You are on page 1of 3

8ኛ

ምንባብ

የራስን ስሜት ማወቅ ማለት በጊዜው ያለንን ስሜት መለየትና በምናልፍባቸው ሁኔታዎች ውስጥ የግል ስሜታችንን መገንዘብ ማለት
ነው፡፡ ይህ ራስን ማወቅ ድክመታችንን እና ብርታታችንንም መለየትንም ያካተተ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ በምናያቸው ነገሮች የሚሰማንን
ስሜት መጠየቅ የሚያስከትለውን ውጤት ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡

በመሆኑም የራሳችንን ሁኔታ እና ስሜቶቻችንን በማጤን እና በመረዳት ለሌሎች የማህበረሰባችን ክፍሎች የሚጠበቅብንን አሻራ
ማሳረፍ ይኖርብናል፡፡ ሰዎች ከእኛ የሚፈልጓቸዉን ነገሮችም መረዳት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

ለሚከተሉት ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክለኛዉን መልስ የያዘዉን ፊደል ምረጡ

1. ከላይ የቀረበው ምንባብ ስንት አንቀፅ አለው


ሀ. አንድ ለ. ሦስት ሐ. ሁለት መ. ሰባት
2. የምንባቡ ርዕስ ምን ሊሆን ይችላል
ሀ. የራስን ስሜት ማወቅ ለ. ራስን ማወቅ ሐ. እውቀት መ. ትምህርት
3. ድርሰቱ በየትኛው የድርሰት አይነት የቀረበ ነው
ሀ. በተራኪ ለ. በገላጭ ሐ. በአመዛዛኝ መ. በስዕላዊ
4. ከምንባቡ መረዳት የምንችለው ምንድ ነው
ሀ. ራስ ወዳድ መሆን ጤናማ እንደሆነ
ለ. ከሌሎች ይልቅ ለራሳችን ቅድሚያ መስጠት እንዳለብን
ሐ. የራስን ስሜት ማወቅ የሌሎችንም ለመረዳት እንደሚያስችል
መ. ለሌሎች ስሜት ግዴለሽ መሆን እንደሚገባ
5. “------ የሚያስከትለውን ውጤት ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡” የተሰመረበት ቃል ፍቺ
ሀ. ማስተዋል ለ. መረዳት ሐ. መገንዘብ መ. ሁሉም
6. የራስን ስሜት ማወቅ ሲባል፡-
ሀ. ጥንካሬን ብቻ መለየት ለ. ደግነትን ብቻ መናገር
ሐ. ጥንካሬንም ደግነትንም መለየት መ. ተናግሮ ማሳመን መቻል
7. የራስን ስሜት መረዳት _________ ን ይጠቅማል
ሀ. ራስን ለ. ህብረተሰብን ሐ. ሌሎችን መ. ሁሉም
8. ------- የሚጠበቅብንን አሻራ ማሳረፍ ይጠበቅብናል
ሀ. ድርሻ ለ. ተፅዕኖ ሐ. ጥፈ መ. ሀ እና ለ
9. ሰዎች ከእኛ የሚፈልጉትን ነገር መረዳት፡-
ሀ. ለእኛም ጠቃሚ ነው ለ. የመረዳት ልክ ያሳያል
ሐ. የሰዎችን መጥፎነት ይገልፅልናል መ. ሁሉም መልስ ናቸው
10. በአጠቃላይ ምንባቡ፤-
ሀ. ከሰዎች ጋር ጥሩ ተግባቦት እንዲኖረን ያደርጋል
ለ. ራሳችንን መረዳት ተገቢ መሆኑን ያስገነዝበናል
ሐ. መልካም ነገሮችንም ለማከናወን ራስን ማወቅ ተገቢ እንደሆነ ይነግረናል
መ. ሁሉም መልስ ናቸው

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛዉን መልስ ምረጡ

1. ስለ አንድ ነገር ብቻ የሚፃፍበት የፅሁፍ ክፍል _________ ይባላል፡፡


ሀ. ዓ.ነገር ለ. ሀረግ ሐ. አንቀፅ መ. ቢጋር
2. በአንቀፅ ውስጥ ጠቅላላ ሀሳቡን የሚይዘው ዓ.ነገር ምን ይባላል

አዘጋጅ፡- መ/ርት፡ ቃላኪዳን


ሀ. ዝርዝር ዓ.ነገር ለ. አንቀፅ ሐ. ሀረግ መ. ሀይለቃል
3. በአረፍተ ነገር ውስጥ ድርጊትን የሚያመለክተው የ ዓ.ነገር ክፍል የቱ ነው
ሀ. ማሰሪያ አንቀፅ ለ. ግስ ሐ. ባለቤት መ. ተሳቢ
4. ሁለት ነገሮችን በማወዳደር የሚፃፍ የድርሰት አይነት የቱ ነው
ሀ. ተራኪ ለ. ገላጭ ሐ. አመዛዛኝ መ. ስዕላዊ
5. “መኪናው ከጂንካ እየመጣ ነው::” ይህ አረፍተ ነገር የተነገረበት ጊዜ _________ ነው
ሀ. ሀላፊ ጊዜ ለ. የአሁን ጊዜ ሐ. የትንቢት ጊዜ መ. ሁሉም
6. _________ ከ አንድ በላይ ቃላት ተቀናጅተው አንድ ትርጉም ወይም ፍቺ የሚሰጡበት ነው
ሀ. ጥምር ቃል ለ. ሀረግ ሐ. ዓ.ነገር መ. አንቀፅ
7. “ጎበዙ ረያን ያጠናል፡፡” በዚህ ዓ.ነገር ውስጥ የስም ገላጭ መሆን የሚችለው ቃል _________ ነው፡፡
ሀ. ረያን ለ. ጎበዙ ሐ. ያጠናል መ. ረያን ጎበዙ
8. ያስመዘገበው ዉጤት በቂ ነው፤ _________ አኩሪ አይደለም፡፡
ሀ. ታዲያስ ለ. ቢሆንም ሐ. እንጂ መ. ከዚያም
9. ከሚከተሉት አንዱ ጥምር ቃል አይደለም፡፡
ሀ. ሽብርቅርቅ ለ. ስነቃል ሐ. አፈጉባኤ መ. ልብወለድ
10. በቋንቋ አጠቃቀሙ በአዕምሯችን ምስልን የሚከስተው የድርሰት አይነት _________ ነው፡፡
ሀ. ተራኪ ድርሰት ለ. ገላጭ ድርሰት ሐ. አከራካሪ ድርሰት መ. ስዕላዊ ድርሰት
11. የልቦለዱን ታሪክ ጊዜና ቦታ የሚገልፀው የልቦለድ አላባ _________ ነው፡፡
ሀ. መቼት ለ. ታሪክ ሐ. ትልም መ. ጭብጥ
12. ከሚከተሉት ውስጥ የአጭር ልቦለድ ባህሪ የሆነው ቱ ነው
ሀ. ነጠላ ውጤት ለ. ጥድፊያ ሐ. ቁጥብነት መ. ሁሉም
13. ደራሲው የሚፈጥራቸው የታሪክ አራማጆች _________ ይባላሉ
ሀ. የእዉን ሰዎች ለ. ገፅባህሪያት ሐ. ድርጊት መ. ሰዎች
14. እርሷ በትምህርት ጉበዝ ነው፡፡ በዚህ ዓ.ነገር ውስጥ ያለው የሠዋሰው ግድፈት _________ ነው፡፡
ሀ. የፆታ አለመስማማት ለ. የቁጥር አለመስማማት
ሐ. የመደብ አለመስማማት መ. ሁሉም
15. ከሚከተሉት አንዱ የዓ.ነገር አካል አይደለም
ሀ. ባለቤት ለ. ስም ሐ. ተሳቢ መ. ማሰሪያ አንቀፅ

ለሚከተሉት ቃላት ትክክለኛዉን ፍቺ ምረጡ

1. በአመዛኙ
ሀ. በሞዛዛው ለ. በአብዛኛው ሐ. በአጋጣሚ መ. ሁሉም
2. ወረርሽኝ
ሀ. ወራሪ ለ. ብዙሀንን የሚያጠቃ ሐ. መከላከያ የሌለው መ. ችግር
3. እፎይታ
ሀ. ድስታ ለ. እረፍት ሐ. ፋታ መ. ሁሉም
4. ዋስትና
ሀ. መተማመኛ ለ. እዳከፋይ ሐ. ተተኪ መ. ሁሉም
5. ቀጣይነት
ሀ. ተከታታይነት ለ. ተያያዥነት ሐ. ልዩነት መ. ሀ እና ለ

ለሚከተሉት ዘይቤያዊ ዓ.ነገሮች ትክክለኛዉን መልስ ምረጡ

1. ልዩነሽ ፀሀይ ነች፡-


ሀ. አነፃፃሪ ለ. ተለዋጭ ሐ. ተምሳሌት መ. አያዎ

አዘጋጅ፡- መ/ርት፡ ቃላኪዳን


2. ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል አለ ጅብ
ሀ. ግነት ለ. ሰዉኛ ሐ. እንቶኔ መ. አያዎ
3. ተነስ! አንተ ድንጋይ አናግረኝ
ሀ. ሰዉኛ ለ. ግነት ሐ. ምፀት መ. እንቶኔ
4. የፊትሽ ጥቁረት እንደ ፀሀይ ያበራል
ሀ. ምፀት ለ. እንቶኔ ሐ. ተምሳሌት መ. አያዎ
5. የልጅቷ እምባ እንደ ጅረት ይፈሳል
ሀ. እንቶኔ ለ. ተለዋጭ ሐ. አነፃፃሪ መ. ተማሳሌት

ለሚከተሉት ቃላት ተቃራኒ ፍቺ ምረጡ

1. ዝንባሌ
ሀ. ችሎታ ለ. አለማወቅ ሐ. አቅም መ. ሁሉም
2. ሸለመ
ሀ. አደላ ለ. ነጠቀ ሐ. ሰጠ መ. አንበሻበሸ
3. ደረመሰ
ሀ. ገነባ ለ. አፈረሰ ሐ. ሰነጣጠቀ መ. በተነ
4. ዘገየ
ሀ. ደረሰ ለ. ቆየ ሐ. አረፈደ መ. ሰነበተ
5. ፋይዳ
ሀ. ጥቅም ለ. ጉዳት ሐ. አገልግሎት መ. ሁሉም

አዘጋጅ፡- መ/ርት፡ ቃላኪዳን

You might also like