሩ ከሄላሎ ጭፈራ የመፍጠን ዓይነት ሁኔታ ሲኖረው እጅግ
ማራክና ቆሞ ለሚመለከት ሰው ቀልብ የሚስብ የመስቀል ጊዜ ጨዋታ ነው፡፡
11 ኛ. ሊላ (Liilla)
ሊላ ሆያ ኤራ ሊላ
ሊላ ማስቃላ ማታ
ሆሴ /Hosse/ እና ጋዜ /Gaze/ በተደጋጋሚ በዕለቱ የሚጫወቱት ሲሆን ከሌሎች ቀናት በተለየ መልኩ
በከፍተኛ ስሜትና ደስታ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ በተለይ ሆሴ ጨዋታ ተቃቅፈው እየጨፈሩ ፊታቸውን ወደ
ምስራቅ በማዞር 10 ሜትር ያህል ወደ ፊትና ኃላ እየሄዱ ጨዋታውን በድምቀት የሚጫወቱት ሲሆን
ወደ ምሰራቅ የዞሩበት ምክንያት የሠላም፣የፍቅር እና የጥጋብ ዘመን ይሆናል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡
ታዲያ በዚህ ሽኝት ጊዜ በአከባቢው ታዋቂ የተባሉ ሽማግለዎች ይገኛሉ፡፡ ቢታንቴዎች
የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት በተገኙበት ፊታቸውን ወደ ምስራቅ የደርጉ ተጫዋቶች ወደ ፊት 10
ሜትር እየጨፈሩ ከተጓዙ በኃላ በአንድነት እጃቸውን ከፍ በማድረግ ማስቃላ ዮ ! ዮ! ሳሮ ባዳ
ሳሮ ያ! መስቀል በደህና ሄደ በደህና ተመለስ እያሉ በመካከላቸው የሚገኘውን ቢታንቴን
ተከትለው በእጃቸው የያዙትን የአዳይ አበባ ወደ ምስራቅ ይወረውራሉ፡፡ በብሔረሰቡ አባባል
ሆሴ ማስቃላ ላይታን ሳሮ ያ! መስቀል ደህና ሁን በዓመቱ በደህና ተመለስ እያሉ በድምቀት
እየጨፈሩ ማስቃላ ዮ! ዮ! ሳሮ ባዳ ሳሮ ያ! መስቀል በደህና ሄደ በደህና ተመለስ ብለው ለአንዴና
ለመጨረሻ ጊዜ የሚሸኙበት ሥርዓት አላቸው፡፡ በእንዲህ ዓይነት መስቀል ሽኝት ከተደረገበት
ዕለት ገምሮ እስከ መጪው ድረስ በብሔረሰቡ የመስቀል ነገር አይነሣም፡፡
(በአቶ ድንበሩ ድርቤ ዲላ፤ ጳጉሜ 2014)
በጎፋ ስለ መስቃላ በዓል ሲነሣ አብሮ የሚነሱ የመስቀል በዓል መገለጫ የሆኑ ሥነ-ቃሎች እንደሚነሱ የጎፋ ዕድሜ
ባለፀጋዎች ይገልፃሉ፡፡ ምክንያቱም ሲያብራሩ ሥነ-ቃል ጎበዙን የበለጠ እንድጎብዝ የምያደርግ ሲሆን ስነፉንም
ከስንፍናዉ እንድወጣና ከጎበዞቹ ተረታ እንዲቆም ያደርጋል የሚል ዕምነት ስላለ ነዉ፡፡ በሌላ መልኩ በመስቀል ወጣቶች
ለጋብቻ የሚመራረጡበትና እርስ በርስ የምዋደዱበት (Mate Selection) የምያደርጉበትና ፍቅር የሚጀምሩበት ጊዜና
ሥፍራ ነዉ የሚል ሀሳብ አላቸዉ፡፡ መስቀል እንደ ዘመን መለወጫ ተወሰደ ላሳለፉት ዓመት ፈጣሪያቸዉን
የምያመሰገኑበትና ለቀጣዩ ዓመት የሚለምኑበት እንድሁም በመስቀል ጥሩ ጥሩ ሰዉነትን የምገነቡ ምግቦች
(Delicious Food) ምበላበትና ዕረፍት የሚወስድበት ጊዜ ስለሆነ የመስቀልን መምጣት በጉጉት በመጠባበቅ በተለያዩ
ሥነ-ቃሎች ይገልፁታል፡፡
1 ኛ ማዝቃላይ ማልኦ ሙዜስ (Mazzeqqalay Mal7o Muzes) ከላይ እንደተገለፀዉ መስቀል ጥሩ ጥሩ ምግብ ያበላል
የሚል መልዕክት ያስተላል፤ ስለዚህ መስቀል ይጠበቃል፡፡
2 ኛ ለላዉ ደግሞ መስቀል በማህበረሰቡ መካከል ልዩነትን በበጎ መልኩ የሚያመጣም ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ተዘውትሮ በስነ-
ቃል የሚነገረዉ፡- ‹‹ማስቃላይ ዱሪያ ዱሪየስ
መስቀል በዓመት አንድ ጊዜ የሚመጣ በዓል ስለሆነ ሰፊ ዝግጅት ስለምፈለግ ጠንካራና ጎበዝ የሆኑ ሰዎች በጊዜ ሲዘጋጁ
ሰነፎች በዓሉ ሲደርስ ነው ተፍ ተፍ ማለት የሚጀምሩበት ስለዚህም ገንዘቡን፤ እህሉን፤ ቅቤውንንና በቤቱ የሌላቸዉን
ነገሮች ለመበደር ሀብታም ቤት ለሚሄዱና በእጥፍ ስለሚከፈል ለባለሀብቱ እጥፍ ትርፍ ይገባል፤ ድሀው ግን የበለጠ
ይደሄያልተ ብሎ ይታወቃል፡፡ በመስቀል እርሻ አይታረስም የመብላት የመጠጣትና የመዝናናት ጊዜ ስለሆነ በመስቀል
እርሻ የምያርስ በሥነ-ቃል ይነገርለታል፡፡ ሌለው ደግሞ በመስቀል የተዉሶ ልብስ አይለበስም፡፡ ነገር ግን አንድ
የተዉሶልብስ (ቀምስ) ለብላ ለመስቀል ጫዋታ የሚትሄድ ሴት መንገድ ዳር ማሣ ያለዉን ገበሬ ሲትመለከት ለምኖ
ባመጣው በሬ በመስቀል እርሻ ሲያርስ አግንታ ‹‹ወሴ ቦራ ወሳ ጋሼ ጎየይሶ ጋዴይ ጋኮ›› ትርጓመው ለምነህ ባመጣሄው
በሬ ወደታች እያልክ የምታርስ ማሣው ታርሶ ይለቅልህ!
እሱም ሲመለከታት የትዉሶ ቀሚስ ለብሳ ለመስቀል ጭፍራ መሄዷንአ ግኝቶ (አይቶ) ጋርሳ ቃሚሴያራ ጋዴ ቤሳ ማአዳ
ማስቃላ ጋዛናዉ ቢያሬ አዴ ኤኮ ይላታል ይህ ማለት ለምኖ ለአንድ ቀን እርሻ በመጣ በሬ ወደ ላይ እየተባለ ይታረሳል
እንጅ ወደታች ካለ መልሶ መላልሶ ያረሰበትን ስለሚያርስ ወደ ታች የሚለዉ ሰነፍ ገበሬ መሆኑን ሲያመላክት በመስቀል
ጊዜ ማረሱ ሌላኛዉ የስንፍና ምልክቱ መሆኑን ያመላክታል፡፡ሌላዉ ለመስቀል የተዉሶ ልብስ የሚትለብስ ሴትና አጭር
ልብስ የሚትለብስ ሰነፍ ሴት መሆኑዋን እሱም ጎሼም አድርጓታል ማለትነዉ፡፡
በጎፋ ሴቶችታ ርክ ዉስጥ Gallo Xammatto (ጋሎ ፃማቶ) የተባለች ሴት ትልቅ ስፍራ ያላት ሴት እንደሆነች
ይናገራሉ:: በአንድ ወቅት መስቀል ሊደርስ ሲል ጦርነት ይነሳል፡፡ ስለዚህም የጎፋ ካዎ ጦርነት ሲያዉጅ እንዲህ ይላል፡፡
Guppiya parra toggadda guppo matha ganxada gumbo toorra oykadda kawo gadho goocha
Guuttoy qaaxin commeysi shoci wodha oyqada ollancha gembo qoxanaw gadha adha!
በዚህ አዋጅ መሠረት በመስቀል ዋዜማ ተዋጊዎቹ ወደ ጦር ሜዳ ሲሄዱ ፈሪዎቹ ለእርሻ ሄደዉ ተመልሰዉ የመስቀል
ጠላ ለመጠጣትበ አንድ ቦታ ተሰብስቦ እያሱ Gallo Xammatto (ጋሎ ፃማቶ) የተባለች ሴት ትመጣና 1 ኛዉን
እግሩዋን ከፊ አድርጋ ፌስ ትለቃለች፡፡ ወንዶቹም በወንድ ላይ የሚትፈሳ ሴት ይህች ሰነፍ ከየት መጣሽ ሲሏት፤ እሷም
መልሳ ወንድ ጦር ሜዳ ወንድን እያገላበጠ የሀገርን ሉዓላዊነት ሲያስከበር ጠላ ተራ የተሰበሰበው እንዴት ዓይነት ሰነፍ
ወንድ ብቻ ነው? በማለት ለጦርነት ትቀሰቅስ ነበርይባላል፡፡
በጎፋ ታሪክ ውስጥ እንሰትና ወተት አይነጣጠሉም፡፡ የማንቤት ነው? የሚያስብላዉ እንሰት የማን ልጅ ነው
የሚያስብለው ወተት፤ ይባላል፡፡ እንሰት ድርቅን ከመቋቋም አልፎ በመስቀል ዝግጅት ቡልኦ (ኢቲማ) የሚሠራው
ከእንሰት ነው፡፡ ሌላዉ ህፃናት በጥሩ ጤንነት እንድያድግ ወተት ሰለሚያስፈልግ ነው ይህ የተመስለው፡፡
በመስቀል የተጣላች ሴት መታረቅ አለባት ካልሆነ ሌላ ሚስት የማግባት ዕድሉ የሰፋ ነው፡፡ በዝህ መሠረት የቀድሞ
ምስቱ የሆነች በመስቀል ጊዜ ተጣልታ የተለየች ለመጪዉ መሰቀልም ተለምና እንቢ በማለቷ ተለያይቶ ሌላ አድስ
ሚስት ያገባል፡፡ መስቀል ከመድረሱ በፍት ይህች አድሷ ሚስት እንሰት መፋቅና ዝግጅት ማድረግ ነበረባት፡፡ ነገር ግን
የዱሮ ሚስት አድሷን በአሽሙር ትነካለች እንድህ ስትል Tokkonna Tonchayarre Ittimmay
Uttoo! ሲትል አድሷ ደግሞ
5 ኛ፤ ሌላዉ በመስቀል ለቅሶና ሐዘን የለም ይባላል ስለዚህ Masqallay Kayo Doggisses መስቀል ሐዘንን ያስረሳል፡፡
በመስቀሉ ዕለት ደግሞ ሰው ከሞተ ማስቃላ ታሚ ሚስ /Mazgalla Tammi Misi/ ይባላል እንጂ አይለቀስለትም፡፡
ሰለዚህ መስቀል የሚደስትቱበትና የሚዝናኑበት እንጂ ሐዘን የለም ይላቸዋል፡፡
6 ኛ፤ በመስቀል ዕለት የተወለደ ልጅ፤ ወንድ ሲሆን ስሙ ማዝቃላ; ሴት ሲትሆን ደግሞ ስሟ ማስቃሎ /Masqallo/
ተብሎ ይሰይማል፡፡ ስለዚህ መስቀል ትልቅ ቦታ ያለውና በብዙ ሥነ-ቃል የሚነገሩ አነጋጋሮችን ያካትታል በመሆኑም የጎፋ
ሕዝብ ቱባ ባህልን አምቆ የያዘ ክብረ በዓል ነው ማለት ይቻላል፡፡
ህዝቡ በየዓመቱ እንድህ አይነቱ ልምላመ አና ምቾት ይምጣልን እያሉ ዮኦ ኦይዳ ማስቃላ በማለት አድስ
ዓመትን ማክበር እንደ ጀመሩ ይነገራል፡፡ በኦይዳ ብሔረሰብ ዘንድ መስቀል በልዩ ድምቀት የምከበር ታላቅ
ህዝባዊ መሠረት ያለዉ ወካይ ባህል ነው፡፡ የመስቀል በዓልን በኦይዳ ሩቅ ያለ ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና
በዕለቱ በየበቱ አቅም በፈቀደ መልኩ እያከበሩ ቤት ያፈራውን ከጎረበት ጋር እና ዘመድ ጠያቅ ከለላቸዉ እና
ጧር ቀባር ከለላቸው አቅመ ደካሞች ጋር አብረው የምያከብሩት በዓልነው፡፡ ይህን ክብረ-በዓል ብዙዎች
በኦይዳ በናፍቆትና በከፍተኛ ጉጉት የምያከብሩት ሲሆን በዮኦ ማስቃላ የተለያዩ በዓል በዓል የምሸቱ ነገሮች
በበዓሉ መቃረብ ወቀት መታየት የምጀምረው ገና ለበዓሉ ሦስተ ወራት ስቀሩት በልዩ ትኩረት የተለያዩ
ቅድመ ዝግጅቶች ያደረጋሉ፡፡ (ነሔሰ 18/2014 ዓ/ም አቶ አየለ አሸናፊ)
በኦይዳ ብሔረሰብ ዘንድ የመስቀል በዓልን ሁሉም የብሔረሰቡ ተወላጆች በዓመት አንድ ጊዜ በወረሃ
መስከረም ለአንድ ሳምንት ያክል እና ከዚያም በላይ ለሆነ ቀናት እንደ አቅሙ በድምቀት ያከብራል፡፡ ለመስቀል
በዓል በብሔረሰቡ አባላት የቅድመ-ዝግጅት ሥራን ሁሉም በመከፋፈል ዮኦ ማስቃላ ስደርስ ምንም ሳይቸገሩ
በሳቅ በደስታ ማክበር እንድችሉ በቅድምያ ከምሰሩ ሥራዎች መካከል ምግብና መጠጥና ለበዓሉ ማድመቅያ
ለልጆችና ሴቶች የምገዙ ወይም የምደረጉ አልባስ ዝግጅት ይገኙበታል፡፡ በዓልበም መጣበት ጊዜ ዕለቱን
በደመቀና እጅግ ባማረ መልኩ ለማክበት የምፈልግ ሰዉ ገና በዓሉ ሳይደርስ ብር መቆጠብ እና ስለመጭዉ
ዘመን ከወድሁ ማሰብና መጨነቅ የተለመደ ነባር የቁጠባ ባህል ማኒቅያ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ሰው
በኦይዳ ቁጠባ ያደርጋል ማለት ነው፡፡
ዮኦ ማስቃላን ለማክበር በኦይዳ ብሔረሰብ ለአቅመ አዳም የበቃ ትዳር የመሰረተ ወንድ ሰው በየቤቱ ለበአዓሉ
ድምቀት የምሆኑ ነገሮችን የማመቻቸት ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በዚህ መሰረት ወንድ ሰው የእርድ በሬ
በዮኦ ማስቃላ ሴቶች ከፍተኛ የሥራ ጫና ያላቸዉ ሲሆን ከበዓሉ መጀመርያ ቤት ዉስጥ የተለያዩ ተግባራትን
ያከናዉናሉ ቤት ማዘጋጀት (ማስዋብ) በበዓሉ ዕለት ለምበላና ለምጠጣ ምግብ እህል መሰብሰብ እና
መፍጨት፡ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች በኦይዳ ለበዓሉ የሤቶች መተባበርያ ማህበር ሁለትና ከሁለት ሴት በላይ
በመሆን በቡድን ይደራጃሉ፡፡ በምደራጁት የበዓል ሥራ ላይ ሴቶች በጋራ በመሆን ለበዓሉ እህል
ይፈጫሉ፤ቅመማ ቅመም ያዘጋጃሉ፡፡ ይህ የሴቶች የሥራ ማህበር ወጋል ተብሎ ይጠራል፡፡ ለበዓሉ የሚፈጩ
እህል ዓነቶች፡- ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ዘንጋዳ (ቀይማ ማሽላ)፣ ገብስ እና ከቅመማ ቅሜም ዓይነቶች
(አብሽ፣ ተልባ፣ ነጭ አዝሙድ ና ጥቁር አዝሙድ፣ ጅንጅብል፣ ፌርጋ (በርበሬ)፣ በሶብላ፣ ድንብላል፣ ኮሮርማ
(ኦካሼ) እና ፈጦ (ስብካ) በወጋል ሆነው እንደ የግለሰቦች ኢኮኖሚ ደረጃ የወጋል አባላት ከራሳቸዉ ጋር
የምፈጩበትን ወፍጮ ይዘው በመምጣት እየተጫወቱና እየዘፈኑ የዮኦን ማስቃላ እህል በደስታ ይሰራሉ፡፡
በኦይዳ ማህበረሰብ በዮኦ ማስቃላ የሚጠጣው ባህላዊ መጠጥ ከገብስ፣ ከጤፍ የሚሰራ ጠላ አለ፡፡ በብሔረሰቡ
የምጠጣው ጠላ ዳና ተብሎ ይጠራል፡፡ ዳና ማለት በኦድኛ ቋንቋ ቦርደ ጠላ ማለት ነው፡፡ በኦዳብ ሔረሰብ
ለዮኦ ማስቃላ ዝግጅት ሦስት ዓነት ቦርደ ጠላዎች በልዩ ጥንቃቀ ይዘጋጃል፡፡ 1 ኛ ባሽንቻ፣2 ኛ ሶንገ በመባል
ይታወቃላ፡፡ ሦስተኛው ጠላ ብዙም ያልጠነከረ ኃይሉ የቀነሰ ጠላ ሲሆን በክብረ-በዓሉ ዕለት ሰው በየፍላጎቱ
(መረጃዉን የሰጡት የብሔረሰቡተ ወላጆች (አቶ ደስታካሳ፣አቶ ግዳሻዉግዛ፣ ወ/ሮ ታመነች ድንቁእና ለሎች
የብሔረሰቡ ተወላጆች፡ነሔሰ/2014 ዓ/ም)
(መረጃዉን የሰጡ የብሔረሰቡ ተወላጆች (አቶ ደስታካሳ፣አቶ ግዳሻዉ ግዛ፣ ወ/ሮ ታመነች ድንቁ እና
ለየብሔረብ ተወላጆች፡ነሔሰ/2014 ዓ/ም)
በኦይዳ ብሔረሰብ የግጭት መንስኤዎች ተብለው በዋናነት የሚጠቀሱት፡- የድንበር መተላለፍ፣ የሴት
ልጅ ጠለፋ፣ በግጦሽ መሬት፣ ነፍስ መግደል እና በሌሎችም ወጣቶች መካከል የሚፈጠሩ የሃሳብ
አለመግባባቶች የግጭት መንስኤዎች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሠረት ኦይዳ ብሔረሰብ ከጥንት
ጀምሮ በባሕላዊ የአስተዳደር ሥርዓቱ እስከ አሁን ድረስ የዘለቀ ነዉ፡፡ በማሕበረሰቡ ግጭቶች እንደየ
ግጭት በዓይነቶች ተለይተዉ በየደረጃው ባሉ ባሕላዊ የአስተዳደር መሪዎች አማካኝነት በተለያዩ ደረጃ
ባሉ /Buca/ ወይም ባሕላዊ የመሰብሰቢያ አደባባይ ግጭቶችን ይፈታሉ፡፡
በፎቶ ( )
ምስል፤- ግጭቶች በተለያዩ ደረጃ ባሉ /Buca/ ወይም ባሕላዊ የመሰብሰቢያ አደባባይ ግጭቶችን ሲይፈቱ
በኦይዳ ብሔረሰብ የሰው ነፍስ ያጠፋ ግለሰብ መፀፀቱን ገልፆ ሲቀርብ ካቲዉ ጉዳዩን መርምሮ የሟች
እና የገዳይን ወገኖች በአንድ ላይ በመሰብሰብ ገዳዩን የጦር ጫፍ አስነክሰው በባሕላዊ የአምልኮ እና
ቃለ-መሀላ ሥርዓት በማስፈፀም በቡጫ ላይ ይቅር አባብሏቸው፣ አግባብቷቸው እና ሠላም አውርደው
እንዲኖሩ የሚደረግበት ሥርዓት ነው፡፡ የባሕላዊ እርቀ-ሠላም አወራረድ ሂደቱን በተመለከተ የሟች
ቤተሰብ እና የገዳይ ቤተሰብ አንዳንድ በግ እንዲያቀርቡ ከተደረገ በኋላ ተጨማሪ አንድ በሬ ቀርቦ
ታርዶ ሁለቱንም በጎች አንድ ላይ በማድረግ ደማቸውን እንዲቀላቀል ይደረጋል፡፡ የሁለቱ በጎች
ደማቸውን የመቀላቀል ምሳሌ በደም ተለያይተን በደም አንድ ሆነናል የሚል ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የበሬዉ
ቆዳ ተገፎ በእንጨት ክብ ቅርፅ ያለዉ ቀዳዳ ተሰርቶ የሟች እና ገዳይ ቤተሰብ ተወካዮች በቀዳዳው
እንዲያልፉ የሚደረግ ሥርዓት ሲሆን ይህም በኦይደኛ ቋንቋ ቡእንቴ /Bu7intte/ /አደባለቀ/ ማለት ነው፡፡
እንደዚህ የሚያደርጉትም ከዚህ ቀደም በግጭት ምክንያት ተለያይተው የነበሩ ደመኞች ታርቀው አንድ
ሆነዋል፣ ሠላም ተፈጥሯል የሚለውን መግባባት ለመግለጽ ነው፡፡
ጎፋ የሚለዉን የቃሉን ትርጓሜ በተመለከተ የተለያዩ ሰዎች በተለያየ መንገድ ይገልጻሉ፡፡ አንዳንዶች ህዝቡ
ጥንታዊ እንደመሆኑ መጠን ስያሜው ከጥንት ጀምሮ የነበረ እንደሆነ ያስቀምጣሉ፡፡ በዚህ አስተሳሰብ
የሚያምኑ ሰዎች ሁለት የተለያየ አገላለጽ አላቸው፡፡ የህዝቡ የቀድሞ መኖሪያ ከሆነው ከጊቤ ወንዝ መነሻ
አከባቢ የተነሳዉ ህዝብ ጥንትም በዚህ ስም ይጠራ እንደነበረና አዲስ መጥቶ በሰፈረበት በውርኪ አከባቢም
ስያሜውን ይዞ እንደቆየ ይነገራል፡፡ በህዝቡ መነሻ ቦታ የማይስማሙ እና የህዝቡን መነሻ ውርኪ እና ኡባ
ሰንሰለታማ ቦታዎች አድርገዉ የሚገልጹት በነዚህ አከባቢዎች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ‘ጎፋ’ ጥንታዊ መገለጫ ሆኖ
በሂደት ወደ አከባቢው የመጡትም እየቆዩ በስሙ መጠራት እንደተጀመረ ያምናሉ፡፡
ሁለተኛው አስተሳሰብ ስያሜዉን ከጎፋ ነጋሲ ጎሳ ከሆኑት ከጎሻናዎች አመጣጥ ጋር የሚያገናኝ ነው፡፡ እንደነዚህ
የአገር ሽማግሌዎች የስሙ ምንጭ የጎሻና ጎሳ የዘር ምንጭ የሆነው ‘ጎሻ’ አሳዳጊ የሆነችው ሴት ”ጎፌ”
ከሚትባል ጋር አያይዘው ያስቀምጣሉ፡፡ ጎፌ ጎሻ የሚባል ልጅ አሳዳጊ ስትሆን ልጁ ከትልቅ ውሃ ሰስንፈፍ
የተገኘ በመሆኑ እናቱ ስለማትታወቅ በአሳዳጊዋ የጎፌ ልጅ /Goof naa7a እተባለ ይጠራ ጀመር፡፡ እየቆየ ጎሻ
ታምራትን ማድረግ ስጀምር በአከባቢው ንጉስ እንዲሆን በህዝቡ እንደተመረጠ እና ጎሻ የሚጠራበት ጎፊነኣ
በጊዜ ሂደት የህዝቡ መጠሪያ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የህዝቡ መነሻ የሆነው የኦሞ ወንዝ ተፋሰስ ውርኪ አከባቢ
ሌሎች የስሙን አመጣጥ አንድ ወቅት ጎፋን ስገዛ ከነበረ ንጉስ ጎባ ጋር ያገናኙታል፡፡ ካዎ ጎባ ታዋቂና ሀያል የሆነ
ከጎፋ አልፎ ዳውሮንና ኮንታን ወርሮ በመያዝ አንድ ላይ አድርጎ ያስተዳደረ ንጉስ እንደነበረ ይነገርለታል፡፡ ከዚህ
የተነሳ በአጎራባች መንግስታት/ አገሮች በግዛቱ ሥር ይኖሩ የነበሩ ሰዎች (Gooba nayta) “የጎባ አገር ሰዎች"
በሚል ስያሜ ይጠሩ እንደነበረና ቆይቶ በጊዜ ሂደት “ጎባታ/ጎባዎች" ስባል ቆይቶ ዛሬ ላይ ህዝቡ የሚጠራበትን
ስያሜ ይዞ እንደቀረ ይነገራል፡፡
የብሄረሰቡ ስያሜ አመጣጥ በተመለከተ የዕድሜ ባለጸጎችም ሆነ በብሄረሰቡ ታሪክ ጥናት ያደረጉ
ተመራማሪዎች ከላይ እንደተገለጸዉ ሁሉም ያላቸውን የተለያየ እምነት በተለያየ ማስረጃ የሚያረጋግጡ
ሲሆን ብሄረሰቡ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለበት ስለመሆናቸው ልዩነት የላቸውም፡፡
ጎፋዎች ከኦሞትክ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ምድብ ስከፈሉ የበርካታ ጥንታዊ ስልጣኔዎች ባለቤት ናቸው፡፡ ህዝቡ
የራሱ የሆነ የአለባበስ፤ ቤት አሠራር፤ የእርሻ አስተራረስ፤ አፈር አጠባበቅ፤ ባህላዊ መድኃኒት ቅመማ
እንዲሁም ዘመን አቆጣጠር ስልት አላቸው፡፡ ከዚህ በላይ ከተገለጹት በተጨማሪ ህዝቡ የአያለ ጥንታዊ
ስልጣነዎች ባለበት መሆኑ ስታወቅሁሉን መዳሰስ የዚህ ጽሁፍ ዓላማ ባለመሆኑ አጠር በማድረግ ጥንታዊ የጎፋ
የዘመን አቆጣጠር ስልት እንደሚከተለው ተዳስሶአል፡፡
የተለያዩ ዘመናዊ የዘመን አቆጣጠር ስልቶች ተዘጋጅተው በአከባቢው ህዝብ ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ጥንቱ
ጎፋ የራሱ የሆነ ባህላዊ የዘመን አቆጣጠር ነበረው፡፡ የጎፋ ዘመን አቆጣጠር ቀዳሚ ከሚባሉ የዓለማችን የዘመን
አቆጣጠር ስልቶች አንዱ ቢሆንም በአግባቡ ተጽፎ የተቀመጠ መረጃ ካለመኖሩ እና ለጎፋ ባህላዊ ሳይንስ
ትኩረት ባለመሰጠቱ በቀዳሚነቱ እንደሌሎች አልተወደሰም፡፡ በመሆኑም አዲሱ ትዉልድ ስለ ጎፋ ባህላዊ
የዘመን አቆጣጠር ያለዉ ግንዛቤ አንስተኛ ከመሆኑም ባሻገር ሙሉ በሙሉ እየተረሳ እና እየጠፋ ይገኛል፡፡ ከዚህ
የተነሣ ስለቀደመው ጎፋ ዘመን አቆጣጥር አጠር ያለ ገለጻ በማቅረብ ትዉልዱ የተሻለ እውቀት እንድኖረውና
ለተመራማሪዎች መነሻ የሆነ መረጃ መስጠት የዚህጽሁፍ ዓላማ ነው፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ አንዳንድ ጸሐፊዎች ሁሉም የዘመን አቆጣጠር ስልቶች አባታቸዉ ግብጻዉያን እንደሆኑ
አድርጎ ማሰብ ስህተት እንደሆነይገልጻሉ፡፡ የዚህ አስተሳሰብ አራማጆች ሰዎች የዕለት ተዕለት ተግባራቸዉን
በአግባቡ እንድመሩ፤ የተከናወኑትንም ለማስተዋስ እንዲሁም በዓለማችን በተወሰነ ጊዜ ተከስተው ከጠፉ
በኃላ በተወሰነ ጊዜ እንደገና ተመልሰዉ የሚመጡ የተፈጥሮ ክስተቶችን ወቅታቸውን ለማወቅና ምላሽ
ለመስጠት በምደረገው ትግል የዘመን አቆጣጠር ስልት እንደተወለደ ይገልጻሉ፡፡ በዚህ መነሻነት ሁሉም ህዝቦች
የራቸዉ የህይወት ፍልስፍና እና የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው በመሆኑ ዘመን አቆጣጠር ባህል ወይም ትውፊት
እንደሆነ ይታመናል፡፡ የሁሉም ዘመን አቆጣጠር ምንጭ በተመለከተ አንድ አይነት አስተሳሰብ ባይኖርም
ጎፋ የጨረቃ ዘመን አቆጣጠር (Lunar calendar) ስልት የሚከተል ሲሆን ጨረቃ በየወሩ ስትከሰትና ተመልሳ
ስትጠፋ ጨረቃን ከወር ጋር በማያያዝ ይቆጥራል፡፡ ወሩ የሚቆጠረው በጨረቃ መታየትና መሰወር ሲሆን አንድ
ወር ከአንድ ሙሉ ጨረቃ እስከሚቀጥለው ሙሉ ጨረቃ ድርስ ያለው ጊዜ ነዉ፡፡ በጥናት እንደተረጋገጠው
ጨረቃ መሬትን አንዴ ዞራ ለመመለስ 29.5 ቀናት የሚፈጅባት እንደሆነ ስታወቅ የጎፋ ወር እንደ ዘመናዊ
የአገርቱ አቆጣጠር 30 ቀናት ያሉት ሳይሆን የዕድሜ ባለጸጎች እንዳረጋገጡት ከ 27 እስከ 30 ቀናት ያለው
ነው፡፡ የወራቱ ቀናት ርዝማኔ መለያየትና የጎፋ የዓመቱ ቀናት ብዛት ስንት እንደሆነ ለማወቅ ቀጣይ ጥናት
የሚያስፈልግ መሆኑ ብታመንምበጥናት እንደተረጋገጠው የጨረቃ አቆጣጠር የዓመቱ ቀናት 354 እንደሆነ
ተረጋግጦአል፡፡ በጸሀይ አቆጣጠር በዓመት 365 ቀናት ያለው ሲሆን በሁለቱም አቆጣጠር ስልቶች መካከል
የአስራ አንድ ቀናት ልዩነት አለ፡፡
የቀንና የሌሊት አከፋፈል በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተለያየ ነው፡፡ ለምሳሌ ቀን በምዕራባውያን አቆጣጠር
እኩለ ሌሊት ስጀምር እስራኤላውያን ከጧቱ አሥራ ሁለት ሰዓት እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ
በአስራ ሁለት ሰዓታት ከፍለው ይቆጥሩታል (ማሞ ጎደቦ 2010)፡፡ ጎፋ ዕለትን ቃማነ/ሌሊት ጋላስ/ ቀን በማለት
ይከፍላል፡፡ ቀኑ ብርሃን የሚታይበትን የዕለትን ክፍል ስያጠቃል ሌሊቱ ብርሃን የማይታይበት የዕለቱ ክፍል ነው፡፡
ቃማ ሁለት ትርጉም አለው፡፡ አንደኛው ቀን ወይም ቀኑንና ሌሊቱን ሁለቱን የሚያጠቃልል ስያሜ ሲሆን
ሁለተኛዉ ብርሃን የማይታይበት የዕለቱ ክፍል ማለት ነው፡፡
ሰዎች የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ለማከናወን የተከናወኑትንም ዘመን ለማስታወስ የዘመን አቆጣጠር ስልት
(calendar) እንደተቀየስ የታርክ ባለሙያዎች ስያረጋግጡ ጊዜን በቋሚ አሀዶች (units)
በዓመታት፤ወራት፤ሳምንታት፤በቀናት፤ሰዓታት፤ሴኮንዶች በመከፋፈል መቁጠር ለሰው ልጅ እንቅስቃሴ አመቺ
ሁኔታን እንደምፈጥር ይታመናል፡፡ ጎፋም በባህላዊ ተክኖሎጂው የተለያዩ የዘመን አቆጣጠር አሃዶች
በማዘጋጀት ስጠቀም እንደነበረ ስታወቅ ዋና ዋና የዘመን መለኪያ አሀዶችም የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
ሣምንት በእንግሊዘኛ ዊክ/week ተብሎ ስጠራ በጎፋ እስ ጊያ ይባላል፡፡ እስ ጊያ ጥሬ ቃሉን ስናይ አንድ ገበያ
ማለት ነው፡፡ ጊያ ሁለት ትርጉም አለዉ፡፡ አንደኛው ገበያ ማለት ሲሆን ሁለተኛው ትርጉም ሳምንት ማለት
ዕለታት በጎፍኛ
እንደ ዕድሜ ባለጸጎች ለጎፋ ስኬታማነትና ውጤት ማጣት ከቀናት ጋር ይያያዛል፡፡ ከዚህ ረገድ ቀናቱን
ገድ/ማጫ ቃማ እና ገደቢስ/አደ ቃማ በማለት በሁለት ይከፍላቸዋል፡፡ ማክሰኞ፤ ሀሙስና ቅዳሜ ገድ ቀናት
ሲሆኑ ሮቡእ/ናዴ አርብ/ላሜ እሁድ/ዎጋ ገደቢስ/ኤቃ ቃማ በመባል ይታወቃሉ፡፡
1. Gusttama (መስከረም)
መስከረም በጎሪጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ ዘጠነኛ ወር ሲሆን 30 ቀናት አሉት፡፡ መስከረም
የተወሰደዉ ሴፕተም ከሚል ቃል ሲሆን ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ በቀድሞ አቆጣጠር ሰባተኛ ወር ቢሆንም
አሁን ግን ዘጠነኛ ወር ነው፡፡ በኢትዮጵያ መስከረም የዓመቱ መጀመሪያ ወር ከመሆኑም በተጨማሪ አዲስ
ዓመት የሚጀመርበትና ዘመን የሚንለወጥበት ወር ነው፡፡ መስከረም ምሴተ-ክረምትከሚል ቃል የመጣ ሲሆን
ትርጉሙ ክረምት አለፈ ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የሚከበርበትና ዘመን የሚለወጥበት ዕለት
እንቁጣጣሽ የሚባል ሲሆን የክርስትና እምነት ተከታየች ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ ይሉታል (ማሞ ገደቦ 2010)፡፡
መስከረም ወይም ጉስታማ በጎፋም የራሱ የሆነ የምታወስበት ታርካዊ ክስተት አለው፡፡ ጉስታማ የጎፋ የአመቱ
መጀመሪያ እና ዘመን የሚለወጥበት ወርነው፡፡ የጎፋ ዓመት መለወጫ በዓል ጋዜ የሚከበረው በዚህ ወር ሲሆን
የዘመን መለወጫ በዓሉ እንደ ሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች የሚከበረው በወሩ መግቢያ ሣይሆን በጉስታማ
አጋማሽ አከባቢ ነው፡፡ ወሩ የጎፋ ብሄራዊ ትልቁ በዓል ጋዜ የሚከበርበት ከመሆኑመም ባሻገር ብርዳመውና
ጥቅምት በጎርጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሰረት የዓመቱ አሥረኛ ወር ሲሆን 31 ቀናት አሉት፡፡ ጥቅምት
ኦክቶበር የተወሰደው ኦክቶ ከሚል ቃል ሲሆን ኦክቶ ማለት በግሪክና በላቲን ቋንቋዎች ስምንት ማለት እንደሆነ
የታሪክ ጸሀፊዎች አትተዋል፡፡ ጥቅምት በኢትዮጵያ የዓመቱ ሁለተኛ ወር ሲሆን በአማርኛ ትርጉሙ
የሚጠቅም፤ ጥቅምን የሚሰጥ፤ የሚበጅ፤ የሚያፈራ ወዘተ የሚል ትርጉም የያዜ ነው (ማሞ ገደቦ በ 2010)
ጥቅምት በጎፋ ከገድ ወራት አንዱ ነው፡፡ መስከረምን/ጉስታማን ተከትሎ የሚመጣ ወር ስለሆነ የክረምቱ
ጨለማ እየጠራ የሚሄድበት በቆላና በደጋው አከባቢ የተለያዩ እህሎች የሚደርሱበት ወር ነው፡፡ ጥቅምት/ጭሻ
አገና በደጋው የጎፋ ክፍል የአተር፤ ባቄላ፤ ገብስ የምታረምበትና እሸት በስፋት የሚገኝበት ወቅት ነው፤
በቆላማውም ቢሆን ጤፍ፤ቦየ የተለያዩ ስራስሮች የምደርሱበት በመሆኑ ወሩ በጎፋ ከጥጋብ ወራት አንዱ ነው፡፡
ዝናባማ የሆነዉ ክረምቱ ወቅት አልፎ ብራማው የጸደይ/ጋባ ወቅት አበቦች በየቦታው ፈክተው የሚታዩበት
ስለሆኑ ወሩ የአበቦች ወር/ ጪሻ አገና እየተባለ ይጠራል፡፡
በጥቅምት የተቆረጡ እንጨት ውጤቶች ነቀዝ ስለማይበላው አርሶ አደሩ በጥቅምት ወር ለልዩ ልዩ
አገልግሎቶች የሚውሉትን ከእንጨት የሚዘጋጁ ቁሰሳቁችን የሚያዘጋጀበት ወርም ነው፡፡ በሌላ በኩል ነፋስ
የሚበዛበት ከሌሎች የዓመቱ ወራት ለየት ያለ ቅዝቃዜ የሚስተዋልበት ስለሆነ ጥቅምት ብርድእና ዉርጭ
የሚያይልበት/ቃሬ ጎዥጎዦ አገና በመባል ይታወቃል፡፡ እንደ ዕድሜ ባለጸጎች ቀደምት ጎፋዎች ጥቅምትን
ከሌሎች ወራት ለየት ያለ ብሄራዊ የስኬት ወር ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ ዘመናዊ አስተዳደር በኢትዮጵያ
ከመመሰረቱ በፊት ወሩ የንግስና ሥርዓት የሚፈጸምበት ወር ነበር፡፡ እንደ ዕድሜ ባለጸጎች በጎፋ የመንግስት
ምስረታ የሚካሄደው በጥቅምት ወር ነበር፡፡
3. ህዳር /Balibabala
ኀዳር በእንግሊዘኛ ኖቨምበር ተብሎ ስጠራ በጎሪጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ አስራ አንደኛ ወር
ነው፡፡ ቃሉ ኖቬምብርስ ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ዘጠነኛ ማለት ነው፡፡ በቀድሞው በሮማውያን
አቆጣጠር ህዳር ዘጠነኛ ወር ነበር፡፡ በቀድሞው አጠራር ዘጠነኛ ወር ቢሆንም በየጊዜው በተደረገው መሻሻል
አሁን አሥራ አንደኛ ወር ሆኖ 30 ቀናትን የያዜ ነው፡፡
ህዳር በኢትዮጵያ ኀደረ ከሚል የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ አደረማለት ነው፡፡ ወሩ አርሶ አደሩ እህሉን
ለመጠበቅ ዱር የሚያድርበት ስለሆነ ስያሜውን ከዚያ ሳያገኝ እንዳቀረ ምሁራን ያምናሉ፡፡ ህዳር በሰሜኑ
ኢትዮጵያ የጥጋብ ወር ከመሆኑ የተነሳ የእርካታና የጨዋታ ወቅት ነው (ማሞ ገደቦ 2010)፡፡
ህዳር/Balibabaala በጎፋም የጥጋብ ወር ነው፤ ጎፋ አከባቢዎች የአገዳ እህሎችና የተለያዩ ሥራሥር ምግቦች
በተለያዩ የዓየር ክልሎች የምደርስበት ነው፡፡ በደጋው ጤፍ፤ ስንዴ፤ ገብስ የመሳሰሉት እና በቆላማው የጎፋ
ክፍልም ዘንጋዳ፤ቦቆሎ፤ ጤፍ፤ ድንች፤ ቦዬ ያሉ የምግብ አይነቶች ለምግብነት የምደርስበት ወር ነው፡፡ እንደ
ዕድሜ ባለጸጎች በአሁኑ ወቅት በተለይ በጎፋ ቆላማዉ አከባቢዎች በብዛት ለምግብነት እየዋለ ያለው ቦቆሎ
ጎፋ ከመግባቱ በፊት የተለያዩ የማሽላ ዝርያዎች በቆላማው የጎፋ ክፍል የተለመደ የምግብ እህል ነበር፡፡ ዘንጋዳ
4. Quriquta (ታህሳስ)
ታህሣሥ በእንግሊዘኛ ዲሴምበር ይባላል፡፡ ታህሣሥ በጎሪጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ አስራ
ሁለተኛ ወር ሲሆን 31 ቀናት አሉት፡፡ ታህሣሥ ዴሴም (Decem) ከሚል ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉም በላቲን
አሥር ማለት ነው፡፡ አሁን በጎርጎሪዮሳውያን የዘመን አቆጣጠር መሰረት ታህሣስ አሥራ ሁለተኛ ወር ቢሆንም
በቀድሞ አጠራር አስረኛ ነበር፡፡ ታህሣስ በኢትዮጵያ አራተኛ ወር ሲሆን የስሙ ትርጉመም ሐሰሰ ከሚል
ከግዕዝ ሥርወ ቃል የተገኘ እንደሆነ እና ትርጓሜዉ ከጥጋብና አዝመራ በተጨማሪ መረመረ፤ ፈለገ፤ አሰሰ፤ከ
ጀለ፤ ተመኘ ማለት እንደሆነ ማሞ ገደቦ በ 2010 ዕትሙ ዘርዝረዋል፡፡ በታህሣሥ በህዳር ያልደረሱ ሰብሎች
የሚደርሱበት ወር በመሆኑ እንደ ህዳር በአብዛኛው የኢጥዮጵያ ክፍሎች በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰዉ
የማይቸገርበት ወር ነው፡፡ እህል አምራች የሆኑ አርሶ አደሮች ደግሞ ያጨዱትነ አዝመራ በአውድማ
ወቅጠውና ወደ ገበያ አውጥተው በመሸጥ ገንዘብ የሚያገኙበት በታህሣሥ ወር ነዉ (ማሞ 2010)
የታህሣሥ ወር ትርጉም በጎፍኛ ምን እንደሆነ ባይደረስበትም ወቅቱ የበጋዉ መግቢያ ስለሆነ የጸሀይ ወቅት
“አዋ አገና” ተብሎ ይጠራል፡፡ በኢትዮጵያ ታህሣሥ ጥር እና ይካቲት የዝናብ እጥረት ያለባቸው የበጋ ወቅቶች
ቢሆኑም ጎፋ በኢትዮጵያ ዓመቱን ሙሉ ዝናብ ከምያገኙ አከባቢዎች አንዱ በመሆኑከጥር አጋማሽ ጀምሮ
የበልጉ ዝናብ መጣል ይጀምራል፡፡ ከዚህ የተነሳ ከሌሎች ተለይቶ ወሩ ዝናብ የለሌበት ወር /አዋ አገና በሚል
ይታወቅ እንደነበረ መረጃ የሰጡ የዕድሜ ባለጸጎች ይናገራሉ፡፡
ጎፋ ሥራ ሥር ምግቦች በብዛት የሚገኙበት አከባቢ ነው፡፡ ቦዬ፤ ጎደሬ፤ እንሰት፤ ድንች በሰፊው ስመረት ከሥራ
ሥሮች ድንችና ጎደሬ በሰፊው ለምግብነት የሚውልበት ወር ነዉ፡፡ ጎደሬ ለምግብነት ለመድረስ ከአምስት እስከ
ስድስት ወራት የሚፈልግ ሲሆን በክረምቱ የተተከለው ደርሶ አርሶ አደሩ ለምግብነትና ለገበያ የሚያውልበት
ወር ስለሆነ ታህሣስ ወር ከገበያ ጎደሬ ለመግዛት የሚፈልግ ስለ ቦዬው ጥራት/ የሚበስል ወይም የማይበስል
አይነት/ ለምለው ጥያቄ ብዙም ስጋት አይገባበትም፡፡ ከዚህ የተነሣ ወሩ ጎደሬ ለምግብነት የሚዉልበት
ወር/ቦይን ጹሮራ ካጽያ አገና/ ተብሎ ይጠራል፡፡ ታህሣስ የደረቅ ወቅት ስለሆነ በጎፋ አርሶ አደሩ እረፍት
የሚያደርግበት፤ለመጪው አዝመራ ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት፤ትዳር ያልመሰረቱ ጥንዶች ትዳር
የሚመሰረቱበት እንዲሁም ቤት የሚጠገንበትና የሚሰራበት ወር ነው፡፡
5. Guxe/ ጥር
ጥር በእንግሊዘኛ ጃኑዋሪ ይባላል፡፡ ጥር በጎሪጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ሲሆን
31 ቀናት አሉት፡፡ ጥር ወይም ጃኑዋሪ (Janu + Arius) or (Janus Month) የጃን ወር ከማለት የመጣ ነው፡፡
ጃንስ የሚባለው የሮማዉያን የበር ጠባቂ የመጀመሪያና የመጨረሻ፤ የመግቢያና የመዉጫ አምላክ መጠሪያ
ስም ሲሆን አሪስ (Arius) ደግሞ “የ” ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በአንድ ላይ ጃኑዋሪ የጃን ወር ማለት ነው፡፡
6. Wogayza/ ይካቲት
የካቲት በእንግሊዘኛ ፈብሯሪ (February) ተብሎ ስጠራ በጎሪጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ
ሁለተኛ ወር ነው፡፡ ይካቲት በመደበኛ ዓመታት 28 ቀናት ያሉት ሲሆን በሰገር ዓመታት ደግሞ 29 ቀናት
ይኖሩታል፡፡ በኢትዮጵያ የካቲት የዓመቱ ስድስተኛ ወር ሲሆን በውስጡ ሰላሳ ቀናትና አራት ሳምንታትን ያቀፈ
ወር ነው፡፡ የካቲት ማለት መከር፤ መክተት፤ አዝመራ መሰብሰቢያ፤ ወደ ጎተራ የሚከተትበት የመከር መካተቻ
ጊዜ ነው (ማሞ 2010፡108)
ወጋይዛ ጥሬ የቃሉ ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ባይታወቅም ይካቲት ወጋይዛ የጎፋ ዋናው የእርሻ ወቅት
ነው፡፡ የኢትዮጵያን የዝናብ ሥርጭት ሁኔታ ባለመሙያዎች ዓመቱን ሙሉ ዝናብ የሚያገኙ አከባቢዎች፤
በጸደይ እና በበልግ ዝናብ የሚያገኙ፤ የክረምት ዝናብ አከባቢዎች፤ በበጋ ዝናብ የሚገኙ አከባቢዎች በማለት
በአራት ይከፍላቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት ጎፋ ዓመቱን ሙሉ ዝናብ ከሚያገኙ አከባቢዎች የሚመደብ በመሆኑ
ከዚህ ምድብ ዉጭ የሆኑ እንደ ሌሎች አከባቢዎች ሶስቱ የበጋ ወራት (ታህሣሥ ጥርና ይካቲት) ደረቅ ወራት
አይደሉም፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ከታህሣሥ ወር ውጪ ቀሪዎቹ ሁሉቱም መጠኑ ይለያይ እንጂ ዝናባማ ወራት
ናቸው፡፡ ጥሪ የበልጉ ዝናብ እያካፋ መምጫው መቃረቡን ምልክት የምሰጥበት ሲሆን ይካቲት ዋናው የበልግ
እርሻ ወቅት ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ በጥንቱ ጎፋም ሆነ ዛሬም ወጋይዛ ዋናው የበልግ ወር / ወጋይዝ ዎጋ ቶርቼ/
በመባል ይታወቃል፡፡
7. Lafa (መጋቢት)
መጋቢት በእንግሊዝኛ ማርች ተብሎ ስጠራ በጎርጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ ሶስተኛ ወር
ሆኖ 31 ቀናት አሉት፡፡ ማርች የመጣው ማርስ ከሚባለው ከጥንት የሮማውያን የጦርነት አምላክ በመሆኑ
ትርጉሙም የጦርነት አምላክ የምል ነበር፡፡ ሮማውያን ለጦርነት የሚያቅዱትና የሚነሱት በዚህ ወር ነበር፡፡
መጋቢት ጥንት የሮማውያን የዓመቱ መጀመሪያ ወቅት ነበር (ማሞ ገደቦ 2010)
በኢትዮጵያ መጋቢት የዓመቱ ሰባተኛ ወር ሲሆን በውስጡ ሰላሳ ቀናትንና አራት ሳምንትትን ያቀፈ ነው፡፡
የቃሉ ትርጉም “መገበ” ከሚል ቃል የተገኘ ስም ሲሆን ትርጉሙ በቁሙ የሚመግብ ወይም በጎተራ የተከተተዉ
የሚበላበት ማለት ነው፡፡
ላፋ/መጋቢት በጎፋም ሰባተኛው ወር ሲሆን በላፋ በይካቲት/ወጋይዛ ተጀምሮ የነበረው የበልግ እርሻ
የሚጠናቀቅበት ቀድሞ የተዘራውና የበቀለው እህል የሚኮተኩትበት ወር ነው፡፡ ይህ ወር አብዛኛው አርሶ አደሩ
ቀደም ሲል ያመረተውን ምርት በበጋ ወቅት ስመገብና ስዝናና የእህል ክምችቱ ተማጦ ጎተራ ውስጥ ከቆጠበው
እየተመገበ የበልጉን እርሻ የሚያካህድበት ወር ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ መጋቢት በጎፋ የምግብ እጥረት
8. Okola (ሚያዚያ)
ሚያዝያ በእንግሊዘኛ አፕሪል ተብሎ ስጠራ በጎርጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ አራተኛ ወር
ነው፡፡ አፕሪል አፍሮዲት ሞንዝ ከምል ከግሪክ ቃል የተወሰደ ሲሆን አፍሮዲት የግሪክ የውበትና የፍቅር አምላክ
ተብላ የምትመለክ እንስት አምላክ ናት፡፡ በጎርጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር አፕሪል 30 ቀናት አሉት፡፡
በኢትዮጵያ ሚያዝያ የዓመቱ ስምንተኛ ወር ሲሆን በዉስጡ ሠላሣ ቀናትንና አራት ሳምንታትን ያቀፈ ነው፡፡
ሚያዝያ “መሐዘ” ከሚል ከግዕዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርሙ ተጎዳኘ፤ ወርሃ- ሠርግ ማለት ነው፡፡
ሚያዝያ እንደ ጥርና እንደ የካቲት ባይደምቅም ከፋስካ በኃላ በሰሜኑ ኢትዮጳያ ክፍል ሠርግ የተለመደ ነው
(ማሞ ገደቦ 2010)፡፡ በጎፋ አቆጣጠርም መያዝያ ስምንተኛ ወር ሲሆን በገጠሩ የጎፋ ክፍል የእህል እጥረት
የሚታይበት ወር ነው፡፡ የበልጉ ምርት ገና ያልደረሰበት የእህል ወቅቶች በማለፋቸዉ የእህል ዋጋ የሚወደድበት
ወር ስለሆነ በጎፋ ገጠር አከባቢ ሚያዝያ ወይም ኦኮላ ለቤት እንስሳት ምቹ ለሰዎች ግን ምቹ ያልሆነ ወር
በመባል ይታወቃል፡፡ ኦኮላ በጎፋ በቂ ዝናብ የሚዘንብበት ወር በመሆኑ ለከብቶች ግጦሽና ውሃ እንደልብ
ይገኛል፡፡ የበልግ ዝናብ ይካቲት ወር ስልምጀምር የተዘሩ ሰብሎች በቅለዉ የበልግ ቡቃያ አምሮ የሚታይበት
ወር ስለሆነ “ኦኮሊ ባዳሊ ኦርዴ ዶሊያ አገና” በመባል ይታወቃል፡፡
9. Hiisa (ግንቦት)
ግንቦት በእንግሊዘኛ ሜይ ተብሎ ስጠራ በጎርጎሪዮስ ዘመን አቆጣጠር መሠረት የአመቱ አምስተኛ ወር ነው፡፡
ግንቦት (ሜይ) ወይም (mayia) ማያ ማለት ታላቅ ማለት ሲሆን የሮማ የጸደይ (spring) እንስት አምላክ
መጠሪያ ስም ነው፡፡ ስለዚህ የማያ ወር ወይም የጸዴይ እንስት አምላክ ማለት ነው፡፡ ሜይ የሚለዉ የግንት ወር
የእንግሊዘኛ ስያሜ ማያ ከሚል ከግርክ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ምግብ የምትሰጥ (መጋቢ) እንደማለት
ነው፡፡ በጎርጎሪዮስ ዘመን አቆጣጠር መሠረት ግንቦት 31 ቀናት አሉት፡፡
በኢትዮጵያ ግንቦት የዓመቱ ዘጠነኛ ወር ሲሆን በውስጡ ሠላሣ ቀናትንና አራት ሳምንታትን ያቀፈ ነዉ፡፡
ግንቦት የሚለው ስያሜ ገነባ፤ ሠራ፤ ከሚለዉ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉም ጎን፤ ጎድን፤ ወገን፤ ማዕዘን፤
ቅርብ፤ አጠገብ ማለት እንደሆነ አቶ ማሞ በ 2010 ዕትሙ በሰፊዉ አብራርተዋል፡፡
ግንቦት ለጎፋም ዘጠነኛ ወር ሲሆን ወሩ በጎፋ በገደ-ቢስነቱ ይታወቃል፡፡ ህሳ/ግንቦት የበልግ ወቅት የመጨረሻ
ወር በመሆኑ በእጁ ያለዉ እህል እየተሟጠጠ ሄዶ የሚቸገርበት ወር ነው፡፡ ወሩ ከበልግ ወራት አንዱ ቢሆንም
የተዛባ የዝናብ ስርጭት የሚታይበትም ወር ነው፡፡ አንዳንዴ ከመደበኛ በላይ ዝናብ በመምጣት በውሃ ሙላት
አርሶ አደሩ ወደ እርሻውና መገባበያ ሥፍራዎች እንዳይንቀሳቀስ ያደርጋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ የዝናብ
እጥረት ተከስቶ የበልጉ እርሻ የሚወድምበት ወር ስለሆነ ግንቦት ስዘንብ ሰዉን ከቤት መውጣት ይከለክላል፤
ስጠፋ እህልን ከነድምጥማጡ ስለሚያጠፋ “ህስ አዊኮ ህንቺ ኡዴስ ቡክኮ ሂታን ፐሸስ”ይባላል፡፡
ሂሳ/ግንቦት በጎፋ የምግብ እጥረቱ ጡዘት ከፍተኛዉን ሥፍራ የሚይዝበት ወር ነው፡፡ በግንቦት አብዛኛዉ ሰው
የሚቸገርብት ወር፤ እህል ያለዉም ቢሆን የዓየር ሁኔታው ከተዛባ በምግብ እጥረቱ ልያገኘው ስለምችል
የሁሉም ሰዉ ተስፋ የሚሟጠጥበት ወር ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ ጎፋ ህሳ/ግንቦት ሁሉም ሰው ስጋት ዉስጥ
ሂሳ /ግንቦት በጎፋ ህዝብ ዘንድ የማይወደድ ወር ነው፡፡ በሂሳ የንግስና ሥነ ሥርዓት አይፈጸምም፤ ጋብቻ
አይመሰረትም፤ብሄራዊ የዕርቅ ሥነ ሥርዓት አይካሄድም፡፡ በቀደምት ጎፋ በሂሳ የአገር መሪ (ንጉሱ) ብሞት
በፈንታ የሚቀመጠው ተተኪ ይሰየምና ሙሉ የንግስና ሥነ ሥርዓት አይፈጸምም፡፡ በዚህ ወር ሥርዓቱ
ብፈጸም ንጉሱ ፍሬያማ አይሆንም፡፡ ህዝቡም ስኬት ይርቀዋል፡፡ የእንስሳትና የሰው በሽታዎች ይበዛሉ፤ እህል
በተፈጥሮ አደጋዎች ይወድማል፤ ከብቶች ይሞታሉ፤ ጦርነት ይበዛል ብሎ ስለምያምን በጥንቱ ጎፋ ነገስታት
የንግስና ሥርዓታቸዉን በግንቦት ወር አይፈጸሙም ነበር፡፡ በአጠቃላይ በሂሳ/ግንቦትአዲስ ኢኮኖሚያዊና
ፖለቲካዊ፤ ሀይማኖታዊ የሆኑ ዕቅዶችን መጀመር ስኬታማነትን እንደምያጎድል ይታመን ነበር፡፡
ሰኔ በእንግሊዘኛ ጁን ተብሎ ስጠራ በጎርጎሪዮስ ዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ ስድስተኛ ወር ነው፡፡ ሰኔ
(June) ወይም ጁኖ ከሚለዉ ቃል የመጣ ስም ሲሆን ጁኖ ደግሞ የሮማውያን የአማልክት አምላክ የተባለች
እንስት አምላክ ስም ነው፡፡ ይህች ጣኦት የጋብቻ፤ የሴቶች መልክና ዉበት አምላክ ትባል ነበር፡፡ በጎርጎሪዮስ
ዘመን አቆጣጠር መሠረት ሰኔ 30 ቀናት አሉት፡፡
ሰኔ በኢትዮጵያ ደግሞ አስረኛው ወር ሲሆን ቃሉ ሰነየ ከሚል የግዕዝ ሥርወ ቃል የመጣና ሠናይ ሆነ፤ አማረ፤
ተዋበ የምል ትርጉም የያዜ ነው፡፡ ሰኔ በዋናነት የዘርና የእርሻ ወቅትነው፡፡ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የሰኔና ሰኞ
መገጣጠም እንደ መጥፎ እድል ወይም አጋጣሚ ይፈጠራል ተብሎ ይታመናል፡፡ ሰኔ አንድ ቀን ሰኞ ከዋለ መጥፎ
ሁኔታ ይፈጠራል የሚል አምልኮ ዓይነት ልማድ አለ (ማሞ 2010)፡፡
ለጎፋ ጮጬ/ሰኔ ወር የሂሳ/ግንቦት ረሀብ ወቅት አልፎ እሸት የሚደርስበት ወቅት ነው፡፡ ወሩ የክረምቱ መግቢያ
እና የበልጉ ወቅት ማብቂያ ስለሆነ በበልግ ወቅቱ የተዘሩ እህሎች የሚደርስበት ነው፡፡ ወሩ የክረምቱ መግቢያ
ስለሆነ የዓየሩ ቅዝቃዜ የምጨምርበት አርሶ አደሩም የበልጉ ሰብል ደርሶ የምግብ እጥረቱ ተቃሎ እሸት
የሚበላበት በመሆኑ ጮጨይ ቾንቸስ ይባላል፡፡ ሰኔ በጎፋ ከገድ ወሮች አንዱ ነው፡፡
ሐምሌ በእንግሊዘኛ ጁላይ ተብሎ ስጠራ በጎርጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር መሠረት የዓመቱ ሰባተኛ ወር ሲሆን
31 ቀናት አሉት፡፡
ሐምሌ በኢትዮጵያ የዓመቱ አሥራ አንደኛ ወር ሲሆን በዉስጡ እንደሌሎቹ የዓመቱ ወራት ሰላሣ ቀናትንና
አራት ሳምንታትን ያቀፈ ነው፡፡ ሐምሌ የሚለው ቃል የተወሰደው ሐምል ከሚለው ጥሬ ቃልሲሆን ሐምል፤
ሐመልማል ወይም አመልማል፤ አመልማሎ እየተባለ ይጠራል፡፡
በጎፋም ላማሀምሌ አስራ አንደኛው ወር ሲሆን የክረምሩ ዝናብ የሚበረታበት አርሶ አደሩም የክረምቱን
የእርሻ ሥራ የሚያካህድበት ወር ነው፡፡ የክረምቱ ወራት ለጎፋ ከባድ የእርሻ ወቅት ነዉ፡፡ በክረምት ወቅት
ከምዘሩ የእህል ዓነቶች አንዱ ጤፍ ሲሆን የዘር ወቅት ተጠብቆ ካልተዘራ ጤፍ ምርት አይሰጥም፡፡ ከዚህ የተነሣ
የክረምቱ እርሻ በጥንቃቄና በትጋት ካልተካሄደ ዉጤት እንደማይኖረ ለመግለጽ ስፈልግ “ስል ሼሻስ ብን አቴስ”
በማለት ሌላውን ያስጠነቅቃል፡፡
ነሐሴ በእንግሊዘኛ ኦዉገስት ተበሎ ስጠራ በጎሪጎሪዮስ ዘመን አቆጣጠር መሠረት ስድስተኛና 30 ቀናት የያዜ
ነው፡፡ ነሐሴ የመጀመሪያ ስሙ ሴክስቲሊስ (Sextilis) ተብሎ ስታወቅ ትርጉሙም ስድስተኛ ወር ማለት ነበር፡፡
በኃላ ግን በሮማዉ ገናና መሪ በነበረዉ በአውጉስጦስ ስም ለቄሳሩ ክብርና የሥራ መታሰቢያ ሲባል በስሙ
ኦውገስት (August) ተባለ፡፡
ነሐሴ በኢትዮጵያ የዓመቱ አሥራ ሁለተኛ ወር ሲሆን ነሐሴ ቃሉ ከታወቁት የብረት ዓይነቶች አንዱ ከሆነው
ነሐስ የተወሰደ ነው፡፡ ነሐሰ፡- ሠራ፤ገ ነባ፤ የሥራ ወር፤ ሥራ የሚደራረብበት ማለት ነው (ማሞ 2010)፡፡
በጎፋ ነሀሴ ወር ጋሊንዳ ተብሎ ስጠራ ወሩ ጤፍ በምበቅልባቸዉ አከባቢዎች የዘር ወቅት ነው፡፡ በአከባቢው
የአየር መዛባት ምክንያት በአሁኑ ወቅት በቆላውና በደጋማ የዓየር ክልሎች የዘር ወቅት እየተለያየ የመጣ መሆኑ
ቢታወቅም በቀደምት ጎፋ ጋሊንዳ ዋና ጤፍ መዝሪያ ወቅት ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ ወሩ በአከባቢው ነሐሴ የጤፍ
መዝሪያ ወቅት“ጋሊንድ ጋሼ አገና” ይባላል፡፡
ወቅት ስንል መሬት በጸሀይ ዙሪያ በምታደርገው ጉዞ ምክንያት የሚፈጠሩ የተወሰኑ ወራትን የያዜ የጊዜ
መፈራረቅ ማለታችን፡፡ በዚህ የጊዜ መፈራረቅ ምክንያት የሚፈጠሩ ወቅቶች ጸደይ፤ በጋ፤ በልግና ክረምት
ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ወቅት በውስጡ ሶስት ሶሰት ወራትን እንደምይዝ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች
ይገልጻሉ፡፡ ወቅቶች ጎልተው የሚታዩት ወይም ተለይተው የሚታወቁት ከምድር ወገብ ራቅ ብለዉ በሚገኙ
(temprate zone) የሰሜንና የደቡብ ንፍቀ ክበባት አካባቢ ነው፡፡ በምድር ወገብ አከባቢ ጎልተው የሚታወቁት
ሁለት ወቅቶች ሲሆን እነሱም በጋ (የደረቅ ወቅት) እና ክረምት (ዝናባማ ወቅት) ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ በምድር ወገብ አጠገብየሚትገኝ አገር ብትሆንም መልካዓ ምድሯ ማለትም የከፍተኛ ተራሮችና
ሰፊ ስምጥ ሸለቆ አገር መሆኗ እንዲሁም የሚትገኝበት አከባቢ ባደረጉላት አስተዋጽኦ ወይም ተጽዕኖ የተለያየ
የዓየር ንብረት እንድኖራት አድረጎአል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ የዝናብ አመጣጥና ሥርጭት እንዲሁም የአየር
ሙቀትና ቅዝቃዜ የተለያየ በመሆኑ በግልጽ የሚታወቁ አራት ወቅቶች ተፈጥረዋል፡፡
ጎፋም በኢትዮጵያ ዓመቱን ሙሉ ዝናብ ከሚያገኙ አከባቢዎች አንዱ ሲሆንከተለያዩ የተፈጥሮ ክስተቶችና
ዓየር ሁኔታ የተነሣ አራቱ ወቅቶች ተለይተዉ ይታወቃሉ፡፡ የጎፋ አራቱ ወቅቶች፡-
ሀ. ፀደይ
1. Gabba/ ፀደይ
2. በጋ /Bone
በጋ በጎፋ ቦኔ/bone ይባላል፡፡ በተለምዶ በጋ ታህሣሥ ፤ጥር እና ይካቲትን የሚያካተት ሲሆን ጎፋ በኢትዮጵያ
ዉስጥ ከሞላ ጎደል ዓመቱን ሙሉ ዝናብ ከሚያገኙ አከባቢዎች አንዱ በመሆኑ የበጋዉ ወቅት አጭር ነው፡፡
የበልጉ ዝናብ በይካቲት ወር የሚጀምር በመሆኑ ይካቲት ለጎፋ ከበልግ ወራት አንዱ ነው፡፡ በ ቦኔ /bone ወቅት
አርሶ አደሩ ከእርሻ ሥራ ውጭ ያሉትን ግንባታ ሥራዎችን እያካሄደ፤ከብቶችን እየተንከባከበ ለመጭው በልግ
እርሻ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርግበት ወቅት ነው፡፡ አርሶ አደሮች ከጸደይ የተረፈውን አዝመራ በመሰብሰብ
እርሻቸውን በደንብ አለስልሰው በማረስ የሚያመቻቹበት እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዮች ሩቅ ያለ ዘመድ
አዝማድ የሚጠይቅበት ወቅት ነው፡፡ በጋ በጎፋ የሰርግ ወቅት ነው፡፡
3. በልግ /Assura/torchche
በልግ በበጋና በክረምት መካከል የሚገኝ ወቅት ሲሆን በጎፋ በልግ አሱራ ወይም ቶርቼ Assura/torchche ይባላል፡፡
የበልግ ወቅት በጎፋ ከይካቲት እስከ ግንቦት ያለዉን ጊዜ የሚሸፍን ነዉ፡፡ ቶርቼ/አሱራ ለጎፋ በዓመቱ ውስጥ ካሉ
ሶስት የእርሻ ወቅቶች ዋነኛው ነው፡፡ የተለያዩ የሰብል ዓይነቶች የሚዘሩበት ወቅት የተለያየ መሆኑ የታወቀ
ቢሆንም አከባቢው ቦቆሎ በብዛት የሚመረትበት በመሆኑ በልግ ለቦቆሎ እርሻ ምቹ ጊዜ ነው፡፡ ይህን ከጎፋ
ዘወትር ጸሎቱ “ፈጣሪ ሆይ ከበልጉ እርሻ አትለየኝ (torchche assi gadha biyaade tana son peeshopa)”
ከሚለው ምን ያክል የበልጉ እርሻ ወቅት ለጎፋ ወሳኝ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በልግ ለጎፋ የረሀብ ወቅት
ነው፡፡
4. ክረምት/ Balggo/Sila
ክረምት በጎፋ ባልጎ/ስላ (Balggo/Sila) ይባላል፡፡ ሰኔ፤ ሀምሌና ነሐሴ የክረምት ወራት ሲሆኑ ወቅቱ ዝናባማ
እና ከሌሎች ወቅቶች ይልቅ ቀዝቃዛማ ወቅት ነው፡፡ የዝናቡ አሰረጫጨት እንደ በልግ ሁሉን አከባቢዎች
በአንዴ የሚያዳርስ ሣይሆን ከአከባቢ አከባቢ እየለያየ ወይም እየቆራረጠ የሚንዘንብ በመሆኑ አርሶ አደሩ
የዝናቡን የተቆራረጠ ስርጭት ሲገልጽ (sili booras issi kacen bukidi issi kacen bukkona aganaw erees)
ሲል ይገልጻል፡፡ የአባባሉ ጥሬ ትርጉም የክረምት ዝናብ ለምያርሰው በሬ በአንደኛዉ ቀንድ እየጣለ ሌላኛውን
ቀንድ ጥይነካ ይችላል እንደማለት ነው፡፡ ክረምት ከበልግ የእርሻ ወቅት ቀጥሎ ሁለተኛው ለአርሶ አደሩ ወሳኝ
የእርሻ ጊዜ ነው፡፡ አከባቢው በጤፍ ምርትም ታዋቅ ሲሆን ስላ/ክረምት ደግሞ ዋነኛው የጤፍ መዝሪያ ወቅት
ነው፡፡
የኢኮኖሚ አምድ
የጎዕብማ ዋና ጽ/ቤት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጎፋ ዞን በሣዉላ ከተማ የሚገኝ
ሲሆን ማህበሩ በሁሉም የዞኑ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አሉት፡፡ ከዞኑ
ዉጪ ደግሞ በአዲስ አበባ፤ በአዋሳ፤ አርባምንጭ፤ ወላይታ ሶደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ከፍቶ
እየተንቀሳቀሰ ሲገኝ በሀገር ዉስጥና በውጭ ሀገራት 150,000 በላይ አባላት አሉ፡፡
1/ ጠቅላላ ጉባኤ፤
3/ ኦዲት ኮሚቴ
4/ ዋና ዳይሬክተር እና
በአቶ እሳያስ ዋሼ
ኦይዳ የበርካታ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦች መገኛ ናት፡፡ እነዚህ የቱሪስት መስህቦች በወረዳዋ
በተለያዩ ቀበልያት መኖራቸዉ በራሱ የኦይዳ ወረዳ የተፈጥሯዊና ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦችን የያዘች በጎፋ
ዞን ከምገኙ የቱሪስት መዳረሻ አከባቢዎች ተርታ አሰልፏታል፡፡ መስህቦቹ የምገኙባቸዉ ስፍራዎችን ጎብኚዎች
በእግር፣ በባህላዊ ተራንስፖርት (በበቅሎ) እና በተሸከርካር (በባለ ሁለትና ሦስት እግር ተሽከርካር እንድሁም
በመኪና በመጓዝ እንደለብ ጎብኚቷቸዉ ለመመለስ የአከባቢ ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ከመሆኑም ባለፈ በየ
ቀየዉ የአርሶ አደሩ እንግዳ አቀባበል ባህሉ ወደ አከባቢዉ እግር ጥሎት ጎራ የምል እንግዳን ተጨማር
የአከባቢዉን ማህበረሰብ ነባር ዕሰት የሆኑትን እግረመንገዳቸውን በጎብኚት ልዩ የጉብኚት ጊዜን እድያሳልፉ
መልካም ዕድልን ይዟል ፡፡ እንድህ ዘና ፈታ በማለት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ቦታዎችን በኦይዳ ጎብኚቶ ማሳለፍ
በኦይዳ ዛሬ የምጀመር አይደለም ብባል ግነት አይሆንም፡፡
ከጎፋ ዞን ዋና ከተማ ከሆነችዉ ሣውላና ከተለያዩ የሀገርቱ ክፍሎች በየዓመቱ ነሔሰ 27 ቀን በዑባ ደብረ ፀሐይ
ወረዳ ደብረፀሐይ ቀበለ በልዩ ድምቀት ወደ ምከበርበት የግንድ አንሳው መዳኃኒዓለም ዓመታዊ ንግስ ክብረ
በዓልን ለማክበር እና ክብረ በዓሉን ለመታደም ወደ ስፍራዉ ከዛሬ 109 ዓ/ም በፊት ጀምሮ የኦይዳን ወረዳ
አቋርጦ የምያልፍ እንግዳ የማይረሳቸዉ የጉዞ ማስታዎች ለዚሁ እንደጥሩ ማሳያ ተደርገዉ ልወሰዱ ይችላሉ ፡፡
ይሁን እንጅ በኦይዳ ወረዳ የቱሪዝም እምቅ አቅሞች ብኖሩም እነዚህን ስፍራዎች በቀላሉ ጎብኚዎች
በመድረስ በፈለጉበት ጊዜ መጎበኘት እንድችሉ በአከባቢዉ በቅ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሥራዎች (መንገድ፤
የሳኣ ጉልኣ ተራራ በኦይዳ ወረዳ ከሚገኙ ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦች አንዱነው ፡፡ የመስህቡ ለላኛዉ
መጠርያ ሳኣ ጉልአ (የመሬት እንብርት) ማለት ነዉ ፡፡ ይህ አስደናቂ ተራራ ከወረዳው ዋና ከተማ ሸፊቴ 4
ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን 2500-3000 ሜትር ከባህር ጠለለ በላይ ከፍታ አለው ፡፡ ከተራራው አናት
ሲወጡ መላው የከተማውን ክፍልና ሌሎች አከበቢዎችን በቀላሉ ማየት ያስችላል ፡፡ ከዚህም የተነሳ
በአካባቢው ቋንቋ ሳኣ-ጉልኣ የሚል ስያሜ አግኝቷል ፡፡ ትርጉሙም የመሬት እንብርት ማለት ነው፡፡ ሳኣ ጉልኣ
ተራራን በሸፊቴ ከተማ ማሃል ላይ ሆኖ ማየት የሚቻል ከመሆኑም በላይ ቀጥብሎ የቆመ መሆኑ ለየት
ያደርገዋል ፡፡ የሳኣ ጉልኣ ተራራ ሙሉ በሙሉ በምባል ደረጃ በሀገር በቀል ዕጽዋቶችና ተራራዉ በደን በመሸፈኑ
በዉስጡ በርካታ የዱር እንስሳት ዝሪያዎችን፣ የዕጽዋትና የአዕዋፍት ዝሪያዎችን ይዟል፡፡ በዉስጡ ከያዛቸው
ዕጽዋት ዝሪያዎች ጥቅቶቹ ዋርካ፣ ሾላ፣ ወይበታ፣ ትናንሽ ቁጥቋጦ፣ ሰንበለጥና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ከእንሳሳት ዝሪያዎች ጦጣ፣ ዝንጀሮ፣ ጅብ እና ከተሳብ እንስሳት እባብና መሰሎችየሚገኙበትነው፡፡
በጥንት ጊዜያት በሳኣ ጉልአ በተራራዉ አናት የባህላዊ እምነት ሐይማኖት መሪዎች(አባቶች) የባህላዊ እምነት
አምልኮት ሥራዓትን እንደምፈጽሙና በተራራዉ አናት ላይ አንድ ምንጭ ዉሃ እንደነበር ፤ ያችን በተራራዉ
አናት ላይ የምትፈልቀዉን ዉሃ ደርሶ የጠጣ ከተላያዩ የስጋ ደዌ ህመም ከመፈወስ ባለፈ ልጅ ያጣ ልጅ
እንድያገኝ፤ሀብት ያጣ ሀብት እንድያገኝ እንደምያደርግ የአከባቢዉ ሀገር ሽመግሌዎች ይናገራሉ ፡፡ በጥንት
ጊዚያት የሰኣ ጉልአ ተራራ በባህናዊ መንገድ እንደምጠበቅና በኦይዳ አከባቢ ያላገቡ ወንዶችና ሴቶች
(ወጣቶች) በተራራዉ አቅራቢያ በመሄድ እንደምዝናኑ ጭምር የአከባቢዉ ተወላጆች ይናገራሉ ፡፡ በአሁኑ
ስዓት ሳኣ ጉልኣ ተራራ በኦይዳ ወረዳ ህዝብ ንቁ የአሬንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካላ ለመጭዉ ትዉልድ በአረንጓዴ
የለመለመችውን ሳኣ ጉልኣን ወይም ኦይዳን ለማስወረስ ታቅዶ በተሰራዉ የመስክ ትግበራ ሳኣ ጉልኣን ጥንት
ወደነበረችበት ቁመና ይመልሳታል የምል ተስፋ ተጥሏል ፡፡ በዚህ አስደናቅ ተራራ የተለያዩ የባህል መዳኃኒት
እፅዋት ዓነቶች እንዳሉና ተራራዉ ለጥባለ መዳማ ቦታ ላይ ወደላይ ቀጥብሎ የወጣ የተራራ ሻኛ መሆኑ ልዩ
ማራክ ስፍራ አድርጎታል ፡፡