You are on page 1of 12

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ትምህርት ቢሮ

የቅድመ መደበኛ፤የመጀመሪያ ደረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ እና


መሰናዶ ትምህርት ቤቶች
የተማሪዎች መተዳደሪያ መመሪያ

የተሻሻለ ረቂቅ

መስከረም 2010 ዓ.ም


አዲስ አበባ
መግቢያ

0
በሀገራችን በየደረጃው የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት ት/ቤቶች የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

ትምህርት የዕድገት ሁሉ ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ ለሁለንተናዊ ልማት መፋጠን ትልቁን ድርሻ ይይዛል፣

ትምህርት ተመራማሪና ችግር ፈቺ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችልና የህብረተሰቡን አመለካከት ወደ

እድገት አቅጣጫ የሚመራ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ሳይንሳዊ ግኝቶች ጋር በማስተዋወቅ

ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ባህላዊ ዕድገቶችን የሚያፋጥን መሣሪያ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ት /ቤቶቻችን

በሰከነና ቀልጣፋ አመራር የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማከናወን ይቻል ዘንድ የተማሪውን ስነምግባር

በተፈለገው አቅጣጫ ለማነፅ መብቱንና ግዴታዎቹን ማሳወቅ አስፈላጊ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ

የትምህርት ተቋማት አንድ ወጥ የአመራርና የርምጃ አወሳሰድ አፈፃፀም መኖሩ ተገቢ በመሆኑ ይህ

የተሻሻለ የመጀመሪያ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የተማሪዎች መተዳደሪያ መመሪያ በአዲስ አበባ

ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ተዘጋጅቷል፡፡

አንቀፅ 1፡ አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የቅድመ መደበኛ፤ የመጀመሪያ ደረጃ፤ ሁለተኛ
ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የተማሪዎች መተዳደሪያ መመሪያ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

አንቀፅ 2፡ ትርጓሜ

1
2.1. #ተማሪ$ ማለት በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ በመንግስትና በግል የመጀመሪያ
ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ መሰናዶ ት/ቤት በመደበኛ እና በማታ የትምህርት ኘሮግራም በመማር ላይ
የሚገኙ ማለት ነው፡፡

2.2. #ቅጥር ግቢ$ ማለት ት/ቤቱ ከመንግስት ወይም በግል በባለቤትነት ወይም በኪራይ የያዘው እና
ለመማር ማስተማር አገልግሎት ወይም ስራ የሚሰጥበት ክልል ማለት ነው፡፡

2.3. #ትምህርት ቤት$ ማለት ማንኛውም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ የመጀመሪያ
ደረጃ፤ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ማለት ነው፡፡

2.4. #የተማሪ ዲስኘሊን ኮሚቴ$ ማለት ተማሪዎች መልካም ስነ-ምግባር ኖሮአቸው እንዲያድጉ ይቻል
ዘንድ ለማስተካከል በየት/ቤቱ የተቋቋመ ኮሚቴ ማለት ነው፡፡

2.5. “የደንብ ልብስ” ማለት በት/ቤቱ ማህበረሰብ የጋራ ስብሰባ በስምምነት የተመረጠ ለተማሪዎች
መለያነት የሚያገለግል ተመሳሳይ የጨርቅ ቀለም፤ ቅርፅ፤መጠን፤ጥራት እና አዘገጃጀት ያለው ልብስ
ነው፡፡

አንቀፅ 3፡ የመመሪያው ዓላማ

3.1. ተማሪዎች 1986 በወጣው የትምህርት እናስልጠና ፖሊሲ መሰረት ተምረው ሀገር ተረካቢ እንዲሆኑ
ለማስቻል፤

3.2. ተማሪዎች መብታቸውንና ግዴታቸውን ጠንቅቀው በማወቅ በትምህርት ቤቱ ውስጥ በሚኖሩ


በማንኛውም መማር ማስተማር፤ አስተዳደራዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማድረግ

3.3. ተማሪዎች በትምህርት ላይ በሚቆዩበት ጊዜ በራስ የመተማመን መንፈስ በጋራ የመኖርና የመረዳዳት
ባህል እንዲያዳብሩ ለማስቻል፣

3.4. ተማሪዎች ለሀገራቸውና ለወገናቸው ተቆርቋሪ ችግር ፈችና መልካም ስነ ምግባር ያላቸው ዜጐች
ሆነው እንዲቀረጹ ለማስቻል፣

3.5. ተማሪዎች፣ የዲሞክራሲ ስርዓት፣ የህግ የበላይነትን፣ እኩልነትን፣ ፍትሐዊነትን፣ የሀገር ፍቅርን፣
የሀላፊነት ስሜትን፣ ጠንካራ የስራ ባህልን፣ ራስን የመቻል፣ የቁጠባ ባህልን ንቁ ህዝባዊ ተሳትፎንና
እውቀትን የመሻት ዕሴቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችሉ፣

3.6. ግዴታቸውን የማይወጡና መብታቸውን ጠንቅቀው የማያውቁ ተማሪዎችን በተደጋጋሚ በሚሰጥ


የምክር አገልግሎት ለማስተካከል፣ ደረጃውን በጠበቀ ማስጠንቀቂያ ለማስተካከልና ካልተቻለም
በመመሪያው መሠረት እርምጃ ለመውሰድና በመመሪያው መሠረት እንዲዳኙ ለማስቻል ነው፡፡

2
3.7. በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተመሳሳይ ጉዳዩች የሚሰጡ ውሳኔዎች
መዘበራረቅን በማስቀረት ተቀራራቢና ወጥነት ያለው አሰራር ለመዘርጋት፤

አንቀፅ 4፡ የተማሪዎች የዲስኘሊን ኮሚቴ አወቃቀር በት/ቤት

4.1. የትምህርት ቤቱ መማር ማስተማር ም/ር/መምህር/ርት----------------- ሰብሳቢ

 በመምህራን ጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ አንድ መምህር---------------- ፀሐፊ


 ከወተመህ የሚወከል አንድ ወንድና ሴት ወላጅ ተወካዩች----------- አባል
 ከተማሪዎች ምክር ቤት አንድ ተወካይ ---------------------------------- አባል
 የሴት መምህራ አንድ ተወካይ ---------------------------------------- አባል
 ከት/ቤት ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ተወካይ አንድ----------------------- አባል

የማታ ተማሪዎችን ጉዳይ ሲታይ ሁለት የማታ ተማሪዎች ተወካዮች በቀን ተማሪዎች ምትክ
በኮሚቴ አባልነት ይሳተፋሉ፣

4.2. የኮሚቴው የሥራ ዘመን ሁለት አመት ይሆናል፤ ሆኖም አባላት እንደገና ሲሰየሙ ለአንድ ተጨማሪ
ዙር ለማገልገል ሊመረጡ ይችላሉ፣

4.3. አንድ አባል ከሁለት ጊዜያት በላይ በአባልነት ሊሰየም አይችልም፡፡

4.4. በጐደለው የኮሚቴ አባላት ምትክ ክፍተት ሳይፈጠር በፍጥነት በየጊዜው እየታየ ይተካል፣

4.5. የኮሚቴው ምልአተ-ጉባኤ ከ 5 ዐ% በላይ (50+1) ሲገኙ ይሆናል፣

4.6. የኮሚቴው አሰያየምና ተጠሪነት፣

4.6.1. የኮሚቴው ስያሜ የተማሪዎች የዲስፕሊን ኮሚቴ የሚባል ሲሆን፤ ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለር/መምህሩ
ይሆናል፡፡

አንቀፅ 5፡ የተማሪዎች የዲስኘሊን ኮሚቴ አወቃቀር በወረዳ ደረጃ

 የወረዳ ስርዓተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ቡድን መሪ ------------- ሰብሳቢ

 የወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ሱፐርቫይዘር--------------------------- ፀሐፊ

 የወረዳ ስርርዓተ ትምህርት ትግበራ ባለሙያ-------------------------------- አባል

 የወረዳ መም/የት/አመ/ልማት ቡድን መሪ ----------------------------------- አባል

 ከወረዳ ወተመህ አንድ ወንድና ሴት ወላጅ ተወካይ ----------------------- አባል

3
 በወረዳው ት/ጽ/ቤት ስር የምትሰራ ሴት የትም/ባለሙያ-------------------- አባል

አንቀፅ 6፡ በክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የተማሪዎች የዲስኘሊን ኮሚቴ አወቃቀር

 የክ/ከተማ ስርዓተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ቡድን መሪ ------------ ሰብሳቢ

 የክ/ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ማህበራዊ ሳይንስ ሱ/ር --------------- ፀሐፊ

 የክ/ከተማ ማህበራዊ ሳይንስ ትግበራ ባለሙያ---------------------------------- አባል

 የክ/ከተማው መም/የት/አመ/ልማት ቡድን መሪ-------------------------------- አባል

 ከክ/ከተማ ወተመህ አንድ ወንድና አንድ ሴት ወላጅ ተወካይ-------------- አባል

 በክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የምትሰራ ሴት የትም/ባለሙያ-------------------------- አባል

አንቀፅ 7፡ የኮሚቴው ስልጣንና ተግባር በት/ቤት ደረጃ

7.1. ተማሪዎችን በሚመለከት የሚከሰቱ ማንኛውንም የዲስኘሊን ጉዳዮች የማየት ስልጣን አለው፣
7.2. ተማሪን ለአንድ አመት ከሚያገሉ ውሳኔዎችና ከነጭራሹ ከት/ቤት የሚያስወግዱ እርምጃዎች
በስተቀር ሌሎች የኮሚቴው ውሳኔዎች የመጨረሻ ይሆናሉ፡፡
7.3. ተማሪን ለአንድ አመት ከትምህርት ገበታ የሚያገሉና ከነጭራሹ ከት/ቤት የሚያስወግዱ የኮሚቴ
ውሳኔዎች የውሳኔ ሀሣብ በር/መምህሩ ቀርቦ ይፀድቃል፣

አንቀፅ 8፡ የኮሚቴው ስልጣንና ተግባር በወረዳ ት/ጽ/ቤት ደረጃ

በወረዳ ደረጃ የተቋቋመው የዲስኘሊን ኮሚቴ በት/ቤት ደረጃ በተማሪዎች የዲስኘሊን ግድፈት ምክንያት
ለአንድ አመትና ከነጭራሹ የተባረሩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትን ተማሪዎችን ይግባኝ ይመለከታል፣
ይመረምራል፣ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል/ ያፀድቃል ወይም ይሽራል፡፡ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለፅ/ቤቱ ኃላፊ
ይሆናል፡፡

አንቀፅ 9፡- የኮሚቴው ስልጣንና ተግባር በክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ደረጃ

በክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ደረጃ የተቋቋመው የዲስኘሊን ኮሚቴ በት/ቤት ደረጃ በተማሪዎች የዲስኘሊን
ግድፈት ምክንያት ለአንድ አመትና ከነጭራሹ የተባረሩ የሁለተኛ መሰናዶ ት/ቤቶች ተማሪዎችን ይግባኝ
በፍትሐዊነት ይመለከታል፣ ይመረምራል፣ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል/ ያፀድቃል ወይም ይሽራል፡፡ኮሚቴው
ተጠሪነቱ ለፅ/ቤቱ ኃላፊ ይሆናል፡፡

አንቀፅ 1 ዐ፡ የተማሪዎች መብት

4
10.1. የመማር፣ ጠይቆ የመረዳትና የማወቅ ፣
10.2. በት/ቤቱ የትምህርት ግብዓቶች የመጠቀም ወይም አገልግሎት የማግኘት፣
10.3. የትምህርታቸውን ውጤትና የምስክር ወረቀት በወቅቱ የማግኘት፣
10.4. የት/ቤቱን የክፍል ውስጥ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች መመሪያዎችን የማወቅና የማግኘት፣
10.5. ከመምህራን ጋር ተገቢ የሆነ የመማር ማስተማር ግንኙነት በመፍጠር ድጋፍና እርዳታ
የማግኘት፣
10.6. የሚደርስባቸውን በደልና ቅሬታ በየደረጃው ላሉ የት/ቤቱ አካላት የማቅረብ፣
10.7. ስለመምህራን የማስተማር ክህሎት የመገምገም አስተያየት ሲጠየቁ የመስጠት፣
10.8. ከመማሪያ ክፍል ውጭ የሚከናወኑ የተጓዳኝ ትምህርት ኘሮግራሞች ላይ የመሳተፍ፣
10.9. በትምህርት ቤት አደረጃጀቶች ውስጥ ለተማሪዎች ከሚሰጠው ልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ
የመምረጥና መመረጥ፣
10.10. ከት/ቤት ወይም በቅርብ ከሚገኝ የጤና ማዕከል የመጀመሪያ ዕርዳታ የማግኘት፣
10.11. በት/ቤት የዕቅድ ዝግጅትና የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ በተወካዮቻቸው አማካኝነት መሳተፍ፣
10.12. ተወካዮቻቸውን በየደረጃው ላሉ የኃላፊነት ቦታዎች የመምረጥ፣
 ተጨማሪ የተማሪዎች መብትና ግደታ ይህንን መመሪያ በማይቃረን ሁኔታ በት/ቤቱ
መቅረብ ይችላል፡፡

አንቀፅ 11፡ የተማሪዎች ግዴታ

11.1. በት/ቤት በሚወጣው የትምህርት ኘሮግራም መሠረት የመገኘት፣

11.2. ያለበቂ ምክንያት ከት/ቤት አለመቅረት፣

11.3. በት/ቤቱ ውስጥና በዙሪያው ተማሪዎች በህይወታቸው ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ተብሎ ከተከለከሉ
ሥፍራዎች እራስን ማራቅ፣

11.4. በክፍል ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት በግልም ሆነ በቡድን በጥሞና የመከታተል፣

11.5. የክፍል ሥራ፤ የቤት ሥራ፤ የቡድን ሥራ የሚሰጡ የችሎታ መመዘኛዎችን ሠርቶ አጠናቆ በጊዜው
የማቅረብ፣

11.6. የት/ቤቱ ኃላፊዎችና መምህራን በአግባቡ የሚሰጡትን ድጋፍ ምክርና መመሪያ መፈፀም፣

11.7. ሴት ተማሪዎችን ከመተንኮስ፣ ከማስፈራራት ከመድፈር ከመደባደብና ሰብአዊ መብታቸውን


ከመጋፋት መቆጠብ፣

11.8. ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመግባባት መስራትና መማር፣

5
11.9. ከማንኛውም የቡድን ጠብ አምባጓሮና ጉልበተኝነት ተግባር ራስን ማቀብ፣

11.10. ለመምህራን፣ ለሠራተኞች፣ ለትምህርት አመራሮችና ለጓደኞቻቸው ተገቢውን ክብር መስጠት፣


/አለመዝለፍ፣ አለማንጓጠጥ፣ አለመስደብ፣ አለመዛት፣ አለማንቋሸሽ……ወዘተ/

11.11. የመማሪያ መጽሐፍትን ሌሎች የትምህርት መሣሪያዎችን በጥንቃቄ መያዝና መጠቀም


አለማበላሸት፣

11.12. የትምህርት ጊዜን በማይሻማ ሁኔታ ዕውቀቱንና ጉልበቱን ለትምህርት ቤቱና ለአካባቢው
ህብረተሰብ አገልግሎት የማዋል፣

11.13. ለጋራ ጥቅም ደህንነተና ለልማት መስራት፣

11.14. የት/ቤቱን ንብረት የመጠበቅ / መቀመጫ ወንበሮችን፣ የመማሪያ ክፍሎችን፣ መስኮቶችን፣ ምድረ
ግቢውን በንፅህና መያዝና መንከባከብ/

11.15. በት/ቤቱ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም በአካልና በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሣሪያ ይዞ


አለመገኘት፣

11.16. በት/ቤት ግቢ ውስጥ ማንኛውንም አይነት የሀይማኖትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች አለማካሄድ፣

11.17. ሕጋዊ ያልሆኑ ስብሰባዎች ላይ ያለመሳተፍ፣

11.18. የግልና የጋራ ንፅህናን መጠበቅ፣

11.19. በደንቡ አንቀፅ 17 መሰረት የተፈቀደውን ሥነ-ሥርዓት የተከተለ የደንብ ልብስ አለባበስና የፀጉር
አያያዝ መጠቀም፣

11.20. የት/ቤቱን የደንብ ልብስ አዘውትሮ መልበስ፣

11.21. በትምህርት ሰዓት ያለ በቂ ምክንያት በት/ቤት ቅጥር ግቢ አለመዟዟር፣

11.22. የት/ቤቱን አጥር ዘሎ አለመውጣት /አለመግባት/ በአጥር አለመቀበልና አለማቀበል፣

11.23. ለትምህርት ቤቱም ሆነ ለህብረተሰቡ ታማኝ መሆን፣

11.24. አለማርፈድ እና ያለበቂ ምክንያት አለመቅረት፣

11.25. ሲጋራ አለማጨስ መጠጥ ጠጥቶ አለመገኘት ጫትና ሌሎች አደንዛዥ ዕጾችን አለመጠቀም፣

11.26. የት/ቤቱን ማህበረሰብና እራሱን ከኤች አይ ቪ ኤድስ የመከላከል፣

11.27. የስርቆት ወንጀል አለመፈፀም፣ ፈተና መኮረጅ ቁማር መጫወት ከመሳሰሉ ሕገወጥ ድርጊቶችና
ከሌሎተ ጥፋቶች መራቅ፣

6
10.28. በት/ቤት ግቢ መታወቂያ ይዞ መገኘት ሲጠየቅ የማሳየት፣

10.29. ማንኛውንም ዓይነት ኤሌክትሮኒክስ (ላፕቶፕ፤ታፕና ሞባይል) መገልገያዎች በትምህርት ቤት ግቢ


ይዞ መገኘት፤

አንቀፅ 11፡ ግዴታቸውን በማይወጡ ተማሪዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች

11.1. ተከታታይ የምክር አገልግሎት የሚያሰጡ ግድፈቶች /ጥፋቶች፣

11.1.1. በተደጋጋሚ የማርፈድ፣

11.1.2. በተደጋጋሚ ያለበቂ ምክንያት መቅረት፣

11.1.3. በተማሪዎች መካከል የሚከሰቱ ቀላል የሀሣብ ግጭትና ያለመግባባት፣

11.1.4. የክፍል ውስጥ ስነ-ስርዓትን ያለማክበር በክፍል መረበሽ መጮህ፣ መብራት ማጥፋት ወዘተ፣

11.1.5. በተደጋጋሚ ሁኔታ የቤት ሥራዎችን፣ የቡድን ሥራዎችን፣ የክፍል ሥራዎችን ያለመስራት ፣

11.1.6. በክበባት ያለመሳተፍ፣

11.1.7. የትምህርት መሣሪያ ይዞ አለመገኘት፣

11.1.8. አጥር ዘሎ መግባትና መውጣት፣

11.1.9. የት/ቤት ንብረትን በቸልተኝነት ማበላሸት፣

11.1.10. በትምህርት ግቢ ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ይዞ መገኘት

11.1.11.የተከለከሉ በዓላትንና ትምህርታዊ ጉብኝቶችን ለማካሄድ ሙከራ ማድረግ

11.1.12. የተከለከሉ የደንብ ልብሶች፤የፀጉር አበጣጠርና መዋቢያዋችን የመጠቀም ጅምሮች ማሳየት

11.2. የምክር አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነትን በተመለከተ

11.2.1. ከላይ በንዑስ አንቀፅ 11.1 የተመለከቱትን ጥፋቶች በተደጋጋሚ ለሚፈፅሙ ተማሪዎች የቤተ
ክፍል ሀላፊ የተማሪውን ሥነሥርዓት ለማስከበር ከተመረጡ ተማሪዎች ጋር በመሆን የተማሪውን በቀላል
የጥፋተኝነት ደረጃ በየጊዜው የተመዘገቡትን ጥፋቶች እየተከታተሉ የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፣
ስለተሰጠው የምክር አገልግሎት መረጃ በተማሪው ማህደር ይቀመጣል፣

7
11.2.2. የተማሪው/ዋ ጥፋት መረጋገጥ በተማሪው የመማር ሁኔታ ላይ ችግር ይፈጥራል ተብሎ
ሲታመንበት ወላጅ በልጁ ጉዳይ እንዲመከርና በቂ መረጃ እንዲኖረው በመጥራት በጋራ እንደጥፋቱ ሁኔታ
በሶስት ተከታታይ ጊዜ የቤተ ክፍሉ ሀላፊ ለተማሪው የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፣ የተማሪውን/ዋን ችግር
ለይቶ የማወቅ ስራ ይሰራል፣ ወላጅ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ይደረጋል፣

11.2.3. ተማሪው ከወላጁና ከቤተ ክፍሉ ኃላፊ የተሰጠውን የምክር አገልግሎት ተቀብሎ ተግባራዊ
ማድረግ ካልቻለ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ይደረጋል፣ ወላጆችም በአራተኛው የግንኙነት ጊዜ
ይህንን እንዲያውቁ ይደረጋል፣

አንቀፅ 12፡ የተማሪዎችን ባህሪ በተመለከተ መረጃ ስለማደራጀት

12.1.የቤተ ክፍል ኃላፊው የተማሪዎቹን የዕለት ከዕለት የባህሪና ትምህርትን የመከታተል ሁኔታዎች
በተመለከተ በቂ መረጃ ከክፍል አለቃዎችና ከመምህራን በመውሰድ ተማሪውን/ዋን ሊገልጻት/ጸው
የሚችል መረጃ ይይዛል፡፡

12.2.ተማሪው/ዋ በት/ቤት ውስጥ ከትምህርት ገበታው/ዋ ሊያስወጣት የሚችል ሁኔታ ሲፈጠር የቤተ
ክፍሉ ኃላፊ ገላጭ የሆነ በየጊዜው የተመዘገበ መረጃ ከወላጁ ጋር የተደረገ ውይይት፣ ተማሪው
የፈረሙበትና ይቅርታ የጠየቁበት፣ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ አጠቃላይ የተማሪውን/ዋን ባህሪ ሊገልፅ
የሚችል መረጃ ለት/ቤቱ ያቀርባል፣

12.3.ከላይ የተመለከተውን መነሻ በማድረግ በጊዜው ከተፈፀመ የባህሪ ግድፈት ጋር በማየት የት/ቤቱ
የዲስኘሊን ኮሚቴ በተማሪው/ዋ ላይ አግባብነት ያለው እርምጃ ይወስዳል፣

አንቀጽ 13፡ ለአንድ አመት ከት/ቤት የሚያስወግዱ ጥፋቶች

13.1. ት/ቤቱና ወላጅ ባላወቁት እና አሳማኝ ባላሆኑ ምክንያቶች ከት/ቤት በአመቱ የትምህርት
ካላንደር 2 ዐ% አለመገኘት፣

13.2. በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ሲጋራ ማጨስ፣ ጫት መቃምና የተለያዩ አደንዛዥ ፅጾችን


መጠቀም የአልኮል መጠጥ መጠጣትና ይዞ መገኘት፣

13.3. በግልም ሆነ በቡድን አምባጓሮ መፍጠር ፣

13.4. የት/ቤቱን ንብረት ሆን ብሎ መስበር፣ ማበላሸት ማጥፋት፣

13.5. በፈተና ወቅት ማወክ፣ የፈተና ሰርዓቱ እንዲደናቀፍ ማድረግ፤መኮረጅና ማስኮረጅ፣

13.6. የት/ቤቱን መምህራንና ሠራተኞች ኃላፊዎችን መሳደብና ማንጓጠጥ፣

13.7. ተማሪዎችን መደብደብ ንብረት መንጠቅ ማስፈራራት፣

8
13.8. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ በመጠቀም ተገቢ ያልሆነ ተግባር ማከናወን (ተማሪ የሚያወናብዱ
መረጃዎች ማስተላለፍ፤ኩረጃ ወዘተ)

አንቀፅ 14፡በማንኛውም ጥፋት በተደጋጋሚ የቤተ ክፍሉና ወላጅ ያደረጉትን ጥረት ተግባራዊ ባለማድረግ
በአንቀፅ አስራ አንድ ላይ በንዑስ አንቀፅ 11.2.3 ላይ የተመለከተውን የማስጠንቀቂያ ጽሁፍ
ተቀብሎ መስተካከል ያልቻሉ ተማሪ ለአንድ አመት ከት/ቤት ይታገዳል፣

አንቀፅ 15፡ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከት/ቤት የሚያስወጡ ጥፋቶች


15.1. በት/ቤት ውስጥና አካባቢ ማንኛውንም አደገኛ መሣሪያዎች ይዞ መገኘት፣

15.2. ማንኛውንም የሰርቆት ተግባር ሲፈፅም የተገኘ ፣

15.3. የት/ቤቱን ንብረትን ሆን ብሎ ለጉዳት ማጋለጥ፣

15.4. በት/ቤት ውስጥና አካባቢ ሴት ወይም ወንድ ተማሪዎችን መድፈር ወይም ለመድፈር መሞከር፣

15.5. ያልተፈቀዱ ስብሰባ፤በዓላት የማክበር ስነ-ስርዓት ማድረግ፣ ሁከት መፍጠር፤ ማሳደምና ከደንብ
ልብስ ላይ ተገቢ ያልሆነ ፅሁፍ መፃፋና ቀጥሎ ማሰፋት

15.6. በፈተና ወቅት ለሌላ ተማሪ መፈተን ወይም ለራስ ማስፈተን፣

15.7. የተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ አቅርቦ መገኘት፣

15.8. መምህራንና የትምህርት ቤቱን ሠራተኞች ለመደባደብ መሞከር መደባደብ፣

15.9. የተማሪን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥልና እስከ ህይወት ማጥፋት የሚያደርስ ድርጊት

15.10. ኢ ስነ-ምግባራዊ አለባበስ፤ልብስ መቅደድና ማቃጠል፤እራቁት ጭፈራ በትምህርት ቤት ጋቢ ውስጥ


ማካሄድ

አንቀፅ 16፡ ለአንድ አመት የታገደ ተማሪ ተመልሶ ወደ ት/ቤት ስለመግባት፣


የታገደ ተማሪ የእግድ ጊዜውን ጨርሶ ወደ ት/ቤት ለመመለስ ጥያቄ ለትምህርት ቤቱ

ሊያቀርብ ይችላል፣ ሆኖም ግን የተማሪዎች መማክርት የወላጅ መምህር ተማሪ ህብረት

እና ወላጁ የተማሪው ባህሪ ስለመሻሻሉ ከሚኖርበት ወረዳ ጽ/ቤት አስተያየት በሚሰጥበት

ጊዜ ይሆናል፡፡

አንቀፅ 17፡- የደንብ ልብስ አጠቃቀም

9
17.1. የተማሪዎች የደንል ልብስ የጨርቅ ዓይነት፤ጥራት እና ቀለም በትምህርት ቤቱ
አስተዳደር፤ተማሪዎችና ወላጆች የጋራ ስብሰባ በውይይት የሚወሰን ይሆናል፡፡

17.2. የወንድ ተማሪዎች የደንብ ልብስ አዘገጃጃት የሱሪ ቬሎ መጠን ከ 18 ኢንች ያነሰ ሊሆን አይችልም፡፡
ሱሪ የሚለብሱ ሴት ተማሪዎችም በዚሁ መጠን የሚያዘጋጁ ይሆናል፡፡

17.3. የሴት ተማሪዎች የደንብ ልብስ አዘገጃጃት የቀሚስ መጠን ከጉልበት በታች የታፋቸውን 2/3 ኛ
ክፍል የሚሸፍን መሆን ይኖርበታል፡፡

17.4 ማንኛውም ተማሪ በጋራ ከተወሰነው የደንብ ልብስ ዓይነት፤ጥራትና ቀለም ውጪ መጠቀም
አይፈቀድም፡፡

17.5. ከት/ቤቱ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም ዓይነት ፅሁፍ ማሳተም፤ሌላ የጨርቅ ዓይነት ቀጥሎ ማሰፋት
እና ያልተፈቀደ የደንብ ልብስ ዓይነት ፤ቅርፅና ይዘት መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

17.6. በህግ በሀይማኖት ምክንያት ከተፈቀደ የደንብ ልብስ ውጪ ማንኛውንም ዓይነት አልባሳት ወደ
ትምህርት ቤት ግቢ ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

አንቀፅ 18፡- የተማሪዎች የፀጉር አቆራረጥ

18.1.የተማሪ ፀጉር ንፅህና የተጠበቀ መሆን ይኖርበታል፡፡

18.2.ለተማሪዎች ፀጉር ቀለም መቀባት አይፈቀድም፡፡

18.3.የወንድ ተማሪ ፀጉር አቆራረጥ አጭርና ያልተበላለጠ መሆን ይኖርበታል፡፡

18.4.ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸውን ማበጠርና ማስያዝ ይኖርባቸዎል፡፡

18.5.ለሴት ተማሪዎች ተንጠልጣይ የጀሮ ጉትቻ/ጌጥ/ ማድረግ አይፈቀድም፡፡ ለወንድ ተማሪ ምንም
ዓይነት የጀሮ ጉትቻ/ጌጥ/ ማድረግ አይፈወድም፡፡

18.6.ለተማሪዎች በክፍል ውስጥ መጥፎ ሽታ ያለው ቅባት ተቀብቶ መምጣት አይፈቀድም፡፡

አንቀፅ 19፡- ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች


19.1.በተለያዩ ከዲስኘሊን ግድፈት ውጭ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ያቋረጡበትን ተገቢ
መረጃ እያቀረቡ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ይደረጋል፣

19.2.ከአንድ ት/ቤት በዲስኘሊን ግድፈት የተቀጣ ተማሪ ትምህርት ቤቱን ለቆ ሲሄድ ወይም መልቀቂያ
ሲጠይቅ ስለተማሪው ሁኔታ በግልፅ በትራንስክሪኘቱ ላይ ይገለፃል፡፡

19.3.የታገደ ተማሪ እገዳውን እስከ ሚጨርስ የትምህርት ማስረጃው አይሰጠውም፡፡

10
19.4. በመመሪያው ውስጥ የተጠቀሱ የዲስኘሊን ጥፋቶች የዲስኘሊን ኮሚቴ ከሚወስነው ውሳኔ
በተጨማሪ እንደየጥፋቱ ሁኔታ ፍርድ ቤት ሊያስጠይቅ ይችላል፡፡

19.5.ለተማሪዎች በሚሰጠው ተከታታይ ትምህርትና ምከር አገልግሎት፣ የጋይዳንስና ካውንስሊንግ


ሠራተኞች፣ የተማሪዎች መማክርት፣ መምህራን፣ የሥነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህራን፣ ወላጅ፣
ተማሪ፣ መምህር ህብረት የሚኒ-ሚዲያ አገልግሎት ሁሉ በቅንጅት ለተማሪዎች ባህሪ መሻሻል
ይሰራሉ፡፡

አንቀፅ 20፡- የመመሪያው ተግባራዊነት ወሰን

ይህ መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር ለሚገኙ የመንግስት፤ የግል፣


የሀይማኖት፣ የድርጅት፣ የሕዝብና ሚሲዩን ት/ቤቶች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አንቀፅ 21

- ይህ መመሪያ በየጊዜው እየታየ በትምህርት ቢሮ የሚያሻሽለው ይሆናል፡፡


- ይህ መመሪያ ከመስከረም 2 ዐዐ 10 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የትምህርት ቢሮ

መሰከረም 2010 ዓ.ም

አዲስ አበባ

11

You might also like