You are on page 1of 12

የበጌምድር መምህራን ትም/ኮሌጅ የ 2013 ዓ.

ም የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም አጭር ሪፖርት

1. በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ወቅት የተከናወኑ ተግባራት

 በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ስራ ለመጀመር አስር አባላት ያሉት ግብረ

ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ ተገብቷል

 ግበረሃይሉም የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ሊሰሩ የሚችሉ ተግባራትና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችንና መልካም

አጋጣሚዎችን የመለየት ስራ ተሰርቷል

 የኮሌጁን ግቢ መማሪያ ክፍሎችን፣ ቢሮዎችንና ህንፃዎችን ኬሚካል በመርጨት ከተዋህሲያን የማፅዳት ስራ

ተሰርቷል

 መማሪያ ክላሶችን በአንድ ክፍል በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት የማዘጋጀትና የድልድል ስራም ተከናውኗል

 3 የሙቀት መለኪያ መሳሪያ ከጤና መምሪያ በማምጣት ቀርቧል እንዲሁም ለሚለኩት ሰራተኞች በቂ ስልጠናና

ኦረንቴሽን ተሰጥቷል

 በግቢው በተመረጡ 10 ቦታዎች ላይ የንፅህና መጠበቂያ ውሃ እና ሳሙና እንዲሁም 4 ቦታዎች ላይ በእግር

የሚሰራ የውሃ ማቅረቢያ ከተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በመግዛት ዝግጁ ተደርጓል

 ተቋርጦ የነበረውን የኮሌጁ የዋይፋይ አገልግሎት እንዲጀመር ተደርጓል

 የ 3 ኛ ዓመት ተማሪዎችን ጥቅምት 09/2013 ዓ.ም እና ለ 1 ኛ እና 2 ኛ ዓመት ህዳር 01/2013 ዓ.ም

ትምህርት ለማሳጀመር በኮሌጁ ድህረገፅና ፌስቡክ ጥሪ በማስተላለፍ በ 09/02/2013 ዓ.ም ከጤና ጥበቃ

ባለሙያ በመጋበዝና ዝርዝር ኦረንቴሽን በመስጠት በወቅቱ ትምህርቱ እንዲጀመር ተደርጓል

 በኮረና ወቅት መማር ማስተማሩን እንዴት እናስቀጥለው የሚለውን የምንከታተልበት ደንብ ከደ/ታቦር

ዩኒቨርስቲ አምጥተን ወደ ኮሌጅ ቀይረን በማዘጋጀት ለመምህራንና ለአስተዳደር ሰራተኞች ስለ ትምህርት

አጀማመርና ስለ ቀጣይ ተግባራት ኦረንቴሽን ተሰጥቷል

 በተለያየ ምክንያት በለቀቁና በሌሉ መምህራን የክፍል ድልድል ዳግም እንዲሰራ ተደርጓል

 ለስነ ንፅህና የሚያገለግሉ ግብዓቶች እንዲሟሉ የማድረግ ስራ ተሰርቷል

 የተጓደሉ የስነ ንፅና ግብዓቶች፡- ማስክ ከደ/ታቦር ዩኒቨርስቲ 450፣ ሳኒታይዘር 30 ሊትርና 500 ማስክ ከጤና

መምሪያ እና 200 የእጅ ጓንት ከደ/ታቦር ሆስፒታል ድጋፍ ተደርጎልን የማሟላት ስራ ተሰርቷል

1
 መምህራን በትምህርት ክፍሎቻቸው አማካኝነት የይዘት መረጣ እንዲያደርጉና የምዘና ስርዓቱም ምን መሆን

እንዳለበት በአካዳሚክ ኮሚሽን ተወስኖ ወደ ስራ ተገብቷል

 የግቢውን ሳር በግልፅ ጨረታ እንዲሸጥና በወቅቱ የማስነሳት ስራ ተፈፅሟል

 የ 1 ኛ እና 2 ኛ ዓመት የማታ ተማሪዎች በክረምት መርሃ ግብር ያልወሰዷቸውን ኮርሶች እንዴት በበጀት አመቱ

መሸፈን እንደምንችል ግልፅ አቅጣጫ ተቀምጧል

 የትምህርት ፕሮግራምና ካሌንደር በወቅቱ ተዘጋጅቶና በአካደሚክ ኮሚሽን ፀድቆ የመማር ማስተማሩ ስራ

በወቅቱ እንዲጀመር የማድረግ ስራ ተሰርቷል

2. የስራ አመራር ቦርድ ድጋፍና ክትትል ያለበት ሁኔታ

 ከ 2013-2022 ዓ.ም የኮሌጁን የ 10 ዓመት የትምህርትና ስልጠና የስራ እቅድ እና የኮሌጃችንን በጀት በማፅደቅ

ወደ ስራ እንዲገባ አድርጓል

 በኮረና ወረርሽኝ ወቅት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር ቢሮው አዘጋጅቶ በላው ቸክሊስት መሰረት

የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በአካል ተገኝቶ ሱፐርቪዥን በማረጋገጥና እና እንዲሟሉ በማድረግ ትምህርቱ

በወቅቱ እንዲጀመር አስችሏል

 የኮሌጁን የሥራ ላይ ስልጠና የሥራ ሂደት ምክትል ዲን የሚመለምሉመልማይ ኮሚቴ በማደራጀትና

ምልመላውን በውጤታማ መንገድ እንዲጨርሱ ክትትልና ድጋፍ አድርጓል

 በመልማይ ኮሚቴ የቀረበለትን የተወዳዳሪዎች ውጤት ወደ 80 በመቶ ቀይሮና የራሱን ግምገማ ከ 20 በመቶ

ጨምሮ በማስላት ከ 1-3 ኛ የወጡ እጩዎችን የራሱን ምክረ ሃሳብ በማካተት ለትም/ቢሮ እንዲላክ አድርጓል

 ኮሌጁ የሚገጥሙትን የተለያዩ ችግሮች በቅርበት በመከታተል እና በመደገፍ እንዲሁም ለችግሮች መፍትሄ

በመስጠት አወንታዊ ሚና ተጫውቷል፡፡

 ቦርዱ በበጀት አመቱ 3 ጊዜ ተገኝቶ ውይይት አድርጓል

3. መማር ማስተማሩን ለመከታተልና ለመደገፍ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ

• የ 2013 የትምህርት ካሌንደር የቢሮውን መነሻ በማድረግ በአካዳሚክ ኮሚሽን ፀድቆ ወደ ስራ ተገብቷል

• በ 2013 1 ኛ ወሰነ ትምህርት የሚሰጡ ኮርሶችን በመለየት እንዲሁም በክረምት መሰጠት ሲገባቸው ያልተሰጡ

ኮርሶችን በማካተት እና ከትም/ክፍሎች ጋር በማናበብ ስሊፕ በወቅቱ ተዘጋጅቶ ተማሪዎችን የመመዝገብ ስራ

ተሰርቷል
2
• የ 2012 ዓ.ም የተማሪዎች ውጤት ትንተና ተሰርቷል

• በ 2012 ዓ.ም መመረቅ የነበረባቸውን ተማሪዎች በመደበኛው ወ=235 ሴ=267 ድምር=502 እና በማታው

መርሃ ግብር ወ=488 ሴ=429 ድምር=917 በጠቅላላው በመደበኛውና በማታው መርሃ ግብር ወ=723 ሴ=696

ድ=1419 ተማሪዎችን ማስመረቅ ተችሏል

• የብሎክ ኮርስ በ 100 ደቂቃና የ 2 ኛ ዓመት ተማሪዎች በ 70 ደቂቃ ፕሮግራም በመስራት ክላሱ በወቅቱ

እንዲጀመር የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡ መማር ማስተማሩም በተቀመጠለት መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል

• የስልጠና ክትትልና ድጋፍ ባለሙያዎች የክፍለ ጊዜ ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ ሳምንታዊ ምደባ ተደርጎ መማር

ማስተማሩን እየተከታተሉ መሆኑ

• የስልጠና ክትትልና ድጋፍ ባለሙያዎች የማታ ትምህርት (የትርፍ ሰዓት) ስራን የስራ ክፍፍልና ምደባ ተደርጎላቸው

እየተከታተሉ መሆኑ

• የቅድመ ስራ ላይ ስልጠና ም/ዲን የመደበኛ ተማሪዎችን የክፍል አለቆች ዘወትር እሮብ ውይይት በማድረግ

የመማር ማስተማሩን ሂደት መገምገምና ማስተካከል መቻሉ እንዲሁም የስራ ላይ ስልጠና ም/ዲን ዘወትር ሰኞ

የክፍል ተወካዮችን የማወያየት ስራ በመስራት መማር ማስተማሩ ጤናማ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል

• ጠቅላላ ተማሪዎችን በመርሃ ግብራቸው መሰረት የአንድ ቀን ውይይት በመማር ማስተማሩ ዙሪያ እና ቀጣይ

መደረግ ስላለባቸው የመማር ማስተማር ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት መግባባት መፈጠሩ

• የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ካውንስል በአዲስ በማደራጀት እና እቅድ አዘጋጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል

• የ 2012/13 የብቃት ፈተና (COC) የተማሪዎች ውጤትን በመደበኛና በማታው መርሃ ግብር ተንትኖ እና

ለትምህርት ክፍሎችም በአፈፃፀማቸው መሰረት ደረጃ እንዲወጣላቸው ተደርጎ ለቀጣይ አመት መሻሻል በሚገባው

ትምህርቶች ላይ በአካዳሚክ ኮሚሽን ውይይት መደረጉ፤ በዚህም መሰረት በመደበኛው የተመዘኑ ተማሪዎች 423

ሲሆኑ 70% እና በላይ ውጤት ያመጡት 159 (37.59%) እንዲሁም በማታው መርሃ ግብር ለምዘና

የተቀመጡት ተማሪዎች 853 ሲሆኑ 70% እና በላይ ያስመዘገቡት 119 (13.95%) እንደ ኮሌጁ ጠቅላላ

የተመዘኑ ተማሪዎች 1276 ሲሆኑ 70% እና በላይ ያመጡት 278 (21.78%) ናቸው

• በክልል ትም/ቢሮ የሚደረጉ ልዩ ልዩ ውይይቶችን በአካዳሚክ ኮሚሽንና በማኔጅመንት የጋራ እያደረጉ መምራት

መቻሉ

• ለትምህርት ክፍሎች ቸክሊት ተዘጋጅቶ መሰጠቱና ያሉበትን አፈፃፀም በሱፐርቪዥን ማረጋገጥ መቻሉ

• የፕራክቲከም ምደባ በወቅቱና በተቀመጠው መርሃ ግብር መሰረት ወቅቱን ጠብቆ እየተፈፀመ መሆኑ

3
• የመማር ማስተማሩን ውጤታማ ለማድረግ የሙዚቃ እና የስነ ጥበብ መምህራን ፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ ልምድ

እንዲያገኙ በማድረግና ያገኙትን ልምድም መሰረት በማድረግ ወደ ተጨባጭ ተግባር የገቡ መሆኑ

• ክበባት ለመማር ማስተማር ስራ አጋዥ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑ ለዚህም የስነዜጋና ስነምግባር ክበብ የአድዋን

በአል በፓናል ውይይት በደመቀ ሁኔታ ማክበሩና ሃገራዊ ስሜት መፍጠር መቻሉ፣ የፀረ ኤድስ ክበብ እና

የሕይወት ጠብታ ክበብ ከሙዚቃና ውዝዋዜ ክበብ ጋር በመቀናጀት በበሽታው አስከፊነትና በደም ልገሳ

አስፈላጊነት መድረክ ፈጥሮ መግባባት መድረሱ

• መምህራን ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተማሪዎችን የመማር ችግር በመፍታት ዉጤታማ ማድረጋቸው

• መምህራን እርስ በርስ ያላቸው ሙያዊ ግንኙነትና መስተጋብር ጤናማና የሙያ ብቃትን ማሻሻል ላይ በማድረግ

ተማሪዎችን በቲቶሪያልና በቡድን ሁነው ማገዛቸው

• መምህራን ለማስተማር ልምምድ /ፕራክተከም/ የወጡ ሰልጣኞችን በሁለት ዙር በመደገፍና ተገቢውን ግብረ

መልስ በመስጠት ተገቢውን ሙያዊ ድጋፍና ክትትል ማድረጋቸው

• የትምህርት ክፍለ ጊዜዎችን በወቅቱ የመጀመርና ላለማባከን የሚደረገው ጥረት አበረታች መሆኑ፣በተለያዬ አስገዳጅ

ምክንያቶች ክፍለ ጊዜዎች ቢባክኑም ለማካካስ ተነሳሽነቱ መኖር፣

• ሁሉም መምህራን የተማሪዎችን የትምህርት ክፍል ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል

ከፍ ለማድረግ በርትተው እየሰሩ ይገኛሉ ፡፡

 መምህራን የሚያስተምሩትን ኮርሶች በተገቢዉ መሸፈንና አሰታፊ የማስተማሪያ ዘዴዎችን፤ሚዲያዎችንና

ስታንዳርዱን የጠበቁ ፈተናዎችን በማዘጋጀት ሠልጣኞችን መመዘን እንዲሁም ማጣቀሻ መፃህፍትን በመጠቀም

ተከታታይነት ያለዉ ድጋፍ ማድረግ

ሠንጠረዥ፤ በተለያዩ ምክንያት የባከኑና የተካካሱ ክ/ጊዚያትያሉበት

ተ.ቁ የባከኑ ክ/ጊዚያት ያሉበት ሁኔታ መደበኛ የማታ

ፕሮግራም ፕሮግራም
2 የባከኑ ክ/ጊዜ ብዛት 145 81
3 የተካካሱ ክ/ጊዜ ብዛት 125 78

4 ያልተካካሱ ክ/ጊዜ ብዛት 20 3

3.1. ከመማር ማስተማር ጋር ተዛማጅነት ያላቸዉ ዋናዋና ተግባራት

በ 2013 ዓ.ም በ 1 ኛዉ ወሰነ ትምህርት የተመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች የሚወስዶቸዉ ኮርሶች ብዛት
4
ተ.ቁ ትምህርት ክፍል 2 ኛ ዓመት የሚወሰዱት የኮርስ 3 ኛ ዓመት የሚወሰዱት የኮርስ ብዛት ( በቁጥር)
ብዛት
( በቁጥር)
1 አማርኛ ስፔሻሊስት 7 4
2 እንግሊዘኛ ሊኔየር 9 2
3 ሒሳብ ሊኔየር 9 2
4 ፊዚክስ ሊኔየር 8 -
5 ኬሚስትሪ ሊኔየር 9 -
6 ባዮሎጅ ሊኔየር 9 -
7 ማህበራዊ ሳይንስ 7 -
8 ሥነዉበትናሰ/ማጎ 8 -
9 ቅድመ መደበኛ 8 7
10 እንግሊዘኛ ስፔሻሊስት - 5
11 ሒሳብና አካ/ሳይንስ - 5
12 ተፈጥሮ ሳይንስ - 5
13 ሥነዜጋና ስነምግባር - 5
14 ሙዚቃ - 7
15 ልዩ ፍላጎት - 5
ጠቅላላ ብዛት 74 47

በ 2013 ዓ.ም በ 1 ኛዉ ወሰነ ትምህርት የተመዘገቡ የማታ ተማሪዎች የሚወስዶቸዉ ኮርሶች ብዛት
ተ.ቁ ትምህርት ክፍል 2 ኛ ዓመት የሚወሰዱት የኮርስ ብዛት 3 ኛ ዓመት የሚወሰዱት የኮርስ ብዛት ( በቁጥር)
( በቁጥር)
1 አማርኛ ስፔሻሊስት 6 5
2 እንግሊዘኛ ሊኔየር 9 4
3 ሒሳብ ሊኔየር 7 5
5
4 ባዮሎጅ ሊኔየር 9 -
5 ማህበራዊ ሳይንስ 6 7
6 ሥነዉበት 8 -
7 ቅድመ መደበኛ 9 9
8 እንግሊዘኛ - 7
ስፔሻሊስት
9 ሒሳብና አካ/ሳይንስ - 9
10 ተፈጥሮ ሳይንስ - 8
11 ሥነዜጋና ስነምግባር - 6
12 ሒሳብ ስፔሻሊስት 7
13 ጤ/ሰ/ማ - 9
14 አርት - 8
15 ሙዚቃ - 8
16 ልዩ ፍላጎት - 7
ጠቅላላ ብዛት 54 99

በ 2013 ዓ.ም የ 1 ኛዉ ወሰነ ትምህርት የተማሪ ሞጁል ጥምርታ

ተ. ትምህርት ክፍል 2 ኛ ዓመት 3 ኛ ዓመት



መደበኛ የማታ መደበኛ የማታ
1ለ 1ለ 1ለ 1ለ 1ለ 1ለ3 1ለ 1ለ 1ለ 1ለ 1ለ2 1ለ3
1 2 3 1 2 1 2 3 1

1 አማርኛ ስፔሻሊስት - -  - -  - -  - -

2 እንግሊዘኛ - - - - - -  - -  - -
ስፔሻሊስት
3 እንግሊዘኛ ሊኔየር - -  - -  - -  - --

4 ሒሳብ ሊኔየር - -  - -  - -  - -

5 ሒሳብ ስፔሻሊስት - - - - - - - - -  - -

6 ባዮሎጅ ሊኔየር - -  - - - - - - - -

7 ኬሚስትሪ - -  - - - - - - - -

8 ፊዚክስ ሊኔየር - -  - - - - - - - -

9 ተፈጥሮ ሳይንስ - - - - - -  - -  - -

10 ማህበራዊ ሳይንስ - -  - - - - -  - -

11 ሥነዜጋና ስነምግባር - - - - - -  - -  - -

12 ሒሳብና አካ/ሳይንስ - - - - - -  - -  - -

13 ሥነዉበት - -  - - - - - - - -

14 ቅድመ መደበኛ - -  - -  - - -  -

6
15 ልዩ ፍላጎት - - - - - -  - - - - -

16 ሙዚቃ - - - - - -  - -  - -

17 አርት - - - - - -  - -  - -

18 ጤ/ሰ/ማ - - - - - -  - -  - -

4. የጥናትና ምርምር ተግባራት

 በየትምህርት ክፍሉ ያሉ መምህራን በመማር ማስተማሩ ሂደት በሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ በተለይም ተግባራዊ

ጥናትና ምርምር ላይ እና በመሰረታዊ ምርምር ሥራዎች ላይ በሁሉም የት/ክፍሎች ተተችተዉ በሂደት ላይ የሚገኙ

ድርጊታዊ ምርምር 12 መሰረታዊ ምርምር ደግሞ 29 በድምሩ 41 የጥናትና ምርምር ስራዎች በመሰራት ላይ

ናቸዉ፡፡ ይህ የሚያመለክተዉ ካለፉት ዓመታት አንፃር ሲታይ የመምራን የጥናትና ምርምር ማድረግ ፍላጎት እየጨመረ

መጥቷል ፡፡

ሠንጠረዥ፡ በ 2013 ዓ.ም የጥናትና ምርምር ርዕሶች

ተ.ቁ ትምህርት ክፍል ከ 2012 ዓ.ም በፊት የተተቹ በ 2012 ዓ.ም የተተቹና በሂደት ላይ ያሉ አጠቃላ
ፕሮፖዛሎች ርዕሶች ይ ድምር
መሰረታ ድርጊታዊ ድምር መሰረታዊ ድርጊታዊ ድምር

1 ቋንቋ 1 1 1 3 4 5
2 ሒሳብ 2 1 3 3 2 5 8
3 ተ/ሳይንስ 9 9 9
4 ማ/ሳይንስ 1 1 1 1 2 3
5 ስነ-ዉበትና 3 3 3
ሰ/ማ/ጎ
6 ስነ-ትምህርት 3 3 9 1 10 13
ድምር 6 2 8 23 10 33 41

 ለአጥኝዎች ሙያዊ ድጋፍ የሚሰጡ የጥናትና ምርምር አሃድ አባላትን በመመደብ በተለይ ለድርጊታዊ

ምርምሮች ‘CRITICAL FRIEND’ በመሆን በትብብር እየሰሩ መሆኑ

5. የኮሌጅ ት/ቤት ግንኙነትና የማህበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎች

• የኮሌጅ ትም/ቤት ግንኙነት ስራን አጠናክሮ ለመስራት ያመች ዘንድ በፊት ከነበሩት ደ/ታቦር እና ፋርጣ ወረዳዎች

በተጨማሪ የወረታ 3 ት/ቤቶችን፣ ከእስቴ ወረዳ 9 ት/ቤቶችን በማካተት በጠቅላላ 4 ወረዳና 25 ት/ቤቶችን አካተናል

እንዲሁም በኮሌጅ ት/ቤት ግንኑነት ለታቀፉ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የትምህርት ባለሞያዎች እና የዞን ትምህርት
7
መምሪያ ሃላፊና ባለሙያዎች በተገኙበት የኮሌጅ ትም/ቤት ግንኑነት አተገባባር ላይ የአንድ ቀን ወርክ ሾፕ አዘጋጅተን

ስልጠና ሰጥተናል፡፡ መግባባትም ላይ ተደርሷል፡፡

• እስቴ ወረዳ ለ 13 ት/ቤት ር/መ/ራን ሱፐርቫይዘሮች በአሳታፊ የመማር ማስተማር ስነዘዴ፣ በእለታዊ የትምህርት እቅድ

ዝግጅት፣ ለ 2 ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በእነዚህ ት/ቤቶች የተሰጠው ስልጠና ምን ውጤት እንደሚያመጣ ለመገምገም

የሚያስችል ሩብሪክስ (rubrics) ተዘጋጅቶ ተልኳል፡፡ በቀጣይም ሱፐርቪዥን ለማድረግ ታቅዷል

• በእስቴ ወረዳ የትምህርት ባለሙያዎች በሙሉ ለ 2 ቀናት በሱፐርቪዥንና በትምህርት እቅድ ዝግጅት ላይ ስልጠና

ተሰጥቷል

• በኮሌጅ ት/ቤት ግንኙነት ለታቀፉ የፋርጣ ወረዳ ትም/ቤቶች ወንድ 43 ሴት 30 በድምሩ 73 መምህራን ለአንድ ቀን

በአሳታፊ የመማር ማስተማር ዘዴና በተከታታይ ምዘና ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

• ለደብረታቦርና ፋርጣ ወረዳዎች ለአምስት ሱፐርቫይዘሮች ለእያንዳንዳቸው 5 ደስጣ ወረቀትና 25 እስክርቢቶ ድጋፍ

ተደርጓል፡፡

• በኮሌጁ ግንኙነት የታቀፉ 4 ቱም ወረዳዎች ትምህርት ጽ/ቤቶች የመምህራንን የስጠና ፍላጎት አሰባስቦ ለኮሌጅ እንዲላክ

ተደርጓል፡፡

 ከ DEC ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለደ/ታቦር መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ለ 2 ቀን በእለታዊ

የትምህርት እቅድ አዘገጃጀት፣ በተከታታይ ምዘና፣ በትምህርት መርጃ መሳሪያ አጠቃቀም፣ በተማሪዎች ተግባራት፣

በጾታ ተሳትፎ በሚሉ ርእሶች ላይ በኮሌጃችን መምህራን ስልጠና ተሰጥቷል

 ከማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍ አኳያ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በመምህራንና የአስ/ሰራተኞች መዋጮ 54,000 ብር

በማዋጣት 20 በግና 10 ፍየል በመግዛት ለሰሜን ጎንደር የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ኮሌጁ የ 50

ሺህ ብር ድጋፍ ማድረግ ተችሏል

 በአዲስ ለተቋቋመው የሐሙሲት ከተማ አስተዳደር የ 50 ደስጣ ወረቀት፣ 10 ቢክ እስክርቢቶ እና 10 የፋይል ማቀፊያ

ኮሌጁ ድጋፍ አድርጓል

8
 የላብራቶሪ ተግባራትን በውጤታማነት ለመስራት ችግር ለገጠመው ለክምር ድንጋይ ት/ቤት የተፈጥሮ ሳይንስ

ትም/ክፍል Beam balance, Litmus paper, Plant press, Mortar & pistle, Droppers, Hand lens,

Petrdish ድጋፍ በማድረግ የት/ቤቱ የቤተ ሙከራ ክፍል ውጤታማ ሁኗል

 ለአልማ በክብር አባልነት ኮሌጁን በማስመዝገብ በአመት 15 ሺህ ብር የአባልነት ክፍያ ይፈፅማል

6. ዋና ዋና መረጃዎችን ለተጠቃሚ ተደራሽ ለማድረግ የተሰሩ ተግባራትና የመረጃ አደረጃጀቱን ዘመናዊ ለማድረግ የተሰሩ
ስራዎች

 ኮሌጁ ዋና ዋና መረጃዎችን ለተጠቃሚ ተደራሽ ለማድረግ ከተሰሩ ተግባራት ዉስጥ በኮሌጁ ስም ዌብሳይት

እና ፌስቡክ ገፆችን በመክፈት መረጃዎችን ለማድረስ የተለያዩ ስራዎችን ይፋ ተደርጓል፡፡ ከእነዚህም መካከል

 የምክትል ዲን የዉድድር ማስታወቂያ

 የተማሪዎች ሞጁል በሙሉ የኮሌጁ ዌብሳይት ላይ እንዲጫን ተደርጓል

 የኮሌጁ የጥናትና ምርምር ዉጤት ስራዎችም በኮሌጁ ስም በተከፈተው ድህረ ገፅ ተጭነው ለተጠቃሚዎች

እንዲደረሱ ተደርጓል

 የፋይናንስ የገንዘብ አጠቃቀም መረጃ ኮምፒዩተራዊ በማድረግ ለሚመለከተው አካል ኢንተርኔት ማድረስ

መቻሉ፣

7. በ 2013 ዓ.ም የኮሌጅ ጥገና ፤የእድሳት እና የግንባታ ሥራዎች

• የኮሌጁ ህንፃ ክረምት ላይ እያፈሰሰ መማር ማስተማሩን በማስተጓጎሉ ምክንያት ከውስጥ ገቢ ብር

300,000 በመመደብ ለማስጠገን ከዞን ከተማ ልማት መምሪያ ጋር የማስጠናት ስራ እየተሰራ ነው

8. የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት የተከናወኑ ተግባራት

9
 የኢንተርኔት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ከውስጥ ገቢ ብር 200,000 በመመደብና በማኔጅመንት ኮሚቴ በመወሰን

የሚመለከታቸው ባለሙያዎችን (አይሲቲ ባለሙያ፣ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ፣ ጥገና ባለሙያ) ፍ/ሰላም

መም/ትም/ኮሌጅ ሂደው ልምድ እንዲያመጡ ተደርጓል

 ቤተ መፅሃፍቱን ዲጂታል ለማድረግ በአካዳሚክ ህንፃና አስተዳደር ህንፃ ክፍሎች ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት

ለማሟላት ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል

9. ለሴት ሠልጣኞች ልዩ ድጋፍ የተከናወኑ ተግባራት

በስርዓተ ፆታ ዩኒት አማካኝነት

 ከሱቅ ሽያጭ የሚገኘውን ትርፍ በአቢሲኒያ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 13733047 የሂሳብ ደብተር በመክፈት ከሚገኘው

ትርፍ 25% በመቆጠብ 75% የሚሆነውን ትርፍ በየጊዜው ችግርተኛ ተማሪዎች እንዲከፋፈሉ ተደርጓል፡፡ ይህም

ለችግረኛ ሴት ሠልጣኞች የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ለአብነት ያህል፡-

 የኢኮኖሚ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሴት ተማሪዎች በመምረጥ ከሱቅ ሽያጭ በተገኘዉ ትርፍ ለሁለት ሴት

ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 600 በድምሩ 1200 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

 ለአንድ በማታዉ መርሃግብር ትምህርቱን የሚከታተል ሰልጣኝ በክፍያ ምክንያትትምህርቱን ሊያቋርጥ በነበረበት

ወቅት ከተቀማጭ ገንዘብ 1200 ብር በማበደር እንዲመዘገብና ትምህርቱን እንዲከታተል ተደርጓል፡፡

 ሱቁ ላይ አገልግሎት ለሚሰጡ ተተኪ ሰልጣኞችን በመምረጥ ለአንድ ሴት ሠልጣኝ 150 ብር እና ለአንድ ወንድ

ሠልጣኝ ደግሞ 250 ብር በአጠቃላይ 400 ብር የአገልግሎት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

 ለሴት ሠልጣኞች በቀን 25/05/2013 ዓ.ም በሕይወት ክህሎት፤በሥርዓተ ፆታ ምንነት፤ በሴት ሰልጣኞች ላይ

የሚደርሱ ፆታዊ ትንኮሳ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

 ለሴት ሠልጣኞች በኮሌጅ ቆይታቸዉ ጊዜ በአጠቃላይ ወደፊት መደረግ ስላለባቸዉ ጉዳዮች የጋራ ዉይይት

በማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

 በኮሌጁ ትምህርትና ስልጠና ላይ እያለች ለወለደች አንድ ሴት ሰልጣኝ የምክር አገልግሎት በመስጠት ሰልጠናዉን

አጠናቃ እንድትመረቅ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

10
 ለሴት ተማሪዎች የሞዴስ መቀየሪያ ክፍል እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ ሴት ተማሪዎችም ድንገተኛ የወር አበባ

በሚያዩበት ጊዜ መታወቂያ በማሳየት ሞዴስ እንዲጠቀሙ ክፍያውንም በተመቻቸው ሰዓት መጥተው

እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

በአመራሩና በመምህራን በኩል የተሰሩ የድጋፍ ስራዎች

 ቼክ ሊስት አዘጋጅቶ ለትምህርት ክፍሎች በመስጠት የተግባራት አፈጻጸም በአካል መከታተል፣መደገፍና

መገምገም መቻሉ፣

 ተግባራት በየሁለት ሳምንቱ በአካዳሚክ ኮሚሽን ይገመገማል፣

 በአለቆች ህብረት፣በተማሪዎች ካውንስል፣በየትምህርትና የስራ ክፍሎች በየሁለት ሳምንቱ እየተገመገመ የሚመራ

መሆኑ

 የመወያያ ትኩረት ነጥቦችም መለያታቸው፤ለአብነት፣አሳታፊ የማስተማር ስነ ዘዴ አተገባበር፤ተከታታይ ምዘና

፤የክፍለ ጊዜ ብክነት፤የተማሪዎች በትብብራዊ መማማር፣ ስነምግባር፣ውጤት መሻሻል … ወዘተ

 በማኔጅመንት ኮሚቴ በየሁለት ሳምንቱ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች እየተወሰኑ መመራታቸው

 ዲኖች ስራዎችን ክፍፍል በማድረግ ክትትልና ድጋፍ ስራ መሰራቱ

 የስልጠና ክትትልና ድጋፍ ባለሙያዎች የተግባር ምደባ ተደርጓል፡፡ የመማር ማስተማሩን ስራም ወርሃዊ ክፍፍል

አድርገው ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

በአካዳሚክ ኮሚሽን አባል የሆኑ መምህራን ብዛት

ተ.ቁ የሥራ ክፍሎች ፆታ ብዛት

1 የቋንቋ ት/ት ክፍል ተጠሪ ወ 1


2 የተ/ሳይንስ ት/ት ክፍል ተጠሪ ወ 1
3 የማ/ሳይንስ ት/ት ክፍል ተጠሪ ወ 1
4 የሒሳብ ት/ት ክፍል ተጠሪ ወ 1
5 የሥነዉበትና ሰ/ማ/ጎ ት/ት ክፍል ተጠሪ ወ 1
6 የሥነ- ትምህርት ት/ት ክፍል ተጠሪ ወ 1
7 የሥርዓተ- ፆታ አሃድ ተጠሪ ሴ 1
8 የሬጅስራር ፅ/ቤት ተጠሪ ወ 1
9 የመምህራን ማህበር ተወካይ ወ 1

11
10. ያጋጠሙ ችግሮች

 የተማሪ ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ መምህራን ከአቅም በታች መጠነ ግብር እንዲይዙ አድርጓል

 የበጀት እጥረት መኖር

 በኮረና ምክንያት ትብብራዊ መማማርን ተግባራዊ ማድረግ አለመቻሉ

 በተደጋጋሚ የተነሱት የመምህራን የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸው

12

You might also like