You are on page 1of 13

1 በ2010 ዓ.

ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1


መመሪያ አንድ፡- ከጥያቄ 1 እስከ ጥያቄ 5 ድረስ ለቀረቡ ቃላት ተመሳሳይ ይሆናሉ

ተብለው ከቀረቡ ትክክለኛውን መልሥ በመምረጥ በመልሥ መስጫው

ወረቀት ላይ አጥቁር(ሪ)

1. አልባሌ

A. የማይባል C. ያልታሰበ

B. የማይረባ D. የሚያስቸግር

2. ዱካ

A. ኮቴ C. መጠን

B. ጫካ D. ዱር

3. ጭምት

A. ግትር C. አመለኛ

B. ክልፍልፍ D. ሠራተኛ

4. እክል

A. አጋማሽ C. ተጨማሪ

B. ጠንቅ D. ጉዳት

5. ዝንባሌ

A. ፍላጎት C. ጉጉት

B. ዕቅድ D. አመለካከት

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 1
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
መመሪያ ሁለት፡- ከጥያቄ 6 እስከ ጥያቄ 10 ድረስ ለቀረቡ ቃላት ተቃራኒ ይሆናሉ

ተብለው ከቀረቡ ትክክለኛውን መልሥ በመምረጥ በመልሥ መስጫው

ወረቀት ላይ አጥቁር(ሪ)

6. ዕድገት

A. ውፍረት C. ውድቀት

B. ህብረት D. ስልጣኔ

7. ባላንጣ

A. ባለጋራ C. ደመኛ

B. ወዳጅ D. ነገረኛ

8. ናረ

A. ረከሰ C. አሻቀበ

B. ቆመ D. ከበረ

9. መፈንደቅ

A. መፍነክነክ C. መፍለቅለቅ

B. መሞላቀቅ D. መተከዝ

10.ለጋስ

A. ቸር C. ሰጪ

B. ንፉግ D. መፅዋች

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 2
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
መመሪያ ሦስት፡- ከዚህ በታች ለቀረቡት ፈሊጣዊ አነጋሮች ትክክለኛውን ፍች

መርጠህ(ሽ) በመልሥ መስጫው ወረቀት ላይ አጥቁር(ሪ)

11. ውኃ ወቀጣ

A. ከንቱ ልፋት C. የውኃ ሽታ

B. ቦይ ቀደዳ D. ብርቱ ጥረት

12. ሣር ቅጠሉ

A. ወጣ ገባው C. ክምሩ

B. አገር ምድሩ D. መኖ

13.ቃል አባይ

A. አውደላዳይ C. ዋሾ

B. መሰሪ D. ጠንካራ

14. ረጋ ሰራሽ

A. መናኛ ሥራ C. በእርጋታ የተሠራ

B. እውቅ ሥራ D. ጠንካራ ሥራ

15. ሞተ ገባ

A. የሞተ ሰው C. ሞት ቤት የገባ

B. ሰው የሞተበት D. ሊሞት ደርሶ የዳነ ሰው

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 3
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
መመሪያ ሦስት፡- በጅምር የቀሩትን ምሳሌያዊ አነጋገሮችና ትርጉም የሚያሟሉትን አባባሎች

በመምረጥ በመልሥ መስጫው ወረቀት ላይ አጥቁር(ሪ)

16.______ አመሏን አትረሳ

A. አይጥ ቀማምሳ C. ድመት መንኩሳ

B. ጥንቸል መንኩሳ D. ጦጣ መንኩሳ

17. ሲሮጡ የታጠቁት ______

A. ሲሄዱ ይወልቃል C. አያስኬድም

B. ይላላል D. ሲሮጡ ይፈታል

18. የትም ፍጪው ዱቄቱን ______

A. አቡኪው C. አምጪው

B. አስፈጪው D. ጋግሪው

19. አንድ አጥንት ______ ፡፡

A. በአውዳመት C. ለጥምቀት

B. በሰንበት D. ለጥቅምት

20. ላም ባልዋለበት ______

A. ኩበት ለቀማ C. ወተት አይገኝም

B. በሬ ማሰማራት D. እረኛ መላክ

21. ሥራ ለሰሪው ______ ላጣሪው፡፡

A. ማገር C. እሾህ

B. ቋሚ D. ወራጅ

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 4
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
22. ፈሪ ከውኃ ውስጥ --------፡፡

A. ይዋኛል C. ይፈራል

B. ያልበዋል D. ይንቀዠቀዣል

መመሪያ አራት፡- ለሚከተሉት ሥነ-ፅሁፋዊና ሥነ ልሣናዊ ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ

በመምረጥ በመልሥ መስጫው ወረቀት ላይ አጥቁር(ሪ)

23.“ባናት” በሚለው ቃል ውስጥ የተዋጠው ሆሄ ______ ነው፡፡

A. በ C. ና

B. ባ D. አ

24. ከሚከተሉት “አፍሪካ አንድነት ድርጅት” የሚለው በምህፃረ ቃል በትክክል ሲፃፍ

A. አ.አ.ድርጅት C. አ.አንድነት ድርጅት

B. አ.አ.ድ. D. አ/ አንድነት ድርጅት

25. በፅሑፍ ከሰው የተወሰደ አባባልን ለይቶ ለማሳየት የሚያገለግል የሥርዓተ ነጥብ

ዓይነት

A. ነጠላ ሠረዝ C. ትዕምርተ ጥቅስ

B. ትዕምርተ አንክሮ D. ድርብ ሠረዝ

26. ከሚከተሉት ቃላት ሁለት ፍቺ የሌለው

A. በላው C. በቀለ

B. አለ D. መጣ

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 5
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
27. የበግ ልጅ ግልገል ______ ሚባል ሁሉ የአህያ ልጅ ውርንጭላ ይባላል፡፡ባዶ ቦታው

ላይ ሊገባ የሚችል አያያዥ

A. ስለ C. እንደ

B. ከ D. የ

28. “ተቀነባበረ” ከሚለው ቃል የማይመሰረት

A. ተቀባ C. ቀረበ

B. ነበረ D. ተቃረበ

29.“ትላልቅ” በሚለው ቃል ላይ የተቀጠለው ቅጥያ ምን ዓይነት ነው?

A. ውስጠ ግንድ C. መነሻ

B. የመድረሻ D. የመነሻና የመድረሻ

30.ሴትየዋ አዲሱን ምጣድ ______፡፡

A. ገራችው C. አሟሸችው

B. አሰለጠነችው D. ጠመደችው

31. አቶ ጉደታ ከቀፎዎቹ ውስጥ ማር ______፡፡

A. አወጣ C. ቀዳ

B. መዘዘ D. ቆረጠ

32. በአንድ አንቀፅ ውስጥ ሌሎች ዝርዝር ዓረፍተነገሮችን አጠቃሎ የሚይዝ____ይባላል፡፡

A. ኃይለቃል C. ምህፃረቃል

B. ስንኝ D. ሃረግ

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 6
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
33. ከሚከተሉት ቃላት መካከል ባለ ኣንድ ምዕላድ የሆነው

A. ጥይት C. ጠመንጃዬ

B. ቅናተኛ D. ላሞች

34. “ልጆቻችን” በሚለው ቃል ውስጥ ባለቤት ኣመልካች ቅጥያ

A. -ቻችን C. -ኦች

B. -ኣችን D. -ን

35. ከሚከተሉት ውስጥ በአንስታይ ፆታ የቀረበው ቃል የቱ ነው?

A. ወሰድን C. ወሰደች

B. ወሰደ D. ውሰድ

36. መጣ ብሎ አመጣጥ ቢል ፃፈ ብሎ ______፡፡

A. አፃፃፍ C. ፀሐፊ

B. ፅሑፍ D. ፅህፈት

37. ከሚከተሉት ውስጥ ሰዋሰዋዊ ስህተት የሌለበት ዓ/ነገር የትኛው ነው ?

A. ቶለሳ ድመቱ በዱላ መታው፡፡

B. እነቶለሺ ነገ ከጊምቢ ይመጣሉ፡፡

C. ልጁ ዳቦውን ቆረጠመው፡፡

D. ሰውየው ዛፉ በመጥረቢያ ቆረጠ

38. ______ ከቃል የበለጠ ከዓረፍተነገር ያነሰ መዋቅር ነው፡፡

A. ግስ C. አንቀፅ

B. አረፍተነገር D. ሃረግ

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 7
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
39. ከድርሰት ዓይነት በቋንቋ አጠቃቀሙ መስታወታዊ በመባል የሚታወቀው የትኛው ነው?

A. አከራካሪ C. ሥዕላዊ

B. ገላጭ D. ተራኪ

40. በፊደል ተራ ቅደም ተከተል አቀማመጥ ትክክል የሆነው የትኛው ነው?

A. ሃብት፣ ሰረቀ፣ ከሸፈ፣ መብት C. ሃብት፣ መብት፣ ሰረቀ፣ ከሸፈ

B. ሃብት፣ ሰረቀ፣ መብት፣ ከሸፈ D. ሃብት፣ መብት፣ ከሸፈ፣ ሰረቀ

41. አንድ ቁም ነገር ከአንድ ጽሑፍ ውስጥ ለማውጣት የምንጠቀምበት ንባብ

A. ሰፊ ንባብ C.ጥልቅ ንባብ

B. ግርፍ ንባብ D. አሰሳ ንባብ

42. ከሚከተሉት ቃላት መካከል ቅጥያ የሌለው ቃል የቱ ነው?

A. በጉ C. ወፎች

B. ቤት D. አልመጣ

43.“የበላው” በሚለው ቃል ውስጥ ያሉ ቅጥያዎች

A. “ው” እና “በ” C. “የ” እና “ላ”

B. “የ” እና “ው” D. “ላው”

44.አንድ ልብ-ወለድ የተፃፈበት አካባቢና ዘመን ምን ይባላል?

A. ጭብጥ C. መቼት

B. ትልም D. ታሪክ

45. ከሚከተሉት ቃላት መካከል ውስጥ ግንድ ቅጥያ የያዘው የቱ ነው?

A. በትልቅ C. ትላልቅ

B. በትልቅነት D. ትልቅነት

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 8
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
መመሪያ አምስት ፡- በሚከተሉትን አረፍተ ነገሮች ውስጥ የተሰመረባቸውን ቃል ወይም ሃረግ

ፍቺ በመምረጥ በመልሥ መስጫው ወረቀት ላይ አጥቁር(ሪ)

46. ተማሪዎቹ በቅጥር ግቢው ውስጥ ሲርመሰመሱ ይታያሉ፡፡

A. ሲጫወቱ C. ሲሰለፉ

B. ሲሮጡ D. ሲተራመሱ

47.የሰው ልጅ ለአፈር ጠሯ ነው፡፡

A. አጋሯ C. ወዳጅዋ

B. ጠላቷ D. ምንጭዋ

48. ዛሬ በከተማችን ፀጉረ ልውጥ ሰዎች ታይተዋል፡፡

A. ሥም የለሽ C. ጥልቅ ባይ

B. አዳዲስ D. ዓይን አውጣ

49.ለአዲስ ዓመት ልብስ እንዳልገዛ ዋጋው አሻቅቧል፡፡

A. ጨመሯል C. ረክሷል

B. ቀንሷል D. አልረባም

50. ንግግርን ለማዳበር ከሚረዱ ነገሮች መካከል የሆነው የቱ ነው?

A. መዳሰስ C. ውይይት

B. ማዳመጥ D. መፃፍ

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 9
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
መመሪያ ስድስት፡- የሚከተለውን ግጥም መሰረት በማድረግ ለቀረቡት ጥያቄዎች

ትክክለኛውን መልሥ የያዘውን ፊደል (ሆሄ) በመምረጥ በመልሥ

መስጫው ወረቀት ላይ አጥቁር(ሪ

አባሮ ለመያዝ ሮጦ ለማምለጥ፣

ታግሎ ድል ለማድረግ ተምሮ ለመብለጥ፡፡

ተፈጥሮን ለማዘዝ ለመግዛት ለመንዳት፣

ከምርቱ ለማፈስ ከምንጩ ለመቅዳት፡፡

አምሮ ለመታየት ፀጉርን ለማበጠር፣

ያስፈልጋል ቀድሞ ሰው ሆኖ መፈጠር፡፡

(ዮሐንስ አፈወርቅ፣39)

51.ግጥሙ ስንት ስንኞች አሉት ?

A. ስድስት C. ሰባት

B. ሦስት D. አምስት

52. “ለመብለጥ” ለሚለው ቃል ግንድ ቃል የሚሆነው

A. መብለጥ C. በለጠ

B. በላጭ D. ብልጥ

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 10
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
53. የግጥሙ አንጓ ብዛት ስንት ነው ?

A. ስድስት C. ሰባት

B. ሦስት D. አምስት

54. ግጥሙ ስለምን ያወራል?

A. ሁሉም የሚሆነው በጊዜው መሆኑ

B. የፈለጉትን ነገር በቀላሉ ማግኘት መቻሉ

C. እንደፈቀዱ መሆን

D. መልዕክቱ ግልፅ አይደለም፡፡

55. የግጥሙ ቤት መድፊያ ቃል የሆነው

A. ለመንዳት C. ለመቅዳት

B. ለማበጠር D. መፍጠር

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 11
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
መመሪያ ሰባት ፡- የሚከተለውን ምንባብ በጥንቃቄ በማንበብ በምንባቡ መሰረት

ለቀረቡት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመምረጥ በመልሥ መስጫው

ወረቀት ላይ አጥቁር(ሪ)

...የዕድሜ ባለፀጎች አለመግባባትን በእልህና በኃይል ከመፍታት ይልቅ በውይይትና

በመደማመጥ መፍታትን ይመርጣሉ፡፡ ማንኛውንም ነገር በእርጋታና በትዕግሥት

ይጨርሳሉ፡፡ ስለዚህ በቤተሰብ፣ በጎረቤትና በግለሰቦች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር

አስታርቀው ሠላም እንዲሰፍን ያደርጋሉ፡፡ ለዚህ ነው “ አስረዝሞ የቆረጠና በሽማግሌ

የታረቀ ፀፀት የለውም” የሚባለው፡፡

የዕድሜ ባለፀጎች እንደጥሩ መፃህፍት ናቸው፡፡መፃህፍት ማንበብ ብዙ ዕውቀት እንደሚገኝ

ሁሉ ከዕድሜ ባለፀጎች ብዙ ዕውቀት ይገኛል፡፡ “ዕድሜ ትምህርት ቤት ነው” ይባላል፡፡

የዕድሜ ባለፀጎች በሕይወታቸው ብዙ ነገር አይተዋል፡፡ ብዙ ነገር ታዝበዋል፡፡ ሰምተዋል፡፡

በሥራ ላይ ካጋጠማቸው መሰናክል ብዙ ትምህርት አግኝተዋል፡፡ ስለዚህ እነርሱን

በመጠየቅና ሲናገሩ በማዳመጥ ስለአካባቢያችን፣ ስለባህላችን፣ ስለታሪካችን፣ ባጠቃላይ

ስለአገራችንና ስለዓለም ብዙ ማወቅ እንችላለን፡፡ …

(ከቀድሞው የ7ኛ ክፍል መማሪያ መፅሐፍ የተወሰደ)

56.“በእልህ ” ሲል ምን ማለቱ ነው ?

A. በቁጭት C. በብስጭት

B. በንዴት D. በደስታ

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 12
1 በ2010 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና 1
57.“አስረዝሞ የቆረጠና በሽማግሌ የታረቀ ፀፀት የለውም” የሚለው ምን ያሳየናል ?

A. ለነገሮች ትኩረት አለመስጠትን C. ትዕግሥት ማጣትን

B. አመዛዝኖ መፈፀምን D. መደባደብን

58. የዕድሜ ባለፀጎች ለችግሮች መፍትሄ ከሚያገኙባቸው መካከል ያልሆነው የትኛው ነው?

A. ለነገሮች ትኩረት ያለመስጠት፣

B. ነገሮችን በውይይትና በመደማመጥ መፍታት፣

C. ነገሮችን በእርጋታና በትዕግሥት መጨረስ፣

D. በመካከር መፍትሄ ማፈላለግ፣

59.“ዕድሜ ትምህርት ቤት ነው” ሲባል

A. ትምህርትን ለማግኘት ማርጀት አለብን ማለት ነው፡፡

B. በዕድሜ ቆይታ ብዙ ነገር ማየትና ማመዛዘን ይቻላል ማለት ነው፡፡

C. ዕድሜ ዘልዛላ ነው፡፡

D. ሲያረጁ አይበጁም ማለት ነው፡፡

60. የዕድሜ ባለፀጎችን በመጠየቅና በማዳመጥ ስለምን ማወቅ እንችላለን ?

A. ስለ ባህላችን C. ስለታሪካችን

B. ስለአገራችን D. ሁሉም መልሥ ናቸው፡፡

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና (የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሆናቸው) ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 13

You might also like