You are on page 1of 2

አቡነ ጎርጎርዮስትምህርትቤቶችለቡቅርንጫፍ

Abune Gorgorious SchoolsLebu Branch


2012 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መለማመጃ ሁለት ለ 6 ኛ ክፍል
ስም ክፍል ቁጥር
ምንባብ
ቋንቋ
ቋንቋ አፍ ነገር ቃል ማለት፡፡ አፍን ቋንቋ የሠኘው ህዳሪ በማህደር ይሆናል፡፡ የእገሌ አመሉ አይታወቅም ሲሉ ቋንቋው ይላሉ፡፡ የሥራው
መግለጫ ማለት ነው፡፡

ስዋስው መሰላል፣ ዕርከር ከታች ወደ ላይ ከላይ ወደታች መመላለሻ (ደረጃ መውጫና መውረጃ) ማለት ነው፡፡ እሱም ዕሰው ካለው
ከግእዝ አንቀፅ ይወጣል፡፡ የስዋስውን ትምህርት ዘይቤ ለማወቅ ከሥር እስከ ጫፍ እየመላለሱ መማር እንዲገባ ያሳያል፡፡ በዘመናችን ግን
አገባብን ብቻ ስዋስው ይሉታል፡፡

አገባብ የቋንቋ ሥርዓት፣ ደንብ፣ ህግ፣ወሰን እና ደንበር ማለት ነው፡፡

መመሪ 1፡ ከአላይ የቀረበውን ምንባብ መሠረት በማድረግ የሚከተሉትን


ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ እውነት ሥህተት ከሆነ ሐሰት በማለት መልስ ፃፉ፡፡

1. አፍን የቋንቋ ማወጫ መንገድ ነው ማለት እንችላለን፡፡


2. በአሁኑ ጊዜ (ዘመናት) ስዋስውን አገባብን ብቻ በማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡
3. እንደ መሰላል የተጠቀሰው ቋንቋ መሠረት በማድረግ ነው፡፡
4. የሰው አመሉ አይታወቅም ሲሉ ልምድ (ፀባዩ) ለማለት ቸነው፡፡
5. ስዋስው ማለት የቋንቋን ሥርዓት፣ ወሰን እና ህግን የሚያካትት የቋንቋ
ሥርዓታዊ መግለጫ አይደለም፡፡

መመሪያ 2. በ “ሀ” ረድፍ ለቀረቡት ቃላት ተመሳሳይ ፍቻቸውን ከ “ለ”


ባሉት ጋር በማዛመድ መልስ ፃፉ፡፡

“ሀ” “ለ”
1. ታማኝነት ሀ. አረመኔ፣ርህራሄ የሌለው

2. ጨካኝ ለ. አገርሽ፣ተንሰራራ

3. ሥር ሰደደ ሐ. መጤ፣ እንግዳ

4. ባይተዋር መ. ሃቀኝነት፣ግልፅነት

5. ተግዳሮት ሠ. ችግር

ረ. መፍትሔ

መመሪያ 3. ለሚከተሉት ጥቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ሆሄ መርጣችሁ ለመልስ


መስጫ በተዘጋጀ ቦታ ላይ ፃፉ፡፡

1. በቀለ ትናንት መጣ፡፡ የተሰመረበት ተውሳከ ግስ ምንን ያገለግላል?


ሀ. ቦታን ለ. ጊዜን ሐ. ሁኔታን መ. ጠባይን

2. ከሚከተሉት ቃላት እምር አመልካች ምዕላድ ያለው የቱ ነው


ሀ. ሰዎች ለ. ልጁ ሐ. ቤታቸው መ. ልጄ

3. በጣም እርቦኛል ስለዚህ ምሳየን መመገብ አለብኝ፡፡ በባዶ ቦታው ላይ


ተስማሚው ስርዓተ ነጥብ ነው?

ሀ. ፣ ለ. ፤ ሐ. ፡፡ መ. ?

4. ከሚከተሉት አነስታይ ፆታ አመልካች ምዕላድ የያዘው የቱ ነው?


ሀ. ድመት ለ. ድመቲቱ ሐ. ቤቱ መ. ቤታቸው

5. ታዩ ወንድሙ ወደ ት/ቤት ሄደ፡፡ በባዶ ቦታው ተስማሚው መስተፃምር

የቱ ነው?

ሀ. ወይም ለ. ስለዚህ ሐ. ና መ. ግን

6. ዘመድ እስኪሰበሰብ በሚል ሰበብ አስከሬን ማሳደር ጎጂ ልማድ ነው፡፡


የተሰመረበት ቃል አገባባዊ ፍቺ ነው፡፡

ሀ. ችግር ለ. ለቅሶ ሐ. ምክንያት መ. ውጤት

7. “መጣሽ” የሚለው ስንተኛ መደብ ነው?


ሀ. ሁለተኛ መደብ ተባዕት ለ. ሁለተኛ መደብ እንስት

ሐ. ሦስተኛ መደብ ተባዕት መ. ሦስተኛ መደብ እንስት

8. ከሚከተሉት ነጠላ ቁጥር የሆነው የቱ ነው?


ሀ. ላሞች ለ. ሰዎች ሐ. ካህናት መ. ጠረጤዛ

9. ከሚከተሉት በማጥበቅና በማላላት ፍቺ የማይቀየረው የቱ ነው?


ሀ. አዛባ ለ. ገና ሐ. በራ መ. መጣ

10. ከግስ በፊት መጥተው ግስን የሚገልፅ ምንድን ነው?


ሀ. መስተዋድድ ለ. ቅፅል ሐ. ግስ መ. ተውሳከ ግስ

You might also like