You are on page 1of 5

የካ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ፅ/ት ቤት የብሩህ ተስፋ ክላስተር ት/ቤቶች የ 2016 ዓ.

ም አማርኛ ሞዴል ፈተና ለ 6 ኛ ክፍል

ምንባብ

ክቡር ሌተናል ጄኔራል ጂጋማ ኬሎ በቀድሞ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ጅባትና ሜጫ አውራጃ በደንዲ ወረዳ ልዩ ስፍራ ዩብዶ
በተባለ ቦታ ከአባታቸው ከአቶ ኬሎ ገሮ ከእናታቸው ከወ/ሮ ደላንዱ ፋንቱ ጥር 20 ቀን 1913 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ አባታቸው በ 1923
ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩአቸው የነበራቸውን 19 ጋሻ መሬት አለቃና አስተዳዳሪ እንዲሆኑ ተናዘውላቸው ሞቱ።ይህም
የመሬት ውርስ ለአቶ ኬሎ ገሮ ልጆች በህግ ጸንቶ ከወረሱ በኃላ አባታቸው ከመሞታቸው በፊት ከጃጋማ ቀድሞ ለተወለዱትም
ሆኑ በኃላ ለተወለዱት ወላጅ አባታቸው አለቃ አድርገው በእግራቸው ስለተኩዋቸው ከታዳጊ ወጣት ዕድሜያቸው ጀምሮ
የአለቅነት ስራ ጀመሩ፡

በ 1928 ዓ.ም ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ከመውረሯ በፊት ያስተዳድሩ ከነበሩት የአባታቸው መሬት እናትና ወንድማቸው
እንዲያስተዳድሩ ወክለውና አዲስ አበባ ድረስ ተጉዘው በወቅቱ ተፈሪ መኮንን ተብሎ በሚታወቀው ትምህርት ቤት ገቡ።
ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እያሉ የደንዲ ወረዳ ገዥ የመሬት ግብር አልገብርም ብለው ትምህርት ቤት ገብተዋል በማለት
ተከትለዋቸው አዲስ አበባ ከመጡ በኃላ በጠመንጃ አስገድደው አስረው ወደ ትውልድ መንደራቸው መለሷቸው፡፡

በወቅቱ ወጣቱ ኋላ ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ዘመናዊ ትምህርት ደህና ሰንብች ብለው የተጠየቁትን የመንግስት ግብር
ከፍለው እዚያው መኖር ጀመሩ ፡፡ በወቅቱ በነበሩት ገዥዎች በመቆጣጠሩ በተነሳው ጦርነት ምክንያት ዘመናዊ ትምህርቱ
ቢጨናገፍባቸውም አቅራቢያቸው ወደነበረው ቄስ ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እያሉ ሚያዝያ
1928 ዓ.ም ጣሊያን በወረራ አዲስ አበባን ጨምሮ የሸዋ አውራጃና የወረዳ ከተሞችን በመቆጣጠሩ በተነሳው ጦርነት
ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ፡፡ ሌተናል ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ለአገርና ለህዝብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሰሩ አንጋፋ የጦር
ሰው የነበሩ ከመሆናቸውም በላይ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወስጥ የረጅም ጊዜ አገልግሎት አበርክተውና የዕድሜ ባለጸጋ
ሆነው በሞት ተለይተዋል፡፡

ምንጭ፡ ታደለ ቴሌ (2004) ገድለ መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ 1953


ዓ.ም፣ ገጽ 117 ተሻሽሎ የተወሰደ

መመሪያ አንድ :- ከተራ ቁጥር ፩ እስከ ፰ ድረስ የቀረቡት ጥያቄዎች ቀጥሎ በቀረበው ምንባብ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡
ምንባቡን በጥሞና በማንበብ ለጥያቄዎቹ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክል የሆነውን መልስ ምረጥ /ምረጪ፡፡

፩. ጃጋማ አባታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የስንት ዓመት ልጅ እያሉ ነበር?

ሀ. የስምንት ዓመት ልጅ ሐ. የአስራ አምስት ዓመት ልጅ

ለ. የአስር ዓመት ልጅ መ. የአስራ ዘጠኝ ዓመት ልጅ

፪. በምንባቡ መሰረት ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ትክከል ነው፡፡

ሀ. የጃጋማ አባት ሃብት ንብረታቸውን ለጃጋማ ብቻ ነው ያወረሱት፡፡

ለ. ጃጋማ የቄስ ትምህርታቸውን እንጂ ዘመናዊ ትምህርታቸውን አላቋረጡም፡፡

ሐ. የጃጋማ አባት ሃብታቸውን እናትና ወንድማቸው እንዲያስተዳድሩ ተናዘዋል፡፡

መ. ጃጋማ አብዛኛውን ዕድሜያቸውን ወታደር በመሆን ሃገራቸውን አገልግለዋል፡፡

፫. ይህ ምንባብ በየትኛው አጻጻፍ ስልት የቀረበ ነው?

ሀ. በአመዛዛኝ ለ. በስዕላዊ ሐ. በተራኪ መ. በገላጭ

፬. የደንዲ ወረዳ ገዥ ጃጋማን ከአዲስ አበባ ወደ ትውልድ ቦታቸው የመለሷቸው በምን

ምክንያት ነበር?

ሞዴል አምስት Page 1


የካ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ፅ/ት ቤት የብሩህ ተስፋ ክላስተር ት/ቤቶች የ 2016 ዓ.ም አማርኛ ሞዴል ፈተና ለ 6 ኛ ክፍል

ሀ. የመሬት ግብር አልገብርም በማለታቸው ሐ. በአባታቸው አለቃ ሆነው በመመረጣቸው

ለ. አባታቸው ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው መ. ዘመናዊ ትምህርታቸውን በማቋረጣቸው

፭. ጃጋማ የጀመሩትን የቄስ ትምህርት ቤት ያቋረጡት በምን ምክንያት ነው?

ሀ. ወደ ትውልድ ስፍራ በመመለሳቸው ምክንያት ሐ. ወደ ጦር ሜዳ በመሄዳቸው ምክንያት

ለ. በጣልያን ጦርነት ምክንያት መ. ዘመናዊ ትምህርት በመጀመራቸው ምክንያት

፮. በምንባቡ መሰረት ‹‹በጠመንጃ አስገድደው›› የሚለው ሃረግ አውዳዊ ፍቺው ምንድን ነው?

ሀ. ጠመንጃ ሸልመው ሐ. ጥይት እየተኮሱ

ለ. ኃይል ተጠቅመው መ. ወታደር ቀጥረው

፯. በምንባቡ መሰረት ‹‹ቢጨናገፍባቸውም›› የሚለው ቃል አውዳዊ ፍቺው ምንድን ነው?

ሀ. ቢጨልምባቸውም ለ. ቢጠፋባቸውም ሐ. ቢቋረጥባቸውም መ. ባይሳካላቸውም

፰. ጃጋማ ኬሎ አለቃና አስተዳዳሪ የሆኑት በማን ላይ ነው?

ሀ. ከጃጋማ ቀድሞና በኃላ ለተወለዱት ሐ. ከጃጋማ በኃላ ለተወለዱት ብቻ

ለ. ከጃጋማ ቀድሞ ለተወለዱት ብቻ መ. ከጃጋማ ጋር አብረው ለተወለዱት

፱. በምንባቡ መሰረት ፀሐፊው ማሳየት የፈለገው ምንድን ነው?

ሀ. የጃጋማ ኬሎን የውትድርና ህይወት ሐ. የጃጋማ ኬሎን አልበገር ባይነት

ለ. የጃጋማ ኬሎን የልጅነት አለቅነት መ. የጃጋማ ኬሎን የዕድሜ ባለጸግነት

መመሪያ ሁለት ፡- ከተራ ቁጥር ፲ እስከ ፴፭ ድረስ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ለእያንዳንዱ ጥያቄ በአጠያየቁ መሰረት
ከተሰጡት አማራጮች መካከል መልስ የሆነውን ምረጥ/ምረጪ፡፡

፲.ከሚከተሉት አማራጮች ውስጥ የወል ስም ያልሆነው የቱ ነው ?

ሀ. ተራራ ለ. አባይ ሐ. ተማሪ መ. ሀገር

፲፩.አቶ በቀለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ዛሬ አረፉ። በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ ያለው የጊዜ

ተውሳከ ግስ የቱ ነው ?

ሀ. ምክንያት ለ. አረፉ ሐ. በደረባቸው ህመም መ. ዛሬ

፲፪.ከሚከተሉት መካከል ‹‹እንጀራ›› የሚለው ቃል በፉካሬያዊ ፍቹ የገባው በየትኛው አረፍተ


ነገር ውስጥ ነው?
ሀ. እንጀራ ባገኝ ብሎ ነው ከሃገሩ የወጣው፡፡ ሐ. ለእራት የሚሆን በቂ እንጀራ ተጋግሯል፡፡
ለ. እንጀራ ሽጣ ነው ህይወቷን የምትገፋው፡፡ መ. ከዳቦ ይልቅ እንጀራ ብትሰጠኝ ይሻለኛል፡፡
፲፫.ቃላትን እና ሀረጋትን አሳጥሮ ለመፃፍ የሚያገለግል ስርዓት ነጥብ የቱ ነው?

ሀ. ቅንፍ ለ. ሁለት ነጥብ ሐ. አቆልቋይ መ. ቃል አጋኖ

፲፬. እጇን አትቅበሩት ይቁም እንዳገዳ ፣

ሞዴል አምስት Page 2


የካ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ፅ/ት ቤት የብሩህ ተስፋ ክላስተር ት/ቤቶች የ 2016 ዓ.ም አማርኛ ሞዴል ፈተና ለ 6 ኛ ክፍል

ሸኝታበታለች ብዙ ብዙ እንግዳ። ይህ ቃላዊ ግጥም በየትኛው ጊዜ ይከወናል ?

ሀ. በስራ ለ. በሙሾ ሐ. በሰርግ መ. በብዓላት

፲፭. ራሱን ችሎ መቆም የሚችል እና ትርጉም የሚሰጥ አነስተኛ የቋንቋ ክፍል ምን ይባላል?

ሀ. ነፃ ምዕላድ ለ. ሀረግ ሐ. ጥገኛ ምዕላድ መ. አንቀጽ

፲፮. የተዋስኩትን መጽሐፍ በማግስቱ እንድመልስ ጠይቆኝ ነበር ። በሚለው አረፍተ ነገር ውስጥ

የተሰመረበት ቃል የምን ተውሳከ ግስ ነው?

ሀ. የቦታ ለ. የሁኔታ ሐ .የጊዜ መ. የምክኒያት

፲፯. ‹‹ወደ ባህር ዳር ለዕረፍት መቼ ትሄጃለሽ››? የሚለው ጥያቄያዊ አረፍተ ነገር ወደ ሀተታዊ አረፍተ

ነገር ሲቀየር የትኛውን አረፍተ ነገር ይይዛል?

ሀ. ወደ ባህር ዳር ለዕረፍት መቼ እንደምሄድ አውቀሃል ሐ. ወደ ባህር ዳር ለዕረፍት ትሄጃለሽ

ለ. ወደ ባህር ዳር ለዕረፍት መሄድ ይቻላልን መ. ወደ ባህር ዳር ለዕረፍት መሄዴ ነው

፲፰.መሰላል ለሚለው ቃል ፉካርሬያዊ ፍች የሚሆነው የትኛው ነው ?

ሀ. መወጣጫ ለ. ረጅም ሐ. መሸጋገሪያ መ. ድልድይ

፲፱.ከትከሻዋ በታች ወርዶ የሚዘናፈለው ዞማ ፀጉሯ ውበቷን አጉልቶታል።የተሰመረበት ቃል አውዳዊ ፍቺ

የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ረጅም ለ. አጭር ሐ. ከርዳዳ መ. ቡኒቀለም

፳. ወይዘሮ አስካለች የታውቁ ቆንቋና ሴት ናቸው። የተሰመረበት ቃል ተቃራኒ ፍቺ የሚሆነው የትኛው

ነው?

ሀ. ሥስታም ለ. ንፉግ ሐ. ለጋስ መ. ገብጋባ

፳፩.ከሚከተሉት ውስጥ ባለንብረት አመልካች ጥገኛ ምዕላድ የያዘው የቱ ነው ?

ሀ. መረጣችሁ ለ. ልጆቻችሁ ሐ. ኢንዱስትሪዎች መ. ተመልካቾች

፳፪.በአሁን ጊዜ የቀረበ ሀሳብን የያዘው አረፍተ ነገር የትኛው ነው?

ሀ. ልጆች ትምህርት ቤት እየሄዱ ነው ለ. ልጆች ትምህርት ቤት ሂደዋል

ሐ. ልጆች ትምህርት ቤት ይሄዳሉ መ. ልጆች ትምህርት ቤት መሄዳቸው የማይቀር ነው

፳፫.ቀጥሎ ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ ነፃ ምዕላድ የሆነው የቱ ነው?

ሀ. አፀዳች ለ. ሰፈራችን ሐ. እንስሳት መ. ውሃማ

፳፬.ተደሰት ብለን ማስደሠት ካልን አዘነ ብለን ምን እንላለን?

ሀ. ማዘን ለ. ማሳዘን ሐ. አዘንተኛ መ. አዘን

ሞዴል አምስት Page 3


የካ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ፅ/ት ቤት የብሩህ ተስፋ ክላስተር ት/ቤቶች የ 2016 ዓ.ም አማርኛ ሞዴል ፈተና ለ 6 ኛ ክፍል

፳፭.ከዚህ ቀጥሎ ተዘበራርቀው የቀረብ ዓ.ነገሮች ተስተካክለው ሲፃፉ

1.ቁርሴን ሳልበላ ተጣድፌ ከቤት ወጣሁ

2. ርዕሰ መምህሩ አንበረከከኝ

3. ትምህርት ቤት የሰልፍ ስነ-ስርዓት አልቆ ደረስኩኝ

4.ማታ ሳነብ አምሽቼ ተኛሁ

5.ከእንቅልፌ ዘግይቼ ተነሳሁ

ሀ.1,3,2,4,5 ለ.4,5,1,3,2 ሐ.5,2,3,1,4 መ. 2,4,1,5,4,3

፳፮. አንቀፅን በተመለከት ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ነጠላ ውጤት ለ. አንድነት ሐ. ግጥምጥምነት መ. ጥምር ውጤት

፳፯.ወንፊት የሚለው ቃል ፉካሬያዊ ፍቺ የቱ ነው ?

ሀ. ዱቄት መንፊያ ለ. ተጫዎች ሐ. ሚስጥር ጠባቂ መ. ወሬኛ

፳፰.ህፃኑ የተበላሸ ምግብ በልቶ ክፉኛ ታመመ። የተሰመረበት ቃል የቃል ክፍሉ ነው።

ሀ. ተውሳከ ግስ ለ. ስም ሐ. ግስ መ. ቅፅል

፳፱.ሐረጓ በርትታ ታጠናለች ፤ ፈተናውን ትደፍናለች። በባዶ ቦታው የሚገባው አያያዥ ቃል

የቱ ነው ?

ሀ. ነገር ግን ለ. ቢሆንም ሐ. ስለዚህ መ. ምክንያቱም

፴ አንድ ቃል በቀጥታ ከሚኖረው ፍቺ ባሻገር የሚሰጠው ሚስጥራዊ ፍቺ ነው ።

ሀ. እማሬያዊ ፍቺ ለ. ተመሳሳይ ፍቺ ሐ. ፉካሬያዊ ፍቺ መ. አገባባዊ ፍቺ

፴፩. ‹‹ቤተሰቦቻችን›› የሚለው ቃል በምዕላድ ተነጣጥሎ ሲፃፍ ?

ሀ. ቤተሰብ - ኦች - ኣችን ለ. ቤተሰብ-ኦቻ - ችን ሐ. ቤተሰብዎች-ኣችን መ. ቤተሰቦች- ኣችን

፴፪.የማይተካውን የልጅነት ጊዜዬን እንደ አቻዎቼ ተደስቼ እና ቦርቄ ነበር ያሳለፍኩት። የተሰመረበት

ቃል ፍቺ የቱ ነው?

ሀ. ዘመዶቼ ለ. ጎረቢቶቼ ሐ. ወላጆቼ መ. እኩዮቼ

፴፫.ጀርጃራው ፈንዛ ከአንተማ አልደረሱም ፣

ያሽኮበኩባል ጮሌው እንደርኩም፡፡ ይህ ቃላዊ ግጥም ከየትኛው ቃላዊ ግጥም ይመደባል?

ሀ. ከእርሻ ቃላዊ ግጥም ሐ. ከአረም ቃላዊ ግጥም

ለ. ከሙሾ ቃላዊ ግጥም መ. ከአጨዳ ቃላዊ ግጥም

፴፬. ለጉብኝት ሀዋሳ ሄደው ነበር ። የሚለው ሀሳብ በየትኛው ጊዜ የቀረበ ነው ?

ሞዴል አምስት Page 4


የካ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ፅ/ት ቤት የብሩህ ተስፋ ክላስተር ት/ቤቶች የ 2016 ዓ.ም አማርኛ ሞዴል ፈተና ለ 6 ኛ ክፍል

ሀ. የወደፊት ጊዜ ለ. የኃላፊ ጊዜ ሐ. የትንቢት ጊዜ መ. የአሁን ጊዜ

፴፭. ልጂቱ በአስራዎቹ መገባደጃ በሀያዎቹ ደግሞ መግቢያ ዕድሜ ክልል ላይ ትገኛለች ።
ዐይኖቿ ኩል አያውቁም ነገር ግን የብር አለሎ ይመስላሉ ። ጥርሶቿ ጥበበኛ ያስቀመጣቸው እምነ በረድ ይመስላሉ
።ከአላፊ አግዳሚው ጥርሶቿን የሚጠብቁ ውብ ከናፍሮቿ ሊፈነድቅ የሚታገል የጥቅምት ወር ጽጌረዳ አበባ
ይመስላሉ። ጸጉሯ ቅባት አያውቅም የሐር ነዶ ይመስላል በአጠቃላይ ልጂቱ . . . እያለ የሚቀጥል አንቀጽ በምን ስልት
የቀረበ ነው?
ሀ. ተራኪ ለ. አመዛዛኝ ሐ. ገላጭ መ. ስዕላዊ

መመሪያ - ከተራ ቁጥር ፴፮- ፵ ላሉት ጥያቄዎች ከተዘረዘሩት ቃላት መካከል በትርጉም የሚለየውን ቃል የያዘውን ፊደል
በመምረጥ መልሱ፡፡

፴፮. ሀ. ጥጋብ ለ. ችግር ሐ. ቸነፈር መ. ረሃብ

፴፯. ሀ. ፍስሀ ለ. ደስታ ሐ. ሀዘን መ. ሀሴት

፴፰. ሀ. እንከን ለ. ህፀጽ ሐ. ነውር መ. ቀና

፴፱. ሀ. ነዋይ ለ. ምኞት ሐ. አንጡራ መ. ጥሪት

፵. ሀ. ገላጋይ ለ. ባላንጣ ሐ. ሽማግሌ መ. አስታራቂ

ሞዴል አምስት Page 5

You might also like