Professional Documents
Culture Documents
2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
i
2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ii
የመጀመሪያ እትም
መ/ ለይአውት ዲዛይን
ምስጋና
በመጀመርያ ምስጋና ለሀያሉ ፈጣሪ ዪሁን በመቀጠል ለመዝገበ ቃላቱ እና መለስተኛ
የሰዋሰው ጽሑፉን ለማዘጋጀት ደፋ ቀና ሲሉ ለነበሩ ሁሉ ምስጋና ይድረሳቸው።
መረጃዎችን በመስጠት ለተባበሩን ለቀቤና ብሄረሰብ አባቶችና ለቀቤነና ወረዳ ባህል
ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት ለቀቤናወረዳ አስተዳደር ለደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ
እንዲሂም ለኢፌድሪ ባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር ባልደረቦች ምስጋናና አክብሮታችንን
ለመግለጽ እንወዳለን
መቅድም
ማውጫ (ፉሽሸቱተ)
መግቢያ..............................................................................................................................vii
አነባበብ/ንበት..........................................................................................................vii
የቀቤና ህዝብና ቋንቋ.........................................................................................................ix
ቀቤኤንሲና ፊደሊ ማዓዳ የቀቤንኛ የፊደል ገበታ...........................................................xi
የመዝገበ ቃለቱ አጠቃቀም...............................................................................................xii
ምልክቶች እና አሕጽሮተ ቃላት ዝርዝር፡-....................................................................xiii
መለስተኛ የቀቤና ቋንቋ ሰዋሰዉ.....................................................................................xiv
ክፍል አንድ: ስም.....................................................................................................xv
ክፍል ሁለት፡ የስማዊ ሐረግ ገላጭ...................................................................xviii
ክፍል ሶስት: ተዉላጠ ስም.................................................................................xxvi
ክፍል አምስት: ግስ............................................................................................xxxiii
ክፍል ስድስት: ተሻጋሪ ግስ...............................................................................xxxvi
ክፍል ሰባት: ተጨማሪ እና ዉልድ ግስ........................................................xxxviii
ክፍል ስምንት: ሥማዊ ሀረግ የምንጠቀምበት ሌላ መንገድ...............................xli
ቀቤንኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት....................................................................................1-66
አባሪ 1-10.........................................................................................................................a-w
vii
መግቢያ
አነባበብ/ንበት
አናባቢ ፊደል
/ə/ እንደ ኧ ይነበባል
/i/ እንደ ኢ ይነበባል
/u/ እንደ ኡ ይነበባል
/e/ እንደ ኤ ይነበባል
/ɨ/ እንደ እ ይነበባል
/o/ እንደ ኦ ይነበባል
/a/ እንደ ኣ ይነበባል
ተነባቢ ፊደል
/ʔ/ እንደ ዕ ይነበባል
/n/ እንደ ን ይነበባል
/t/ እንደ ት ይነበባል
/m/ እንደ ም ይነበባል
/h/ እንደ ህ ይነበባል
/r/ እንደ ር ይነበባል
/b/ እንደ ብ ይነበባል
/s/ እንደ ስ ይነበባል
/l/ እንደ ል ይነበባል
viii
ሀ. ሕዝቡ
የቀቤና ሕዝብ የሚኖረው በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ ወልቂጤ ከተማና
ዙሪያ ሲሆን ከአዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ 150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ወልቂጤ
የጉራጌ ዞንና የቀቤና ወረዳ ዋና ከተማ ሲሆን ከሀዋሳ 450 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።
የቀቤና ህዝብ በሰሜን ከኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ጎሮ ወረዳ፣ በደቡብ
በኩል ከጉራጌ ዞን ቸሃ፣ እዣና አበሽጌ ወረዳዎች ፣ እንዲሁም በምዕራብ በኩል
ከጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሲሆን በምስራቅ ከጉራጌ ዞን ኮኪር ጌዳባኖ እና ሙህር-
አክሊል ወረዳዎች ይዋሰናል። የቀቤና ወረዳ ሃያ አራት (24) ቀበሌዎች አሉት።
በ 1999 ዓ.ም. በተካሄደ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የቀቤና ሕዝብ 52, 000 ነበር።
ለ. ቋንቋው
ቀቤና በደጋማው ምስራቃዊ የኢትዮ-ኩሻዊ ቋንቋ ቤተሰብ የሚመደብ ነው ። የቀቤና
ቋንቋ በከፍተኛ ደረጃ ከሀላባ ቋንቋ ጋር ዝምድና እንዳለው ዶ/ር ኦንጋዬ የፈቀደ
(2012፡13) እና የክራስ (2001፡43) ጥናቶችን በመጥቀስ ለማሳየት ችሏል።
በተጨማሪ ቋንቋው ከከንባትኛ ቋንቋ ጋር ግንኙነት እንዳለው እንዲሁም ገልጿል።
x
1. ዐ 14. ደ
2. ነ 15. ወ
3. ተ 16. ዘ
4. መ 17. ፈ
5. ሀ 18. ጠ
6. ረ 19. ሸ
7. በ 20. ጀ
8. ሰ 21. ቸ
9. ለ 22. ጨ
10. ገ 23. ዠ
11. የ 24. ኘ
12. ከ 25. ጰ
13. ቀ 26. ፐ
አማርኛ ቀቤናሲና
1. ስም ሱዕማ
2. ቅጽ ል ሀለጠ
3. ተዉላጠ ስም ሱዕሚ ዶኦረሻ
4. ግስ ጊስሰ
5. ግስ ቴሱ ተዉሳከ
6. መስተጻምር ዐፈቀም ሲሳኑ
7. ትምህርተ አንክሮ ወጌጨ
8. ዉልድ ቃል ዒልሊችቹ ከላማችቺ
9. ዉልድ ግስ ዒለመ ጊስሰ
xiii
- ሰረዝ
/ አማራጭ
1 አንደኛ መደብ
2 ሁለተኛ መደብ
3 ሶስተኛ መደብ
ሴ. አነስታይ
ወ ተባእት
ብ. ብዙ
ነ. ነጠላ
xiv
ቀው ሴኤጨ
ክፍል አንድ: ስም
የቀቤንሲና ቋንቋ ስሞች በጾታ ፣ በቁጥር እና በተለያዩ ሰዋሰዋዊ ምድቦች ቅርጻቸውን
ይለውጣሉ ወይም ይራባሉ። በሚከተሉት ንዑስ ክፍሎች በእያንዳንዱ ሰዋሰዋዊ
ምድብ ላይ መወያያዎች ቀርበዋል።
1.1 ጾታ
ፆታ በወንድና በሴት መካከል ያለውን ልዩነት በሰዋሰዋዊ ጥናት ሊያሳይ የሚችል
ነው። በቀቤንሲና ቋንቋ ዓረፍተ ነገር ሲመሰረት የጾታ ልዩነት በተመለከተ በግስ ላይ
ሊታይ ይችላል።
ምሳሌ 1:
ሀ. booru ametʃo ቦኦሩ ዐሜቾ ‘በሬመጣ ።’
saati ameto ሳኣቲ ዐኦሜቶ ‘ላምመጣች።’
ለ. isu ametʃo ኢሱ ዐሜቾ ‘እሱ መጣ።’
isə ameto ኢሰ ዐሜቶ ‘እሷመጣች።’
ምሳሌ 2:
ሀ. holəti ameto ሆለቲ ዐሜቶ ‘በግመጣ።’
holtʃu ametʃo ሀልቹ ዐሜቾ ‘በግ (ወ.) መጣ።’
holtʃuti ameto ሆልቹቲ ዐሜቶ ‘በግ (ሴ.)መጣች።’
ለ. tʃ'uulu ametʃo ጩኡሉ ዐሜቾ ‘ልጅ መጣ።’
tʃ'uulu ametʃo ጩኡሉ ዐሜቾ ‘ልጅ (ወ.)መጣ።’
tʃ'uuliti ameto ጩኡሊቲ ዐሜቶ ‘ልጅ (ሴ.) መጣች።’
ግሱ በቃሉ መጨረሻ በ/-to/-ቶ ካቆመ ጾታው ተባእት ሲሆን /-tʃo/-ቾ ኮሆነ ደግሞ
አነስታይ መሆኑ ማወቅ ይቻላል።
በሌላ መንገድ አነስታይን እና ተባህትን በተመለከተ እንደሚከተለው በቃላት ለይቶ
ለማሰቀመጥ ተችሏል።
xvi
ምሳሌ 3:
አንስታይ ተባእታይ
məntʃutə መንቹተ ሴትየዋ məntʃu usu መንቹኢሱ ሰውዬው
amətə ዐመተ እናት ana ዐና አባት
aməbetuta ዐመቤቱታ እህት aməbetu ዐመቤቱ ወንድም
məntʃutə መንቹተ ሚስት məntʃu መንቹ ባል
saatə ሳኣተ ላም boora ቦኦራ በሬ
haftut ሀፍቱት ልጃገረድ hardi ሀርዲ ወጣት
meat ሜኣት ሴት ləba ለባ ወንድ
1.1 ቁጥር
ምሳሌ 4:
ሀ. booru ametʃo ቦኦሩ ዐሜቾ በሬመጣ።
boorə-ti ameto ቦኦረቲ ዐሜቾ በሬዎች መጡ።
ለ. saati ameto ሳኣቲ ዐሜቶ ላምመጣች።
lələ-ti ameto ለለቲ ዐሜቶ ላሞች መጡ
ሐ. mənu ametʃo መኑ ዐሜቾ ሰው መጣ።
mənakə-ti ameto መናከቲ ዐሜቶ ሰዎችመጡ።
መ. tʃ'uulu ametʃo ጩኡሉ ዐሜቾ ልጅ መጣ።
tʃ'uulə-ti ameto ጩኡለቲ ዐሜቶ ልጆች መጡ።
ሠ. haftuti ameto ሀፍቱቲ ዐሜቶ ልጃገረድ መጣች።
haftanu-ti ameto ሀፍታኑቲ ዐሜቶ ልጃገረዶች መጡ።
ረ. holəti ameto ሆለቲ ዐሜቶ በግ መጣ።
holləə-ti ameto ሆለኧቲ ዐሜቶ በጎች መጡ።
በቀቤንሲና ቋንቋ የብዙ ቁጥር ቅርጻቸው ውስብስ ቢሆንም በተወሰነ ደረጃ ምሳሌ
4ሀ እና 4ሐ ላይ የሚታየው ቅጥያ /-ti/ ቲ/ት የብዙ ቁጥር ምልክት መሆኑን
xvii
ምሳሌ 5:
ሀ. faaŋo osəjo ፉኣንጎ ዖሰዮ ሌባ ተኛ።
faaŋetʃu-isu osəjo ፋኣንጌቹ ዒሱ ዖሰዮ ሌባው ተኛ።
ለ. məntʃuti osəo መንቹቲ ዖሰኦ ሴት ተኛች።
məntʃu-isə osəo መንቹ ዒሰ ዖሰኦ ሴትየዋ ተኛች።
ሐ. mənu osəjo መኑ ዖሰዮ ሰው ተኛ።
mənatʃu-isu osəjo መንቹ ዒሱ ዖሰዮ ሰውዬው ተኛ።
መ. holəti ameto ሆለቲ ዐሜቶ በግ መጣ።
holtʃtu-isu ameto ሆልቹ ዒሱ ዐሜቶ በጉ መጣ።
ሠ. wuʃəti ameto ውሸቲ ዐሜቶ ውሾች መጡ።
wuʃət-isə ameto ውሸቲሰ ዐሜቶ ውሾቹ መጡ።
ረ. wusitʃu ametʃo ውሲቹ ዐሜቾ ውሻ መጣ።
wusitʃu-isu ametʃo ውሲቹዒሱ ዐሜቾ ውሻው መጣ።
በአንዳንድ ስሞች መጨረሻ ላይ የእምርነት አመልካቹ /-isu/isə/ ተመሳሳይ ሲሆን
ቅጥያ አመልካች የሌላቸው ስሞች ደሞ ተፈጥሯዊ ትርጉም ይኖራቸዋል።
ምሳሌ 6:
tʃ’uulu ጩኡሉ ልጅ
tʃ’uulu-isu ጩኡሉ ዒሱ ልጁ tʃ’uul-isə ጩሊ ዒሱ ልጅቷ
boora ቦኦራ በሬ boor-isu ቦኦሩ ዒሰ በሬው
saati ሳኣቲ ላም saat-isə ሳኣቲ ዒሰ ላሟ
xviii
ምሳሌ 7:
kə təʃitai bokakətə ከ ተሸታኢ ቦካከተ
እነዚህ ውብ ቤቶች
‘እነዚህ ውብ ቤቶች’
ምሳሌ 8:
kə kiinu ከ ኪኢኑ ይህ ድንጋይ
kə məntʃuu ከ መንቹዑ ይህ ሰው
kə feeletʃuu ከ ፌኤሌቹዑ ይህ ፍየል
kə boora ከ ቦኦራ ይህ በሬ
tə saatə ተ ሳኣተ ይህች ላም
xix
ምሳሌ 9:
hikə kiinu ሂከ ኪኢኑ ያ ድንጋይ
hikə məntʃuu ሂከ መንቹዑ ያ ሰው
hikə feletʃuu ሂከ ፌኤሌቹዑ ያ ፍየል
hikə boora ሂከ ቦኦራ ያ በሬ
hitə saatə ሂተ ሳኣት ያች ላም
ከላይ እንደምናየው /tə/ ተን እያገለገለ ያለው ለአነስታይ ቅርብ ሲሆን kə/ከን ደግሞ
ለተባእት እና ለሌሎች አመልካች ሆኖ ያገለግላል፡: ከርቀት አንጻር ደግሞ hitə/ሂተ
ለአነስታይ ሩቅ አመልካች ብቻ ሲያገለግል hikə/ሂከ ደግሞ ለተባእት እና ለሌሎች
ሩቅ አመልካች ሆኖ ያገለግላል።
2.1.3 ጾታ አመልካች (ጠቋሚ)
ምሳሌ 10:
ቅርብ
tə məntʃuutə ተ መንቹኡተ ይች ሴት
kə məntʃuu ከ መንቹዑ ይህ ሰው
tə saatə ተ ሳኣት ይች ላም
kə boora ከ ቦኦራ ይህ በሬ
ሩቅ
hitə məntʃuutə ሂተ መንቹኡተ ያች ሴት
hikə məntʃuu ሂከ መንቹዑ ያ ሰው
hitə saatə ሂተ ሳኣተ ያች ላም
hikə boora ሂከ ቦኦራ ያ በሬ
xx
ምሳሌ 11:
ለቅርብ
kə bookku ከ ቦኦክኩ ይህ ቤት
kə bookkakə-tə ከ ቦኦክካከተ እነዚህ ቤቶች
kə holətə ከ ሆለተ ይህ በግ
kə holəə-tə ከ ሆለተ እነዚህ በጎች
ለሩቅ
hikə booku ሂከ ቦኦኩ ያ ቤት
hikə bookkakə-tə ሂከ ቦኦክካከተ እነዚያ ቤቶች
hikə holətə ሂከ ሆለተ ያ በግ
hikə holəə-tə ሂከ ሆለተ እነዚያ በጎች
2.2 ቁጥር
ቁጥር በስማዊ ሀረግ ውስጥ በማካተት በመጠን የስም ገለጭ ሊሆን ይችላል።ቁጥር
በስማዊ ሀረግ ውስጥ ሲጨመር የስሙን ትክክለኛ መጠን/ብዛት ለማወቅ ያስችላል።
በቀቤንሲና ቋንቋ ሁለት አይነት ቁጥር አለ። እነሱም መጣኝ/መቁጠሪያ እና ደረጃ
አመልካች ቁጥር ይባላሉ።
xxi
ምሳሌ 12:
mətu መቱ አንድ ləmu ለሙ ሁለት
səsu ሰሱ ሶስት ʃoolu ሾኦሉ አራት
ontu ዖንቱ አምስት leu ሌኡ ስድስት
ləməla ለመላ ሰባት hezətu ሄዘቱ ስምንት
honsu ሆንሱ ዘጠኝ tonu ቶኑ አስር
ምሳሌ 13:
mətu hak’a መቱ ሀቃ አንድ ዛፍ
mətu booku መቱ ቦኦኩ አንድ ቤት
ምሳሌ 15:
ሀ mətik’k’i hak’a መቲቅቂ ሀቃ የመጀመሪያው ዛፍ
ləmik’k’i hak’a ለሚቅቂ ሀቃ የሁለተኛው ዛፍ
səsik’k’i hak’a ሰሲቅቂ ሀቃ የሦስተኛው ዛፍ
ለ mətik’k’i booku መቲቅቂ ቦኦኩ የመጀመሪያው ቤት
ləmik’k’i booku ለሚቅቂ ቦኦኩ የሁለተኛው ቤት
səsik’k’i booku ሰሲቅቂ ቦኦኩ የሦስተኛው ቤት
የደረጃ አመልካች ቁጥር ከስም በፊት ሲመጣ የቃሉ መጨረሻ አናባቢ ቅርጹ ወደ
i/ኢ ይቀየራል።
2.3 ቅጽል
ቅጽል የንግግር(የቃል)ክፍል ሲሆኑ በስማዊ ሀረግ ውስጥ የስም ገላጭ ቃል ሆኖ
ያገለግላል። በቀቤንሲና ቋንቋ አብዛኛውን ጊዜ ቅጽል ከስም በፊት ይመጣና ስምን
ይገልጻል።
ምሳሌ 16:
miilkamu faarʃu ሚኢልካሙ ፋኣርሹ ቆንጆ ፈረስ
gəmbəla okona/odinut ገምበላ ዖኮና/ዖዲኑት ጥቁር ጨርቅ
wadʒu hinkuta ዋጁ ሂንኩታ ነጭ ጥርስ
biʃə saatə ቢሸ ሳኣተ ቀይ ላም
mədila tʃ'uulu መዲላ ጨኡሉ ወፍራም ልጅ
k’ətʃ'u meatə ቀጩ ሜኣተ ቀጭን ሴት
keemənu ʃaant’a/borsa ኬኤመኑ ሻኣንጣ/ቦርሳ ከባድ ቦርሳ
በቅጽል ላይ የብዙ ቁጥር: የብዙ ቁጥር ምልክት በቅጽል ላይ አይታይም።
ምሳሌ 17:
miilkamu faarʃakətə ሚኢልካሙ ፋኣርሻከተ ቆንጆ ፈረሶች
gəmbəla okonakətə ገምበላ ዖኮናከተ ጥቁር ልብሶች
wadʒu hinkutə ዋጁ ሂንኩተ ነጭ ጥርሶች
biʃə lələtə ቢሻ ለለተ ቀይ ላሞች
mədiila tʃ'uulətə መዲኢላ ጩኡለተ ወፍራም ልጆች
xxiv
ምሳሌ 18፡
ሀ. gəbətʃu faaŋa ገበቹ ፋኣንጋ አጭር ሌባ
gəbətʃu isu faaŋa ገበቹ ዒሱ ፋኣንጋ አጭሩ ሌባ
ለ. gəbətʃu məntʃtʃutə ገበቹ መንችቹተ አጭር ሴት
gəbətʃu isə məntʃtʃutə ገበቹ ዒሰ መንችቹተ አጭሯ ሴት
ሐ. mədiila boora መዲኢላ ቦኦራ ወፍራም በሬ
mədiilu isu boora መዲኢሉ ዒሱ ቦኦራ ወፍራሙ በሬ
መ. mədiila saatə መዲኢላ ሳኣተ ወፍራም ላም
mədiila isa saatə መዲኢላ ዒሳ ሳኣተ ወፍራሟ ላም
ምሳሌ 18:
miilkamu faarʃu ሚኢልካሙ ፋኣርሹ ቆንጆ ፈረስ
miilkamu-isu faarʃu ሚኢልካሙ ዒሱ ፋኣርሹ ቆንጆው ፈረስ
በቀቤና ቋንቋ በቅጽል ላይ የእምርነት ምልክት /-isu/ ይታይበታል።
መሰረታዊ የስማዊ ሀረግ ቅደም ተከተል ባህርይ
በቀቤና ቋንቋ የስማዊ ሀረግ ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ማየት ይቻላል።
ምሳሌ 19:
hikə ʃoolu k’iraraanu k’ələt’aakətə ሂከ ሾኦሉ ቂራራኣኑ ቀለጣኣከተ
እነዚያ አራት ረጃጅም ጦር
ʃoolk’k’i isu k’oomərə məntʃttʃtu ሾአልቅቂ ዒሱ ቆአመረ መንቹተ
አራተኛውጠንካራሰው
xxv
ምሳሌ 20:
ነጠላ አማርኛ ብዙ አማርኛ
1. ani/ ዐኒ እኔ nəu/ነዑ እኛ
2. ati/ ዐቲ አንቺ/ አንተ hanu/ ሀኣኑ እናንተ
3. isu/ዒሱ እሱ issə/ዒሰ እነሱ
3. isə/ዒሰ እሷ
ምሳሌ 21:
rijadi harutʃtʃu ሪያዲ ሀሩችቹ የሪያድ አህያ
isi harutʃtʃu ዒሲ ሀሩችቹ የሱ አህያ
xxvii
ምሳሌ 22:
i haritə ዒ ሀሪተ የኔ አህዮች
ki haritə ኪ ሀሪተ ያንተ አህዮች
ki haritə ኪ ሀሪተ ያንቺ አህዮችህ
isi haritə ዒሲ ሀሪተ የሱ አህዮች
ise haritə ዒሴ ሀሪተ የሷ አህዮች
ni haritə ኒ ሀሪተ የኛ አህዮች
kine haritə ኪኔ ሀሪተ የናንተ አህዮች
issa haritə ዒሳ ሀሪተ የነሱ አህዮች
xxviii
ምሳሌ 23:
ባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ
ku məntʃtʃu ይህ ሰዉ gonu aburi gəlasintʃwa
ጥሩ ገበሬ ነው።
ኩ መንችቹ ጎኑ ዐቡሪ ገላሲንቿ
tʃ'a isa ልጅቷ kəbensina afo rosisa የቀቤና ቋንቋ
ጫ ኢሳ ቀቤንሲና ዐፎ ሮሲሳ ታስተምራለች
i aməbetu የኔ ወንድም hunda enkenamoha በጣም ብልህ ነው
ዒ ዐመቤቱ ሁንዳ ዔንኬናሞሃ
ati ዐቲ አንተ i beʃaha ዒ ቤሻሃ የእኔ ጓደኛ ነህ
4.1 ባለቤት
ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ የዓረፍተ ነገር መዋቅር ተለዋዋጭነት ቢኖርም
በቀቤነሲና ቋንቋ መሠረታዊ የዓረፍተ ነገር መዋቅር ባለቤት – ተሳቢ – ግስ ነው።
ባለቤት በዓረፍተ ነገር ውስጥ ድርጊት ፈጻሚ ሰው ወይም ነገር ነው። ብዙውን ጊዜ
ባለቤት በስማዊ ሐረግ ወይም ተውላጠ ስም ነው። ከዚህ በተጨማሪ ባለቤት
በአረፍተ ነገር መጀመሪያ ላይ ይገኛል።
ምሳሌ 24:
ባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ
ku məntʃtʃu ይህ ሰዉ gonu aburi gəlasintʃwa ጥሩገበሬነው።
ኩ መንችችቹ ጎኑ ዐቡሪ ገላሲንቿ
ati ዐቲ አንተ i beʃaha ዒ ቤሻሃ የእኔ ጓደኛ ነህ
ከላይ በተጠቀሰው ምሳሌ መሠረት ስማዊ ሐረግ እንደማሰሪያ አንቀጽ ጥቅም
ላይ ውሏል። ማሰሪያ አንቀጹ ስለባለቤት ገለጻ የሚያደርግ ከሆነ እየተነገረለት ያለው
ስማዊ ሀረግ ማሰሪያ አንቀጽ ነው።
ምሳሌ 25:
ani aburi gəlasintʃwa ዐኒ ዐቡሪ ገላሲንቿ 'እኔ ገበሬ ነኝ።
ati aburi gəlasintʃwa ዐቲ ዐቡሪ ገላሲንቿ 'አንቺ ገበሬ ነሽ።
ati aburi gəlasintʃwa ዐቲ ዐቡሪ ገላሲንቿ 'አንተ ገበሬ ነህ።
isu aburi gəlasintʃwa ዒሱ ዐቡሪ ገላሲንቿ 'እሱ ገበሬ ነው።
isə buri gəlasintʃotə ዒሳ ዐቡሪ ገላሲንቾተ 'እርሷ ገበሬ ናት።
nəw aburi gəlasinnətə ነዑ ዐቡሪ ገላሲንነተ 'እኛ ገበሬ ነን።
hanu aburi gəlasinnətə ሀኑ ዐቡሪ ገላሲንነተ ‘እናንተ ገበሬዎች ናችሁ።
issə aburi gəlasinnətə ዒሰ ዐቡሪ ገላሲንነተ 'እነሱ ገበሬዎች ናቸው።
4.2.2 ገላጭ እንደማሰሪያ አንቀጽ
ስለባለቤት ተጨማሪ ነገር የሚያወራ ከሆነ የስም ገላጩ እንደ ማሰሪያ አንቀጽ
ሊያገለግል ይችላል።
xxx
ምሳሌ 26:
ባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ
ku habəru ይህ ቅጠል biʃaha ቀይ ነው
ኩ ሀበሩ ቢሻሃ
ku habəru ይህ ቅጠል bololok’waha ቢጫ ነው
ከ ሀበሩ ቦሎሎቋሃ
hiku məntʃtʃu ያ ሰዉ hundə hilaha በጣም መጥፎ ነው
ሂኩ መንችቹ ሁንዳ ሂላሃ
hiti məntʃtʃutə ያች ሴት hilət በጣም መጥፎ ናት
ሂቲ መንችቹተ ሁንዳ ሂለተ
ቀደም ብለን እንደተመለከትነው ቅጽል በዓረፍተ ነገር ውስጥ እንደ ማሰሪያ
አንቀጽ ሆና ጥቅም ላይ ይውላል።.
4.2.3 ቁጥር እንደማሰሪያ አንቀጽ፡
በዓረፍተ ነገር ውስጥ ስለባለቤት ስለትክክለኛ ቁጥር ወይም ብዛት መናገር ከተፈለገ
ቁጥሩም እንደማሰሪያ አንቀጽ ሊያገለግል ይችላሉ።
ምሳሌ 27:
ባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ
issə ዒሰ እነሱ səsuwa ሰሱዋ ሶስትናቸው
issə ዒሰ እነሱ ontuwa ዖንቱዋ አምስትናቸው
isu ዒሱ እሱ mətik’kiha መቲቅቂሃ መጀመሪያነው
isu ዒሱ እሱ mətik’k’iha hak’i መቲቂያ ሀቂ መጀመሪያነበር
በሰንጠረዥ ላይ በአረፍተ ነገር ውስጥ ያሉት ቁጥሮች እንደማሰሪያ አንቀጽ
ያገለግላሉ።
4.2.4 ባለንብረትነት እንደማሰሪያ አንቀጽ
በዓረፍተ ነገር ውስጥ ባለቤት ስለአንድ ሰው ንብረትነት የሚያወራ ከሆነ የተገለጸው
ባለንብረት እንደ ማሰሪያ አንቀጽ ሆኖ ያገለግላል።
xxxi
ምሳሌ 28:
ዕባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ
kun ይህ kiineha የርስዎ ነው
ኩን ኪኢኔሃ
hikun ያ kiineha የርስዎ ነው
ሂኩን ኪኢኔሃ
ku ይህ harutʃtʃu kiineha አህያ ያንተ ነው
ኩ ሀሩችቹ ኪኢኔሃ
hiku ያ harutʃtʃu kiineha አህያ ያንተ ነው
ሂኩ ሀሩችቹ ኪኢኔሃ
ku ይህ harutʃtʃu habuuri gəlasintʃtʃi isəha አህያ የገበሬው ነው
ኩ ሀሩችቹ ሀቡኡሪ ገላሲንችቺ ዒስሃ
hiku ያ harutʃtʃu haburi gəlasintʃtʃi isəha አህያ የገበሬው ነው
ሂኩ ሀሩችቹ ሀቡኡሪ ገላሲንችቺስ ዒሲሃ
ከላይ እንዳየነዉ ባለቤትነት ም እንደዚሁ የአረፍተ ነገሩ ማሰሪያ አንቀጽ
መሆን እንደሚችል ያሳያል።
4.2.5 ገላጭ እንደማሰሪያ አንቀጽ
በዓረፍተ ነገር ውስጥ ገላጭ እንደ ማሰሪያ አንቀጽ ሆኖ ያገለግላል። ማሰሪያ
አንቀጹ አሉታዊም አዎንታዊም ይችላል።
ምሳሌ 29:
ባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ
isu ዒሱ እሱ faaŋetʃoa ፋኣንጌቾኣ ሌባ ነው
isu ዒሱ እሱ faaŋa habaa ፋኣንጋ ሀባኣ ሌባ አይደለም
booru isu በሬው biʃaha ቢሻሃ ቀይ ነው
ቦኦሩ ዒሱ
booru isu በሬው biʃa haba ቀይ አይደለም
ቦኦሩ ዒሱ ቢሻ ሀባ
isə ዒሰ እሷ gəbətʃotə ገበቾተ አጭር ናት
isə ዒሰ እሷ gəbətʃo təbaa ገበቾ ተባኣ አጭር
አይደለችም
xxxii
ምሳሌ 30:
ባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ
isu እሱ faaŋaha ሌባነው
ዒሱ ፋኣንጋሃ
isu እሱ faanga hak’ii ሌባነበር
ዒሱ ፋኣንጋ ሀቂዒ
harutʃtʃu isu አህያዉ biʃaha ቀይነው
ሀሩችቹ ዒሱ ቢሻሃ
harutʃtʃu isu አህያዉ biʃa hak’ii ቀይነበር
ሀሩችቹ ዒሱ ቢሻ ሀቂዒ
xxxiii
ክፍል አምስት: ግስ
በቀቤኤንሲና ቋንቋ ግስ የዓረፍተ ነገር የማዕዘን ድንጋይ ነው።ብዙ ጊዜ የዓረፍተ
ነገር ማሰሪያ አንቀጽ ግስ ነው። ግስ አንድ ድርጊት ሲፈጸም ክስተትን ፣ ሂደትን ፣
ሀሳብን ወይም ድርጊትን ይገልፃል።
ምሳሌ 31፡
ባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ
wu isu ዉ ዒሱ ውሃው zaazənuዛኣዘኑ ይፈሳል
tʃ’a isə ጫ ዒሰ ልጅቷ osəwo ዖሰዎ ተኛታለች
i aməi osut የኔ ወንድሞች bitənta ይጣላሉ
ዒ ዐመዒ ዖሱቲ ቢተንታ
ki anu ኪዐኑ ያንተ አባት reejo ሬኤዮ ሞተ
i aməi osut የኔ ወንድሞች bitənto ተጣሉ
ዒ ዐመኢ ዖሱቲ ቢተንቶ
5.1 ግስ ላይ መደብ አመልካች
በቀቤኤንሲና ቋንቋ ዉስጥ ግስ ከባለቤት ጋር ይስማማል። በ 1 ኛ መደብ ነጠላ
ቁጥር ያለዉ ባለቤት 1 ኛ መደብ ነጠላ ቁጥር ግስ ይፈልጋል።የሚከተሉት
ምሳሌዎች በሁሉም መደቦች ላይ መስማማቱን ያሳያል።
ምሳሌ 32:
ani dəgudam ዐኒ ደጉዳሚ 'እኔ እሮጣለሁ።'
ati dəgudanti ዐቲ ደጉዳንቲ 'አንተ ትሮጣለህ።
ati dəgudanti ዐቲ ደጉዳንቲ 'አንቺ ትሮጫለሽ
isu dəgudənu ዒሱ ደጉደኑ 'እሱይሮጣል
isə dəguda ዒሰ ደጉዳ 'እሷ ትሮጣለች
nəu dəgudam ነዑ ደጉደም 'እኛእንሮጣለን
hanu dəgudenəntə ሀኑ ደጉዴነንተ 'እናንተ ትሮጣለችሁ'
issə dəguda ዒሰ ደጉዳ 'እነሱይሮጣሉ።'
xxxiv
ምሳሌ 33:
isə beereta dəgudo ዒሰ ቤኤሬተ ደጉዶ ‘ትናንት እሷ ሮጣለች።
isə tesu dəguda ዒሰ ቴሱ ደጉዳ ‘አሁን እሷ ትሮጣለች።
isə gəatə dəguda ዒሰ ገኣተ ደጉዳ 'ነገ እሷ ትሮጣለች።'
ከላይ የተሰመረባቸው ቃላቶች ጊዜ ማሳያ ሲሆን መቼ እንደተፈጸመም ያስረዳናል።
ምሳሌ 34:
rorru woktetʃ biritə isə dəgudok’i
ሮርሩ ዎክቴች ቢሪተ ዒሰ ደጉዶቂ 'ከረጅም ጊዜ በፊት እሷ ሮጣ ነበር።'
አንድ ነጠላ ሂደት ወይም ተደጋጋሚ ድርጊትወይም ክስተት በሚገልጽበት ጊዜ
የመጀመሪያው ግስ መደቡን ጠቋሚ ነዉ። የተሰመረባቸዉ ተዉሳከ ግሶች ተደጋጋሚ
ወይም ቀጣይነት ያለዉ ዐረፍተ ነገር ስንሰራ የምንጠቀምበት ነዉ።
ምሳሌ 35:
isu mismaros fək’əransi wok’əro
ዒሱ ሚስማሮስ ፈቀራንሲ 'እሱ ሚስማሩን ደጋግሞ መታ።'
isə dəgudənənjo
ዒሰ ደጉደነንዮ 'እሷእየሮጠች ነው።'
isə gumərə dəguda
ዒሰ ጉመረ ደጉዳ 'እሷሁልጊዜ ትሮጣለች።'
5.3 አዎንታዊ እና አሉታዊ ዓረፍተ ነገር
ልክ እንደ ሌላ ማሰሪያ አንቀጽ በቀቤንሲና ቋንቋ የዓረፍተ ነገርሩ ይዘት አዎንታዊ እና
አሉታዊ ማድረግ ይችላል።
xxxv
ምሳሌ 36፡
ani faaŋaha ዐኒ ፋኣንጋሃ እኔ ሌባ ነኝ።
ani faaŋa haba ዐኒ ፋኣንጋ ሀባ እኔ ሌባ አይደለሁም።
ani dəgudam ዐኒ ደጉዳም እኔ እሮጣለሁ።
ani dəgudam-ba ዐኒ ደጉዳምባ እኔ አልሮጥም።
ani aburi gəlasintʃo ዐኒ ዐቡሪ ገላሲንቾ እኔ ገበሬ ነኝ።
ani aburi gəlasintʃo haba ዐኒ አቡሪ ገላሲንቾ ሀባ እኔ ገበሬ አይደለሁም።
ከላይ በአረፍተ ነገር ውስጥ የተሰመሩት ቃል/ቅጥያ haba/-ba አሉታዊ
መሆናቸውን ያሳያል።
xxxvi
ምሳሌ 37:
ተሸጋሪ ግስ ኢተሸጋሪ ግስ
muru ሙሩ መቁረጥ dəguudu ደጉኡዱ መሮጥ
dəgu ደጉ ማወቅ ubu ዑቡ መዉደቅ
motʃ’otʃ’u ማዳመጥ t’iizu ጢኢዙ መታመም
ሞጮጩ
assu ዐሱ መስጠት rewu ሬው መሞት
የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ብዙውን ጊዜ ድርጊቱን እየፈጸመ ያለ ሰው/ነገር ነው;፡
እንዲሁም ተሳቢዉ ብዙ ጊዜ ሰዉ ወይም እቃ ሆኖ ድርጊቱን የሚቀበል ነው።
ስለባለቤቱ ማን ነው? ብለን እንጠይቃለን። ስለተሳቢዉ ማንን? ብለን እንጠይቃለን።
በዓረፍተ ነገር ውስጥ ባለቤት ቡዙ ጊዜ በአረፍተ ነገር መጀመሪያ ላይ ሲገኝ ተሳቢ
ደግሞ ባለቤትን ይከተላል። አንዳንድ ጊዜ ባለቤት በግልጽ ላይታይም ይችላል።
ምሳሌ 38:
ሀ. wusitʃtʃu isə adəntʃuiseta gəmito
ውሲችቹ ዒሰ ዐደንቹ ዒሴታ ገሚቶ ዉሻዋ ድመቷን ነከሰች።
ለ. adəntʃtʃu isə wusitʃtʃuiseta gəmito
ዐደንችቹ ዒሰ ውሲችቹ ዒሴታገሚቶ ድመቷ ውሻዋን ነከሰች።
ምሳሌ 39:
abədi kitabə isu k'ərəjoዐብዲ ኪታበ ዒሱ ቀረዮ አብዲ መጽሐፉን አነበበ።
isu holtʃu isu gorətʃ’o ዒሱ ሆልቹ ዒሱ ጎረጮ እሱ በጉን አረደ።
isəbooku isu idʒarto ዒሰ ቦኦኩ ዒሱ ዒጃርቶ እሷ ቤቱን ሠራች
isə book’olo isu hirito ዒሰ ቦኦቆሎ ዒሱ ሂሪቶ እሷ በቆሎውን ገዛች።
ምሳሌ 40:
sitina esa leeo ሲቲና ዔሳ ሌኤኦ ሲቲና እኔን አየችኝ።
sitina keesa leoha ሲቲና ኬኤሳ ሌኦሃ ሲቲና አንተን አየችህ።
sitina keasa leoha ሲቲና ኬኤሳ ሌኦሃ ሲቲና አንችን አየችሽ።
sitina isu leosi ሲቲና ዒሱ ሌኦሲ ሲቲና እሱን አየችዉ።
sitina isetə leose ሲቲና ዒሴተ ሌኦሴ ሲቲና እሷን አየቻት።
sitina neesa leone ሲቲና ኔኤሳ ሌኦኔ ሲቲና እኛን አየችን።
sitina kiinetə leeohine ሲቲና ኪኢኔተ ሌኤኦሂኔ ሲቲና እናንተን አየቻችሁ።
sitina isatə leosə ሲቲና ዒሳተ ሌኦሰ ሲቲና እነሱን አየቻቸዉ።
xxxviii
ምሳሌ 41:
ሀ. i annu geeba orojoh muuzitə herrijoh
ዒ ዐንኑ ጌኤባ ዖሮዮዕ ሙኢዚተ ሄርሪዮዕ
‘የኔ አባቴ ወደ ገበያ ሄዶ ሙዝ ገዛ።’
ለ. i annu geeba orojoh muuzitə herrinu
ዒ ዐንኑ ጌኤባ ዖሮዩዕ ሙኡዚተ ሄርረኑ
‘የኔ አባቴ ወደ ገበያ ሄዶ ሙዝ ይገዛል።’
ሌላ ተጨማሪ ግስ ድርጊት በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚከናወን ለማሳየት ያገለግላል።
ምሳሌ 42:
isə dagudənəni heani isu ametʃtʃoh
ዒሰ ዳጉደነኒ ሄዓኒ ዒሱ ዓሜችቾህ
‘እሷ እየሮጠች ሳለ እሱ መጣ።’
በድርብ ግስ ላይ ቅርጽ፣ መደብ ወይም ጊዜ ላይ መረጃ ሳይሰጡ ስለድርጊቱ
ለመናገር ጥቅም ላይ ይውላል።
ምሳሌ 43:
ሀ. agu tʃ’uulatə hundə t’uumah
ዐጉ ጩኡላተ ሁንደ ጡኡማሀ
‘መጠጣት ለሕፃን በጣም አስፈላጊ ነው።’
ለ. azutə agu tʃ’uulatə hundə t’uumah
ዐዙተ ዐጉ ጩኡላተ ሁንደ ጡኡማህ
‘ወተት መጠጣት ለህጻን በጣም አስፈላጊ ነው።’
xxxix
ምሳሌ 44:
reu→ʃuu ሬዑ→ሹዑ ‘መሞት→መግደል’
ሌሎች የመንስኤ ቃላት ደግሞ የሚመሰረቱት በቃሉ መካከል ቅጥያ /-is-/ -ኢሱ-
በማስገባት ነው።
ምሳሌ 45:
roosu→roosisu
ሮዖሱ→ሮዖሲሱ ‘መማር→ማስተማር’
wəmaihu→wəmasu
ወማዒሁ→ወማዒሀኑገዐሰሱ ‘መንገስ→ማንገስ’
itu→itisu
ዒቱ→ዒቲሱ ‘መብላት→መመገብ (ማብላት)’
dəgudu→dəgusisu
ደጉዱ→ደጉሲሱ ‘መሮጥ→ማስሮጥ’
orisəmu→orisu
ዖሪሰሙ→ዖሪሱ ‘መቸገር→ማስቸገር’
afuulu→afuʃʃu
ዓፉዑሉ→ዓፉሽሹ ‘መቀመጥ →ማስቀመጥ’
7.2.2 ተለዋዋጭ
ተለዋዋጭ ባለቤቱ እርስ በርሱ ድርጊቱን የሚፈጽምበት የግስ ዉልድ ነዉ ።የቃሉ
ባለቤት ሁልጊዜ ብዙ ቁጥር ነዉ። በቀቤነሲና ቋንቋ የተለዋዋጭ ድርጊትን ለማወቅ
xl
ምሳሌ 46:
hok’k’əru→hok’k’ərə-k’əmu
ሆቅቀሩ→ሆቅቀረቀሙ መምታት→መመታታት
leu→lea-k’əmu
ሌዑ→ሌዐቀሙ ማየት→መተያየት
abbisu→ abbisə-k’əmu
ዓብቢሱ→ዓብቢሰቀሙ ማክበር→መከባበር
bitəmu→bitəbə-k’əmu
ቢተሙ→ቢተበቀሙ መጣላት→መጠላላት
ahjusu→ajusə-k’əmu
ዓህዩሱ→ዓዩሰቀሙ ማግባት→መጋባት
ምሳሌ 47:
itʃoo→itə-moh ዒቾዖ→ዒተሞዕ በላ→ተበላ
wək’k’əro→wək’ərə-mo ወቅቀሮ→ወቅቀረሞዕ መታ→ተመታ
fəhɳoh→fəhntəjoh ፈዕኞዕ→ፈዕንተዮዕ ከፈተ→ተከፈተ
t’ufo →t’ufə-moh ጡፍዖ→ጡፈሞዕ ዘጋ→ተዘጋ
ʃijoh→ʃeemasi ሺዮዕ→ሼኤማሲ ገደለ→ተገደለ
kətəboh→kətəbə-moh ከተቦዕ→ከተበሞዕ ፃፈ→ተፃፈ
assijoh→assə-moh ዓስሲዮዕ→ዓስሰሞዕ ሰራ–ተሰራ
xli
ምሳሌ 48:
i annu wussitʃiha isi k’əw maalə assijosi
ዒ ዐንኑ ውስሲቺሀ ኢሲ ቀው ማኣለ ዓስሲዮሲ
'የኔ አባትለውሻዉ ትንሽ ስጋሰጠው’
i aməti ise odinusə atosə
ዒ ዐመቲ ዒሴ ዖዲኑሰ ዓቶሰ 'የኔ እናትለሷ ልብሷን ሰጠቻት።’
rijad-i ሪያዲ ‘ለሪያድ’
hajat-e ሀያቴ ‘ለሀያት’
hanan-e ሀናኔ ‘ለሀናን’
ምሳሌ 49:
mooggantʃi boorsə ሞኦግጋንቺ ቦኦርሰ ‘የሌባው ቦርሳ’
zəzəlantʃatʃi gizzə ዘዘላንቻቺ ጊዝዘ ‘የነጋዴው ገንዘብ’
annii booku ዓንኒዒ ቦከኩ ‘የአባቴ ቤት’
abbənii bokku ዓብበኒዒ ቦክኩ ‘የወንድ አያቴ ቤት’
harre dubu ሀርሬ ዱቡ ‘የአህያ ጅራት’
xlii
ምሳሌ 50:
kədir-i harrutʃtʃu ከዲሪ ሀርሩችቹ ‘የከድር አህያ’
kədir-i harritə ከዲሪ ሀርሪተ ‘የከድር አህዮች’
rəmzija harrutʃtʃu ረምዚያ ሀርሩችቹ ‘የረምዚያ አህያ’
rəmzija harritə ረምዚያ ሀርሪተ ‘የረምዚያ አህዮች’
8.3 ቦታ / locative
ቦታ አጠቃላይ አካባቢን ሲያሳይ በቀቤንሲና ቋንቋ በስማዊ ሀረግ ውስጥ ቦታ
አመልካቹ በስም በመጨመር /-ni/ ኒ በመጠቀም መግለጽ ይቻላል።ቦታን ለማወቅ
‹የት?› የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለብን።
ምሳሌ 51:
geebo giira-ni buubo
ጌኤቦ ጊኢራኒ ቡኡቦ 'ገበያ በእሳት ወደመ።'
i anu tʃaambuulakətə hakəne hirijo
ዒ ዐኑ ጫኣንቡኡላከተ ሀከኔ ሂሪዮ 'የኔ አባት ቲማቲሞችን የት ሸጠ?’
i anu tʃaambuulakətə geba-ni hirijo
ዒ ዐኑ ጫኣንቡኡላከተ ጌኤባኒ ሂሪዮ 'አባቴ ቲማቲሞችን ገበያ ላይ ሸጠ።'
odinuti t’ərəbeezi aleeni afoulito
ዖዲኑቲ ጠረጴኤዚ ዐሌኤኒ ዐፎኡሊቶ ‘ልብስ ጠረጴዛ ላይ ተቀመጠ።’
8.4 አቅጣጫ
አቅጣጫ ወደ አንድ አካባቢ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሲሆን አቅጣጫውን በስማዊ
ሐረግ ውስጥ በስም ላይ /-ba/ ባ በመጨመር ማወቅ እንችላለን። አቅጣጫን ለማወቅ
ወዴት? የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለብን።
xliii
ምሳሌ 52:
i aməti uftuta gəjto
ዒ ዐመቲ ሀፍቱታ ገይቶ 'የእኔ እናት ልጃገረድ ጠራች።’
haftusə haka-ba oroto?
ሀፍቱሰ ሀካባ ዖሮቶ ‘ልጃገረድዋ ወዴት ሄደች?'
haftusə aməi-ba oroto
ሀፍቱሰ ዐመኢባ ዖሮቶ ‘ልጃገረድዋ ወደ እናቴ ሄደች።’
geeba waalti ጌኤባ ዋኣልቲ ‘ወደ ገበያ’
wəlk’it’itə waalti ወልቂጢተ ዋኣልቲ ‘ወደ ወልቅጤ’
rooʃ mini waalti ሮኦሽ ሚኒ ዋኣልቲ ‘ወደ ትምህርት ቤት’
ምሳሌ 53:
haftu isə ameetou hakəm biitʃet-i
ሀፍቱ ዒሰ ዐሜኤቶሁ ሀከም ቢኢቼቲ 'ልጃገረድ የመጣቸው ከየት ነበር?'
haftuti geebeetʃtʃ-i ameto
ሀፍቱቲ ጌኤቤኤችቺ ዐሜኤቶ 'ልጃገረድ ከገበያ መጣች።'
haftuti amaantə-i ameeto
ሀፍቱቲ ዐማኣንተዒ ዐሜኤቶ 'ልጃገረድ ከእናቴ መጣች።'
8.6 መሳሪያዊ / instrument
መሣሪያ አንድን ድርጊት ለመፈፀም የምጠቀምበት እቃ ወይም ዘዴ ነው። መሣሪያው
በስማዊ ሐረግ ውስጥ በስም መጨመር ላይ -ni/ -ኒ ይገለጻል። መሣሪያውን ለማወቅ
'ከምን ጋር?' የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለብን።
ምሳሌ 54:
geebosi mii-ni bəjo ጌኤቦሲ ሚኢኒ በዮ 'ገበያው በምን ጠፋ?
geebo giiraa bəjo ጌኤቦ ጊኢራኣ በዮ 'ገበያ በእሳት ወደመ።'
xliv
ምሳሌ 55:
kəbaa ከባኣ ‘እዚህ’
hikəbaa ሂከባኣ ‘እዚያ’
k’eerəʃbaa ቄኤረሽባኣ ‘ሩቅ’
wooro wali ዎኦሮ ዋሊ ‘ታች’
ali ዐሊ ‘ላይ’
ada ዐዳ ‘ቀጥታ’
guurətə ጉኡረተ 'ግራ'
məkkitə መክኪተ ‘ቀኝ’
səmooni ሰሞኦኒ ‘አናትላይ'
giidənu ጊኢደኑ ‘ቅርብ’
teesu ቴኤሱ ‘አሁን'
etəru ዔተሩ ‘በኋላ’
tesuni ቴኤሱኒ ‘ወዲያዉኑ’
የቦታ ተዉሳከ ግሶች “የት?”የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል።
xlv
ምሳሌ 56:
biritə ቢኢሪተ ‘በፊት'
itəron ዔተሮኦኒ ‘በስተመጨረሻ'
mətorə ሜኤጦረ ‘አንድጊዜ'
kəbəri ከበሪ 'ዛሬ'
gəatə ገኣተ 'ነገ'
beretə ቤኤሬተ 'ትላንት'
kəzəmaani/kəbira ከዘማኣኒ/ከቢኢረ 'በዚህዓመት'
ametənu zəmaani ዐሜኤተኑ ዘማኣኒ 'በሚቀጥለውዓመት'
ለጊዜ አመልካች ተዉሳከ ግስ “መቼ?” የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል።
8.7.3 ሁኔታዊ (ባህራዊ) ተዉሳከ ግስ
ምሳሌ 57፡
ʃəfiteeni ሸፊኢቴኤኒ 'በፍጥነት'
leləni ሌኤለኒ 'በዝግታ’
guːmər ጉኡመረ 'ሁልጊዜ'
mətomətoor መቶ መቶኦረ 'አንዳንድ ጊዜ’
k’ədireni ቀዲኢሬኒ 'በኃይል'
k’orəp’iiʃani ቆረጲኢሻኒ ‘በጥንቃቄ’
hunda ሁንዳ 'በጣም'
ሁኔታዊ ተዉሳከ ግሶች “እንዴት?” የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል።
xlvi
ቀቤንኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት
1
ዐመተ 2
ነዑ ተስ እኛ ነድደ ስ ሰንደል
ነተሩተ ስ የበር መቀርቀሪያ ነዘሩ ስ ቃል መግባት
ነቤ መሲችቹተ ስ ገባሎ ነፈተ ስ ጥድፊያ
ነብሴተ ስ ነብስ ነጠለ ስ ነጠላ
ነስሲዮዕ ተስ አሳደገ ነሻኣጢሾዕ ግ አነቃቃ
ነቆዕ ግ ኮራ ነጵጲዮዕ ግ አደገ
ነዳመተ ስ መፀፀት
ኑ
ኑኒቹ ስ ቁላ ኑባኣቹ ስ አሮጌ
ኒ
ኒገ ስ 1) ጅማት 2) የደም ስር ኒከ ስ የጋብቻ ቃል ኪዳን
ኒጋኣራ ስ ደደሆ ኒጃሰ ስ የወር አበባ
ኒጃሰ 10
ና
ናኣኑተ ስ ሹሩባ ናጅጆዕ ተስ አደነቀ
ናሀሴተ ስ ነሀሴ
ኖ
ኖምኖሙ ቅ ወጠጤ ኖኩተ ስ እልህ
መ ተግ ምን መረተ ስ ዘንዶ
መዕሲዮዕ ስ ወሰደ መረርሲጩ ግ ማዘን
መዕሊቶ ስ 1) ፀነሰች 2) ሌላ ቦታ መሪቻሙ 1) ቅ ቆለጣም 2) ስ
ሄደች ሀፍረተ ገላ
መዕላንችቹ ስ 1) አጋሰስ 2) መራኣቲተ ስ ምራት
የጭነት ፈረስ መርቴሉተ ስ መዶሻ
መዕዲለ ስ ዎፍራም መርዱፈ ስ የወንዶች ልብስ
መንኑ ሀለቅቆረ ቅ ሰው ሰራሽ መሰነ ስ ብሳና
መንኒዪ ተግ የወንድ ዘር ፈሳሽ መሰላኣለ ስ መሰላል
መንና2 ስ ሰው መሰከሮመ ስ መስከረም
መንና1 ስ ሰው መሱለተ ስ ራእይ
መንዘራተ ስ መነፅር መሲሱ ተግ ማኣመካኛት
መንችቹዒሱ ቅ ሰውየው መስሰቱ ስ መጠየፍ
መንችቹተ ስ ሚስት መስሲሱ ስ ማሳበብ
መኖመተ ቅ ስብዕና መስችቹ ስ ጠላት
መተ መስ ከ--ጋር መለዕሊሞ ስ 1) መገጣጠሚያ 2)
መተኣተ ስ ሙስና ልዩነት
መተዓተ ስ ጉዞ መለተ ስ ምግል
መቱ ስ አንድ መለቡ ስ ማር
መቱ መቱ ቅ አንድንድ መለሎዕ ግ 1) መረጠ 2) ለየ
መቱጌኤሱ ተግ ጥቂት መላተ ዐፍሺዮዕ ስ 1) ምልክት
መቲቅቂ ስ አንደኛ አደረገ 2) ፈረመ
መታኣተ ተግ ምናልባት መላቲሽሾዕ ግ አመላከተ
መቴኤመ ስ ብቸኛ መልተተ ቅ መንታ
መቶ መቶረ ተግ አንድንድ ጊዜ መገንቤኤሱተ ስ ለአራስ ጥየቃ
መቶረ ተስ አንድ ጊዜ የሚወሰድ ምግብ
13 ሙሳፊሬ
በጨራተ ስ ቃቁቻ
ቡ
ቡኡⶄዕ ግ ሳለ ቡሉቡኡላ ስ ድርቅ
ቡዑቡ ተስ መቃጠል ቡሉኩተ ስ ቡሉኮ
ቡዑጡተ ስ ወላጅ አልባ ቡልሉ ስ የፀጉር ድርቀት
ቡዕረ ስ ዋና ቡካለ ስ ብጉር
ቡዕራኣቲቹ 1) ስ ተወርዋሪ ኮከብ ቡኬሲዮዕ ስ አቦካ
2) ቅ በጣም ቆንጆ ቡኡኮዕ ስ በሰበሰ
ቡዕጣኣረ ስ 1/ 8 ኛ ቡቁተ ስ ምንጭ
ቡነተ ስ የቡና ተክል ቡቅቂ ዐስሲዮዕ ግ አበራ
ቡቱሁ ቅ መንቀል ቡኡደ ስ ቀንድ
ቡቱኮዕ ተስ ነቀለ ቡዱስከ ስ ሊጥ ማዞሪያ ቅል
ቡኡቴ ዐመተ ስ እፉኝት ቡኡዲ ለሉ ቅ የቀንድ ከብት
ቡኡሩ 1) ስ ቅቤ 2) ግ መቀባት ቡጡተ ስ የሙት ልጅ
ቡርቱካነ ስ ብርቱካን ቡጣኣራ ቅ ንዑስ (አንድ ስምንተኛ)
ቡርሪ ዪዮዕ ግ በረረ ቡሸ ተግ መልከ ጥፉ
ቡኡሮዕ ስ ቀባ ቡኡሹ ስ ንፍሮ
ቡቡ ስ 1) መንደድ 2) መናደድ ቡኡሾዕ ተግ ነፋ
ቡቡቁ ተግ መበስበስ/ እንሰት ቡጀ ስ ቅስም
ቡቦዕ ተግ 1) ተቃጠለ 2) ነደደ ቡችቸ ስ አፈር
ቡኡሰናተ ስ ሳንባምች ቡኡጴ ሆመለ ቅ የእንቁላል ቅርፊት
ቡሰዳ ስ እምስ ቡኡጴሶዕ ተግ እንቁላል ጣለች
ቡሱንቡሾዕ ተግ በሰበሰ ቡኡጵጳ ስ እንቁላል
ቡሳዉተ ስ የሜዳ ፍየል
ቢ
ቢዕረቲ ስ ጠመንጃ ቢተሪ ግ ጋብቻ
ቢኢንከሲ ስ በስርዓቱ ቢታይተ ስ ጡንቻ
ቢተተ ተስ ጠብ ቢኢረ ስ የእጅ ጉድጓድ
ቢረቲ ዲስጢተ 26
ሱ
ሱዑመሞዕ ግ ተመረዘ ሱኡረተ ስ ምስል
ሱዑመኛ ዎርራ ተግ መርዘኛ እባብ ሱሪተ ስ ሱሪ
ሱዕመ 1) ስ ስም 2) ቅ ዝና ሱቢተ ስ ጠዋት
ሱዕመ ቤኤሱ ግ ስም ማጥፋት ሱቤ ሰላቲ ስ የጠዋት ሰላት
ሱዕሚ ሰችቺሳ ተግ የስም ገላጭ ሱኡለተ ቅ ጭንቅ
ሱዕረተ ስ ጓል ሱሉሙተ ስ ጊደር
ሱነተ ቅ ጭማሪ ሱገ ስ ስንጥር
ሱንቂዮዕ ግ ሳመ ሱኩኡቱ ስ ዝግታ
ሱመ ፉሽሹ ግ ስም ማውጣት ሱዋኣከ ስ የጥርስ መፋቂያ ብሩሽ
ሱሙኒተ ስ ሃያ አምስት ሳንቲም ሱችቾዕ ግ ሰቀለ
ሱምሚ ስ መርዝ
ሲ
ሲናንቁረ ስ ከእበት የተስራ ዱቄት ሲሲቡ ግ ማፍተልተል
ማስቀመጫ ሲሊንሰ ስ የቆላ ቁስል
ሲናቁሪ ስ በእበት የተሰራ ገበቴ ሲሊንሱ ግ ማሟሸት
ሲንቲራ ስ ፍንጭት ሲሊቀመ ግ ደቃቅ
ሲንሲዕኒተ ቅ ወረት/ ሞቅታ ሲኢጉ ግ ማካፋት
ሲንጠ ስ ተረከዝ ሲኢጉተ ስ ካፊያ
ሲቲረ ስ ሻሽ ሲጠለ ተግ ረጅም ቀጭን
ሲሬ መላኣተ ስ መሰረታዊ ምልክት ሲጃኣረተ ስ ሲጋራ
ሲቢሰ ስ ከቀርከሃ የሚሰራ የእንሰት ሲኢጵጱተ ስ አግብቶ የፈታ ወንድ
መፋቂያ
ሳ
ሳንሰ ስ ለምግብነት የሚውል የዱባ ሳኣቢ ስ ፅድቅ
ቅጠል ሳሲዮነ ስ ቅንቅን
ሳተ ስ ላም ሳኣጢኒተ ስ ሳጥን
ሳሂኒተ ስ ሳህን ሳቻ ስ ሳይዘራ የቀረ ማሳ
ሳቻ 30
ሴ
ሴኤሙ ስ ቀንድ የሌለው የቀንድ ሴብባ ስ አባሎ
ከብት ሴሉ ስ አልኮል
ሴኤሙተ ተግ ቀንድ የሌላት ከብት
ሶ
ሶዕረ ስ ጣሪያ ሶሃ ስ ገብስ
ሶኦተሉተ ስ ብርብራ ሶኦሩ ግ መቀለብ
ሶኦቲተ ስ ወደ ታች የተከደነ ሳር ሶክኮዕ ስ ላከ
ቤት ሶቀማኣንችቹ ስ ተላላኪ
ሶኦመኒ ስ ፆም ሶቀሞዕ ተግ ተላላከ
ሶሙ ግ መጠገን ሶኦዙ ስ 1) ንጋት 2) ጎህ
ሶኦሞ ስ ሞክሼ ሶኦዝዙ ስ 1) ንጋት 2) የሙት
ሶሂዕኑተ ስ መልክት መንፈስ
ላ
ላ መስ -ም--እና ላኣሎንጨ ስ 1) የአረም ዝርያ 2)
ላአገተ ስ ድምፅ እንግዴ ልጅ እምቢ ላላቸው
ላኣሉተ ስ ፍሬ ከብቶች የሚሰጥ
ላኣላሙ ግ ማመንታት ላዋተ ስ ጠራራ
ላኣላዊሽ ተስ አዛዙሮ ላኣፈ ስ ልል/ ደካማ
ላኣጤኒ ሌዑ ግ መቅመስ
ላኣጮዕ ግ ላሰ
ሌ
ሌዑ ተግ ማየት ሌኤሊሱ ግ ማቀናጣት
ሌዒሸተ ተስ አመለካከት ሌኤሎ ሌኤጎ ቅ ማቀማጠል
ሌዓተ ስ የማር ወለላ ሌኤገ ስ ሾላ
ሌዓቀሙ ተግ መተያየት ሌያዉ ስ ስልሳ
ሌዔጠ ቅ ሌጣ ሌኤቃ ስ ብድር
ሌዔጂሱ ተግ ማግራት ሌቄኤሱ ተግ ማበደር
ሌዕዮዕ ግ አየ ሌቄኤጪዮዕ ግ ተበደረ
ሌንቄኤቁተ ስ እንቅስቃሴ ሌቄጭጩ ስ መበደር
ሌንቄኤቂዪዮዕ ተግ ተንቀሳቀሰ ሌው ስ ስድስት
ሌንቄቂዮዕ ግ ተወዛውዘ ሌጨ ስ ጨቅላ
ሌማ ስ ቀርከሃ
ሎ
ሎኦሜተ ስ ሎሚ ሎክከተ ስ 1) እግር 2) እግርጌ
ሎቦበተ ስ መልመጃ ሎክካን ከጅጆዕ ተግ በእግር ረገጠ
ሎቦብሱ ተግ ማላመድ ሎቅሎቅ ዩ ተግ ማቅለሽለሽ
ሎቦኦቦዕ ግ ሞከረ ሎቆመ ተግ ልክስክስ
ሎሎሱተ ስ ማነቆ ሎኦዲ ዩ ቅ ቀስ ማለት
ሎኦሎሱተ ስ መነቆ ሎዲዪዮዕ ተግ ቀስ አለ
ሎክከ ሆቢተ ስ ዉስጥ እግር ሎኦዲዪዮዕ ግ ረጋ አለ
ሎክከ ዙሩዕማከተ ስ የእግር ጣቶች ሎጂተ ስ ጤዛ
33 ገለጢዮዕ
ገዓተ ቅ ነገ ገመጮዕ ግ ሳለ
ገዓተ ሆሽሺ ቅ ከነገ ወዲያ ገሚተ1 ስ ምጥ
ገዕሙ ግ መንከስ ገሚተ2 ስ ቁርጠት
ገዕሚሲሱ ተግ ማስነከስ ገምና ቅ ደርባባ
ገዕሚዮዕ ግ ነከሰ ገምበ ዩ ግ መጋጠም
ገዕበለ ዋሊ ተግ ዳር ያዝ ገምበለ ሀቅቀ ስ ጥቁር እንጨት
ገዕበሉ ግ መሰወር ገምበጠ ስ የአህያ ጀርባ ቁሱል
ገዕለ ስ 1) ውርጭ 2) የሸክላ ስባሪ ገምቤኛ ተግ በአጋጣሚ
ገዕዲ ስ ዕጣ ፈንታ ገሞኦጂተ ስ ቆላ
ገኑተ ስ ገና ገሩ ስ መርታት
ገንበለ ዒልሊተ ስ ጥቁር የአይን ገራ ስ ሆድ
ክፍል ገርቢ ስ ምዕራብ
ገንበለ መንዙተ ስ ጥቁር አዝሙድ ገበለ ስ ዳር
ገንበለ ሸረባንችቹተ ቅ ጥቁር ገበሽሹ ግ 1) ማግለል 2) መደበቅ
ሸረሪት ገበችቹ ቅ አጭር
ገንሲኢጩ ግ ማማጥ ገብቦ ስ ወፍ ዘራሽ
ገንሲጭጩ ግ መማጥ/ ለሰው ገብቦጢሾዕ ግ አሳጠረ
ገንሹ ስ ንፍጥ ገቦኦጢሱ ተግ ማሳጠር
ገንሹ ከዕሙ ግ መናፈጥ ገሰረ ስ ጎሽ
ገቱ ግ መቀርቀር ገሰጡ ስ ከመጠን ያለፈ ጥጋብ
ገቲተ ስ ጓሮ ገሲመ ቅ ጧት
ገመርዲነ ስ የእናቶች ቀሚስ ገለዕጡ ግ ማመስገን
ገመጡ ግ መሳል ገለቲ ስ ምስጋና
ገመጥሲሱ ተግ ማስሞረድ ገለጢዮዕ ስ አመሰገነ
ገመጥሲሾዕ ግ አሰላ
ገልበ 34
ቄ
ቄዔሎዕ ተግ አሸነፈ ቄሌቄሌዩ ቅ መቅበዝበዝ
ቄኤዕሩ ተግ መራቅ ቄኤልተዑ ግ 1) መሸነፍ 2)
ቄዕራሸባዕ ተግ ሩቅ መድከም
ቄንደለ ቅ ልበ ደንዳና ቄኤልተዮዕ ግ ደከመ
ቄኤረዑ ግ መለጋት ቄጉ ስ ደም
ቄኤሪሱ ተግ ማራቅ/ መለጋት ቄጉ አጋንቹተ ስ እስስት
ቄኤሪሸተ ተግ ርቀት ቄጉ ፉሽሹ ስ 1) የደም ካሳ
ቄኤርሱ ቅ ማራቅ ማውጣት 2) ማድማት
ቄኤቢተ ስ ቄብ (ለዶሮ) ቄጌዪዮዕ ግ ደማ
ቄኤሰ ስ አይብ ቄኤዩ ስ ማደግ
ቄኤለሙ ተግ መሸነፍ ቄዝዙ ተግ መሸመት
ቄኤሉ ግ ማሸነፍ ቄጥጠ ስ ካርድ
ቄጥጠ 46
ቆ
ቆዑ ስ መቅኔ ቆረኙ ስ ማቀናጀት
ቆኦዕረንዳ ስ ቁራ ቆረጱተ ስ ጥንቃቄ
ቆዕሩ ስ መታጠቅ ቆረጵጱ ግ መጠንቀቅ
ቆዕቡ ተግ መዉጣት/ እንጨት ላይ ቆሩ ግ መመርመር
ቆዕይተዮዕ ተግ ተሸነፈ ቆኦሩ ተግ መጠውለግ
ቆነረሞ ተግ የተደራጀ ቆርቆሩተ ስ ቆርቆሮ
ቆነሩ ተግ ማደራጀት ቆርጠቢተ ስ እክርዳድ
ቆንቋኛ ቅ ስስታም ቆኦርጢሱ ስ መሸረፍ
ቆንተተ ስ ኩክ ቆቡተ ስ ጉሎ
ቆንባኣተ ስ ቆለጥ ቆቡቲ ተግ ሞኝ፤ ለጋ፤ ፈጥኖ ያደገ
ቆንቦረ ስ ቀንበጥ ቆለቢተ ስ የሴት የጉርድ ልብስ
ቆኦንጡተ ስ ቂም ቆለሌተ 1) ስ ክብ 2) ተግ
ቆንጨረ ስ የቅቤ ማስቀመጫ ድቡልቡል
ቆንጮኦሮዕ ተግ ተኮማተረ ቆሉ ስ መመከት
ቆተ ሙኡሚ ቅ ዳገት ጫፍ ቆሉተ ስ ስርጥ
ቆተተ ስ ተራራ ቆልቆሊዩ ተግ መንቀዥቀዥ
ቆኦቲ1 ስ ስልጣን ቆኦልቆዱ ተግ ነጎድጓድ
ቆኦቲ2 ተግ አቅም ቆኮዕ ግ ተሻለ
ቆመረ ተስ ጥብቅ ቆኦቀ ስ ማየት የተሳነው
ቆመርሲዮዕ ተስ አጠበቀ ቆኦቀነተ ስ በረሮ
ቆመዱተ ስ ቋንጣ ቆኦቂሱ ተግ ማሳወር
ቆኦሙ ተግ መጨቆን ቆኦቂሌ ስ ቆቅ
ቆምመረ ግ 1) ጠንካራ 2) ጎበዝ ቆቄኤራተ ስ እንጥል
ቆምመሪሲዮዕ ቅ አጠናከረ ቆቆባኣተ ስ ጠጠር
ቆምመሮዕ ተግ ጠነከረ ቆቆሰ ስ ደረቅ የእንሰት ቅጠል
ቆምቦኦረ ስ እንቡጥ ቆደሚ ስ ተበዳ/ ተበጂ
ቆሂሰሙ ተግ መሻሻል ቆደቀሙ ስ መባዳት
ቆኦረ ቅ የጠወለገ ቆፈሞዕ ግ ተደናቀፈ
ቆኦረሱ ስ የእንቦሳ እበት ቆፈፈሩ ተግ መቆርፈድ
47 ደጉጆዕ
ቆጠ ስ ቆጥ ቆጪተ ስ ጉሊት
ቆኦጠ1 ቅ ቀበጥ ቆጫ ስ ኤሊ
ቆኦጠ2 ቅ ኩራተኛ፤ ቀብራራ ቆጭ ቆጨ ስ በወተት ውስጥ ረግቶ
ቆኦጡ ቅ 1) መንቀባረር 2) ቀበጥ የማይሟሟ ነገር
ቆጅጆዕ ቅ የገብረ ስጋ ግንኙነት ቆኚተ ስ ዎገል
ፈፀመ ቆኦኚተ ስ ወገል
ፊጭጪ ዩ ተግ ፉት ማድረግ
ፋ
ፋኣና ስ ፏፏቴ ፋኣሩ1 ስ መፍላት
ፋኣንጋ ስ ሌባ ፋኣሩ2 ተግ መንተክተክ
ፋኣንቹተ ስ ሽሬ ፋኣርሱ ግ ማፍላት
ፋኖሰ ስ ፋኑስ ፋኣርሹ ስ ፈረስ
ፋኣኖስ ስ ፋኖስ ፋይደተ ስ ጥቅም
ፋኣረተ 1) ስ ተስፋ 2) ተግ ፋኣፉዱ ቅ መቆፈር
ዘለቄታ
ፌ
ፌዕሌውተ ስ ፍየል ፌኤሽሾዕ ግ አስቀረ
ፌኤነ ስ ጋት ፌኤጩ ተግ ማስቀረት
ፌንጠ ስ ፌንጠ
ፎ
ፎኦዕሉ ቅ መማጥ/ ለከብት ፎኦላጪዮዕ ግ አረፈ
ፎኦንቆለ ስ ተቃራኒ ፎኦሎጪሱ ግ ማሳረፍ
ፎንቆልቸ ስ ማንሻ ፎያቲ ግ እረፍት
ፎኦንቆልቸ ስ ጭድ ማገላበጫ ፎኦቀተ ስ ዳሌ
ፎንጡ ግ ማነስ ፎኦቃተ ቅ በሓላ
ፎንጢሱ ተግ ማሳነስ ፎኦዱ ስ በእንጨት ላይ የሚፈጠር
ፎኦንጢዮዕ ተግ ቀነሰ ጉድጓድ
ፎኦረነተ ስ ትኩሳት ፎኦጢኑተ ስ የእህል ስጦታ
ፎኦሊ ስ ትንፋሽ ፎኦጣ ስ ፎጣ
ፎኦሊ ፉሽሹ 1) ግ መተንፈሰ 2) ፎጭ ፎጨ ስ ከቆጮ ውስጥ
ስ ማረፍ የሚወጣ ቆሻሻ
ፎጭ ፎጨ 58
ጣ
ጣኣንሰሱ ግ ማባበል ጣኣጠረ ስ ቆጮ ሲጨመቅ የሚወጣ
ጣኣንሱ ግ ማታለል ፈሳሽ
ጣኣንቁረ ስ ከርስ ጣኣጡ ግ መጠቅለል
ጣኣረ ግ ንፁህ ጣጦሱ ግ ማለቅለቅ
ጣኣለሉ ስ መምረግ ጣኣጮዕ1 ስ 1) ጠቀለለ 2)
ጣኣዉለ ስ ጣዉላ ጠመጠመ
ጣኣፋ ስ ጤፍ ጣኣጮዕ2 ተግ ጠመዘዘ
ጤ
ጤዐተ ስ ውድ ጤዕሽሸተ ግ ጣእም
ጤዑ ግ 1) መወደድ 2) ጣፋጭ ጤኔተ ቅ ቅድም
ጤዒሙ ቅ ጣፋጭ ጤኤንሳኣሱ ስ ኮሶ የተጠጣ እለት
ጤዕና ስ ዝናብ የሚበላ ምግብ
ጤዕኔችቺ መስ ከ-በፊት ጤኤሙ ስ ኮሶ
ጤዕሌሉ ስ መሐላ ጤኤራቲ ግ ፈሪ
ጤዕየ ቅ ጎደሎ ጤኤሬጭጩ ግ መስጋት
ጤዕየተ ስ ተዳፋት ጤኤርችቹ ስ ፍንጢጣ
ጤዕዪሾዕ ግ ቀነሰ ጤሌሉ ስ ማላ
ጤዕዮዕ ግ 1) ተወደደ (ለዋጋ) 2) ጤኤጆዕ ስ ለመጠ
ጣፈጠ
ጦ
ጦዕጮዕ ስ ፈነዳ ጦኦሎዕ ስ ጠበሰ
ጦንቡ ግ መለጠፍ ጦጉ ቅ ጨው የሌለው
ጦንቁተ ስ መበያ የሌለው ምግብ ጦኦቀኘዲ ቅ ወጠጤ/ ለሰው
ጦረዱ ግ መርገም ጦኦፎ ቅ ፈጀ
ጦቦለ ቅ በጊዜ ጦኦፎዕ ግ ጨረሰ
ጦኦለቱተ ስ ጥብስ ጦጢሱ ተግ ማፈንዳት/ ማስጮህ
ጦኦሉ ግ መጥበስ ጦጦናአተ ስ የእሳት ፍንጣሪ
61 ሺረኘ
ሽክከ ስ ወጥመድ
ሾ
ሾንቡ ስ ሳንባ ሾሉ ስ ለብ ለብ ማድረግ
ሾኦንኮረ ስ ሸንኮር ዐገዳ ሾኦሉ ስ አራት
ሾኦቲተ ስ ፖፖ ሾኦሊቅቂ ስ አራተኛ
ሾምቦኦቁተ ስ ሸበቆ ሾክከ2 ቅ ጠማማ
ሾኦሮጠጡ ግ ጥሬና ብስል አንድ ላይ ሾክከ1 ቅ ጎባጣ
መልቀም ሾሸ ስ ልል
ሾለ ዩ ስ መዝናናት ሾሺሾዕ ስ አላላ
63 ጄኤዛዒ
ቹራኣንቹሬ ስ ዡዋዡዌ
ቺ
ቺዕፒነ ስ የእንሰት ቅጠል አገዳ
ቼ
ቼንቺተ ስ ሃምሳ ሳንቲም ቼኤፉ ግ መለፍለፍ
ጪ
ጪዒዎ ቦክኩ ተግ የወፍ ጎጅጆ ጪኢሩ ግ ማቆጥቆጥ
ጪዕመስሲዮዕ ስ ሰበሰበ ጪራኮቲተ ስ ጤናዳም
ጪዕሊተ ስ ቂጥ ጪቤተ ስ ቅጫም
ጪዕቂ ዲስጢተ ስ ሸክላ ድስጥ ጪልመ ስ ጨለማ
ጪዕችቹ ስ ጥሩ ገድ ጪኢኩተ ስ በገብስ የሚሰራ ባህላዊ
ጪኑ1 ስ ሰገራ ምግብ
ጪኑ2 ስ ዝገት/ ለብረት ጪኢቂሱ ስ ማረጋገጥ
ጪሚ ዐስሲዮዕ ስ 1) ቆለለ 2) ጪቃ ስ ጭቃ
ከመረ ጪዉተ ስ ወፍ
ጪረሞሀ ቅ ምንጥር ጪፈለቁ ግ መጨፍለቅ
ጪሩ ግ መጋጥ ጪችቺ ሀቅቀ ስ ጨጮ
ጫ
ጫአንቡሌተ ስ ቲማቲም ጫቲ ዒሰ ተስ ልጅቷ
ጫንቁለ ስ ጮር ጫኣቤተ ስ እንጀራ
ጫኣንፉሩ ግ መቧጨር ጫኣፈ ስ ቅርንጫፍ
ጫኣተ ስ ጫት ጫኣፉራ ስ ጭረት
ጬ
ጬኤሩ ተግ ኮስማና ጬፊቱተ ስ ቁርጥ ስጋ በቅቤ ጠቅሶ
ጬፈንሱ ተግ መነካከር መብላት
ጮ
ጮኦሙ ስ መስባት ጮርቅቂተ ተስ አለንጋ
ጮማ ስ 1) ስብ 2) ጮማ ጮኦሮቀ ስ ረግረግ/ የቦካ አፈር
ጮምቡ ስ የቡና አተላ ጮኦባሩ ስ ክትፎ
ጮኦምቢሱ ተግ ሁለተኛ ቡና ጮልፎኦፉ ተግ ጎታታ
ማፍላት ጮሎንገ ግ እንጥፍጣፊ
ጮኦረ ስ ልቅምቅሞሽ ጮቆርሰ ስ ሰርዶ
ጮኦርቀ ተግ ለጋ እሸት ጮቆሉ ተግ መጨለፍ
ጮጵ ዐስሱ 66
ፓፓዬ ስ ፓፓያ
a
ጊሲሳ/ ግስ ዓሲዮዕ / ሰጠ
ገጊነቱ ሰሲቅቂ መደቢተ (ዒሱ) ባለቤት ሶስተኛ መደብ (እሱ)
- ዓሲዮዔ - ሰጠኝ
- ዓሲዮሀ - ሰጠህ
- ዓሲዮሄ - ሰጠሸ
- ዓስሲዮኪዕነ - ሰጠሆት
- ዓስሲዮሲ - ሰጠው
- ዓስሲዮሴ - ሰጣት
- ዓስሲዮዕነ - ሰጠን
- ዓሰሲቴንተስ - ሰጣችሁት
- ዓስሲዬሂዕነ - ሰጣችሁ (ብዙ)
- ዓስሲዬሂዕነ - ሰጧቸው (አክብሮት)
ጊስሳ፡- ዓስሲዮዕ / ሰጠ
ገጊነቱ ሰሲቅቂ መደቢተ (ዒሱ) ባለቤት ሶስተኛ መደብ (እሱ)
- ዓስሲቶዕ - ሰጠችኝ
- ዓስሲቶሄ - ሰጠችህ
- ዓስሲቶሄ - ሰጠችሽ
- ዓስሲቶሂዕነ - ሰጣችዎት
- ዓስሲቶሴ - ሰጠቻት
- ዓስሲቶሲ - ሰጠችው
- ዓስሲቶዕነ - ሰጠችን
- ዓስሲቶሂዕነ - ሰጠቻችሁ(ብዙ)
- ዓስሲቶሂዕነ - ሰጠቻችሁ(አክብሮት)
ገስሳ/ግስ፡- ዓዒዮዕ / ወሰደ
- ዓዒቶዔ - ወሰደችብኚ
- ዓዒቶሄ - ወሰደችህ
- ዓዒቶሄ - ወሰደችሽ
- ዓዒቶሂዕነ - ወሰደችሆት
- ዓዒቶሴ - ወሰደቻት
- ዓዒቶሲ - ወሰደችው
- ዓዒቶዕነ - ወሰደችን
- ዓዒቶሂዕነ - ወሰደቻችሁ
- ዓዒቶሂዕነ - ወሰደቻችው(ብዙ)
- ዓዒቶሂዕነ - ወሰደቻችሁ(አክብሮት)
ጊስሳ/ግስ ዓሲዮዕ / ሰጠ
ገጊነቱ መቲቅቂ መደቢተ(ነዑ) ባለቤት አንደኛ መደብ (አኛ)
ዓሲኖንከ ሰጠንህ
ዓሲኖንከ ሰጠንሽ
f
ዓሰሲኖንኪዕነ ስጠንዎት
ዓስሲኖንሲ ሰጠነው
ዓስሲኖንሴ ሰጠናት
ዓስሲኖንኪዕነ ሰጠናችሁ
ዓስሲኖንሰ ሰጠናቸው(ብዙ)
ዓስሲኖንሰ ሰጠናቸው (አክብሮት)
ጊስሳ/ግስ ዓዒዮዕ / ወሰደ
ዓዒኖንከ ወሰድንህ
ዓዒኖንከ ወሰድንሽ
ዓዒኖንኪዕነ ወሰድንዎት
ዓዒኖንሲ ወሰድነው
ዓዒኖንሴ ወሰድናት
ዓዒኖንሰ ወሰድናቸው (ብዙ)
ዓዒኖንኪዕነ ወሰድናቸው (አክብሮት)
ጊስሳ/ግስ ፡- ዓሰሲዮዕ/ ሰጠ
ገጊነቱ፡- ለሚቅቂ መደቢተ (ዐዕኑ) ባለቤት ሁለተኛ መደብ(እናንተ)
ዓቴንተዔ ሰጣችሁኝ
ዓቴንተሲ ሰጣችሁት
ዓቴንተሴ ሰጣችኋት
ዓቴንተዕነ ሰጣችሁን
ዓሲቴንተሰ ሰጣችኋቸው (ብዙ)
ዓሲቴንተሰ ሰጣችኋቸው (አክብሮት)
ጊስሳ/ግስ፡- ዓዕዮዕ / ወሰደ
ዓዒቶንተዕ ወሰዳችሁኝ
ዓዒቴንተሰ ወሰዳችኋት
ዓዒቴንታኣነ ወሰዳችሁን
ዓዒቴንታሰ ወሰዳችኋቸው (ብዙ)
ዓዒቴንታሰ ወሰዳችኋቸው (አክብሮት)
g
ጊስሳ/ግስ ፡- ዓሲዮዕ/ ሰጠ
ገጊነቱ ሰሲቅቂ መደቢተ (ዒስሰ) ባለቤት ሶስተኛ መደብ (እነርሱ)
ዓሲዮዔ ሰጡኝ
ዓሲቶሄ ሰጡህ
ዓሲቶሄ ሰጡሽ
ዓሲቶሂዕነ ሰጠሆት
ዓሲቶሲ ሰጡት
ዓሲቶሴ ሰጧት
ዓሲቶዕነ ሰጡን
ዓሲቶሂዕነ ሰጡዋችሁ
ዓሲቶሰ ሰጡዋቸው (ብዙ)
ዓሲቶሰ ሰጡዋቸው (አክብሮት)
ጊስሳ/ግስ ፡- ዓዒዮዕ / ወሰደ
ገጊነቱ ሰሲቅቂ መደቢተ ዐብቢኚ (ዒሰሳ) ባለቤት ሶስተኛ መደብ አክብሮት (እሳቸው)
ዓዒቶዔ ወሰዱኝ
ዓዒቶሄ ወሰዱህ
ዓዒቶሀሄ ወሰዱሽ
ዓዒቶሂዕነ ወሰድዎት
ዓዒቶሲ ወሰዱት
ዓዒቶሴ ወሰዱዋት
ዓዒቶዕነ ወሰዱን
ዓዒቶሂዕነ ወሰዱዋቸሁ
ዓዒቶሂዕነ ወሰዱዋችሁ (ብዙ)
ዓዒቶሂዕነ ወሰዱዋችው (አክብሮት)
የሶስተኛ መደብ አክብሮት ከሶስተኛ መደብ ብዙ ቁጥር ጋር እርባታው አንድ ነው ለዚህም በሶስተኛ
መደብ ብዙ ቁጥር የቀረበውን በዚህ ስር ከተዘረዘረው ጋር በማነጻጸር ይመልከቱ
ጊስሳ/ግስ ፡- ዓሲዮዕ/ ሰጠ
ዓሴመዔ ሰጡኝ
ዓሴመሄ ሰጡሽ
ዓሴመሂዕነ ሰጡዎት
ዓሴመሲ ሰጡት
ዓሴመሴ ሰጧት
ዓሴመዕነ ሰጡን
ዓሴመሂዕነ ሰጡዋችሁ
ዓሴመሰ ሰጡዋቸው(ብዙ)
ዓሴመሰ ሰጡዋቸው(አክብሮት)
h
ጊስሳ ግስ
ዓዒዮዕ ወሰደ
ዓዓንኬ እወስድሀለሁ
ዓዓንከ እወስድሻለሁ
ዓዓንኪዕነ እወስድዎታለሁ
ዓዓንሲ እወስደዋለሁ
ዓዓንሴ እወስዳታለዉ
ዓዓንኪዕነ እወስዳችኋለሁ
ዓዓንሳ እወስዳቸዋለሁ (ብዙ)
ዓዓንሳ እወስዳቸዋለሁ (አክብሮት)
i
መሲዮዕ ወሰደ
መሲታንተዔ ትወስደኛለህ
መሲታንቲሲ ትወስደዋለህ
መሲታንቲሴ ትወስዳታለህ
መሲታንቲዕነ ትወስደናለህ
መሲታንቲሰ ትወስዳቸዋለህ(ብዙ)
መሲታንቲሳ ትወስዳቸዋለህ (አክብሮት)
ገጊነቱ ለሚቅቂ መደቢተ (ዐቲ)
ባለቤት ሁለተኛ መደብ (አንቺ)
ዓሲዮዕ ሰጠ
ዓሲታንተዔ ትሰጭኛለሽ
ዓሲታንቲሲ ትሰጭዋለሽ
ዓሲታንቲሴ ትሰጫታለሽ
ዓሲታንቲዕነ ትሰጭናለሽ
ዓሲታንቲሳ ትሰጫቸዋለሽ (ብዙ)
ዓሲታንቲሳ ትሰጫቸዋለሽ (አክብሮት)
መሲዮዕ ወሰደ
መሲታንተዔ ትወስጅኛለሽ
መሲታዓቲሲ ትወስጅዋለሽ
መሲታንቲሴ ትወሰጃታለሽ
መሲታንቲዕነ ትወስጅናለሽ
መሲታሲታንቲሰ ትወሰጃቸዋለሽ (ብዙ)
መሲታንቲሰ ትወሰጃቸዋለሽ (አክብሮት)
j
መሲዮዕ ወሰደ
መስሲታዔ ይወስዱኛል
መሴነሂዕነ ይወሰዱዎታል
መሴኑሲ ይወሰዱታል
መሴኑሴ ይወስዷታል
መሴዔኑዕነ ይወሰዱናል
መሴኑሰ ይወሰዱዋቸዋል (ብዙ)
መሴኑሰ ይወስዱዋቸዋል (አክብሮት)
ዓዒዮዕ ወሰደ
ዓዓነዔ ይወስደኛል
ዓዓነሄ ይወሰድሀል
ዓዓነሄ ይወስድሻል
ዓዓነሂዕነ ይወሰድዎታል
ዓዓኑሲ ይወሰደዋል
ዓዓኑሴ ይወስዳታል
ዓዓኑዕነ ይወስደናል
ዓዓነሂዕነ ይወስዳችኋል
ዓዓኑሰ ይወስዳቸዋል(ብዙ)
ዓዓኑሰ ይወስዳቸዋል (አክብሮት)
k
መሲዮዕ ወሰደ
መሲታዔ ትወስደኛለች
መሲታሄ ትወስድሀለች
መሲታሄ ትወስድሻለች
መሲታሂዕነ ትወስድዎታለች
መሲታሲ ትወስደዋለች
መሲታሴ ትወስዳታለች
መሲታዕነ ትወስደናለች
መሲታሂዕነ ትወስዳችኋለች
መሲታሰ ትወስዳቸዋለች (ብዙ)
መሲታሰ ትወስዳቸዋለች (አክብሮት)
መሲዮዕ ወሰደ
መሰናንከ እንወሰድሀለን
መሲናንከ እንወስድሻለን
መሰናንኪዕነ እንወስድዎታለን
መሲናንሲ እንወስደዋለን
መሲናንኪዕነ እንወስዲታለን
መሲናንኪዕነ እንወስዳችኋለን (አክብሮት)
መሲናንሰ እንወስዳቸዋለን (ብዙ)
መሲናንሰ እንወስዳቸዋለን (አክብሮት)
መሲዮዕ ወሰደ
መሲቴነንተዔ ትወሰዱኛላችሁ
መሲቴነንተሲ ትወስዱታላችሁ
መሲቴነንተሴ ትወስዱዋታላችሁ
መሲቴንተዕነ ትወሰዱናላችሁ
መሲናነንተሴ ትወስዱዋቸዋላችሁ (ብዙ)
መሲቴነንተሰ ትወሰዱዋቸዋላችሁ (አክብሮት)
ገጊነቱ ሰሲቅቂ መደቢተ ዐብቢኚ (ዒስሳ) ባለቤት ሶሰተኛ መደብ አክብሮት (እሳቸዉ)
መሲዮዕ ወሰደ
መሲታዓ ይወሰዱኛል
መሲታሀ ይወስዱሀል
መሲታሀ ይወስዱሻል
መሲታሂዕነ ይወስዱዎታል
መሲታሲ ይወሰዱታል
መሲታሴ ይወስዷታል
መሲታዕነ ይወሰዱናል
መሲታሂዕነ ይወሰዷችኋል
መሲታሂዕነ ይወስዱዋቸዋል (ብዙ)
መሲታሂዕነ ይወስዱዋቸዋል (አክብረት)
ከላይ እንደተገለፀዉ ለአክብሮት ያለዉ የግስ እርባታ ልክ እንደ ሶስተኛዉ መደብ ብዙ ቁጥር ነዉ፡፡
የሚከተሉትን እርባታዎች በብዙ ቁጥር ካለዉ ጋር በንፅፅር ይመልከቱ፡፡
ጊስሳ ግስ
ዓሲዮዕ ሰጠ
ዓሴነዕ ይሰጡኛል
ዓሲታሄ ይሰጡሀል
ዓሲታሄ ይሰጡሻል
ዓሲታሂዕነ ይሰጠዎታል
ዓሲታሲ ይሰጡታል
ዓሲታሴ ይሰጧታል
ዓሲታዕነ ይሰጡናል
ዓሲታሂዕነ ይሰጡዋችኋል
ዓሲታሂዕነ ይሰጡዋቸዋል (ብዙ)
ዓሲታሂዕነ ይሰጡዋቸዋል (አክብሮት)
ዓሲዮዕ ሰጠ
ዓሲቶንተዔ ሰጠሸኝ
ዐሲቶንቲሲ ሰጠሸዉ
ዓሲትንቲሴ ሰጠሻት
ዓሲቶንቲዕነ ሰጠሸን
ዓሲቶንቲሳ ሰጠሸቸዉ (ብዙ)
ዓሲቶንቲሰ ሰጠሸቸዉ (አክብሮት)
መሲዮዕ ወሰደ
መሲቶንቱዔ ወሰድሽኝ
መሲቶንቲሲ ወሰድሽዉ
መሲቶንቲሴ ወሰድሻት
መሲቶንቲዕሰ ወሰድሸት
መሲቶንቲሰ ወሰድሻቸዉ (ብዙ)
መሲታንቲሰ ወሰድካቸዉ (አክብሮት)
ገጊነቱ ለሚቅቂ መደቢተ ዐብቢኚ (ዐዕኑ) ባለቤት ሁለተኛ መደብ አክብሮት (እርሰዎ/አንቱ)
ዓሴመዔ ሰጡኝ
ዓሴመሲ ሰጡት
ዓሴመሴ ሰጧት
ዓሴመዕነ ሰጡን
ዓሴመሰ ሰጡዋቸዉ (ብዙ)
ዓሴመሰ ሰጡዋቸዉ (አክብሮት)
o
ገጊነቱ ሰሲቅቂ መደቢተ ዐብቢኚ (ዒስሰ) ባለቤት ሶስተኛ መደብ አክብሮት (እሳቸዉ)
ጊስሳ: መሲዮዕ ግስ: ወሰደ
መሲቷዔ ወሰዱኝ
መሲቶሀ ወሰዱህ
መሲቶሀ ወሰዱሽ
መሲቶሂዕነ ወሰዱዎት
መሲቶሲ ወሰዱት
መሲቶሂዕነ ወሰዱዋት
መሲቶዕነ ወሰዱን
መሲቶሂዕነ ወሰዱዋችሁ
መሲቶሰ ወሰዱዋቸዉ (ብዙ)
መሲቶሰ ወሰዱዋቸዉ (አክብሮት)
የሶስተኛ መደብ አክብሮት በሶስተኛ መደብ ብዙ ቁጥር የቀረበዉን በዚህ ስር ከተዘረዘረዉ ጋር
በማነፃፀር ይመልክቱ፡፡
ጊስሳ: ዓሲዮዕ ግስ: ሰጠ
ዓሴመዔ ሰጡኝ
ዓሴመሄ ሰጡህ
ዓሴመሄ ሰጡሽ
ዓሴመሂዕነ ሰጡዎት
ጊነቱ ስሲቅቂ መደቢተ ዐብቢኚ (ዒስሰ) ባለቤት ሶስተኛ መደብ አክብሮት (እሳቸዉ)
መስሲዮ ወሰደ
መስሰተዕ ይወስዱኛል
መስሲታሀ ይወሰዱሀል
መስሲታሀ ይወስዱሻል
መስሲታሂዕነ ይወስዱዎታል
መስሲተሲ ይወሰዱታል
መስሲታሰ ይወስዷታል
መስሲታዓነ ይወስዱናል
መስሲተሂዕነ ይወስዷችኋል
ዓዒተሂዕነ ይወስዱዋቸዋል (ብዙ)
ዓዒተሂዕነ ይወስዱዋቸዋል (አክብሮት)
ከላይ አንደተገለፀዉ ለአክብሮት ያለዉ የግስ እርባታ ልክ አንድ ሶስተኛዉ መደብ ብዙ ቁጥር ነዉ፡፡
የሚከተሉትን እርባታዎች በብዙ ቁጥር ሰር ካለዉ ጋር በንፅፅር ይመልከቱ፡፡
ጊስሳ: ዓስሲዮዕ ግስ: ሰጠ
ዓስሲተዕ ይሰጡኛል
ዓስሲተሀ ይሰጡሀል
ዓስሲተሀ ይሰጡሻል
ዓስሲተሂዕነ ይሰጠዎታል
ዓስሲታሲ ይሰጡታል
ዓስሲታሰ ይሰጧታል
ዓስሲታዓነ ይሰጡናል
ዓስሲታሂዕኔ ይሰጡዋችኋል
ዓስሲታሂዕነ ይሰጡዋቸዋል (ብዙ)
ዓስሲተሂዕነ ይሰጡቸዋል (አክብሮት)
w