You are on page 1of 3

አቤም ዩዝ አካዳሚ

“መማር ለለውጥ”
ስም: 2016 ዓ.ም. አንደኛ ሩብ ዓመት ክፍል _4 ተኛ ቁጥር _________
ቀን: ሙከራ 2 የትምህርት ዓይነት አማርኛ የመምህሩ/ቷ ስም

ያህዮቹ እናት
በአንድ ወቅት በአንድ መንደር ውስጥ አንዲት አሮጊት ሴት በብቸኝነት ትኖር ነበር። እርስዋም ሁለት አህዮች
ነበሯት።አህዮቹ በብዙ መንገድ እሷን ይጠቅሟት ነበር።ይኸውም ለጭነት; ለክራይ; ለአርሻ ስራ ታውላቸው ነበር።በየአለቱ
ጠዋዋት ቁርሷን በልታ ቡናዋን ጠጥታ አህዮቹን ከሚያድሩበት ቤት በመውጣቸት ሳር እንዲበሉና ውሃ እንዲጠጡ ወደ ሜዳ
ትወስዳቸው ነበር።ከእለታት አንድ ቀን አህዮቹን እየነዳች ስትሄድ ከመንገድ ዳር የተቀመጡ ሁለት ጎረምሶች አይተዋት
ሊሰድቧት እና ሊያፌዙባት ፈልገው ደምጻቸውን ከፍ በማድረግ "እንደምን አደሩ የአህዮቹ እናት ? " አሏት።አሮጊቷም ስድብ
መሆኑን ገብቷት በተራዋ " እንደምን አደራችሁ ልጆቼ? " በማለት ስቃባቸው አህዮቿን እየነዳች ሄደች። ጎረምሶቹም
ከአሮጊቷ ባገኙት መልስ አፍረውና አንገታቸውን አቀርቅረው ወደቤታቸው ሄዱ።

I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሠረት ትክክል የሆነውን እውነት ካልሆነ ሐሰት በማለት መልሱ።
1. ጎረምሶቹ በኩራት ወደ ቤታቸው ሄዱ።

2. አሮጊቷ የምትኖረው ከባሏ ጋር ነበር።

3. ጠዋት ጠዋት አህዮቿን ሳር ታበላቸው ነበር።

4. መንገድ ዳር ያገኘቻቸው ሁለት ጎረምሶች ነበሩ።

5……….. አሮጊቷ ጎረምሶቹን ሙልጭ አርጋ ሰድባቸው ነበር።


II. በ " ሀ" ስር የሚገኙትን ቃላት በ"ለ" ስር ከሚገኙት ቃላት በምንባቡ መሠረት በትርጉም ከሚመሳሰሏቸው
ጋር አዛምዱ።

ሀ ለ
1. አቀርቅረው ሀ. ማሾፍ

2. ጎረምሶች ለ. አንገታቸውንደፍተው

3.ማፌዝ ሐ. ጊዜ

4. ወቅት መ. እየመራች

5. ½.….እየነዳች ሠ. ወጣቶች
III. የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንብባችሁ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል በመምረጥ ክፍት ቦታው ላይ ጻፉ።

1. በውስጡ ሁለት እና ከዚያ በላይ ግሶችን የሚይዘው ዐ. ነገር የቱ ነው?

ሀ. ነጠላ ዓረፍተ ነገር ለ. ውስብስብ ዓረፍተ ነገር ሐ.መስተዋድዳዊ ዓረፍተ ነገር መ.ጥያቄያዊ ዓረፍተ ነገር

2. ዛሬ ዝናብ ዘንቦ ነበር ።ስለሆነም ጓሯችን ጭቃበጭቃ ሆነ። በዚህ ዓረፍተ ነገር ውስጥ የተሰመረባት

የመስተዋድድ ዓይነት የቱ ነው?

ሀ. አፍራሽ ለ. አማራጭ ሐ. ምክንያታዊ እና ውጤት መ ሁሉም መልስ ናቸው

3.________ማለት የቃላት ቀጥተኛ ወይም መደበኛ ፍቺ ማለት ነው::

ሀ. ፍካሬያዊ ፍቺ ለ እማሬያዊ ፍቺ ሐ ሰምና ወርቅ መ አውዳዊ ፍቺ

4. ሮቤል ባህሪዉ አይመግጥም እንዳው እንደ እስስት ነው።በዚህ ዐረፍተ ነገር ዉስጥ እስስት የሚለው

ቃል ፍካሬያዊ ፍቺው ምንድነው ?

ሀ. ቀለሟን የምትቀያይር እንስሳ ለ ባህሪውን የሚቀያይር ሰው ሐ ደስተኛ መ ተስፋቢስ

5. መሬት የሚለው ቃል ፍካሬያዊ ትርጒሙ የቱ ነው ?

ሀ. ቻይ ለ. መኖሪያ ቦታ ሐ. ደረቅ መ ሞኝ

IV. የሚከተሉትን ጥገኛ መስተፃምሮች በባዶ ቦታ ላይ አስገቡ ::

እንደ ስለ ከ በ እየ

1. ክረምቱ ገባ ቴኳንዶ ስልጠና እመዛገ በለው ::

2. የእህቴ ልደት ሚከበር ስጦታ ገዛን።

3. መምህርቷ መጣች እያለ ስልኳ ጠራ ።

4. እኔ ጓደኞቼ ጋር በቡድን አጠናሁ::


5……….. መምህራኖች መርከብ ሽርሽር ሄዱ ::

You might also like