You are on page 1of 17

የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ አደረጃጀትና

አሠራር መመሪያ

(በሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት


የተዘጋጀ)

ነሐሴ 2010 ዓ.ም

ሀዋሳ
ክፍል አንድ

መግቢያ

የሀገራችን የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ የሀገሪቱን የትምህርት ሥርዓት አደረጃጀት፣


የትምህርቱን አላማና ይዘት ህብረተሰቡ የደረሰበትንና ወደፊት ሊደርስበት የሚፈልገውን
የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ኑሮ ዕድገት ደረጃን በሚያንፀባርቅ መልኩ ይዘጋጃል
ይህንንም ተከትሎ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን፣ አጋዥ መመሪያዎችንና ማኑዋሎችን
በማዘጋጀት ተግባራዊም ያደርጋል።

በመሆኑም የትምህርት ዓላማዉ ታዳጊው ትውልድ በሕብረተሰቡ ዘንድ ተፈላጊነት


ያላቸውና በሥራ ሊተረጐሙ የሚችሉ ባህሪያትን (ዕውቀትን፣ ልዩ ልዩ ችሎታዎችን፣
ክህሎቶችን፣ ልምዶችን የተስተካከለ አመለካከትን ወዘተ.) እንዲጨብጥና በሕብረተሰቡ
የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ ንቁ ተሳታፊና አምራች ዜጋ እንዲሆን ማድረግ ነው። እነዚህ
የተነደፉት የትምህርት ዓላማዎች በተግባር ሊተረጐሙ የሚችሉት ደግሞ አስፈላጊ
ግብዓቶች ተሟልተው፣ ተደራጅተውና በአግባቡ አገልግሎት ላይ ውለው የሚሰጠው
ትምህርት የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ ሲገኝ ነው።

በየደረጃው የሚካሄዱ የትምህርት ፕሮግራሞች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ


እንዲሆኑፖሊሲዉን ተከትሎ ያሉትን ስትራቴጂዎችና ስታንዳርዶችን በጠበቀ መልኩ
የተቀረፀዉን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ በማድረግ ትምህርቱ ወደ ሚፈለገዉ የጥራት
ደረጃ እንዲደርስ ያስችል ዘንድ በተለይም የሣይንስ ትምህርቶች በቤተ-ሙከራ በተግባር
ተደግፈዉ እንዲሰጡ ማድረግ የሚጠበቅ ነዉ፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ መንገዶችና በተለያዩ አካላት እስካን በተደረገዉ ግምገማ በአጠቃላይ
የሣይንስ ትምህርቶችን በቤተ-ሙከራ አስደግፎ ከማስተማር አንፃር ከፍተኛ ከፍተት
ያለበትና በአብዛኛዉ ትምህርቱን መምህር ተኮር በማድረግ በገለፃ ዘዴ የሚሰጥ በመሆኑ
የሚፈለገዉን ዉጤት ማግኘት አልተቻለም፡፡ለዚህም እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ጉዳዮች
ዋና ዋናዎቹ፡- የሳይንስ መምህራን ትምህርቱን በቤተ-ሙከራ በተጨባጭ የትምህርት
መርጃ መሳሪያዎች አስደግፎ አለመስጠት፣ የትምህርት ቤትአመራሮችበቤተ-ሙከራ
ለሚሰጠዉ ትምህርት ተገቢውን ትኩረት አለመስጠትና ግብዓት አለማሟላት፣ ተገቢዉን
ክትትልና ድጋፍ አለማድረግ፣ መምህራን የሣይንስ ትምህርቶችን በተግባርና ወቅቱ
ባፈራቸው አዳዲስ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች አስደግፎ አለመስጠት፣ በየትምህርት ዓይነቱ
በስታንዳርድ መሰረት የተደራጀ የቤተ-ሙከራ ክፍሎች አለመኖርእንዲሁም የሣይንስ
ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ ወጥ የሆነ የአደረጃጀት አሠራርና አጠቃቀም መመሪያ አለመኖር
የሚሉት በምሳሌነትየሚጠቀሱ ችግሮች ናቸው፡፡

በመሆኑም በሣይንስ ትምህርቶች አተገባበር ውጤታማነት ላይ ያለውን ችግር በመገንዘብ


በክልል ደረጃ የተዘጋጀዉንየቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃየትምህርት
ቤቶች ስታንዳርድ(2005)፣የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የነጥብ
ሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰድ (JEG) ሰነድ (2009)መነሻ በማድረግ በክልላችን ነባራዊ
ሁኔታ የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ አደረጃጀትና አሠራር መመሪያተዘጋጅቷል፡፡

ትምህርት ቤቶችስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ የተደራጁ የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-


ሙከራዎች በማደራጀት፣ የአሠራርና የአጠቃቀም ሥርዓት በማበጀት ትምህርቱን በተግባር
አስደግፎ በመስጠት የትምህርቱን ጥራትና ተገቢነት በማስጠበቅየተማሪዎችን ዉጤት
ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ በሁሉም ትምህርት ቤቶችየሣይንስ ትምህርቶችቤተ-
ሙከራዎችን ስርዓት ባለው መልኩ ለመምራትና ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ይህ
መመሪያ አምስት ክፍሎች ያሉት ሆኖ ተዘጋጅቷል፡፡ እነዚህም፡- ክፍል አንድ መግቢያ
ክፍል ሁለት አጠቃላይ ሁኔታ፣ ክፍል ሶስት የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ አደረጃጀት፣
ክፍል አራት የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ አሠራር/በየደረጃው ያለው አካል ተግባርና
ኃላፊነት እና ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ጉዳዮች በሚል ተደራጅቶ ቀርቧል፡፡
ክፍል ሁለት

አጠቃላይ ሁኔታ

አንቀጽ 1፡ አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ አደረጃጀትና አሠራር መመሪያቁጥር------


-/2011” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

አንቀጽ 2፡ ትርጓሜ

የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

1. “የሣይንስ ትምህርቶች” ማለት፡- በመጀመሪያና በሁለተኛ ደረጃትምህርት ቤቶች


የሚሰጡትን የአካባቢ ሣይንስ፣ የተቀናጀ ሣይንስ፣ የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪና የባዮሎጂ
ትምህርት ዓይነቶች ናቸዉ፡፡
2. “ቤተ-ሙከራ” ማለት:- ለአካባቢ ሣይንስ፣ ለተቀናጀ ሣይንስ፣ ለፊዚክስ፣ ለኬሚስትሪና
ለባዮሎጂ ትምህርት ዓይነቶች አስፈላጊ የሆኑ ኢኩፕመንት፣ አፓራተስና ኬሚካሎች
የሚገኙበትና ሣይንሳዊ ሙከራዎች የሚከናወኑበት ክፍል ነው፡፡
3. “በመጀመሪያና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች” ማለት፡- ከ1ኛ - 12ኛ ባሉት
የክፍል ደረጃዎች የመማር ማስተማሩ ሂደት የሚከናወንበት የትምህርት ተቋም
ነዉ፡፡
4. “የትምህርት ቤቶች ስታንዳርድ” ማለት፡-የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች ሊያሟሉ የሚገባቸዉ የሰዉ ሀብት፣ መማሪያ ማስተማሪያና አገልግሎት
መስጫ ህንፃዎች፣ የዉስጥ አደረጃጀትና የትምህርት ግብዓቶችተሟልቶላቸዉ
የመማር ማስተማሩን ሥራጥራትና ዉጤታማነትን ለማስጠበቅ የሚረዳ
መስፈርት/መለኪያ ነዉ፡፡
አንቀጽ 3

የተፈፃሚነት ወሰን

1. ይህ መመሪያ በክልሉ በሚገኙ ዞኖች፣ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርናልዩ ወረዳዎች ስር


በሚገኙ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑየመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
2. በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ጾታ የተገለጸ ቃል ሁሉ ለሴት ፆታም ያገለግላል፡፡

አንቀጽ 4

የመመሪያው አስፈላጊነት

የሣይንስ ትምህርቶችን በቤተ-ሙከራ አስደግፎ ከማስተማር አንፃር ያሉ ከፍተቶችን


በመቅረፍቤተ-ሙከራዎችንበማደራጀትተገቢዉን አገልግሎትእንዲሰጡ
ለማስቻል፣ ትምህርቱንተግባር ተኮርና አሳታፊ በማድረግ የሣይንስ ትምህርቶችን ዉጤት
በማሻሻል ብቁ፣ ተመራማሪና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት፣ የሣይንስ መምህራንና የቤተ-
ሙከራ ባለሙያዎችን የሣይንስ ቤተ-ሙከራ አጠቃቀም ላይ እገዛ ለማድረግ፣ በየደረጃዉ
ያለዉ የትምህርት አመራር በቤተ-ሙከራ አሠራርና አጠቃቀም ዙሪያ ተገቢዉን ድጋፍና
ክትትል ለማድረግ እንዲያስችለዉ፣ ትምህርት ቤቶችያላቸዉን ሀብት በአግባቡ
እንዲጠቀሙ ለማስቻል፣ የመምህራንና የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ፣ በየአካባበዉ
ከሚገኙ ቁሳቁሶች የትምህርትመርጃ መሣሪያዎችን ማዘጋጀትና መጠቀም እንዲችሉ
ለመርዳት እና ለመማር ማስተማር ስራ የተገዙ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶች በአግባቡ ጥቅም
ላይ እንዲዉሉ ለማስቻል ነዉ፡፡

አንቀጽ 5

የመመሪያዉ ጠቀሜታዎች፡ -

1. የሣይንስ ቤተ-ሙከራ ክፍሎችን በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሠረት በማደራጀት


ተገቢዉን አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላል፤
2. የሣይንስ ትምህርቶችን በቤተ-ሙከራ አስደግፎ ከማስተማር አንፃር የሚስተዋሉ
ከፍተቶችን ለመቅረፍ ያግዛል፤
3. በየደረጃዉ ያለዉ የትምህርት አመራር በቤተ-ሙከራ አሠራርና አጠቃቀም ዙሪያ
ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እንዲያስችላቸዉ፣
4. በትምህርት ቤቶች የሣይንስ ትምህርቶችን ጥራት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ
ይኖረዋል፤
5. የመምህራንና የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማጎልበት፣
6. በየአካባበዉ ከሚገኙ ቁሳቁሶች የትምህርትመርጃ መሣሪያዎችን አዘጋጅተዉ
እንዲጠቀሙ ይረዳል፤
7. መምህራንና ተማሪዎች ከዘመናዊ የሣይንስና ቴክኖሎጂ አዳዲስ ግኝቶች ጋር
እንዲተዋወቁ፤

አንቀጽ 6

ዓላማ

1. አጠቃላይ ዓላማ

የሣይንስ ትምህርቶችን ዉጤታማ ለማድረግ ቤተ-ሙከራዎችን በየደረጃዉ ባሉ ትምህርት ቤቶች


በስታንዳርዱ መሠረት በማደራጀት አገልግሎት እንዲሰጡ በማስቻል የትምህርቱን ጥራትና ዉጤት
ለማስጠበቅ ነዉ፡፡

2. ዝርዝር ዓላማዎች
የሣይንስ ቤተ-ሙከራ ክፍሎችን በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሠረት በማደራጀት
ተገቢዉን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ፤
የሣይንስ ትምህርቶችን በቤተ-ሙከራ አስደግፎ ከማስተማር አንፃር የሚስተዋሉ
ከፍተቶችን በመቅረፍ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል፤
በየደረጃዉ ያለዉ የትምህርት አመራር በቤተ-ሙከራ አሠራርና አጠቃቀም ዙሪያ
ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ፣
በትምህርት ቤቶች የሣይንስ ትምህርቶችን ጥራት ለማስጠበቅ፤
የመምህራንና የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ፣
በየአካባቢያቸዉ ከሚገኙ ቁሳቁሶች የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን አዘጋጅተዉ
እንዲጠቀሙ ለማስቻል፤
መምህራንና ተማሪዎች ከዘመናዊ የሣይንስና ቴክኖሎጂ አዳዲስ ግኝቶች ጋር
እንዲተዋወቁ ለማድረግ፤

አንቀጽ 7

መርሆዎች

በየደረጃው ያሉ ትምህርት ቤቶች በሣይንስ ቤተ-ሙከራ አደረጃጀትና አሠራር


የሚከተሉትንመርሆዎች በመከተል ተግባሩን ያከናውናሉ፣ ኃላፊነቱንም በአግባቡ
ይወጣሉ፡፡

• በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች፣ መምህራንና የቤተ-ሙከራ ባለሙያዎች


ጠንካራ የሥራ ባህል ሊኖራቸዉ ይገባል፡፡
• መምህራንና የቤተ-ሙከራ ባለሙያዎችበመማሪያ ማስተማሪያ መፅሐፍት ዉስጥ
የተቀመጡት የተግባር ሥራዎች ሳይንጠባጠቡ በወቅቱ ማከናወን፤
• የትምህርት አመራሮች፣ የሣይንስ መምህራንና የቤተ-ሙከራ ባለሙያዎች በሥርዓተ
ትምህርቱን በመከተልጊዜን በአግባቡ በመጠቀም እቅዳቸዉን በውጤታማነት
መፈፀም፡፡
• የትምህርት አመራሮች፣ የሣይንስ መምህራንና የቤተ-ሙከራ ባለሙያዎች የእርስ
በርስ መማማርንና መደጋገፍ
• ትምህርት ቤቶች መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር
ተባብረውናተደጋግፈው መሥራት
• ፍትሃዊና ተደራሽ የሆነ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ
ክፍል ሶስት

የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ አደረጃጀት

በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች የሣይንስ


ቤተ-ሙከራቸዉበመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከአካባቢዉ ከሚገኙ ቁሳቁሶች
ተደራጅተዉ የተግባር ትምህርት የሚሰጥበት ሁለገብ የሣይንስ ክፍል እና በሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤቶች ደግሞ ራሳቸዉን በቻሉ ሦስት የቤተ-ሙከራ ክፍሎች (የፊዚክስ፣
የኬሚስትሪና የባዮሎጂ)ተደራጅተዉ በተግባር የተደገፈ የሣይንስ ትምህርቶች የሚሰጥባቸዉ
ሆነዉ ይደራጃሉ፡፡

አንቀጽ 8

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁለገብ የሣይንስ ክፍል አደረጃጀት

በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት


ቤቶች ሁለገብ የሣይንስ ክፍልየሚከተሉት አደረጃቶች ይኖሩታል፡፡

1. ሁለገብ የሣይንስ ክፍል ከ1ኛ -4ኛ ክፍል 7ሜX15ሜ = 105ካ.ሜ መጠን ያለው
ሲሆን ከ5-8ኛ ክፍል ደግሞ 8ሜX15ሜ = 120 ካ.ሜ መጠን ያለው ሆኖ
ይዘጋጃል፡፡
2. በሁለገብ የሣይንስ ክፍሎች(ከ1ኛ - 4ኛ እና ከ5ኛ - 8ኛ) ዉስጥ ተገቢዉን
አገልግሎት ለመስጠት መደራጀት የሚገባቸዉ ቁሳቁሶች የመምህሩ ወንበርና
ጠረጴዛ /Demonestration Table/፣ በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ የተማሪ ጠረጴዛዎች፣
የላቦራቶሪ መቀመጫ/stool/፣ ጥቁር ሰሌዳ፣ የማስታወቂያ ሰሌዳ፣ የቁሳቁስ
ማስቀመጫ መደርደሪያዎች፣ ቁም ሳጥን፣ ንብረት መስቀመጫ ትንሽ ክፍል፣
የሣይንስ ኪቶች፤ ለደረጃው የሚያስፈልጉ ኬሚካሎች እና የውሃ ቧንቧ መስመር
/የውሃ መያዣ ጄርካን/በመጀመሪያ ደረጃ ትምሀርት ቤቶች ስታንዳርድ መሠረት
ይደራጃል፡፡
3. ከአካባቢያቸው የሚገኙ የተለያዩ በሳይንስ ቤተ ሙከራ ማስተማሪያነት ሊውሉ
የሚችሉ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ ያደራጃሉ፤ አገልግሎት ላይ ያውላሉ፡፡
4. ሁለገብ የሣይንስ ክፍሉን በደረጃዉ የሚያስተምሩ የሣይንስ መምህራንና የሣይንስ
ትምህርት ክፍል ተጠሪዎች በጋራ ያደራጃሉ

አንቀጽ 9

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሣይንስ ትምህርቶች (የፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባዮሎጂ)


ቤተ-ሙከራ ክፍሎችአደረጃጀት

በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት


ቤቶችየሣይንስ ትምህርቶች (የፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባዮሎጂ)ቤተ-ሙከራክፍሎች
የሚከተሉት አደረጃቶች ይኖሩታል፡፡

1. የሣይንስ ትምህርቶች (የፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባዮሎጂ)ቤተ-ሙከራክፍሎች ልዩ ልዩ


ኬሚካሎች፣ አፓራተስና ኢኩፕመንት የሚቀመጡበት መጋዘን/Store/ እና መምህሩ
ትምህርቱን ከማቅረቡ በፊት ልምምድ የሚያደርግበት የዝግጅት ክፍል እንዲሁም
ተማሪዎች የሚለማመዱበት ክፍል/Demonestration room/ ያሉት ሆኖ ይደራጃል፡፡
2. የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ ክፍሎች፡-
ሀ/ የፊዚክስና የኬሚስትሪቤተ-ሙከራ እያንዳንዳቸዉ፡-
የተግባር መለማመጃ ክፍል /Demonestration room/ 17.7ሜX5.85ሜ =
103.55 ካ.ሜ፣
የዝግጅት ክፍል 2.4ሜX5.8ሜ = 13.92 ካ.ሜ፣
መጋዘን/Store/ 3.3ሜX5.8ሜ = 19.14 ካ.ሜ
በአጠቃላይ የህንፃዉ/Block/ መጠን መጠን 24.44ሜX6.25ሜ = 152.75
ካ.ሜመጠን እና

ለ/ ባዮሎጂቤተ-ሙከራ የተግባር መለማመጃ ክፍል

የተግባርመለማመጃክፍል /Demonestration room/ 15.00ሜX5.55ሜ = 87.75


ካ.ሜ፣
የዝግጅት ክፍል 2.44ሜX2.86ሜ = 6.86 ካ.ሜ፣
መጋዘን/Store/ 3.3ሜX2.85ሜ = 9.4 ካ.ሜ
በአጠቃላይ የህንፃዉ/Block/ መጠን መጠን 6.0ሜX18ሜ = 108 ካ.ሜ መጠን
ያላቸዉ ሆኖ ይደረጃሉ፡፡

3. ሦስቱም ቤተ-ሙከራዎች የዉሃ(የሚሠራ ቧንቧ፣ መታጠቢያ ሳህኖች/Sink)የመብራት


አገልግሎት፣ የቆሻሻ ማስወገጃ/Septic Tank/ ያላቸዉ ሆነዉ መደራጀት
ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. በሰዉ ኃይል ረገድ ሶስቱም ራሳቸዉን የቻለ የቤተ-ሙከራ ባለሙያ/Laboratory
technicians/ ይኖራቸዋል፡፡
5. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሣይንስ ትምህርቶች (የፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና
ባዮሎጂ) ቤተ-ሙከራ ክፍሎችዉስጥ በተማሪዎች ቁጥር ላይ ተመስርቶ ተገቢዉን
አገልግሎት ለመስጠት ያስችል ዘንድ መደራጀት የሚገባቸዉ ቁሳቁሶች የመምህሩ
ወንበርና ጠረጴዛ /Demonestration Table/፣ በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ የተማሪ
በርጩማ/Stool/፣ጥቁር ሰሌዳ፣ የማስታወቂያ ሰሌዳ፣ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት፣
የቁሳቁስ ማስቀመጫ መደርደሪያዎች፣ ማሳያ ቁም ሳጥኖች እና የተማሪዎች አግዳሚ
ጠረጴዛዎች ያሉት ቤተ-ሙከራ ክፍሎች በሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤቶች
ስታንዳርድ መሠረት ይደራጃሉ፡፡
6. ከአካባቢያቸው የሚገኙ የተለያዩ በሳይንስ ቤተ ሙከራ ማስተማሪያነት ሊውሉ
የሚችሉ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ ያደራጃሉ፤ አገልግሎት ላይ ያውላሉ፡፡
7. የቤተ-ሙከራ ክፍሎችን በዋናነት የቤተ-ሙከራ ባለሙያዎች/Laboratory
technicians/ ኃላፊነት ወስደዉ የሚያደራጁ ሲሆን እነሱ ባልተሟሉበት ትምህርት
ቤት የሣይንስ ትምሀርቶችን በሚያስተምሩ በሣይንስ መምህራንና በሣይንስ
ትምህርት ክፍል ተጠሪዎች ይደራጃል፡፡
8. ሦስቱም ቤተ-ሙከራዎች የእሳት አደጋመከላከያ/Fire Extinguisher/ እና ሌሎች
የአደጋ ጊዜ መከላከያ የቅድመ ጥንቃቄ ማቴሪያሎች የተሟሉለት ሆኖ ይደራጃል፡፡
ክፍል አራት

የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ አሠራር/በየደረጃው ያለው አካል ተግባርና


ኃላፊነት

ከክልል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ያለዉ መዋቅር በሣይንስ ቤተ-ሙከራዎች አሠራር


ዙሪያ ሊያከናዉኗቸው የሚገቡ ተግባርና ሀላፊነታቸዉ ቀጥሎ ባሉት አንቀፆች ተከፋፍሎ
ተቀምጧል፡፡

አንቀጽ 10

የክልል ትምህርት ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት

1. የክልል ትምህርት ቢሮ ለቤተ-ሙከራ ተግባራትአጋዥ የሆኑ ስትራቴጂዎችንና


የአሠራር መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ያሰራጫል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
2. የቤተ-ሙከራ ተግባራት ተቀርፆ ሥራ ላይ በዋለዉ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት
የሣይንስ ትምህርቶች በተግባር ተደግፈዉእየተሰጡ መሆኑን ይከታላል
ይደግፋል፤ግብረ-መልስ ይሰጣል፤
3. በየደረጃዉ ላሉ አካላት በቤተ-ሙከራ አተገባበር ዙሪያ የአቅም ግንባታ
ሥልጠኛዎችን ይሰጣል፣ ውጤታማነቱንም ይከታተላል፤
4. የቤተ-ሙከራ ግብዓቶች/የሰዉ ሀይልና ማቴሪያሎች/ እንዲሟሉ ያደረጋል፤
5. የሣይንስ ቤተ-ሙከራ ክፍሎች በስታንዳርድ መሠረት መደራጀታቸውንተገቢውን
አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤

አንቀጽ 11

የዞን/ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርትምህርት መምሪያተግባርና ኃላፊነት

1. ለቤተ-ሙከራ ተግባራትአጋዥ በሆኑ ስትራቴጂዎችና የአሠራር መመሪያዎች


መሠረት ትም/ጽ/ቤቶችትምህርት ቤቶችን መደገፋቸዉንና ትምህርት ቤቶች ደግሞ
ተግባራዊ ማድረጋቸዉንይከታተላሉ ይደግፋሉ፤ግብረ-መልስ ይሰጣሉ፤
2. የቤተ-ሙከራ ተግባራት ተቀርፆ ሥራ ላይ በዋለዉ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት
የሣይንስ ትምህርቶች በተግባር ተደግፈዉ በትምህርት ቤቶች እየተሰጡ መሆኑን
ትም/ጽ/ቤቶች መከታተላቸዉንና መደገፋቸዉን ይከታተላሉ፣ ይደግፋሉ፤ግብረ-
መልስ ይሰጣሉ፤
3. በቤተ-ሙከራ አተገባበር ዙሪያ በየደረጃዉ ላሉ አካላት የአቅም ግንባታ
ሥልጠናዎችን ይሰጣሉ፣ ውጤታማነቱንም ይከታተላሉ፤
4. የቤተ-ሙከራ ግብዓቶች/የሰዉ ሀይልና ማቴሪያሎች/ እንዲሟሉ ያደረጋሉ፤
5. የሣይንስ ቤተ-ሙከራ ክፍሎች በስታንዳርድ መሠረት መደራጀታቸውንና
ተገቢውንአገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ፤
6. በዞን/ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሥር ያሉ ትምህርት ቤቶች በተቀመጠዉ የትምህርት
ቤቶች ስታንዳርድ መሠረት ሁለገብ የሣይንስና የቤተ-ሙከራ ክፍሎች መደራጀትና
አለመደራጀታቸዉን ለይተዉ መረጃ ይይዛሉ፣ ክፍተት ያለባቸዉን ለይተዉ
እንዲደራጁ ያደርጋሉ፤

አንቀጽ 12

የልዩ ወረዳ/ወረዳ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

1. ለቤተ-ሙከራ ተግባራትአጋዥ በሆኑ ስትራቴጂዎችና የአሠራር መመሪያዎች


መሠረት ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ማድረጋቸውንይከታተላሉ ይደግፋሉ፤ግብረ-
መልስ ይሰጣሉ፤
2. የቤተ-ሙከራ ተግባራት ተቀርፆ ሥራ ላይ በዋለው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት
የሣይንስ ትምህርቶች በተግባር ተደግፈውበትምህርት ቤቶች እየተሰጡ መሆኑን
ይከታተላሉ፣ ይደግፋሉ፤ግብረ-መልስ ይሰጣሉ፤
3. በቤተ-ሙከራ አተገባበር ዙሪያ ለመምህራንና ለሳይንስ ቤተ-ሙከራ ባለሞያዎች
የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን ይሰጣሉ፣ ውጤታማነቱንም ይከታተላሉ፤
4. የቤተ-ሙከራ ግብዓቶች/የሰው ሀይልና ማቴሪያሎች/ያሟላሉ፤ እንዲሟሉም ያደረጋሉ፤
5. የሣይንስ ቤተ-ሙከራ ክፍሎች በስታንዳርድ መሠረት መደራጀታቸውንና ተገቢውን
አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ፤
6. ትምህርት ቤቶች በተቀመጠው የትምህርት ቤቶች ስታንዳርድ መሠረት ሁለገብ
የሣይንስና የቤተ-ሙከራ ክፍሎች መደራጀቱንና አለመደራጀቱን ለይተው መረጃ
ይይዛሉ፣ ክፍተት ያለባቸውን ለይተው እንዲደራጁ ያደርጋሉ፤

አንቀጽ 13

የትምህርት ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት

1. በስትራቴጂዎችና በአሠራር መመሪያዎች መሠረት ትምህርት ቤቶች የቤተ-ሙከራ


ሥራዎችንተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
2. ከተለያዩ አካላት በድጋፍና ክትትል ወቅት የተሰጡትን ግብረ መልሶች በማካተት
ለውጤታማነት ይሰራሉ፡፡
3. የቤተ-ሙከራ ሥራዎችንበተመለከተ የቀረበውን እቅድ በመገምገም ተገቢውን በጀት
በመመደብ ወደ ተግባር እንዲገባ ያደርጋሉ፣ ይከታተላሉ፣ ይደግፋሉ፤ግብረ-መልስ
ይሰጣሉ፤
4. በቤተ-ሙከራ አተገባበር ዙሪያ ለመምህራንና ለሳይንስ ቤተ ሙከራ ባለሞያዎች የአቅም
ግንባታ ሥልጠናዎችን ይሰጣሉ፣በጋራ አቅማቸውን የሚገነባቡበትን መንገድ ይቀይሳል፣
ውጤታማነቱንም ይከታተላሉ፤
5. የቤተ-ሙከራ ግብዓቶች ያሟላሉ፡፡
6. የሰው ሀይል እንዲሟላ ያደርጋሉ፡፡
7. የሣይንስ ቤተ-ሙከራ ክፍሎችንበስታንዳርድ መሠረትያደራጃሉ፤ለአገልግሎት ዝግጁ
ያደርጋሉ፤
8. መምህራን ለሣይንስ ቤተ-ሙከራ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከአካባቢያቸው በመሰብሰብ
እና በማደራጀት በጥቅም ላይ እንዲውሉ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋሉ፡፡
9. በሣይንስ ቤተ ሙከራ ውስጥ የተደራጁ ኬሚካሎች፣ አፓራተሶችና ሞዴሎች በአግባቡ
ተይዘው ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ ስለመሆናቸው የቅርብ ክትትልና ድጋፍ
ያደርጋሉ፡፡
10. በሣይንስ ቤተሙከራ ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች በየሴሚስተሩ መጨረሻ የንብረት
ቆጠራ ያካሂዳሉ፡፡
አንቀጽ 14

የሣይንስ መምህራን ተግባርና ኃላፊነት

1. በመማሪያና ማስተማሪያ መጽሃፍ ውስጥ የተቀመጡ የቤተ-ሙከራ ተግባር


ሥራዎችንበቤተ-ሙከራ ውስጥ እንዲሞከሩ ሳይዘሉና ሳያስቀሩ በትምህርት እቅዱ
መሰረት ይሰራሉ፣
2. በድጋፍና ክትትል ወቅት የተሰጡትን ግብረ መልሶች በማካተት ለውጤታማነት ይሰራሉ፡፡
3. የቤተ-ሙከራ ተግባራትንበተመለከተ እቅድ ያዘጋጃሉ፤ በእቅዱ መሰረት ተግባራዊ
ያደርጋሉ፡፡
4. በቤተ-ሙከራ አተገባበር ዙሪያ በጋራ አቅማቸውን የሚገነባቡበትን መንገድ
ይቀይሳሉ፣ለውጤታማነቱም ይሰራሉ፤
5. የቤተ-ሙከራ ግብዓቶች በአግባቡ መግለጫዎቹን በመስጠትና በመመዝገብ በጋራ
በመሆን ያደራጃሉ፡፡
6. ከሣይንስ ትምህርት ሙከራ በኃላ የተጠቀሙባቸውን እቃዎች፣ መሳሪያዎችና
ኬሚካሎች ፅዳትና ደህንነት ይጠብቃሉ፤ በተገቢ ቦታቸው ይመልሳሉ፡፡
7. መምህራን ከአካባቢያቸው በሚገኙ ለሣይንስ ቤተ ሙከራ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን
በማሰባሰብና በማደራጀት በጥቅም ላይ ያውላሉ፡፡
8. የተበላሹ ወይም የተሰበሩ እቃዎችን ቀላል ጥገና ያደርጋሉ፡፡
9. በየጊዜው የሚከናወኑ የሙከራ ውጤቶችንና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን
ለመረጃና ለጥናት እንዲያገለግሉ አደራጅተው ይይዛሉ፡፡
10. በሣይንስ ቤተ ሙከራ ውስጥ የተደራጁ ኬሚካሎች፣ አፓራተሶችና ሞዴሎች በአግባቡ
ተይዘው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የድርሻቸውን ኃላፊነት ይወጣሉ፡፡
11. ትምህርት ቤቱ በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት በሣይንስ ቤተሙከራ ውስጥ የሚገኙ
ንብረቶች በየሴሚስተሩ መጨረሻ የንብረት ቆጠራ በሚደረግበት ወቅት
ይሳተፋሉ፣መገለጫ የሌላቸውን ንብረቶች መገለጫዎቻቸውን ይጽፋሉ ይመዘግባሉ፡፡
12. በእቅዱ መሰረት የተሰሩ የቤተሙከራ የተግባር ስራ ሪፖርቶችን ለሚመለከተው
አካል ያቀርባሉ፡፡
አንቀጽ 15

የሳይንስ ቤተሙከራ ባለሞያ/Laboratory technician/ተግባርና ኃላፊነት

1. የቤተ-ሙከራ ሥራዎች በተመለከተ እቅድ ያዘጋጃል፤ በእቅዱ መሰረት ተግባራዊ


ያደርጋል፡፡
2. ማንኛውም የሣይንስ ቤተሙከራውን ቋሚና አላቂ ንብረት ከትምህርት ቤቱ ንብረት
ክፍል በኃላፊነት ይረከባል፡፡ለተፈለገው አላማ ብቻ እንዲውል ያደርጋል፡፡
3. ከቀዳሚ መምህራን /ከትምህርት ክፍል ኃላፊዎች/ ጋር በመሆን ኬሚካሎችንና
መሳሪያዎችን ለአጠቃቀምና ለቁጥጥር አመቺ በሆነ መንገድ ያደራጃል፣ስለ
መሳሪያዎቹ አጠቃቀምና አያያዝ ዝርዝር መግለጫ እያወጣ ለመምህራንና
ለተማሪዎች ያሳውቃል፡፡
4. ቤተ-ሙከራውንና የቤተ-ሙከራ መሳሪያዎችን ንጽህናና ደህንነት ይጠብቃል፡፡
5. በተግባር ጊዜ የሚያስፈልጉትን ኬሚካሎችና መሳሪያዎች በመምህራን ጥያቄ
መሰረት አዘጋጅቶ ያቀርባል፤ የመማር ማስተማሩ ሂደት ሲያበቃ መሰሪያዎችንና
ኬሚካሎችን በየቦታቸው በትክክል ይመልሳል፡፡
6. አገልግሎት ሲሰጡ የሚሰባበሩትንና ከጥቅም ውጭ የሆኑትን መሳሪያዎች ዝርዝር
እየያዘ ከምክንያታዊ መግለጫ ጋር ወዲያውኑ ለትምህርት ቤቱ አቅርቦ እንዲጠገኑ፤
እንዲተኩ ወይም ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
7. መሳሪያዎችና ኬሚካሎች ከማለቃቸው በፊት በቀዳሚ መምህራን / የትምህርት ክፍል
ኃላፊዎች/ አማካይነት መጠየቂያውን በማዘጋጀት ለትምህርት ቤቱ ያቀርባል
አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
8. በቀዳሚ መምህራን /የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች/ አማካይነት በሣይንስ ቤተሙከራ
ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች በየሴሚስተሩ መጨረሻ የንብረት ቆጠራ በማድረግ
ለትምህርት ቤቱ ያቀርባል፡፡
9. መምህራን በላቦራቶሪ ውስጥ የተግባር ስራ ሲያከናውኑ ተሳትፎና እገዛ ያደርጋል፡፡
10. ከቀዳሚ መምህራን ጋር በመሆን የሣይንስ ቤተሙከራ የመጠቀሚያ የጊዜ ሰሌዳ
ያወጣል፡፡
11. የተበላሹ ወይም የተሰበሩ የቤተ ሙከራ እቃዎችን ቀላል ጥገና ያደርጋል፡፡
12. ከአካባቢ በሚገኙ ቁሳቁሶች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን በማዘጋጀት ስራ ላይ
ይሳተፋል፡፡
13. በየጊዜው የሚከናወኑ የሙከራ ውጤቶችንና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን
ለመረጃና ለጥናት እንዲያገለግሉ አደራጅቶ ይይዛል፡፡
14. ከመምህራን ጋር በመሆን በቤተ ሙከራ ውስጥ የሚገኙትን ኬሚካሎች ጠባይና
አደገኛነት በተመለከተ የአጠቃቀም ጥንቃቄአቸው/safty rules/ ጋር መግለጫ እያወጣ
ተማሪዎች እንዲያውቁና በአጠቃቀም ጊዜ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ
ያሳውቃል፡፡
15. አዲስ የመጡና በእቃ ግምጃ ቤት ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎችና መሳሪያዎችን
ክትትል እያደረገ ወደ ቤተ ሙከራ ክፍል ተወስደው አገልግሎት እንዲሰጡ
ያደርጋል፡፡
16. በየሩብ ዓመቱ መጨረሻ ስለስራው እንቅስቃሴ በተመለከተ ተጠሪ ለሆነለት ክፍል
በጽሁፍ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

ክፍል አምስት

ልዩ ልዩ ጉዳዮች

አንቀጽ 16

ከዚህ የሣይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራ አደረጃጀትና አሠራር መመሪያበፊት የወጡ


መመሪያዎች በዚህ ተሽረዋል፡፡

አንቀጽ 17

መመሪያውን ስለማሻሻል

ይህ መመሪያ በማናቸውም ጊዜ በስራ ላይ የሚያጋጥሙትን ችግሮች የትምህርት ቢሮ


ሲያምንባቸው መመሪያውን ሊያሻሽል ይችላል፡፡
አንቀጽ 18

የመመሪያው ተፈፃሚነት

ይህ መመሪያ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ትምህርት ቢሮ ከፀደቀበት ……………… ጀምሮ


ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

መመሪያውን ያፀደቀው የበላይ አመራር

እሸቱ ከበደ (ዶ/ር)

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ትም/ቢሮ ኃላፊ

You might also like