You are on page 1of 18

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት ተቋማት አመራር

የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት


በ2011 ዓ.ም የኮሌጅ ዲፕሎማ ተመራቂ መምህራን የ ውህድ ማህበራዊ
ሳይንስ የትምህርት አይነት (ከ5-6ኛ ክፍል) ለሙያ ብቃት ማረጋገጫ
የሚሰጥ ምዘና

አጠቃላይ መግለጫ
ይህ ፈተና ሁለት ክፍሎችን ይዟል፡፡ በክፍል አንድ 80 የምርጫ
ጥያቄዎች ሲኖሩ 40 የጂኦግራፊ ፡ 40 ደግሞ የታሪክ ጥያቄዎች
ናቸው፡፡ በክፍል ሁለት ደግሞ 10 አጭር መልስ ስጡ ጥያቄዎች ያሉ
ሲሆን 5ቱ የጂኦግራፊና 5ቱ የታሪክ ናቸው፡፡
እንደየ ጥያቄዎች ትእዛዝ ሁሉንም የፈተና ዓይነቶች በመስራት
መልሱን በካፒታል ፊደል በመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ በግልፅ ፃፉ፡፡
መልሶችን ለመፃፍ እስክርቢቶ ብቻ ተጠቀሙ፡፡
ለፈተናው የተፈቀደው ጊዜ 2፡00 ሰዓት ነው፡፡ ፈታኙ ተጨማሪ
መመሪያዎችን ሊነግራችሁ ይችላል፡፡
ማንኛውም ዓይነት ማጭበርበር ወይም የማጭበርበር ሙከራ በቀጥታ
ከፈተና አዳራሹ ያስወጣል፡፡

ፈታኙ ጀምሩ ካላለ በስተቀር ይህን ገፅ መግለበጥና ማንበብ የተከለከለ


ነው፡፡

0
ክፍል አንድ- ለሚከተሉት 80 የምርጫ ጥያቄዎች አራት አራት አማራጮች
የተቀመጡ ሲሆን ከተሰጡት አማራጮች መልስ ይሆናል የምትሉትን በመምረጥ
በመልስ መስጫ ወረቀ ፃፉ(እያንዳንዱ 1 ነጥብ )

የጂኦግራፊ ትምህርት የይዘት እውቀት ጥያቄዎች (29 ነጥብ)


1. የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ድንበር በውሀ መዋሰኑ ያለው መልካምድራዊ ጠቀሜታ
ምንድን ነው

A. ለውሃ ትራንስፖርት አቅርቦት C. ለኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫነት

B. ለመስኖ እርሻ አገልግሎት D. ለኢንዱስትሪ ልማት

2. የኢትዮጵያ የስነ ህዝብ ባህሪይ መገለጫ የሆነው?

A. ከፍተኛ የከተማ ህዝብ ብዛት C. ዝቅተኛ የህዝብ እድገት

B. አነስትኛ የወጣቶች ቁጥር D. ከፍተኛ ውልደት እና ዝቅተኛ የሞት መጠን

3. በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የህዝብ ጥግግት እንዲኖር ያስቻለው ምክንያት

A. የብዙ ከተሞች እድገት መኖር

B. የተሻለ የሰራ እድል መኖር

C. በጣም ያደገ መሰረተ ልማት ስላለ

D. ለግብርና ስራና ለሰፈራ አመች የሆነ መልካምድራዊ አቀማመጥ ስላለው

4. በትክክል የተዛመደው የቱ ነው

A. ሳመር(Summer)-ክርምት C. ዊንተር(winter)-በልግ

B. ኦቱመን(Autumn)-በጋ D. ስፕረንግ (Spring)-መኸር

5. የደቡብ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ቦታዎች ዋና የዝናብ ወቅታቸው

A. በመኸር B. በበጋ C. በፀደያ D. በክረምት

6. የአፍሪካ ቀንድ ሃገራትን በብዛት አካሎ የሚገኝ ውሃማ አካል

A. የሜደትራንያን ባህር C. የአረብያን ባህር

B. የቀይ ባህር D. የሙት ባህር

1
7. ከገሞራዊ ተግባራት አንጻር አብዛኛዎቹ የምስራቅ አፍሪካ ተራራዎች የምን ውጤቶች
ናቸው

A. የቅልብሽ B. የገሞራዊ ቡልቅ C. የአጎብጓቢ በረድ D. በግጥግጦሽ

8. አብዛኞች የኢትዮጵያ ወንዞች በፏፏቴዎች እና በፍጥነት በመፍሰሳቸው በይበልጥ

ሊኖራቸው የሚችል እምቅ አቅም

A. ለውሃ ትራንስፖርት C. ለአሳ እርባታ

B. ለመስኖ ስራ D. ለኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫነት

9. ስለ ዝቄ ህዋ ትክክል የሆነው የቱ ነው

A. የከባቢ አየርን 75% የአየር ይዘት ይይዛል C. የታችኛው ከባቢ አየር መገኛ ነው
B. ከፍተኛ የአዞን ንጣፍ መገኛ ነው D. ከመሬት በላይ ከ50-80 ከ.ሜ ይገኛል

10. ከሚከተሉት አንዱ በተፈጥሮ የተገኘ አፍላሽ ጋዝ ነው

A. ኦክስጅን B. ናይትሮጅን C. ክሎሮፍሎሮካርበን D. ካርበንዳይ ኦክሳይድ

11. ያለ ካርታ ሚዛን ያንድን ቦታ መገኛ ከሌሎች ቦታዎች አንፃር ለመግለጽ


የምንጠቀምበት የካርታ አይነት

A. ንድፍ ካርታ C. የጠቅላላ አገልግሎት ካርታ

B. መልክአምድራዊ ካርታ D. አትላስ ካርታ

12. በመልካምድራዊ ካርታ ውስጥ የውሃማ አካላትን ለመግለጽ የምንጠቀመው ቀለም

A. ቀይ B. ሰማያዊ C. ቡናማ D. አረንጓዴ

13. በሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚገኝ የዱር እንስሳ

A. አንበሳ B. ኒያላ C. ጭላዳ ዝንጀሮ D. ዋሊያ

14. እጽዋቶች የአከባቢያችን የአየር ንብረት እንዳይበከል በምን አይነት መንገድ ይጠቅማሉ

A. ካርቦንዳይ ኦክሳይድን በመምጠጥ C. ለዱር እንስሳት መጠለያነት

B. አፈርን ከመሸርሸር በመጠበቅ D. ለማገዶነት

2
15. ለዱር እንስሳት መሰደድ ዋነኛው ሰው ሰራሽ ምክንያት

A. የገጠር ሰፈራ C. ዳግም ድነና

B. ማድነን ( ደን ማልበስ) D. ብሄራዊ ፓርክ ማቋቋም

16. በኢትዮጵያ የደን ሽፋን እየቀነሰ እንዲመጣ ካደረጉት ሰው ሰራሽ ምክንያቶች


የሚመደበው

A. የግብርና የደን ልማትና አያያዝ መኖር C. ዳግም ድነና

B. ማደነን ( ደን ማልበስ) D. ደን ጭፍጨፋ

17. ፈጣን የህዝብ እድገት መኖር በተፈጥሮ እጽዋቶች ላይ ሊያደርስ የሚችለው አሉታዊ

ተጽእኖ በምን መንገድ ነው

A. ብዛህይወትን በማጥፋት C. ለእርሻ የሚሆን ቦታን በማስፋፋት

B. በህገወጥ አደን D. በድነና

18. በኢትዮጵያ በመጥፋት ላይ የሚገኝ የዱር እንስሳ

A. ጅብ B. ቀበሮ C. ቀይ ቀበሮ D. አንበሳ

19. ከሚከተሉት ውስጥ የዱር እንስሳትን ለመንከባከብ አነስተኛ ድርሻ ያለው

A. ብሄራዊ ፓርክ B. ጥብቅ ደን C. የእንስሳት መናኸሪያ D. ተክላት ግብርና

20. የኮንሶ ህዝብ የሚታወቅበት የአፈር ጥበቃ ዘዴ

A. የግብርና ደን ልማት C. ብስባሽ በመጨመር

B. B. እርከን ስራ D. መሬት በማሳደር

21. የማከር/ሰብልን ማፈራረቅ/ ጠቀሜታ የሆነው

A. እጽዋትን ለመንከባከብ C. የአፈር ለምነትን ለመጠበቅ

B. የአፈራ መሸርሸርን ለመከላከል D. የአፈርን ተፈጥሯዊ ይዘት ጠብቆ ለመያዝ

22. የዋሊያ እና የጭላዳ ዝንጀሮ መገኛ ብሄራዊ ፓርክ

A. የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ C. ማንጎ ብሄራዊ ፓርክ

B. የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ D. አዋሽ ብሄራዊ ፓርክ

3
23. የብሄራዊ ፓርኮች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሆነው

A. ለስነ ውበት B. ለቱሪዝም C. ለብዛህይወት D. ለዱር እንስሳት እንክብካቤ

24. ከኤች አይ ቭ ኤድስ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን እንዴት መርዳት ይኖርብናል

A. ማግለልና መድሎ ባለማድረግ C. መርዳት አያስፈልግም

B. የህክምና አገልግሎት በመስጠት ብቻ D. ምንም ባለመስራት

25. በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ፈጣን የህዝብ እድገት መኖር ከሚያመጠው ተፅእኖ ውስጥ
የማይመደበው

A. የደን ጭፍጨፋ C. የአየር ንብረት መዛባት

B. ወጥነት የሌለው ስርዓተ ምህዳር ጥበቃ D. የአከባቢ ጥበቃ

26. የመልካም አስተዳደር መገለጫ ባህሪያት የሆነው

A. ተጠያቂነት አለመኖር B. ህግን ማክበር C. ሙስና D. ግልጸኝነት አለመኖር

27. በመልካም አስተዳደር ተጠያቂነት ማለት

A. ግልፀኝነት C. ሙስናን ማስወገድ

B. የሃላፊነት ስሜት D. ተገቢ ምላሽ መስጠት

28. ከሚከተሉት አንዱ የህፃናት መብት ጥሰትን ያሳያል

A. የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ C. ትምህርት እንዲማሩ ማድረግ

B. ከአደጋ መጠበቅ D. ስም የማግኘት

29. ከናይል ወንዝ ተፋሰስ ሃገራት ውስጥ ከፍተኛ የውሃ መጠን የምታበረክት የትኛዋ
ሀገር ናት

A. ግብፅ B. ሱዳን C. ኢትዮጵያ D. ኡጋንዳ

የጂኦግራፊ ትምህርት የማስተማር ስነ ዘዴን የተመለከቱ ጥያቄዎች (11 ነጥብ)


30. ለአንድ ክፍለ ጊዜ የማስተማር ስራ የምናዘጋጀው የትምህርት እቅድ

A. እለታዊ እቅድ B. የምዕራፍ እቅድ C. አመታዊ እቅድ D. ሳምንታዊ እቅድ

31. መምህሩ ያስተማረውን ትምህርት ተማሪዎች ምን ያህል ተረድተዋል ብሎ


የሚገመግምበት ተግባር
A. ማጠናከር B. ምዘና C. ማጠቃለል D. መርጃ መሳሪያ

4
32. በማስተማሪያ ክፍል ውስጥ መጀመሪያ ሊከናወን የሚገባ ተግባር

A. ማቅረብ/ገለጻ B. መግቢያ C. ማጠናከር D. ምዘና

33. በውይይት የማቅረብ ዘዴ ለተማሪዎች ያለው ጠቀሜታ

A. ልምድና እውቀታቸውን ለማካፈል C. በመስክ ያዩትን የመተግበር ልምድ

B. በጥያቄና መልስ እውቀታቸውን ለማሳደግ D. ለማስታዎስና ለማቅረብ

34. የፕሮጅክት ዘዴ ለመተግበር የግድ ሊኖረን የሚገባን

A. በተግባር መማርን C. በክፍል ውስጥ መማርን

B. በምልከታ መማርን D. በቤተ ሙከራ መማር

35. በጂኦግራፊ ትምህርት ጥናት ውስጥ ከፍተኛው የአእምሮ ተግባር

A. ምልከታ C. አመክንዮ/ ምክንያታዊነት/

B. ማስታዎስ D. በተግባር የሚለካ ችሎታ

36. የነገሮችንና የሰዎችን ስርጭት ለማሳየት የምንጠቀምበት ጂኦግራፊያዊ መርጃ መሳሪያ

A. ካርታ B. ሉል C. ጂፒኤስ ( GPS) D. ጂአይ ኤስ (GIS)

37. በክፍል ውስጥ ከሚከናወነው የማስተማር ተግባራት በተጨማሪ ስነ መልካምድርን


ለማስተማር የተሸለው የማስተማሪያ መንገድ

A. በመስክ ጉብኝት C. በሰርቶ ማሳየት

B. በጥያቄና መልስ D. ስልቶችን በመንገር

38. በጂኦግራፊ ትምህርት የተከታታይ ምዘና ያለው ጠቀሜታ ምንድን ነው

A. የመገንዘብ ችሎታን ከፍ ለማድረግ

B. እሴታዊና ክህሎታዊ ውጤቶችን ለማምጣት

C. እውነታዎችን እንዲገነዘቡ ለማገዝ

D. ተማሪዎችን ስርዓተ ትምህርቱ በደንብ እንዲያውቁት ማድረግ

39. ከሚከተሉት የፈተና አይነቶች በይበልጥ ለግምታዊ መልስ የተጋለጠው

A. ምርጫ B. አዛምድ C. እውነት/ ሀሰት D. አጭር መልስ

5
40. ተማሪዎች በአንድ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የተማሩትን ለመረዳት የምንጠቀምበት የተሸለ
የምዘና ዘዴ

A. ማጠቃለያ ፈተና B. ተከታታይ ምዘና C. ድንገተኛ ፈተና D. የቤት ስራ

የታሪክ ትምህርት የይዘት ዕዉቀት ጥያቄዎች (30 ነጥብ)


41. ከሚከተሉት መካከል ታሪክን የበለጠ የሚገልጸዉ የትኛዉ ነዉ?

A. ስለአለፈዉ ጊዜ ዉጤቶች ያጠናል

B. ስለወደፊቱ ጊዜ ይተነብያል

C. ስላለፈዉ ጊዜ የሚያወሳ፣ ያሁኑን የሚያስገነስብና ስለወደፊቱም የሚተነብይ ነዉ

D.የጥንቱን ሆሚኒድስ ቅሪተ- አካል ያጠናል

42. የአንድኛ ደረጃ የታሪክ መረጃ ምንጭ ምሳሌ ያልሆነዉ የቱ ነዉ?

A. ሐዉልቶች B.ጥንታዊ ሳንቲሞች C. ህንጻዎች D. መጽሐፍት

43. የኢትዮጵያ የመካከለኛዉ ዘመን ታሪክ ፡-

A. ከአክሱም መንግስት መዉደቅ በኋላ ይጀምራል

B. በክርስቲያኑ መንግስት የግዛት ማስፋፋት ስኬት ይታወቃል

C. ከይኩኖ አምላክ ወደ ሥልጣን መምጣት ጋር አክትሟል

D. የላሊበላ ዉቅር አቢያተ ክርስቲያናት የታነጹበት ዘመን ነዉ

44. ዳግማዊ ቴዎድሮስ፡-

A. ግብጽ ሀገራችን ላይ የነበራትን ተጽዕኖ እንዲያከትም አድርጓል

B. ለኢትዮጵያ አንድነት መሰረት ጥሏል

C. በሱዳን መሐዲስቶች ተሸንፏል

D. የጣሊያንን የቅኝ ግዛት መስፋፋት በፅኑ ታግሏል

6
45. በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከ1906 –1930 የነበረዉ ጊዜ የሚታወቅበት፡-

A. በማዕከላዊ መንግስት ሥልጣን መጠናከር

B. ከዉጭ ወራዎች ጋር በነበረ ጦርነት

C. በፖለቲካ አለመረጋጋት ችግር

D. በሰሜን ኢትዮጵያ በጣሊያን የቅኝ ግዛት ማስፋፋትና መያዝ

46. ከኢትዮጵያ ቅሪተ አካል የጥናት ቦታዎች የሉሲ ቅሪተ አካል የተገኘበት ክልላዊ መንግስት፡

A. ኦሮሚያ B. አፋር C. ትግራይ D. ሶማሊ

47. ኢትዮጵያ የሰዉ ዘር መገኛ ናት የሚባለዉ በምን ምክንያት ነዉ?

A. የብዙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መገኛ ስለሆነች

B. ከምስራቅ አፍሪካ ሃገራት መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሕዝብ ስላላት

C. በርካታ ቅርተ-አፅም ስለተገኘባት

D. የጥናታዊ ሥልጣኔና መንግስታት ባለቤት ስለነበረች

48. የኑቢያ ግዛት፡-

A. መገኛዉ አፍሪካ ቀንድ ነበር

B. ሱዳን ላይ በርካታ ቅርሶችን ትቶ አልፏል

C. ከምዕራብ አፍሪካ ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዱ ነበር

D. ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ4ኛዉ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አክሱምን ይዞ ነበር

49. ለአክሱም መንግስት ዕድገትና ብልፅግና የኢኮኖሚ መሰረት የነበረዉ፡-

A. ከአርሶ አደሩ ይሰበሰብ የነበረዉ የእርሻ ግብር ገቢ

B. በቀይ ባህር ንግድ የነበረዉ የበላይነት

C. ከባሪያ ንግድ ይገኝ የነበረዉ ገቢ D. ከቱሪዝም ይገኝ የነበረዉ ቀረጥ ገቢ

7
50. አክሱም ታዋቂ የነበረችዉ፡-

A. ወደ ሰሜን አፍሪካ ባደረገችዉ አስደናቂ የግዛት ማስፋፋት

B. በመሰረተችዉ ዲሞክራሲያዊ መስተዳድር

C.በአስገራሚዉ ሐዉልቷና በህንጻ ፍርስራሾቿ

D. በከፍተኛ ደረጃ በተከማቸዉ የወርቅ ሃበቷ

51. የክርስትና ሀይማኖት፡-

A. የኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች ሃገር በቀል እምነት ነዉ

B. ወደ ኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ የገባ በደቡብ አረቢያ ነጋዴዎቸ አማካኝነት ነዉ

C. ወደ አክሱም ከገባ በኋላ በነንጉሳዊያን ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷል

D. ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ በእስልምና ሃይማት ተተክቷል

52. እስልምና ወደ ኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ የገባዉ፡-

A. በሙሰሊም አረቦች ጦርነት C. በግብጽና በሱዳን በኩል

B. በዋናነት በሙሰሊም አረቦች የንግድ ግንኙነት D. ከመካ በመጡ ሙስሊም ስደተኞች

53. ከአፍሪካ እናት ቋንቋ ቤተሰብ መካከል በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተናጋሪ ያለዉ፡-

A. ኒሎ - ሰሃራን B. ኒጀር - ኮንጎ C. ኮይሳን D. አፍሮ- ኤስያቲክ

54. የዛጉዌ ሥርወ-መንግስት፡-

A. በግዙፉ ሐዉልት ይታወቃል

B. መስራቾቹ የላስታ ኩሽቲክ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ነበሩ

C. የቀይ ባህርን ንግድ በበላይነት ተቆጣጥሮ ነበር

D. የክርስትና ሃይማትን ወደ ኢትዮጵያ አስገብተዋል

55. ካዎ የሚለዉን የማዕረግ ስም የሚጠቀሙ ነገስታቶች፡-

A. የወላይታ B. የዳሞት C. የከፋ D. የጊቤ መንግታት

56. በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ከተመሰረቱት የሙስሊም ሱልጣኔቶች መካከል ቀደምቱ

የትኛዉ ነዉ?

A. ሸዋ B. ዳዋሮ C. ሐድያ D. ኢፋት

8
57. በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የመካከለኛዉ ዘመን በክርስቲያኑና በሙስሊም መንግስታ

መካከል የነበረዉ ግጭት ዋናዉ ምክንያት፡-

A. የሃይማት ልዩነት C. ዘይላንና የንግድ መስመሩን የመቆጣጠር ፍላጎት

B. የቀይ ባህር ንግድ ላይ የነበረዉ ፉክክር D. የዉጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት

58. ከሚከተሉት ታሪካዊ ክስተቶች መካከል የጎንደሮች የግዛት ዘመን መጀመርን

የሚያመላክተዉ የትኛዉ ነዉ?

A. የእየሱሳዊያን ከጎንደር መባረር C.የስሱንየስ በፋሲለደስ መተካት

B. የኦርቶዶክስ ሃማኖት መጠናከር D. የጎንደር በዋና ከተማነት መቆርቆር

59. ከሚከተሉት የዉጭ ሃይሎች ዉስጥ በዮሐንስ IV ዘመነ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ

ቀጥተኛ ወታደራዊ ጥቃት ያላደረገዉ የቱ ነዉ?

A. ግብጽ B. እንገሊዝ C. ጣሊያን D. ሱዳን

60. በጉርኣ ጦርነት፡-

A. ወራሪዉ ጦር በተሳካ ሁኔታ ተደምስሷል

B. መሐዲስቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ወታደር አጥተዋል

C. ለጣሊያን ጦር መንገድ ከፍቷል

D. ዮሐንስና ንጉስ ምንሊክ ጠላትን በጋራ ተዋግተዋል

61. ከሚከተሉት ዉስጥ ስለከፋ መንግስት እዉነት የሆነዉ፡-

A. ነገስታቱ ሚክሪቾ የሚባል የማዕረግ ስም ነበራቸዉ

B. በደንብ የተደራጀ የመከላከያ ስልት ነበረዉ

C. የዳግማዊ ቴዎድሮስ የአንዲት ኢትዮጵያ አካል ነበር

D. የሱዳን መሐዲስቶችን ጥቃት በብቃት መክቶ መልሷል

62. በኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት፡-

A. ነገስታቱ ፍጹም ስልጣን አለቸዉ

B. የፖለቲካ ስልጣ በሽማግሌዎች ቡድን ክፍፍል መሰረት ይከናወናል

C. የገዳ ባለስልጣናት የሚኖሩት በቤተመንግታት ዉስጥ ነበር

D. አባዱላ የጠቅላላ ጉባኤዉ የበላይ ነዉ

9
63. የሐረር ኢሚሬት፡-

A. ምስራቅ ኢትዮጵያ ላይ የተከሰተ የክርስቲያን መንግስት ነበር

B. ሐረር ከተማ ላይ በርካታ የእስልምና ማስተማሪያ ተቋማትን ገንብቷል

C. እ.ኤ.አ. በ1875 የመጣዉን የግብጽ ወራሪ ሃይል ድል አድርጓል

D. ከኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም ሞት በኋላ በክርስቲያኑ መንግስት ስር

ተጠቃሏል

64. በሽንብራ ኩሬ ጦርነት፡-

A. የክርስቲያኑ መንግስት ሠራዊት አኩሪ ድል ተቀዳጅቷል

B.ንጉሰ ነገስት ልብነ ድንግል ተገድሏል

C. የሙስሊም ጦር የክርስቲያኑን ሃይል ደምስሷል

D. የፖርቱጋል ወታደሮች የክርስቲያኑን መንግስት አግዘዋል

65. የሕይወት ስምምነት፡-

A. በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል የተፈረመ ዉል ነበር

B. በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል የነበረዉን ጦርነት እንዲያበቃ ያደረገ ነበር

C. ምጽዋንና ሌሎች የጠረፍ ግዛቶች ለኤትዮጵያ እነዲመለሱ ያስቻለ ነበር

D. ኢትዮጵያን በብዙ ሁኔታ ተጠቃሚ ያደረገ ስምምነት ነበር

66. የአዲስ አበባ ጁቡቲ የባቡር መስመር፡-

A. በጦር ካሳ ፈንታ በጣሊያኖች የተገነባ ነዉ

B. ኢትዮጵያን ከዉጭዉ ዓለም አገናኝቷል

C. ጁቡቲን ወደ ኢትዮጵያ እንድትመለስ የማድረግ ዓላማም ነበረዉ

D. የተለያዩት በአደዋ ጦርነት ጊዜ ነበር

67. የሚከተሉት አማራጮች ከአንዱ ሌላ ሁሉም ስለአደዋ ጦርነት ትክክል ናቸዉ፡፡ ትክክል

ያልሆነዉ፡-

A. የመሐዲስቶችን ስጋት በብቃት አስወግዷል

B. ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን እንድታስከብር አድርጓል

C. በኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል


D. ጣሊያንን ለብቀላ አነሳስቷል
10
68. እ.ኤ.አ. በ1906 ለተከሰተዉ የፖለቲካ ቀዉስ ዳግማዊ ምንሊክ የወሰደዉ ርምጃ፡-

A. የሶስተዮሽ ስምምነት ፈራሚ ሃይሎችን ዕቅድ መቀበል

B. የሃገሩን ዘጎች ለማስተማር ዘመናዊ ትምህርት ቤት ለመክፈት መወሰን

C. የመጀመሪያዉን የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቋቋም

D. ንግስት ዘዉዲቱን እንደራሴ አድርጎ መሾም

69. እ.ኤ.አ. ግንቦት 5 ቀን 1941፡

A. የእንግሊዝ ሃይል አዲስ አበባን ከጣሊያን ጦር ነጻ አወጣ

B. ማርሻል ግራዚያኒ ቤተመንግስት ዉስጥ ቆሰለ

C. የኢትዮጵያ ንጉሳዊ አገዛዝ እነደገና ተመለሰ

D. የጣሊያን ሰራዊት ከአዲስ አበባ ለቆ ወጣ

70. ከሚከተሉት መካከል ሰለ 1931 የኢትዮጵያ ሕገመንግስት እዉነት የሆነዉ የትኛዉ ነዉ?

A. ያለተማከለ ፖለቲካዊ ሥልጣን ለማምጣት ያለመ ነበር

B. ባላባቶች በንጉሰ ንገስቱ ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ አድርጓል

C. ለአብዛኛዎቹ ግዛቶች የራስ ገዝ አስተዳደር ፈቅዷል

D. የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮን ፈጥሯል

የታሪክ ትምህርት የማስተማር ሥነ ዘዴ ጥያቄዎች (10 ነጥብ)


71. ዝርዘር ዓላማ ማዘጋጀት በዋናነት የሚጠቅመዉ፡-

A. ለዕለታዊ ትምህርት ዕቅድ C. ለሴሚስተር ትምህርት ዕቅድ

B. ለዓመታዊ ትምህርት ዕቅድ D. ለምዕራፍ ትምህርት ዕቅድ

72. ከሚከተሉት ዉስጥ እንደአጠቃላይ የትምህርት ዓላማ የሚቆጠረዉ የትኛዉ ነዉ?

A. ተማሪዎች ሃገራቸዉን በካርታ ላይ ያሳያሉ

B. ተማሪዎች የታሪክ ትምህርትን ጠቀሜታ ያደንቃሉ

C. ተማሪዎች የአክሱም መንግስት ዉድቀት ምክንያቶችን ይገልጻሉ

D. ተማሪዎች ክርስትና ወደ አክሱም እንዴት እንደገባ ያብራራሉ

73. መምህሩ ያለፈዉን ትምህርት የሚያጠናክርበት የዕለታዊ ትምህርት ዕቅድ አካል፡-

A. መግቢያ B. ገለጻ C. ማጠናከሪያ D. ግምገማ

11
74. ከሚከተሉት መካከል አንዱ የዕለታዊ ትምህርት ዕቅድ አይነተኛ ባህሪያ አይደለም፡፡

A. ግልጽ ዓላማ

B. ለታቀደዉ ትምህርት የሚያስፈልጉ የትምህርት መሳሪያዎች ዝርዝር

C. ከጅምሩ እስከ ፍጻሜዉ የሚያገለግል ቅደም ተከተላዊ ዝግጅት

D. አጠቃላይ ዓላማ

75. በመማር ማስተማር ሂደት ተማሪ አሳታፊ ያልሆነዉ ሥነ ዘዴ የቱ ነዉ?

A. ጥያቄና መልስ B. ገለጻ C. የቡድን ዉይይት D. የቡድን ፅብረቃ

76. ብዙን ጊዜ የተማሪዎች መማር በጥያቄና መልስ የሚገመገመዉ፡-

A. በምዕራፍ ትምህርት መጨረሻ C. የዕለቱ ትምህርት ዕቅድ እንደተጠናቀቀ

B. ዓመታዊ ዕቅድ ከመጠናቀቁ በፊት D. የምዕራፍ ትምህርት ከመጠናቀቁ በፊት

77. ከሚከተሉት የማስተማሪያ ሥነ ዘዴዎች ከፍተኛ የተማሪዎች ተሳትፎ የሚይታይበት

የትኛዉ ነዉ?

A. የዉይይት ዘዴ B. የገለጻ ዘዴ C. የሚና ጨዋታ ዘዴ D. የተረት ትርክት ዘዴ

78. በተጋባዥ እንግዳ “ስለማይጨዉ ጦርነት” ለማስተማር የሚስማማዉ ሥነ ዘዴ፡-

A. ተረት ነገራ B. ቡድን ዉይይት C. ሰርቶ ማሳየት D. ሙከራ

79. ከሚከተሉት ዉስጥ የተከታታይ ምዘና መለያ ባህሪያት ያልሆነዉ፡-

A. ለተማሪዎች ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉ

B. ለተማሪዎች መሻሻል ሰፊ ዕድል ማመቻቸቱ

C. ተከታታይ ምዘና ምርመራም ነዉ

D. በአመዛኙ በመንፈቀ-ዓመት ወይም በአመቱ መጨረሻ መተግበሩ

80. በገለጻ የማስተማር ዘዴ ዉስንነቱ፡-

A. በተወሰነ ክፍለ ጊዜ ብዙ ርዕሶችን ማጠናቀቅ ማስቻሉ

B. የተማሪዎችን የማዳመጥ ክህሎት ማዳበሩ

C. ተማሪዎች ላይ መሰላቸትን መፍጠሩ

D. የተማሪ ልዩነት ተደራሽ አለማድረጉ

12
ክፍል ሁለት- አጭር መልስ ስጡ
የጂኦግራፊ ትምህርት የይዘት ጥያቄዎች

81. ሁለት ጨዋማ ያልሆኑ ውሃማ አካላትን ዘርዝሩ (2 ነጥብ)

82. በህዝብ አሰፋፈር ላይ ልዩነት የሚፈጥሩ ፊዚካዊ እና ማህበራዊ- ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች

ሁለቱን ጥቀሱ (2 ነጥብ)

83. የአለም ሙቀት መጨመር በአርብቶ አደሩ ላይ የሚያሳድሩትን ሁለት ተጽእኖዎች ጥቀሱ

( 2 ነጥብ)

84. የጂኦግራፊ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (GIS) ለካርታ ስራ የሚሰጠውን ጠቀሜታዎች ሁለቱ

ዘርዝሩ (2 ነጥብ)

የጂኦግራፊ ትምህርት የማስተማር ስነ ዘዴ ጥያቄዎች

85. ሁለት የተከታታይ ምዘና አይነቶችን ዘርዝሩ (2 ነጥብ)

የታሪክ ትምህርት የይዘት ዕዉቀት ጥያቄዎች (7 ነጥብ)

86. ለአክሱም መንግስት መዉደቅ ምክንት ከነበሩ ሁኔታዎች መካከል ሶስቱን ጻፉ፡፡ (2.5
ነጥብ)

87. ከዳግማዊ ምንሊክ ዘመን ጠቃሚ ታሪካዊ ክስተቶች ዉስጥ አምስቱን ግለጹ፡፡ (2.5 ነጥብ)

88. ከዘመነ መሳፍንት መሰራተዊ መገለጫ ባህሪያት ሁለቱን ለይታችሁ ጥቀሱ፡፡ (2 ነጥብ)

የታሪክ ትምህርት የማስተማር ሥነ ዘዴ ጥያቄዎች (3 ነጥብ)

89. “የገዳ ስርዓት“ የሚለዉን ርዕስ ለማስተማር ታሳቢ ያደረጉ ሶስት ዝርዝር ዓላማዎችን
ንደፉ፡፡ (1.5 ነጥብ)

90. “የአደዋ ጦርነት“ የሚለዉን ይዘት ለማስተማሪ ተስማሚ የሆኑ ሶስት የመርጃ
መሳሪያዎችን ጸፉ፡፡ (1.5 ነጥብ)

13
የኮሌጅ ዲፕሎማ ተመራቂ ተመዛኝ መምህራን የመልስ መስጫ ወረቀት

ቀን --------/-------2011 ዓ/ም
ስም: የአባት ስም: የአያት ስም: ጾታ: ወ

በአማርኛ በአማርኛ በአማርኛ
(እባክዎን ሳጥኑ ዉስጥ የ
_________________ _________________ _________________
√ ምልክት ያስቀምጡ )
በእንግሊዝኛ በእንግሊዝኛ በእንግሊዝኛ

_________________ _________________ _________________


ክልል የትምህርት ዓይነት የፈተና ጣቢያ የሰለጠነበት
ኮሌጅ/ዩኒቨርስቲ
--------------------------- -------------------------- --------------------------
--------------------------

የትምህርት ደረጃ: የስልጠና ሞዳሊቲ:

------------------------- ስፔሻሊስት ጀኔራሊስት ሊኒየር

ውህድ

በ---------------------------------------የትምህርት አይነት

የተመረቀበት( ቀችበት) ሳይክል: ክፍል (1-4) ክፍል (5-6)

ክፍል (5-8) ክፍል (1-8)

ፕሮግራም : መደበኛ የማታ

(እባክዎን ሳጥኑ ዉስጥ የ √ ምልክት ያስቀምጡ )

የክልል መለያ ቁጥር የትምህርቱ መለያ ቁጥር የኮሌጅ መለያ ቁጥር የተፈታኝ መለያ ቁጥር

14
የኮሌጅ ዲፕሎማ ተመራቂ ተመዛኝ መምህራን የመልስ መስጫ ወረቀት

ቀን --------/-------2011 ዓ/ም
የክልል መለያ ቁጥር የትምህርቱ መለያ ቁጥር የኮሌጅ መለያ ቁጥር የተፈታኝ መለያ ቁጥር

1. _____________________ 35. _____________________ 69. _____________________


2. _____________________ 36. _____________________ 70. _____________________
3. _____________________ 37. _____________________ 71. _____________________
4. _____________________ 38. _____________________ 72. _____________________
5. _____________________ 39. _____________________ 73. _____________________
6. _____________________ 40. _____________________ 74. _____________________
7. _____________________ 41. _____________________ 75. _____________________
8. _____________________ 42. _____________________ 76. _____________________
9. _____________________ 43. _____________________ 77. _____________________
10. _____________________ 44. _____________________ 78. _____________________
11. _____________________ 45. _____________________ 79. _____________________
12. _____________________ 46. _____________________ 80. _____________________
13. _____________________ 47. _____________________ 81. _____________________
14. _____________________ 48. _____________________ 82. _____________________
15. _____________________ 49. _____________________ 83. _____________________
16. _____________________ 50. _____________________ 84. _____________________
17. _____________________ 51. _____________________ 85. _____________________
18. _____________________ 52. _____________________ 86. _____________________
19. _____________________ 53. _____________________ 87. _____________________
20. _____________________ 54. _____________________ 88. _____________________
21. _____________________ 55. _____________________ 89. _____________________
22. _____________________ 56. _____________________ 90. _____________________
23. _____________________ 57. _____________________ 91. _____________________
24. _____________________ 58. _____________________ 92. _____________________
25. _____________________ 59. _____________________ 93. _____________________
26. _____________________ 60. _____________________ 94. _____________________
27. _____________________ 61. _____________________ 95. _____________________
28. _____________________ 62. _____________________ 96. _____________________
29. _____________________ 63. _____________________ 97. _____________________
30. _____________________ 64. _____________________ 98. _____________________
31. _____________________ 65. _____________________ 99. _____________________
32. _____________________ 66. _____________________ 100. ____________________
33. _____________________ 67. _____________________
34. _____________________ 68. _____________________

15
የኮሌጅ ዲፕሎማ ተመራቂ ተመዛኝ መምህራን የመልስ መስጫ ወረቀት

ቀን --------/-------2011 ዓ/ም

የክልል መለያ ቁጥር የትምህርቱ መለያ ቁጥር የኮሌጅ መለያ ቁጥር የተፈታኝ መለያ ቁጥር

ክፍል ሁለት - ለአጭር መልስ ጥያቄዎች


81. ሀ. -------------------------------------------------------------------------

ለ.-------------------------------------------------------------------------

82. ሀ. --------------------------------------------------------------------------

ለ· -------------------------------------------------------------------------

83. ሀ. ---------------------------------------------------------------------------

ለ.--------------------------------------------------------------------------

84. ሀ. ---------------------------------------------------------------------------

ለ.----------------------------------------------------------------------------

85. ሀ. ---------------------------------------------------------------------------

ለ.-----------------------------------------------------------------------------

86. ሀ. ----------------------------------------------------------------------------

ለ.------------------------------------------------------------------------------

ሐ.----------------------------------------------------------------------------

87. ሀ. ----------------------------------------------------------------------------

ለ.------------------------------------------------------------------------------

ሐ.----------------------------------------------------------------------------

መ.----------------------------------------------------------------------------

ሠ.----------------------------------------------------------------------------

88. ሀ. ----------------------------------------------------------------------------

ለ.------------------------------------------------------------------------------
16
የኮሌጅ ዲፕሎማ ተመራቂ ተመዛኝ መምህራን የመልስ መስጫ ወረቀት

ቀን --------/-------2011 ዓ/ም

የክልል መለያ ቁጥር የትምህርቱ መለያ ቁጥር የኮሌጅ መለያ ቁጥር የተፈታኝ መለያ ቁጥር

ክፍል ሁለት - ለአጭር መልስ ጥያቄዎች

89. ሀ. ----------------------------------------------------------------------------

ለ.------------------------------------------------------------------------------

ሐ.----------------------------------------------------------------------------

90. ሀ. ----------------------------------------------------------------------------

ለ.------------------------------------------------------------------------------

ሐ.----------------------------------------------------------------------------

17

You might also like