You are on page 1of 17

1

2
የዝክረ- አድዋ ርዕሰ ጉዳዮች (ዋና ዋና ጭብጦች)

መግቢያ፡-

ከአዉሮፓዊያን አሰሳና ግኝት ማግስት ቅኝ አገዛዝ እንደተጀመረ ይታወቃል፡፡ ከ 1870 ዎቹ እስከ 1880 ዎቹ ባለዉ ጊዜ
ዉስጥ ማለትም ሁሉም አህጉራት ቅኝ ግዛት ስር ከገቡ በኋላ “አፍሪካን በአፍሪካ ዉስጥ መበዝበዝ”በሚል
መርህአዉሮፓዊያን ፊታቸዉን ወደ አፍሪካ አዞሩ፡፡ በኢንዱስትሪ አብዮት መጎልበት ምክንያት የባሪያ ንግድ ከጥቅሙ
ጉዳቱ ስላመዘነባቸዉ “ነጻ ንግድ”በሚል ሽንገላአፍሪካዊያን ጋር አሳሳችና አዘናጊ ስምምነቶችን እየተፈራረሙ
እግራቸዉን በአፍሪካ የጠረፍ ግዛቶች ተከሉ፡፡ ወቅቱ በአህጉረ አዉሮፓ አዳዲስና ጠንካራ ብሄራዊ መንግስታት (ጀርመንና
ጣሊያን) የተመሰረቱበትና ወደ ቅኝ ገዥነትፉክክርና ዉድድር የገቡበት ጊዜም ስለነበር የአፍሪካን ቅርምት (scramble of
Africa) አፋጠነዉ፡፡

ለስዊዝ ካናል ግንባታ በፈረንሳይና እንግሊዝ የፈሰሰዉን ግዙፍ እንቨስትመንት የመክፈል አቅም ያጣችዉን ግብፅን በ 1882
ያስቀደመዉ ያፍሪካ ቅርምት፤ በአራቱም የአህሪቱ ክፍል በጣም ፈጣን በሆን ሁኔታ ፉክክሩ ተጧጧፈ፡፡ ቅኝ ገዥዎችንም
ወደ እርስ በእርስ ግጭት አስገባቸዉ ፡፡ ይህም የበርሊን ጉባኤን(1884-5) ወለደ፡፡ ከጉባኤአቸዉ ማግስት በጉባኤ ዉሳኔ
አንቀጽ 34 መሰረት ቅርምቱ እንዳሰቡት ሰላማዊ ሊሆን ባለመቻሉ፤ ሕይወትንና ንብረትን በጠየቀዉ የሀይል እርምጃ
መላ አፍሪካን በ 1900 ተቀራምተዉ አጠናቀቁ፡፡ እነሆ ታላቋ ሃገራችን ከዚህ ቅርምት ዳነች፤ በታምር ሳይሆን አደዋ ጦር
ሜዳ ላይ በተከፈለ የንብረት፣ የአካል፣ የደምና የሕይወት መስዋዕትነት፡፡

አዉሮፓዊያን “ነጻ ንግድ”የሚሉትን ሽንገላ ገሸሽ አድርገዉ“አፍሪካን በአፍሪካ ዉስጥ መበዝበዝ”መርሃቸዉን አዉን
ማድረጉን ተያያዙት፡፡ በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲአቸዉ የጥሬ ዕቃ፣ የርካሽ ጉልበትና የሸቀጥ ማረገፊያ ገባያ ፍላጎትና ጥም
አረኩባት፡፡ ጣሊያንም ይህንኑ ለማግኘት ስትል በሰ/አፍሪካ በዋናነት በአፍሪካ ቀንድ ላይ ትኩረቷን ኢትዮጵያ በማድረግ
ስትራወጥ ነበር በተባበረ የሃብሾች ክንድ የተደቆሰችዉ፡፡ በአድዋ ሽንፈት ምክንያትም የአዉሮፓዊያንመዘባበቻ፣ የዜጎቿን
በቁጣ የገነፈ አመጽ ማስተናገጃ ሂነች፡፡

ዓድዋ የኢትዮጵያ ወይም የአፍሪካዊያን ድል ብቻ ሳይሆን የመላዉ ዓለም ጥቁር ህዝቦች ኩራትና ክብርን ያጎናተፈ፣
የሰዉ ልጆችን

(የነጮችና ጥቁሮችን) እኩልነትን ያረጋገጠና ለሰባዊ መብቶች መከበር ህያዉ ቀንዲል ያቀጣጠለ ድል ሆኖ በዓለም በታሪክ
የተመዘገበ ሉላዊ ሃብት/ እሴት ነዉ፡፡የዘንድሮዉ የ 125 ኛ አመት የአድዋ ክብረ በዓል አከባበር ምናልባትም እስከዛሬ ታይቶ
በማይታወቅ መልኩሃገራዊ፣ አህጉራዊና ሉላዊ ትኩረት ተሰጥቶት እየተዘከረ ይገኛል፡፡ የበጌምድር መም/ራን ትምህርት
ከሌጅ የማህበራዊ ሳይንስ ትም/ት ክፍልም የአገርህን ዕወቅ ክበብም ዝክረ አደዋን ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ
ለመዘከር ለፓናል ዉይይት በሚያመች ሁኔታ በሚከተሉት ነጥቦች ዙሪያ አጫጭርመነሻ ሃሳቦችን እንዲህ ያቀርባል፡፡

3
የ 125 ኛ ዓድዋ ክብረ በዓል ለፓናል የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮች (ዋና ዋና ጭብጦች)

1. ቅድመ- አደዋ ታሪካዊክስተቶች፡-

 የአድዋ ጦርነት ምንነትና የማንነት ጉዳይ፣

 ቅድመ ዓድዋ ታሪካዊ ሁነቶች

 መሰረታዊ የጦርነት መነሻ ምክንያቶች (Basic Causes)


 ቅጽበታዊ/የቅርብ መነሻ ምክንያተች (Immediate Causes)

2. የአደዋ ጦርነት ሂደት (The Course of the War)

3. ድህረ አደዋ (የአደዋ ድል ዉጤቶችና ፋይዳቸዉ) /Consequences & Significances of the War)

4. ከአድዋ የምንማረዉ ምንድን ነዉ (Lesson of Adwa)

5.ከዓድዋ እንዳንማር የጠጋረጡብን ተግዳሮቶች ምንድን ናቸዉ

1. ቅድመ- አደዋ ታሪካዊክስተቶች፡-


1.1. የአድዋጦርነትምንነትናየማንነትጉዳይ
 ምንነት፡-
 የህብረ ብሔራዊ አንደነት ዓርማ ፣
 የነጻነት ቀንዲል፣ ሉዓላዊነታችን ያረጋገጠ የጀግኖቻችን የመስዋዕትነት ዉጤት
 ኩራታችን ፣ክብራችን፣ አንድነታችን ፣ማንነታችን …
 ሰንደቃችን ከፍ ብሎ እንዲደምቅና እንዲዉለበለብ ያደረገ፣ የአይበገሬነት ምልክት፣
 ዉስጣዊ የሐሳብና የፍላጎት ልዩነትን አጥፍቶ ጠንካራ የሥነልቦን ዉቅር የፈጠረ፣

 እዉነተኛዉ የሃገር ፍቅር ስሜን የሚያንጸባርቅ ህያዊና ታላቅ እሴታችን


 ዘመን ተሸጋሪ ሁለመናችን ነጋሪ ነዉ ፤ዓድዋ … ወ.ዘ.ተ ፡፡

 ዓድዋ የማን ነዉ፡.


 የዓድዋ ጦርነት በጣሊያንና በኢትዮጵያ መካከል የተካሄድ የአንገዛም ባይነትህጋዊ (Just War) ጦርነት ነዉ

4
 ለአፍሪካና ለዓለም ጥቁር ሕዝቦች የፀረ ዘረኝነትና የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግሎች ምሳሌ
 ̋ Where ever we go wu have a machine gun ….˝ የትም ብንሔድ እኛ መትረየስ አለን፤ እናሸንፋለን የሚሉትን
የነጮች ትምክህት ያኮላሸ፣

 የሰዉ ልጅ እኩልነት በዓልም በተግባር ያሳየ፣ የሰባዊ መብት ዘላለማዊ ጠበቃ ነዉ አድዋ፡፡
 አድዋ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካና የአልም ጥቁር ሕዝቦች ክብርና ኩራት የሆነ አንጸባራቂ፣ ዘላለማዊና ሕያዊ
የሆነሉላዊ እሴት ነዉ፡፡ … ወ.ዘ.ተ.

2. የዓድዋ ጦርነት መሰረታዊመነሻ ምክንያቶች

ሉላዊና ምክንያቶች፡-
 የሰሜንና የአፍሪካ ቀንድ የንግድ መስመር መዘጋትን ተከትሎ የአዉሮፓዊያን አሰሳና ግኝት መጀመር
 ዘመናዊ እርሻ /በካቢያንና ሰሜን አሜሪካ/ መጀመርና የሰዉ ጉልበት ፍላጎት፣
 የባሪያ ንግድ መፋጠን /ትራይአንጉላር የባሪያ ንግድ/- አፍሪካ- አሜርካ- አዉሮፓ
 የኢንዲስትሪ አብዮትመፈንዳትና ዕድገት፣
 የጨለማዉ አህጉር ፣በተለይም የምስራቅ አፍሪካ ተፈላጊነት መጨመር
 የኦቶማን ቱርክ መዳከምና የግብጽ መጠናከር፣
 በ 1869 የስዊዝ ቦይ መከፈትና ጠቀሜታዉ
 የአዉሮፓዊያን ስለአፍሪካ ያላቸዉ አመለካከት መለወጥ ፟አፍሪካን በአፍሪካ ዉስጥ መበዝበዝ ፟
 የባሪያ ጉልት አላስፈላጊነት መከሰት/ የነጻ ንግድ ስምምት መጀመር
 የኢንዱስትሪ አብዮትመጎልበትና ፍላጎት መጨመር (ጥሬ ዕቃ፣ ገባያና ርካሽ ጉልበት)
 አፍሪካን ለመቀራመት መሯሯጥ መጀመር፣
 ወኪሎቻቸዉ፡- አሳሾች፣ የንግድ ኩባንያዎች፣ ሰባኪዎች፣ የጂኦና ሳይንስ ቡድኖች፣ ወታደራዊ ሃይሎች…..
 የበርሊን ጉባኤ (1884-85) - አንቀጽ 34
አህጉራዊ ምክንያቶች፡-
 የኦቶማንን መዳከም ተከትሎ- የግብጽ ነጻነት መረጋገጥ (መሐመድ አሊ-1805)
 የመሐመድ አሊ የግዛት ማስፋፋት ፖሊሲ ትግበራ እስከ አባይ ምንጪ….
 በምዕ/ በሱዳን- መተማ- እነደጃዝማች ክንፉ ሃይሉ፣ ካሳ ሃይሉ /ደባርቂ….

 በዘመነ ዮሐንስ 4 ኛ፡- -በ 1887 ተ/ሃይማት መተማ ላይ ድርቡሽን ድል አደረገ፣


- ጥር 1/1888 ግን ደንቢያ ላይ በአቡ አንጃ መሸነፍ
 በምዕ/በሱዳን- ወለጋ- እነራስ ጉበና / ነጆ- ጉቴ ዳሊ……
 በምስራቅ- በቀይ ባህር በኩል (በ 3-ግንባር)፡- - በ 1875 በሰ/ምዕስራቅ- በምጽዋ ግንባር/ ጉንደት
-1875 በምስራቅ- በታጁራ ግንባር

5
-በደ/ምስራቅ- በዘይላ ወደብ - ሐረር
-በ 1876 በሰ/ምስራቅ- ምጽዋ- ጉርኣ ግንባር
 የሕይወት ስምምነት (1885)- የመተማ ጦርነት(1889) እና የጣሊያን ከሰያዓቲ ወደ አስመራ መገስገስ፣
 የጣሊያን አፍሪካ ቀንድ እግሯን ማስገባት፡- -በ 1838 ጁሴፔ ሰፔቶ አሰብን መግዛት
- በ 1869 የአሰብ ለጣሊያን መርከብ ድርጅት መተላለፍ

-በ 1882 ለጣሊያን መንግስት ስር መሆን (Protectorate Zone)

-የካቲት፣ 1885 በእንግሊዝ ፈቃድ ምጽዋን ማግኘት

 የኢትዮ- ጣሊያን የመጀመሪያ ግጭት መከሰት (ዶጋሊ 1887)፣


 የጣሊያኖች የምንሊክን ጓደኝነት በጥብቅ መፈለግ ፣
 በ 1890 የኤርትራ በጣሊን ስርመዋል፣

ሱዳን- መሐዲስት- ጎንደር ጣሊያን- ሰዓቲ

ዮሐንስ 1888

ምንሊ
ክና
/
ተ ሃይ
ማት

6
ሀገራዊ ምክንያቶች
 የዘመነ መሳፍንት(1769- 1885)ዉርስ (Legacy of Zamane Masafnt)
 የደ/ቴዎድሮስ- ካሳ ምርጫ፣ ሌሎች የአካባቢ(1855- 1868)
 ካሳ ምርጫና ተ/ጊዮርጊስ፣ ምንሊክና ተ/ሃማት (1872-1889)
 ምንሊክ እና ተ/ሃይማኖት (1882) እምባቦ፤
 የታላቁ ርሃብ በኢትዮ . (1882- 1892)
 የእንስሳት ወረርሽን በሽታ፣ የአንበጣ ወረራ፣ ድርቅና የፈንጣጣ ወረርሽን መከታተል፣
 የምነልክ ጉዳቱን ለመቋቋም የግዛት ማስፋፋ ፍጥነት መጨመርና ዉጤቱ (ወላይታ)
 ቅጽበታዊ/የቅርብ መነሻ ምክንያተች (Immediate Causes)

ሀ. የጣሊያንና የምንሊክ ይፋዊ ግንኙነት፡- (አዎንታዊና አሉታዊ ጎንነበረዉ)

 1876 በኦ. አንቲኖሪ የተመራ የጂኦግራፊ ማህበረሰብ መምጣት (ስዉር የቅኝ ግዛት ተልዕኮ ይዞ የመጣ) ፣
 በኋላ ….. ላበረከተዉ አስተዋጽኦ የዩኬ ሮያል ካምፓኒ ተሸላሚ የሆነ
 1882 የካ.ፔ. አንቶኖሪ /የጣሊያን ተወካይ/ መምጣትና ልዩ ልዩ ስምምነቶች መፈረም
 ግንቦት 21፣1883፣ የወዳችነትና የንግድ ስምምነት (ይዘቱ፡- የቆንስላ ልዉዉጥ፣ ነጻ ንግድና የዜጎች እንቅስቃሴ፣ ነጻ
ሃይማኖታዊ ስብከት- 17 ኛዉ ክ.ዘ.)

ለ. የዶጋሊ ግጭት 1887

 1887 የገለልተኝነት ስምምነት መፈረም (ጣሊያኖች ከዮሐንስ ጋር ሲጋጩ እነዳያግዝ፣ መሳሪያ ሊሰጠዉ)
 ግንቦት 2፣ 1989 የዉጫሌ ዉል መፈረም/ 20 አንቀጽ…..)
 ወቅቱ በ 1887 ጣሊያኖች ምንሊክ እንዳስፈለጋቸዉ ሁሉ፣ ምኒልክ ከእነርሱ በላይ በ/የፈለገበት ነበር፣
 ምክንያቱ ዮሐንስ 4 ኛ ጎጃምን እንዳጠቃ እኔንም ያጠቃኛል የሚል ስጋት ነዉ፣
 ይህ ዉል የኢትዮ-ጣሊያን ግንኙነት ከ/ደረጃ እንደደረሰ ያስመሰለ፣
 የኢትዮ- ጣሊያን ወዳጅነት ማብቂያ መጀመሪያ ያደረገ ዉል፣

ሐ. የዉጫሌ ስምምነት አንቀጽ 3 እና 17 የተፈጠረዉ አለመግባባት፣

7
 አንቀጽ 3- ድንበር ነክ ይዘት ያለዉና ከ 1890 በኋላ ለጣሊያንን የኤርትራ ይዞታ ያረጋገጠ፣

 በጥር 1፣1889 የኔፓልስ ስምምነት የተጠናከረ ˝̋በጠጨባጭ የተያዘ̋̋˝የሚል ሐረግ በመጨመር….

 በ 1890 የኤርትራ ቅኝ ግዛትነት በጣሊያን በታወጅ

 አንቀጽ 17፣ የዉጭ ግንኙነት ….. የአማርኛዉና የጣሊያንኛዉ ትርጉም ልዮነት፣


 አማርኛዉ፡- ˝የኢትየ. ንጉሰ ነገስት ከአዉሮፓ ነገስታት ጋር የሚያደርገዉን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት
አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል፡፡̋
 ጣሊያንኛዉ፡- ˝የኢትዮ. መንግስት ከዉጭ አገር መንግስታት ጋር የሚያደርገዉን ግንኙነት በኢጣሊያን
መንግስት በኩል ማድረግ ይገባቸዋል፡፡˝

 የአጼ ምኒልክ አቋም፡- ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አጠንክረዉ ቀጠሉበት፣


 ለጣሊያኑ ንጉስ ኡምቤርቶ፣ ጣሊያኖች ሳያዉቁ ለእንግሊዝና ፈረንሳይ መንግስታት ደብዳቤ(1891) ላኩ፡፡
 የአዉሮፓዊያን ምላሽ፡- ….. ግንኙነት ማድረግ የሚቻለዉ በዉጫሌ ዉል መሰረት ነዉ የሚል ነበር፡፡
በዚህ ምላሽ የጣሊያንን ተንኮል ዘግይተዉም ቢሆን ተረዱ፣
 የጣሊያን አቋም፡ 1. በበርሊን ጉባኤ ዉሳኔ አንቀጽ 34 መሰረት አዉሮፓዊያንን ማሳመን ቀላል ነበር፣
2.ኢትዮጵያን በማግባባትና በማማለል፣ በበላይነት ስሜትና በማስፈራራት ለማሳመን መጣር ግን ቀላል አልነበረም፡፡

ሀ. የማግባባት ፖሊሲን (Persuasion Policy)- የአንቶኖሊ መስመር - በምኒልክ ዉጫሌን (1893) መሻር ከሸፈ፣

ለ. የመከፋፈል ፖሊሲም (Subversion Policy)- የባራቴሪ መስመር እንዲሁ ፣

 ዋና ዓላማ፡-
 በ 1887 ምንሊክ የሐንስ ላይ የፈጸሙትን ምንሊክ ላይም ለመተግበር መሞከር ነበር፡፡
 በዳ/ምኒልክ ላይ ቁርሾ ያላቸዉን የአካባቢ መሳፍንትን መኳነትን(የትግራይ ገዥዎችን) በማሳመን ጎናቸዉ ማሰለፍ፣
 ጥሩ ምሳሌ፡- የ 1891 ዱ የመረብ ስምምነት ይጠቀሳል፡፡ (ራስ መንገሻ ዮሐንስ፣ ፊ/ስዩም፣ ደጃ/ መሸሻ ወርቁ)
 ግን ጅምሩ ላይ የተሳካ ይመስል የነበረዉ የመረብ ስምምነት ሰኔ 1894 በነራ/መንገሻ ወደ አ.አ. መሄድ ከሸፈ፤
 ታህሳስ 1894 በደጃ/ባህታ ሐጎስ የተመራዉ የኤርትራ ገበሬዎች አመጽ….. (ከመሬት የማፈናቀል ፖሊሲም ችግር )

 የአድዋዋዜማልዩነቶችበሃገርፍቅርስሜትናበምኒልክየአመራርጥበብ.ሲከሽፉ፣
የጣሊያን የአድዋ ዋዜማተስፋ የሰንቃባቸዉ የነበሩ ዉስጣዊ ልዩነቶች፡-
 ምኒልክ እና- ራስ ሚካኤል ---ወሎ
 ንጉስ ተ/ሃይማኖት- ከጣሊያኖች ጋር ግንኙነት ማድረጉን ምኒልክ እንዳወቀ፡-
̋ …. ላተ ብዙ አላዝንም፤ ግን ብዙ አድባራት ያለበት ሀገር ያሳዝነኛል፤ በቅርቡ መጥቼ አመድ አደርግሃለሁ፡፡˝የሚል መልክት ላከበት
 ራስ መንገሻ ዮሐንስ------ ትገራይ፣ በራ አሉላ ማግባባት በራሱ u ጊዜ የተመለሰ፣
 የአዉሳ (ደንከል) ሱልጣን በሻምበል ፔርሲኮ አማካኝነት በርከት ገንዘብና መሳሪያ የተሰጠዉ፤

8
 በምትኩ 20 ሺ ጦር በምኒልክ ላይ የሚዘምት እንዲመለምል የተጠየቀ- በራሱ ጊዜ ለምኒልክ ያደረ፣
 ራስ መኮነን ወ/ሚካኤል------ ሐረር (በዳ/ምንሊክ ዕዉቅና….)
 ራስ ስብሃትና ደጃ/ሐጎስ- ከአድዋ 2 ሳምንት ቀድመዉ ከ 600 ጦር ጋር ወደ ምኒልክ በራሳቸዉ ጊዜ የገቡ፣
 የእነራስ ስብሃት አቋም (Though we eat their money, we will not fight our country & our king) ክንፈ አ. 157.

መ. የጣሊያኖች መኩራራትና ኢትዮጵያን አሳንሶ ማየት (ንቀት)

 ˝ኩራት ዉድቀትን ይቀድማል̋ እንዳሉት ፈላስፎች


 የዳ/ምኒልክ የክተት አዋጅ ጭብጦች እና ቀድመ ዝግጅት

“…….ይቅርታ አድርግልኝ፡፡
ሀገርናሃይማኖትየሚያጠፋጠላትባህርተሸግሮመጥቷል፤እኔምያገሬሰዉመድከሙንአይቼእስካሁንብታገሰዉምእያለፈእ
ንደፍልፈልመሬትይቆፍርጀመር፡፡አሁንግንበእግዚአብሔርእርዳታአገሬንአሳልፌአልሰጠዉም፡፡
ያገሬሰዉጉልበትያለህበጉልበትህ፣ጉልበትየሌለህበፀሎትህ፤ለልጅህ፣ለሚስትህ፣ለሃይማትህስትልዕርዳኝ፡፡
ዘመቻዬጥቅምትላይነዉናየሸዋሰዉበጥቅምትወርወረኢሉከተህላገኝህ፡፡
ወስልተህየቀረህእንደሁማሪያምንትጣላኛለህ፡፡” (እ.ኤ.አ. መስከረም 17፣ 1895)
ሀ. ይቅርታ - የረቀቀ ዲፕሎማሲ

ለ. አንድነት/ ህብረት - ሃገራዊ ሉዓላዊነትን በጋራ ማስከበር

ሐ. ማስጠንቀቂያ- ግዴታና ሃላፊነት

2. የአደዋ ጦርነት ሂደት (The Course of the War)

 የጣሊያን የመጨረሻዉ አማራጭ ፖሊሲ ትግበራ (ወታደራዊ ቴክኖሎጂ)-አደድዋ ላይ የከሸፈ

 የዳ/ምኒልክ ለማይቀረዉ ጦርነት ዝግጅትና ዉጤታማነት


 በዉጫሌ ዉል አንቀጽ 17 ዉዝግብዲፕሎማሲያዊ ጦርነትን እያካሄደ፣ ለጦርነትም ይዘጋጅ ነበር፣
 በአገር ቤት…. ልዩ ታክስ በበሬ 1 ጠገራ ብር በመጣል፣2 ሚልዮን ብር እና የምግብ እህል ክምችት … ፣
ከ 1887 ስምምነት ካገኘዉ ጦር መሳሪያ በተጨማሪ 100 ሺህ በላይ ካራቢነር ጠመንጃ ገዝቷል፣/200 ሺ/
 በዉጭ፡- ጠንካራ ዲፕሎማሲን መሰረተ-
ሀ. ከጁቡቲ - አዲስ አበባ የባቡር መስመር ግንባታን ለፈረንሳይ ሰጠ፣
ለ. ወደ ሩስያ የዛሩ መንግስት አንድ ሉክ በመላክ ጠንካራ ግንኙነት ፈጠረ፣
 ዳ/ምኒልክ ጦርነቱን ፈጥኖ ለመጀመር አልፈለገም ነበር፡- (Lobby group- ፊ/ገበየሁ፣ ን/ጣይቱ….)
 100 ሺ ጦር - ወረኢሉ ከቷል፣
 ካረበኞቹ ፈረሶች በላይ የሚሆኑ አጋሰሶች (ስንቅና ትጥቅ ማጓጓዣዎች)

9
 በንግስት ጣይቱ በኩል የተደረገ ዝግጅት፡-ጦርነቱ እንዲጀመር ከማግባባ ባሻገር
 ከ 20 ሺ በላይ ሴቶችን በማሰባሰብ ምግብና መጠጥ፣ የመመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁስ፤
 ባህላዊ መድሃኒቶች፣ የቁስል መጠገኛ፣ ካምብ ጠባቂዎችና የባህል መድሃኒት አዋቂዎችን አዘጋጁ፣
 ጦሩ በሰ/ኢትዮጵያ ሲያልፍ በእንክብካቤ እያሳደረ ስንቅ እየሰነቀ እንዲያሳልፍ አዘዙ፣
 በመጨረሻም 5-209 20-30 ሺ) ሺህ ጦር እየመሩ ወደ ግንባር ዘመቱ፣ 1200 ሤት ተዋጊ ዘማችች ነበሩ፡፡
 የጦሩ አሰላለፍ፡- በጦርነቱ ማግስት ጸሐፍት ምን አሉ፡-
˝ ….. ምኒልክ ያለጥርጥር የላቀ ብቃት ያለዉ ፖለቲከኛ፣ አርቆ አስተዋይና አቻ የሌለዉ ፖለቲካን የማሽተት ተሰጥኦ
የታደለዉ የጣሊያንን መስፋፋት በዝምታ ይቀበላል የማይባል ሰዉ ነበረ፡፡ …. እስከዛሬ ድረስ ያሳየዉ
መለሳለስለታክቲክ ብቻ እንደነበረ ተረጋገጠ፡፡̋ (Anderzie Bartiski &Y.Mantiel Niyechiko, The History
of Ethio., p.340- Alemayehu Abbebe)
 ባራቴሪ፡- ሰኔ 1894 ወደ ሮም በመሄድ ለፓርላማዉ ባሰማዉ ድንፋታ˝ ምኒልክን ለማሸነፍ ብዙ ዕርዳታ አያሻኝም ̋

3. የአደዋ ጦርነቶች፡-
 አድዋ የአንድ ጊዜ ብቻ ጦርነት አይደለም፣
 የኢትዮ- ጣሊያን ጦርነት (1894-1896) ጀምሮ ይጠናቀቃል፣
 ታህሳስ 1894 የጣሊያን ጦር ድንበር ጥሶ ገባ፣
1. የቆአቲትና ሰናፌ ጦርነት (ጥር 14/ 1895)፡
የራስ መንገሻ እና የባራቴሪ ጦር ከአምባላጌ በፊት ገጠሙ- ድል የመንገሻ ነበር፣
በጀ/አርሞንዲ የተመራ ጦር መጣና ጦርነቱ ተፋፋመ፣
ስለመሸ ዉጊያዉ ቆመ፤ በማግስቱ መንገሻና ራ/አሉላ ወደ ሰናፌ አፈገፈጉ፣
የጣሊያ ጦር የእነመንገሻን ቀጠና በሙሉ ይዞ ፣ ወደ አዲግራት ገሰገሰ፣
ምንሊክ ለባራቴሪ ጦሩን እንዲያስወጣ ጠየቀ፣
ባራቴሪ በንቀት ጦሩ- ወደ ደቡብ ገፍቶ መቀሌ እንዲገባ አዘዘ፣ መስከረም 1895 መላ ትግራይን ያዘ፣
ሻ/ቶሴሊ- ግስጋሴዉን ገቶ የመቀሌና የአምባላጌን ግንባር አጠናከረ፣

2. የአምባላጌ ጦርነት (ታህሳስ 1895)

 ደ/ትግራይ አምባላጌ ላይ ፊ/ገበየሁ እና ሻ/ ቶሴሊ ተጋጠሙ


 ድል የኢትዮ. - ዉጤት፡-
 በኢትዮ. በኩል በጣሊያን በኩል
 የመጀመሪያዉ ታላቅ ድል ተደርጎ ተወሰደ፣ - ሻለቃዉን ጭምሮ 2 ሺ ወታደሮች ሞቱ
 200 ሞት- 300 ቁስለኛ ነበር፣ - የተረፉ 286 ወታደሮች ወደ መከሌ ሸሹ፣
 ወታደራዊ ድል ብቻ ሳይሆን ፖ/ዊና ስነ ልቦናዊ ፋይዳ… - ድንጋጠ የፈጠረ…..
 የንጉሱን ክብርና የወ/ሩን ሞራል አሳደገ፣ - ተቃራኒ ሁኔታን….

10
 ዉስጣዊ ልዩነት በሃጋረዊ አንድነት ስሜት ተተካ፣ - ባራቴሪ መላ ጦሩን አዲግራ እንዲከት አዘዘ፣
- ትዛዙ ለጀ/አርሞንዲ ሲደርስ የሻለቃዉም ሽነፈት ተሰማ፣
2. የመቀሌ መያዝ- ጥር 7-21/1896 (The Siege of Makkale)
 በራ/ መኮንን የሚመራዉ ጦር ታህሳስ 8/1895 ደርሶ መከሌን ከበበ፣
 የእንዳ እየሱስን ምሽግ ጥሶ መግባት ከባድ ነበር፣
 የንግስት ጣይቱ 900 ጦር ጣሊያኖች ዉሃ የሚያገኙበትን ምንጩን ተቆጣተረ (ብልሃቱ የንግስቲቱ ነበር)
 በጣሊያን በኩል፡- ጄ/አርሞንዲ አዲግራት ገባ፤
 ጣሊያኖች በዉሃ ዕጦት መከሌን እንዲለቁ ተገደዱ፣
 1500 ጦር ይዞ ምሽጉን እንዲያጠናክር የታዘዘዉ ሻ/ ጋሊኖ ምሽጉን በባራቴሪ ትዛዝ ጥር 24/1895 ለቆ ወጣ
 የመቀሌ መለቀቅ በዲፕሎማሲ እንድምታዉ‹-
 ባራቴሪ የጋሊኖ ጦር በሰላም ከወጣ፡- - ጥረ ገንዘብ ለምኒልክ ሊሰጥ፣
- የጋሊኖ ሃይል ለወደፊቱም በዉጊያ እንደማይሰለፍ ቃል ገባ፣
 ምኒልክ ለዲፕሎማሲያዊ ፍጆታ የታሊያን ጦር በሰላማዊ መንገድ እንዲወጣ ፈቀደ፡፡

4.የአድዋ ጦርነት መጋቢት 1/1896)


 ጥቅል የጦርነቱ አሰላለፍ፡-

 በኢትዮ. በኩል በጣሊያን በኩል፡-


 በዳ/ምኒልክ አዛዥነት ስር የነበሩ የጦር መሪዎች፣ - በጀ/ባራቴሪ
 ፊ/ገበየሁ - የመሐል ጦር አዛዥ - ጀ/አልቤርቶኒ-
 ራ/ሚካኤል - ጀ/አርሞንዲ-
 ራ/መንገሻና ራስ አሉላ - ጀ/ዳቦርሜዳ-
 ዋግሹም ጓንጉል - ጀ/ኤሊና- ተጠባባቂ ጦር አዛዥ
 የንግስት ጣይቱ እና የን/ተ/ሃይማኖት አማካሪ ጦር -
 የኢትዮ. ኦ.ተ.ቤ.ክ/ያን- ቅ/ጊዮርጊስ ታቦትን ይዛ ዘምታ ነበር፡፡
 ከመሳሪያና ትጥቅ አንጻር፡-
 በኢትዮ. በኩል በጣሊያን በኩል
 100 ሺ የሰዉ ሃል ከተራ መሳሪያ ጋር 56 ዘመናዊ መድፍ የጫኑ ታንኮች ከ 20 ሺ የሰለጠነ …

60 ሺዉ የተሸለ መሳሪያ ያጣጠቀ -በሰለጠኑ አዛዥዎች የሚመራ ዘመናዊ ትጥቅ ያለዉ

 የስነ ልቦና ዝግጅት፣ ቁርጠኝነት፣ የመልካ ምድር ዕዉቅና -የላቀ የስልጠና ዝግጅት ግን የመረጃ ዕጦት..
 ጠላቱን ኣሳንሶም አግዝፎም ያላየ በሃገር ፍቅር የዋጀ.. ጠላቱን ዝቅ አድረጎ የሚደነፋ፣ የሚፎክር…
 የሁለቱም ወገኖች የ 2 ሳምንት የምሽግ ቆይታ ስጋትናእንተለጀንስ

11
 በምኒልክ ባራቴሪ
 ትዕግስት በማጣትና ስንቅንም በመስጋት ለመጀመር ተነሳሳ፣ - በትንስ ጦር ትንኮሳ ጠላቱን ለማስቆጣት ሞከረ
 ሠራዊቱ ከምሽግ ቀድሞ እንዳይወጣ ራ/መንገሻና አሉላ… - የባሻ አዉአሎምን መረጃ አምኖ ተቀበለ፣
 በሻዉ ለሁለቱም የሚሰልሉ በመምሰል ሃገራቸዉን ያስቀደሙ -የኢትዮ ጦር በበዓል እንደማይዋጋ ለባራቴሪ አሳመኑ፣
 ከፊ/ገበየሁ ጋር የራ/ሚካኤል፣መንገሻና ዋግሹም ጦር ዝግጁ ነበር፣ - ዕሁድ መጋ 1/1896 ከንጋቱ 11፡32 ደቂቃ ጀመረ፡፡
-የጀ/አርቤርቶኒ ጦር በፊ/ገበየሁ ግንባር ጥቃት ሰነዘረ፣
 ፊ/ገበየሁ- ጎራዴዉን መዞ ወደ ዋናዉ የጦር ሜዳ ተወርዉሮ ገባ -ልበሙሉን ጀግና በጥይት መተዉ ገደሉት፣
o ጦሩ የመሪዉን አስከሬን ይዞ አፈገፈገ፣ - አርቤርቶኒ ወደፊት ለመግፋት ዕድል ተከፈተልን ብሎ..
o ደጃ/ባልቻ ክፍተቱን ለመሙላት እየፎከረ ገባ፣ - ከባራቴሪ እርዳታ ጠየቀ፣ አልደረሰለትም፣
o በ 1878 ጀምሮ የምኒልክ መድፍ ጠባቂ የነበረዉ ጀግና የታሊያንን ታንክ በጎራዴዉ ማርኮ የአርቤርቶኒን ጦር አተረማመሰዉ፡፡
እንዲህም ተብሎ በጦሩ ሞራል ሰጪ አዝማሪዎች ተገጠመለት፡
̋ገበየሁ ቢሞት ተተካ….. ባልቻ፣
መድፍ አገላባጭ….. ብቻ ለብቻ፡፡˝እኔም ባንድ ወቅት የድርሻን…..
ጥይት ቢያልቅበት …መች ቆመ ፈዞ፣
ከወገቡ ላይ …ጎራዴ መዞ፣
የነጭ ጠላቱን … አነገት ጠምዝዞ፣
እንደ ጦስ ደሮ …ጥሎ- ቀንጥሶ፣
ታንኩን ማረከዉ … ባልቻ አባ ነፍሶ፣
የገበየሁ ደም መች ቀረ …ፈሶ፡፡
(አልኩት- በ 1978-አድዋ-ወሊሶ)
 የባራቴሪ ዕዞችና ዉጤታቸዉ፡-
 ለጀ/አርቤርቶኒ- የጀ/አርሞንዲ ጦር ፈጥኖ እንዲደርስለት፣ የጀ/ዳቦር ሜዳም እንዲጠጋ ታዘዘ፣
 በልዩ ልዩ ችግሮች (መልካምድር፣ የተሳሳተ የካርታ ንባብ፣ የመረጃ ዕጦት…) ፈጥነዉ መድረስ አልተቻላቸዉም፣
 ከጀ/ኤሊና ፣ቀጥሎም ከጀ/አሪሞንዲ ጋር መገናኘት አቃተዉ፣
 4 ቱን ብረጌዶች በስህተት አራርቆ መመደቡን የተረዳዉ ከስንፈቱ በኋላ ነበር፡፡(ባሻ አዉአሎምንና አጋሮቹን ያስታዉሷል)
 የኢትዮ. ጦር፡-
 የፊ/ ገበየሁ ጦር ፈጥኖ በመረጋጋት የአልቤርቶኒን ሃይል ገጠመዉ፣
 አልቤርቶኒ እዝ ስር የነበረዉ የጣሊያ ጦር 4፡00 ሰዓት ላይ ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ፡፡ እርሱን ጨምሮ፣/ መድፎቹ/
 አርቤርቶኒ በቅሎዉ በጥይት ሲመታ መሬት ላይ ተዘረረ፣ የኢት. አርበኞች ተወርዉሮዉ እንደ ንብ አረፉበትና ማረኩት
 የኢትዮ. ሃይል በጦር ዜማዎች ደስታና ሐዘኑን መግለጽ ጀመረ፣
 ጣሊያኖች፡-
o ተርበተበቱ፣ ፈረጠጡ፣ ከምረኮ የተረፉት ሌሎች ብረጌዶች ጋር ተቀላቀሉ፣
o ያልተነኩት ክ/ጦሮችም ዜናዉ ሲደርሳቸዉ ባሉበት ሁነዉተረበተበቱ፣

12
4. የአደዋ ድል ዉጤቶችና ፋይዳቸዉ (Consequences & Significances of the War)

 ቅጽበታዊ ዉጤቶች፡-

በኢትዮ. ፡- በጣሊያን…….
 ሞት፡- ከ 4-6 (10 ሺ) ሞት - 6-8 ሺ
 ቁስለኛ 10 ሺ - 2500
 ምርኮኛ‹- የለም - 3500
 ጦር ሜዳ ላይ ከወደቁ ታዋቂ ጀግኖቻችን ጥቂቶቹ፡-
ፊታዉራሪ ገበየሁ- የጀግኖች ጀግና- አርኣያ፣ ደጃ/ መሸሻ፣ ደጃ/ጫጫ፣
ልዑል ዳምጠዉ፡- በሩስያ የኢትዮ. አምባሳደር የነበሩ
ቀ/ታፈሰ፣ ቀ/ገነሜ…… ወ.ዘ.ተ.
 የምኒልክ የርህራሄ ጥግን የሚያሳይ ዉሳኔ፡-
 እጅ የሚሰጡ የጣሊያን ወታደሮች እንዳይገደሉ አዘዘ፣ /አስካርስን አይጨምርም ነበር/
 ለ 2 ቀናት ብቻ ድሉ በደስታ እንዲከበር (ለ 7 ዓመት በሐዘን አድዋ ሳይከበር እንደቆየም ይነገራል)
 ለእግዚአብሔር የምስጋና ሥርዓተ- ቅዳሴ እንዲከናወን - በአቡነ ማቶዎስ አማካኝነት ታዘዘ፣
 በጣሊያን በኩል፡-
 በጋቢት 3/1896 ምሽት ሽንፈታቸዉ ይፋ ሆነ፣
 በሁሉም ከተሞቻቸዉ የአፍሪካ የቅኝ ግዛት ፖሊሲአቸዉ ላይ የተቃዉሞ ሰልፍ ተደረገ፣
 ጠ/ሚ ክሪስፒ ስልጣን ለቀቀ፣
 በባራቴሪ ምትክ ጀ/አንቶኒዮ ባልዴሴራ ተሾመ፣
 የአድዋ አንጸባራቂ ድል ተከታታይ ዉጤቶችና ፋይዳዉ
 ከበርካታዎቹ ዉጤቶች ዉስጥ 10 ሩንጠቅለል አድርግን እናንሳ፡-
1. የኢትዮ. ሉዓላዊነት መከበር
 ጥቅምት 26 1896 ከ 6 ወር በኋላ የአዲስ አበባ ስምምነት መፈረም፡- ይዘቶቹም፡-
 የዉጫሌ ዉል በይፋ ተሰረዘ
 የኢትዮ- ጣሊያን ጦርነት በይፋ ቆመ፣
 ጣሊያን ከ 17 ሺ ሊሬ በላይ የቶር ካሳ እንድትከፍል ተወሰነ፣
13
 የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ተከለለ (መረብ- በለስ-ሙና ወንዝ መለስ)
2. በ 1900 መላ አፍሪካ በቅኝ ግዛት ስር ሲገባ የኢትዮ ፍጹም ሉዓላዊነትና ነጻነት በመላዉ ዓለም ታወቀ፣

3. በአዉሮፓ ጥልቅ ድንጋጤን ፈጠረ

 The outcome of the battle of Adwa produced a profound shock over Europian power…
 የሰለጠነዉ የአዉሮፓ ሃይል በአፍሪካዊዉ ጥቁር መሪና ሠራዊቱ መሸነፍ እዉነተኛና ጥልቅ ድንጋጤን መፍጠሩ…
 በሃገረ ጣሊያን አመጽ አቀጣጥሎ የሥልጣን ሽግሽግ እንዲፈጠር አደረገ፣
 የምሥ/አፍሪካ የጣሊያን ጦር አዛዥና የድዋዉ ኮማንደር ጀ/ ባራቴሪ ለፍርድ ቀረበ፣

4.የእንግሊዝ ስጋትና የፖሊሲ ለዉጥ -በሱዳን አስከተለ

 እንግሊዝ በአድዋ ድል የተነቃቁትና የተጠናከሩት መሐዲስቶች አገዛዝ ስጋት አሳደረባት፣


 ስጋቷ ፈረንሳይ ከአፍሪካ ቀንድ ተደርድራ ወደ መሐል እንድትገባ ኢትዮ. በር ትከፍታለች የሚል ነበር፣
 በ 1880 ዎቹ የመሐዲስቶች እንቅስቃሴን፣˝ በዝምታ የማየት ̋ ፖሊሲ ይዛ የነበረችዉ እንድትቀይር ተገደደች፣
 በ 1898 መሐዲስቶችን እምድሩማን ላይ በመጨፍጨፍ የአንግሎ- ግብጽ የጋራ አስተዳደር መሰረተች፣
 የእንግሊዝ ስጋት እዉን የሆነዉ በምኒሊክ የዲፕሎማሲ ጥበብ ነበር፡-
 ኢትዮ.- ፍራንስ የሁለትዮሽ ጥቅምን የሚያስጠብቅ ስምምነት ተፈራረሙ፣
 ኢትዮ. ፈረንስይ ወደ ተራንስ አፍሪካ ለምታደርገዉ ወታደራዊ ዘመቻ ሎጂስቲክና መንገድ መሪ…

-ለከሊፋ አብደላሂ ደግሞ አፍሪካዊ ህብረት ፈጥረን እንታገል የሚል ደብዳቤ ጻፈ፣

-ከእግሊዝ ጋርም በተፈራረመዉ የወዳጅነት ስምምነት በመሐዲስቶች ላይ ጫና ለመፍጠር ተስማማ፣

 ዳ/ምኒልክ፡- የሶስቱንም አጎራባች ሃይሎች በዚህ መልክ አለዝቦ፣


 3 ኛ ዙር የግዛት ማስፋፋት ፖሊሲዉን ተገበረ (1896-1900)
 እንግሊዝና ፈረንሳይ ፋሹዳ (1898) ላይ እንዲፋጠጡ አደረጋቸዉ፣
5. አለም አቀፍ አዎንታዊ ተጽዕኖ መፍጠር
 አድዋ የኢትዮ. ብቻ ሳይሆን የመላዉ አፍሪካና የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ነጻነት ክብር ኩራትን ያጎናጸፈ ድል
 ምልክትነቱ ፡- በደ/አፍሪካና በካሪቢያን ሃገራት -ኢትዮጵያኒዝም የሚል ሃይማታዊ እንቅስቃሴ አስጀመረ፣
-ሰ/አፍሪካ ለይም ፡- ሳኑሲዝም፣ በመሃል አፍሪካ-በኮንጎ፤- ኪንባንጉይዝም
-በሰ/አሜሪካ ፀረ-ዘረኝነት ትግልን ….
- የፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብ እንዲጎለብት፣

14
- ቅኝ ግዛት ከአፍሪካ ምድር እንዲጠፋ …..

6. የአዉሮፓን ቅኝ ገዥ ሃሎች አመለካከትና ዓላማ አስለዉጧል

 አንጸባራቂዉ የአድዋ ድል፡-


 የቅኝ አገዛዝን መዕበል የገታና አህጉራዊ ቅርጽና ታሪክን ያስተካከለ፣
 የቅኝ ገዥዎችን ቅስም የሰበረ፣ ተደፍቶ የነበረ የቅኝ ተገዥዎችን አንገት ቀና ያስደረገ፣
 መሪዎችም ሆኑ ነጋዴዎቻቸዉ አቋማቸዉን እንደገና እንዲመረምሩ ያስገደደ፣
 ይንኑ የአመለካከት ለዉጥ የጣሊያን ወዳጅ የሆነዉ (ወገንኛዉ) ጆ. በረክሌ እንዲህ ይገልጸዋል፡፡
̋ ከሰፊዉ የፖለቲካና የታሪክ ትንታኔ አኳያ የዓድዋ ጦርነት በአፍሪካ ምድር አዲስ ሀይል መነሳቱን
የሚያበስር ይመስላል፡፡የዚያች አህጉር ተወላጆች የማይናቅ ወታደራዊ ኋይል ሊሆኑ እንደሚችሉ
ልናሰላስልእንገደዳልን፡፡ እንዲያዉም አሁን ነገሩ አስቂኝ ቢመስልም ይሕ ሁኔታ (አድዋ ማለቱ ነዉ)
ጨለማይቱ አህጉር በላይዋ ላይ ስልጣኗን ባንሰራፋችዉ በአዉሮፓ ላይ የምታደርገዉ አመጽ የመጀመሪያዉ
ምዕራፍ ነዉም ተብሏል፡፡˝
 ይህ ሰዉ ከአድዋ ድል 11 ዓመታት በኋላ በዕዉነት ተገዶ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን አረጋግጧል፡፡
˝ አድዋ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የጥቁር ህዝቦች ድልና ሙሉ በሙሉ ነጮችን ያሸነፈ፤
የ 19 ኛዉን ክ.ዘ. አመለካከት የቀየረና የነጭ የበላይነትን ያስወገደ ድል ነዉ፡፡ ̋
 የወቅቱ ሃያላኖች ጣሊያንን አስቀድመዉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ከነጻዋ ሃገር ኢትዮ. ጋር ጀመሩ፣
 እነርሱም፡- ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ሰ/አሜሪካ፣ ጀርመን፣ቤልጅየም፣ ቱርክና ሌሎችም ነበሩ፣
7. አድዋና የኤርትሪያሁኔታ
 በአዲስ አበባዉ ስምምነት (ጥቅምት 24/1896) ድንበር ክለላ መሰረት የኤርትራን ቅ ተገዥነት ይፋ ማድረጉ…
 የምኒልክ አቋም፡- የሠራዊቱ መድከምና መታመም፣ የተጨበጠ ድልን ቀድሞ ለማስከበርና ለማጠናከር
 የምሁራን የጠለያየ አስተያየትና የኋለናዋ ኤርትሪያ ሁኔታ፡-
 ኤርትሪያ (ባህረ ነጋሽ)፡- - ከአክሱም - 1890 የኢትዮጵያ አካል
-1890- 1941 የጣሊያን ቅኝ ግዛት
- 1941- 1952 የእንግሊዝ አስተዳደር ስር
- 1952- 1953 ከኢትዮ. ጋር በኮምፌዴሬሽን ተቀላቀለች
- 1953 – 1983 አንዷ የኢትዮ. ጠ/ግዛት፣
- 1983 እስከአሁን ነጻ አፍሪካዊት ሃገር ሆነች፡፡
8. አገራዊና አህጉራዊ ወሰን ክለላን እዉን አደረገ (አድስ ካርታ ተፈጠረ)

 የድንበር ኮሚሽን በማቋቋም የወረቀት ላይ ድንበርክለላ ተፈጠረ (Delimitation)


 በሂደት የተፈጥሮ መልካምድሮችን በመጠቀም የወሰን ክለላዉ ለመስራት ተመክሯል (Dimarkation)-ኢትዮ- ኬንያ
 ከሌሎች አጎራባች ቅኝ ገዥዎች ጋር፡-

15
 መጋቢት 1897 ላይ - ኢትዮ-ጁቡቲ - ግንቦት 1902 ኢትዮ.-እንግሎ-ግብጽ
 ሰኔ 1897 ኢትዮ- ከእንግሊዝ (ሰ/ሱማሊ ላድ) - 1907 ኢትዮ- አንግሎ- ኬንያ
 ሐምሌ 1906 ኢትዮ. - ኤርትሪያ - 1908 ኢትዮ- ጣሊያን ሱማሊ ላንድ

9. የአንድ አስርተ ዓመት ፍጹም ሰላምና መረጋጋት


 የዉጭ ወረራ ፣የዉስጥ ሽኩቻ የሌለበት፣
 የአድዋ አርበኞች ለአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት አስተዋጽኦ እያበረከቱ ሰላምን ያጣጣሙበት፣
10. የሳይንስና ቴክኖሎጅ መግባትና መስፋፋት
 ሌላዉ ትልቁ የአድዋ አንጸባራቂ ድል ትሩፋት ነዉ፣ በሃገሪቱ አዳዲስ ለዉጦች በተከታታይ እንዲፈጠሩ አድርጓል፣
 የንግድ ማንሰራራትን ተከትሎ ከአዲስ አበባ ሌላ ከተሞች ተስፋፉ-
 የመንገድ መሰረተ ልማት- የጁቡቲ - ድሬ ዳዋ፣ የድሬ - የአዲስ አበባ፣ የአዲስ አበባ - ናይል
 የዘመናዊነት መስፋፋ፡- የባንክ፣ ትምህርት ቤ/ት፣ ሆቴል፣ ስልክ ፣ ፖስታ፣….. ወዘተ.
 ባቡሩን ተከትሎ የአዳዲስ ሃሳቦች፣ ባህል … ፍሰትና ለዉዉወጥ ….

5. ከአድዋ የምንማረዉ(Lesson of Adwa)


 ብዙ ነበር፤ ነዉም፣

.6 ከአድዋ የሚፈለፈዉን ያህል ለምን መማር አቃተን፣

 በጣሊያን 3 ኛ ዙር ወረራን ስናስብ/ ዶጋሊን አንድ ብለን/


 አንድነት ህብረት ፣ቁርጠኝነትና ሃገራዊ ስነ ልቦናእንደአሁናዊዉ ሲጠፋ እንዲህ ተብሎም ነበር፣
̋ አጥንቱን ልልቀመዉ …መሬቱን ቆፍሬ፣
ጉበናን ከሸዋ…… አሉላን ከትግሬ፡፡˝
˝ሁላችን ተባብረን …. ካረገጥን አንድ እርካብ፣
ነገራችን ሁሉ …የእምቧይ ካብ የእምቧይካብ፡፡̋

16
17

You might also like